🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አድራቹሃል🙏
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
✍ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞች ጉዞ ላይ ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛው ሐዘን በተሞላበት አንደበት እንዲህ አለው።
«ፈጣሪ ይህን ሁሉ ሀብት ለእነዚህ ሰዎች ሲያድል እኛ የት ነበርን?»
ጓደኛውም አጠገቡ ነበረና ና ብሎ ወደ ሆስፒታል ይዞት ሔዶ እንዲህ አለው። «ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሽታን ሲያድል እኛ የት ነበርን?»
✅ "ያለንን ብናውቅ የጎደለን የለም!!!"*
ሠናይ ውሎ 💚💛❤️
@Simetin_Begitim
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
✍ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞች ጉዞ ላይ ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛው ሐዘን በተሞላበት አንደበት እንዲህ አለው።
«ፈጣሪ ይህን ሁሉ ሀብት ለእነዚህ ሰዎች ሲያድል እኛ የት ነበርን?»
ጓደኛውም አጠገቡ ነበረና ና ብሎ ወደ ሆስፒታል ይዞት ሔዶ እንዲህ አለው። «ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሽታን ሲያድል እኛ የት ነበርን?»
✅ "ያለንን ብናውቅ የጎደለን የለም!!!"*
ሠናይ ውሎ 💚💛❤️
@Simetin_Begitim
#pic 6
#ገጣሚ
#ከበደ_ሚካኤል
ምርጥ ታሪካዊ ፣ የታዋቂ ኢትዮጵያውያን ሰዎችን እና አስደናቂ ፎቶዎችን ከአጭር Description ጋር ይላኩልን እኛ ደግሞ መልሠን ወደ እናንተ እናደርሳለን በ @Haile_Melekot ይላኩልን ፡፡
አብረን እንማማር፡፡
@Simetin_Begitim
#ገጣሚ
#ከበደ_ሚካኤል
ምርጥ ታሪካዊ ፣ የታዋቂ ኢትዮጵያውያን ሰዎችን እና አስደናቂ ፎቶዎችን ከአጭር Description ጋር ይላኩልን እኛ ደግሞ መልሠን ወደ እናንተ እናደርሳለን በ @Haile_Melekot ይላኩልን ፡፡
አብረን እንማማር፡፡
@Simetin_Begitim
ሁለት መላጦች
(ብርሃነ ኅሊና - ከበደ ሚካኤል)
.
ሁለት በራ ሰዎች ሲያልፉ በጎዳና
እቃ መሬት ወድቆ ብልጭ ሲል አዩና
ተሽቀዳድመው ሄደው ከቦታው ሲደርሱ
ተፎካከሩበት ሁለቱም ሊያነሱ
በኋላም ተማተው በጥፊ በጡጫ
አንደኛው ነጠቀ በጉልበቱ ብልጫ
አገላበጠና ቢመለከት ፈጥኖ
እቃውን አገኘው ማበጠሪያ ሆኖ
እስኪ ሁላችሁም በሉ ፍረዱት
እሱ ራሱ በራ ጠጉር የለበት
ሮጦ ተማቶ ቀምቶ ቢያመጣ
ምን ያደርግለታል ሚዶ ለመላጣ
ሰዎች ይፋጃሉ አስበው ሳይፈርዱ
የተጣሉበትን ጥቅሙን ሳይረዱ
@Simetin_Begitim
(ብርሃነ ኅሊና - ከበደ ሚካኤል)
.
ሁለት በራ ሰዎች ሲያልፉ በጎዳና
እቃ መሬት ወድቆ ብልጭ ሲል አዩና
ተሽቀዳድመው ሄደው ከቦታው ሲደርሱ
ተፎካከሩበት ሁለቱም ሊያነሱ
በኋላም ተማተው በጥፊ በጡጫ
አንደኛው ነጠቀ በጉልበቱ ብልጫ
አገላበጠና ቢመለከት ፈጥኖ
እቃውን አገኘው ማበጠሪያ ሆኖ
እስኪ ሁላችሁም በሉ ፍረዱት
እሱ ራሱ በራ ጠጉር የለበት
ሮጦ ተማቶ ቀምቶ ቢያመጣ
ምን ያደርግለታል ሚዶ ለመላጣ
ሰዎች ይፋጃሉ አስበው ሳይፈርዱ
የተጣሉበትን ጥቅሙን ሳይረዱ
@Simetin_Begitim
ለውብ ቀን💚💛❤️
የሙላ ናስሩዲን ጨዋታ
.
ቤት ቀየርን
...
ሌባው ናስሩዲን ቤት በሌሊት ገብቶ አብዛኛውን
ንብረቱን ዘርፎ በገባበት በር ውልቅ አለ፡፡
ናስሩዲን ድምጽ ሳያሰማ ሁኔታውን ሲከታተል
ነበር፡፡ ከተኛበት ተነስቶ ብርድ ልብሱን
እንደተከናነበ በቀስታ ሌባውን ተከተለው፡፡ ሌባው
የዘረፈውን ንብረት ይዞ ቤቱ ሲገባ ናስሩዲንም
ዘው አለ፡፡ ለመተኛትም ራሱን አስተካከለ፡፡
በነገሩ የተገረመው ሌባ "ምን እያደረክ ነው?"
ሲል ጠየቀው፡፡
ናስሩዲን መለሰ፦ "ልተኛ ነዋ፡፡ ቤት ቀየርን እኮ፡፡
አልቀየርንም እንዴ?"
ሠናይ ውሎ ብሩህ ቀን💚💛❤️
@Simetin_Begitim
የሙላ ናስሩዲን ጨዋታ
.
ቤት ቀየርን
...
ሌባው ናስሩዲን ቤት በሌሊት ገብቶ አብዛኛውን
ንብረቱን ዘርፎ በገባበት በር ውልቅ አለ፡፡
ናስሩዲን ድምጽ ሳያሰማ ሁኔታውን ሲከታተል
ነበር፡፡ ከተኛበት ተነስቶ ብርድ ልብሱን
እንደተከናነበ በቀስታ ሌባውን ተከተለው፡፡ ሌባው
የዘረፈውን ንብረት ይዞ ቤቱ ሲገባ ናስሩዲንም
ዘው አለ፡፡ ለመተኛትም ራሱን አስተካከለ፡፡
በነገሩ የተገረመው ሌባ "ምን እያደረክ ነው?"
ሲል ጠየቀው፡፡
ናስሩዲን መለሰ፦ "ልተኛ ነዋ፡፡ ቤት ቀየርን እኮ፡፡
አልቀየርንም እንዴ?"
ሠናይ ውሎ ብሩህ ቀን💚💛❤️
@Simetin_Begitim
# ከጅምላ # እንድናተርፍ
ችርቻሮ ትተን
የልዩነት ሩጫ — የጎጥ እሽቅድድም
ተባብረን እንሩጥ
ሁላችንን ይዛ — ኢትዮጵያ እንድትቀድም
* * *
✍ሙሉቀን ሰ•
@Simetin_Begitim
ችርቻሮ ትተን
የልዩነት ሩጫ — የጎጥ እሽቅድድም
ተባብረን እንሩጥ
ሁላችንን ይዛ — ኢትዮጵያ እንድትቀድም
* * *
✍ሙሉቀን ሰ•
@Simetin_Begitim
#ኧረ_አምሳለ!
(ምልዕቲ ኪሮስ ኃይሌሥላሴ)
ሰዉ በዘመን ጅረት...................
ዘመን በሠዉ ጀርባ እንደገሠገሠ
ይኸዉልሽ እንግዲ ክፉ ቀን ደረሰ...
ይኸዉ እንዲ ሆነ:
አንች ስትሄጅ;-
ፀሀይ ጠዋት ቀረች
ጨረቃ አኮረፈች
ሰማይ አለቀሰ
መሬት ተቆረሰ
ጨዋታ ፈረሰ....
አንች ሳትኖሪ:-
አኩኩሉ አይነጋም...
በሰኞ ማክሰኞ ዉብ ቤት አይገዛም ...
በሌባና ፖሊስ ባባሮሽ ጨዋታም...
እንደሮጠ ቀርቷል ማንም ሰዉ አልመጣም....
ህፃናቱ ከቦ አሁንም ቁጭ ብሏል...
መሐረቤን ብሎ አንድ ልጅ ይዞራል...
ህፃናቱ ከቦ ቁጭ ብሏል አሁንም...
መሃረቡን ያየም አየሁኝ አይልም ...
ብጫቂ መሐረብ መች ሆነና ቁቡ...
ነገረ ጨዋታዉ አንች ነሽ አሳቡ....
ኧረ አምሣለ.... ኧረ ሆይ...
ጨዋታ ለዛ አጣ አንዴ ብቅ በይ....
የህፃናት ተረት ከግማሹ አለቀ...
ትመጣለች ብሎ አንቺን የጠበቀ....
ቤትና ሃገር ቤት የሚል ሃሳብ መክኖ...
የሀገሪቱ ጉብል ቀረ ተበትኖ...
እንካ ስላንትያ እንቆቅልሻቸዉ...
ሳይፈታ ቀረ እርቀሽባቸዉ....
'ቢበስል ባይበስል ትመጭ ይመስል'
ብለን ያሟረት ነዉ....
ለካስ አንች ላይ ነዉ....
ኧረ አምሣለ ኧረ ምነዉ...
ደጅሽ የተከልሽዉ ምን አይነት እንኮይ ነዉ....
ያዉም በአኩኩሉ በዉሸት ጨዋታ...
እንደተደበቀች እሷ ብቻ ቀርታ....
ምድር በትካዜ ሰማይ በመከራ...
አለ እስካሁን ድረስ እምባዉን ሲያዘራ.....
የምሥኪኑ ደሀ አገዳዉ አሽቶ...
ይሄዉ ባንች ምክንያት ዝናቡ በርትቶ....
የቀየዉ ገበሬ እህል ተበላሸ....
ኧረ አምሳለ እያለ በነጋ በመሸ.,.
ያገር ሽማግሌ ያገሪቱን ዳኛ...
ስልጣኑን ወሠደዉ ነጠቀዉ ቀማኛ.,.
ፍርድ ተጏደለ...
ድሃ ተበደለ...
መነኩሴም ያለቅሳል ኧረ አምሣለ እያለ .....
ኧረ አምሣለ ኧረ ሆይ....
ያሳደገሽ መንደር አይናፍቅም ወይ....?
የእናቶች እህታ የህፃናት እምባ....
ወዴት አደረሰሽ ወዴት ይዞሽ ገባ....
የእረኛ እሮሮ...
ያዝማሪ ከበሮ...
የገጣሚ ዋይታ...
ያጋፋሪ እምቢልታ....
የዋሽንቱ ቅኝት ዜማና ምታቸዉ...
ኧረ አምሣለ ሆነ አፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ....
አለመምጣት አለ...
አለመምጣት አለ አለመተያየት...
ባንድ አምሣለ ናፍቆት ግጥም ብሎ መቅረት....
ስለእማምላክ ቢሉት አንጀቱ ሚራራ...
በራብሽ ከች የሚል ከጭንቅሽ 'ሚጋራ....
ሀገር-እግር የለዉም ወጥቶ አይፈልግሽም...
እርግማኑም ክፋ ላንችም አይቀናሽም...
ወንዝና ተራራም ወገን አይሆንሽም....
....... እናም...
ሠዉና ቀየዉን እያሠናሠነ...
የጉብሉን መዝሙር አጣፍጦ የከየነ....
ሰዉ ማለት... ሰዉ ማለት ...
ሰዉ ማለት ሃገር ነዉ ባይልም በቃሉ....
ይግባሽ አንድ ሚሥጥር - ሰዉን ከሠዉ ብቻ የመቀላቀሉ::
@Simetin_Begitim
(ምልዕቲ ኪሮስ ኃይሌሥላሴ)
ሰዉ በዘመን ጅረት...................
ዘመን በሠዉ ጀርባ እንደገሠገሠ
ይኸዉልሽ እንግዲ ክፉ ቀን ደረሰ...
ይኸዉ እንዲ ሆነ:
አንች ስትሄጅ;-
ፀሀይ ጠዋት ቀረች
ጨረቃ አኮረፈች
ሰማይ አለቀሰ
መሬት ተቆረሰ
ጨዋታ ፈረሰ....
አንች ሳትኖሪ:-
አኩኩሉ አይነጋም...
በሰኞ ማክሰኞ ዉብ ቤት አይገዛም ...
በሌባና ፖሊስ ባባሮሽ ጨዋታም...
እንደሮጠ ቀርቷል ማንም ሰዉ አልመጣም....
ህፃናቱ ከቦ አሁንም ቁጭ ብሏል...
መሐረቤን ብሎ አንድ ልጅ ይዞራል...
ህፃናቱ ከቦ ቁጭ ብሏል አሁንም...
መሃረቡን ያየም አየሁኝ አይልም ...
ብጫቂ መሐረብ መች ሆነና ቁቡ...
ነገረ ጨዋታዉ አንች ነሽ አሳቡ....
ኧረ አምሣለ.... ኧረ ሆይ...
ጨዋታ ለዛ አጣ አንዴ ብቅ በይ....
የህፃናት ተረት ከግማሹ አለቀ...
ትመጣለች ብሎ አንቺን የጠበቀ....
ቤትና ሃገር ቤት የሚል ሃሳብ መክኖ...
የሀገሪቱ ጉብል ቀረ ተበትኖ...
እንካ ስላንትያ እንቆቅልሻቸዉ...
ሳይፈታ ቀረ እርቀሽባቸዉ....
'ቢበስል ባይበስል ትመጭ ይመስል'
ብለን ያሟረት ነዉ....
ለካስ አንች ላይ ነዉ....
ኧረ አምሣለ ኧረ ምነዉ...
ደጅሽ የተከልሽዉ ምን አይነት እንኮይ ነዉ....
ያዉም በአኩኩሉ በዉሸት ጨዋታ...
እንደተደበቀች እሷ ብቻ ቀርታ....
ምድር በትካዜ ሰማይ በመከራ...
አለ እስካሁን ድረስ እምባዉን ሲያዘራ.....
የምሥኪኑ ደሀ አገዳዉ አሽቶ...
ይሄዉ ባንች ምክንያት ዝናቡ በርትቶ....
የቀየዉ ገበሬ እህል ተበላሸ....
ኧረ አምሳለ እያለ በነጋ በመሸ.,.
ያገር ሽማግሌ ያገሪቱን ዳኛ...
ስልጣኑን ወሠደዉ ነጠቀዉ ቀማኛ.,.
ፍርድ ተጏደለ...
ድሃ ተበደለ...
መነኩሴም ያለቅሳል ኧረ አምሣለ እያለ .....
ኧረ አምሣለ ኧረ ሆይ....
ያሳደገሽ መንደር አይናፍቅም ወይ....?
የእናቶች እህታ የህፃናት እምባ....
ወዴት አደረሰሽ ወዴት ይዞሽ ገባ....
የእረኛ እሮሮ...
ያዝማሪ ከበሮ...
የገጣሚ ዋይታ...
ያጋፋሪ እምቢልታ....
የዋሽንቱ ቅኝት ዜማና ምታቸዉ...
ኧረ አምሣለ ሆነ አፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ....
አለመምጣት አለ...
አለመምጣት አለ አለመተያየት...
ባንድ አምሣለ ናፍቆት ግጥም ብሎ መቅረት....
ስለእማምላክ ቢሉት አንጀቱ ሚራራ...
በራብሽ ከች የሚል ከጭንቅሽ 'ሚጋራ....
ሀገር-እግር የለዉም ወጥቶ አይፈልግሽም...
እርግማኑም ክፋ ላንችም አይቀናሽም...
ወንዝና ተራራም ወገን አይሆንሽም....
....... እናም...
ሠዉና ቀየዉን እያሠናሠነ...
የጉብሉን መዝሙር አጣፍጦ የከየነ....
ሰዉ ማለት... ሰዉ ማለት ...
ሰዉ ማለት ሃገር ነዉ ባይልም በቃሉ....
ይግባሽ አንድ ሚሥጥር - ሰዉን ከሠዉ ብቻ የመቀላቀሉ::
@Simetin_Begitim
እዘኝ አዛኝቱ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ወሩ መሥከረም ነው...
ቀኑ በሃያ አንድ ፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር
ግሸን ደብረ ከርቤ...
የ'መብርሐንን ፣ በአሏን ለማክበር
ከክርስቲያኖች ቤት...
አርፍጄ እንደደረስሁ ፣ታቦት ወጥቶ ነበር፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከታቦቱ አጠገብ...
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ካህኑ ይሰብካል
አንዳንዱ ምእመን ፣
ተአምር ያዘለ ..
ብጫቂ ወረቀት ፣ ለካህኑ ይልካል
ደግሞ ሌላ ተአምር...
ለካህኑ ጆሮ ፣ ዲያቆኑ ያንሻኩካል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ካህኑ!
"ታ'ምር ነው ምእመናን ፣ አንድዜ እልል በሉ
አንኳኩ ይከፈታል ፣
ጠይቁ ይሰጣል ፣ ይላልና ቃሉ
"አፀደ ማርያም"
የተባለች እናት ፣ የማርያም ምስክር
ልጇን አስተምራ ፣ በስቃይ በችግር
ካንዱ ይንበርስቲ...
ተመርቆ ወጥቶ ፣ ያለ ሥራ ሲኖር
አምና በዚህ ሰዓት...
ከደጇ መጥቼ ፣ ተማፅኛት ነበር
ፀሎቴን ሰምታለች!
ልጄም ሥራ ይዞ ...
መቶ ዶላር ልኳል ፣ ካሜሪካን ሀገር፡፡"
ስብከቱን አቋርጦ ፣ ተአምር ሲናገር...
በሴቶች እልልታ ፣ በወንዶች ጭብጨባ
የኢትዮጵያዊት ስለት...
ካሚሪካን ሀገር ፣ ተልኮ ሲገባ
ጥያቄ አምጣለሁ ፣ ዐይኔ እስኪያረግዝ እንባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አላለሁ...
ምንድነው እዚህ ሀገር ፣ ተምሮ መመረቅ?
እርግማን አይደል ወይ...
ሰው ሀገር ለመሥራት ፣ ተቸግሮ ማወቅ?
።፣፣፣፣፣።።።፣።፣፣
ምኑ ነው እውቀቱስ...
የተማሩት ነገር ፣ ላገር ካልጠቀመ
ምንስ ነው መቸገር....
ወድቀው ከፍ ያረጉት ፣ ሰው ሀገር ከቆመ?
ወይስ አልተቻለም...
እዚሁ ተምሮ ፣ እዚሁ ሀገር መስራት?
የተማረው ሁሉ...
ጥሏት ከነጎደ ፣
ማነው ይችን ሀገር ፣ የሚያስተዳድራት?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምንድነው እማምላክ
የሠው ሀገር ገንዘብ ፣ የሰው ሀገር ፍራንክ
በእልልታ ታጅቦ ፣ ከደጅሽ ሚመጣ?
በማለት እያማጥኩ...
ጥያቄ እየወረድኩ ፣ ጥያቄ ስወጣ...
።።።።፣፣።።።።
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ የካህኑ ስብከት
ከታቦቱ ፊት ላይ....
"ተቃጠልኩኝ " የሚል
"አሰናብቺኝ " የሚል
በሰው ላይ ያደረ ፣ ያጋንንት ጩኸት
ከታቦቱ ዙርያ...
"አይኔ ነሽ ብርሃኔ
እመቤቴ ማርያም ፣ አብሶማ ለኔ"
እያለ ሚዘምር ፣ ክብ የሰራ ወጣት
ይህንን እያየሁ
ብዙ ጥያቄዎች ፣ ሳምጥ ሳጠራቅም
አንድ አይነ ስውር ሰው...
ፊቴ ተደቀነ ፣ ምፅዋት ሊለቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምነው እመብርሀን
ታደዪ ይመሥል...
አይኔ ነሽ እያለ
አብሶማ እያለ ፣ ወጣቱ ሲዘምር
ምን ይሰማው ይሆን...
ከደጅሽ የመጣ ፣ ምስኪን አይነስውር?
ስል እጠይቃለሁ ፣ ደግሞ እታዘባለሁ
ጥያቄ እያማጥሁ ፣ እንባ እወልዳለሁ፡፡
እዘኝ አዛኝቱ!!!!!
@Simetin_Begitim
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ወሩ መሥከረም ነው...
ቀኑ በሃያ አንድ ፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር
ግሸን ደብረ ከርቤ...
የ'መብርሐንን ፣ በአሏን ለማክበር
ከክርስቲያኖች ቤት...
አርፍጄ እንደደረስሁ ፣ታቦት ወጥቶ ነበር፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከታቦቱ አጠገብ...
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ካህኑ ይሰብካል
አንዳንዱ ምእመን ፣
ተአምር ያዘለ ..
ብጫቂ ወረቀት ፣ ለካህኑ ይልካል
ደግሞ ሌላ ተአምር...
ለካህኑ ጆሮ ፣ ዲያቆኑ ያንሻኩካል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ካህኑ!
"ታ'ምር ነው ምእመናን ፣ አንድዜ እልል በሉ
አንኳኩ ይከፈታል ፣
ጠይቁ ይሰጣል ፣ ይላልና ቃሉ
"አፀደ ማርያም"
የተባለች እናት ፣ የማርያም ምስክር
ልጇን አስተምራ ፣ በስቃይ በችግር
ካንዱ ይንበርስቲ...
ተመርቆ ወጥቶ ፣ ያለ ሥራ ሲኖር
አምና በዚህ ሰዓት...
ከደጇ መጥቼ ፣ ተማፅኛት ነበር
ፀሎቴን ሰምታለች!
ልጄም ሥራ ይዞ ...
መቶ ዶላር ልኳል ፣ ካሜሪካን ሀገር፡፡"
ስብከቱን አቋርጦ ፣ ተአምር ሲናገር...
በሴቶች እልልታ ፣ በወንዶች ጭብጨባ
የኢትዮጵያዊት ስለት...
ካሚሪካን ሀገር ፣ ተልኮ ሲገባ
ጥያቄ አምጣለሁ ፣ ዐይኔ እስኪያረግዝ እንባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አላለሁ...
ምንድነው እዚህ ሀገር ፣ ተምሮ መመረቅ?
እርግማን አይደል ወይ...
ሰው ሀገር ለመሥራት ፣ ተቸግሮ ማወቅ?
።፣፣፣፣፣።።።፣።፣፣
ምኑ ነው እውቀቱስ...
የተማሩት ነገር ፣ ላገር ካልጠቀመ
ምንስ ነው መቸገር....
ወድቀው ከፍ ያረጉት ፣ ሰው ሀገር ከቆመ?
ወይስ አልተቻለም...
እዚሁ ተምሮ ፣ እዚሁ ሀገር መስራት?
የተማረው ሁሉ...
ጥሏት ከነጎደ ፣
ማነው ይችን ሀገር ፣ የሚያስተዳድራት?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምንድነው እማምላክ
የሠው ሀገር ገንዘብ ፣ የሰው ሀገር ፍራንክ
በእልልታ ታጅቦ ፣ ከደጅሽ ሚመጣ?
በማለት እያማጥኩ...
ጥያቄ እየወረድኩ ፣ ጥያቄ ስወጣ...
።።።።፣፣።።።።
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ የካህኑ ስብከት
ከታቦቱ ፊት ላይ....
"ተቃጠልኩኝ " የሚል
"አሰናብቺኝ " የሚል
በሰው ላይ ያደረ ፣ ያጋንንት ጩኸት
ከታቦቱ ዙርያ...
"አይኔ ነሽ ብርሃኔ
እመቤቴ ማርያም ፣ አብሶማ ለኔ"
እያለ ሚዘምር ፣ ክብ የሰራ ወጣት
ይህንን እያየሁ
ብዙ ጥያቄዎች ፣ ሳምጥ ሳጠራቅም
አንድ አይነ ስውር ሰው...
ፊቴ ተደቀነ ፣ ምፅዋት ሊለቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምነው እመብርሀን
ታደዪ ይመሥል...
አይኔ ነሽ እያለ
አብሶማ እያለ ፣ ወጣቱ ሲዘምር
ምን ይሰማው ይሆን...
ከደጅሽ የመጣ ፣ ምስኪን አይነስውር?
ስል እጠይቃለሁ ፣ ደግሞ እታዘባለሁ
ጥያቄ እያማጥሁ ፣ እንባ እወልዳለሁ፡፡
እዘኝ አዛኝቱ!!!!!
@Simetin_Begitim
#ሞቶ_ማሸነፍን
ፈሪ ሸሽቶ ሊድን — በአፉ ሊሾምበት
ሺ ገዳይ ነኝ ይላል — ሺ ሟች በሌለበት
* * *
በየጦሩ ሜዳ — በየትግሉ አቀበት
ጀግናው ሞቶ አልቆ—ማን ይመስክርበት
* * *
‘ኃሊት ተኪዶ እንኳን — እሬሳ ቢቆጠር
የሞተ ካለ እንጂ — በቃላቱ ጠጠር
አንድም ሰው ላይገኝ—የእሱ ጦር የወጋው
አላዩም ብሎ ነው — ለቀሪው ‘ሚያወጋው
# እኛም # ሁልጊዜ
የተረፈ አግነን — የሞተ እየረሳን
ፈሪ በምላሱ — ሰላም ከሚነሳን
ገዳይ ብቻ ማድነቅ — እዳይሆንብን ሱስ
ሞቶ ማሸነፍን — እንማር ከእየሱስ
* * * * *
ከአርቲስት ቴውድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
######### # #########
ሠናይ ቀን ውብ ውሎ ይሁንላችሁ 💚💛❤️
@Simetin_Begitim
ፈሪ ሸሽቶ ሊድን — በአፉ ሊሾምበት
ሺ ገዳይ ነኝ ይላል — ሺ ሟች በሌለበት
* * *
በየጦሩ ሜዳ — በየትግሉ አቀበት
ጀግናው ሞቶ አልቆ—ማን ይመስክርበት
* * *
‘ኃሊት ተኪዶ እንኳን — እሬሳ ቢቆጠር
የሞተ ካለ እንጂ — በቃላቱ ጠጠር
አንድም ሰው ላይገኝ—የእሱ ጦር የወጋው
አላዩም ብሎ ነው — ለቀሪው ‘ሚያወጋው
# እኛም # ሁልጊዜ
የተረፈ አግነን — የሞተ እየረሳን
ፈሪ በምላሱ — ሰላም ከሚነሳን
ገዳይ ብቻ ማድነቅ — እዳይሆንብን ሱስ
ሞቶ ማሸነፍን — እንማር ከእየሱስ
* * * * *
ከአርቲስት ቴውድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
######### # #########
ሠናይ ቀን ውብ ውሎ ይሁንላችሁ 💚💛❤️
@Simetin_Begitim
#አብረሀም_ሊንከን
እግዚአብሄር ድሆችን ይወዳቸዋል ለዚህም ነው
አብዝቶ የፈጠራቸው በሚል አባባሉ የሚታወቀው
በአሜሪካ ለሚኖሩ ጥቁሮች ሙሉ ነፃነትን ቤት
የማግኘነት መብትን እንዲሁም ጥቁሮች የዩናይትድ
ስቴትስ የጦር ሀይል አባል ሆነው ከነጮች እኩል
ለሀገራቸው ደማቸውን ማፍሰስ መብታቸው እንደሆነ
ያወጀው አስራ ስድስተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
#አብረሀም_ሊንከን ለሠው ልጆች መብት እና እኩልነት ለባረከተው አስተዋጽኦ አለም ዘወትር ስታከብረው ትኖራለች ፡፡
#ከአብረሀም_ሊንከን እኛስ ኢትዮጵያውያን ምን እንማራለን ? መልሡን ለናንተ ትቼአለው ።
ሠናይ ቀን ውብ ውሎ ተመኘውላችሁ💚💛❤️
@Simetin_Begitim
እግዚአብሄር ድሆችን ይወዳቸዋል ለዚህም ነው
አብዝቶ የፈጠራቸው በሚል አባባሉ የሚታወቀው
በአሜሪካ ለሚኖሩ ጥቁሮች ሙሉ ነፃነትን ቤት
የማግኘነት መብትን እንዲሁም ጥቁሮች የዩናይትድ
ስቴትስ የጦር ሀይል አባል ሆነው ከነጮች እኩል
ለሀገራቸው ደማቸውን ማፍሰስ መብታቸው እንደሆነ
ያወጀው አስራ ስድስተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
#አብረሀም_ሊንከን ለሠው ልጆች መብት እና እኩልነት ለባረከተው አስተዋጽኦ አለም ዘወትር ስታከብረው ትኖራለች ፡፡
#ከአብረሀም_ሊንከን እኛስ ኢትዮጵያውያን ምን እንማራለን ? መልሡን ለናንተ ትቼአለው ።
ሠናይ ቀን ውብ ውሎ ተመኘውላችሁ💚💛❤️
@Simetin_Begitim
ለውብ ቀን💚💛❤️
የሙላ ናስሩዲን ጫወታ
ናስሩዲን አንዳንዴ እንደ ሞኝ ይቁጥሩት የለ ፤ አንድ ቀን
የሚያውቁት ሰዎች መንገድ ዳር ቆመው " ነስሩ የፍርድ
ቀንኮ ከሳምንት በኃላ ነው .. እ ለምን ንብረት ሁሉ
የማይጠቅምህ ከሆነ ከፍየሎችህ አንድ ሁለቱን አርደህ
አትጋብዘንም " ይሉታል :: "መርሃባ" አለ ነስሩዲን :: ቤት
ወሰዳቸው ::
ወቅቱ ይወብቅ ነበርና ከቀሚስ ውጪ የደረቡትን ካባ እና
ጥምጣም አንደኛው ክፍል አስቀምጠና ወደ ኸልዋ አመሩ
፤ ፍየሎቹ ተገፈው ተጠብሰው ማዕዱ እስኪመጣ ሊጠብቁ
..
ተበላ ፥ ተጠጣ .. ሊሄዱ ፈለጉ ካባቸው ቢፈለግ የለ ፥
ጥምጣም የለ .. ናስሩዲንን ጠየቁት
"እሳቱን ለማቀጣጠል ከእንጨትጋ ጨምሬዋለሁ"
"ለምን ??" ተበሳጭተው
"የፍርድ ቀንኮ ከ
ሳምንት በኃላ ነው .. ካባ አይጠቅም ወላ
ጥምጣም "::
ሠናይ ውሎ ውብ ቀን
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር
@Simetin_Begitim #Share
የሙላ ናስሩዲን ጫወታ
ናስሩዲን አንዳንዴ እንደ ሞኝ ይቁጥሩት የለ ፤ አንድ ቀን
የሚያውቁት ሰዎች መንገድ ዳር ቆመው " ነስሩ የፍርድ
ቀንኮ ከሳምንት በኃላ ነው .. እ ለምን ንብረት ሁሉ
የማይጠቅምህ ከሆነ ከፍየሎችህ አንድ ሁለቱን አርደህ
አትጋብዘንም " ይሉታል :: "መርሃባ" አለ ነስሩዲን :: ቤት
ወሰዳቸው ::
ወቅቱ ይወብቅ ነበርና ከቀሚስ ውጪ የደረቡትን ካባ እና
ጥምጣም አንደኛው ክፍል አስቀምጠና ወደ ኸልዋ አመሩ
፤ ፍየሎቹ ተገፈው ተጠብሰው ማዕዱ እስኪመጣ ሊጠብቁ
..
ተበላ ፥ ተጠጣ .. ሊሄዱ ፈለጉ ካባቸው ቢፈለግ የለ ፥
ጥምጣም የለ .. ናስሩዲንን ጠየቁት
"እሳቱን ለማቀጣጠል ከእንጨትጋ ጨምሬዋለሁ"
"ለምን ??" ተበሳጭተው
"የፍርድ ቀንኮ ከ
ሳምንት በኃላ ነው .. ካባ አይጠቅም ወላ
ጥምጣም "::
ሠናይ ውሎ ውብ ቀን
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር
@Simetin_Begitim #Share
"ኢልመ ገልማ አባ ገዳ"
-
ርቱዕ ጀማ፥ ብጹዕ ጀማ
ለካ አንተነህ...
አባ ገዳ፥ ኢልመ ገልማ
ያደ ኦሮሞ ሻማ
ዋቃ ገዲኒ፥ ነማ ኦሊኒ
ሱማ፥ አከ ሱማ
የተሰኘው፥ እንደአክሱማ
የተባልከው፥ ፍጹም ጀማ
ለካ አንተነህ......
-
አገ ኦጋ፥ ጂገ ሎጋ
አባ ሰርዳ፥ አባ ገዳ
አባ ፈርድ፥ ነበልባሉ
እም ቅድመ-ኦሪት፥ ባህሉ
ያኢ ቢያ፥ አባ ቃሉ
ቃ’ሉ’፥ የማይቀለበስ ቃሉ
ለካ አንተነህ........
-
ሴኧ’ት፥ አርካ
ኦ’ግ ገዳ፥ የአድባር ዋርካ
ያ’ዴ እናቴ፥ ያዴ እሴቴ
ያ’ዴ አቴቴ፥ ያዴ እቴቴ
ያቴ ኦራ፥ የኩሽ ነዶ
አባ ቦኩ፥ አከሚዶ
ባናትህ ጸሃይ፥ ከለቻ
የምትጠልቅ፥ አንተ ብቻ
የካም ኢደ ኢዶ ምድር
ተነባቢ፥ አስር ምስጢር
አባ ወሮ፥ አባ ወራ
አባ ባሮ፥ አባ በራ
አባ ካሮ፥ አባ ከራ
የጅቡቲም፥ ጀበጂሾ
የመቅዲሾም፥ መቀዲሾ
የነሙቴሳ፥ ከምበልኣ
እንደ ባሮ፥ ከምበልኣ
መነ..ደላ፥ አከ መንደላ
መቀ..ደላ፥ አከ መቅደላ
የፉላኒ፥ ካኖ ደላ
የምትሰኝ፥ የምታሰኝ
የጎና ቤት፥ አባ ከራ
የላሊ ቤት፥ ላሊ በራ
የከረዩ፥ አባ ከራ
በጎፈሬህ፥ ስሪት ላባ
አዶ አዶዬ፥ ውብ ቀዘባ
አዳ የከለቻ ተሸላሚ
የአዱ ግንባር፥ ተቀዳሚ
የአዲስ ዘመን፥ መጸው አደይ
አዳ አዱኛን፥ እልል እሰይ
የምታሰኝ፥ የምትሰኝ
አዱ አዱኛ፥ አባ ቢሌ
የአካ ኪሌ፥ የአባቢሌ
ለካ አንተነህ........
-
ገዳ ገዳም፥ የአለም ሰላም
ገዳ ቢሉሱማ ሳቃ
ፈካ ጉራቻ፥ አካ ዋቃ
የጻህፍት አምላኩ አኒ
ያለበሰህ ድርብ ከኒ
የጥቁር ፥ ፈርኦን ልሳን
የአዴ ኣዳ፥ ፀሃይ ብርሃን
የአዱሊስ፥ አዱኛ ኪዳን
አባ ገዳ፥ አባ በኣል
የቅድመ አክሱማዊት ቃል
የአስርቱ በሮች፥ መሰላል
የማለዳ ንጋት፥ ፀዳል
የኦሩስ፥ ኦሪሳ ተምሳል
ለካ አንተነህ...........
-
ኣገ ኦጋ፥ ጂገ ሎጋ
ያኢ ቢያ፥ አባ ቃሉ
የማይቀለበስ፥ ቃሉ
ርቱዕ፥ ጀማ
የተባልከው፥ አገሱማ
እንደ አክሱማ
ያደ ኦሮሞ፥ ሻማ
አባ ገዳ፥ ኢልመ ገልማ
ለካ አንተነህ..........
(ፀጋዬ ገ/መድህን 1964)
@Simetin_Begitim
-
ርቱዕ ጀማ፥ ብጹዕ ጀማ
ለካ አንተነህ...
አባ ገዳ፥ ኢልመ ገልማ
ያደ ኦሮሞ ሻማ
ዋቃ ገዲኒ፥ ነማ ኦሊኒ
ሱማ፥ አከ ሱማ
የተሰኘው፥ እንደአክሱማ
የተባልከው፥ ፍጹም ጀማ
ለካ አንተነህ......
-
አገ ኦጋ፥ ጂገ ሎጋ
አባ ሰርዳ፥ አባ ገዳ
አባ ፈርድ፥ ነበልባሉ
እም ቅድመ-ኦሪት፥ ባህሉ
ያኢ ቢያ፥ አባ ቃሉ
ቃ’ሉ’፥ የማይቀለበስ ቃሉ
ለካ አንተነህ........
-
ሴኧ’ት፥ አርካ
ኦ’ግ ገዳ፥ የአድባር ዋርካ
ያ’ዴ እናቴ፥ ያዴ እሴቴ
ያ’ዴ አቴቴ፥ ያዴ እቴቴ
ያቴ ኦራ፥ የኩሽ ነዶ
አባ ቦኩ፥ አከሚዶ
ባናትህ ጸሃይ፥ ከለቻ
የምትጠልቅ፥ አንተ ብቻ
የካም ኢደ ኢዶ ምድር
ተነባቢ፥ አስር ምስጢር
አባ ወሮ፥ አባ ወራ
አባ ባሮ፥ አባ በራ
አባ ካሮ፥ አባ ከራ
የጅቡቲም፥ ጀበጂሾ
የመቅዲሾም፥ መቀዲሾ
የነሙቴሳ፥ ከምበልኣ
እንደ ባሮ፥ ከምበልኣ
መነ..ደላ፥ አከ መንደላ
መቀ..ደላ፥ አከ መቅደላ
የፉላኒ፥ ካኖ ደላ
የምትሰኝ፥ የምታሰኝ
የጎና ቤት፥ አባ ከራ
የላሊ ቤት፥ ላሊ በራ
የከረዩ፥ አባ ከራ
በጎፈሬህ፥ ስሪት ላባ
አዶ አዶዬ፥ ውብ ቀዘባ
አዳ የከለቻ ተሸላሚ
የአዱ ግንባር፥ ተቀዳሚ
የአዲስ ዘመን፥ መጸው አደይ
አዳ አዱኛን፥ እልል እሰይ
የምታሰኝ፥ የምትሰኝ
አዱ አዱኛ፥ አባ ቢሌ
የአካ ኪሌ፥ የአባቢሌ
ለካ አንተነህ........
-
ገዳ ገዳም፥ የአለም ሰላም
ገዳ ቢሉሱማ ሳቃ
ፈካ ጉራቻ፥ አካ ዋቃ
የጻህፍት አምላኩ አኒ
ያለበሰህ ድርብ ከኒ
የጥቁር ፥ ፈርኦን ልሳን
የአዴ ኣዳ፥ ፀሃይ ብርሃን
የአዱሊስ፥ አዱኛ ኪዳን
አባ ገዳ፥ አባ በኣል
የቅድመ አክሱማዊት ቃል
የአስርቱ በሮች፥ መሰላል
የማለዳ ንጋት፥ ፀዳል
የኦሩስ፥ ኦሪሳ ተምሳል
ለካ አንተነህ...........
-
ኣገ ኦጋ፥ ጂገ ሎጋ
ያኢ ቢያ፥ አባ ቃሉ
የማይቀለበስ፥ ቃሉ
ርቱዕ፥ ጀማ
የተባልከው፥ አገሱማ
እንደ አክሱማ
ያደ ኦሮሞ፥ ሻማ
አባ ገዳ፥ ኢልመ ገልማ
ለካ አንተነህ..........
(ፀጋዬ ገ/መድህን 1964)
@Simetin_Begitim
እረፉ!
“ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ።
እረፍ!
“ቆሜያለሁ!” ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘናህ ቆዳዬን አትግፈፍ።
እረፍ!
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየአልጋህ እደር በየእንቅልፍህ አልም።
እረፊ!
በኩረጃ ንባብ ትርጉም አትግደፊ
በሰባራ መርፌሽ የሰው ልክ አትስፊ።
.
.
.
.
ማን አንደጠለፈኝ ማን እንደሰበረኝ
ጠያቂ አጣሁ እንጂ መልስማ ነበረኝ።
ምክንያት ታመመ መፍትሄ ታመመ
ከጥያቄው በፊት መልሱ እየቀደመ።
ሌብነት ገነነ
ግርግር ገነነ
ብልጭልጭ ገነነ
ድንግርግር ገነነ
ኪሳራ ገነነ
ደላሎች ገነኑ፣ ደላሎች ጀገኑ
ባልዋለ ገበያ ዋጋ እየተመኑ!!!!!
©ከእያዮ ፈንገስ ተውኔት
ደራሲ :-በረከት በላይነህ
ተዋናይ ግሩም ዘነበ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
“ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ።
እረፍ!
“ቆሜያለሁ!” ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘናህ ቆዳዬን አትግፈፍ።
እረፍ!
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየአልጋህ እደር በየእንቅልፍህ አልም።
እረፊ!
በኩረጃ ንባብ ትርጉም አትግደፊ
በሰባራ መርፌሽ የሰው ልክ አትስፊ።
.
.
.
.
ማን አንደጠለፈኝ ማን እንደሰበረኝ
ጠያቂ አጣሁ እንጂ መልስማ ነበረኝ።
ምክንያት ታመመ መፍትሄ ታመመ
ከጥያቄው በፊት መልሱ እየቀደመ።
ሌብነት ገነነ
ግርግር ገነነ
ብልጭልጭ ገነነ
ድንግርግር ገነነ
ኪሳራ ገነነ
ደላሎች ገነኑ፣ ደላሎች ጀገኑ
ባልዋለ ገበያ ዋጋ እየተመኑ!!!!!
©ከእያዮ ፈንገስ ተውኔት
ደራሲ :-በረከት በላይነህ
ተዋናይ ግሩም ዘነበ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"እርሙን ተደፋፍሮ ፣ አንድ ቀን ቢዋጋ
አላስቀምጥ አለን
በየ መድረኩ ላይ ፣ ያንኑ እያወጋ"
ያለውን ባናውቅም
እኛም እንላለን
"ነፍጠኛ" ሲባል ፣ ወይ
እነሱም ይላሉ ፣ " ወዬ " ሲባል "መንጋ"
ሳይጠሩት አቤት ባይ
ሁለት መንጋ መሃል ፣ ሀገር ተሰንጋ
እንዴት ብሎ ይንጋ?
ነፍጠኛ አይደሉም ወይ ፣ እነ ጃገማ ኬሎ ፣ እነ
አብዲሳ አጋ
@Simetin_Begitim
አላስቀምጥ አለን
በየ መድረኩ ላይ ፣ ያንኑ እያወጋ"
ያለውን ባናውቅም
እኛም እንላለን
"ነፍጠኛ" ሲባል ፣ ወይ
እነሱም ይላሉ ፣ " ወዬ " ሲባል "መንጋ"
ሳይጠሩት አቤት ባይ
ሁለት መንጋ መሃል ፣ ሀገር ተሰንጋ
እንዴት ብሎ ይንጋ?
ነፍጠኛ አይደሉም ወይ ፣ እነ ጃገማ ኬሎ ፣ እነ
አብዲሳ አጋ
@Simetin_Begitim
ለፈገግታ😂😂😂
ሜሪ: ቢራ ትጠጣለህ?
ዲ: አዎ
ሜሪ: በቀን ምን ያህል ትጠጣለህ
ቴዲ: ሶስት ቢራ
ሜሪ: 1 ቢራ ስንት ነው?
ቴዲ: 15 ብር
ሜሪ: ለስንት አመት ጠጥተሃል?
ቴዲ: 20 አመት ብቻ
ሜሪ: አየህ እስከዛሬ ለቢራ በቻ
324,000 ብር አውጥተሃል
ያንን ገንዘብ ቆጥበህ ቢሆን
ከነ ወለዱ አውሮፕላን ትገዛ
ነበር!
ቴዲ: አንቺ ቢራ ትጠጫለሽ?
ሜሪ: አልጠጣም
ቴዲ: የታለ አውሮፕላንሽ?
😳😳😳😳😳😳
@Simetin_Begitim
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
ሜሪ: ቢራ ትጠጣለህ?
ዲ: አዎ
ሜሪ: በቀን ምን ያህል ትጠጣለህ
ቴዲ: ሶስት ቢራ
ሜሪ: 1 ቢራ ስንት ነው?
ቴዲ: 15 ብር
ሜሪ: ለስንት አመት ጠጥተሃል?
ቴዲ: 20 አመት ብቻ
ሜሪ: አየህ እስከዛሬ ለቢራ በቻ
324,000 ብር አውጥተሃል
ያንን ገንዘብ ቆጥበህ ቢሆን
ከነ ወለዱ አውሮፕላን ትገዛ
ነበር!
ቴዲ: አንቺ ቢራ ትጠጫለሽ?
ሜሪ: አልጠጣም
ቴዲ: የታለ አውሮፕላንሽ?
😳😳😳😳😳😳
@Simetin_Begitim
🤩🤩🤩🤩🤩🤩
#እውነቱን ተናግሮ አሳዳሪ ማጣት
እውነቱን ተናግሮ
የመሸበት ማደር
እያለ ሲሰብከኝ ፣ የመሸበት ሀገር
ስሰማና ሳምን ፣ ቆይቼ ሰንብቼ
በድንገት መሽቶብኝ ፣
አንቺ ጋር ለማደር ፣ ከቤትሽ መጥቼ
እወነቱን ብናገር ፣ ባልሽ ግን ጠመደኝ
እንኳን ሊያሳድረኝ
መዋያ አሳጣኝ ፣ ቀን እያሳደደኝ
ዳሩ ብሳደድም
እውነቱን ተናግሮ
በነጋበት መሸሽ ፣ እንዳለ አልዘነጋም
እውነቴም አንቺው ነሽ
ስትሔጅ መሽቷል ፣ ካልመጣሽ አይነጋም
✍በላይ በቀለ ወያ
#መልካም የትምህርት እና የስራ ቀን ውብ ሰኞ ተመኘንላችሁ፡፡
@Simetin_Begitim
እውነቱን ተናግሮ
የመሸበት ማደር
እያለ ሲሰብከኝ ፣ የመሸበት ሀገር
ስሰማና ሳምን ፣ ቆይቼ ሰንብቼ
በድንገት መሽቶብኝ ፣
አንቺ ጋር ለማደር ፣ ከቤትሽ መጥቼ
እወነቱን ብናገር ፣ ባልሽ ግን ጠመደኝ
እንኳን ሊያሳድረኝ
መዋያ አሳጣኝ ፣ ቀን እያሳደደኝ
ዳሩ ብሳደድም
እውነቱን ተናግሮ
በነጋበት መሸሽ ፣ እንዳለ አልዘነጋም
እውነቴም አንቺው ነሽ
ስትሔጅ መሽቷል ፣ ካልመጣሽ አይነጋም
✍በላይ በቀለ ወያ
#መልካም የትምህርት እና የስራ ቀን ውብ ሰኞ ተመኘንላችሁ፡፡
@Simetin_Begitim
ፈገግ የሚያሰኝ እውነታ😂😂😂
አሁን ባለው አስተሳሰባችን "ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው " ሲባል ሊከፋው የሚገባው ሰው ሳይሆን ዝንጀሮ ነው
😏
©ዝንቅ መዝናኛ
@Simetin_Begitim
@WalyasHood
አሁን ባለው አስተሳሰባችን "ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው " ሲባል ሊከፋው የሚገባው ሰው ሳይሆን ዝንጀሮ ነው
😏
©ዝንቅ መዝናኛ
@Simetin_Begitim
@WalyasHood
<<
ዕንቁራሪቶች ሀይቁ ዳር ተሠብስበው አብዝተው
ስለጮሁ ሀይቁ የእንቁራሪቶች ነው
ማለት አይደለም ፡፡
ለክብራቸው ሲሉ ዝም ያሉ ብዙ አሳውች ሀይቁ ውስጥ
አሉ!
>>
እኔ አይደለም ያልኩት
ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድን ነው።
©ከወዳጄ የFb ገፅ የተመነተፈ
@Simetin_Begitim
ዕንቁራሪቶች ሀይቁ ዳር ተሠብስበው አብዝተው
ስለጮሁ ሀይቁ የእንቁራሪቶች ነው
ማለት አይደለም ፡፡
ለክብራቸው ሲሉ ዝም ያሉ ብዙ አሳውች ሀይቁ ውስጥ
አሉ!
>>
እኔ አይደለም ያልኩት
ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድን ነው።
©ከወዳጄ የFb ገፅ የተመነተፈ
@Simetin_Begitim
ለውብ ቀን የሙላ ነስሩዲን ጫወታ 💚💛❤️
አንድ ቀን ነስሩዲን መርከብ ተከራይቶ ለንግድ ወደሌላ
ሀገር ይሄዳል መሀል ላይ ማእበሉ መርከቧን ሊገለብጣት
ደረሰ የመርከቧ ካፒቴን ጸልዩ አላቸው ሁሉንም ሰራተኞቹ
መጸለይ ጀመሩ ናስረዲን ጋ ሲመጡ ዘና ብሎ ቁጭ ብሏል
ጸልይ እንጂ ሲለው ካፒቴኑ አልጸልይም ገንዘቤን ከፍዬ
እኮ ነው የምሄደው እናንተ ጸልዩ!!
መልካም ቀን ውብ ውሎ ተመኘንላችሁ!!
@Simetin_Begitim
አንድ ቀን ነስሩዲን መርከብ ተከራይቶ ለንግድ ወደሌላ
ሀገር ይሄዳል መሀል ላይ ማእበሉ መርከቧን ሊገለብጣት
ደረሰ የመርከቧ ካፒቴን ጸልዩ አላቸው ሁሉንም ሰራተኞቹ
መጸለይ ጀመሩ ናስረዲን ጋ ሲመጡ ዘና ብሎ ቁጭ ብሏል
ጸልይ እንጂ ሲለው ካፒቴኑ አልጸልይም ገንዘቤን ከፍዬ
እኮ ነው የምሄደው እናንተ ጸልዩ!!
መልካም ቀን ውብ ውሎ ተመኘንላችሁ!!
@Simetin_Begitim