TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" 53 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባን የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ለማድረግ በአብላጫነት ይደግፋሉ " - የአፍሮባሮሜትር ጥናት

(በኢዮብ ትኩዬ)

66 በመቶ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር የሥልጣን ዘመን እንዲገደብ እንደሚሹ መመላከቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ #አፍሮባሮሜትር ይፋ ካደረገው ጥናት ተረድቷል።

የዳሰሳ ጥናቱ ከላይ ከተጠቀሰው የገደብ ፍላጎት በተጨማሪ 67 በመቶ ኢትዮጵያውያን የሕገ መንግሥቱን መሻሻል እንደሚፈልጉ፣ ነገር ግን የራስን ዕድል በራስ የመወሰንና በባንዲራው ያለውን አርማ በተመለከተ የሕዝቡ አስተያየት እንደተከፋፈለ ያስረዳል።

በጥናቱ ቁልፍ ግኝቶች መሠረት፦

- 67 በመቶ ኢትዮጵያውያን የሕገ መንግሥቱን መሻሻል የሚደግፉ፣ 16 በመቶዎቹ  ሕገ መንግሥቱ  ሙሉ ለሙሉ እንዲወገድ፣ እንዲሁም ቀሪዎቹ 16 በመቶዎቹ ደግሞ አሁን ባለበት እንዲቀጥል የሚፈልጉ ናቸው።

- በ2012 ዓ.ም ከተካሄደው የአፍሮባሮሜትር ዳሰሳ ጥናት አንጻር፣ በዚህ ጥናት ሕገ መንግሥቱ እንዲቀየር የደገፉ በአምስት በመቶ ብልጫ አላቸው። 

ይህንኑን ብልጫ በተመለከተ የተቀመጠውና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የጥናቱ ግራፋዊ መግለጫ፣ በ2020 69 በመቶቹ፣ በ2023 67 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች ሕገ መንግሥቱ መሻሻል እንዳለበት፣ በ2020 18 በመቶ፣ በ2023 16 በመቶዎቹ ዜጎች ሕገ መንግሥቱ ባለበት እንዲቀጥል እንዲሁም በ2020 11 በመቶ፣ በ2030 16 በመቶዎቹ ዜጎች ደግሞ ሕገ መንግሥቱ በአዲስ ይቀየር ብለው እንደሚስማሙ ያስረዳል።

- የተጠቆሙ የሕገ መንንግሥት ማሻሻያዎችን በተመለከተ፣ 67 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች የሥራ ቋንቋዎችን ለፌደራል መንግሥት እንዲደረግ፣ 66 በመቶዎቹ የጠቅላላ ሚኒስትር የሥልጣን ዘመን እንዲገደብ እንዲሁም በ2012 ዓ.ም 35 በመቶ፣ በአሁኑ ጥናት ደግሞ 53 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባን የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ለማድረግ በአብላጫ ይደግፋሉ።

በዚህም 67 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች ተጨማሪ የሥራ ቋንቋዎች ለሕገ መንግሥቱ እንደሚያስፈልግ፣ 30 በመቶ የሚሆኑት አያስፈልግም ብለው እንደሚቃወሙ እንዲሁም 4 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከመቃወሙም ከመደገፉም እንዳልሆኑ የጥናቱ ገላጭ ግራፍ ያስገነዝባል።

ገላጭ ግራፉ አክሎም፣ 66 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች የጠቅላይ ሚኒስትር የሥልጣን ገደብ እንዲደረግ፣ 27 በመቶዎቹ ደግሞ መገደቡን እንደሚቃወሙ እንዲሁም 7 በመቶ የሚሆኑት ከመደገፉም ከመቃወሙም እንዳልሆኑ ያሳያል።

በተጨማሪም 54 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች አዲስ አበባን የፌደሬሽኑ አባል ማድረግን እንደደሚደግፉ፣ 34 በመቶዎቹ እንደሚቃወሙ፣ 12 በመቶዎቹ ደግሞ ከመቃወሙም ከመደገፉም እንዳልሆኑ በግራፍ ተቀምጧል።

እንዲሁም፣ 46 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን አንቀጽ 39ኝን ለማስወገድ እንደሚደግፉ፣ 47 በመቶዎቹ እንደሚቃወሙ፣ 7 በመቶዎቹ ደግሞ ከመቃወሙም ሆነ ከመደገፉ ጎራ እንዳልሆኑ ተመላክቷል።

በተጨማሪም፣ 29 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች በባንዲራ መሀል ላይ ያለውን ብሔራዊ አርማ ማስወገድን እንደሚደግፉ፣ 62 በመቶዎቹ እንደሚቃወሙ እንዲሁም 9 በመቶዎቹ ደግሞ ከመደገፉም ከመቃወሙም ጎራ እንዳልሆኑ የጥናቱ ግራፍ ያስረዳል።

ጥናቱ የተካሄደው በ2,400 ቃለ መጠይቆች፣ ዕድሚያቸው 18 ከዚያ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በማሳትፍ እንደሆነ፣ ከግንቦት 17 እስከ ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መረጃው እንደተሰባሰበ፣ የናሙናው መጠን በአገር አቀፍ ደረጃ የተሰራና የስህተት ኅዳጉ +/-2 በመቶ፣ የአስተማማኝነት ደረጃው 95 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia