የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ውይይት አደረገ

ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም እና የቀሪ ወራት ስራዎች በተመለከተ ከ11 ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የስራ ሂደት አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አደረገ።

በውይይቱ የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በሚያዚያ ወር ድጋፍና ክትትል የታዩ ስራዎች በድክመትና ጥንካሬ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠርካለም ጌታሁን ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱ በአጠቃላይ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተደረጉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችና ስልጠናዎች ለባለድርሻ አካለት ፣ ለሲቪክ ማህበራት ፣ለበጎ ፈቃደኞች፣ ለፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች፣ ለፖለቲካ አመራሮች እና ለሀይማኖት አባቶች በተለያዮ ርዕሰ ጉዳዮች የተሰጡ ስልጠናዎች ና የግንዛቤ ሰራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።

በተለይ በደንብ ቁጥር 150/2015 ዓ.ም ለማሰፈፀም ተሻሽሎ በወጣው ደንብ ቁጥር 167/2016 ዓ.ም እና በወንዞች ዳርቻ ልማት አስመልክቶ በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች በመፍጠር የግንዛቤ ስራው ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ እና ውጤቶች መገኘቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በመድረኩ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ በተደረገ የክትትልና ድጋፍ ግብር መልስ ለማሳያነት የሚሆኑ የለሚ ኩራ ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የአዲስ ከተማ እና የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች በጥንካሬ እና በክፍተት የነበራቸው ግብረ መልስ በመድረኩ ለማቅረብ ተችሎል።

በመጨረሻም በውይይቱ በቀረበው ሪፖርት እና ግብረ መልስ ላይ ከተሳታፊዎች አስተያየት እና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶባቸው የቀጣይ ወራት የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍1
የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ከ6ኛ ዙር ዕጩ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር በስልጠናው ዙሪያ ውይይት አደረጉ

30/08/2017 ዓ.ም
**ይርጋለም/አፖስቶ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ እየሰጠ በሚገኘው የ6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ሂደት ላይ የባለስልጣኑ እና ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመረሮች በተገኙበት ከሰልጣኞች ጋር ውይይት ተካሄደ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ አዲስ ምልምል ሰልጣኙ ስልጠናውን አጠናቆ በቀጣይ ወደ ስራ ሲቀላቀል ለተቋሙ ግንባር ቀደም ሰራተኛ በመሆን ትልቁን አስተዋጾ ያበረክታል ለዚህም ሰልጣኙ በስልጠና ወቅት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም ስልጠናውን በብቃት ሊያጠናቅቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በስልጠና ወቅት እያለፍን ያለነው ውጣውረድ ለግል ህይወታችንም ሆነ በስራ ላይ ለሚጠብቀን መንገድ ጠቃሚ ሆኖ አግኝተነዋል ያሉት ሰልጣኝ ኦፊሰሮቹ ቀጣይ የምንወስዳቸው ስልጠናዎችም የበለጠ ብቁ ጠንካራ ሆነን እንድንወጣ ያደርገናል በማለት ሀሳብ ሰጥተዋል።

በተለይ ስልጠናውን እየሰጡ እና እያስተባበሩ ላሉት የባለስልጣኑ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና አስተባባሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

በመጨረሻም ከሰልጣኙ ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች በባለስልጣኑ አመራሮች ማብራሪያ በመስጠት ሰልጣኙ ስልጠናውን በተነሳሽነትና በሞራል በመውሰድ የበቃ ኦፊሰር ሆኖ በመውጣት ለተቋሙ ትልቅ ግብአት መሆን እንደሚገባቸው በመግለጽ ውይይቱ ተጠናቋል።

በሳምራዊት ዘሪሁን

ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ
👍141