الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22K subscribers
372 photos
17 videos
7 files
913 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
የሩቅያ አንቀፆች👆

   በመልካም ዱዓቹህ አትርሱን!! 

ሃሳብና አስተያየታችሁን በዚህ አድርሱኝ

@jezakellah @jezakellah

Join us on telegram channel
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
💍:::::::በጋብቻ ለሊት::::::::💍

በጋብቻ ለሊት የሚፈፀሙ ተግባሮች📌

1፡- ባገባህበት ወቅት የምታደርገው ድንቅ ዱዓ..👇
“አላሁመ ኢኒ_አስአሉከ ኸይረሃ ወኸይረ ማ ጀበልተሃ ዓለይሂ ወአኡዙ ቢከ ሚን ሸሪሃ ወሸሪ ማ ጀበልተሃ አልይሂ

አላህ ሆይ! እኔ የዝችን ሴት መልካም ጎን እና እንድታዘነብል ያመላከትካትን በጎ ነገር እጠይቀሃለሁ፤ ከተንኮሏና ካዘነበለችበት መጥፎ ነገር ባንተ እጠበቃለሁ)፡፡”

2፡- የሰርግህን ቀን ዉሎ ካሳለፍክ በኋላ ምሽት ላይ ሚስትህ ጋር አንድ ላይ ስትሆኑ ብቸኝነት ይሰማታል፣ ፍርሀት ይወራታል፣ሀፍረት ይሰማታልና አጫውታት፣ ዘና አድርጋት!

3፡- ረከዓተይን አሰግዳት፡፡ ይህ ሶላት ባል የቤቱ አባወራና አስተዳዳሪ እንዲሁም ጠባቂ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በተጨማሪም ሁለታችሁም በዛ ለሊት ፍርሃት እንዳይሰማችሁና ለወደፊት የትዳር ህይወታችሁ መሳካት ጥሩ አስተዋፅኡ አለው፡፡

4፡- ወተት አጠጣት (ይህ ለርሷ መረጋጋትን ያደርግላታል)፡፡ صلى الله عليه وسلم አንድ ባል ሚስቱ ጋር ከመገናኘቱ በፊት ወተት እንዲያጠጣት መክረዋል፡፡

5፡- ራሷን(ግንባሯን) ይዘህ የሚከተለውን ዱዓ አድርግ👇👇👇

ቢስሚላህ አላሁመ ጀንኒብነ ሸየጧነ ወጀንኒብነ ሸይጧኒ ማ ረዘቅተና

በአላህ ስም! አላህ ሆይ! ሰይጣንን አርቅልን፤ያበረከትክልንን ነገርም ከሸይጧን አርቅልን)”

#እርሷም ግንባርህን ይዛ ይህን ዱዓ ታሰማለች፡፡ ይህ ዱዓ ለወደፊት የትዳር ህይወታህ መቃናት፣ የምትወልዷቸው ልጆች ከሸይጧን እንዲጠበቁና መልካም ልጆች እንዲሆኑ ይረዳል፡፡ትዳሩ ያማረና የሰከነ እንዲሆንም ያግዛል፡፡

ይህ የተወዳጁ # صلى الله عليه وسلم ሱና ነው፡፡ ባረከሏሁ ፊኩም

ይህ መልዕክት እርሶ ጋ አይቀመጥ ለሌሎች ሼር በማድረግ የአጅር ተካፍይ ይሁኑ👆

💍::::::::ቴሌግራማችን::::::::💍

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
Forwarded from ❥ አልሀምዱሊላህ ❥
‏﷽
۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى
النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا
عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ ﷺ

💍::::::::ቴሌግራማችን::::::::💍

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
 👉 ፍቅረኛ መያዝ ከሚያመጡብን መዘዞች

ክፍል አንድ👇

የቦይ-ገርልፍሬንድ ግንኙነት ከኢስላም አንፃር ሁለመናው ይፋ የወጣ ዝሙት ከመሆኑም በላይ አታላይነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ በርካታ ወንዶችና ሴቶች ወደፊት እንጋባለን በሚል መንፈስ ይህንን ግንኙነት ይጀምሩና ግንኙነታቸው በጠለቀ ቁጥር ወደ ወሲብ ይገባሉ፡፡ አንዴ ዝሙት ላይ ከወደቁ ደግሞ የመጋባትም ሆነ የወደፊት የትዳር ሕይወታቸው በብዙ መልኩ ይቀንሳል፡፡ በዚህም ዓይነት በሕገወጥ ወሲብ ውስጥ ተዘፍቀው ጊዜያቸውን በወንጀል ላይ ያሳልፉና ከዚያም በአሳዛኝ ሁኔታ ሳይጋቡ ግንኙነታቸው ከፍፃሜ ይደርሳል፡፡


    🍁🍁🍁🍁🍂🍂🍂🍂🍁🍁🍁🍁

  
  Please👉 ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
    ቢያንስ ለ10 ጓደኞቻችሁ ፎርዋርድ አድርጉ


Join us on telegram
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
❥::::::ሷሊህ ጥሩ የሆነች ሚስት:::::❥

☞❥ሚስት የባሏን  ➷ደግነቱ መልካምነቱን ጥሩነቱን ከመካድ ልትጠነቀቅ ይገባታል።

❥ ☞በሷም ላይ ➷ግዴታ አለባት በጥሩነቱ በመልካምነቱ  በለጋስነቱ  እሱን በማመስገን ላይ በሚውልላት ጥሩ ባህሪ ሁሉ  ማመስገን አለባት 👌

☞በዚህ ላይም ችልተኛ ልትሆን አይገባትም

❥የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል እና
☞☞ባሏን የማታመሰግን ➷ሴት አላህ ❥ በእዝነት አይኑ አይመለከታትም ።

📚((صححه الألباني))

☞ባልሽን ማመስገንሽ እሱን ማስደሰትሽ ለሱ ጥሩ ሚስት ➷በመሆንሽ እሱን ብቻ ሳይሆን ጌታሽንም ጭምር እንደምታስደስች አትዘንጊ።

☞❥እሱን ማስከፋትሽ እና እሱን ☞ከማመስገን ችልተኛ እሱ ላች ☞እሚውልልሽን ውለታ አሳንሰሽ ማየትሽ ሁሌም ሰላም እምትነሽው እምትረብሽው።
ለመቆጣትም ሰበብ ከሆንሽው እሱን ብቻ ሳይሆን ጌታሽንም ጭምር እንዳስቆጣሽ አትዘጊ

☞ሁልጊዜ አላህ ባች ላይ የባል ሀቅ  ያስቀመጠልሽን  ተዋጭ ግዴታሽን ☞ከመታዘዝ በላይ የታዘዝሽውን
ከመተግበር በላይ ምን አለና እህቴ ።

#ሼር_በማድረግ ያስተላልፉ

💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
 👉 ፍቅረኛ መያዝ ከሚያመጡብን መዘዞች

ክፍል ሁለት👇

ሁለቱም ወንድና ሴት በርካታ ዓመታትን በቦይ-ገርልፍሬንድነት አብረው ከቆዩ ወሲብ ባያደርጉ እንኳን ለመጋባት ያላቸው ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ቀስ በቀስ እየጠፋ ይሄዳል፡፡ ጥልቅ ጓደኝነታቸው እየቀዘቀዘ ይመጣል፡፡ ከዚያም በኋላ ልክ በመስመር ላይ እንደተገናኙ ሰዎች ይሆናሉ፡፡ ወደ ትዳር ዓለም ቢገቡም ተራ ሕይወትን የሚመሩ ይሆናሉ፡፡ ከዚያም ትዳር ወሲብ ብቻ ስላልሆነ ለመፋታት ሰፊ ዕድል ይኖራቸዋል፡፡ 
ምክንያቱም አላህ(ሱብሃነ ወተዓላ)በሃላል ለሚጋቡት እንጂ በሃራም ለሚገናኙት አይደለም መዋደድና መተዛዘንን እንደሚያደርግ ቃል የገባው። እናም በሃራም ያሉበት ስሜት የውሸት ፍቅርና ሸይጧን ወደ ዚና ለማስገባት የሚያጠምድበት መንገድ ነው። ከዚህ የሸይጧን ወጥመድ አላህ ይጠብቀን!
   እንመለስ ወደ አላህ አላህ ይባርካችሁ
   🍁🍁🍁🍁🌺 🌸 🌼🍁🍁🍁🍁

  Please👉 ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
    ቢያንስ ለ10 ጓደኞቻችሁ ፎርዋርድ አድርጉ

ከዚህ ለመውጣት ከአለሰህ በታች እገዛ ለሚያስፈክጋችሁ ወይም በዚህ ጉዳይ ጥያቄ ካላችሁ መመካከር እ ችላለን ሚስጥራችሁ የተጠበቀ ነው።
👉 @jezakellah

Join us on telegram
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
❥:::::::::በትዳር ዉስጥ::::::::❥

አንዲት ሴት ባል አግብታ ከባልዋ እናት ጋር ትኖር ነበር. በአጭር ግዜውስጥ የባልየው እናት እና ሚስትዮው በሆነው ባልሆነው መጣላት ጀመሩ.
በሀገሪቱ ህግ መሰረት ደግሞ ማነኛዋም ሚስት ለ ባልዋ እናት የመታዘዝ እና የመገዛት ግዴታ አለባት. የባልየው እናትየባህል አጋጣሚ ተጠቅመው ያስቃይዋት ጀመሩ. በዚ ምክንያትም ባልየው ስላም አጣ እቤታቸውም ሰላም ያጣ ሆነ. ይሄንን መቃቃም ያቃታት ሚስትም የባህል መድሃኒት የሚሸጥ የአባትዋ ጋደኛ ጋር እርዳታ ፍለጋ ሄደች.

የለችበትን ከባድ ሁኔታ አስረድታም መርዝ እንዲስጣት እናስትሞት ካለችበት ስቃይ እንዲገላግላት እያለቀሰች ለመነቺው.
ሰውየውም ካዳመጣት ቦሃላ ስላሳዘነቺው ሊረዳት ፍቃደኛ ሆነ. ´እንዲህም አላት´ የባልሽ እናት ሰው እንዳይጠረጥር መድሃኒቱ ከረጂም ግዜ ቦሃላ ነው ሚገላት. ´በነዚ ወራቶች ውስጥ አንቺ ጥሩ ጥሩ ምግብ እያበስልሽ እዛ ውስጥ እየጨመርሽ ስጫት, የፈለገችውን እርጊላት ታዘዥያት እንደ እናትሽ ተንከባክብያት. ቁታሽንምእናትዋ ተቆጣጣሪ ብሎ እስጠንቅቆ መክራት, ሳምንታት አለፉ ሚስትየውም ጥሩ ምግብ ማብሰል እና እንደ መንከባከብ ጀመረች, ባለ መድኃኒቱ ሰውየ ያላትን እያስታወስች ንዴትዋን መቆጣጠር ቻለች, በሆነው ባልሆነው መቆጣትም አቆመች .የባልየው እናትም።

ለሚስትየው ያላቸው አመለካከት ተቀይሮ እንደልጃቸው ማየት ጀመሩ. ለጋደኘቻቸውን እና ለዘመዶቻቸው ጥሩ ምራት እንደ አገኙ መናገር ጀመሩ ለ 7 ወራትም እቤታቸው በፍጹም ደስታ ተሞልቶ አለፈ. አንድ ቀን ሚስትዮ ባለ መድኃኒት ሰውየው ጋር ሂዳ እንደ መጀመሪያ ግዜው እያለቀሰች መርዙን ማክሸፍያ መድኃኒት እንዲሰጣት ለመነቺው እንዲህም አለቺው"

የባሌ እናት እኔ እንዳሰብካት ሴት አልነበረችም ልክ እንደልጅዋ ነው ምታየኝ አሁን በጣም ተቀይራለች እንድትሞትብኝ አልፈልግም ታስፈልገኛለች" መድኃኒት ቀማሚው እንዲህ አላት" ምንም የማያሳስብሽ ነገር የለም የሰጠሁሽ መርዝ ሳይሆን ጤናዋን የሚያሻሽል ቢታሚን ነው, መርዙ ያለው አእምሮሽ ውስጥ ነበር እሱም በስጠሻት ፍቅር ከሽፍዋል አላት.
ጥላቻን #ፍቅር ነው ሚያሸንፈው, ለፍቅር ደግሞ መስዋዕት መክፈል እድለኝነት ነው አላት።..👌

ከፁሁፉ መልካም ነገር እንደተረዳቹ ተስፍ አለኝ ። በዚዉ አጋጣሚ እህቶቼ ለባሏቻቹ እናት መልካም ሰዉ እና መልካም ፍቅር እድኖራቹ መልክቴን መስተላለፍ እወደለዉ። بارك الله فيكم

#ሼር በማድረግ አስተላልፉ


💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
Audio
ትዳር የዲን ግማሽ ነው ይባላል ስለዚህ ሳያገባ የሞተ ሰው የዲኑን ግማሽ ያጣልን

በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
❥::::::::::::ትዳር በኢስላም:::::::::❥

#በሸሪያ ሴት ልጅን ማግባት በእድሜ አይደለም እድሜዋ ስላነስ አትመረጥም እንዲሁምም እድሜዋ ስለገፋም አትተውም።

ሴት ልጅ የምት መረጠው በዲኗ ነው። ለዚህም በአቡ ሁረይራ {ረዲየላሁ ዓንሁ} የተተላለፈዉን ሀዲስ እንመልከት፦

የአላህ መልዕክተኛ {ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም} እንዲህ ይላሉ፦ ሴት ልጅ ለአራት ነገራቶች ትታጫለች
1↝ለመልኳ
2↝ለገንዘቧ
3↝ለዘሯና
4↝ለዲኗ
ዲን ያላትን ያልመረጠ እጁ አመድ ይፈስ ብለዋል።

💍::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
"ሴት ልጅ ትክክለኛውን ደስታ
የምታገኘው ቤት ውስጥ ስትሆን ነው"

በኢስላም፦ ሴት ልጅ ያለ በቂ ምክንያት ከቤት እንዳትወጣ የወጣችም እንደሆነ ከባእድ ወንዶች ጋር እንዳትቀላቀል የማይፈቀድላት ወንዶችንም አትኩራ ከመመልከት ዓይኗን ሰበር ታድርግ " መባሉ
ሴትን መበደልና ነፃነቷንም መግፈፍ ነው የሚሉ አሉ!
ታድያ ጀነት ውስጥም ነፃነት የለም ማለት ነው! ?
( فِيهِنَّ قَاصِرَاتُ الطَّرْف لَمْ يَطْمِثْهُنَّ إِنْسٌ قَبْلَهُمْ وَلَا جَانٌّ )
[ጀነት ውስጥ ከባሎቻቸው በፊት ሰውም ይሁን ጂን ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን ባሎቻቸው ላይ ያሳጠሩ የገደቡ ፣ሴቶች አሉ] አርረሕማን 56
( (حُورٌ مَقْصُورَاتٌ فِي الْخِيَامِ)
[ ጀነት ውስጥ ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች ሴቶች አሉ ከዕንቁ በተሰሩ ድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ < የተገደቡ መውጣት የማይፈልጉ ናቸው የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣትም ደማቅ የኾኑ ናቸው] አርረሕማን 71 / 73
~ እህቴ ሆይ አትታለይ ላንቺ የሚበጀውን ከማንም በላይ አሏህ ነው የሚያውቀው አስተሳሰብሽን አስተካክይ!

💍::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
⇨ምናልባት አንዳንድ ጊዜ የአላህ ፈቃድ
ፍላጎትህ ላይ ተቃራኒ ሊሆን ይችላል,

ነገር ግን ከታገስክ የአላህ ምርጫ ላንተ
የበለጠና የተሻለ እንደሆነ ትረዳለህ።
ስለዚህ ለማጋጥምህ ፈተና ሁሉ ሶብር
አድርግ።ኢንሻአላህ የተሻለዉን ትወፈቃለህ እና። #ሼር

💍::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
☞  ጥሩ ሕይወትን ለመምራት☜

ጥሩ ሕይወትን ለመምራት የሚረዱ 10 መርህዎች
1 )ሰውን አትጥላ ልብህን ንፁሕ አድርግ።
2 አትጨነቅ በአላህ ተመካ
3)ቀለል ያለ ኑሮ ኑር

4) ባለህ ነገር ተደሰት በተሰጠህ ነገር አመስጋኝ ሁን።
5 )ብዙ በሰጠህ ቁጥር ብዙ ታገኛለህ።

6) ፈገግታ አብዛ ፈገግታ ሰደቃ ነው።
7) በፍቅር ኑር ለአላህ ብለህ ውደድ።
8) ዱዓን አብዛ ብዙ ዱዓ ባደርክ ቁጥር፤በረካን ታገኛለህ።

9)  እውቀትህን ለሌሎች አካፍል አንድ የቁርአን አንቀጽም እንኳን ብትሆን።
10). አላህን በብዛአስታውስ፤ልብህ እርጋታን ታገኛለች አላህ ያግራልን!!!
#ሼር_አድርጉ
💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
❥...ባልሽ ካንቺ ሚፈልጋቸው ነገሮች..❥

1☞, በይፋም ሆነ በድብቅ አላህን በቅን ልቦና መታዘዝ አላህ ከሰዎች ጋር ያለንን ሁኔታ እንዲያሰተካክል እኛ ከአላህ ጋር ያለንን ሁኔታ እናስተካክል

2,☞ እሱ በሌለበት ራስሽን፣ንብረቱን፣ልጁቹንና ቤቱን ተንከባከቢ

3, ☞ሲመለከትሽ የተዋብሽ ሁኚ፣ሲያወራሽ አስተሳሰብሽን ቅን አድርጊ፣ፈገግታ ልመጂ

4,☞የትም ስትሄጂ ፍቃድ ጠይቂ፣ባደረገልሽ ነገር አመሰግኚ፣እሱን አንዳች ነገር ለመጠየቅ ስትፈልጊ አመቺ ጊዜ ምረጪ

5,☞ከቤት ስትወጪ ሂጃብሽን ጠብቂ፣በችግሮ ጊዜ ታገሺ፣በፀጋ ጊዜ አታባክኚ፣ከውሸት ተጠበቂ፣ከንዴት ብስጭት ለመራቅ ሞክሪ

6,☞ከኩራትና ራስወዳድ ከመሆን ተቆጠቢ፣እዚህች አለም ብቻ ሳይሆን በቀጣዩም አለም የማረ ህይወት እንዲገጥመሽ በኢባዳሽ በርቺ

7,☞ከአላህ ተሰፍ ማትቆርጥ ጠንካራ ሁኚ፣አንቺ ከእሱ ላይ ካለሽ ሃቅ እሱ ባንቺ ላይ ያለው ሃቅ በላጭ መሆኑን የተረዳች ሁኚ

8,☞ስህተትሽን አትካጂ፣ካጠፍሽ ይቅርታን ልመጂ፣ዚክር አብዢ፣ከእሱ በኩል ማገኘት የፈለግሺውን አቅም በፈቀደ መልኩ ጠይቂ

9☞,ባለቤትሽ አጠገብ ሌሎች ሴቶች ከማድነቅ ተቆጠቢ፣የእሱን ፍላጎት ሁሌም አስቀድሚ

10,☞በህሪውን ተረጂ፣በኢባዳ አበርቺው፣አይዞህ በይው።
#ሼር

💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
"በዚች ምድር ላይ እንደ ረሱል ﷺ ያፈቀረ እንደሳቸውም የተፈቀረ የለም። ወደፊትም አይኖርም!🌹
ሰሉ አለ ነቢ አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ነቢይና ሙሀመድﷺ🌹👌

መልካም ጁምዓ
💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
☞::::ፍቅር_በኢስላም::::☜

💍ጋብቻ በኢስላም ልዩ ትኩረት ከተቸራቸው ማህበራዊ ጉዳዮች አንዱ ነው። ጋብቻ ኢስላም ከሰጣቸው እና ካበረታታቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። የነብያት ፈለግም ነው።

《•ኢስላም ለትዳር ድንጋጌና ስርአትን በመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶታል። የባለ ትዳሮች መብት መከበር የጋብቻው ግንኙነት እንዲያጎለብትና እንዲረጋ ያደርጋል። በመንፈስ የተረጋጋ፤ በእምነቱ የፀና ፣ በሁሉም የማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይሰጣል።

《•በጋብቻ ሰንሰለት የተቆራኘ ፍቅር አንድም ለስሜት አንድም የአምልኮ ዋጋ ያለው ነው። ከወንጀልም መጠበቂያ ነው። የረሡል ﷺ ሱና ነው።

《•የአላህን ዉዴታ በመሻት በምትለግሰው ምፅዋት ምንዳ ታገኛለህ ሌላው ቀርቶ ለባለቤትህ በምታጎርሳት ጉርሻ እንኳ ምንዳ አለህ አንቺም ምንዳ አለሽ።

《•አልሃምዱሊላህ ከኢስላማዊ ድንጋጌዎች መካከል ኢስላም ለአንድ ጋብቻ ትክክለኛነት በባልም ሆነ በሚስት በኩል የግድ ሊሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን አስቀምጧል። በሀይማኖቷና በባህሪዋ ጠንካራዋን እንድንመርጥ ይመክራል።

《•ምክኒያቱም ወደፊት ለልጆችህ እናትና ተንከባካቢ፣ ለአንተ ደግሞ በመልካም ነገር ላይ የምታግዝህና የምታጠናክርህ በመሆኗ ነው።



《• ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ባለ ሀይማኖቷን (ዲን ያላትን) ምረጥ አለያ እጅህ አመድ አፋሽ ትሆናለች። (አል ቡኻሪ 4802 /ሙስሊም 1466)

《• ባለቤትህ ጥብቅና ጨዋ መሆን አለባት። በዝሙትና በእንዝላልነት የምትታወቅ ሴትን ማግባት ክልክል ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ይላል፦ ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ (ተፈቀዱላችሁ) አል ማኢዳህ 5፡5

《•ለዘላለሙ ሊያገባቸው እርም ከተደረጉ መሀሪሞች መካከል መሆን የለባትም። አንዲት ሴትን ከእህቷ ወይም ከአክስቶቿ ማለትም ከአባቷ እህት ወይም ከእናቷ እህት ጋር በአንድ ላይ ማግባት አይፈቀድለትም።

《•በጣምራዎች መካከል ፍቅር ሳይኖር ሳይዋደዱ አይሆንም በጭራሽ ፍቅር አንዱ ህይወታችን ነው። ሁሉመ ሰው ወደርሱ ይሮጣል ምድርን በሙሉ በቀኝም በግራ ፍቅርን ይፈልጋል። የሚወደውን ሲያጣ በጣም ያዝናል። አላህ ﷻ ይወደናል ፣ ይጠብቀናል፣ ይምረናል፣ ምንም ጥላቻ የሌለበት ላጣኸው ነገር አትዘን /አትዘኝ/ አላህ ማንንም አይበድልም።

《• ረሡል ﷺ አንዲት ሴት የምታጠባው ልጅ እሳት ላይ እንዲወረወር ትፈልጋለችን?አሉ "ላ ላ ላ" ያረሡለሏህ ሲሏቸው አላህ ከዛም በላይ አዛኝ ነው። አሉ

《•የምትወዱትን ስታጡ አላህን አመስግኑ ለበጎ ነው። የሰው ልጅ ሀብታም፣ ደሃ፣ የተማረ፣ መሀይም..አለ ሁሉም ፍቅር ፈላጊ ነው።

《• ፍቅር የሰው ልጅ ሲከተለው እንደ ኳስ የሚንከባለል ይመስላል ፣ተስፋ እንቆርጣለን። ፍቅር አይንከባለልም የሚንከባለለው የሰው ልጅ ነው። የወደደ፣ ያፈቀረ፣ ጆሮው ሰምቶ ደንቆሮ ፣አይኑ አይቶ እውር ይሆናል፤ ፍቅር ሳይሆን እውሩ የሰው ልጅ ሲያፈቅር ባፈቀረው ሰው ምክኒያት የፈረደበት ደካማ ጎን ነው።

《• ምክኒያቱም፦ የሰው ልጅ ከፍተኛ ቦታ ለፍቅር ስለሚሰጥ። ወንድ ልጅ በፍቅር ምክኒያት ትንሽ ሊለዝብ ይችላል ሴት ልጅ ግን መለዘብ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ አቋሟን ለእርሡ ብላ ትለውጣለች።

《• ሴት ልጅ ትዳሯን ቤቷን እንደ ቤተ መንግስት ነው የምታየው። ሴት ልጅ ሹመት ቢሰጣት አንድ ወንድ የሚያፈቅራትን ያክል ክብርና ኩራት አይሰማትም። ሴት ልጅ እውነተኛ ፍቅር ከያዛት ከልብ የሚያፈቅራት ወንድ ካገኘች ቤተ መንግሥት ውስጥ አለምን ከሚመራው ንጉስ የበለጠ ደስታ ይሰማታል።

ወንድ ልጅ ፍቅር በአይኑ ይገባዋል። ይህ ማለት ወንድ ልጅ ባገኘው አጋጣሚ፣ የተዋበች ቆንጆ ልጅ ሊያፈቅር ይችላል። በውበትም በአልባሳትም፣ በብልጭልጭ ነገሮች ላይ ሁሉ አይኑ ያርፋል

《• ሴት ደግሞ በጆሮዋ ነው ፍቅር የሚገባት ጥሩ ነገር የሚያወራትን፣ ባገኘው አጋጣሚ ፍቅሩን የሚገልፅላትን፣ ሲያስከፋት ይቅርታ የሚጠይቃትን ስጦታ (ሲዋክ ) እንኳ ቢሆን የሚገዛላትን እና ደግሞ ስታወራው በቁም ነገር የሚያዳምጣትን፣ ባታወራው እንኳ ፊቷን አይቶ መከፋቷን የሚረዳት ችግሯን ሳታወራው የሚፈታላት ትወዳለች።

《• ወንድ ልጅ አቀባበልን ይወዳል። ከውጭ ሲመጣ #ተኳኩላ_ምግብ_ሰርታ ማታ ከሆነ ልጆቿን አስተኝታ የምትጠብቀውን ሴት ይወዳል።

《•ባል እና ሚስት ከተሳካ የሚዋደዱ ቢሆኑ ይመረጣል። ግን እንደ እድል ሆኖ ባል እና ሚስት ሁሉም ባይሆን ብዙዎቹ የሚዋደዱ (የሚፋቀሩ) አይደሉም። ነገር ግን ትዳር በራሱ የራሱ ህግ ስላለው ተከባብረው ተደማምጠው ብዙ ልጆች ወልደው አብረው አርጅተው ይሞታሉ።

《• ትዳር የብዙዎች ፍላጎት ቢሆንም ለጥቂቶች ብቻ ነው የሚሳካው። አንዲት እንግሊዎት የመንግስት ልጅ ነበረች። ከአባቷ በጣም ብዙ ንብረት ወረሰች፣ እርሷ ግን ገንዘቧን አስቀምጣ ደሃ አገባች። አንድ ድሀ የሆነ በዜግነቱ ህንዳዊ አገባች። እቤቱ ወሰዳት ግን የምትፈልገውን ፍቅር አላገኘችም ተፈታች። ከዛም በኋላ እንግሊዛዋ ዶክተር አገባች ተፈታች። ፈረንሳዊ አገባች ተፈታች። ብዙ ባል አገባች ተፈታች። #በመጨረሻ_ግን_በጣም_ጥሩ_ትዳር_አገኘች ወለደች።

《•ከዛ አንቺ እጅግ በጣም ሀብታም ነሽ ለምንድን ነበር እያገባሽ የምትፈችው በማለት ተጠየቀች። እሷም ጥሩ ህይወት እና የሚወደኝ እና የምወደው ባል ፈልጌ ነው አለች። የሚያግዘኝን የሚመቸኝን እየፈለግኩ ትዳር በገንዘብ ብዛት አይሳካም መተጋገዝን ፍቅርን ይጠይቃል።

《• ከሚወድሽ ወይም ከሚወድህ ሰው ጋር መኖር እረፍት ነው። ከደስታ ሁሉ ደስታ ከሚወዱት ጋር መኖር ነው። ለብዙዎች ባይሳካም ተስፋ አትቁረጡ ብዙ የለፉበት ነገር ትርፍ አለው።

#አንዳንድ_ሰዎች_መፍትሄውን እጃቸው ላይ አስቀምጠው እየረዱህ እንደሆነ ለማስመሰል ይጥራሉ።

#ለአንተ የሚያስፈልግህን ወሳኝ ነገር ከመስጠት ይልቅ ስትጣጣር ትንሽ ጥቅም ያለው ነገር ይመርጣሉ።

#በቀላሉ ማዳን እየቻሉ በቀላሉ ያጠፉሀል።

#ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ስትጣጣር ከማገዝ ይልቅ "አብሽር አይዞህ" እያሉ ምንም ሳያግዙህ አቅምህን ያስጨርሡሀል።

《• በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ስትሆን አላህን አስታውስ እርሡ አላህ በጥቁር ጨለማ፣ በጥቁር ድንጋይ ላይ የምትራመድን ጥቁር #ጉንዳን_የእርምጃዋን_ኮቴ_የሚሰማ ታላቅ ጌታ ነውና! እርሱን ለምን (ተማፀን) በእርሡም ተመካ!

💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
☞ከአማኞች ሁሉ ምርጡ •ስነምግባሩ ጥሩው እና •ለባለቤቱም መልካም የሆነው ነው
#ረሱልﷺ🌹

💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَىٰ ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا
ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ!

(ሱራ አል-ኢስራእ 32)

ዝሙትን አትስሩት ብቻ አይደለም አሏሁ ታኣላ ያለው አትቅረቡት ነው!!!

ወጣት ሆይ አስተንትን አስተንትኚ
አላህ ሁላችንንም ይጠብቀን.አሚን🤲

💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃