The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አዲስ_መረጃ
#አስገራሚ_ውድድር
#ቃሉን_ጻፈው
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

"ቃሉን ጻፈው" የተሰኘ መጽሐፍ ቅዱስን በእጅ ጽፎ የመጨረስ አመታዊ ውደድር ተጀመረ።

1. ለወቅታዊ ጉዳዮች ከሚሰጥ ያልተገባ ትኩረትና ጭንቀት ራስን በመሰወር ዘላለምን የሚያስብ የሕይወትን ቃል ትኩስ አጀንዳና ርዕስ ማድረግ
2. የእግዚአብሔርን ቃል በማወቅ ነፃ መውጣትን ማቀጣጠል
3. የእጅ ጹሑፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂን በዚህኛው ዘመን ታሪክ ውስጥ መጻፍ
4. ቅዱሳት መጽሐፍትን ጠብቀው ያቆዩ ቅዱሳን አባቶችን ማስታወስና አርዓያነታቸውን መከተል
5. እውነተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ለማጥፋት ከሚቆም ሀይል ፊት በተቃርኖ መቆም የሚሉ አላማዎች ያሉት እንደሆነም ታውቋል።

ፕሮጀክቱ መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ፊደል እና ያለ ቃል ስህተት በእጅ ጽፎ የማጠናቀቅ ውድድርን በአገር አቀፍ ደረጃ የማድረግ ሥራ ሲሆን ቀድመው ላጠናቀቁ ሰዎች ሽልማት ይሰጣል፡፡ ለተቀሩት ደግሞ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ይበረክታል፡፡

ይህ ውድድር 2ኛ ዙር ሲሆን በ2012ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ተከናውኖ ውድድሩን ላሸነፉ ተሳታፊዎች የማበረታቻ ሽልማት እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰቷቸዋል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#አስገራሚ_ክስተት_እና_አዲሱ_ሉዓላዊ_የሚል_መዝሙር
ይህን ጥያቄ የጠየቀችኝ ማሂ(ቡቹ) ነች። ማሂ እኔን ትንሹን ወንድሟን ለማስመረቅ
ከቤተሰቦቼ ጋር አርብ መስከረም 8 ነበር ወደ ሀዋሳ የመጡት። አርብ ሀዋሳ
መናኸርያ ሲደርሱ ሄጄ ተቀብያቸው ወደ ማረፍያቸው ወሰድኳቸው። ከአርብ ጀምሮ
እስከ ቅዳሜ ማታ ድረስ በጣም የሚያስደስት የቤተሰብ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው።
ቅዳሜ ከምረቃው ፕሮግራም በኃላ ዘመድ ቤት ቆይተን አመሻሽ ላይ ወደ
ማረፍያቸው ወሰድኳቸው። እሁድ ከቸርች በኃላ ከሰዓት ነበር ወደ አርባምንጭ
ለመመለስ ያሰቡት። ነገር ግን እኔ ሌላ ፕሮግራም ስለነበረኝ እሁድ ወደ ሀላባ
ከተማ ልወጣ ነበርና ጥዋት ቁርስ በልተው እንዲወጡ ተነጋግረን ተለያየን። እሁድ
በማለዳ ስልኬ ጮኸ ! ማሂ ነበረች። " ቶሎ ና እንጂ አንተን እየጠበቅን ነው "
አለችኝ። እሺ ብዬ ወዲያው ልብሴን ለባብሼ ወደ ማረፍያቸው ሄጄ አገኘዋቸው።
ከወትሮው በተለየ መልኩ ማሂ ተረጋግታለች። ቁርስ እንድንበላ መናኸርያ ፊት
ለፊት ወደሚገኝ ሆቴል ገባን። ከስጋ ውጪ ሌላ ምግብ ስላልነበር አማራጭ
አልነበረንም። ወንድሜና አባቴ ቁርጥ ስለሚወዱ ጥሬ ስጋ አዘው መብላት ጀመሩ።
ማሂ ግን ጥሬ ስጋ ስለማትወድ ስልኳን ከፍታ FB መጠቀም ጀመረች። ሰሞኑን
የወጣ "ሉአላዊ" የተባለ አዲስ መዝሙር ስለነበር FB ላይ ብዙ ሰዎች
የመዝሙሩን ግጥም እየፃፉ post አድርገዋል። ማሂ በተደጋጋሚ ስላየች "ቆይ ግን
እግዚአብሔር ሉአላዊ ማለት ምንድነው ? አለችኝ። እኔም የማውቀውን መናገር
ጀመርኩ። እግዚአብሔር ሉአላዊ ማለት እርሱ በሚሰራው ስራ ማንም
አይጠይቀውም ማለት ነው። ሁልጊዜም ጌታ በሚያደርገው ነገር ሁሉ አዋቂ ነው።
ለምን እንዲህ አደረክ ወይም ለምን እንደዚህ ሆነ አይባልም። እግዚአብሔር እርሱ
አዋቂ ነው። የሚያደርገውን ሁሉ በራሱ ፍቃድና እውቀት ላይ ብቻ ተደግፎ
ያደርጋል። እኛ እግዚአብሔርን ለመክሰስም ሆነ ለመሟገት ምንም ስልጣን
የለንም። እግዚአብሔር ብቻውን የሚወስን ብቻውን የሚያደርግ ሉአላዊ አምላክ
ነው ብዬ አወራዋት። ልክ ይሄንን እያወራን ሳለ አባቴ በቃ እንውጣ ብሎን ከሆተሉ ወጥተን ወደ መናኸርያ ገብተን መኪና ውስጥ ገቡ። ከሸኘዋቸው በኃላ ወደ
ፕሮግራሜ ለመሄድ ከጓደኞቼ ጋር እየተዘጋጀን እያለ ወንድሜ ደውሎ መኪና
እንደተገለበጠና ብዙዎቹ እንደቆሰሉም ከባድ ነገር እንደተፈጠረ ነገረኝ። ተሯርጠን ወደ አደጋው ቦታ ብንደርስም እህቴን ማትረፍ አልቻልንም። እንግዲህ እግዚአብሔር ፈቅዶ በተፈጠረው የመኪና አደጋ እህቴ ላትመለስ አሸለበች። ነገር ግን በመጨረሻው
ሰዓት ትልቅ ትምህርት አስተምራኝ ተለየችኝ። እህቴ ይህንን አስወርታኝ ይሄ አደጋ
ከተፈጠረ በኃላ እንዴት አድርጌ እግዚአብሔርን ለምን ብዬ ልጠይቀው ? በፍፁም
አልቻልኩም። ለአንድም ቀን እህቴን አጥቼ መኖር እችላለው ብዬ አስቤ አላውቅም
ነበር። ነገር ግን ይኸው ዛሬ ቀኔን መኖር ቻልኩ። ስለ ሁሉም እግዚአብሔር
ይመስገን። እግዚአብሔር ሉአላዊ አምላክ ነው !!
በረከት መልካሙ
#አዲስ
#አስገራሚ
#ቤተክርስቲያን #ድንግል #ሴቶች #አላገኘሁም አለች።

ቤተክርስቲያኑ ድንግል ሴቶችን ለመሸለም ማስታወቂያ ብታወጣም አሸናፊ ማግኘት አልቻልኩም ብላለች።

የኡጋንዳ ቤተ ክርስቲያን ለድንግል ሴቶች ዳጎስ ያለ ሽልማት መዘጋጀቱን ቢገልፅም ተሸላሚ ድንግል ሴት ማግኘት እንዳልቻለ ቢቢሲ የኡጋንዳ መንግስታዊ ሚዲያ የሆነው ኒው ቪዥንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

የሽልማቱ ዓላማ የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት ለማበረታታት ነው የተባለ ሲሆን፤ ሴቶች ከሰርጋቸው ቀደም ብለው እንዲወዳደሩ ማስታወቂያ አውጥቶ ቆይቷል።

ቤተ ክርስቲያኗ ባወጣችው ማስታወቂያ እድሜያቸው ለጋብቻ የደረሱ ሴቶች ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት እንዲወዳደሩ ጥሪ አቅርባ ነበር።

የኡጋንዳ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ስቴፈን ካዚምባ፥ ውድድሩ ለሁለቱም ጾታዎች ቢሆንም የወንድ ድንግሎችን መለየት ባለመቻሉ በውድድሩ ማሳተፍ አልተቻለም ብለዋል።

ድንግል የሆኑ ሴቶች ግን በኡጋንዳ እናቶች ህብረት እንዲመዘገቡ ጥሪ የተደረገ ሲሆን፥ ከተመዘገቡ በኋላ አሸናፊዎቹ ይለያሉ ተብሎም ነበር።

ይሁንና ለውድድሩ አሸናፊ ድንግሎች ዳጎስ ያለ የገንዘብ ሽልማት ብናዘጋጅም አሸናፊ አላገኘንም ብለዋል ሊቀ ጳጳስ ካዚምባ።

ይሁንና ሊቀ ጳጳሱ ለውድድሩ አሸናፊ ድንግሎች ስለሚሸለመው ገንዘብ መጠን ከመናገር ተቆጥበዋል።