TIKVAH-ETHIOPIA
1.4M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥንቃቄ📌ይህ 5,143 ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ የአማርኛ ገፅ #አይደለም። በዚህ ገፅ የተዛቡ መረጃዎች እየተሰራጨ በመሆኑ ጥንቃቄ አድርጉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትዝብት📌የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታቸውን ከ12 ሰዓት ጀምረው ማየት እንደሚችሉ በትልልቅ የመንግስት እና የግል መገናኛ ብዙሀን አሰራጭቷል። ይህ በተባለበት ሰዓት ተማሪዎች ውጤት ይታይባታል በተባለበት ድረገፅ እና የSMS ቁጥር ያለማያቋረጥ ሙከራ ቢያደርጉም ምንም ውጤት ለማየት አልቻሉም። ዝግጅት ካልተደረገበት እና ሲስተሙ በአግባቡ የማይሰራ ከሆነ ለምን ለህዝብ ይፋ ተረገ?? ይህን መሰሉ አሰራር የተቋሙን ታማኝነት ያሳጣዋል። በሌላ በኩል ተቋሙ ውጤት ማይታይበት ችግሩ ምን እንደሆነና ለምን እንዲህ ሊሆን እንደቻለ በመግለፅ ህዝቡን ይቅርታ ሊጠየቅ ይገባው ነበር። ብዙ ተማሪዎችን እና ወላጆችን በአሰራር ክፍተት #ማስጨነቅ ፍፁም ተገቢ #አይደለም። ሊታረም ሊስተካከል ይገባዋል።

ህዝብ ይከበር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀጫሉ ሁንዴሳ...

“•••እነኚህ ሰዎች ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ሰርተው #ያስደመሙኝ ነገር አለ። ከዚህ በፊት ኦሮሞ እንደ አገር አፍራሽ ተደርጎ ብዙ ተሰርቶበታል። አሁን ግን ኦሮሞ አገር አፍራሽ እንዳልሆነ፣ ትልቅ ሃሳብ ያለው እንጂ የሚያሳስብ እንዳልሆነ፣ ያገሪቱ ጋሻ እንደሆነ ባለም ላይ አስመስክረዋል። በእርግጥ ሁሉም ነገር ተሟልቶ ተጠናቋል ማለት አይደለም#ለዘመናት የተተበተበብንን ትብታብ በጣጥሶ ነገሮችን ለማስተካከል #አይደለም ስምንት ወር #ስምንት አመትም አይበቃም። አሁን የታሰርንበትን እስራቶችን (ቋጠሮዎችን) በመፍታት ደረጃ ላይ ነው ያሉት። ደግሞም #ሁሉንም ነገር ከነሱ ብቻ መጠበቅ የለብንም። #እኛም እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንሰራቸው ነገሮች አሉ።”

ሀጫሉ ሁንዴሳ ከOBN ቴሌቪዝን ጋር በነበረው ቆይታ የተናገረው!

©Daniel Ragassa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
fake page🔝

ከላይ ያለው የፌስቡክ ገፅ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ #አይደለም

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ በEBS ስም የተከፈተና ከ46,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የቴሌግራም ቻናል የEBS ቴሌቪዥን #አይደለም

ከዚህ ቀደም "አዲስ ነገር" EBS በሚል በቴሌግራም ላይ የተከፈተ ገፅ ትክክለኛ እንዳልሆነ ከEBS ሰዎች የደረሰንን መልዕክት ማጋራታችን አይዘነጋም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EOTC

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ?

- በዓለ ጥምቀቱን ለማክብረ በመንግሥት ዘንድ ቤተክርስቲያን ይሄን ትበል ፣ አለበለዚያ እንዲህ አይደለም የሚሉ መልዕክቶች ደርሰውናል።

- ቤተክርስቲያን ሰላሟን ታውጃለች።

- አሉ አሉ እየተባሉ ስለተነገሩ ንግግሮች እና ግለሰቦች፣ ጳጳሳት እና ሊቃነጳጳሳት ከሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ታያለች፣ ትመክራለች ታስተምራለች። ህግ አላት በህጓ መሰረት ትገስፃላች። ከዚህ ውጭ ሱሪ በአንገት አውጣው የሚባል ነገር ቤተክርስቲያን አትሸከምም አትቀበለም።

- ሰላሟን እያወጀች፣ ሰላሟን እየሰበከች በሰላም መንገድ ትጓዛለች።

- ሁል ጊዜ ቤተክርስቲያን መሞትን ስራዬ ብላው ይዛ ኖራለች ወደፊትም ሞት ከሆነ በሰላም ለመቀበል ዝግጁ ናት።

- " ይሄን ካደረግሽልኝ ይሄን አደርግልሻለሁ " የሚል መደራደሪያ የላትም ፣ ሊኖራትም አይችልም። ድርድሯ ሰላምና ሰላም ብቻ ነው።

- እኔ ያልኩሽን አድርጊ የሚል በቀኝም ይሁን በግራ ፤ ከገዢውም ክፍል ይሁን እገዛለሁ የሚል ሃሳብ ቢመጣ ያን ተቀብላ የማስተናገድ አቅምም ብቃትም የላትም።

- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች፣ በዓሉ ዓለም አቀፍ ስለሆነ የተለያየ እምነት ያላችሁ ልጆች ፣ የሌላ እምነት ተከታይ ሆናችሁ በዓሉ በዓላችን ነው የምትሉ፣ የምትደግፉ በዓሉን እራሳችሁ አክባሪዎች ፣እራሳችሁ የፀጥታው አስተናጋጆች የሰላም መሪዎች ሆናችሁ በዓሉ በሞቀና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ቤተክርስቲያን መልዕክት ታስተላልፋለች።

- የፀጥታ አካላት ትላንት እንዲህ ተብያለሁ ይሄ እንደገና በተቃውሞ ካልታወጀልኝ በስተቀር ይሄን አላደርግም የሚለውን አስተሳሰብ ትቶ ህግን በህግ ስርዓትን በስርዓት ለመፈፀም አእምሮውን አስፍቶ የተሻለ ስራ እንዲሰራ ቤተክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

- ሌላው ሌላው ችግር በመድረክ ዙሪያ፣ ማነው ጥፋተኛ ? ምን አስቦ ነው ? ምን ብሎ ነው ? የሚለውን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመክርበት የሚዘክርበት፣  የሚገሰፀውን የሚገስፅበት ፣ ከቀኖና የወጣውን ከቀኖና ወጥተሃል የሚልበት የራሱ ስርዓት ስላለው ለህጉ እንተወዋለን።

- " ይሄን በሉ ይሄን አድርገ፣ ይሄን ካላደረጋችሁ ይሄን አናደርግም " የሚባል መያዣ ነገር ቤተክርስቲያን አስተናግዳ አታውቅም ፤ ወደፊትም አታስተናግድም።

- እገሌ እገሌ ባልልም ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ናት በዓሉም የህዝብ ነው ይሄን መያዣ አናድረግም ችግሩ ችግር ሳይሆን እንዲፈታ ይደረግ በመልካም ነገር በዓሉን በሰላም እናክብር ብለው የተናገሩ መሪዎች አሉ በዚህ አጋጣሚ ሊደነቁ ይገባል። ከመሪዎች የሚጠበቀው ይሄ ነው። ችግርን እንዴት እንፍታው ችግርን እንዴት እናስወግደው ፣ ሰላም እንዴት እናስፍን ነው መባል ያለበት።

- በየሄድንበት " ደግሞ ለኦርቶዶክስ፣ ለተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ቃሉም ይከብዳል በየቢሮው ስንሄድ ቢያንስ አይሆንም አይባልም " ያንን ያንን ያርሙ " ይላሉ።

- " ኦርቶዶክስ ሃገር ናት ፣ ለሀገር ዋልታ ናት፣ ምሰሶ ናት አምድ ናት ይሄን ታሪክ አይክደውም። ዘመን ቢያስረጃትም ዘመን ቢጥላትም ዘመን ያነሳታል።

- ዛሬም ሲደረግላት እያመሰገነች ነው። ለሀገር ሰላም ማድረግ ያለባትን እያደረገች ነው ፤ በየመስሪያ ቤቱ ስንሄድ " ደግሞ ለኦርቶዶክስ " የሚለው ቃል ሊታረም ይገባል።

- ቤተክርስቲያን ትከበር ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥም #በሃይማኖት_ስም እንደፈለገ የሚዋኙ ሰዎች ቆም ብለው ያዳምጡ፣ የሚናገሩትንም ይመርምሩ ፣ ሃይማኖታዊ ቃል ነው አይደለም ይበሉ ከሃይማኖታዊ ቃል ውጭ የሆነው ሁሉ የእኛ #አይደለም

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia