Berbir Mereja / በርብር መረጃ
6.24K subscribers
19.4K photos
659 videos
5 files
16.5K links
Welcome back to our channel, where we bring you the latest updates and news from around the world.
Download Telegram
በ2017 የትምህርት ዘመን  ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ሲያካሂዱ  የልደት ሰርተፍኬት መቀበል አስገዳጅ ሆነ

የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ ስርዓት ዘመናዊ የትምህርት ስርዓት መዘርጋት እንዲቻል  እንዲሁም ያልተመዘገበ ልደት ክምችትን ሙሉ ለሙሉ ለማቅለል የልደት ምዝገባ ሰርተፍኬትን በከተማዋ ባሉ  ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ቅበላ የምዝገባ ቅድመ ሁኔታ አሰራር ስርዓት አስገዳጅ መሆኑን አስታውቋል።

በመሆኑም እስካሁን የልደት ምዝገባ ያላከናወኑ ህፃናት እና ተማሪዎች በወረዳ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ቀርበው መመዝገብ እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮናስ ዓለማየሁ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ከከተማው የትምህርት ቢሮ ጋር ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን ከመደበኛ ቀናት በተጨማሪ  ከሰኔ 22 ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን የዚህ ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑንም ሃላፊው ገልጸዋል።በምዝገባ ወቅት ወላጆች ነዋሪ የሆኑበት የወረዳ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት  የወላጆች ማንነትን የሚገልፅ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት፣ ከወረዳው አስተዳደር መደበኛ ነዋሪነቱን የሚገልጽ  የድጋፍ ደብዳቤ ወይም ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ባልደረባነታቸው እና ዜግነት የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤና የመስሪያ ቤቱን መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

የህፃኑ ወላጆች በህይወት ካሉ አባት እና እናት ሁለቱም በአካል መቅረብ ያለባቸው ሲሆን ልደቱን ለማስመዝገብ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሁለት አንዳቸው ያልቻሉ ሲሆን አንዳቸው ለሌላቸው ልዩ የልደት ውክልና በመስጠት ማስመዝገብ ይቻላሉ።  ከወላጆቹ አንዱ በህይወት የሌለ ከሆነ ደግሞ  በህይወት ያለው ወላጅ የሟች ወላጅን ህጋዊ የሞት ማስረጃ ሲያቀርብ ልደቱ ይመዘገባል፡፡

ልደቱ ሲመዘገብ የህፃኑ አባት ያልታወቀ እንደሆነ የእናትየዋ አባት ስም የልጁ አባት ስም ሲሆን የእናትየዋ አያት ስም ደግሞ የልጁ አያት ስም ሆኖ ይመዘገባል፡፡  ከወላጆቹ አንዱ የውጪ አገር ዜጋ ከሆነ የህፃኑ ዜግነት በኢትዮጵያዊ ወላጅ ውሳኔ መሰረት የሚመዘገብ መሆኑም ተነግሯል።

በመሆኑም ወላጆች ልጆቻቸውን  ለ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ሲያካሂዱ  የልደት ሰርተፍኬት  አስገዳጅ  እንደሆነ ሊገነዘቡ  እንደሚገባ አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
በቦንጋ ከተማ ከተወለደች ሰባት ቀን የሞላት ህፃን ተጥላ በህይወት ተገኘ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ማሪያም ቤተክርስቲያን አከባቢ ከተወለደች ሰባት ቀናት የሚሆናት ጨቅላ ህፃን ተጥላ መገኘቱን የቦንጋ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን  እንደገለፁት የአከባቢው ህብረተሰብ አመሻሽ ላይ የህፃን ድምፅ ሰምተው፤ ህፃኗን በህይወት መኖሯን ሲያረጋግጡ ለፖሊስ በማሳወቅ ወደ ህክምና ወስደዋል። የህፃኗ ጤንነት ተረጋግጦ ለቦንጋ ከተማ ሴቶችና ህፃናት የስራ ሂደት ዳይሬክቶሬት እንደተሰጠች ገልፀዋል፡፡

በከተማዉ በተደጋጋሚ ጊዜ ተወልደዉ የሚጣሉ ህፃናት እየተበራከቱ በመምጣቱ ተወልደው የሚጣሉ ህፃናት ማቆያ አለመኖሩ ችግር እንደሆነ ተገልፆል።

ከዚህ ቀደም በከተማ ዉስጥ ተወልደዉ የተጣሉ ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ህፃናት መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን በቦንጋ ገብረፃዲቅ ሆስፒታል ትብብር በማድረግ በጊዜያዊነት እንዲቆዩ ተደርጓል።በጉድፈቻ ለማሳደግ የሚፈልግ ሰዉ ቦንጋ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት በአካል ቀርቦ በሕጋዊ መንገድ መውሰድ ይችላል ተብሏል፡፡

የሰባት ቀን ጨቅላ  ህፃን ልጆን  ወልዳ የጣለችዉን እናት ፖሊስ እያፈላለገ እንደሚገኝ ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡


አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን “የመንግሥት ኃይሎች”  ‘ሰላማዊ ሰዎችን’ እንደገደሉ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ጥቃቱ ሰኔ 19/ 2016 ዓ/ም መፈፀሙ የተነገረ ሲሆን፤ ቢያንስ 15 ንጹሃን ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ ሾላ ሜዳ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሰኔ 19 በመንግሥት ኃይሎች ደርሷል በተባለ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸውን እና አራት የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎቹ ነግረውኛል ብሏል።

በከተማዋ ‘አጋም በር መገንጠያ’ በተባለ ሰፈር ጥቃቱ በዕለቱ 11፡30 አካባቢ እንደተፈጸመ አንድ ከጥቃቱ የተረፉ እማኝ፤ በጥቃቱ በአብዛኛው ማዳበሪያ ለመውሰድ ከተለያዩ ቀበሌዎች የመጡ አርሶ አደሮች እንደተገደሉ ለጣቢያው ገልጸዋል።

ከመንግስት አካላት መረጃ ለማግኘት ያደረኩት ሙከራ አልተሳካም ሲል ከመንግስት በኩል መካተት የነበረበት ምላሽ እንዳልተካተተ ዘገባው ጨምሯል።

በአማራ ክልል በሰኔ ወር መጀመሪያ ቀናት በምዕራብ ጎጃም እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች “በመንግሥት ኃይሎች” ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ጠዋት ወደ ደሴ አቅንተው የልማት ስራዎችን እንደጎበኙ እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት እንዳደረጉ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ደሴ ማቅናታቸውን ተከትሎ ከወልዲያ እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢዎች ለተወሰኑ ሰዓታት ወደ ደሴ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ እንደነበር ገልፀውልኛል።

🎯ደሴ ከተማ የመሰረተ ልማት ስራዎች ተመርቀዋል።

🎯ሀይቅ ከተማ ስራ ቀድሞ የተጀመረ ቢሆንም የገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን በይፋ የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።


አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
#ኢራን

"እስራዔል ሊባኖስን የምታጠቃ ከሆነ ምላሽ ለመስጠት እገደዳለሁ" - ኢራን

በተ.መ.ድ የኢራን ተወካይ በኤክስ ገጹ ባሰራጨው መረጃ እስራዔል ይፋዊ ጦርነት ከጀመረች ኢራን ጦርነቱን የማጥፋት ኃላፊነት አለባት ብሏል፡፡

ጦርነቱን ለማስቆም "ከታጋይ ቡድኖች ጎን መሰለፍን ጨምሮ አሉ የተባሉ አማራጮችን" ትጠቀማለች ነው የተባለው፡፡

የሂዝቦላህ ደጋፊ እንደሆነች የምትገለጸው ኢራን እስራኤልን አስጠንቅቃለች፡፡ በኒዮርክ ያለው የኢራን ኢምባሲ በኤክስ አካውንቱ እንዳስታወቀው እስራኤል ሊባኖስን ካጠቃች ደብዛዋ ሊጠፋ ይችላል ብሏል፡፡

ለእስራኤል የሀገርነት እውቅና የነፈገችው ኢራን እስራኤል በሊባኖስ ላይ ጦርነት ካወጀች በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች ሁሉ የተቀናጀ ጥቃት እንደሚከፍቱም አስጠንቅቃለች፡፡

ይሁንና ኢራን በቀጥታ ወደ ጦርነቱ እንደምትገባ እና እንደማትገባ በይፋ ያልተናገረች ሲሆን በሊባኖስ ላይ ሙሉ ጦርነት ከታወጀ ግን እስራኤል ህልውናዋ የሚጠፋት ይሆናል ብሏል፡፡

ቱርክ ከሰሞኑ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣችው መግለጫ እስራኤል በሊባኖስ ላይ ይፋዊ ጦርነት ካወጀች ለሊባኖስ የቀጥታ ድጋፍ እንደምታደርግ አስጠንቅቃለች፡፡

ኢራን በሄሊኮፕተር አደጋ የሞቱትን ኢብራሂም ራይሲን የሚተካ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ከትናንት ጀምሮ ሀገር አቀፍ ምርጫ እያካሄደች ትገኛለች፡፡ #gulftoday

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
ኢትዮጵያ በ2023 ብቻ ኢንተርኔት በመዝጋት ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊየን ዶላር በላይ ማጣቷ ተገለጸ፣ ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ቀዳሚነቱን ይዛለች

የኢትዮጵያ ኢኮኖሞ በ2023 ብቻ ኢንተርኔት በመዝጋቱ አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገደማ ማጣቱን አንድ ጥናት አመላከተ።

የመብት እና ዲሞክራሲ ማዕከል (Center for Rights and Democracy (#CARD)) ያካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ኢንተርኔት በመዘጋቱ ሳቢያ በቀዳሚነት በርካታ ገቢ ያጣው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ነው።

በ2023 ብቻ በኢትዮጵያ ለ14ሺ 910 ሰአታት የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል፤ ከ29 ሚሊየን በላይ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ተጎጂ ሁነዋል ብሏል።

ኢንተርኔት እንዲቋረጥ የተደረገው በግጭቶች እና አለመረጋጋት ምክንያት መሆኑንም ጥናቱ አመላክቷል።

የኢንተርኔት መዘጋት በሀገሪቱ እየተስፋፋ ነው ያለው ተቋሙ የዜጎችን መብት እየገደበ ነው ሲል በአጽንኦት አሳስቧል።(አዲስ ስታንዳርድ)

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
የሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት ስራ አስኪያጅ ደቡብ ኮሪያ ይዘውት ከሄዱት የባህል ቡድኑ ጋር ኮበለሉ

ከ15 ቀን በፊት የኮሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት የተቀሰቀስበትን 74ኛው ዓመት መታሰቢያ በዓልን አስመልክቶ የአዲስ አበባ እህት ከተማ በሆነችው የደቡብ ኮሪያዋ ቹንቺዮን ከተማ ላይየኢትዮጵያን ባህል ለማቅረብ የሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልከሪም ጀማል ይዘው ከሄዱት የባህል ቡድን አባላት ጋር ደቡብ ኮሪያ ላይ መጥፋታቸውን የቴአትር ቤቱ የባህል ቡድን አባላትና ሰራተኞች ነግረውኛል:: ከቀናት በፊትም በጊዜያዊነት ለቴአትር ቤቱ ኃላፊ መመደቡንም እነዚሁ ሰራተኞች ነግረውኛል::እኔም ጉዳዩን ለማጣራት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነጥበብ ቱሪዝም ቢሮ የባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ሰርፀ ፍሬስብሐት ጋር ደውዬ ነበር:: እርሳቸውም እንደነገሩኝ የተፈጠረውን ጉዳይ አሁን ቴአትር ቤቱን የሚያስተዳድረው የልማት ድርጅት የእርሳቸውም ቢሮ መረጃ እንደደረሰውና እንደሚያውቀው ገልፀውልኝ ብዙውን ተከሰተ የተባለውን ዝርዝር ጉዳይ ዛሬ እንደሰሙት ገልፀውልኝ በጉዳዩ ላይ ማጣራት እያደረጉ እንደሆነ ነግረውኛል:: በጉዳዩ ላይ ጥቂት መረጃ ሰጥተውኛል::

የኮሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት የተጀመረበትን 74ኛው ዓመት መታሰቢያ በዓልን ምክንይት በማድረግ የአዲስ አበባ እህት ከተማ በሆነችውና የኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ሐውልት በሚገኝበት ቹንቺዮን ከተማ የባህል ፌስቲቫል በየአመቱ ይካሄዳል:: በዚህ ዓመትም በዚህ ፕሮግራምና በሁለቱ እህት ከተሞች መካከል በሚካሄደው የባህል ልውውጥ ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ የሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት እና የኦሮሚያ ክልል የባህል ቡድን አባላት ወደ የደቡብ ኮሪያዋ ቹንቺዮን ከተማ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋ እንዲሄዱ ተመረጡ:: ከዚያም የሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ:ከውጭ ጉዳይ: ሚኒስትር የተላከላቸውን ደብዳቤ አያይዘው በላኩት መሰረት በዚህ የባህል ዝግጅት ላይ ከተማዋን ወክለው እንዲሳተፉ በኃላፊያችን በዶ/ር ሂሩት ካሳው ተፈርሞ ተሰጣቸው:: የሆነው ይህ ነው::

ከዚያም...

የሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ በአቶ አብዱል ከሪም የተመራው የባህላዊና የውዝዋዜና የዳንስ ቡድን ከኦሮሚያ ባህል ቡድን ቀድሞ ደቡብ ኮሪያ ይደርሳል:: ከጥቂት ቀናት በኃላ የሄደው የባህል ቡድን በዚህ መሃል በሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት ስራ አስኪያጅ የሚመራው የልዑካን ቡድን ደቡብ ኮሪያ ከገባ በኃላ የቴአትር ቤቱ ስራ አስኪያጅን ጨምሮ ሁሉም ተጏዦች ኮበለሉ:: በዚህ ሳቢያ ከሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት የባህል ቡድን አባላት ጋር ዝግጅቱን ሊያቀርብ ወደ ደቡብ ኮሪያ ለመሄድ የተዘጋጀውና ለጉዞ ኤርፓርት የደረሰው የኦሮሚያ የባህል ቡድን አባላት የሐገር ፍቅር አባላት በመጥፋታቸው ከኤርፖርት እንዲመለሱ ተደርገዋል:: ሌላው የሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት ባህላዊ ውዝዋዜና የዳንስ ቡድን አባላት እንደነገሩኝ ከሆነ ደቡብ ኮሪያ ለመሄድ በስራ አስኪያጃችን በኩል አሟሉ የተባልነውን መረጃ አሟልተንና በፕሮግራሙ የምናቀርባቸውን ስራዎች እየተለማመድን ባለበት ሁኔታ ነው ቴአትር ቤቱን ወክለው የሄዱት አባላት መጥፋታቸውን የሰማነው ብለውኛል በመገረምና በማዘን:: ታዲያ ስራ አስኪያጁ ማንን ይዘው ነው የሄዱት? ብዬ ጠየኳቸው ከቀሩት ባህል ቡድኑ አባላት አንዱን" እኔ እንደምሰማው ከሆነ ብዙ ገንዘብ እየከፈሉ በእኛ ስም የሄዱ እንዳሉ ሰምቻለሁ::" ብሎኛል::

ይህን የቴአትር ቤቱ የባህል ቡድን አቤቱታ በተመለከተ የባህል ኪነጥበብ ቢሮ ኃላፊው
"በደረሰን መረጃ መሰረት ከሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት የባህል ቡድን አንድም የቴአትር ቤቱ የባህል ቡድን አባላት ወደ ደቡብ ኮሪያ እንዳልሄዱ ይህንንም ጉዳይ በተመለከተ ኮሚቴ ተዋቅሮ ማጣራት እየተደረገ እንደሆነ አቶ ሰርፀ ነግረውኛል:: አቶ አብዱል ከሪም ጀማል የሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት ስራ አስኪያጅ ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ ቴአትር ቤቱን በከፍተኛ ኃላፊነትና በእውቀትና በትጋት ሲያገለግሉ የቆዩና በቴአትር ቤቱ ሰራተኞችም በስራቸው የተመሰገኑ ወጣት የቴአትር ባለሙያ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል:::

ባሳለፍነው ወር ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በደቡብ ኮሪያና አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በተጨማሪምጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር የአዲስ አበባዋ እህት ከተማ ወደሆነችው ቹንቺዮን ከተማ በመሄድ የኢትዮጵያ ኮሪያ ጦርነት መታሰቢያ ሃውልት ጋር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠው የኢትዮጵያ የኮርያ ጦርነት ዘማቾች መታሰቢያ መዐከልንም መጎብኝታቸው ይታወቃል::

Via Yetebarek Walelegen

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
ሀዉቲ 4 መርከቦችን አወደማቸዉ

ቀይ ባሕርን በእሳት ያጠራት በኢራን የሚደገፈው ሃውቲ ከእስራኤል እና አሜሪካ ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 4 የንግድ መርከቦች በባለስቲክ ሚሳኤል እና በድሮን መደብደቡን ሁሉም ይወቅልኝ ብሎ በሰበር ዜና ከተፍ ብሏል። አንደኛው መርከብ ለእስራኤል ዘይት ጭኖ ወደ ሃይፋ ወደብ ሲጓዝ የነበረ ነው ተብሏል።

የየመኑ በቀይ ባህር እና በሜዲትራኒያን ባህር ላይ በአራት የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረጋቸውን የንቅናቄው ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሪያ ተናግረዋል። እንደ ሳሪያ ገለጻ ጥቃቱ የተፈጸመው በሃውቲ ብቻ ሳይሆን በኢራቅ በሚገኙ እስላማዊ ሃይሎች ድጋፍ ጭምር ነው።

እንደ ያህያ ሳሬ ገለጻ የሁቲዎች እና የኢራቅ እስላማዊ ተቃውሞ የሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጦ ወደ እስራኤል ሃይፋ ወደብ ይሄድ የነበረውን ዋለር ዘይት ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት አድርሰዋል። "መርከቧ የተጠቃችው በተያዘችዉ ፍልስጤም ወደቦች ላይ የሚደረገውን መንገድ በመተላለፉ ነው" ሲሉ ያህያ ሳሬ የሃውቲ ንብረት ለሆኑት አል ማሲራህ የቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግሯል።

ከዚህ ውጪ ሃውቲዎች በሜዲትራኒያን ባህር ዮሃንስ ማርስክን ኮንቴይነር መርከብ ላይ፣ እንዲሁም ዴሎኒክስ የተሰኘውን ፈሳሽ ኬሚካሎች እና በቀይ ባህር ውስጥ የሚገኘውን አዮኒስ የጅምላ ተሸካሚ መርከብ ላይ ጥቃት አድርሰዋል። ዮሃንስ ማርስክ እና ዴሎኒክስ የሚሳኤል ጥቃት ሲደርስባቸው የተቀሩት በውሃ ውስጥ በሚምዘገዘጉ ሰው አልባ ድሮኖች ጥቃቱ ተፈጽሞባቸዋል።

ሃውቲ በአንድ ግዜ አራት መርከብ መምታቱን ተከትሎ እስራኤል ሲጠብቃት የነበረው የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከብ ከቦታው ጥሎ መውጣቱ ለጥቃት እንዳጋለጣት አመላክቷል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
የቻይናው ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስረመቀ

የቤጂንግ የውጭ ቋንቋዎች ጥናት ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋ ያስተማራቸውን የመጀመሪያዎቹን ተማሪዎች አስመርቋል።

በቻይና የአማርኛ ቋንቋን በብቸኝነት የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያዎቹን ተማሪዎች በይፋ አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው እየሰጠው ያለው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የሃገራቱን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያግዛል ተብሏል።

በዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ጂያ ዴዦንግ የተመራ ልዑክ የፊታችን ማክሰኞ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርግ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
1 ሺህ 169 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 169 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለተመላሽ ወገኖችም ድጋፍ እየተደረገና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከ52 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያን ተመልሰዋል፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
አትሌት በላይ ዝቁ አስፋው እና መቅደስ ሽመልስ የ"መቻል ለ ኢትዮጵያ" የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን አሸነፉ

የ"መቻል ኢትዮጵያ" የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን በወንዶች አትሌት በላይ ዝቁ አስፋው እና በሴቶች አትሌት መቅደስ ሽመልስ አሸነፈዋል፡፡

በግሉ የተዋዳደረው አትሌት በላይ ዝቁ አስፋው የ"መቻል ለ ኢትዮጵያ" የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን አሸነፏል፡፡

ጠንካራ ፉክክር ያደረገው ሌላኛው አትሌት ጌታነህ ሞላ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ ደሞዝ በቀለ በሦስተኛነት ውድድሩን ጨርሷል፡፡

በሴቶች የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን አትሌት መቅደስ ሽመልስ አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች፡፡
እንዲሁም አትሌት መብራት ግደይ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
አሜሪካ ለእስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ አውዳሚ ቦምቦች መላኳ ተገለጸ

አሜሪካ ለእስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ ባለ2000 ፓውንድ ክብደት ያላቸው አውዳሚ ቦምቦች መላኳ ተገለጸ

የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር የጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ 10000 ባለ 2000 ፓውንድ ክብደት ያላቸውን አውዳሚ ቦምቦችና በሺዎች የሚቆጠሩ ሚሳይሎችን ጨምሮ በርካታ ተተኳሾችን ለእስራኤል መላኩን ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

እንደባለስልጣናቱ ከሆነ ጦርነቱ ከተጀመረት ከባለፈው ጥቅምት እስከ ቅርብ ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ አሜሪካ፣ ቢያንስ 14000 ኤምኬ-84 ባለ 2000 ፓውንድ ቦምቦችን፣ 6500 ባለ 500 ፓውንድ ቦምቦችን፣3000 ከአየር ወደ መሬት የሚተኮሱ ሚሳይሎችን፣ 1000 ከመሬት በታች ያለ ምሸግ የሚያፈርሱ ቦምቦችን፣ 2600 ከአየር ላይ የሚወረወሩ ቦምቦችን እና ሌሎች መሳሪያዎችን ሰጥታለች።

እኝህ ባለስልጣናት የጦር መሳሪያዎቹ ወደ እስራኤል የተላኩበትን ቀን በዝርዝር ባይጠቅሱም፣ አሜሪካ ለአጋሯ እስራኤል የምታደርገውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንድታቆም ብትጠየቅም አለመቀነሷን ያሳያል ተብሏል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
"የኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር የገባችውን ስምምነት ካቋረጠች የሆብዮ ወደብ እንድትጠቀም እፈቅዳለሁ" የሞቃዲሾ አስተዳደር

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት በቱርክ አስታራቂነት ሁለቱን ሀገራት በአንካራ የድርድር ጠረጴዛ ላይ መቀመጣቸው ተሰምቷል።

በኢትዮጵያ እና በሞቃዲሾ አስተዳደር መካከል በሚካሄደው ውይይት የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ ሲሆን የውይይቱ አጀንዳ የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት እና በቀጠናው ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ያካትታል ተብሏል።

ዛሬ በአንካራ እየተካሄደ ይገኛል በተባለው ዉይይት የሶማሊያ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ከሶማሌ ላንድ ጋር የገባችውን ስምምነት ካቋረጠች ኢትዮጵያ በ ጋልሙዱግ ግዛት የሚገኘውን የሆብዮ ወደብ እንድትጠቀም አቅደዋል ነዉ የተባለዉ።

በሁለቱም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አማካኝነት በጠረጴዛ የተቀመጡት ሀገራቱ ኢትዮጵያ ከሞቃዲሾ አስተዳደር ጋር ስምምነት ላይ ከደረሰች እና ወደ የሆብዮ ወደብ ካቀናች በቀጣናው ያላትን ተፅዕኖ የበለጠ እንደምታሳድግ ይጠበቃል።
Capital

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja