የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ብልሹ አሰራር ለመታገል የአመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

19/09/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለማዕከል፣ ክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች ብልሹ አሠራርን ለመታገል የአመራሩ ሚና የላቀ መሆኑን የሚገልፅ የምክክር መድረክ ተካሄዷል።

ሳሬም ሆቴል አዳራሽ በተዘጋጀው ስልጠና ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት የስነ-ምግባርና ብልሹ አሠራርን ለመታገል ሁሌም አመራሩ ግንባር ቀደም በመሆን ታግሎ የሚያታግል ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በባለስልጣኑ ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ መነሻ የሆነ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይትና ምክክር ተካሄዶበታል።

በስልጠናው ተሳታፊዎችም የተለያዩ ሃሳብና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን መሰል ስልጠናዎች ለስራ ቅልጥፍና እና ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ ያለው ሚና የላቀ በመሆኑ መሠል ስልጠናዎች ተጠናክሮ መቀጠል እዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በማጠቃለያው እንደተናገሩት ከላይ እስከ ታች ድረስ ያለው አመራር አስቀድሞ ተቋሙን መውደድና በእኔነት ስሜት ለፈፃሚው ስራን ማውረድና ግልፅና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ተግባሩ መከናወኑን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተከናወኑ ተግባራትን በወቅቱ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ማድረግና ማንኛው ከተቋሙ አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣን አካል በፍፁም ሰብአዊነት ማገልገል እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም በዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መድረኩ ጠናቋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
👍2😁1
ህገ-ወጥ እርድ በማከናወን ስጋ ለማከፋፈል የሞከረን ግለሰብ በቁጥጥር በማዎል 16 የቁም እንስሳና 15 ሺህ ብር መቀጣቱ ተገለፀ

ግንቦት 20/2017ዓ/ም
**የአዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በመኖሪያ ግቢ ውስጥ ህገ-ወጥ እርድ በማከናወን ስጋ በማከፋፈል የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር በማዎል 16 የቁም እንስሳቶች በመውረስ 15 ሺህ ብር መቀጣቱ ገለፀ።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሂርጴ ጅፋራ ከዚህ በፊት በወረዳው ለግለሰብና ለተቋም ሰፊ ግንዛቤ መፈጠሩ በመግለጽ በዛሬው ዕለት ከጧቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ከህብረተሰቡ በተገኘው ጥቆማ መሰረት በተደረገ ክትትል በህብረተሰባችን ጤና ለማስጠበቅና የአካባቢ ውበት ለማስጠበቅ ሲባል በደንቡ መሠረት እርምጃ መወሰዱን ገልፀዎል።

በቦታው የተገኘው የታረዱ ከ20 በላይ የፍየልና የበግ ስጋ ለቄራዎች ድርጅት እንዲወገድ ማስረከባቸው የገለጹ ሲሆን መረጃው ለሰጡ የህብረለሰብ ክፍሎችና ኦፕሬሽኑ ለሰሩ ኦፊሰሮች ምስጋና አቅርበዋል።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ የመንግስትና የህዝብ ገቢ በማሳጣት በህብረተሰቡ የጤና ችግርና የአካባቢ የውበት የሚያበላሽ መሆኑ በመረዳት ህገ-ወጥ ተግባራትን ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 9995 በመጠቆምና ሀላፊነቱ እንዲወጣ መልዕክቱን አስተላልፏል ፡፡

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍3🖕1
የስነ-ምግባር ችግሮችና ብልሹ አሰራርን መከላከልና መፀየፍ እንደሚገባ ተገለፀ

20 - 09 - 2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት የባለስልጣኑ እና የክ/ከተማ አመራሮች በተገኙበት ከ119 ወረዳዎች ሽፍት አስተባባሪዎች ጋር ግምገማዊ የስልጠና መድረክ ተካሄደ ።

በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ ራሱን በቴክኖሎጂ በማዘመን፣ የገጽታ ግንባታ ስራዎችን በማጠናከር ፣ ብልሹ አሰራርን በመታገል ፣ የኦፊሰሩን ሙያዊ አቅም በማጠናከርና አዲስ የፖራ ሚሊተሪ ኃይል መልምሎ በማሰልጠን ከተማችን ከደንብ ጥሰት የጸዳች ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በርካታ ስራዎች በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል ።

አክለውም ብልሹ አሰራር ሌብነት እንደ ሀገር ፣ ከተማ እና ለተቋማችን ገጽታ ግንባታ ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ በመገንዘብ ሁሉም አካል ሊከላከለውና ሊጸየፈው እንደሚገባ ገልጸዋል ።

የስነ-ምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል ለሽፍት አስተባባሪዎች የተዘጋጀው የስልጣንና ሰነድ በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል።

ሽፍት አስተባባሪዎች ያለውን የስራ ጥንካሬ በማስቀጠል እና አንዳንድ የሚስተዋሉ የስነ-ምግባር ክፍተቶችን በማስተካከልና በማሻሻል በቀጣይ ስልጠናውን ጨርሰው ወደ ስራ የሚቀላቀለውን የፖራ ሚሊተሪ ኃይል ለመቀበልና ከብልሹ አስራር የጸዳ ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ተገልጿል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ከአመራሩ የሚሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣትና ብልሹ አሰራርን ለመታገል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል ።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍2