TIKVAH-ETHIOPIA
1.38M subscribers
54.6K photos
1.35K videos
197 files
3.61K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ዙሪያ የአሶሳ ፖሊስ ምን አለ ?

የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው " ሰላም ሰፈር " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ረቡዕ ከጧቱ በግምት 2:45 ላይ እንደሆነ አመልክቷል።

" በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል በተፈጠረ በሀሳብ ያለመግባባት ምክንያት ተጠርጣሪው በአሰቃቂ ሁኔታ ጀርባዋ ላይ #በጩቤ_በመውጋት የተማሪዋ ህይወት እንዲያልፍ አድርጓል " ሲል ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝም አሳውቋል።

የከተማው ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ከዩኒቨርስቲው ግቢ ውጭ እንደሆነ አመልክቷል።

ተጠርጣሪው የግቢ ተማሪ ያልሆነና ከአዲስ አበባ ዱከም ከተማ አቋርጦ ወደ አሶሳ ከተማ ለስራ ጉዳይ በመምጣት የወንጀል ድርጊቱን እንደፈጸመ ገልጿል።

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚድያዎች " ድርጊቱ የተፈጸመው በግቢ ውስጥ ነው " በሚል የሚሰራጨው እና የብሔር ግጭት አስመስለው የሚወራው ፍጹም ከእውነት የራቀ እና ሁለቱም የአንድ ብሔር ተወላጅ እንዲሁም በጓደኝነት አብረው የነበሩ መሆኑን የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።

#AssosaPolice

@tikvahethiopia