ስብእናችን @ HUMANITY 🌍
840 subscribers
29 photos
5 videos
5 files
31 links
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ኑ እናንብብ ትልልቅ እውቀቶችን እንጨብጥ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ #ሙስሊም #ክርስቲያኑ ሁሉም በፍቅርና በቅንነት የሚኖርባት ድንቅ ምድር ነች ።

ልጇቿም ባንድም በሌላ መልኩ በእኩልነት በመተሳሰብና በመከባበር በአብሮነት የሚኖሩባት የፈጣሪ ቃልኪዳን ያላት እፁብ ድንቅ ሀገር ነች።

አምላኬ ሆይ የዚህች ድንቅ ሀገር ባለቤት ስላረከን እናመሰግናለን ።
ሀገራችንንም ፍቅር ፣ ሰላም ፣ ደስታ የሰፈነባት ሀገር ስላረክልን እናመሰግናለን ።

📌Channel link👇Press Bell Icon🔔To Notified New Videos
🔔 https://youtube.com/channel/UCa8YfLAyCtj137m9JKr9TOg

Join us
@temesgen2010
ሼር ይደረግ
ለአስተያየት For Comment
@Temuvlog1
#ለብሩህ_ቀን_ይቺን_ምክር_ጀባ_ልበላችሁ

🧤ህይወት እየቀለለ እንዲሄድ አትመኝ!

እንደውም አንተ እየጠነከርክ መሄድ ነው ያለብህ።
አየህ ትልቅ ነገር የሚፈልግ ሰው ትልቅ ዋጋ ይከፍላል!
አይምሮህን ለትናንሽ ድሎች ሳይሆን ለታላቅነት አዘጋጀው።💪

ግሩም ድንቅ ቀን ተመኘሁ🙏

📌Channel link👇Press Bell Icon🔔To Notified New Videos
🔔 https://youtube.com/channel/UCa8YfLAyCtj137m9JKr9TOg

Join us
@temesgen2010
ሼር ይደረግ
ለአስተያየት For Comment
@Temuvlog1
አሁን ከሚከፈልህ በላይ ስትሰራ ትንሽ ቆይቶ ከሰራኸው በላይ ይከፈልሀል" ይለናል ናፖሊዮን ሂል ። ተማሪም ሁን ሰራተኛ አብዛኛው ሰው ከሚያጠናው ከሚዘጋጀው ወይ ከሚሰራው ጨመር አርነህ የምትሰራ ከሆነ ከፍ ለማለት ብዙ አይፈጅብህም ። የአብዛኞቹን ስኬታማ ሰዎች የህይወት መንገድ ጠጋ ብላችሁ ስታዩ አሁን የደረሱበት ከመድረሳቸው በፊት ከሚያገኙት ገቢ ብዙ እጥፍ ይለፉ ነበር ፤ ቢያንስ ለ 12 ሰዓታት በሳምንት 6 ቀን ይሰሩ ነበር ። ጂም ሮን "አሁን ስለምታገኘው ገቢ ብዙም አትጨነቅ ፣ ግን ነገ ስለምትሆነው ሰው አብዝተህ ተጨነቅ ምክንያቱም የነገው ገቢህ የሚወሰነው ነገ በምትሆነው ማንነት ነው" ይለናል ። በቃ ነገ እንድታገኝ ለምትፈልገው ሀብት ስትል አሁን ከምታገኘው ገቢ በላይ መስራት ራስህን ማሻሻል አለብህ ። ይሄን ተግባር ዛሬውኑ ጀምረው ቆይ ከሰሞኑ እጀምራለው አትበል! ጊዜው ሲሄድ አይታወቀንም ፤ እቴጌ ጣይቱም እኮ "ነበር ለካ እንዲ ቅርብ ነው" ብለው ነበር ።

ለተጨማሪ ምርጥና አስተማሪ የስኬት ፅሁፎች ቻናላችንን Join ያድርጉት
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇
📌Channel link👇Press Bell Icon🔔To Notified New Videos
🔔 https://youtube.com/channel/UCa8YfLAyCtj137m9JKr9TOg

Join us
@temesgen2010
ሼር ይደረግ
ለአስተያየት For Comment
@Temuvlog1
#ለመላው_የእስልምና_እምነት ተከታይ ወዳጆቼ በሙሉ እንኳን ለ1442ኛው የዒድ አል አድሃ (ዐረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

ኢድ ሙባረክ ! ሰላም ለሀገራችን ይሁን 🙏
አሜን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Join 👇👍
@temesgen2010
✞✞✞እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

🌺ደብረ-ታቦር /ቡሄ/

【ቡሄ ፣ ጅራፍ ማስጮህ ፣ ችቦ ማብራትና ሙልሙል ዳቦ】
ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?

በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ነሐሴ ውስጥ እጅግ በርካታ በዓላቶች ይከበራሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ በጾመ ማርያም/
ፍልሰታ/ መገባደጃ ላይ የምናከብረው ከጌታችንንና
ከአምላካችን ከመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኝ አበይት
በዓላት መካከል አንዱ የሆነው {የደብረ-ታቦር } በዓል ትልቁና
ዋነኛው ነው፡፡

🌹ደብረ-ታቦር ጌታችን ያዕቆብ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ
ታቦር ተራራ ካወጣቸው በኃላ በዛ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና
ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ዕለት ነው ። ታዲያ ይህን እለት
ሀገራችንና ቤተ- ክርስቲያናችን በቀላሉ አክብራው የምታልፍ
በዓል አይደለም፡፡ ይልቁንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም
አስባው አክብራው ታልፋለች እንጂ፡፡ ስለዚህም ዛሬ እንደ
እግዚአብሔር ፈቃድ በዚህ በደብረ-ታቦር በዓል ትርጉማቸውን
አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ለበርካታ ጊዜያት የምንፈፅማቸውን
ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡ ከስሙ ለመጀመር ያህል

🌹የደብረ-ታቦር በዓል
በሀገራችን ቡሄ እየተባለ ነው ሚጠራው ቡሄ ምን ማለት ነው?
🎋ቡሄ🎋
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም
እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል
ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን
ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት
የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ
ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

እስኪ የሙልሙል ዳቦውን ነገር ካነሳን እርሱስ ሃይማኖታዊ
ትርጉም ይኖረው እንደሆነ የታሪኩንም አመጣጥ በዛው
እንመልከት:―

🍞ሙልሙል ዳቦ🍞

ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን
አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን
እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች
በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን
በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉንትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ
መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ሜቴ 10፣12/
ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡

🔥ችቦ ማብራት🔥

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡
ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን
ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ
ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ
የችቦ ታሪክ ቅድም ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡
ሌላው እረኞችን ስናነሳ ጅራፋቸውንም ማንሳታችን አይቀሬ ነው፡፡ በሀገራችንም ከበዓሉ ቀን መድረስ አንስቶ ለበርካታ ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ጅራፍ ይጮሃል ያ ደግሞ ምሳሌ ነው፡፡

የጅራፍ ምሳሌነት

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር
በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ
በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡ የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣ ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ
የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ለማስተላለፍ ከመኖሪያ ቤት ርቆና በሜዳ በተራራማ አካባቢ ብናረገው ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን በርችት መቀየሩ የሚያመጣውም የሚስጢር ተፋልሶ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው
ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት
ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ
ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን
ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን
ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን
ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው
መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።
አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን

“መ ል ካ ም በ ዓ ል”

@temesgen2010 👈join አድርጉ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 30 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 19 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
#የሰንበት_ቅምሻ

ከዕለታት አንድ ቀን ሰራተኞች ቢሮ ሲገቡ ከመግቢያ በሩ ላይ የተጻፈ ማሳሰቢያ ቢጤ ይመለከታሉ።

👉"በካምፓኒው ውስጥ እድገታችሁን ሲያደናቅፍ የነበረው ግለሰብ በትናንትናው ዕለት ስላረፈ በስርዓተ-ቀብሩ ላይ እንድትገኙልን እንጋብዛችኋለን" ይላል።

የስራ ባልደረባቸው ስላረፈ ብዙሃኑ ሰራተኞች አዘኑ።
ዳሩ ግን ቢከፉም ሁሉም ተደነቁ። "ምንም እንኳን ቢሞትም እድገቴን ሲያደናቅፍ የነበረው ሰውዬ ግን ማን ነበር?" ሲሉ አሰቡ። ለማየትም ጓግተው አንድ በአንድ ከሬሳ ሳጥኑ እየቀረቡ ቢመለከቱ ድንገት የሚናገሩት ቃል ጠፋቸው። አልጠበቁም። ሌላ ሰው ጥልቅ ስሜታቸውን የነካ ይመስል ከሬሳ ሳጥኑ አጠገብ ቆመው ፈዘው ዝም አሉ።
የሬሳ ሳጥኑ ከውስጡ መስታውት ቢሆን እንጂ አንዳችም አልነበረውም። ሁሉም ወደ ውስጥ ቢመለከቱ፣ ያዩት የራሳቸውን ምስል ብቻ ነው። ከመስታውቱ አጠገብ አንድ ጥቆማ ሰፍሯል።
👉"ስኬትህን የመገደብ ብቃት ያለው አንድ ግለሰብ አለ። እሱም እራስህ ነህ።"

#ኃያል_ሀሳብ_ኃያል_ውጤት
#ኃያል_የኃያልነታችን_መግለጫ

@temesgen2010 👈 join አድርጉ

#መልካምና_ድንቅ_እለተ_ሰንበት_ይሁንልን
ስኬት ፈፅሞ የመጨረሻ አይደለም፣
ውድቀትም ፈፅሞ አደገኛ አይደለም!


ውድቀት አንድ መልካም ነገር ቢኖረው ለመሞከራችሁ ማረጋገጫ መሆኑ ነው። ትልቅ ስህተት የምትሰሩት፣ ውድቀትን መፍራት ስትጀምሩ ነው። በህይወት ምንም ስህተት የማይሰሩ የማይሰሩ ሰዎች ስህተት ለመስራት እድሉን ያላገኙ ናቸው። እድሉን ያላገኘበት ምክንያትም ለመስራት ሞክረው ባለማወቃቸው ነው።

የራሳችሁን እምቅ ሀይል ፈትኑት። እስከዛሬ ከሰራችሁት የበለጠ ለመስራት ራሳችሁን ጠይቁ። ከራሳችሁ በወላሉ ልታገኟቸው ከምትችሏቸው የላቁ ነገሮችን ለማግኘት ጠብቁ። አሁን ያላችሁ ወይም የተጠቀማችሁበት፣ ሙሉ በሙሉ ያላችሁ (የተጠቀማችሁበት) አይደለም።

የእናንተ እምቅ ሀይል ገደቡ ፈጣሪ ነው ። እምቅ ሀይላችሁን አውጥታችሁ ተጠቀሙበት።

አንድን ነገር ሳይሞክሩ ከመቅረትና ሊያሳኩ የሚችሉትን ነገሮችን ሳያውቁ ከመቅረት ይልቅ ሞክሮ መውደቅ የተሻለ ነው መውደቅ ከተባለም ነገር ግን ውድቀት ለስኬት መወጣጫ መሰላል ነው።

#ኃያል_ሀሳብ_ኃያል_ውጤት
#ኃያል_የኃያልነታችን_መግለጫ


https://www.facebook.com/HayalETH01/ 👈 join አድርጉ

@temesgen2010 👈 join አድርጉ

#መልካምና_ድንቅ_እለተ_ረቡዕ_ይሁንልን
🌼 አዲስ ዓመት አዲስ አንተ! 🌼
፨፨፨፨፨፨//////////////፨፨፨፨፨፨
ቆርጠህ እስካልተነሳህ ድረስ ምንም የሚቀየር ነገር እንደማይኖር ከማንም በላይ ልብህ በሚገባ ያውቀዋል። ቀኑን መቁጠር፣ ዘመንን መቀየር ያንተ ለውጥ ከሌለበት ምንም የተለየ ክስተት አይደለም። የአዲስ ዘመንን ወኔ በሚገባ ተጠቀመው። የአሸናፊነትን እምነት ወደውስጥህ ማስረፅ ጀምር። ከባለፈው አመት የተለየ ፍፁምና እንከን አልባ አመት አትጠብቅ። በአዲሱ አመት እቅድህ ምንድነው? ትልቁ ሃሳብህ ምንድነው? ሃሳብህ እውን ለመሆን ከዚህ አመት የተሻለ ትክክለኛ ጊዜ እንደማይኖረው አስተውል። አመታትን ብቻ በመቀየር ህይወት አይቀየርም፤ ዘመንን በዘመን በመተካት ብቻ ህይወት አንድ እርምጃ ወደፊት ፈቀቅ አይልም። ለረጅም ጊዜ ይህን አዲስ አመት ስትጠብቀው እንደነበር አስታውስ። በአዲሱ አመት ይህን አደርጋለሁ፣ በመጪው አመት ይህን እጀምራለሁ፣ ይህን ባህሪዬን አሻሽላለሁ ብለህ እንደነበር አስታውስ።

አዎ! ጀግናዬ..! አዲስ አመት አዲስ አንተ፣ አዲስ አመት አዲስ ማንነት። በወሬ ብቻ እራስህን መግለፅ የምታቆምበት ጊዜ አሁን ነው፤ በእራስህ መኩረት የምትጀምረው፣ ጊዜው ያንተ እንደሆነ የምታስመሰክርበት ወቅት፣ ለወነገው አንተ የምትታመነው፣ ወደፊትህን በብሩህ ተስፋ የምትሞላው አሁን ነው። ለማሸነፍ ከዚህ አመት የተሻለ ጊዜ የለህም፣ ሊኖርህም አይችልም። አዲሱን አመት እንደምታከብረው ለአዲስ ፈተና ምንያክል ዝግጁ እንደሆንክ እርግጠኛ ሁን። በአዲስ አመት አዲስ ተስፋ አለ፣ ወደ አዲስ ማንነት የሚገፋን ውስጣዊ ሃይል አለ። ይህን ወኔ ወደኋላ አትመልሰው፣ ይህንን መነቃቃት አዳፍነህ አታስቀረው፣ ይህን ተነሳሽነት ዋጋ ቢስ አታድርገው። ለእራስህ የገባሀውን ቃል ለመፈፀም ብዙ ጊዜ ቀጠሮ ብታስቀምጥም ከአዲሱ አመት የሚልቅ ትክክለኛ ሰዓት ግን ልታስቀምጥ አትችልም።

አዎ! ሀሳብህን በተግባር፣ እቅድህን በስራ የምትቀይርበትን አመት ይህ አመት ነው። አያንዳንዱ የተሰጠችን የመኖር እድል፣ የተጨመረችልን ውድ ጊዜ ትርጉም የሚኖተራት በተግባርና በተግባር ብቻ ነው። ስንፍናህ የሚያበቃው አሁን ነው፣ ከመካከለኛነት የምትወጣው አሁን ነው፤ የአቋም ማሻሻያ የምታደርገው፣ አዲስ ማንነትን የምትገነባው፣ በተለየ ግሩም ስብዕና የምትገለጠው፣ የምትመኘውን ሰው ሆነህ የምትገኘው አሁን ነው። ከወትሮው በተለየ በአዲሱ ዘመን በአዲስ ወኔ ተነስ፣ በተለየ መንገድ ህይወትህን አሸንፍ፣ እራስህን በሚያስገርም መንገድ ብቁ ለማድረግ ተንቀሳቀስ። ባለፈው አመት ያጣሀውን ለሌላው ሰው የሚገባ እንደሆነ አስበህ ተወው፣ በአዲሱ አመት ያንተ የሆነው ወዳንተ እንደሚመጣም ከልብህ አምነህ ተዘጋጅ፣ እርሱንም ለማግኘት በአዲስ ወኔ፣ በተለየ ንቃት ወደ ጉዞ ግባ።
🌼🌻 መልካም አዲስ ዓመት! 🌻🌼
🌼🌻 2016 ዓ. ም🌻🌼
ጣፋጭ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫
ስብእናችን ቲዩብ
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
JOIN FOR MORE: t.me/Temesgen2010

በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://youtu.be/TWvhmm0tHj8
ስብእናችን ቲዩብ Humanity TUBE /
“በከረመ እውቀት አዲስ ችግር መግጠም አያዋጣም “

” አዲስ ነገር መማር ”

በየቀኑ አዲስ ነገር መማር የሚችል በየቀኑ ማደግ ይችላል።

በከረመ እውቀትና መረዳት አዲስ ውጤት አይመጣም።አዲስ ነገር ማወቅ አእምሯችንን በማንቃት ውስጣዊ አሰራራችንን ያድሳል።

በቀን ውስጥ 20 ደቂቃ በመመደብ ስለምንሰራው ስራ ፣ስለጤናችን ፣ስለቤተሰብ ህይወት ፣ስለመንፈሳዊ ህይወት ፣ቋንቋችንን ለማሻሻል ፣ስለ ማርኬቲንግ እና ስለ ሌሎችም ጉዳዮች እራሳችንን አዲስ ነገር በማስተማር በየቀኑ ማደግ እንችላለን።

መጥረቢያ ሲሞረድ በፍጥነት እና በቀላሉ እንደሚቆርጥ ሁሉ ሰውም በአዲስ እውቀት እራሱን ሲሞርድ ውጤታማ ይሆናል።

በየቀኑ በመማር ያለማወቃችንን መጠን እንቀንስ ።
መልካም ቀን 🙏
May your determination lead you to success and fulfillment!!

Wishing you the strength to overcome hurdles and the wisdom!!

Let the canvas of the New Year be painted with the colors of your dreams and your brush be filled with paint of joy!

💫
ስብእናችን ቲዩብ
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
JOIN FOR MORE: t.me/Temesgen2010

ድንቅ ቀን ይሁንልን
"My experience has been that there are times to teach and times not to teach. When relationships are strained and the air charged with emotion, an attempt to teach is often perceived as a form of judgment and rejection."

From the book; The 7 habits of highly effective people by Stephen R Covey

💫
ስብእናችን ቲዩብ
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
JOIN FOR MORE: t.me/Temesgen2010

ድንቅ ቀን ድንቅ ሳምንት ይሁንልን ።
➡️🅰️🔤🅰️🔤🅰️⬅️
በዚህ ቀን የኢትዮጵያን ጀግንነት እና አንድነት እናከብራለን! የአድዋ ድልን ስንዘክር የኢትዮጵያ ህዝብን ፅናት እና ሀገር ወዳድነት አብረን እንዘክራለን። ለነፃነታችን እና ለሉዓላዊነታችን የታገሉትን ጀግኖች እያመሰገንን፣ መልካም የአድዋ ድል ቀን እንላለን!

💫
ስብእናችን ቲዩብ
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
JOIN FOR MORE: t.me/Temesgen2010
"A leader is one who knows the way, goes the way and shows the way."

The greatest leadership is to be exemplary. You must do, act, say and be the person you want your team to be.

                          ****

"መሪ ማለት መንገዱን የሚያቅ፣ መንገዱን የሚሄድ፣ እና መንገዱን የሚያሳይ ነው።"

ትልቁ የአመራር መገለጫ ለሌላው አርአያ መሆን ነው። ስለዚህ በአመራር ላይ ቡድኖ እንዲሆን እንደሚፈልጉት ሰው መሆን፣ መናገር እና ማድረግ ይኖርብናል።
Take time!!



“Give me six hours to chop down a tree and I will spend the first four sharpening the axe.” ― Abraham Lincoln

🔷እየሄዱ መቆም የመሄድን አቅም መጨመር ነው… መዘግየት አይደለም… እያረፉ መጓዝ የብልህነት ከፍታ ነው … ስንፍና አይደለም… ‘በየመሃሉ’ ማለት መታደስ ነው… ኋላ መቅረት አይደለም… ለረጅም ሰዓት ያሽከረከረ ሹፌር ጥጉን ይዞ ‘እረፍት’ የሚወስደው የበለጠ መጓዝ እንዲችል ነው… የጋለው ሞተር ቀዝቅዞ አቅም መግዛት አለበት… የዛለ ክንዱም በርትቶ መሪ ማዞር አለበት… በየሰከንዱ በምንስበው አየር የመታደስ ያህል ነው – ‘በየመሃሉ’ ማለት… አንዴ በሳቡት አየር ዕድሜ ልክ ልኑር አይባልምና…

ሰውየው በአንድ ድርጅት ውስጥ በእንጨት ቆራጭነት ስራ አምስት ዓመት ያህል ቢያገለግልም ሁሌም የደመወዝ እድገት እንደናፈቀው ነው… ከእርሱ በኋላ የተቀጠሩ ሰራተኞች ዓመት ሳይደፍናቸው የክፍያ መሻሻል አይተዋል… እናም ሰውየው ዘወትር ‘ለምን?’ ይላል… የድርጅቱ ኃላፊ ‘እንደምታውቀው ድርጅታችን ውጤት ተኮር ነው… ብዙ የሰራ ብዙ ያገኛል… አንተን እንደማይህ የዛሬ አምስት ዓመት ትቆርጥ የነበረውን እንጨት ነው ዛሬም የምትቆርጠው… ይሄ ደግሞ ላንተ ለውጥም ሆነ ለድርጅቱ እድገት አንዳች አይፈይድም’ ብሎታል… እናም ይለፋል… ይጥራል… ይግራል… ጠብ የሚል ነገር የለም…

🔶በድጋሚ አለቃውን አግኝቶ ጠየቀ… ‘እስኪ ካንተ በኋላ የተቀጠሩትን ቆራጮች ተመልከታቸው… በየጊዜው መሻሻል እያሳዩ ነው… ለምን እነርሱን አታማክራቸውም… ለምሳሌ እከሌን ማናገር ትችላለህ… ምናልባት እኔና አንተ የማናውቀውን ምስጢር ይጠቁምህ ይሆናል’… ሲል መለሰለት…

🔹ሰውየው የተጠቆመው ሰው ዘንድ ሄዶ ችግሩን አስረዳው… ባለሙያውም ሁኔታውን በደንብ ካጤነ በኋላ ‘ለመሆኑ መጥረቢያህን ከሳልከው ስንት ጊዜ ሆነህ?’ ሲል ጠየቀው… እንጨት ቆራጩ እንደ ማሰላሰል አለ… በጣም ቆይቶ ነበር… በጣም… ባለሙያው አከለለት… ‘ይኸውልህ.. እኔ በየጊዜው የተወሰኑ የእንጨት ክምሮችን ከቆረጥኩ በኋላ መጥረቢያዬን እሞርዳለሁ… በዚህም ምክንያት ብዙ እንጨት መቁረጥ ችያለሁ’ አለው… ሰውየው ለረጅም ጊዜ የተደበቀበት የስኬት ምስጢር ለካ ‘በየመሃሉ’ ማለት ነው…

🔸ብዙዎቹ መጥረቢያዎቻችን ደንዘዋል… ችግሩ ዛሬም በትናንት አቅማቸው እንዲያገለግሉን እየጠበቅን ነው… ነጋ ጠባ በሚቆርጡት እንጨት ጥርሶቻቸው ተሸራርፎ አልቋል… ችርችፍ ብሏል… ዶልዱሟል…

🔺ላሞችህ ወተት እንዲሰጡህ የምትጠብቀው መመገብ እንዳለብህ ዘንግተህ ከሆነ ችግር አለ… የገባው ነው የሚወጣው .. መልኩን ከመቀየሩ ውጪ… የአገልግሎት ማሻሻያ ሳያደርግ ከፍተኛ ገቢ የሚጠብቅ ድርጅት… ሳያነብ ልጨኛ ጽሑፍ መፃፍ የሚፈልግ ‘ደራሲ’… በአግባቡ ሳያስተምር ጎበዝ ተማሪዎችን ማየት የሚናፍቅ መምህር… የድርሻውን ሳይወጣ ያደገች ሃገር ማየት የሚሻ ሕዝብ… የሚጠበቅበትን ሳያደርግ የሚጠበቅብህን የሚጠይቅ መንግስት… ለአርዓያነት ሳይበቃ ‘የተመረቀ ልጅ’ የሚጠብቅ ቤተሰብ… ሁሉም የደነዘ መጥረቢያቸውን አስተውለውት አያውቁም… የአንዳንዶቹ እንዲያውም ዝገት ጀምሮታል…

ከድግሪህ በኋላ ማንበብ ካቆምክ ድግሪህ እርባን የለውም… ዶክትሬትም ቢሆን… ከሽልማት በኋላ መስራት ካቆምክ መሸለምህ ከንቱ ነው… ቅዱስም ብትሆን… ዜኖች እንዲህ ይላሉ… “Before enlightenment, chop wood, carry water. After enlightenment, chop wood, carry water.”

🔸መጥረቢያህን ሳል… በመቁረጥ ላይ ብቻ እንደተመሰጥክ ያስታውቃል… ስትሞርድ ስለት ብቻ አይደለም የምትጨምረው… የሆነ የምታራግፈው ቆሻሻም አለ… ውጋጅ ነገር… አሮጌ አስተሳሰብ… ጠማማ ገጽታ… የተንሸዋረረ እይታ… ግድግዳ ኩራት…

ለመሞረድ የምታጠፋው ጊዜ የባከነ አይደለም… ነዳጅ እንደመጨመር ነው… የሆነ ጊዜ ድንገት ቀጥ ትላለህ… ምናልባት ያኔ ለመሞረድ ሁነኛ ጊዜህ አይሆን ይሆናል… እናም መቆሚያህ እንዳያጥር መቋቋሚያህን አጽና…

A woodsman once asked “what would you do if you had just five minutes to chop down a tree?’… He answered, ‘I would spend the first two & a half minutes sharpening my axe.”…

MORAL OF THE STORY
📍 Let us take a few minutes to sharpen our perspective.

             ሰናይ ሰንበት!!🙏

💫
ስብእናችን ቲዩብ
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
JOIN FOR MORE: t.me/Temesgen2010