" ችግሩ ከአቅማችን በላይ ነው " - መሰቦ ሲሚንቶ
የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ፤ ለጊዜው ስሚንቶ ማምረት ማቆሙን አሳውቋል።
ፋብሪካው የሲሚንቶ ማምረት ስራ ያቆመው አጋጠመኝ ባለው " የጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት " ነው።
መሰቦ ፥ " ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሲሚንቶ ለማምረት የምንጠቀምባቸው ጥሬ እቃዎች በተለያዩ ጊዚያት በአግባቡና በወቅቱ ለማግኘት አልቻልንም " ብሏል።
" የተለያዩ ጥሬ እቃዎች ሚገኙባቸው ቦታዎች ከሚኖር ማህበረሰብ ጋር የተፈጠረው ችግር በጊዚያዊነት እና በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና የአከባቢው ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ጥረት ቢደረግም እስከ አሁን መፍታት አልተቻለም " ብሏል ፋብሪካው፡፡
እነዚህ ችግሮች ምን ምን እንደሆኑ በይፋ ከመናገር ተቆጥቧል።
" የተፈጠረው ችግር ከእኔ አቅም በላይ ነው " ያለው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ችግሩን የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ እስኪሰጠው ድረስ ለጊዜው ሙሉ በሙሉ ሲሚንቶ ማምረት አቁሞ በጥገና ስራ እንደሚገኝ አሳውቋል።
#Tigray #Messebo
@tikvahethiopia