Daily Wisdom ደይሊ ዊዝደም
349 subscribers
83 photos
6 videos
2 files
93 links
በጊዜውም አለጊዜውም ቃሉን ስበክ።
#ትምህርት
#ስብከት
#ታሪክ
#መፅሐፍት
#ይከታተሉን
አጋር @ws_youth
Download Telegram
Pastor Bini Hailu Ruth:
#የዕለቱ_መልዕክት
(ዘውትር ማለዳ ጠዋት 2:00 መልካም ንባብ)
      👇 👇👇
#ብርሃናችን_ያዙ!
    ******
"እነዚህ ትዕዛዞች መብራት ናቸውና ፤ ይህችም ትምህርት ብርሃን ፣ የተግሳፅ ዕርምትም የሕይወት መንገድ ናት።" ምሳ 6:23 (አ.መ.ት)
      *****
የተወደዳችሁ ቅዱሳን ቤተሰቦቼ በያላችሁበት ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ። የተትረፈረፈ የእግዚአብሔር ፍቅር እና ሰላም በውስጣችሁ እንደማያቋርጥ ወንዝ ይፍሰስላችሁ። ሁላችሁንም በክርስቶስ ፍቅር እወዳችኋለሁ መልካም ቆይታ!
     🕥*****
                መግቢያ
የአዲሳ'ባ መንገዶች በምሽት ድምቅ የማለት ምክንያታቸው ጨለማቸውን የሚገልፅላቸው ታላላቅ ፖዉዛዎች ስለተገጠመላቸው ነው። ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጲያ ስትሄዱ ደግሞ ምሽት ላይ ድቅድቅ ከሚባል የጨለማ ግድግዳ ጋር እየተጋጫችሁ የምትሄዱ ነው የሚመስለው። እኔ የምኖረው እዚህች ፋሪ የተባለ ሰፈር ላይ ነው። እና ትንሽ የውስጥ መንገድ አላት እና አንድ ቀን ቤተክርስቲያን አምሽቼ ሰፈር ስደርስ አከባቢው በከባድ ጨለማ ተመቷል። አይንን በእሾህ የሚያስወጋ ጨለማ ነው። ትንሽ ይረብሻል። ግን የማውቀውና የለመድኩት መንገድ ስለሆነ ድፈረት እና እርምጃዬ ተጣጣሙልኝ። ራመድ ራመድ ...የሞባይሌን መብራት ማብራት ስጋት ራመድ ራመድ...!
አይዟችሁ ቤቴ ገብቻለሁ።
ይህቺ አለም እና ሲስተሟ ከዚህ የባሰች ጨለማነች ድፍረት ኖሯችሁ የማታሸንፋት ጨለማ ያለባት ነች። ይሄን ጨለማ መግፈፍ የሚችለው ድፍረታችን እና ብርሃናችን መሆን የሚችለው ቃሉና ቃሉ ብቻ ነው። ቃሉ ውስጥ ትዕዛዛቱ አሉ።
#የእኛ ብርሃን ምንድን ነው ?
1. እውነት መንገድ የሆነው ክርስቶስ ነው።
“ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።”  ዮሐንስ 1፥9
ይሄን ሐሳብ የማብራራት አይደለም አላማዬ ግን ይሄ ብርሃን ወደ ህይወታችን ከገባ በኋላ የእኛ ህይወት ብርሃን ነው። ይሄ የማያጠራጥር እውነት ነው። እናንተ በክርስቶስ ስለሆናችሁ የብርሃን ልጆች እና ብርሃን ናችሁ።
2. ትዕዛዞቹ መብራት ናቸው።
በነገራችን ላይ ትዕዛዝ ዕውነተኛ መብራት ነው።  ልጆች ያላችሁ ልጆቻችሁን ይሄ ነገር አታድርጉ ካደረጋችሁት አደጋ አለው። ስትሏቸው ያላዩትን እንዲያዩ መብራት እያበራችሁላቸው ነው። ለምሳሌ አሁን በመጣው ቨይረስ ምክንያት ትዕዛዛት ተላልፈዋል ትዕዛዛቶቹ በህይወታችን ሊገጥመን ከሚችል አስቸጋሪ ነገር ሊከልሉን የሚችሉ መብራቶች ናቸው። እንደ እኔ ሰፈር በድፍረት ተራምዳችሁ ልታልፋት አትችሉም። ምክንያቱም ጉድጓድ የቱ ጋር እንዳለ አታውቁም።
የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ግሩም የትዕዛዛት መብራት አለው።
ዳዊት
"ህግ ለእግሬ መብራት ፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው።" መዝ 119:105
በትዕዛዙ አለመሄድ በሌሊት መመላለስ ማለት ነው። ኢየሱስ ደግሞ እንደዚህ አለ :- “በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል አላቸው።”  ዮሐንስ 11፥10
#የመሰናከያን መንገድ አትምረጡ!  ትዕዛዛቱን እንከተል። ኢየሱስ ራሱ "ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ ነው" ያለው። ትዕዛዛቱ ፍቅራችንን ማሳያ መንገዳችንን ገላጮች መብራት ናቸው። መብራት በባህሪው ያሳይሃል እንጂ ኗሪው ተራማጁ አንተ ነህ።
ለሕዝቄል በትንቢታዊ መንፈስ ለእኛ ለአዲስ ኪዳን ኗሪዎች እግዚአብሔር እንደዚህ ብሏል “መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።”
  — ሕዝቅኤል 36፥27
መንፈስ ቅዱስን የሰጠን በትዕዛዙ እንድንሄድ ነው። ትዕዛዛቱ የህይወታችን መብራቶች ናቸው። ትዕዛዝ ለሚወደድ ሰው ጨለማውን ያልፍ ዘንድ የሚሰጥ መብራት መሆኑ ከገባን በትዕዛዛቱ እንሄዳለን።
2. #ቃለ እግዚአብሔር ትምህርት ብርሃን ነው።
የተወደዳችሁ ቤተሰቦቼ ፦ ዕውቀት ብርሃን እንደሆነ ታውቃላችሁ። ትምህርት የብርሃን መንገድ ጨለማን የሚገፍ ፣ የመሃይምነት ወይም የአላዋቂነትን ጎዳና የሚያስወግድ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ደግሞ የበለጠ ብርሃን ነው። ይሄንን የብርሃን መንገድ የምናገኘው ቃሉን በመማር ነው።
የቃለ እግዚአብሔር ትምህርት
- የጥበብ መንገድ ነው ጥበብን የሚያበዛ ማሽን ነው። ምሳ 9:9
- የሚያፀና ነው። መዝ 18:35
- የህይወት ምንጭ ነው ምሳ 13:14 ፣ 2ኛ ጢሞ 4:3 እና ቲቶ 1:9
ብዙ ማንሳት ይቻላል። ብርሃን የሰው ልጅ ህይወት ነው። ያለብርሃን ህይወትም ዕድገትም የለም። ያለ ትምህርት ህይወትም ዕድገትም የለም።
ቃሉን መማርን ውደዱ። በግል ጊዜያችሁ ከቃሉ ጋር ተጣበቁ። የቃሉን ትምህርት ንብ ከአበባ ውስጥ ምግቧን እንደምትቀስም ቁጭ ብላችሁ ቃሉን ከመፅሐፍ ቅዱስ ላይ ቅሰሙ። አሁኑኑ ጀምሩ ። ቀጥሉ አታቋርጡ አብዙ።
3.የተግሳፅ ዕርምትን ውደዱ።
የማትገሰፁ ፍፁም ፣ የማትስቱ ቅዱስ ራሳችሁን አታድርጉ። ምክንያቱም ተግሳፅና ዕርምት የህይወት መንገድ ነው። የህይወት ጎዳናችሁ እንዲቀናላችሁ። በትዕዛዙ መብራት ፣ በትምህርቱ ብርሃን መገሰፅን ውደዱ አትጥሉት።
ሰው እንደ እግዚአብሔር ቃል ሲገስፃችሁ አሜን ማለትን አበርቱ! አሜን ማለትን ጨምሩ። ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ሰው ስሜቱን ሊጭንባችሁ ሲሞክር እንጂ እንደ ቃሉ ትምህርት መንገዳችሁን ሊያቀናላችሁ ሲሞክር አሜን ብላችሁ ታረሙ። መታረም ነገ ላይ የተሻለ ህይወት መረከቢያ ጎዳናችሁ ነው።
እኔ ብቻ ልክ እና ልክ ነኝ ከሚል ስሜት ውጡ። የምትሳሳቱ ፣ ልትታረሙና ልትገሰፁ የሚገባችሁ አይነት ሰው መሆናችሁን ተረዱ። ፍፁም ክርስቶስ ብቻ ነው። ሌሎቻችን ሁሉ በትምህርት የሚታረም በትዕዛዛቱ መብራት የሚወገድ እንከን እና ደካማ ጎን ያለን ሰዎች ነን።
በመጨረሻም ብርሃናችሁ የሆነውን የቃሉን እውነት ያዙ እላችኋለሁ። እርሱ ብቻ ነው እውነተኛውን መንገድ የሚያሳያችሁ።
               *****************
እወዳችኋለሁ ብርሃናችሁን ያዙ!
             👇👇👇
#ራሳችሁን ጠብቁ ፣ እጆቻችሁን በሳሙና ሁልጊዜ ታጠቡ!
#የ444 መልዕክትን ተግባራዊ አድርጉ ከፀሎታችሁ እና ከጥንቃቂያችሁ ባሻገር በሽታውን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በአቅማችሁ ደግፋ። ሌሎችን መንከባከብ ራስን መንከባከብ ተደርጎ ይቆጠራልና።
እወዳችኋለሁ
ቡሩካን ናችሁ!!
@ቢኒያም ኃይሉ(መጋቢ)
18/7/2012 ዓ.ም
Forwarded from LikeBot
#የህይወት_ማዕዶት!
(ዘውትር ማክሰኞና ሐሙስ ብቻ የሚቀርብ)

ግንቦት 11/2012
ማክሰኞ
ቢኒያም ኃይሉ(መጋቢ)

#ቃለ_እግዚአብሔር

ደስታዬ ያለው ፣ ህይወቴ ያለው ቃሉ ላይ ነው። ቃሉን አለማንበብና ከቃሉ መንፈስ ጋር አለመገናኘት ማለት የህይወትን መንገድ መሳት ፣ ከህይወት አለም መራቅ ነው። ቃሉ ህይወት ነው። ምግባችን ነው። ጥንካሪያችን ነው። ኃይላችን ነው።

“ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።” ኤርምያስ 15፥16

የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የራሱ የእግዚአብሔር ስልጣን ፣ ኃይል ፣ ተግባር እና ሰራዊት እንዳለ እናውቃለን።
ቃሉ ታዲያ ከእግዚአብሔር ሲወጣ ደግሞ የሚሰራውም ያው የራሱን የእግዚአብሔርን ያህል ነው። ቃሉ ማንነቱ ነው።
ቃሉ ያገኛቸው ሙሴ ከገዳይነት ወደ አዳኝነት ፣ ጳውሎስ ከአሳዳጆነት ወደ ሰባኪነት እንዲሁም ወደተሳዳጅነት ፣

ቃሉ ህይወት ቀያሪ ነው። ጨለማው ላይ ብርሃን ይብራ አለ እንጂ እንደቶማስ ኤዲሰን አምፖል ለማምረት አልሞከረም። እርሱ ቃል ውስጥ በቀን እና በጨለማ የሚሰለጥኑ ትላልቅ ብርሃናትና ከዋክብቶች አሉ።

ምድር ውስጥ ያሉትን ይገለጡ አለ እንጂ እንደ ገበሬ አላረሰም አልኮተኮተም አልዘራም። እርሱ ቃል ውስጥ ዘሩም ፣ ኩትኳቶውም ፣ የማብቀልና የማፍራቱም የመከታተሉም ነገር አለ።

ውሃ ውስጥ ያሉትን አዘዛቸው ተርመሰመሱ ያሌለ አይነት ዝርያ የለም ሁሉም ዝርያ የመጣው ከምንድን ነው ? ከቃሉ ውስጥ ነው።

ቃሉ ከአፋ ከወጣ መስራት ያለበትን መፈፀም ያለበትን ነገር እና አስፈፃሚ ሰራዊቶቹን ሁሉ ይዞ ነው የሚወጣው። እርሱ አለምን የሚያስተዳድራት ከአፋ በሚወጣው ቃሉ እና ቃሉ በሆነው ስብዕና ባለው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አለቀ!

ቃለ እግዚአብሔርን ስትሰማ እንደተረት እና ተራ ነገር አትስማው ህይወት ሁሉ ያለበት ቃል መሆኑን እየተረዳህ ስማው።

ኢየሱስ እንዲህ አለ "እኔ የነገርኳችሁ ቃል መንፈስ ነው ህይወትም ነው።" ዮሐ 6:36

ህይወታችን ቃሉ ነው። ዳግመኛ የተወለድነው ከማይጠፋው ከእግዚአብሔር ቃል ነው። ያ ዘር የማይጠፋ ዘር ነው።

እግዚአብሔር ሰማያቱን ያፀናው ሰራዊታቸውን ሁሉ ያቆመው በቃሉ ነው ። ሰማይ ያለምሶሶ ቆሟል ብለሃል ልክ ነው ግን በማይታየው አለም ቃል የተባለ ምሶሶ አለ እርሱም ከመለኮት የወጣው ቃል ነው።

ፀኃይ ትወድቃለች ብለን ዘንግተን አናውቅም ነገር ግን በሰማያት ላይ እንደቤታችን አንፖል ጠፍሮ የያዛት ጠንካራ ገመድ የለም ግን ቃሉ ወጥሮ ይዟታል። ዙረቷን ሳታዛባ የቀጠለችው እግዚአብሔር ባወጣው ቃል ነው።

ስንቱን ልጥራልህ ስንቱንስ ልዘርዝርልህ ለእግዚአብሔር ቃል ክብር እንዲኖርህ ፣ ባለህ ላይ ደግሞ የበለጠ ለማከል ነው።

ቃሉን አክብረው ፣ ተቀበለው እንደሚልህ ሁንለት ቃል ውስጥ ያለ በጀትና ኃይል ማንኛውንም ነገር ለመፈፀምና ለማስፈፀም የሚችል ኃይል ነው።

"የእግዚአብሔር ቃል አያረጅም ፣ የኢየሱስ ቃል አያረጅም ዘላለም ይኖራል.." እያበራ፣ እየገዛ ፣ እየሸነፈ ፣ እያኖረ ፣ እያበረታ ይኖራል።

ቃሌ ከሚያልፍ ሰማይና ምድር ይለፍ ማለቱን ስታስብ ይሄን ያህል የተናገረውን ለማድረግ የሚተጋ በጣም ታማኝ አምላክ እንዳለህ ሊሰማ ይገባል።

እግዚአብሔር ታማኝ ነው ፣ በቃሉም ታማኝ ነው።

ቃለ- እግዚአብሔር የቀየረው ብቻ ጌታውን ያመስግን ቃሉንም ያክብር።

ቡሩካን ናችሁ!

❤️ኢየሱስ ይወዳችኋል

@ቢኒያም ኃይሉ(መጋቢ)
ለጥያቄዎ @BiniservantofGod

👉share it ሼር ይደረግ👈

💁‍♂💁‍♀ @workofgrace🙏
👉👉 @workofgrace
👉👉 @workofgrace
👉👉 @workofgrace
👆👆👆👆👆
🀄️🀄️ሉን JOIN US