Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
86.8K subscribers
8.14K photos
399 videos
18 files
18.3K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 414 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 935 ሰዎች አገገሙ

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,901 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 414 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 935 ሰዎች ሲያገግሙ 9 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። 336 ሰዎች በጽኑ ታመዋል።
እስካሁን በአጠቃላይ 96,583 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 53,452 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,478 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የሦስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ በበይነ መረብ ተካሂዷል

የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ባደረጉት ስብሰባ በድርድሩ ቀጣይ አካሄድና የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሶስቱ ሀገራት ሁለት ሁለት ባለሞያዎችን በመሰየም በድርድሩ አካሄድ እና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት የሰየማቸው ባለሞያዎች ተጨማሪ ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ ለውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሪፖርት እንዲያቀርቡ መግባባት ላይ ተደርሷል።

የባለሙያዎች ስብሰባ ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን የደረሰበትን ጉዳይም በጥቅምት 24 ለሚካሄደው የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሦስትዮሽ ድርድር ያቀርባል እንደ ሚኒስቴሩ መግለጫ።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
በምእራብ ወለጋ ዞን ኦነግ ሸኔ የሽብር ጥቃት መፈጸሙን ክልሉ አስታወቀ

ትናንት በምእራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በፈፀመው የሽብር ጥቃት ሰላማዊ ዜጎችን በጭካኔ ህይወታቸውን ማጥፋቱን የኦሮሚያ መንግስት ኮሙኒኬሽን ገልጿል፡፡
የክልሉ መንግስት በኦነግ ሸኔ ላይ የሚወስደውን እርምጃ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/the-oromiya-regional-state-announced-that-a-terrorist-attack-had-taken-place-in-the-west-welega-zone
በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት መፈጸሙን የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ

ፓርቲው ትላንት ምሽት በወረዳው በአማራው ላይ የቡድን ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
በዘለቄታዊ መፍትሄው ላይ እንደ አማራ ለመምከር በቅርቡ ሁሉን አሳታፊ የሆነ የሕዝብ መድረክ እንደሚዘጋጅም ገልጿል፡፡
https://am.al-ain.com/article/amhara-prosperity-party-says-racially-motivated-attack-took-place-in-guliso-woreda-west-welega-zone
የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ ራሳቸውን ለይተዋል

የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር ንክክ እንዳላቸው ከተለዩ በኋላ ራሳቸውን መለየታቸውን በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ ምንምእንኳን የቫይረሱ ምልክት ባይታይባቸውም በዓለም ጤና ድርጅት ፕሮቶኮል መሰረት ራሳቸውን ለይተው እንደሚቆዩና ከቤታቸው ሆነው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ቴሌግራም https://web.telegram.org/#/im?p=@alainamharic
ታንዛኒያ ምርጫን ተከትሎ የዋና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪን አሰረች

ተቃዋሚዎች ምርጫው መጠነ ሰፊ ማጭበርበር ታይቶበታል በማለት ምርጫው እንዲደገም፤ ፕሬዘዳንት ማጉፉሊ 84 በመቶ በማግኘት በድጋሚ ወደ ስልጣን ያመጣውን የምርጫ ውጤት ለመቃወም ጥሪ አቅርበዋል፡፡https://am.al-ain.com/article/tanzania-arrested-leader-of-main-opposition-leader
“የጸጥታ አካላት ጥቃቱ ወደተፈጸመበት አካባቢ ተሠማርተው እርምጃ እየወሰዱ ነው”-ጠ/ሚ ዐቢይ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በምእራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡
“ሁኔታው እንደ መሪም እንደ ዜጋም ልብ ይሰብራል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
https://am.al-ain.com/article/pm-abiy-ahmed-says-security-forces-are-deployed-in-the-area-where-the-attack-took-place
አሜሪካውያን ቀጣዩን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ነገ የመጨረሻ ድምጽ ይሰጣሉ

ከዋናው የድምጽ መስጫ ቀን በፊት እስካሁን 94 ሚሊዮን ሰዎች ድምጻቸውን መስጠታቸው ተገልጿል
የሁለቱ ተቀናቃኞች የመጨረሻ ቅስቀሳ እና የእስካሁኑ ሂደት ምን ይመስላል?👇
https://am.al-ain.com/article/americans-will-go-to-the-polls-tomorrow-to-elect-their-next-president
አልጀሪያ አዲስ ህገመንግስት አጸቀች

የአልጀሪያ ህገመንግስት ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘች ከፈረንጆቹ 1962 ወዲህ ለ8ኛ ጊዜ ተሻሽሏል፡፡ኃላፊው እንደገለጹት እንዲጸድቅ በአዎንታ ድምጽ የሰጡት 3.3 ሚሊዮን ወይም 66.8 በመቶ ናቸው ብለዋል፡፡https://am.al-ain.com/article/algeria-approves-new-constitution-in-referendum
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 359 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 953 ሰዎች አገገሙ

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,726 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 359 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 953 ሰዎች ሲያገግሙ 11 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። 353 ሰዎች በጽኑ ታመዋል።
እስካሁን በአጠቃላይ 96,942 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 54,405 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,489 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
በኦስትሪያ ቬና በሽብር ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ

ትናንት ምሽት በኦስትሪያ ዋና ከተማ ቬና 6 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት 3 ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ 15 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡
ጥቃቱ የተፈጸመው በእስላማዊው ጽንፈኛ ቡድን አይኤስ ደጋፊ እና በግብረአበሮቹ መሆኑን የኦስትሪያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ካርል ኔሃመር ተናግረዋል፡፡ በቴሌቪዥን በተላለፈው መግለጫቸው ህዝቡ በቤቱ እንዲቆይ አሳስበዋል፡፡
ጥቃቱን ከፈጸሙት ግለሰቦች አንዱ በፖሊስ የተገደለ ሲሆን ሌሎቹን ፖሊስ እያፈላለገ ነው፡፡
ኢሰመኮ የግድያውና የሰራዊቱ መውጣት ምክንያት እንዲታወቅ መንግስት ነጻ ምርመራ እንዲጀምር ጠየቀ

ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ በቦታው የነበረው የፌደራል ወታደሮች መውጣታቸውን ተከትሎ 60 አባላት ባሉት ቡድን ግድያ መፈጸሙን ከአካባቢው ምንጮች ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

ኢሰመኮ የፌደራልና የክልል መንግስታት በግድያው ላይ በአፋጣኝ ምርመራ እንዲጀምሩና፣ ለጥቃት ተጋላጭ መሆኑ ለረጅም ጊዜ ከሚታወቀው ቦታ ሰራዊቱ እንዲወጣ የተደረገበት የጀርባ ምክንያት እንዲታወቅና የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡https://am.al-ain.com/article/ehrc-demands-the-government-to-launch-investigation-into-killings-military-withdrawal
በአፍጋኒስታን መዲና በተፈጸመ የሽብር ጥቃት 22 ሰዎች ተገደሉ

ዩኤኢ በካቡል ዩኒቨርሲቲ ላይ ያነጣጠረውን ይህን ጥቃት አውግዛለች፡፡
አይኤስ ከአፍጋኒስታን በተጨማሪ በኦስትሪያም ጥቃት ፈጽሟል፡፡
https://am.al-ain.com/article/a-terrorist-attack-in-the-afghan-capital-has-killed-at-least-22-people
የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ባለሥልጣን የኢትጵያ ጉዳይ እግጅ አሳሳቢ ነው አሉ

በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት በትንሹ 54 ሰዎች መገደላቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጿል፡፡
የአፍሪካ ሕብረትም ጥቃቱን አውግዟል፡፡
https://am.al-ain.com/article/euhigh-representative-vice-president-josep-borrell-released-statement-on-the-latest-dev-t-in-ethiopia
መንግስት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች አነስተኛ ቁጥር ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ልዩ ጥበቃ እንዲያደርግ ተጠየቀ

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ የሕገ መንግስት ማሻሻያ መደረግ አለበት ብሏል፡፡
በንጹኃን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በመዋቅራዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት ጉባዔው ገልጿል፡፡
https://am.al-ain.com/article/the-government-is-asked-to-provide-special-protection-to-a-small-number-of-communities-in-different-parts-of-ethiopia
“የሰማሁት ዜና ልቤን ሰብሮታል…” ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በንጹኃን ብሔር ተኮር ጥቃት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡
ፕሬዝዳንቷ “ልናሰምረው እና ልናከብረው የሚገባን ቀይ መስመር ተጥሷል” ብለዋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/the-news-i-heard-broke-my-heart-president-sahilework-zewde