የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጠረ

18/09/2017 ዓ.ም
* አዲስ አበባ *

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወንዝና የወንዞች ዳርቻ ልማት ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ለሲቪክ ማህበራት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን በደንቡ 180/2017 ዙሪያ በተለያዩ መድረኮች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን በተደጋጋሚ መሰጠቱን እና ግንዛቤ እንደሚቀጥል በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል ።

"የወንዝ እና ወንዞች ዳርቻ ብክለት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ የህግ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ኮርሳ አቅርበዋል።

በሰነዱ በከተማዋ 76 ወንዞች መኖራቸውና የወንዞች ፅዳት ለህብረተሰቡ የጤና ስጋት በመፍጠራቸው ንጽህናቸው ለመጠበቅ ደንቡን መውጣቱ ገልጸዋል።

የወንዞች ደህንነት ለማስጠበቅ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በዚሁ ዙሪያ ጥናት ማጥናቱን ገልጸው ይህንን ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ ከ2 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ የቅጣት መጠን መቀመጡንም አስታውቀዋል።

የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ስራዎች ለመስራት ከሲቪክ ማህበራቱ እገዛ እንደሚያስፈለግ እና ሲቪክ ማህበራቱ በደንብ ቁጥሩ ላይ የተሰጣቸው ስልጠና በሚኖሩበት አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲያስገነዝቡ መልዕክት ተላልፏል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋረ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባውን:- የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
1👍1
ባለስልጣኑ ልምዱን እና ተሞክሮውን ለመንገዶች ባለስልጣን ልዑካን ቡድን አባላት አጋራ

18/9/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት ሙስናና በለሹ አሰራሮችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ በተቋም አደረጃጀት፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ያለውን ልምድና ተሞክሮ አጋርቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ በልምድ ማጋራቱ ወቅት የተቋሙ አደረጃጀት እና ተቋሙ በማጠናከር የተቋሙና የከተማዋን ገጽታ በመቀየር ሂደት በርካታ ስራዎች ማከናወኑን ለልዑካን ቡድኑ አባላት ገልፀዋል።

በልምድ ልውውጡ ባለስልጣኑ እንደየስራ ክፍላቸው ብልሹ አሰራር ከመከላከልና ከመቆጣጠር ረገድ የተተገበሩ ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች ገለጸፃ አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ለልዑካን ቡድኑ አባላት አስረድተዋል፡፡

የመንገዶች ባለስልጣን የልዑካን ቡድን አባላት ተቋሙ የተደራጀበት እና ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመነጋገር እየሰራ ያለው ውጤታማ ስራዎች አድንቀው የወሰዱት ተሞክሮ እና ልምዱን በተቋማቸው ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።

ዘገባው :-የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
በኮሪደር ልማት ደህንነት ጥበቃ የታየውን መልካም ስራ በወንዝ ዳርቻ ብክለትና መከላከል ላይ ማስቀጠል እንደሚገባው ተገለፀ።

ግንቦት 19/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለተለያዩ የሀይማኖት አባቶች ፣አባገዳዎች ፣ ሀዳ ስንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣ አርቲስቶች ፣ የብሎክ አደረጃጀት ሀላፊዎች እና ለየተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በወንዝና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

መድረኩ በሀይማኖት አባቶና በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረ።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ከተማ አስተዳደሩ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ልማት ከብክለት በመከላከል የኢኮኖሚ ምንጭ እንዲሆኑና በጤና ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ለማስቆም ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ጠቅሰዋል።

በመድረኩ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ከ70 በላይ ወንዞች ሲኖሩ ከመርዛማ ኬሚካል፣ ከመፀዳጃ ቤት ፍሳሾች እና ከበካይ ቆሻሻዎች መከላከል ደህንነታቸው ለማስጠበቅ ደንብ 180/2017 መውጣቱ አስታውቀዋል።

ስልጠናው በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት የግንዛቤ ማስጨበጥ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደመረ በለጠ በሰነድ ቀረቧል።

በስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ብክለት፣ በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ፣ መፍትሔዎች እንዲሁም የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 የተደነገጉ አስተዳደራዊ እርምጃዎ በዝርዝር ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

በስልጠናው ተሳታፊዎች ባለስልጣኑ በሚያከናውናቸው ተግባራት የከተማዋ የጀርባ ኦጥንት በመሆኑን በተለይ በወንዝና በወንዝ ዳርቻ ብክለት መከላከል ላይ ተቋሙን በማገዝ የድርሻቸው እደሚወጡ ቃል ገብተዋል።

በእለቱ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየት እና ጥያቄዎች ሰፊ ውይይት በማድረግ ባለስልጣኑ የቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል እና በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በመድረኩ መሠጠቃለያ የወጣው ደንብ ተግባራዊነት የህብረተሰብ እገዛ አስፈላጊ በመሆኑ የዛሬ ስልጠና መድረክ ተሳታፊዎች ለአካባቢአቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ እንዲፈጥሩ መልእክት ተላልፏል።

ዘገባው፦ የባለስልጣኑ የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡