الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
21.8K subscribers
374 photos
17 videos
7 files
913 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::::::☜   ክፍል አስር/⑩    #ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ 3/#የሴቶች_ቁጥር_በእጅጉ_መጨመር_እና       #በአንፃሩ_የወንዶች_ቁጥር_መቀነስ   በአለም ላይ በተደረገው ጥናት እና ቆጠራ በየክፍለ ዘመኑ ያሉ ወንዶች በቁጥር እጅግ አናሳ ሲሆን የሴቶች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ነው።ይህም የሚሆንበት የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ የተወሰኑትን ለናሙና ያክል…
☞:::ትዳር በኢስላም :::☜

 
#ክፍል
...ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ
6#አንዳንድ_ወንዶች_በተፈጥሯቸው_የፆታዊ_
ፍላጎት_ጅማዕ_አቅም_ከፍተኛ_መሆን ይህ ከፍተኛ ሸህዋ ያለው ወንድ አንዲት ሴት ብቻ ትብቃህ ቢባል ከሁለት ነገሮች አንዱ  መከሰቱ አይቀሬ ነው።በአንድ በኩል ሴቷን ከአቅም በላይ ለሆነ ጉዳት ሊያጋልጣት ሲቺል ብሎም የእድሜ ልክ ታማሚም አድርጎ ሊጥላት ይችላል።በሌላ በኩል ይህ ሰው ይቺ አንድ ሚስት የማትበቃው ከሆነ እና ሁለተኛ ሚስት ማግባት ያልተፈደቀ ከሆነ አማራጩ አንድና አንድ ነው።እሱም ዲኑና ዱኒያውን የሚያበላሽበትን ፣የሚስቱን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥልበትን አስከፊና አጥፊ የሆነውን
#ዝሙትንና_በሀራም_ መንገድ_ስሜቱን_ማርካት ምርጫው ያደርጋል። አላህ ይጠብቀን የምንሰማውና የምንታዘበውም ነገር ይህንን ያረጋገጠ ነው።ከሚስቱ ውጭ በሀራም መንገድ ሲባልግ እጅ ከፍንጅ የተያዘ ወይም ለሰራተኝነት የያዛት ሴት ላይ ሀራም የሚፈፅም ወይም በሹክሹክታ የሚታማ ሰዎች ዘንድ ቁጥብ መስሎ የሚቀርብ ማንነቱን አዋቂው አላህ ብቻ ነው።በተለይማ ሚስቱ አቅመ ደካማ ወይም ረጅም የወር አበባ የምታይ ወይም ራስ በራስ የምትወልድ ከሆነች እና ለረጅም ጊዜ በወሊድ ደም ላይ የምትቆይ ከሆነች ይህ ሰው ስሜቱ ተቋቁሞ ማለፍ ለእርሱ ከባድ ፈተና ነው። አንዳንድ ጊዜ ካላገቡት ወንዶች የበለጠ በሸህዋ የሚሰቃይ ሊሆን ይችላል።እንደነዚህ አይነቶችን ችግሮች ለመፍታት ሲባል ሁሉን አዋቂ የሆነው አላህ ለሰው ልጆች በዝሙት መንገድ ራሳቸውን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ፈቀደ።
#ሙስሊሟ_እህቴ_ሆይ„ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ትንሽ ምክር ልለግስሽ ወደድኩ፣ የባልሽን ሁኔታ እና ማንነት መገንዘብ ብዙ ይከብድሻል ብዬ አላስብም ባልሽ በአንቺ #በቂ_እርካታ አላገኘም ብለሽ የምታስቢ ከሆነ ጉዳዩ በደንብ ሊያሳስብሽ ይገባል።ከዚህ ቀጥሎ የሚመጣው ነገር ሊያስፈራሽ ይገባል። በመጀመሪያ ባልሽን ለማርካትና ለማስደሰት ባልሽ የሚፈልጋትን ሴት ለመሆን ሞክሪ። ይህን አልፎ በቂ እርካታ የማያገኝ ከሆነ በአንቺ አነሳሽነት ከባልሽ ጋረወ በግልፅ ለመወያየት ሞክሪ ፣የሚፈልገውን ተረጂው ፣ስሜቱን እንዲደብቅሽ አታድርጊ፣የማትረጂው ከሆነ ባልሽ ከአንቺ እየራቀ ሌሎችን ማየት ይጀምራል። #በዝሙት አስቀያሚ መድረክ ታድሞ የዱኒያውንም የአኼራውንም ህይወቱን ከማበላሸቱ በፊት እንዲሁም ማንነታቸው ከማይታወቁ ሴቶች ጋር ተጨማልቆ የአንቺም የቤትሽም ህልውና አደጋ ላይ ከመውደቁ በፊት ልትነቂ ይገባል።
☞ባልሽን ስሜቱን ተረድተሽ ሁለተኛ የሚያስፈልገው ከሆነ ከአንቺ ጋር ተስማሚ፣ለአንቺም ለባልሽም አሳቢ ለዲኗ ተቆርቋሪ የሆነችውን ሴት እንዲያገባ ምከሪው ብቸኛው መፍትሄ
#የአንቺ_ቅንነት ነው። አንዳንድ ባሎች ሚስቶቻቸውን በግልፅ በስሜት እንደማያረኳቸውና ተጨማሪ ሚስተረ ማግባት እንደሚፈልጉ ሲያወያየረዋቸው በአብዛኞቹ ሚስቶች ላይ ቀናነት አይታይባቸውም።እንደውም #ሁለተኛ_የምታገባ_ከሆነ_እኔን_ፍታኝ የሚል ለመስማት የማያስደስት ንግግር ሲናገሩ ይደመጣሉ።ለእንዲህ አይነቱ ችግር መፋታት መፍትሄ ያመጣል የሚል አስተሳሰብ የለኝም፣ይቺ እህት በዚህ ምክንያት ከዚህኛው ባሏ ብትፋታ ቀጥላ ከምታገባው ባሏ ጋር ለመስማማቷ ምን ዋስትና አላት??ፍቺ ቀላል ነገር አይደለም ምን አልባት ቤተሰብ ተመስርቶ ከሆነ ያን ቤተሰብ አፍርሶ ችግር ላይ መጣል እጅግ ከባድ ሊሆን ይችላል።የሚያሳዝነው አንዳንድ ሙስሊም ተብዬ ሴቶች ከካፊር ሴቶች የወረሱት ነገር ባሎቻቸው በሀላል መንገድ ሁለተኛ ከሚያገባባቸው ከፈለጋት ሴተኛ አዳሪ ጋር እንደፈለገ ቢሆን ደስታውን አይችሉትም።ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!! ይህ በአላህ ዲን አማኝ ከሆነች ሙስሊም ሴተወ አይጠበቅም፣ይህ ለዲን ተቆርቋሪ ከሆነች ሴት ሊሰማ አይገባም። ይህ የሱሀብይ ሴቶችን ፈለግ ከምትከተል ሴት የሚጠበቅ አይደለም።
7#የመጀመሪያዋ_ሚስት_መውለድ_አለመቻልባል የመውለድ ችሎታ እያለው ሚስቱ በተለያየ ምክንያት አለመውለዷ ቢረጋገጥና ባል ልጅ የመውለድ ፍላጎት ቢኖረው በእነዚህ ሁለቱ ባልና ሚስቶች መካከል ሊከሰት የሚችለው ነገር 2 አማራጭ ብቻ ነው።
ሀ/ ልጅ ወልዶ የሰውየው ዘሩ ወደኃላ ቅሪት እንዲኖረው የማትወልደውን ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሚስት ማግባት
ለ/ የመጀመሪያዋን ሚስት ሳይፈታ ሌላ ሁለተኛ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ፣ከእነዚህ ሁለት አማራጮች ሊወጣ አይችልም።ነገር ግን የመጀመሪያውን ተግባራዊ ቢያደርጉት በአመዛኙ የተፈታችው ሴት ባል የማግኘት እድሏ የጠበበ ነው።ምክንያቱም የተፈታች እና መውለድ የማትችል ሴት የሚፈልግ ወንድን ፈልጎ ማግኘት በጣም ከባድ ነው እና በዚህም ምክንያት ይቺ ሴት ፈታኝ የህይወት ውጣ ውረድ ሊገጥማት ይችላል።
ማገናዘብ የሚችሉት አብዛኛዎቹ ሴቶች ያለጥርጥር ሁለተኛውን አማራጭ ይከተላሉ። ምክንያቱም ከሞቀ ቤቷ፣የምትከበርበት ቀዬዋ እና ከሚያስብላትና ከሚንከባከባት ባሏ ትታ ወጥታ ያለተንከባካቢ ሜዳ ላይ መውደቅን አትፈልግም።ለእነዚህ መሰል ጥቅሞች ሲባል ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ተደነገገ።
☞ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ፣የአላህ ተውፊቅ ሳይሆን ቀርቶ አንቺ ልጅ ለመውለድ ካልታደልሽ መውለድ የሚችለው ባልሽን አይዞህ ብለሽ ከጎኑ በመቆም ነገሮችን አመቻችተሽ በዲኗ ጠንካራ በአኽላቋ ምስጉን፣ልጆችን በተርቢያ ልታሳድግ የምትችል ሚስት እንዲያገባ እገዛ አድርጊለት፣ ይህ ታላቅ ተግባር ነው፣በዚህ ስራሽ ከሰው ጥሩ ነገር አትጠብቂ
#አላህ ግን አጅርሽን እጥፍ ድርብ አድርጎ እንደሚከፍልሽ አትጠራጠሪ።
8#ሚስቱ_ለረጅም_ጊዜ_የሚቆይ_ህመም_ታማሚ_የሆነችበት_ወን   የአላህ ውሳኔ ሆኖ ሚስቱ ለረጅም ጊዜ የአልጋ ቁራኛ የሆነችበት ሰው ያለው አማራጭ ከሶስት አንዱ ሊሆን ይችላል።
#አንደኛ_አማራጭ፣ በእድሜ ልኩ እንደሷው ታማሚ ሆኖ ስሜቱን አፍኖ ይዞ ልጅም እንኳን ባይወልድ መካን ሆኖ ዱኒያ በቃኝ ብሎ መኖር ሊሆን ይችላል።ነገር ግን ይህ በአብዛኛው ሰው ካለመኖሩ በተጨማሪ ኢስላም እንደዚህ ያለ ጭፍን ሰው አምላኪነትን ይቃወማል።አንድ ሰው ስለታመመ የሌላው ሰው ህይወት አላህ በማይወደው መንገድ ማበላሸት የተወገዘ ነው። ምክንያቱም የሰው ልጅ ወደዚች ምድር የመጣበት ዋነኛ አላማ አላህ በብቸኝነት መገዛት ነው ፣ህይወቱም ሞቱም እርዱም ስግደቱም ለአላህ ስለሆነ።
#ሁለተኛው_አማራጭ፣ ሚስቱ የረጅም ጊዜ ታማሚ ከሆነች እና ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት ዝሙት ዎች የመውደቅ አደጋ ከተጋረጠበት የታመመች ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሚስት አግብቶ የግሉን ህይወት መምራት ሊሆን ይችላል። ይህን ተግባር አንዳንድ ሰዎች ሊቀበሉት ይችላሉ።ነገር ግን ሌላ አማራጭ የሚኖር ከሆነ አብራው  የኖረችው ሚስቱን አሁን ስለታመመች አሁን መፍታቱ ታላቅ ግፍ ነው።ህ
#ሶስተኛው_አማራጭ፣ የታመመች ሚስቱ በቤቷ እያለች ሌላ ሚስት ፈልጎ በማግባት ሁለቱን በክብር ማስተዳደር ሊሆን ይችላል።ይህ አማራጭ ወደር የሌለው አማራጭ ነው ምክንያቱም ባልም ሚስትንም እኩል ፍትህ ይሰጣል።ባልም ሚስትህ ስለታመመች አብረህ  ተጎሳቆል ብሎ አያስገድድም።ሚስትንም ስለታመመሽና ባልሽን መንከባከብ ስላልቻልሽ ቤቱን ለቀሽ ውጭ ብሎ አያስገድዳትም።
☞ከአንድ በላይ በሸሪዓችን ባይፈቀድ ኖሮ ከላይ ያሳለፍናቸው  አንደኛው ወይም ሁለተኛው አማራጭ ተግባራዊ መሆኑ የሚያጠራጥር አልነበረም።ከአንድ በላይ ባይፈቀድ ኖሮ የዚች ታማሚ ሴት እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም ነገር ግን
#ሀያሉ
ጌታችን ጥበበኛ ስለሆነ ለወንዶች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ፈቀደላቸው።