TIKVAH-ETHIOPIA
1.41M subscribers
55K photos
1.37K videos
199 files
3.67K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
AudioLab
#ምርጫ2013

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማህበር ሥራ አስፈጻሚዎች በ #ምርጫ2013 የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ተሳትፎና የሚዲያዎች ሚና ላይ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሰጡት ገለፃ።

- ጋዜጠኛ ሲሳይ ሳህሉ
- ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ
- ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት

@tikvahethiopia
Audio
AudioLab
#ምርጫ2013

በምርጫ ወቅት የምንጠቀማቸው ቃላቶች ፦

በአሁን ወቅት በተደጋጋሚ ለሚነሱት የምርጫ ቃላቶች ማብራሪያ እንዲሰጡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስን ጋብዘናል።

ማብራሪያ የተሰጠባቸው ቃላቶች፦

- ኳራንታይን
- ውጤት ማጣራትና ማረጋገጥ

በተጨማሪም ወ/ሪት ሶልያናን ስለ ቅሬታ አቀራረብ እና ውጤት ስረዛ ጥያቄ አቅርበንላቸዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና የሰጡትን ምላሽ ከላይ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

#TikvahFamily #ምርጫ2013

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ኳራንቲን የተደረጉ /በምርመራ ላይ ያሉ ጣቢያዎች ስንት ናቸው ?

በአዲስ አበባ የመጫረሻ #ኳራንቲን ፣ ምንም የማይደረግበት ወይም ደግሞ ወደውጤት ቋት ውስጥ የማይገባ በሚል የተያዙ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አሳውቀዋል።

አንደኛው በምርጫ ክልል 24 ያለ ሲሆን ሌላኛው በንፋስ ስልክ ያለ ነው።

ከዛ ውጭ እንደገና በመቁጠር እና ሰነዶችን እንደገና በማየት የሚስተካከሉ ሊኖሩ ይችላሉ።

NB : በምርጫው ሂደት "ኳራንቲን ማድረግ" ማለት ከዋናዎቹ ውጤቶች ጋር ሳይቀላቀል ማግለል ወይም ደግሞ መለየት እና በልዩ ሁኔታ ማጣራት ማለት ነው።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ኢትዮጵያ በ2 ዙር የምታደርገው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያውን ዙር አጠናቃ የውጤት ይፋ መሆን እየተጠበቀ ነው።

ምርጫው ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያለው ዜጋ የተሳተፈበት መሆኑ መግለፁ ይታወሳል።

ዛሬ አውሮፓ ህብረት ፣ እንግሊዝና ጀርመን፣ ጃፓንን ጨምሮ 12 ሀገራት ምርጫውን አስመልክቶ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

ምርጫውን ተዓማኒ ለማድረግ የተሻሻሉ ሕችን ማውጣትን ጨምሮ ምርጫ ቦርድ የወሰዳቸውን ርምጃዎች አድንቀዋል፡፡

ሲቪል ማኅበራት በምርጫው ሂደት ያሳዩት ጉልህ ተሳትፎ አመርቂ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ሆኖም ግን ፥ አንዳንድ ተቃዋሚዎች በታሰሩበት ፣ የፖለቲካ ምኅዳሩ በተገደበበት፣ ጋዜጠኞች በሚዋከቡበት፣ የጸጥታ ችግር ባለበትና ፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት ምርጫ ዘመቻ ለማድረግ በተቸገሩበት ሁኔታ ውስጥ ምርጫው መካሄዱን የገለጡት ሀገራቱ፣ የሀገሪቱን ችግሮች ለመቅረፍ ሁሉን ዐቀፍ ብሄራዊ ንግግር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

አሜሪካም ከኢትዮጵያ ምርጫ ጋር በተያያዘ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል መግለጫ አውጥታለች።

አሜሪካ ምርጫው በአለመረጋጋትና ግጭት ውስጥ የተካሄደ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነጻ እና ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ ነው ብላለች።

አንዳንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መታሰራቸው እና ሌሎችም ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን ሁሉን ዐቀፍ ብሄራዊ መግባባት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ብላለች።

በድኅረ-ምርጫ ለፖለቲካዊ ንግግር፣ ግጭቶችን ለመፍታትና ለብሄራዊ ዕርቅ አሜሪካ እገዛ አደርጋለሁ ብላለች። የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡና ተኩስ እንዲቆም ድጋሚ ጠይቃለች። #Wezema

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ምርጫ ከተደረገባቸው 440 ምርጫ ክልሎች ውስጥ 221 የሚሆኑ የምርጫ ክልሎች ውጤቶቻቸውን መለጠፋቸውን ወይዘሪት ሶሊያና አሳውቀዋል።

ከምርጫ ክልሎቹ መካከል ከ50 % በላይ የሚሆኑት ናቸው ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶቻቸውን የለጠፉት።

በአማራ ክልል 40 የምርጫ ክልሎች ውጤት የለጠፉ ሲሆን በኦሮሚያ 125 የምርጫ ክልሎች ውጤት ለጥፈዋል ተብሏል።

አዲስ አበባ ከተማ ባሉ 10 የምርጫ ክልሎች ውጤት አሳውቀዋል፤ በከተማ ያሉ ሌሎች የምርጫ ክልሎች ቆጠራ አለመጠናቀቁ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፦ በደቡብ ክልል በቁጫ የምርጫ ክልል ሲካሄድ የነበረው ቆጠራ እንዲቆም ተወስኗል።

ቆጠራው እንዲቆም የተወሰነው በነበረው ተገቢ ያልሆነ አሰራር እና የጸጥታ ችግር ምክንያት እንደሆነ ወ/ሪት ሶልያና ሽመልስ ገልጸዋል።

ቦርሩ በቁጫ የምርጫ ክልል በሂደቱ ላይ ተገቢ ያልሆኑ አሰራሮች እንደነበሩ ቅሬታዎች ለቦርዱ ሲቀበል የነበረ ሲሆን ጉዳዩ እስኪጣራ ቆጠራ እንዲቆም ተወስኗል።

በምርጫ ክልሉ ሲቀርቡ ከነበሩት ቅሬታዎች በተጨማኢ የጸጥታ ችግር እንዳለ ቦርዱ መረጃ ስለደረሰው ቆጠራው ቆሞ የምርጫ ቁሳቁሶች ባለበት ታሽጎ እንዲቀመጥ ወስኗል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በድሬደዋ በ6 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ችግር እንዳጋጠመው ቦርዱ ገለጸ።

በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ስድስት የምርጫ ጣቢያዎች የክልል ምክር ቤት ምርጫ ሳይካሄድ እንደቀረ እንዲሁም ከስድስቱ በአንዱ ጣቢያ የህዝብ ተወካዮች ምርጫ ጭምር ሳይካሄድ መቅረቱን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ገልጿል።

ሪፖርቱ አሁን እንደደረሳቸው የገለጹት የቦርዱ የኮሚውኒኬሽን አማካሪ ሶልያና ሽመልስ ''የክልል ምክር ቤት የድምጽ መስጫ ወረቀት አልደረሰንም'' በሚል ምርጫው ሳይካሄድ እንደቀረ የምርጫ ክልሉ ኃላፊ መግለጹን የጠቆሙ ሲሆን ይህንን ግን አስቀድመው ሪፖርት አለማድረጋቸውን ነው ያነሱት።

በእነዚህ ጣቢያዎች ላይ ምን ይሆናል የሚለውን ቦርዱ መመልከቱን አንስተው ''እነዚህ ጣቢያዎች ላይ አንድ ፖርቲ ብቻ ነው የሚወዳደረው። የአንድ ፖርቲ ውድድር ስለሆኑ በክልል ምክር ቤት ደረጃ የሚኖረውን ውጤት አይቀይሩትም ስለዚህ ምንም አይነት ተጨማሪ ምርጫ ማድረግ አያስፈልግም ብሎ ቦርዱ ወስኗል'' ብለዋል።

ከስድስቱ አንዱ ጣቢያ ላይ ከክልል ተወካዮች ምክር ቤት በተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም አለመካሄዱን ያነሱት ወ/ሪት ሶልያና ''...በአጠቃላይ የተወካዮች ምክር ቤት ውጤት ታይቶ ውጤቱን የሚቀይር ከሆነ ተጨማሪ ውሳኔ ቦርዱ የሚወስን ይሆናል።'' ሲሉ ገልጸዋል።

6ቱ ጣቢያዎች ከዚህ ቀደም የመራጮች ምዝገባ በትክክል ያልተካሄደባቸው ተብለው የተለዩ እንደሆኑ ያስታወሱት ወ/ሪት ሶሊያና ለዚህ ችግር መፈጠር ኃላፊነት የሚወስደው አካል የቱ ነው የሚለውን እያጣሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013_እና_አዲስአበባ

ምርጫ ቦርድ ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ምርጫ ሂደት ላይ በፓርቲዎች (በተለይ ደግሞ በባልደራስ ፓርቲ) ሲነሱ ለነበሩ ቅሬታዎች እና አቤቱታዎች በተወሰኑት ላይ ምላሽ ሰጥቷል።

ለቅሬታዎቹ እና አቤቱታዎቹ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ናቸው።

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በየምርጫ ጣቢያው በተለጠፈው የውጤት መግለጫ ወረቀት ላይ ተሰረዟል/ተደልዟል ስለሚባለው ጉዳይ ?

ወ/ሪት ሶሊያና : ምርመራ አድርገናል ፤ የየምርጫ ክልል ኃላፊዎች ስርዝ ድልዝ ተደረገበት የተባለውን ጣቢያ ተመልከትው ችግር ይኑርበት አይኑርበት የሚለውን ድጋሚ ቆጥረው እያረጋገጡልን ነው፤ የውጤት ማሳወቅ ሂደት ላይ ስርዝ ድልዝ መኖሩ ነው እንጂ ችግር ያለበት አልተገኘም፤ በቆጠራው ላይ ያለው እና የተፃፈው ቁጥር ትክልል ነው የሚል ሪፖርት ደርሶናል።

የምርጫ ቆጠራው ችግር አለበት ስለሚባለው ጉዳይ ? (ባልደራስ ፓርቲ ያቀረበው ቅሬታ)

ወ/ሪት ሶሊያና : በአዲስ አበባ አብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሁሉም ፓርቲ ወኪሎች ተገኝተው ነው ቆጠራ የተደረገው ፤ አ/አ ላይ የፓርቲ ወኪል ለምርጫ ጣቢያ ልኮ የምርጫ ጣቢያ አልቀበልም ያለበት ምንም አይነት ምርጫ ጣቢያ የለንም ፤ ሁሉም ቦታዎች የፓርቲ ወኪሎች ተገኝተዋል ፤ እራሳቸው ወኪሎቻቸውን እስከላኩና አቅማቸው ፈቅዶ ከ1 ሺህ በላይ ጣቢያዎች ላይ እስካስቀመጡ ድረስ። ወኪሎቹ የምርጫ ሂደቱ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ተከታትለው ውጤቱ ላይ ፈርመዋል ሁሉም ቦታዎች ላይ ማለት ይቻላል። ወኪሎች ያሉባቸው ፊርማዎች ኖረውን ነው የመጣነው የምርጫ ሂደቱን ስናደርግ።

ይቀጥላል👇
#ምርጫ2013_እና_አዲስአበባ

ማንነታቸው የማይታወቁ ጣቢያዎች ተከፍተው ነበር ? (ባልደራስ ፓርቲ ያቀረበው ቅሬታ)

ወ/ሪት ሶሊያና : ፍፁም ሀሰት ነው። አዲስ አበባ ላይ ማንነታቸው የማይታወቁ ጣቢያዎች የሉንም። ሁሉም ጣቢያዎች ኮድ አላቸው፤ ኮድ የሌላቸው ያገኘናቸው 2 ጣቢያዎችን እንኳን ድጋሚ ኮድ ሰጥተን ምርጫ እንዲካሄድ አድርገናል።

አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የባልደራስ ፓርቲን ውጤት እያሳነሱ እንዲፅፉ ተደርገዋል ? (የባልደራስ ፓርቲ ቅሬታ)

ወ/ሪት ሶሊያና : ይህ ፍፁም ሀሰት ነው። ፓርቲ ወኪሎች ያሉባቸው ቦታዎች ከሆኑ የፓርቲ ወኪሎቻቸው እራሳቸው ይህን አይተው ዝም አይሉም። ወኪሎቹ እራሳቸው እንደዚህ ያለ አቤቱታ አቅርበው (በእኔ ፓርቲ ላይ ያለው ውጤት በትክክል አልተቆጠረም/በትክክል አልተፃፈም ብለው) ያቀረቡት ሪፖርት የለም። ያን አይነት አቤቱታ የቀረበበት የምርጫ ጣቢያም የለንም።

በወረቀት እጥረት የተነሳ ደጋፊዎቻችን ወደቤቶቻቸው ሄደዋል ተብሎ ስለተነሳው ቅሬታ ?

ወ/ሪት ሶሊያና : እስከ ለሊቱ 7 ሰዓት ከ10 ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት አከናውነናል። የድምፅ መስጫ ወረቀት ባለመኖሩ የተቋረጠብን ምርጫ ጣቢያ የለም። ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት ነበር ነገር ግን ባለው እያካሄዱ እያለ ተጨማሪ ወረቀቶችን ማድረስ ችለናል። ስለዚህ መሰረታዊ የሆነ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ተቋርጦ የድምፅ መሥጫ ወረቀት ባለመኖሩ የተነሳ ሰው ተበትኖ/ተመልሶ ኑ ወረቀት መጥቷል እና ድምፃችሁን ስጡ የተባለበት አንድም ቦታ የለም፤ ስለዚህ ወረቀት አልቆ ደጋፊዎቼ ተመለሱ የሚለው በከፍተኛ ደረጃ #የተሳሳተ መረጃ ነው።

ይቀጥላል👇
#ምርጫ2013_እና_አዲስአበባ

በአዲስ አበባ ድምፅ ሰጪው ረጅም ሰልፍ ነበረበት የሚልም ቅሬታ ነበር ፤ይሄ ጉዳይ እንዴት ይታያል ?

ወ/ሪት ሶሊያና : ምንም ጥያቄ የለውም ፤ በተወሰነ ደረጃ የድምፅ ሰጪዎች መንገላታት ቢያሳዝንም በሌላ በኩል ሲታይ ድምፅ ሰጪዎች በድምፅ መስጠት ሂደቱ ላይ ለመሳተፍ ረጅም ሰዓት ወስደው በከፍተኛ Trunout ወጥተው ድምፅ መስጠታቸው በጣም የሚያስደስት ነው፤ ይህም በቦርዱ በጥሩ ጎኑ የታየ ነው።

በአጠቃላይ በአ/አ የነበረው ምርጫ በወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፦

"... አዲስ አበባ በጣም ጥቂት ችግር ካለባቸው ፤ አብዛኛው የምርጫ ሂደት (ሁሉም ማለት ይቻላል) ፓርቲዎች ሆኑ የግል ተወዳዳሪዎች ወኪሎቻቸውን ያስቀመጡበት ፤ በቆጠራ ሂደቱ ላይ አብዛኛዎቹ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሂደቱ እስኪጠናቀ ድረስ ታዝበው #ፈርመው የሄዱበት የቆጠራ ሂደት ያካሄድንበት ነው። በእርግጥ በአዲስ አበባ ጣቢያዎቹ ብዙ ቢሆኑም በከፍተኛ ደረጃ የፓርቲ ወኪሎች የተገኙበት ፣ ታዛቢዎች የተገኙበት፣ ዜጎች በጣም በረጅም ሰልፍ ሰዓት ወስደው የመረጡበት ፣ እስከ ለሊቱ 7 ሰዓት ሰፍል ላይ ያለው ሰው እንዳይቋረጥ ብለን ማንኛውም ድምፅ ሰጪ ድምፁን እንዲሠጥ ያደረግንበት ፣ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ከልሎች ቦታዎች በተሻለ ሁኔታ ግልፅ የሆነበት እና ሚዲያን የሲቪክ ማህበራትም ፣ የፓርቲ ወኪሎች እኛም እራሳችን እየዞርን ያየንበት ነው።"

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

378 የምርጫ ክልሎች የምርጫ ውጤት አስረከቡ።

ከየክልሎቹ የሚሰበሰቡ የምርጫ ድምጽ ውጤቶች ርክክብና ጉብኝት ተደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው የመገናኛ ብዙሀን ጉብኝት በአጠቃላይ ከየምርጫ ክልሎች ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚመጡ የምርጫ ውጤቶች ርክክብ ሒደት እና በአሁኑ ሰአት የውጤት አሰባሰብ ሒደቱ ተጎብኝቷል።

በመረጃ ርክክቡም የሚጠበቁ መስፈርቶችን መሠረት በማድረግ ከየምርጫ ክልሎች በሚጠበቀው መልኩ መሆኑ እየተረጋገጠ ርክክብ ተደርጓል።

378 የምርጫ ክልሎችም የምርጫ ውጤት አስረክበው የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከጥቂት ደቂቃ በኃላ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን የሚከታተሉ የቲክቫህ አባላት በቦታው ይገኛሉ።

መግለጫውን በቀጥታ በ Voice Chat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

ቦርዱ በተለያዩ ምክንያቶች የሁሉንም የምርጫ ክልሎች ውጤት በአስር ቀናት ውስጥ መግለጽ እንዳልቻለ አስታውቀዋል።

- የመደመር ሂደቶች አለመጠናቀቅ፣
- በትራንስፖርት ችግር ወደ ማዕከል ውጤት ተጠቃሎ አለመድረሱ
- የፖለቲካ ፖርቲዎች አቤቱታ ባቀረቡባቸው የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ማዕከል ተጠቃሎ አለመድረስ ለመዘግየቱ በምክንያትነት አንስተዋል።

ለቦርዱ ውጤት አያድርሱ እንጂ ምርጫ ክልሎቹ በአካባቢያቸው የምርጫ ውጤት የተለጠፈ መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።

እስካሁን የ26 ምርጫ ክልሎች ውጤት ገና ለቦርዱ ጽሕፈት ቤት እንዳልደረሰ ገልፀዋል።

በአፋር ክልል 7 እና በአዲስ አበባ 8 ምርጫ ክልሎች ውጤት ካላሳወቁት መካከል ይገኙበታል፡፡

ከላይ ባለው Voice Chat 'Join' በማለት በቀጥታ ማዳመጥ ትችላላችሁ::

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ተጨማሪ #የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶችን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እያሳወቁ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

(ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ/ም)

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በቦታው ተገኝተዋል።

መግለጫውን በVoiceChat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013 አጫጭር መረጃዎች ፦

- ምርጫ ቦርድ የተጠቃለለ የምርጫ ውጤት በዚህ ሳምንት አሳውቃለሁ ብሏል። ከዚህ ቀደም ለቦርዱ ያልደረሱ 30 የምርጫ ውጤቶች አሁን ላይ ተጠቃለው ገብተዋል።

- የቁጫ ምርጫ ክልል የድምጽ ቆጠራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባሉበት በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው።

- ኦሮሚያ ክልል ነገሌ የምርጫ ክልል ድምፅ ባልተሰጠባቸው 30 የምርጫ ጣቢያዎች በቀጣይ ሀሙስ ድምጽ ይሰጣል።

- የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ምርጫ በተወዳደሩበት ኦሮሚያ ክልል ጎማ ቁጥር 2 በሰፊ ድምፅ አሸንፈዋል።

- ዛሬ ይፋ በተደረጉ የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶች የአብኑ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተወዳደሩበት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ምርጫ ክልል ማሸነፋቸው ተገልጿል።

- ከምርጫው ቀን አንስቶ ከቆጠራ እና ድመራ ጋር በተያያዘ በ153 የምርጫ ክልሎች 31 ፓርቲዎች፣ 7 የግል ተወዳዳሪዎች በጽሁፍ፣ ስልክና በSMS አቤቱታ አቅርበዋል። ምርጫ በተካሄደባቸው በሁሉም ክልሎች ቅሬታ ቀርቧል።
• በአማራ ክልል 49 ምርጫ ክልሎች፣
• በደቡብ ክልል 40 ምርጫ ክልሎች
• በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ምርጫ ክልሎች
• በአፋር ክልል በ21 ምርጫ ክልሎች በርካታ ቅሬታ የቀረቡባቸው ናቸው።

#SolainaShimeles #NEBE

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በዛሬው ዕለት በነገሌ ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ዕጩዎች ምርጫ እየተካሄደ ነው።

ምርጫው ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ ነው እየተካሄደ ሚገኘው።

ለምርጫው ከ150 በላይ ታዛቢዎችና የምርጫ አስፈጻሚዎች መመደባቸውን ተገልጿል።

በምርጫ ክልሉ ለሁለቱም ምክር ቤቶች ሁለት በግል፣ አንድ ከኢዜማ እንዲሁም አራት ከብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎች ለውድድር ቀርበዋል። #ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከ20 ደቂቃ በኃላ የምርጫውን ውጤት ይፋ ያደርጋል። NB : ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች ምርጫ ቦርድ ውጤት በሚያሳውቅበት ሰዓት የ"Voice Chat" ዳግም የሚጀምር ይሆናል። @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ከ20 ደቂቃ በኋላ ይጀምራል ተብሎ የነበረው የምርጫ 2013 ውጤት መግለጽ መርኃግብር መዘግየት ገጥሞታል።

ምክንያቱን ለማወቅ ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

በአሁን ሰዓት የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአዳራሹ ተገኝተዋል።

የውጤት ማሳወቁ ሂደት ተጀምሯል። ከላይ በ Voice Chat ያዳምጡ።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በምርጫ ላይ 2013 በምርጫ አስፈፃሚነት ሀገራቸውን ያገለገሉ ዜጎች ክፍያ እንደዘገየባቸው ጠቁመዋል።

የምርጫ አስፈፃሚዎች " ክፍያ ዘገየብን ፤ ለመዘግየቱ ምክንያት ምንድነው ? መቼ ነውስ ክፍያው የሚፈፀምልን ?" ሲሉ ጥያቄያቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ምላሽ የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽ አማካሪ የሆኑት ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ክፍያው የዘገየው ፥
- ንብረት ርክክብ መጠናቀቅ ስላለበት፣
- የበጀት መዝጊያ ስለሆነም መልሶ መከፈት ስላለበት፣
- የመጨረሻው ክፍያ ስለሆነ
- በድምፅ መስጫ ቀን ሰው ስለተጨመረ ቁጥሩ ብዙ በመሆኑ ነው ብለዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና ፥ የምርጫ አስፈፃሚዎች ክፍያ እንደተለመደው እንደሚከፈል የገለፁልን ሲሆን መታገስ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛውን አጠቃላይ ምርጫን በዋናነት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ማስፈፀሙ ይታወሳል።

- በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ በታዪ ጉልህ ግድፈቶች፣
- በመራጮች ምዝገባ ላይ በቀረቡ አቤቱታዎችን ለማጣራት ጊዜ በማስፈለጉ
- ከጸጥታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የተነሳ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድምፅ አሰጣጥ ያልተደረገባቸው ቦታዎች እንዳሉ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ ቀሪ ምርጫ ያልተከናወነባቸው የምርጫ ክልሎችን፣ የምርጫው ሂደት ያለበትን ሁኔታ እና የመሳሰሉትን በመገምገም ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

* ውሳኔዎቹን ከላይ በተያያዘው ምስል ያንብቡ።

@tikvahethiopia