TIKVAH-ETHIOPIA
1.4M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#OromoFederalistCongress

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ባወጣው መግለጫ :

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ባወጣው መግለጫ መንግስት በኃይል ዘጋብኝ ያላቸው ጽህፈት ቤቶቹ ተከፍተውና የታሰሩ አባሎቹ እንዲፈቱ በድጋሚ ጠይቋል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አስፈላጊ ከሆነ የምርጫ መርሐ ግብሩ ተሻሽሎ እና የፖለቲካ ምህዳሩ ለሁሉም ዜጎች ተመቻችቶ ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የተሳካ ብሔራዊ መግባባት ተደርጎ የተሳካ ብሔራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ሲልም ጠይቋል።

ፓርቲው በመግለጫው ለዜጎቿ ሁሉ የምትሆን ኢትዮጵያ እንድትፈጠር በሚደረገው ሠላማዊ ትግል ጎን በፅናት እቆማለሁ ሲል አረጋግጧል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OFC #Ethiopia

" በአንድ ፓርቲ ፍላጎትና ሙሉ ቁጥጥር በሚመራ መንገድ የ120 ሚሊዮን ህዝብ ቁመት የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በፍጹም አይፈጠርም !! " - ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (ለቪኦኤ ሬድዮ ከሰጡት ቃል) ፦

" ዋና የኢትዮጵያ ችግር ፈጣሪ መንግሥት ነው። ይሄ ምንም ጥያቄ የለውም።

ከፖለቲካ ኃይሎች ጋር ሆነን ፣ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡም ጋር ሆነን ሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላደረግነው ነገር የለም።

ዋናው ጉዳይ ስልጣን የያዘው ቡድን ሀቀኛ ፍትሃዊ የሚባለውን ነገር በጭራሽ አይፈልገውም።

' ስልጣን እኛ እጅ ነው ' ተንበርከኩና እኛ ጋር ግቡ ወይም የስልጣን ፍርፋሪ ኑና ውሰዱ ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጵያ ህዝብ ከመገዳደል ፖለቲካ ወደ መደራደር ፖለቲካ እንዲገባ አይፈልግም።

ችግሩ ይሄ ነው በአንድ እጅ ማጨብጨብ አይቻልም።

እኛ የምንችለውን ያክል ይሄ ሀገር መሸጋገር የሚችለው ፣ የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር መምጣት የሚችለው ፣ የተሳካ ሰላም እና መረጋጋት መምጣት የሚችለው ሁሉም የኢትዮጵያ ኃይሎች የተሳተፉበት ፦
- ብሔራዊ እርቅ
- ብሔራዊ ድርድር
- ብሔራዊ ምክክር ሲደረግ ነው እያልን ስንጠይቅ ነበር።

ፖለቲካ እስከሚገባን ድረስ አሁን እየተገፋ ባለበት መንገድ 3 ነገሮች በኢትዮጵያ ምድር መሆን አይችሉም።

1ኛ. ሀቀኛ ሰላምና መረጋጋት አይመጣም ፥ ሰላምና መረጋጋት አሁን እየገፉ ባሉበት መንገድ መምጣት አይችልም። እኛም ኖርን አልኖርን !

2ኛ. በኢትዮጵያ ምድር ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ፣ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ፣ ሀቀኛ ፌዴራላዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፣ በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ስልጣን ላይ የሚወጣ መንግሥት ፣ የህዝቡን ይሁንታ ካጣ ከስልጣን የሚወርድ መንግሥት መፍጠር አይቻልም።

3ኛ. በአንድ ፓርቲ ፍላጎት ፣ ሙሉ ቁጥጥር በሚመራ መንገድ የ120 ሚሊዮን ህዝብ ቁመት የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በፍጹም አይፈጠርም።

አንድ ቀን እነሱም ሰምተው ፤ ችግሩም ደግሞ አስተምሯቸው መስመር ሊይዝ ይችላል።

እኛ እንሞክር ነበር አሁንም ያንኑ ህጋዊ እና ሰላማዊ ትግላችንን እንቀጥላለን።

በሀገሪቱ ግጭት ያባባሰው ስር የሰደደው የፖለቲካ ችግር የሚፈታው በፖለቲካዊ ንግግር ብቻ ነው። "


#OromoFederalistCongress

@tikvahethiopia