Berbir Mereja / በርብር መረጃ
6.24K subscribers
19.4K photos
659 videos
5 files
16.5K links
Welcome back to our channel, where we bring you the latest updates and news from around the world.
Download Telegram
ሰሜን ኮሪያ በዛሬው እለት ሁለት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን የደቡብ ኮሪያ መከላከያ አስታወቀ።

ፒዮንግያንግ ለአሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ “ከባድ ምላሽ” እሰጣለሁ የሚል ዛቻ ባሰማች ማግስት ነው ሚሳኤሎቹን ያስወነጨፈችው።

በ10 ደቂቃ ልዩነት የተወነጨፉት አጭር ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎች ወደ ሀገሪቱ ሰሜን ምስራቃዊ አቅጣጫ መተኮሳቸውን ደቡብ ኮሪያ ገልጻለች።

የመጀመሪያው ሚሳኤል 600 ኪሎሜትሮችን ከተጓዘ በኋላ ቾንግጂን በተባለው አካባቢ የውሃ ዳርቻ ውስጥ መውደቁ የተነገረ ሲሆን፥ ሁለተኛው ግን 120 ኪሎሜትሮችን ከተጓዘ በኋላ ሳይፈነዳ እንዳልቀረ ተገምቷል።

ሴኡል በዛሬው እለት ፒዮንግያንግ ያደረገችውን የሚሳኤል ሙከራ “ጸብ አጫሪና የኮሪያ ልሳነ ምድርን ውጥረት የሚያባባስ ነው” ያለችው ሲሆን፥ ከአሜሪካ ጋር የመሰረተችውን ወታደራዊ ትብብር ለሚያውክ ማንኛውም ድርጊት ለመመከት አጻፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።

አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን “የነጻነት ጥግ” የሚል ስያሜ የሰጡትና የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ (ቲወዶር ሩዝቬልት) ጭምር የተሳተፈችበን ግዙፍ ወታደራዊ ልምምድ ተጠናቋል።


አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ እየመከሩ እየመከሩ ነው

በቱርክ መንግስት አመቻችነት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ተገናኝተው በመምከር ላይ እንደሚገኙ በርካታ የሶማሊያ እና የቱርክ መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ይገኛሉ።

በሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ ልዑክ አንካራ መግባቱን የጠቀሙት መገናኛ ብዙሃኑ የልዑኩ ዋነኛ አላማ በቱርክ መንግስት አመቻችነት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለሚደረገው ንግግር ለመታደም መሆኑን አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ ይሁን በሶማሊያ መንግስታት በኩል ስለሁኔታው በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።

የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ እንደሚያሳየው በአንካራ የሚገኘው የሁለቱ ሀገራት ልዑክ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ስምምነት ዋነኛ አጀንዳው መሆኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ቢቢሲ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ባሰራጨው ዘገባ የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቱርክ መግባታቸውን አስታውቋል።

ዛሬ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም. በሚደረው ውይይት ላይ ለመሳተፍ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ ፊቅ እና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ አንካራ ገብተዋል ብሏል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ የሚያደርጉት ንግግር “ድርድር” እንደሆነ የሶማሊያ የውጪ ጉዳይ ሚስቴር አመልክቷል ያለው ዘገባው የውጭ ጉዳይ ሚስቴሩ ዘግይቶ ከኤክስ ገጹ ላይ በሰረዘው ጽሑፍ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቱርክ አደራዳሪነት ለሚደረገው ንግግር አንካራ ገብተዋል ማለቱን ጠቁሟል።

በሁለቱ አገራት መካከል ስለሚደረገው ንግግር ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰጠ ማረጋገጫ ባይኖርም አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሶማሊያው አቻቸው ቀደም ብለው ቱርክ መግባታቸውን የቢቢሲ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የነዳጅ አጠቃቀም ብዝበዛን ለመቆጣጠር የሚረዳ ሲስተም  በ13 ተቋማት ላይ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

የኢፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም የነዳጅ አጠቃቀም ብዝበዛን ለመቆጣጠር፣ ጊዜን ለመቆጠብ ፣ተጠያቂነትን ለማስፈን እና መሰል ጠቀሜታዎች  ያሉት ሶፍተዌር መሆኑን የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ለሙከራ ትግበራዉ የተመረጡ ተቋማት 13 መሆናቸውን እና  የኢፍሊት ማኔጅመንትን ምንነትና ጠቀሜታ በማስቀደም ሶፍትዌር በማልማት ተግባሩን ለማከናወን ባለስልጣኑን ያነሳሳዉ በኢጂፒ ሲስተም የተገኘዉ የሚታይ ዉጤትና በሃገር ሃብት ላይ የሚያበረክተዉ ጉልህ አስተዋጽዖ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛ ሃብት የሚፈስበትን የተሸከርካሪና መለዋወጫ አስተዳደር አሰራር ሂደትን በማዘመን የተሽከርካሪ ስምሪትና አጠቃቀምን በማሻሻል የሚባክነዉን ሃብት መቆጠብና በተገቢዉ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችለዉን ሲስተም ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የኢፍሊት ማኔጅመንት ሶፍትዌር የማልማት ስራ በባህር-ዳር ዩኒቨርሲቲ ተጠናቅቆ ለሙከራ ትግበራ ዝግጁ ሆኖ ለዉይይት ቀርቧል፡፡

ሲስተሙን ያለማዉ ባህር- ዳር ዩንቨርሲቲ መሆኑን በማስታወስ ሙከራዉ በ13 ተቋማት ላይ እንደሚጀምርና ቀስ በቀስ ሁሉንም የፌደራል ተቋማት የሚያካትት እንደሆነ እና   ዋና ዓላማዉም የሃገርን ሃብት  ከብክነት ለመከላከል የሚረዳ ብሎም የቁጠባ ባህልን የሚያበረታታ እና ሙስናን የሚዋጋ አዋጭ ሲሲተም ነዉ ብለዋል፡፡

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
#አልተሳካም‼️
#በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በናይጀሪያ መንግስት በሽርክና ሊቋቋም ታስቦ የነበረው አየር መንገድ አለመሳካቱ ተጠቆመ‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለስልጣናት እና የናይጄሪያ መንግስት ባለስልጣናት መካከል በሽርክና የጋራ አየር መንገድ ለመመስረት ያደረጉት ውይይት አለመሳካቱ ተገለጸ።

የናይጄሪያ መንግስት ከውጭ አየር መንገድ ጋር በመተባበር በሽርክና ለመስራት አውጥቶት የነበረውን እቅድ ትቶታል ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደነገሩት አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ በዘገባው አስታውቋል።

ከናይጀሪያ አየርመንገድ ጋር የነበረው ሂደት አለመሳካት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአህጉሪቱ ከሚገኙ አየር መንገዶች ጋር ፍትሀዊ በመሆነ ድርሻ በሽርክና ለመስራት የየዘውን ስትራተረጂ አያስቆመውም ሲሉ ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹለት ዘገባው አመላክቷል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
ሁሉም ተሽከርካሪዎች በአስቸኳይ ወደ ማዳበሪያ ማጓጓዝ እንዲገቡ ታዘዘ

አራት ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ተደራርበው ጅቡቲ መግባታቸው ታውቋል።

ካፒታል ከምንጮችዋ እንደተረዳችው ከትላንት እሁድ ሰኔ 23 ጀምሮ የትኛውም ከጅቡቲ የሚነሳ የጭነት መኪና ከማዳበሪያ ውጭ መጫን እንደማይች መንግስት ለትራንስፖርት ማህበራት እና የግል አንቀሳቃሾች አስታውቋል።

ማዳበሪያ የማጓጓዝ ዘመቻ መታወጁን የገለፁት ምንጮች። በቀጣዩ 15 ቀን ተሽከርካሪዎች በሙሉ ማዳበሪያ ወደ መሃል አገር ያጓጉዙ መባሉን ጠቅሰዋል።

ትእዛዙ የመጣው በተመሳሳይ ቀን ማለትም ትላንት ሰኔ 23 ቀን እንደሆነ የታወቀ ሲሆን።

ሌላ ጭነት የያዙ ተሽከርካሪዎች ጭነቱን በማውረድ ማዳበሪያ እንዲያጓጉዙ መታዘዙ ታውቋል።

ከማዳበሪያ ውጭ ይዘው ወደ አገር ለመግባት የሚሞክሩ ተሽከርካሪዎች ካሉ ጉምሩክ እንደማያስተናግዳቸው ይወቁት መባሉን ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል።

ካፒታል ባገኘችው መረጃ ባለፈው ሳምንት በCIF ግዥ የተፈፀመበት ማዳበሪያ የያዙ 4 መርከቦች ተደራርበው ጅቡቲ ገብተዋል።

ይህም የጭነት ማጓጓዝ ሂደቱ ላይ ጫና የሚፈጥር ነው የሚሉት ምንጮች ባለፉት ጥቂት አመታት የመርከቦች አገባብ የተናበበ መሆኑ በርከቦች ቆይታ እና ጭነት ወደ አገር ውስጥ የማስገባት ሂደት ከፍተኛ መሻሻል ታይቶበት ነበር።(Ethiopian business)

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
20 ሮኬቶች የእስራኤል ከተሞች ላይ ተርከፈከፉ፡፡

የፍልስጠየም ታጣቂ ቡድን ዛሬ ሰኞ ማለዳ ላይ ወደ እስራኤል ከተሞች ከ7 ወራቶች ወዲህ ግዙፍ ነዉ የተባለ የሮኬት ጥቃት መፈፀማቸዉን ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል፡፡

በተወነጨፉት 20 ሮኬቶች አንድ ወታደር ሲገደል ሌሎች 9 ከፍተኛ ሻለቃዎች ጉዳት አስተናግዷል፡፡ ወታደሮቹ ህንፃ ዉስጥ ባሉበት ነዉ ሰለባ የሖኑት እንደ ዘገባዉ፡፡

ታዲያ በጥቃቱ ወታደሩ መገደሉ በጋዛ ዘመቻ እስራኤል ያጣቻቸዉን ወታደሮች ቁጥርን 319 አድርሶታል፡፡የእስራኤል እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ለጥቃቱ ሀላፊነቱን ወስዷል፡፡

እንደ እስራኤል መከላከያ ሃይል ገለጻ፣ ወታደሮቹ ቀደም ብለው ይንቀሳቀሱበት ከነበረው በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ከካን ዮኒስ አካባቢ ቢያንስ 20 ሮኬቶች መወርወራቸዉንና ጉዳት ማድረሳቸዉን አረጋግጧል፡፡


አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
ቀለብ ላለመቁረጥ ሲል ትምህርት ቤት ድረስ ሄዶ የአራት አመት ልጁ ላይ የግድያ ሙከራ የፈጸመው አባት በጽኑ እስራት ተቀጣ

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በደኖ ወረዳ ኮዬ ቀበሌ ነዋሪ የሆነዉ ከድር አህመድ የተሰኘዉ ግለሰብ ለልጁ ወርሃዊ ተቆራጭ ላለማድረግ ሲል የአራት አመት ህጻን ልጁ ላይ የግድያ ሙከራ መፈጸሙ ተሰምቷል።ግለሰቡ በፍቺ ካጠናቀቀዉ የትዳር ህይወቱ ላገኘዉ አንድ የአራት አመት ህጻን ልጅ ላይ ነዉ መርዝ በመስጠት የግድያ ሙከራዉን ያደረገዉ።

የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሳሊም ቱጂሃን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ፥ ግለሰቡ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት አክረም ከድር የተሰኘዉ የአራት አመት ህጻን ልጅ ላይ አደገኛ ነዉ ፥ የሰዉልጅንም በፍጥነት ይገድላል የተባለዉን ለጫት ተክል ተባይ ማጥፊያነት የሚገለግል መርዝን በምግብ አድርጎ የሰጠዉ።ተከሳሽ ህጻን አክረም የሚማርበት ብሪቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመሄድ ከጓደኞቹ ጋር ሲጫወት የነበረዉን ጨቅላ በመጥራት እና ከትምህርት ቤቱ በማስወጣት በሚወደዉ ምግብ ዉስጥ መርዙን እንደሰጠዉ ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል ብለዋል።

መርዙ የጣፋጭነት ባህሪ አለዉ ያሉት...ከዚህ ቀደምም በዞኑ ይህንኑ የተባይ ማጥፊያ ጠጥተዉ አምስት ህጻናት ህይወታቸው ማለፉን አስታዉሰዋል።የአረም ማጥፊያ የተቀላቀለበትን ምግብ የተመገበዉ ህጻን ወደ ትምህርት ቤቱ ቢመለስም በግማሽ ሰዓት ዉስጥ ማስመለስ እና መሬት ላይ ወድቆ መንፈራፈር ይጀምራል።ህጻናት ጓደኞቹ የአክረምን ህመም ተመልክተዉ ለመምህራን በሰጡት ጥቆማ ህጻኖ ወደ በደኖ ጤና ጣቢያ ተልኮ የህክምና እርዳታ አግኝቶ ህይወቱ ተርፏል ብለዉናል።

ከዚህ በመቀጠል ፖሊስ በምርመራዉ ወላጅ አባቱ ባደረገዉ ድርጊት በቁጥጥር ስር አዉሎ ፥ ህጻኑ የግድያ ሙከራ እንደተፈጸመበት በሰዉና በህክምና ማስረጃ አረጋግጧል። የካቲት 14 2016 ዓ.ም በዐቃቤ ህግ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 27 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በግድያ ሙከራ ክስ እንደመሰረተበት ገልጸዋል።

ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ከድር አህመድ በገዛ ልጁ ላይ የግድያ ሙከራ በመፈጸሙ በ 7 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲሉ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሳሊም ቱጂሃን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
"በዓለም ላይ ዝቅተኛው የመብራት ታሪፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሆነ ከዓለም ጋር እኩል ለመሰለፍ  የታሪፍ ጭማሪ እናደርጋለን "  [መብራት ኋይል]‼️
እነሱ:-  የነዳጅ ዋጋ ኬንያ ላይ፣ የወኋ ዋጋ ጅቡቲ ላይ፣ የኢንተርኔት ዋጋ ኤርትራ ላይ፣ የመብራት ታሪፍ በዓለም ላይ ውድ ነው። ከዓለም እኩል ለመሆን የዋጋና የታሪፍ ጭማሪ እናደርጋለን። አዳዲስ የግብር ዓይነቶች ማለትም እንደ ፕሮፐርቲና የተሽከርካሪ ታክስ ያሉትን ሁሉም ሀገራት ስለሚያስገብሩ እናንተም ትገብራላችሁ

እኛ:- ኬንያ ውስጥ አማካይ ዝቅተኛ ግብር የማይከፈልበት የደሞዝ መጠን 111.5 ዶላር ወይም 6438 ብር ነው። የገቢ ግብር ደግሞ አራት እርከን ብቻ ያለው ሲሆን ዝቅተኛው የደሞዝ ግብር የሚጀምረው ከ10% ነው። ከፍተኛው የደሞዝ ግብር ደግሞ 32.5 % ሲሆን በዶላር 2326 ወይም በብር 132,558 በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ላይ ይጣላል። 

ኢትዮጵያ ውስጥ ዝቅተኛው ግብር የማይከፈልበት ደሞዝ 600 ብር ወይም 10.5 ዶላር በታች ሲሆን 10% ይከፈልበታል። ከፍተኛው የደሞዝ ገቢ ግብር 35 % ሲሆን ደሞዝህ  ከ10,000 በላይ ወይም 175.4 ዶላር ከሆነ ጀግሞ 35% ትገብራለህ። ቫት፣ ቲኦቲና ወዘተን ሳይጨምር ማለት ነው።
ከኬንያና ከዓለም ልምድ በመቅሰም የመብራት፣ የወኋ፣ የፕሮፐርቲ ታክስና የተሽከርካሪ ግብር በመጨመር ከዓለም ጋር እኩል እንዳደረጋችሁን ሁላ የደሞዝ እድገት፣ የገቢ ግብርና ዝቅተኛ የደሞዝ መጠንንም በልምድ ልውውጡ አካታችሁ ከዓለም ሕዝብ ጋር እኩል አድርጉን።
ሙሼ ሰሙ የፃፉት ነው

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
እያንዳንዱ የፍልስጤም እስረኛ በአማካይ 30 ኪሎ ግራም ያህል መቀነሱን የአል-ሺፋ ሆስፒታል ዋና ሃላፊ አስታወቁ

የአል-ሺፋ ሆስፒታል ዋና ኃላፊ አቡ ሳልሚያ በእስራኤል ማረሚያ ቤት ስላለው ሁኔታ መረጃን አፋርተዋል፡፡በምርመራ ክፍል ውስጥ በርካታ እስረኞች የተገደሉ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን በእስራኤላውያን ወታደሮች ስር ይገኛሉ፡፡የእስራኤላውያን ዶክተሮች እና ነርሶች የፍልስጤም እስረኞችን ይደበድባሉ ፤ ያሰቃያሉ እንዲሁም የታሳሪዎችን እንደ ግዑዝ እቃ አድርገው ይቆጥሩታል ብለዋል።በእስራኤላውያን ወታደሮች የተያዘ እያንዳንዱ እስረኛ ወደ 30 ኪሎ ግራም በአማካይ ክብደት ቀንሷል፣ ምግብም ተከልክሏል።

የአል-ሺፋ ሆስፒታል ዋና ሃላፊ ሶስት ጊዜ ፍርድ ቤት ብቀርብም ምንም አይነት ክስ አልቀረበብኝም ይህ ማለት በፖለቲካ ምክንያት እንደያዙኝ ያሳያል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ከባድ ስቃይ ደርሶብናል፤ የእስራኤል ወታደሮች የእስረኞቹን ክፍል በኃይል በየቀኑ በመዉረር ጥቃት ያደርሱብን ነበር ሲሉ ተደምጠዋል።ከጠበቆች ጋር አልተገናኘንም፣ ወይም የትኛውም ዓለም አቀፍ ተቋም አልጎበኘንም።ለሁለት ወራት ያህል አንድም እስረኛ በቀን ከአንድ ዳቦ በላይ አልተመገበም ሲሉ አክለዋል፡፡

በሌላ በኩል የእስራኤል ጦር ቢያንስ 16 ፍልስጤማውያንን በዌስት ባንክ በሙሉ ማሰሩን ዋፋ የዜና ወኪል ዘግቧል።ከመኖሪያ ቤታቸው እና በወታደራዊ ኬላዎች የታሰሩትን፣ በጭቆና እጃቸውን የሰጡ እና ታግተው የተወሰዱት ሰዎች መኖራቸዉ ተሰምቷል፡፡የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የአል-ሺፋ ሆስፒታል ዳይሬክተር መሃመድ አቡ ሳልሚያን ጨምሮ የፍልስጤም እስረኞች ከጋዛ እንዴት እንደተፈቱ አፋጣኝ ምርመራ እንዲደረግ ማዘዛቸውን ከቢሮአቸው የወጣዉ መግለጫ አመላክቷል።

ከተለያዩ የእስራኤል የፖለቲካ ሰዎች ውግዘት ያስከተለው ከእስር መፈታት በኔጌቭ ሳዴ ቴማን ካምፕ መታሰራቸውን በመቃወም በጠቅላይ ፍርድ ቤት በተደረገው ውይይት ላይ መሆኑን የኔታንያሁ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። አቤቱታውን ማን እንዳቀረበው አልታወቀም።ጽህፈት ቤቱ “የተፈቱት እስረኞች ማንነት በጸጥታ ኃላፊዎች ሙያዊ ግምት ውስጥ በማስገባት ማንነት የሚወሰን ነው” ብሏል።


አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
Update‼️
በቱርክ አደራዳሪነት ትናንት አንካራ ውስጥ የተነጋገሩት ኢትዮጵያና ሱማሊያ ነሃሴ 27 በድጋሚ ለመነጋገር መስማማታቸውን የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሐካን ፊዳን ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫም፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የሱማሊያው አቻቸው አሕመድ ፊቂ በኹለቱ አገሮች ልዩነት ዙሪያ በተናጥል ግልጽነት የተሞላበት ውይይት እንዳደረጉና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ በንግግር ለመፍታት እንደተስማሙ ገልጧል።

የኹለቱን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ንግግር የመሩት፣ የቱርኩ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሐካን ፊዳን ናቸው።


አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
ለጥበቃ በተሰጠዉ የጦር መሳሪያ የስራ ባልደረባዉን የገደለዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

የኢሉባቡር ዞን ፖሊስ መምሪያ ፤ ታረቀኝ አለማየሁ የተባለዉ ግለሰብ በያዩ ወረዳ የያዩ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጥበቃ ሰራተኛ ሆኖ እያገለገለ እያለ በስራዬ ጣልቃ እየገባ ነዉ በሚል የስራ ባልደረባዉን መግደሉን ፖሊስ መምሪያዉ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን የላከዉ መረጃ ያመላክታል።

ግለሰቡ ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት አስቦና አቅዶ የስራ ባልደረባዉን ለመግደል ተዘጋጅቶ ተኩሶ መግደሉን በማስረጃ መረጋገጡን ያገኘነዉ መረጃ ጠቁሟል።

ፖሊስ ምርመራዉን አጠናቅቆ ፤ ዐቃቢ ህግ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 32 ንዑስ በአንቀጽ 1 እና 540 መሰረት በግድያ ወንጀል ክስ የመሰረተበት መሆኑም ተገልጿል።

በዐቃቢ ህግ የተመሰረተዉን ክስ ሲመለከት የቆየዉ የኢሉባቡር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፤ ተከሳሽ ታረቀኝ አለማየሁ የቀረበበት ክስ በማስረጃ በመረጋገጡ እና መከላከል ባለመቻሉ ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በ 10 አመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የኢሉባቡር ዞን ፖሊስ መምሪያ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን የላከዉ መረጃ ያመላክታል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
" በትልቅ ቁጠባ በ33 ቢሊዮን ነው እየተተገበረ ያለው " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፥ የከተማው 5ቱ ኮሪደር ስራ እየተተገበረ ያለው በ33 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህን የተናገሩት ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ፥ መጀመሪያ ላይ የ5ቱም ኮሪደር ስራ ሲጠና ኮንሰልታንቶችና አጥኚው ቡድን መንገድ እና የመንገድ መሰረተ ልማት የሚፈጀው ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ እንደገለጹ አስረድተዋል።

" ይህ እንግዴ በወቅቱ ጥናት ነው በዚህ ተለዋዋጭ ገበያ " ያሉት ከንቲባዋ " እስካሁን ድረስ የተጠኑትን 5 ኮሪደሮች እየተገበርን ያለነው በ33 ቢሊዮን ነው " ብለዋል።

በ33 ቢሊዮን ብር እየተተገበረ ያለው ስራም " ትልቅ ቁጠባ የተተገበረበት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ስራው ብክነትን በመከላከል፣ የሚወጣውን ወጪም አስፈላጊ ነገር ላይ ብቻ እንዲሆን እየተደረገ ነው ብለዋል።

አንዳንድ በከተማው አስተዳደር የሚሰሩ ስራዎችም ለኮንትራክተሮች እንዳልተሰጡ የተናገሩት ከንቲባዋ ፥ ለአብነት የሜክሲኮ መንገድ በኮንትራክተር ሳይሆን በራስ አቅም መሰራቱን ገልጸዋል።


አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
የቀድሞ የፔንታጎን አማካሪ " ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም ላይ የበላይ ሆና ለመቀጠል ያላትን ፍላጎት እርግፍ አድርጋ መተው አለባት -ይህ ካልሆነ ግን ዩናይትድ ስቴትስ እንደ አገር ከተመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ አይታው የማታውቀው ታላቅ ውርደት ይገጥማታል" ብለዋል።

የቀድሞ የፔንታጎን አማካሪ ዳግላስ ማክግሪጎር አክለውም "በአሁኑ ጊዜ ዩናይትድ ስቴትስ ዓለምን ለመቆጣጠር የሚያስችላት በቂ የገንዘብ ድጋፍ እና የሌሎች አገሮች እምነት የላትም" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።


በነገራችን ላይ
#ዳግላስ_አቦት_ማክግሬጎር በጡረታ የተገለሉ አሜሪካዊ ኮሎኔል፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ ደራሲ፣ የቀድሞ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ እና የፖለቲካ ተንታኝ ናቸው።

#ማክግሬጎር በባህረ ሰላጤው ጦርነት ወቅት የታንክ ውጊያው ዋና አዛዥ - አዋጊ እና ቀደምት መሪ የነበሩ ሲሆን እ.አ.አ በ1999 ኔቶ በዩጎዝላቪያ ላይ ለፈጸመው ጭፍጨፋ እና ላደረሰው የቦምብ ጥቃት ከፍተኛው እቅድ አውጪ - በቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ አስተዳደር ከፍተኛው ተጽዕኖ ፈጣሪ ነበሩ።


አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
የሩስያ የኒዩክለር ሰርጓጅ መርከቦች በብሪታንያ አቅራቢያ "ከዚህ በፊት ታይተው የማያውቁ" እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል - ሲል #ብሉምበርግ ዘግቧል።

የሩሲያ ፌዴሬሽን መንግስት ጥንቃቄ የተሞላበት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለማካሄድ ቢያንስ ለሁለት ጊዜ ያህል የጥቃት ሰርጓጅ መርከቦችን ወደ አይሪሽ ባህር ልኳል - የብሪታንያ መንግስት ግን ስለ ሁኔታው አንዳች እውቀት አልነበረውም ሲል መረጃውን ይፋ አድርጓል።

ብሉምበርግ ስለ ሃሊቡት እና የቫርሻቪያንካ ፕሮጀክቶች የባህር ሰርጓጅ መርከቦች ሚስጢራዊ የተባሉ ዝርዝሮችን ባስነበበበት በዚህ እትሙ "ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ እርምጃ" ነበር - በዚህም የብሪቲሽ መከላከያ ሚኒስቴር በእንግሊዝ እና በአየርላንድ ዙሪያ የባህር ላይ የደህንነት ስራዎችን እንዲያካሂድ አስገድዶታል ፡ ሲል ጽፏል።

ጽሑፉ ዩናይትድ ስቴትስ🇺🇸አሜሪካ ስለ ባሕር ሰርጓጅ መርከቦቹ በቂ መረጃ እንዳላት ቢገልጽም የብሪቲሽ መከላከያ ሚኒስቴር ግን ሁኔታውን አስመልክቶ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም - ብሏል ብሉምበርግ።


አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
#Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ አቶ ካሳሁን ጎፌን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾሙ።

ወ/ሮ ሽዊት ሻንካን ደግሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ቀጀላ መርዳሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶች እና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ከዛሬ ሰኔ 26 /2016 ዓ/ም ጀምሮ እንደ ተሾሙ ታውቋል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja