TIKVAH-ETHIOPIA
1.41M subscribers
55K photos
1.37K videos
199 files
3.67K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አበረታቷቸው🙏

" ከበርካታ ችግሮች ጋር እየታገልንም ቢሆን ከ90 በላይ ህጻናትን ቁርስ አብልተን ወደትምህርት ቤት እንልካለን " - ተዋናይትና ደራሲ ሀና ፍቃዱ

የበጎ ልቦች የእርዳታ ድርጅት በቅን አሳቢ ወጣት የሀዋሳ ልጆች የተመሰረተ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ሲመሰረት ጥቂት አረጋዉያንን በየቤቱ እየሄዱ ማገዝና አልፎ አልፎ ለህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ የማገዝ አላማ አንግቦ ነበር።

አሁን ላይ ከ90 በላይ ህጻናትን ቁርስ አብልቶ ወደትምህርት ቤት የሚልክና ከ30 በላይ አረጋዉያንን እየተንቀሳቀሰ የሚረዳ ድርጅት ለመሆን በቅቷል።

በድርጅቱ ውስጥ በማስተባበርና ቅን ልብ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን እየጠየቀች ገንዘብ በማሰባሰቡ በኩል የነቃ ተሳትፎ የምታደርገዉ ተዋናይትና ደራሲ ሀና ፈቃዱ ፥ " እቅዳችን በምግብ ችግር ትምህርት ቤት የሚያቋርጡ 30 ልጆችን መርጠን ቁርስ በማብላት ወደ ትምህርት ቤት መላክ ቢሆንም አሁን ላይ ከ90 በላይ ልጆችን እያስተናገድን ነው " ብላለች።

" ለዚህም ሀገር ውስጥና ውጭ ሀገር የሚኖሩ ልበ ቀናዎች እያገዙን ነው " የምትለው ሀና ፥ " እገዛዉ ከጠበኩት በላይ ሆኖ በኢትዮጵያዊነቴ እንድኮራ አድርጎኛል " በማለት በሶሻል ሚዲያና በአካል የሚያግዟቸውን አካላት አመሰግናለች።

ይሁንና አሁን ላይ ያለው የህጻናት ቁጥር በጣም በማሻቀቡ ከፍተኛ ድጋፍ ያሻናል በማለት ማህበረሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርባለች።

በድርጅቱ ውስጥ " የሰኞን የቁርስ ወጭ እኔ እሸፍናለሁ " ብሎ ህጻናቱ ጋር ያገኘነዉ የባህርዳር ከነማዉ ተጫዋች ፍሬዉ ሰለሞን ወይም ጣቁሩና ባለቤቱ በህጻናቱ ሁኔታ ልባቸዉ እንደተነካና ለወደፊቱም ቤተሰብ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

" ሁላችንም ተባብረን ህጻናቱን ልንረዳ ይገባል " የሚለዉ ተጫዋቹ በሚቀጥለዉ ሲመጣ ጓደኞቹን ይዞ እንደሆነ ገልጾ " የበጎ ልቦችን ሁኔታ እየመጣችሁ ጎብኙ " በማለት ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎቹን ቁርስ አብሎት ለመሸኘት በቀን ከ8 ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር የሚጠይቅ ሲሆን ሀና ፍቃዱን ጨምሮ ሌሎችም የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በሚያደርጉት ጥረት ተማሪዎቹ የሚመገቡት።

አስተባባሪዎችን በስልክ ቁጥር 0911992312 ወይም 0926441657 ደውለው አግኟቸው።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia