የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ጀመረ ።

20 - 09 - 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ለማዕከል ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎች ፣ ባለሙያዎች እና የክ/ከተማ አስተባባሪዎችና ሲቪል ሰራተኞች ሁለተኛ ዙር ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል ።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው ስልጠና በጊዜ አጠቃቀም ፣ውጤታማ የቡድን የትብብር ችሎታ እና የራስ ተነሳሺነት ወይም እራስን ማስተዳደር በሚሉ ርዕሶች ላይ የሚሰጥ ይሆናል ።

እየተሰጠ ያለው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በሰልጣኞቹ ላይ የአመለካከትና የዕውቀት ዕድገት እንደሚያመጣ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ገልጸዋል ።

ስልጠናው ለምንሰራው ስራ እና ለግል ህይወታችን ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ በንቃትና ትኩረት በመስጠት መከታተል እንደሚገባ አሳስበዋል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
2
ኦፊሰሩ ከብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ የደንብ ጥሰትን መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ ።

21/ 09/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለአዲስ ከተማ ፣ ቂርቆስ እና ልደታ ክ/ከተማ ከሚገኙ ኦፊሰሮች ጋር ግምገማዊ የስልጠና መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በ7/24 ቀን ከሌሊት አመራሩና ኦፊሰሩ ተቀናጅቶ በመሰራት በከተማችን ፈጣን እድገት ላይ ተቋማችን የበኩሉን ሚና በብቃት በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የዛሬው ስልጠና ለቀጣይ ስራዎችን አጠናክሮ ለመስራት የሚያግዝ በመሆኑ በአግባቡ እንዲከታተሉ አሳስበዋል ።

በከተማችን ውስጥ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን አስቀድመን መከላከል እንዲሁም ሁሉም አካል ራሱን ከብልሹ አሰራር መቆጠብ እንደሚገባ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

የስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የኦፊሰሩ ሚና በሚል የተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል።

በአንዳንድ የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ላይ የሚታዩ የስነምግባርና ብልሹ አሰራር ችግሮችን በመቅረፍ በአዲስ መንፈስና በመልካም የስራ ተነሳሽነት በቅርቡ ተመርቀው ወደ ሰራ ከሚገቡት ከ6ኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር በመቀናጀት በመንግስትና በህዝብ የተጣለባችሁን ኃላፊነት በብቃት የሚወጣ ሃይል ልትሆኑ ይገባል ሲሉ አቶ እዮብ ተናግረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊ ኦፊሰሮች እንደተናገሩት የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ነው።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል።

በተያያዘ ዜና በቦሌ ክላስተር የካ፣ ቦሌ ፣ ለሚ ኩራ እና ጉለሌ ክ/ከተማ የስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የኦፊሰሩ ሚና በሚል መሪ ቃል የስልጠና መድረክ አካሂደዋል ስልጠናው በሶስተኛ ክላስተር ለተቀሩት ክ/ከተማዎች በነገው ዕለት የሚቀጥል ይሆናል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍2
ሕብረተሰቡን በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባ ተገለፀ።

22/09/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮና ንፋስ ስልክ ላፍቶና አራዳ ክፍለ ከተማ አመራርና ኦፊሰሮች ጋር በስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተመለከተ ግምገማዊ ስልጠና መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራና ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

"የስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የኦፊሰሩ ሚና" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት በሁሉም ረገድ እየዘመነች ያለች ከተማን ደንብ መተላለፍ በአግባቡ ለመከላከል እና ህብረተሰቡን በታማኝነት ለማገልገል ከፍተኛ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሌም በስነ-ልቦና ዝግጁ በመሆን ተልዕኳችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

በቅርቡ አስመርቀን ወደ ስራ የምናሰማራቸውን የ6ተኛ ዙር ኦፊሰሮቻችንን ጨምረን የሰው ኃይል አቅማችንን የበለጠ በማጠናከር ሕገ-ወጥነትንና የደንብ መተላለፍን በአስተማማኝ መልኩ የምንከላከል ይሆናል ብለዋል።

ሁሉም ኦፊሰር በተመደበበት ቀጠና ላይ በሰዓቱ በመገኝት ከስነ-ምግባርና ብልሹ አሠራር በፀዳ መልኩ ተልእኮውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

በትላንትናው ዕለት ከተቀሩት ክፍለ ከተማ ኦፊሰሮችና አመራሮች ጋር ውጤታማ ውይይት መካሄዱ ይታወሳል።

መረጃው ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
2👍1