ስብእናችን @ HUMANITY 🌍
822 subscribers
29 photos
5 videos
5 files
31 links
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ኑ እናንብብ ትልልቅ እውቀቶችን እንጨብጥ
Download Telegram
#የሰንበት_ቅምሻ

ከዕለታት አንድ ቀን ሰራተኞች ቢሮ ሲገቡ ከመግቢያ በሩ ላይ የተጻፈ ማሳሰቢያ ቢጤ ይመለከታሉ።

👉"በካምፓኒው ውስጥ እድገታችሁን ሲያደናቅፍ የነበረው ግለሰብ በትናንትናው ዕለት ስላረፈ በስርዓተ-ቀብሩ ላይ እንድትገኙልን እንጋብዛችኋለን" ይላል።

የስራ ባልደረባቸው ስላረፈ ብዙሃኑ ሰራተኞች አዘኑ።
ዳሩ ግን ቢከፉም ሁሉም ተደነቁ። "ምንም እንኳን ቢሞትም እድገቴን ሲያደናቅፍ የነበረው ሰውዬ ግን ማን ነበር?" ሲሉ አሰቡ። ለማየትም ጓግተው አንድ በአንድ ከሬሳ ሳጥኑ እየቀረቡ ቢመለከቱ ድንገት የሚናገሩት ቃል ጠፋቸው። አልጠበቁም። ሌላ ሰው ጥልቅ ስሜታቸውን የነካ ይመስል ከሬሳ ሳጥኑ አጠገብ ቆመው ፈዘው ዝም አሉ።
የሬሳ ሳጥኑ ከውስጡ መስታውት ቢሆን እንጂ አንዳችም አልነበረውም። ሁሉም ወደ ውስጥ ቢመለከቱ፣ ያዩት የራሳቸውን ምስል ብቻ ነው። ከመስታውቱ አጠገብ አንድ ጥቆማ ሰፍሯል።
👉"ስኬትህን የመገደብ ብቃት ያለው አንድ ግለሰብ አለ። እሱም እራስህ ነህ።"

#ኃያል_ሀሳብ_ኃያል_ውጤት
#ኃያል_የኃያልነታችን_መግለጫ

@temesgen2010 👈 join አድርጉ

#መልካምና_ድንቅ_እለተ_ሰንበት_ይሁንልን
ስኬት ፈፅሞ የመጨረሻ አይደለም፣
ውድቀትም ፈፅሞ አደገኛ አይደለም!


ውድቀት አንድ መልካም ነገር ቢኖረው ለመሞከራችሁ ማረጋገጫ መሆኑ ነው። ትልቅ ስህተት የምትሰሩት፣ ውድቀትን መፍራት ስትጀምሩ ነው። በህይወት ምንም ስህተት የማይሰሩ የማይሰሩ ሰዎች ስህተት ለመስራት እድሉን ያላገኙ ናቸው። እድሉን ያላገኘበት ምክንያትም ለመስራት ሞክረው ባለማወቃቸው ነው።

የራሳችሁን እምቅ ሀይል ፈትኑት። እስከዛሬ ከሰራችሁት የበለጠ ለመስራት ራሳችሁን ጠይቁ። ከራሳችሁ በወላሉ ልታገኟቸው ከምትችሏቸው የላቁ ነገሮችን ለማግኘት ጠብቁ። አሁን ያላችሁ ወይም የተጠቀማችሁበት፣ ሙሉ በሙሉ ያላችሁ (የተጠቀማችሁበት) አይደለም።

የእናንተ እምቅ ሀይል ገደቡ ፈጣሪ ነው ። እምቅ ሀይላችሁን አውጥታችሁ ተጠቀሙበት።

አንድን ነገር ሳይሞክሩ ከመቅረትና ሊያሳኩ የሚችሉትን ነገሮችን ሳያውቁ ከመቅረት ይልቅ ሞክሮ መውደቅ የተሻለ ነው መውደቅ ከተባለም ነገር ግን ውድቀት ለስኬት መወጣጫ መሰላል ነው።

#ኃያል_ሀሳብ_ኃያል_ውጤት
#ኃያል_የኃያልነታችን_መግለጫ


https://www.facebook.com/HayalETH01/ 👈 join አድርጉ

@temesgen2010 👈 join አድርጉ

#መልካምና_ድንቅ_እለተ_ረቡዕ_ይሁንልን