Berbir Mereja / በርብር መረጃ
6.24K subscribers
19.4K photos
659 videos
5 files
16.5K links
Welcome back to our channel, where we bring you the latest updates and news from around the world.
Download Telegram
" ኢትዮጵያ አሁን ያላትን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት 10 ወደቦች ያስፈልጓታል " - ጅቡቲ

ጅቡቲ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ በሚል ከኢትዮጵያ 100 ኪ/ሜ ርቆ የሚገኘውን የ ' ታጁራ ወደብ ' ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት የሚል የመፍትሄ ሀሳብ አቅርባለች።

ለጊዜው በምን መልኩ ፤ እንዴት ነው የምትጠቀመው የሚለው በዝርዝር አልታወቀም።

ኢትዮጵያ ይህን የጅቡቲ ጥያቄ ትቀበለው አትቀበለው እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም።

የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዩሱፍ " ይሄ ለኢትዮጵያ በጣም የሚጠቅም ነገር መሆኑን እናውቃለን።

ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ ሸማቾች ያሏት ትልቅ ሀገር እንደመሆኗ ኢትዮጵያ ከ3 እና 4 በላይ ወደቦች ያስፈልጓታል።

ኢትዮጵያ አሁን ያላትን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት 10 ወደቦች ያስፈልጓታል።

እኛ እነዚህን የኢትዮጵያን ፍላጎቶች እንረዳለን። የሚጠበቀውን ለማድረግም እንሞክራለን።

ኢትዮጵያ የባህር ኃይል ጦር ሰፈር መገንባት አትችልም ግን ኢትዮጵያ ከአንድ በላይ ወደብ እንዲኖራት ለመርዳት እንፈልጋለን።

ኢትዮጵያ ከአንድ በላይ መተላለፊያ እንዲኖራት በማገዝ የተፈጠረውን ውጥረት በማርገብና ሁሉም እንዲረጋጋ በማድረግ በዋናው ቁምነገር ላይ ማተኮር አለብን።

እንደ ጅቡቲ ያለን ሚና ያ ነው። ላለፉት ዓመታት ስናደርግ የነበረውም ያንን ነው። አሁንም በነዚህ መርሆች ላይ መስራታችንን እንቀጥላለን።

እኛ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የነበረው መልካም ግንኙነት ወደነበረበት እንዲመለስ እንፈልጋለን " ብለዋል ለቪኦኤ በሰጡት ቃል።

ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት የአፍሪካ ግዝፏ ሀገር #ኢትዮጵያ የባህር በር አልባ ስትሆን ያላት ፍትሃዊ ጥያቄዋ ላለፉት በርካታት አመታት እንደ ሀገር አጀንዳ ሳይሆን ቆይቷል። ጉዳዩም በዚህ ልክ ተነስቶ አያውቅም ነበር።

ከወራት በፊት ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ ግን ጉዳዩ የዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኗል።

ምንም እንኳ ስምምነቱን ተከትሎ ሶማሊያ አኩርፋ ግንኙነቷን ብታሻክርም ችግሩን ለመፍታት በሚል የተለያዩ የመፍትሄ ሀሳቦች መቅረብ ጀምረዋል።

ሀገሪቱ (ሶማሊያ) ከ " ኢትዮጵያ ጋር አልነጋገርም " ብትልም ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ ያላትን አቋም ከተመለከተች በኃላ በአሸማጋዮች አማካኝነት ወደ ውይይት ጠረጴዛ መጥታለች። ምንም እንኳ እስካሁን ውይይቶቹ ፍሬ አልባ ቢሆኑም።

#ETHIOPIA

☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️ ☄️  ☄️ ☄️  ☄️

☄️⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ          ☄️

☄️📱  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                           ☄️

☄️📱  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/            ☄️

☄️📱  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja                      ☄️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በጫሞ ሐይቅ ላይ የደረሰውን የጀልባ መስጠም አደጋ ተከትሎ የነፍስ አድን ሥራ እየተከናወነ ነው

#Ethiopia | ከአቡሎ አርፋጮ ወደ አርባምንጭ ከተማ 16 ሰዎችን እና ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ጫሞ ሐይቅ ላይ መስጠሟን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜም ሦስት ሰዎች በሕይወት መገኘታቸውን መምሪያው አረጋግጧል፡፡

አደጋው ትናንት 10 ሠዓት ከ20 ገደማ መከሰቱን የገለጹት በመምሪያው የሕዝብ ግንኙነትና ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ÷ አሁንም የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ ከልክ በላይ መጫን ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመው÷ በጀልባዋ ላይ የነበሩት ተሳፋሪዎች የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

     
🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆

⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ         

  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                          

  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/           

  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM