ስብእናችን @ HUMANITY 🌍
822 subscribers
29 photos
5 videos
5 files
31 links
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ኑ እናንብብ ትልልቅ እውቀቶችን እንጨብጥ
Download Telegram
#የሰንበት_ቅምሻ

ከዕለታት አንድ ቀን ሰራተኞች ቢሮ ሲገቡ ከመግቢያ በሩ ላይ የተጻፈ ማሳሰቢያ ቢጤ ይመለከታሉ።

👉"በካምፓኒው ውስጥ እድገታችሁን ሲያደናቅፍ የነበረው ግለሰብ በትናንትናው ዕለት ስላረፈ በስርዓተ-ቀብሩ ላይ እንድትገኙልን እንጋብዛችኋለን" ይላል።

የስራ ባልደረባቸው ስላረፈ ብዙሃኑ ሰራተኞች አዘኑ።
ዳሩ ግን ቢከፉም ሁሉም ተደነቁ። "ምንም እንኳን ቢሞትም እድገቴን ሲያደናቅፍ የነበረው ሰውዬ ግን ማን ነበር?" ሲሉ አሰቡ። ለማየትም ጓግተው አንድ በአንድ ከሬሳ ሳጥኑ እየቀረቡ ቢመለከቱ ድንገት የሚናገሩት ቃል ጠፋቸው። አልጠበቁም። ሌላ ሰው ጥልቅ ስሜታቸውን የነካ ይመስል ከሬሳ ሳጥኑ አጠገብ ቆመው ፈዘው ዝም አሉ።
የሬሳ ሳጥኑ ከውስጡ መስታውት ቢሆን እንጂ አንዳችም አልነበረውም። ሁሉም ወደ ውስጥ ቢመለከቱ፣ ያዩት የራሳቸውን ምስል ብቻ ነው። ከመስታውቱ አጠገብ አንድ ጥቆማ ሰፍሯል።
👉"ስኬትህን የመገደብ ብቃት ያለው አንድ ግለሰብ አለ። እሱም እራስህ ነህ።"

#ኃያል_ሀሳብ_ኃያል_ውጤት
#ኃያል_የኃያልነታችን_መግለጫ

@temesgen2010 👈 join አድርጉ

#መልካምና_ድንቅ_እለተ_ሰንበት_ይሁንልን