በወረባቦ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ሰብላቸውን ላወደመባቸው አርሶአደሮች ድጋፍ ማቅረብ ተጀመረ
በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ የበረሃ አንበጣ ሰብላቸውን ላወደመባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አስቸኳይ የዕለት ቀለብ ድጋፍ ማቅረብ መጀመሩን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን አስታውቋል፡፡
የፌዴራል መንግስት ያቀረበው ስንዴና የምግብ ዘይት በቀጥታ ለተጎጂዎች እየተሰራጨ እንደሚገኝም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ገልጿል፡፡
በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ መንጋ በወረባቦ ወረዳ በ13 ቀበሌዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡
በወረዳው 9ሺህ 682 ሄክታር ሰብል ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡ በተጨማሪም 2ሺህ 267 ሄክታር የግጦሽ መሬትና 22 ሺህ 289 ሄክታር ደን እና ቁጥቋጦ ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡
በዚህም ከ10 ሺህ በላይ የቤተሰብ ሀላፊዎች ተጎጂ ሲሆኑ በአጠቃላይ ከ61 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ለችግር ተጋልጠዋል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው

ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በአፋር ተገደሉ
የትምህርት ሚኒስቴር ሁለት ባልደረቦቹ በአፋር ክልል ለሥራ በሄዱበት ወቅት ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታወቀ፡፡ አቶ ሙላት ጸጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት ድንገት ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የትምህርት ሚኒስቴር ሁለት ባልደረቦቹ በአፋር ክልል ለሥራ በሄዱበት ወቅት ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታወቀ፡፡ አቶ ሙላት ጸጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት ድንገት ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
በፈረንሳይ ኒስ ከተማ ሶስት ሰዎች በጩቤ ተወግተው ተገደሉ
በፈረንሳይ ኒስ ከተማ ሶስት ሰዎች ቤተክርስቲያን ውስጥ በጩቤ ተወግተው መገደላቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የከተማዋ ከንቲባ ክርስቲያን ኤስትሮሲ በመሀል ከተማው በሚገኘው ኖትሬ ዳም ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመው ጥቃቱ የሽብር ድርጊት ስለመሆኑ ማስረጃዎች ያመለክታሉ ብለዋል፡፡
ተጠርጣሪው ጥቃቱን ከፈጸመ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ የፈረንሳይ ብሄራዊ የፀረ-ሽብር አቃቤ ህጎች የግድያ ምርመራ ከፍተዋል፡፡ ተጨማሪ ሰባት ሰዎችም መጎዳታቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

በሁለት ቀናት 6 ኪ.ግ ያህል ኮኬይን በቦሌ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ጋር በመተባበር በዛሬው እለት ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ዱባይ ሊጓዝ የነበረ 3.35 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገለፀ፡፡
የፌደራል ፖለስ በፌስቡክ ገጹ እንደገለጸው ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ ፣ የታይላንድ ዜግነት ያላት ተጠርጣሪ ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ ለመጓዝ ሻንጣዋን ስታስፈትሽ ነው አደገኛ ዕፁ እና ግለሰቧ በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡
ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ አራት ሰዓት ደግሞ ከአዲስ አበባ ወደ ታይላንድ ባንኮክ ሊጓዝ የነበረ 2.6 ኪ.ግ የሚመዝን ኮኬይን የታይላንድ ዜግነት ካላት ተጠርጣሪ ጋር እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል፡፡ በድምሩ በሁለቱ ቀናት 5.95 ኪ.ግ. ኮኬይን ተይዟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሶማሌ ክልልን እና ድሬዳዋ ከተማን ጎብኝተዋል
በዛሬው ዕለት በሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን የጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በሶስት ፕሮጄክቶች ተከፋፍሎ የሚገነባውን የጎዴ ቀላፎ - ፈርፈር የመንገድ ፕሮጀክት ጨምሮ ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው እና ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተያዘላቸውን የመንገድ ፕሮጄክቶች ግንባታ አስጀምረዋል፡፡ ከጅግጅጋ - ገለልሽ የተገነባው 56 ኪ.ሜ መንገድም ተመርቆ ለአገልግሎት ተከፍቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ 2,000 ሄክታር የቆላ ስንዴ ሰብል የለማበትን የጎዴ የመስኖ ግድብን እና በሶማሌ ክልል አውባሬ ወረዳ የበርሃ አንበጣ ያደረሰውን ጉዳት እንዲሁም በወረዳው በ100,000 ሄ. መሬት ላይ የሚለማውን የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡
ከሶማሌ መልስ ወደ ድሬዳዋ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው በ150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባውን የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ መርቀው ከፍተዋል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 488 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 960 ሰዎች አገገሙ
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5866 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 488 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 960 ሰዎች ሲያገግሙ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
እስካሁን በአጠቃላይ 95,789 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 51713 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,464 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ቴሌግራም https://web.telegram.org/#/im?p=@alainamharic
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5866 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 488 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 960 ሰዎች ሲያገግሙ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
እስካሁን በአጠቃላይ 95,789 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 51713 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,464 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ቴሌግራም https://web.telegram.org/#/im?p=@alainamharic
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
Telegram Web
Access your Telegram messages from any mobile or desktop device.
በቱርክ እና ግሪክ የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው
መነሻውን በኤጂያን ባህር የቱርክ እና የግሪክ አዋሳኝ አካባቢ በማድረግ በተለይ በቱርክ ኢዝሚር ከተማ አርብ ዕለት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እስከ ትናንት ምሽት የሟቾች ቁጥር 39 መድረሱን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ ከሟቾቹ 37ቱ በቱርክ ሁለቱ ደግሞ በግሪክ የተከሰተ መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡
ቢያንስ በቱርክ 885 ሰዎች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የነፍስ አድን ሰራተኞች ከ 100 በላይ ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስጥ በህይወት ማውጣታቸውን ዘገባው ያመለክታል፡፡
በኢዝሚር ከተማ 20 ህንጻዎች መፈራረሳቸውንም ነው ሲኤንኤን በዘገባው ያመለከተው፡፡

የሱዳኑ አልቡርሃን አዲስ አበባ ገቡ
ከሰሞኑ በካይሮ ጉብንት አድርገው የነበሩት የሱዳን የሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ አል ቡርሃን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
አል ቡርሃን በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽና በተለያዩ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
ፎቶ ፋይል

በቱርክ የ 70 ዓመት አዛውንት ከ34 ሰዓታት በኋላ ከፍርስራሽ ውስጥ ወጡ
አርብ ዕለት የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በቱርክ ኢዝሚር ከተማ እየተካሔደ ባለው የነፍስ አድን ስራ የ 70 ዓመት አዛውንት ከ34 ሰዓታት በኋላ ከፍርስራሽው ውስጥ መውጣታቸውን ዘ ናሺናል ዘግቧል፡፡
ቱርክን እና ግሪክን በመታው የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን በትንሹ 60 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ከ900 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከሟቾቹ 58ቱ ቱርካውያን ናቸው፡፡ የነፍስ አድን ስራው አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከ100 በላይ ሰዎችን ከህንጻ ፍርስራሽ ውስጥ በህይወት ማውጣት ተችሏል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
አርብ ዕለት የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በቱርክ ኢዝሚር ከተማ እየተካሔደ ባለው የነፍስ አድን ስራ የ 70 ዓመት አዛውንት ከ34 ሰዓታት በኋላ ከፍርስራሽው ውስጥ መውጣታቸውን ዘ ናሺናል ዘግቧል፡፡
ቱርክን እና ግሪክን በመታው የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን በትንሹ 60 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ከ900 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከሟቾቹ 58ቱ ቱርካውያን ናቸው፡፡ የነፍስ አድን ስራው አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከ100 በላይ ሰዎችን ከህንጻ ፍርስራሽ ውስጥ በህይወት ማውጣት ተችሏል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የሦስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ በበይነ መረብ ተካሂዷል
የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ባደረጉት ስብሰባ በድርድሩ ቀጣይ አካሄድና የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገልጿል።
ሶስቱ ሀገራት ሁለት ሁለት ባለሞያዎችን በመሰየም በድርድሩ አካሄድ እና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት የሰየማቸው ባለሞያዎች ተጨማሪ ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ ለውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሪፖርት እንዲያቀርቡ መግባባት ላይ ተደርሷል።
የባለሙያዎች ስብሰባ ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን የደረሰበትን ጉዳይም በጥቅምት 24 ለሚካሄደው የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሦስትዮሽ ድርድር ያቀርባል እንደ ሚኒስቴሩ መግለጫ።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 359 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 953 ሰዎች አገገሙ
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,726 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 359 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 953 ሰዎች ሲያገግሙ 11 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። 353 ሰዎች በጽኑ ታመዋል።
እስካሁን በአጠቃላይ 96,942 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 54,405 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,489 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,726 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 359 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 953 ሰዎች ሲያገግሙ 11 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። 353 ሰዎች በጽኑ ታመዋል።
እስካሁን በአጠቃላይ 96,942 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 54,405 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,489 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
በኢትዮጵያ የዩኤኢ ኤምባሲና የዱባይ የንግድ ምክር ቤት ስራ ፈጣሪዎችን እንደሚያበረታቱ ገለጹ
በአዲስ አበባ የሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኤምባሲ እና የዱባይ የንግድ ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ጽህፈት ቤት በኢትዮጵያ ሴት ስራ ፈጣሪዎችን በማበረታታት በኩል ግንባር ቀዳሚ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ የሴቶች ኢኮኖሚ አቅምን ለማሳደግ የተቋቋመው ‘ሴንተር ፎር አክስለሬትድ ዉሜን ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት’ እና በዱባይ የሚገኘው ‘ኢቮልቪን ዉሜን’ የትብብር መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
በስምምነቱም ሴት ስራ ፈጣሪዎች አቅማቸው እንዲጎለብት የሚያደርጉ ስልጠናዎች እና ሌሎች የቁሳቁስ ድጋፎች እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኤምባሲ ስምምነቱን የተፈራረሙት ሁለቱ ድርጅቶች ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ድጋፎችን እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በኢትዮጵያ ለታዳጊ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የምታደርገው ድጋፍ በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶችን ለማብቃት የምትሰራው ስራ አካል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ‘አዋሬ ገበያ’ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ
በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ አዋሬ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሰክሪታሪያት አስታወቀ።
ከሌሊቱ 10 ሰአት አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ በአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች፣ በፖሊሶች እና የአካባቢው ወጣቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ተክሌ ተናግረዋል።
የእሳት አደጋውን መንስኤ እና ያደረሰውን ጉዳት በፖሊስ እየተጣራ መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሰክሪታሪያት ገልጿል።

በአሜሪካ ምርጫ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ጆ ባይደን አሸናፊነታቸውን ለማረጋገጥ የዋና ዋና ግዛቶችን ውጤት በመጠበቅ ላይ ናቸው፡፡ እስካሁን ተቆጥሮ በተጠናቀቀው ድምጽ ትራምፕ 213 ባይደን ደግሞ 224 ወካይ ድምጽ ማግኘታቸውን ታይም አግቧል፡፡
ይሁንና አሸናፊውን ለመለየት ከፍተኛ ድምጽ ያላቸው እና የምርጫውን ውጤት የሚወስኑ ግዛቶች የመጨረሻ ሪፖርት ይጠበቃል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
ይሁንና አሸናፊውን ለመለየት ከፍተኛ ድምጽ ያላቸው እና የምርጫውን ውጤት የሚወስኑ ግዛቶች የመጨረሻ ሪፖርት ይጠበቃል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
"ዛሬ በነበረው ኦፐሬሽን በሁሉም ግንባር የጠላትን ፍላጎት ያኮላሸ ስራ ተሰርቷል"-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ምሽት ለኢቲቪ በሰጡት መግለጫ "በዛሬው ዕለት በነበረው ኦፐሬሽን በሁሉም ግንባር የጠላትን ፍላጎት ያኮላሸ ስራ ተሰርቷል" ብለዋል።
መንግሥት ተገዶ ወደጦርነት ገብቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ የነበረው የሕወሓት ትንኮሳ ሁሉ ከሽፏል ሲሉ ተናግረዋል። መከላከያ ሰራዊት ትንኮሳውን እስከመጨረሻው እንዲያከሽፍ ጥሪ ያቀረቡም ሲሆን በቀጣይ ቀናት ስለሚኖሩ ኦፐሬሽኖች እንደአስፈላጊነቱ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ምሽት ለኢቲቪ በሰጡት መግለጫ "በዛሬው ዕለት በነበረው ኦፐሬሽን በሁሉም ግንባር የጠላትን ፍላጎት ያኮላሸ ስራ ተሰርቷል" ብለዋል።
መንግሥት ተገዶ ወደጦርነት ገብቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ የነበረው የሕወሓት ትንኮሳ ሁሉ ከሽፏል ሲሉ ተናግረዋል። መከላከያ ሰራዊት ትንኮሳውን እስከመጨረሻው እንዲያከሽፍ ጥሪ ያቀረቡም ሲሆን በቀጣይ ቀናት ስለሚኖሩ ኦፐሬሽኖች እንደአስፈላጊነቱ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
አሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ከኢራቅ እና አፍጋኒስታን ልታስወጣ ነው
እስከ መጪው ወርሃ ጥር የመጀመሪያ ሳምንት ድረስ ሃገራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ከኢራቅና አፍጋኒስታን እንደምታስወጣ የአሜሪካ ተጠባባቂ የመከላከያ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ሚለር ተናገሩ፡፡
ከነጩ ቤተ መንግስት ሊሰናበቱ የጥቂት ወራት እድሜ የቀራቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሶማሊያ የተሰማራ ጦራቸውን ሙሉ ለሙሉ ሊያስወጡ እንደሚችሉም ተነግሯል፡፡
በአሁኑ ወቅት በኢራቅ 3 ሺ፣ በአፍጋኒስታን 4 ሺ 500 ገደማ የአሜሪካ ወታደሮች ይገኛሉ፡፡
አሜሪካ ከ2001ዱ የአል ቃይዳ ጥቃት በኋላ አክራሪዎችን ለመዋጋት የያዘችውን ዐቅድ ማሳካቷንም ነው ተጠባባቂ መከላከያ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡
ዘገባው የሲጂቲኤን ነው
#AlAinAmharic

በዚያድ ባሬ የስልጣን ዘመን የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዑመር ቃሊብ አረፉ
በዚያድ ባሬ የፕሬዝዳንትነት ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሶማሊያን ሲያገለግሉ የነበሩት ዑመር አርቴ ቃሊብ በ89 ዓመታቸው አረፉ፡፡
እ.ኤ.አ ከ1991 እስከ 1993 ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ቃሊብ በሶማሊ ላንድ ሃርጌሳ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ነው ያረፉት፡፡
ብዘዎች በጥሩ ዲፕሎማትነታቸው ያውቋቸዋል የሚለው የጎብጆግ ኒውስ ዘገባ ቃሊብ በ1972ቱ ጦርነት የኡጋንዳ-ታንዛኒያን ከማሸማገል ባለፈ ሃገራቸው አረብ ሊግን በአባልነት እንድትቀላቀል ለማድረግ የሚያስችል ብርቱ ጥረት ማድረጋቸውን ይጠቁማል፡፡
በዚህ ጥረታቸውም ሃገራቸውን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት እስከማገልገል ደርሰው ነበር፡፡
ቃሊብ የዚያድ ባሬ መንግስት በወቅቱ በኢትዮጵያ ሶማሌ ጎሳዎች ዘንድ ተቀስቅሶ የነበረውን አመጽ ለመደገፍ ያደርግ የነበረውን ጥረት ይቃወሙ እንደነበርና በዚህም ለእስር እስከመዳረግ እንደደረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
#Somalia