TIKVAH-ETHIOPIA
1.4M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቫት

መንግስት በመሰረታዊ ፍጆታ በሆኑ #ምግቦች ላይ #ቫት እንዲያስቀር ተጠየቀ።

መንግሥት ከድጎማ ይልቅ መሠረታዊ የዜጎች ፍጆታ በሆኑ ምግቦች ላይ የሚጣለውን የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲያስቀር ፐርፐዝ ብላክን ጨምሮ ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት መንግሥትን ስለመጠየቃቸው ሪፖርተር አስነብቧል።

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ፍስኃ እሸቱ በሰጡት ቃል ፤ ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥያቄው በአካል መቅረቡን የገለፁ ሲሆን የጉዳዩ ዋነኛ ባለቤት የሆነው የገንዘብ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ምልክታ እንዲያደርግ ጥያቄ ለማቅረብ በሚቀጥለው ሳምንት ቀጠሮ መያዙን ገልፀዋል።

ዶ/ር ፍስኃ እሸቱ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

" ለዋጋ ግሽበት አንዱና ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ያለው ጉዳይ በተለይ በምግብ ውጤቶች ላይ የሚጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጉዳይ ነው።

ዝቅተኛ ገቢ ያለው ኅብረተሰብ ክፍል በሚመገበው ምግብ ላይ 15 በመቶ ታክስ መጨመር ትልቅ ተፅዕኖ አሳድሯል።

ከወር በፊት ይኸው ጥያቄ ለሚመለከታቸው አካላት ቀርቧል። የገንዘብ ሚኒስትሩን ለማግኘት ጥረቶች እንደተደረጉ ነው፤ ምናልባት በሚቀጥለው ሳምንት ዕድሉ የሚሳካ ከሆነ ጥያቄውን በግምባር ለማቅረብ እየተሰራ ነው።

ጥያቄውን በአዋጅ ሳይሆን በመመርያ ደረጃ መመለስ የሚቻል ነው። የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ይሁንታ ካገኘ መስተካከል የሚችል ነው።

አነስተኛ የሆነ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሟቸው በተለይም የአትክልት እና የፍራፍሬ ውጤቶች (ሽንኩርት ፣ ቲማቲም እና ሌሎችም) ከታክስ ነፃ ናቸው ከሚባሉት እንቁላልና ሥጋ በበለጠ ተዘውታሪ በመሆናቸው፣ መንግሥት ከእነዚህ ምርቶች የሚሰበሰበው ቫት እንዲቀር ተጠይቋል።

ፐርፐዝ ብላክ የምርት ውጤቶቹን ቫት በማከል ነው ለሸማች የሚያቀርበድ ይህም ምርቶችን በጣም በረከሰ ዋጋ እንዳያቀርቡ አንዱ እንቅፋት ሆኗል።

ኢትዮጵያ ውስጥ #የዋጋ_ንረት_መባባስ የጀመረው #የተጨማሪ_እሴት_ታክስ አሠራር ከመጣ ወዲህ መሆኑን ጥናት ያስረዳል።

መንግሥት ለሚያከናውናቸው ሥራዎች #ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ሳይረሳ ነገር ግን በሁሉም ምግብ ፍጆታዎች ላይ ሳይሆን ኅብረተሰቡ በመሠረታዊነት የሚጠቀምባቸውን ምርቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ማድረግ ይገባዋል። "

🍏🥬🫑🥕🍋🍌🍇🍎🍓🍍🧄🥔🍅🌶

#ቫት ፦ የገንዘብ ሚኒስቴር ከሃያ (20) ዓመታት በፊት ያወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) አዋጅን የሚተካ ረቂቅ ማዘጋጀቱ ይታወሳል።

ረቂቅ አዋጁ መንግሥት ከቫት ታክስ የሚሰበስብበትን መሠረት የሚያሰፋ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሥራ ላይ ያለው አዋጅ በ1994 ዓ.ም. ከወጣ በኋላ በ2001 ዓ.ም. እና በ2011 ዓ.ም. ለሁለት ጊዜያት መጠነኛ ማሻሻያዎች ተደርጎበት የቀጠለ ሲሆን ፣ አዲስ እየወጣ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ሲፀድቅ የበፊቱን ይሽራል ተብሏል፡፡

በረቂቅ አዋጁ በሰንጠረዥ ሁለት አንቀጽ ስምንት ከታክስ ነፃ የሆኑ አቅርቦቶች መዘርዝር ሥር የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያ ላይ ዝርዝራቸው የሚወሰን የምግብ አቅርቦቶች እንደሚኖሩ የተደነገገ ሲሆን የትኞቹ ናቸው በሚለው ላይ ምንም ተጨማሪ ማብራሪያ አለመስፈሩ ታውቋል፡፡

Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ (www.Ethiopianrepoter.com)

@tikvahethiopia