ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.37K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
3.3K ቤተሠብ ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ስለኢትዮጵያ ብቻ ወጋቸው ያደረጉ አባላት አፍርተናል ፡፡ ወጋችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት ስለ ኢትዮጵያ ኑ አብረን እንስበክ ፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ተራ የመንደር አጥር ምትፈርስ ሳይሆን ከፀና አለት የተሠሰራች ግንብ ናት ፡፡ አናፂዋም ስለ ኢትዮጵያ መቼም አያንቀላፋም ፡፡

ለወዳጅዎ #share በማድረግ ብዙ ወዳጆችን አብረን እናፍራ፡፡ ግጥም ፣ አስተማሪ ፅሁፎች ካላችሁ በ @Simetin_Begitimbot እና @Haile_melekot ይላኩልን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@Simetin_Begitim
መውደቅን ሳይሆን አለመነሳትን ፍራ ፡፡ አለም ላይ ሀያል እሚባሉ ሀገሮች ሰዎች ሁላ ብዙ የውድቀት ታሪክ አላቸው ፡፡ ነገር ግን ውድቀትን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው ስህተታቸውን አርመው አንቱ ለመባል በቅተዋል ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ከውድቀት ወደ ውድቀት እያመራን በስንፍና እና በሞቀ ድህነት ውስጥ ተጠቅልለን እየተኛል የ3000 ዓመት ታሪክ ባለቤት ነን እያልን እንኩራራለን ፡፡ ወዳጄ ሆይ ንቃ አንቺም እህቴ ንቂ አሁን እያመራን ያለነው ወደ ቁልቁለት ነው ሳላማችን ቁልቁል እየሄደ ነው ጨዋነታችን ቁልቁል ተመዘግጎ ገደል ገብቷል ወድቆ መነሳት ከታሪካችንም እሚከብደን ስለሆን እንንቃ የኢትዮጵያ ቤዛ አዲሱ ትውልድ ነው ከታሪክ ተምሮ እና መርምሮ ካለንበት የውድቀት ጎዳና እሚሻግረን የአዲሲቱ ኢትዮጵያ ቤዛ ወጣቶች ናቸው ፡፡
🇪🇹ኢዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ🇪🇹
🇪🇹ወድደቅ መሸነፍ አይደለም🇪🇹
🇪🇹የኢትዮጵያ ቤዛ እኔ ነኝ 🇪🇹🇪🇹

#ኢትየጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር!
#ይህን መልክት #Share በማድረግ ለወዳጅዎ የጋሩ
@Simetin_Begitim
#ኢትዮጵያዊ
#ወጎች
👌ግጥም
👌ወግ
👌ትምህርታዊ ፅሁፎች
እና ስለ ኢትዮጵያዊነት ብቻ እምናወጋበት Channel ወጋችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት በቅንነት ለወዳጅዎ #Share ያድርጉ ፡፡

@Simetin_Begitim
ውድድሩ ሊያልቅ የቀረው 28 ደቂቃዎች ብቻ ነው የውጤት ለውጥ እንዲኖር #Share ያድርጉ፡፡

@Simetin_Begitim
ለውብ ቀን💚💛❤️
የሙላ ናስሩዲን ጫወታ

ናስሩዲን አንዳንዴ እንደ ሞኝ ይቁጥሩት የለ ፤ አንድ ቀን
የሚያውቁት ሰዎች መንገድ ዳር ቆመው " ነስሩ የፍርድ
ቀንኮ ከሳምንት በኃላ ነው .. እ ለምን ንብረት ሁሉ
የማይጠቅምህ ከሆነ ከፍየሎችህ አንድ ሁለቱን አርደህ
አትጋብዘንም " ይሉታል :: "መርሃባ" አለ ነስሩዲን :: ቤት
ወሰዳቸው ::
ወቅቱ ይወብቅ ነበርና ከቀሚስ ውጪ የደረቡትን ካባ እና
ጥምጣም አንደኛው ክፍል አስቀምጠና ወደ ኸልዋ አመሩ
፤ ፍየሎቹ ተገፈው ተጠብሰው ማዕዱ እስኪመጣ ሊጠብቁ
..
ተበላ ፥ ተጠጣ .. ሊሄዱ ፈለጉ ካባቸው ቢፈለግ የለ ፥
ጥምጣም የለ .. ናስሩዲንን ጠየቁት
"እሳቱን ለማቀጣጠል ከእንጨትጋ ጨምሬዋለሁ"
"ለምን ??" ተበሳጭተው
"የፍርድ ቀንኮ ከ
ሳምንት በኃላ ነው .. ካባ አይጠቅም ወላ
ጥምጣም "::
ሠናይ ውሎ ውብ ቀን
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር

@Simetin_Begitim #Share
#ለሰላም_የምችለውን_ሁሉ_አደርጋለሁ!

1ሚሊዮን ተከታይ የለኝም። ቢያንስ እያንዳንዳቸው 1000 ጓደኛ ያላቸው እስከ 5000 ጓደኞች ግን አሉኝ።

#ከዛሬ_ጀምሮ_በሃገሬ_ጉዳይ_ዳር_ቁጭ_ብዬ_ተመልካች_ላለመሆን_ቃል_እገባለሁ

እናንተስ?

#ሰላምለኢትዮጲያ
#PeaceForEthiopia

#ሼር #share
አብዛኛዎቹ የዓለም ሀገራት ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ አቁመዋል፡፡ የኛው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን እስከዛሬዋ ቀን ድረስ አላቆመም ፡፡ ይህ ገዳይ ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ ቢገባ ተጠያቂው አንድና አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው ፡፡ ሀገራችን እያጋጠማት ያለው የፖለቲካ ቀውስ ሳያንስ ደህና ጤና ጠቢያ እንኳን የሌላት ሀገራችን እንዲህ አይነት ወረርሽኝ ገባ ማለት በታሪካችን የማንወጣው በችግር ላይ ችግር በሀዘን ላይ ሀዘን በቀውስ ላይ ቀውስ ነው የምናየው እሡንም በህይወት ከተረፍን ፡፡ እናም እንደኔ እይታ ከሆነ አየር መንገዳችን በቶሎ እርምጃ መውሰድ አለበት ፡፡
#Share
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ሼር #SHARE

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች፦

COVID-19 በትኩሳት እና ደረቅ ሳል ይጀምራል። ከሳምንት በኋላ የመተንፈስ ችግር ያጋጥማል። በበሽታው የተያዘ ሰው እስከ 14 ቀናት ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች የበሽታ ምልክት ሳያሳዩ በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ።

ኮሮና ቫይረስ መድሃኒት አለው?

ቫይረሱን ከሰውነት ውስጥ የሚያስወግድ መድሃኒት የለም። ሃኪሞች በሽተኞችን እያከሙ የሚገኙት የታማሚዎችን የበሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ በማድረግ ነው።
ለመተንፈስ የሚረዱ ቁሶችም ጥቅም ላይ ይውላሉ።

እራሴን ከቫይረሱ እንዴት ነው መጠበቅ የምችለው?

የዓለም ጤና ድርጅት የሚከትሉትን እንዲያደርጉ ይመክርዎታል፦

- እጅዎን ይታጠቡ- ቫይረሱን ሊገድሉ በሚችሉ ሳሙናዎች

- በቫይረሱ የተበከሉ ነገሮችን ሊነኩ ስለሚችሉ፤ በእጅዎ ዓይን፣ አፍ እና አፍንጫዎን ከመነካከት ይቆጠቡ።

- ወደ የሚያስነጥሱ፣ የሚያስሉ እና ትኩሳት ወዳለባቸው ሰዎች አይጠጉ። ቢያንስ የ1 ሜትር እርቀት ይፍጠሩ።

- ሲያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን ይሸፍኑ - ከዚያም እጅዎን ይታጠቡ። ይህን ማድረግዎ በቫይረሱ ተይዘው ከሆነ የማሰራጨት ዕድልዎን ያጠባሉ።

በቫይረሱ እርሶ ወይም ሌሎች መያዛቸውን ከተጠራጠሩ፦ እራሰዎን ያግልሉ፤ በቤትዎ ይቆዩ ሌሎችም ተመሳሳይ እንዲያደርጉ የበኩልዎን ይወጡ። 8335 ላይ በመደወል ለማሕብሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በፍጥነት ያሳውቁ።

ምንጭ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መደናገጥ እና አጉል ፍራቻ፣ ከበሽታው እኩል አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ!

ጠቃሚ ምክሮች፦

- ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል መራቅ
- እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን አይንኩ
- ከሰዎችጋር አይጨባበጡ፣
- እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣
- ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣
- በሚያነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣
- በስራ ቦታ፣በትራንስፖርት እና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣
- መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ!

#ሼር #SHARE

#ጤናሚኒስቴር
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት፦

በአገራችን በዛሬው እለት አንድ ኮሮና ቫይረስ ያለበት ሰው የተገኘ በመሆኑ ህብረተሰቡ እነዚህን ምክሮች በመከተል እራሱን እና ቤተሰቦቹን ከበሽታው እንዲከላከል አሳስባለሁ።

- እጃችንን በውሃ እና በሳሙና አዘውትሮ መታጠብ

- የጉንፋን ምልክት ከታየብን ከቤት አለመውጣት፣ ሰው የሚበዛብት ቦታ አለመሄድ

- ንክኪ የሚያስፈልጋቸው የሰላምታ መንገዶችን መተው

- ሰው በብዛት የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከሆነ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ

- ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ በንቃት የራሱን እና የቤተሰቡን ጤና መጠበቅ

#DrAbiyAhmed

#Share
የፊት ማስክ አጠቃቀም እና አወጋገድ

- የፊት ማስኮን ከማድረግ በፊት እጅም በሳሙና መታጠብ።

- በማስኩ አፍና አፍንጫን መሸፈን ምንም ክፍተት ሳይኖረው።

- ማስኩ አፍንጫዎ ላይ እንደተመጠ እንዲቆይ የአፍና የአፊንጫዎን ጠርዝ በጣቶ መጫን።

- ማስኩን በሚያወልቁበት ወቅት ክዳን ባለው ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ይጣሉት ወይንም ያቃጥሉት።

- ማስኩን አድርገው እያለ ማስኩን በእጆ ባይነኩ ይመረጣል። ለመንካት ከፈለጉም እጆን በሳሙና ታጥበው መሆን አለበት


#ሼር ያድርጉ
#Share it
Forwarded from ዝንቅ መዝናኛ (Mr. Nobody)
ሁልሽም ፕሮፋይልሽን ወደ ጥቁር ከመቀየርሽ በፊት እንጠንቀቅ!!

ብዙ እድል ተሰጥቶናል፤ በአግባቡ እንጠቀምበት። ይህ በሽታ በመንግስት አቅምና ጥንካሬ ሳይሆን በግለሰቦች ጥንቃቄ ስለሆነ የጉዳት መጠኑ የሚወሰነዉ እያንዳንዳችን የግላችንን ጥንቃቄ እናድርግ። በኃላ ማንም ተወቃሽ ማንም ወቃሽ መሆን አይችልም በዚህ ጉዳይ። ጣሊያን፣ ስፔን፣ አሜሪካና ኢራን ከኛ የተሻለ የጤና አጠባበቅ system አላቸዉ፤ ግን አልዳኑም። ጣሊያን ዛሬ ከቻይና የበለጠ ሞት በትንሽ ጊዜ አስመዝግባለች። ወገኖቼ የአየር መንገድ በራራ በማስቆም ቢሆን ጣሊያንን አሜሪካ እንኳን አልቀደመቻትም። ግን የሚሆነዉን እያየን ነዉ። ትላንት ጣሊያን የአለም ሪከርድ የሆነዉን የሞት መጠን አስመዝግባለች። ስለዚህ ለሁሉም ነገር ሰበብ መፈለጉንና ጣት መጠቋቀሙን ትተን በግል እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ ጥንቃቄ እናድርግ። ይህ በንዝህላልነት በኢትዮጵያ ላይ ብቻ የመጣ ጋሬጣ ሳይሆን በአለማችን ላይ ዘር፣ ቀለም ሳይል የመጣ የሁላችንም ፈተና ነዉ። አንድ ላይ ከተባበርን፣ እያንዳንዳችን የየራሳችንን ኃላፊነት ከተወጣን ይህን ወረረሽኝ ብዙ እልቂት ሳያስከትል መቆጣጠር እንችላለን። ካልሆነ ግን ነገ ፕሮፋይል አይደለም ቆዳችንን ብንገለብጥ ምንም ለዉጥ አናመጣም። ዛሬም ያለንን ትንሽ ሰዓት ቁም ነገር እንስራበት።

የወረረሽኙን መጠንና ክብደት ያልተረዱ ብዙ ወገኖች ስላሉ ይህንን መልዕክት በሁሉም ሶሻል ሚድያ ላይ በማጋራት የበኩላችንን እንወጣ።

#Share
#Please
#BeSeriousCoronaIsSerious

@ZiniQ ዝንቅ መዝናኛ
🖍አስርቱ ˝የመ˝ ሕጎች - ለኮሮና‼️

👉መታጠብ (በሳሙና / በሳኒታይዘር )
👉መጉመጥመጥ (ውሀ ለብ አርገህ በትንሽ ጨው)
👉መጥረግ (በአልኮል )
👉መራራቅ (ስትቆሙ/ስትቀመጡ )
👉መታቀብ (ከመጨባበጥ /ከንክኪ )
👉መተው (ስብሰባ/ህዝብ የሚበዛበት ቦታ
👉መቀመጥ (ቤትህ /ሆቴል ውስጥ )
👉መመገብ (በሽታ ለመቋቋም )
👉መከታተል (መረጃን ከታማኝ ምንጭ )
👉መፀለይ (ወደ ፈጣሪ )

VIA ዶክተር አለ 8809

#SHARE ይደረግ
ጠቃሚ መልዕክት!

🧼 እጃችሁን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ታጠቡ

👋🏾 አትጨባበጡ/አትሳሳሙ

🙅🏽‍♀️ ማህበራዊ መስተጋብርን በጣም ቀንሱ!

አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ከቤት አትውጡ

☎️ ትኩሳት ፣ ሳል እና ትንፋሽ ማጠር...ምልክት ከታየባችሁ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ነፃ የስልክ መስመሮች ይደውሉ ፦

አዲስ አበባ - 8335 /952 ፣ ትግራይ ክልል - 6244 ፣ አፋር ክልል - 6220 ፣አማራ ክልል - 6981 ፣ ኦሮሚያ ክልል - 6955 ፣ ሱማሌ ክልል - 6599 ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል - 6016፣ ደቡብ ክልል - 6929 ፣ ሀረሪ ክልል - 6864 ፣ ጋምቤላ ክልል - 6184፣ ድሬዳዋ ከተማ - 6407

#SHARE #ሼር

#HaymanotGirma
💐ጠዋት ጠዋት ትዳር ያምረኛል ! ..

ሁሌም ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ሚስት ማግባት ያምረኛል። በቃ አለ አይደል ልክ እንደ
አማርኛ ፊልም ሚስቴ ቀድማኝ ተነስታ ሸሚዜን ለብሳ በዚያ ውብ እግሯ ቤት ውስጥ ሽር
ጉድ ብላ ሚገርም ቁርስ ከጁስ ጋር ሰርታልኝ በልቼ ምናምን ቡናዬን ጠጥቼ። የተተኮሰ
ልብስ ራሷ መርጣ አምጥታልኝ እሱን ለብሼ እስከበር ድረስ ሸኝታኝ ከንፈሯን ስሜ ቀኔን
ረሃ ሆኜ ብጀምር ደስ ይለኝ ነበር።
But ... life is not like z movie my brother!! ሁሉም ወንድ ሊያገባ ሲወስን የሚታየው
ከላይ የገለፅኩት አይነት ህይወት ነው። በርግጥ እህቶችም የሚሰሩን ሿሿ ቀላል አይደለም
ብራዘር ድንገት ቺክህ የወንደላጤ ቤትህ ከመጣች በምቾት ታጨናንቅሃለች።
ትንከባከብሃለች። በአንድ ድስት ሰባት አይነት ወጥ ስትሰራ “አረረረ ጆርዳና in the
house” ምናምን ብለህ ትቀውጠዋለህ። እየተሽከረከረች ያቺኑ አንድ ክፍል ቤትህን
ታፀዳለች። እንደ ስፓይደር ማን ግድግዳው ላይ ተራምዳ ሁሉ ኮርኒስህን ልትወለውል
ትችላለች። አንተ እያወለቅክ አልጋህ ስር የጣልከውን ካልሲ ፈገግታ ከፊቷ
ሳይጠፋ (በሆዷኮ ይሄ በስባሳ እያለችህ ነው) አውጥታ አጥባ እንደቋንጣ ታሰጣልሃለች።
በቃ ምን አለፋህ ከሷ ጋር መኖር ሰቨን ስታር ሆቴል አዘግቶ መዝናናት እንዲመስልህ
ታደርግሃለች። ባራት እንቁላል አምስት አይነት ወጥ ሰርታ ስታበላህ እነዚህ አድሃሪና ቡርዧ
የሆቴል ቤት ባለቤቶች ሲበዘብዙህ እንደኖሩ ይሰማሃል! እሷን ማግባት ትመኛለህ። ትዳር
ማለትኮ .... እያልክ ለጓደኞችህ ማብራራት ትጀምራለህ። የሙሽራ መኪና ስታይ አይንህ
ይንከራተታል። እንተዋወቃለን ወይ? የሚለው ፕሮግራም ቋሚ ደምበኛ ትሆናለህ። በቃ
ፋይናሊ ሽማግሌ ትልካለህ። እናትና አባቷ በየቀኑ « አንቺ ልጅ አግብተሽ አትፋቺንም
እንዴ ?» ሲሏት እንዳልኖሩ እየተጀነኑ ምን አለው? ማን ነው? ምናምን ብለው በመከራ
ይፈቅዱልሃል!
ከዛ መልአኳ እጮኛህ ስለሰርግ ትጀነጅንሃለች። እንደጀነጀነችህ ግን አትባንንባትም።
በስታየል ነው ምታሰምጥህ። አለ አይደል «እኔኮ ሰርግ አሎድም ግን እነማሚ
እንዳይከፋቸው አነስ ያለች አንድ መቶ ሰው ብቻ ጠርተን ቀለል አርገን እንደግስ .. ግን
ካልተመቸህ ይቅር» ትልሃለች! አረ ጣጣ የለውም ምናምን ብለህ እድሜ ልክህን ኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ ተሰልፈህ የቆጠብካት ፍራንክህ ላይ ትፈርድባታለህ!
እናቱ ቀለል ያለ ያለችውን ሰርግ የ አንድ ሺ ሰው ካርድ በማሰራት ትጀምረዋለች
ቀለል አርጋ የሃያ ሺ ቬሎ፣ ቀለል አርጋ ሜካፕ ሰላሳ ሺ ፣ ቀለል አርጋ ሊሞ ሃምሳ ሺ ፣
ወዘተ ብላ በአንዴ ከአበዳሪ ሐገራት ተርታ አውጥታህ ኢኮኖሚህን በጠረባ ትጥለዋለች።
የሰርግህ ቀን በሰው መኪና እንደታቦት አደባባይ ሲያዞሩህ ይውሉና አንተ የማታውቀውን
አንድ ሺ ሰው ሆድ ሞልተህ እጅህን እያጠላለፍክ ኬክ ትጎራረስና በአደባባይ ሃብቴ ሃብትሽ
ነው ብለህ ፈርመህ ኮትህን አንጠልጥለህ ወደቤት ይዘሃት ትገባለህ!!
የመጨረሻው መጀመሪያ! እንዲል የድሮ ደራሲ the tragic part of your life begins :
ጠኋት ከእንቅልፍህ የሚገርም የጀነሬተር ድምፅ ያነቃሃል! ብንን ስትል እያንኮራፋች ነው
ካሁን አሁን ተነስታ ምርጥ ቁርስ ሰራችልኝ ብለህ ብትጠባበቅ እናቱ ተኝታ
ህልም እየቀያየረች ታያለች። ምርር ሲልህ ትቀሰቅሳታለህ። ጠላትህ ቅይር ይበል በዚያ
ሻካራ ድምጿ አፍጥጣ « ሰው ከእንቅልፌ ሲቀሰቅሰኝ ደስ አይለኝም » ብላ ተመልሳ
ትተኛለች። በሆድህ “ እቺ ነገር ያቺ ነገር ነች ?” እያልክ ፆምህን ወደስራ ስትወጣ በር ላይ
ለሰርግ ብር ጎሎህ የተበደርከው ሰውዬ ከቦክሰኛ ልጁ ጋር ይጠብቅሃል ... ......., ..
ምፅ እኔ አፈር ልብላ!
ማታ ቤት ስትገባ ካልሲዎችህ በር ላይ ተከምረው ይጠብቁሃል! እሱን አጥበህ
ስትጨርስ ጨው እንደ Dead sea የበዛበት ሽሮ ወጥ ይቀርብልህና “ከበላህ ብላ ካልበላህ
አፈር ብላ” ትባላለህ!
በዘጠኝ ወሯም አንድ ጩኸታም ፈልፈላ ትወልድልሃለች። በየደቂቃው ዋኣኣይ ነው።
በየሰከንዱ ኡኡ ነው። አናትህን ያዞረዋል። በመስኮት አውጥተህ ወርውረው ወርውረው
ይልሃል። ለሊት ይነሳና ይቀውጠዋል። እሷ ምርር ሲላት ላሽ ትለዋለች። ቢቸግርህ ተነስተህ
ጡጦ ትሰጠውና ተመልሰህ ተኝተህ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርግህ ጡጦውን ሻት አርጎት
እንደገና ዋኣኣይ ይላል። በቃ ትነቅላለህ! ይሄ ሰውዬ ለምን አይተወኝም ግን? ትላለህ።
የሶስት ወሩን ልጅ “ና ልብ ካለህ ወጥተን እንነጋገር ” ምናምን ሁሉ ልትለው ትችላለህ :
በገባህ በወጣህ ቁጥር ያ በደጉ ግዜ ስንት ነገር ያሳየህ ጡቷ ላይ እንደአልቂት ተጣብቆ
ሲመጠምጣት ደምህ ይፈላል። ዘመዶቿ አያልቁም ዛሬ አባቷ ፣ ነገ አጎቷ፣ ከነጎዲያ አክስቷ
እየመጡ ጠብ እርግፍ ብለህ ታስተናግዳለህ። እሱ ሳይበቃቸው ምነው ጠቆርሽ? ምነው
ከሳሽ? እያሉ ወፍራ ጆንሲናን ያከለችውን ሴትዮ ይጨቀጭቋታል። ፕራይቬት ላይፍ ብሎ
ነገርህ ይናፍቅሃል! ብቸኝነትህ በአይንህ ውል ይልብሃል!
ለሊት አንተ የልጅህን ዳይፐር ለመቀየር ስትታገል ፍሬንዶችህ ክለብ ሆነው ይደውሉልህና
ዘፈን ይጋብዙሃል! ሲኦል ሆነህ ከመንግስተሰማይ ሚደወልልህ ያህል ትቀናለህ ! ከዚያ
ህይወትህን መለስ ብለህ በትካዜ ታስታውሰዋለህ። ከዚያም ሴትየዋ ከትዳር በፊት የነበራት
ማራኪ ባህሪ የምርጫ ቅስቀሳ መሆኑ ይገባህና “All women are politicians ” ብለህ
መፈላሰፍ ትጀምራለህ።
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
#Share_share_it

🙌እጃችሁን መታጠብ እንዳረሱ😷

@endenaendena
@endenaendena

@simetin_begitim
@simetin_begitim