Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
97.8K subscribers
8.91K photos
405 videos
18 files
21.3K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
የምግብ ብክነት የከፋባቸው የአፍሪካ ሀገራት

እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ሪፖርት ከሆነ በዓለማችን በየዓመቱ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ምግብ ሳይበላ ይጣላል።

ወደ አፍሪካ ስንመጣ ደግሞ የምግብ ዕጥረት ያለባቸው ሀገራት መገኛ የሆነው ምስራቅ አፍሪካ ብክነቱ ከፍተኛ የሆኑ ሀገራት ይገኙበታል።

ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሲሸልስ እና ሩዋንዳ የምግብ ብክነት ከፍየኛ ከሆነባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4ixaYZw
የቡልጋሪያው እግርኳስ ክለብ ለቀድሞ ኮከቡ በስህተት የህሊና ጸሎት አድርጓል

ስታዲየም ውስጥ የህሊና ጸሎት የተደረገለት ተጫዋች ሞቱን በቴሌቪዥን ከተመለከተችው ሚስቱ ሰምቷል።

https://bit.ly/4i5SoYF
አቃቢ ህግ በእነ ዮሀንስ ቧያለው መዝገብ ስር በተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ላይ ምስክሮችን ማሰማት ጀመረ

በዚህ መዝገብ ስር 52 ተጠርጣሪዎች የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዋል። አቃቢ ህግ ተከሳሾቹ ባስተላለፉት ትዕዛዝ ምክንያት የደረሱ ጉዳቶችን ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች አቅርቧል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4iemZmZ
የሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ የአሜሪካ ጉብኝት በሀገራቱ መካከል እያደገ ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያጠናር ነው ተባለ

የአረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የአቡዳቢ ም/አስተዳዳሪ ሼክ ታኖን ቢን ዛይድ በአሜሪካ ጉብኝ እያደረጉ ነው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4iCHn1b
ፑቲን እና ትራምፕ በተጠባቂው የስልክ ውይይታቸው በምን ጉዳዮች ላይ ተነጋገሩ?

ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ፕሬዝዳንት ፑቲን 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ የፈጀ የስልክ ውይይት አድርገዋል። የዩክሬን ጦርትና የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማደስ የውይይታው አካል ነበር።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4kYMY3n
እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው ጥቃት የተገደሉ የሃማስ አመራሮች እነማን ናቸው?

እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት በርከት ያሉ የሃማስ አመራሮች መገደለቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል።

ከእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር እና ከፊልስጤም ውስጥ የሚገኙ ምንጮች እንዳረጋገጡት ከሆነ በሌሊቱ ጥቃት 4 ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በርከት ያሉ መካለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የሃማስ አመራሮች ተገድለዋል።

እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው መጠነሰፊ የአየር ጥቃት ከ400 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hhsXCe
ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ ከአሜሪካ የግምጃ ቤት ኃላፊ ጋር ተወያዩ

ስለ ቀጣይ ጊዜ ኢንቨስምት፣ ቴክኖሎጂ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በኢነርጂና በንግድ አጋርነት ላይ መክረዋል። የአረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የአቡዳቢ ም/አስተዳዳሪ ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ በአሜሪካ ጉብኝ እያደረጉ ነው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4iclcin
አረብ ኢምሬትስ እስራኤል በጋዝ የፈጸመችውን የአየር ድብደባ በጽኑ አወገዘች

የአረብ ኤሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ባለፈው ጥር ወር የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ ተጨማሪ ንጹሐን ጉዳትን በማስከተል በጋዛ ሰርጥ የሚታየውን ሰብዓዊ አደጋ የሚያባብስ ነው በማለት ማስጠንቀቁን የኤሚሬትስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁኔታውን ለማርገብ አስቸኳይ እርምጃዎችን እንዲወስድ እና አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እና ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ ሁሉንም ጥረቶችን እንዲያደርጉ ጠይቋል።

ከአረብ ኢምሬትስ በተጨማሪም ግብጽ፣ ቱርክ፣ ቻይና እና ሩሲያ ጨምሮ በርካታ ሀገራት በጋዛ የተፈጸመውን ጥቃት አውግዘዋል።

ጥቃቱን እነማን አወገዙ? በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3XXqN3K
ኢራን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ማባረሯን አስታወቀች

የአሜሪካ ጦር ንብረት ነው የተባለው ሰው አልባ አውሮፕላን በቴህራን አቅራቢያ ቅኝት በማድረግ ላይ ነበር ተብሏል።

የኢራኑ ኤፍ-14 የተሰኘው የውጊያ አውሮፕላን የአሜሪካ ሰው አልባ የስለላ አውሮፕላንን እንዳባረረ ተገልጿል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት ጽሁፍ " በየመን ያለው ሁቲ ቡድን ለሚያደርገው እያንዳንዱ ጥቃት ሀላፊነቱን የምትወስደው ኢራን ናት" ብለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4kxRVQG
አቃቢ ህግ በእነ ዮሀንስ ቧያለው መዝገብ ስር በተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ላይ ምስክሮችን ማሰማት ጀመረ

የፍትህ ሚኒስቴር በእነ ዮሀንስ ቧያለው መዝገብ ባሉ 52 ተጠርጣሪዎች ላይ የፖለቲካ ርዕዮትን በሀይል ለማስፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፣ በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ እንዲሁም የሽብር ወንጀሎችን ለመከላከል የወጣውን ህግ ጥሰዋል በሚል ከአንድ ዓመት በፊት ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

ከ52ቱ ተከሳሾች መካከል 16ቱ ተከሳሾች አዲስ አበባ ልደታ በሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህገ መንግስት እና ሽብር ወንጀሎች ችሎት የቀረቡ ሲሆን የአቃቢ ህግ ምስክሮች በተከሳሾች ላይ የምስክርነት ቃላቸውን እንደሰጡ የተከሳሾች ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአል ዐይን ተናግረዋል።

አቃቢ ህግ ተከሳሾቹ ባስተላለፉት ትዕዛዝ ምክንያት የደረሱ ጉዳቶችን ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች አቅርቧል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4iemZmZ
ፑቲን እና ትራምፕ በተጠባቂው የስልክ ውይይታቸው በምን ጉዳዮች ላይ ተነጋገሩ?

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚ ፑቲን በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ተነግሯል።

ሁለቱ መሪዎች 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በፈጀ የስልክ ውይይታቸው የዩክሬን ጦርትና የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማደስ የውይይታቸው አካል ነበር።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4kYMY3n
“ከአረብ ኢምሬትስ ጋር ያለን ግንኙነት በታሪክ ጠንካራ ነው”- ትራምፕ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድን በዋይት ኃውስ ተቀብለው አነጋረዋል። የአረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የአቡዳቢ ም/አስተዳዳሪ ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ በአሜሪካ ጉብኝ እያደረጉ ነው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ- https://bit.ly/42dav9o
⭕️ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድን በዋይት ኃውስ ተቀብለው አነጋገሩ

📌ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙትን የአረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የአቡዳቢ ምክትል አስተዳዳሪ ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ አል ናህያንን በዋይት ኃውስ ተቀብለው አነጋግረዋል።

📌በዋይት ኃውስ በነበራቸው ቆይታም በሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት፣ በፀጥታ፣ኢኮኖሚያዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ትብብርን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ውይይት አድርገዋል።

📌ፕሬዝዳንት ትራምፕ "የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአለም ላይ ሰላም እና ደህንነትን ለማስፈን በጋራ የሚሰሩ የሁልጊዜ አጋር ናቸው" ሲሉም ገልጸዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ- https://bit.ly/42dav9o
ኤርትራ በትግራይ ክልልም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እንደማትገባ ገለጸች

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ “ጊዜ ያለፈበት” ሲሉ ተችትዋል። አዲስ አበባ አስመራን ለውስጥ ችግሮቿ ተጠያቂ ከማድረግ እንድትቆጠብም አሳስበዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ- https://bit.ly/4iCgfit
ለ22 ዓመት ሴት መስሎ በሴቶች ገዳም ውስጥ የኖረው ሰው

የሚረዳው አጥቶ ወደ ገዳም የገባው ሰው በመጨረሻም ጾታው ሲታወቅበት ከገዳም መውጣቱ ተገልጿል

በገዳሙ ውስጥ ከሴቶች ጋር በሚኖርበት ወቅት ወንድነቱ እንዳይታወቅበት ከባድ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3E1XW7D
ቱርክ የፕሬዝደንት ኢርዶጋንን ዋና ተቀናቃኝ አሰረች

የኢስታንቡል ገዥ ቢሮ እስሩን ተከትሎ በከተማዋ ሁሉም ስብሰባዎች እና ተቃውሞዎች እንዳይካሄዱ ለአራት ቀናት የሚቆይ እግድ አስተላልፏል።

https://bit.ly/3FF7NRt