Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
91.4K subscribers
8.28K photos
401 videos
18 files
18.8K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
በኢትዮጵያ የዩኤኢ ኤምባሲና የዱባይ የንግድ ምክር ቤት ስራ ፈጣሪዎችን እንደሚያበረታቱ ገለጹ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኤምባሲ እና የዱባይ የንግድ ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ጽህፈት ቤት በኢትዮጵያ ሴት ስራ ፈጣሪዎችን በማበረታታት በኩል ግንባር ቀዳሚ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ የሴቶች ኢኮኖሚ አቅምን ለማሳደግ የተቋቋመው ‘ሴንተር ፎር አክስለሬትድ ዉሜን ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት’ እና በዱባይ የሚገኘው ‘ኢቮልቪን ዉሜን’ የትብብር መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
በስምምነቱም ሴት ስራ ፈጣሪዎች አቅማቸው እንዲጎለብት የሚያደርጉ ስልጠናዎች እና ሌሎች የቁሳቁስ ድጋፎች እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኤምባሲ ስምምነቱን የተፈራረሙት ሁለቱ ድርጅቶች ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ድጋፎችን እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በኢትዮጵያ ለታዳጊ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የምታደርገው ድጋፍ በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶችን ለማብቃት የምትሰራው ስራ አካል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የዩኤኢ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጠ/ሚኒስትር የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ

በሶስት ዙር በተካሔዱ ክሊኒካዊ ሙከራዎች ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከ ሼክ መሐመድ ቢን ራሺድ በተጨማሪ ሌሎች የዩኤኢ ከፍተኛ ባለሥልጣናትም ክትባቱን ወስደዋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/sheikh-mohammed-bin-rashid-al-maktoum-receives-covid-19-vaccine
“ጥቃት ፈጻሚ የተባሉት ከታወቁ ፣ ለምን የማያዳግም እርምጃ መውሰድ አልተቻለም?“ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት

“ከ2 ዓመት በፊት በለውጥ ስሜት ስራ ስንጀምር የነበረን ተስፋ አሁን የለም“ ብለዋል የም/ቤት አባላቱ፡፡
በም/ኦሮሚያ በተፈጸመው ግድያ ጠ/ሚ ዐቢይ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/the-ethiopian-house-of-peoples-representatives-ask-the-pm-for-explanation-about-the-killing-in-oromia-region
ሰበር ዜና
ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ገለጹ
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ የሚከተለው ነው
ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል። ይህ ሠራዊት ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ነው። በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው። ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታትና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል።
መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንዳይጎዳ በማሰብ፣ ጦርነት እንዳይፈጠር የትእግሥቱ ጫፍ ድረስ ታግሷል። ጦርነት የሚቀረው ግን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም።
የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል። ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል፣ በየአካባቢው ሊከሠቱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በንቃት እንዲቃኝና ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀርባለሁ።
“የመከላከያ ሠራዊት በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል” ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን የገለጹት ጠ/ሚ ዐቢይ ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል ብለዋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/pm-abiy-ahmed-defense-forces-is-commanded-to-take-measures-to-defend-the-country
በአዲስ አበባ ‘አዋሬ ገበያ’ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ አዋሬ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሰክሪታሪያት አስታወቀ።
ከሌሊቱ 10 ሰአት አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ በአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች፣ በፖሊሶች እና የአካባቢው ወጣቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ተክሌ ተናግረዋል።
የእሳት አደጋውን መንስኤ እና ያደረሰውን ጉዳት በፖሊስ እየተጣራ መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሰክሪታሪያት ገልጿል።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
ከምሽቱ 4 እስከ 5 ሰዓት በአማራ ክልል ላይ ከሕወሐት ጥቃት መፈጸሙን የአማራ ክልል አስታወቀ

የአማራ ክልል ር/መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ በአማራ ክልል በሶሮቃ እና በቃራቀር አካባቢ የተሰነዘረው ጥቃት በልዩ ኃይል ተመክቷል ብለዋል፡፡
የትግራይ ክልል ባወጣው መግለጫ የትግራይ አየር ክልል መዘጋቱን እና የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ መከልከሉ ገልጿል፡፡
https://am.al-ain.com/article/the-amhara-regional-state-announced-that-tplf-carried-out-attack-on-the-amhara-region
በአሜሪካ ምርጫ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ጆ ባይደን አሸናፊነታቸውን ለማረጋገጥ የዋና ዋና ግዛቶችን ውጤት በመጠበቅ ላይ ናቸው፡፡ እስካሁን ተቆጥሮ በተጠናቀቀው ድምጽ ትራምፕ 213 ባይደን ደግሞ 224 ወካይ ድምጽ ማግኘታቸውን ታይም አግቧል፡፡

ይሁንና አሸናፊውን ለመለየት ከፍተኛ ድምጽ ያላቸው እና የምርጫውን ውጤት የሚወስኑ ግዛቶች የመጨረሻ ሪፖርት ይጠበቃል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
ትዊተር ምርጫውን የሚያሳስት ሊሆን ይችላል ያለውን የትራምፕ ትዊት አገደ

#USElections2020 ትራምፕ “እኛ አያሸነፍን ነው፤ እነሱ ግን ምርጫውን ለመስረቅ እየሞከሩ ነው…”ብለው ነበር የጻፉት፡፡እስካሁን ባለው ውጤት ጆ ባይደን በ225 ወካይ ድምጽ እየመሩ ነው፡፡https://am.al-ain.com/article/twitter-restricts-trumps-tweet-alleging-it-mislead-election
ምርጫውን ካላሸነፉ ለክስ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚሔዱ ትራምፕ ተናገሩ

የምርጫው ሙሉ ውጤት ይፋ ከመደረጉ በፊት ትራምፕና ባይደን ማሸነፋቸውን እየገለጹ ነው፡፡
እስካሁን በተቆጠሩ ድምጾች ባይደን በመምራት ላይ ሲሆኑ ትራምፕ ድምጽ እየተሰረቀ ነው ብለዋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/trump-said-he-would-go-to-the-supreme-court-if-he-did-not-win-the-election
የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ

የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ህገመንግስትንና የህዝብ ሰላም አደጋ ላይ የሚጥልና የፌደራል መንግስት የተሰጠውን ኃላፊነት የሚያደናቅፍ ሁኔታ በመከሰቱ ምክንያት መታወጁ ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል በሚገኘው መከላከያ ሃይል ላይ ህወሓት ጥቃት መሰንዘሩንና መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ ትናንት ሌሊት አስታውቀው ነበር፡፡
የትግራይ ክልል በበኩሉ ዘሬ ጠዋት ባወጣው መግለጫ በክልሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥሏል፡፡
ለኋይት ሀውስ የሚደረገው ፉክክር ቀጥሏል

የምርጫውን አሸናፊ ለማወቅ የአራት ግዛቶች ውጤት ይጠበቃል፡፡
አሸናፊው ሳይታወቅ ቀናት ሊቆጠሩ ይችላል ተብሏል፡፡ ለምን?
https://am.al-ain.com/article/the-race-for-the-white-house-continues
#Election2020 #አሜሪካምርጫ2020
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በደቡብ ሞሮኮ ቆንስላ በመክፈት የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር ሆነች
#UAE_Morocco #ዩኤኢ_ሞሮኮ
መንግስት “ሉአላዊነት የሚገዳደር” ሁኔታ በመኖሩ አስቸኳይ አዋጅ ማወጁን ገልጿል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል በሚገኘው መከላከያ ሃይል ላይ ህወሓት ጥቃት መሰንዘሩንና መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ ትናንት ሌሊት አስታውቀው ነበር፡፡

የትግራይ ክልል በበኩሉ ዛሬ ጠዋት ባወጣው መግለጫ በክልሉ የሚደረግ በረራ ማገዱንና የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን አስታውቋል፡፡https://am.al-ain.com/article/federal-government-declares-a-six-month-state-of-emergency-for-tigray-region