ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.43K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
ትላንት መስከረም 17 የመሥቀል
ዕለት የንጉሡ ልደት ነበር ፡፡ ንጉሡን ሣናስታውሠው በማለፋችን በኢትዮጵያዊ ወጎች ስም ይቅርታ እንጠይቃለን ፡፡
ነገር ግን ዛሬ ቀኑን ሙሉ ንጉሡን ጥልዬን ስናስታውስ እንውላለን ፡፡
# መስከረም 17 የሀገር ልጅ ጥላሁን ገሠሠ ልደት
//ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ እና የ 1953ቱ
መፈንቅለመንግስት //
# ኢዮብ ዘለቀ
"የመፈንቀለ መንግስት ሙከራው በተካሄደ በአራተኛው ቀን
መሰለኝ ጃንሆይ ጉብኝታቸውን አቋርጠው አዲስ አበባ ገቡ
።አሁን አገር ሰላም ነው አልሁና እኖርበት ወይም በጭንቅ
ሆኜ ሁኔታውን እከታተልበት ከነበረው ፊት በር እየተባለ
ከሚጠራው ሰፈር ወጣሁና አራት ኪሎ አቶ ሻወል ቤት
ገባሁ ።ለካ ጦር ሰራዊት ይከታተለኛል ።ድንገት ጀርባዬን
በሰደፍ ደቅኖ ቀጥል አለኝ ።
ከዛ ሌሎችም በጥፊ በርግጫ እያዳፋ እንዲያውም
የሌለኝን መአረግ ሁሉ እየስጡኝ ''የኛ መቶ አለቃ!
የሾሙህ የሸለሙህ ጃንሆይ መጥተዋል ምን ይዋጥህ?
አንተ ከሀዲ! ለሰንደቅ አላማህና ለንጉስህ የገባህውን ቃል
በልተህ መንግስት ልትገለብጥ ሞከርህ አይደል..
..''አሳሬን ያሳዩኝ ጀመር። መልስ ለመስጠትና ''መቶ አለቃ
ቀርቶ ወታደር አይደለሁም ፤ሲቪል ነኝ '' ብዬ ለመናገር
እንኳ ፋታ አልሰጡኝም ።ቁም ስቅሌን አሳዩኝ ።በዚህ
አይነት ሁኔታ መከራዬን እያሳዩ ወስደው አሁን ሸራተን
አዲስ ወደ ተሰራበት አካባቢ ከነበረ ሽንት ቤት ውስጥ
አስገቡኝ ።እውነት ለመናገር ያን ሁሉ መከራ ከማየት ያን
እለት ብሞት እመርጥ ነበር ።
አንዴ በርግጫ ፣ሊያውም በወታደር ጫማ ፣እንደገና በጥፊ
፣እንደገና በቆመጥ.. ....እረ ስንቱ ይነገራል? እና እንዲህ
እንደ አውድማ ላይ ገብስ ሲወቁኝ ውለው ሽንት ቤት
ከዘጉብኝ ከተወሰነ ሰአት በኃላ ''አራተኛ ክፍለጦር
''ወሰዱኝ ።
እዚያ ስደርስ የያዙኝ ወታደሮች በኩርንችት ጫማ
እስከሚበቃቸው ከወቀሩኝ በሁዋላ ለዘቦች አስረከቡኝ ።
ሰውን እንደ እባብ መቀጥቀጥ በህግ የተፈቀደ እስኪ
መስል ድረስ የአራተኛ ክፍለጦር ወታደሮችም መፈጠሬን
እስክጠላ ገረፋኝ ።እረ ''ገረፋኝ'' የሚለው ቃል
አይገልጸውም ።ሕሊና ያለው ሰው በመሰሉ ላይ
ይፈጽመዋል ተብሎ የማይታሰበውን የጭካኔ እርምጃ
ወሰዱብኝ ።"
(ክቡር ዶ/ር አርስቲት ጥላሁን ገሠሠ እንደተናገረው )
(ከላይ በፎቶው ላይ የምንመለከተው ጥላሁን በ ወታደሮች
በቁጥጥር ስር ሲውል ነው )

@Simetin_Begitim
አበባዉ ለምለሙ ዛፉ ሳሩ ቅጠሉ
በፍጥረት አለም ላይ አምሮ የሚታየዉ ሁሉ
ዉብ የሆነዉ ነገር የሚያምረዉ በሙሉ
ሀሩ ቀጭን ኩታዉ ጌጥና እንቁና ሉሉ
♪♪
የወርቅ የአልማዝ መስቀሉና እርባን ስራዉ በሙሉ
ጨዋነት ደግነቱና ቁምነገሩ በሙሉ
ምንም ነገር ሳይቀረዉ መልኩ ያንቺ እኮ ነዉ አምሳሉ
♪♪ ♪♪ ♪♪
ተራራዉ ፏፏቴዉ መስኩ ደኑና ጭቃዉ
የቀስተ ደመና ቀለም ብሩህ ጨረቃዉ
ሳቅና ፈገግታዉ ፍቅርና ስሜቱ
የሰዉ ሰዉነቱ ክብሩና ጌትነቱ
♪♪ ♪♪ ♪♪
ካባ ጃኖዉ ቀሚሱና የአንገት ጌጡ ሃብሉ
ለህይወት የሚጠቀም ብዙ መልካም ነገር ሁሉ
ምንም ነገር ሳይቀረዉ መልኩ ያንቺ እኮ ነዉ አምሳሉ
♪♪
ካንቺ ጋር አብሮ መዋል ህይወት ለማደስ
በጣም ደስ ያሰኛል ልብን ያረካል መንፈስ
ፈገግታሽ ሃኪም ነዉ ህመምን ያድናል
ፍቅርሽ ደጋፊ ነዉ ቢይዝ ልብ ይጠግናል
♪♪
የህይወት ጥልቅ ሚስጥርና የደስታ ትርጉም ሁሉ
ዉበትን ስሜትን ፍቅርን ብቻ እኮ ነዉ ይላሉ
ታዲያ ፍቅርስ ቢሆን መልኩ ያንቺ እኮ ነዉ አምሳሉ
♪♪
የፍቅር ሙሉ ስሜቱ ሁሉ ነሽ አምሳሉ
የፍቅር ሙሉ ስሜቱ ሁሉ ነሽ አምሳሉ
♪♪

ጋሽ ጥሌ በውብ ድምፁ ካቀነቀናቸው ዜማዎች ውስጥ

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
# ኢትዮጲያችን #ጥላሁን_ገሰሰ
በስንታየሁ አለማየሁ

መደመም ውሰጤን ሲሞላው
ግርምት አፌን ሲያሲዘኝ
እንዲህ ባዲስ አመት በር
በመስከረም የአበባ ወር
አንድምታዬን መግለፅ ሲያመረኝ
ጥላሁን ነው ትዝ የሚለኝ፡፡
ጋሼ ዛሬ መስከረም 17 ዕለት በሕይወት ቢኖር ኖሮ 79ኛ ዓመቱን ይይዝ ነበር፡፡ ክቡር ዶከተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ዛሬ ልደቱ ነው፡፡ እንደ ጥላሁን አይነቱን ምርጥ ኢትዮጲያዊ ስብዕና ዓመቱን ሙሉ ዘክሮ ፣ ዓመቱን ሙሉ ሲያከብሩት ቢዘልቁ ከፍ ያለ ደስታና ክብር የሚያስገኝ ነው የሚመስለኝ፡፡
ንጉሱን ዛሬ በልደቱ ቀን እናስታውሰው ብለን እንጂ መቼስ ስለሱ ያልተባለ ፣ ያልተፃፈ እና ያልተነገረ ነገር ሳይኖር ቀርቶ አይደለም፡፡ ጥላሁን ከኢትዮጲያ ሰንደቅነቱ ባለፈ በመስከረም ወር ተፈጥሮ በድምፁም ወርሃ መስከረምን ያነገሰ ፣ የአዲስ ዓመት መባቻን አድምቆ በአድባርነት የቆመ እውነተኛ አርቲስት ነው፡፡
ከልጅነት እስከ እውቀት አዲስ ዓመት ሲመጣ ፣ በዓሉን በዓል ከሚያስመስሉልን ጣዕመ ዜማዎች ውስጥ እንደ ዘሪቱ ጌታሁን እንቁጣጣሽ ፣ እንደ አስቴር አወቀ እዮሃ አበባዬ ሁሉ የጥላሁን ገሰሰም ወርቃማ ስራዎች ይገኙበታል፡፡ ጥሌ እንቁጣጣሽ ሲል ፣ የ 13 ወር ፀጋ ሲል እንዲሁም ክረምት አልቆ በጋ ሲል እንደተለመደው ትንፋሹ ከስጋ አልፎ ከነፍስ የሚሰካበት ዘዬ አለው፡፡
በያመቱ ለኛ እንቁጣጣሽ
ደስ ይበለን እንኳን ደህና መጣሽ
እያለ አደይ አበባዋን ልክ እንደ ሰው በመልካም ምኞት ይቀበላታል፡፡ ሰለኛ ስትል መውጣቷንም ከገጣሚው ተቀብሎ በውብ ዜማው ከሽኗታል፡፡ አበባን የአይን ቀለብ ፣ ልምላሜን የመንፈስ እርካታ አድርጎ የማድረግ ስነ-ልቦናዊም ፣ ሰዋዊም ሳይንስ አለ፡፡ ይህንኑ እውነታ ነው ጥላሁን ያውመ ከአዲስ አመት መንፈስ ጋር አገናኝቶ በውብ ድምፁ ያቀነቀነው፡፡ በአበቦች መዓዛ መርካታችንንም እንዲህ አስረግጦ ገልጧል….
ክረምት አልቆ በጋ
መስከረም ሲጠባ
አውዳመት አልፎ
አዲሱ ሲገባ
በአበቦች መዓዛ ረከቷል ልባችሁ
ረክቷል ልባችሁ
ሕዝቦች ሁሉ በጣም እንኳን ደስ አላችሁ
እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
የአዲስ ዓመት መባቻን በዚህ አይነት የደስታ መንፈስ ያውድና ….የማይሰለቸው ጥላሁን የ13 ወር ፀጋ ሲል ከጰጉሜ እስከ ጰጉሜ ዓመቱን ሙሉ ስላሉን ክብረ በዓላት ፣ ጭፈራና ፈንጠዚያዎች ፣ ሰርጉና ፋሲካው ፣ ውብ ኢትዮጲያዊ ቀለሞችን በዜማው ሲያሳምር እናስተውላለን፡፡
በፀሀይ ብርሃን ደምቃ ክረምትና በጋ
የትውልድ ሃገር ያላት የ አስራ ሶስት ወር ፀጋ
ወግና ልማዳችን የወረስነው ካበው
አውዳመቱ ትዝታው አይጠፋም ያው ነው
.
እንኳን ደረስክ ሲባባል
ወዳጅ ከጎረቤቱ
ትዝታው መች ይጠፋል
አቤት ማስደሰቱ፡፡
.
አቤት ባዲሱ አመት
ዘመኑ ሲለወጥ
ያበቦቹ ሽታ መአዛው ሲመስጥ
ኮበሌው ሲጨፍር
ሲል መስከረም ጠባይ
ኮረዳዋም ባታሞ
ስዞር በራሷ ቀዬ
አሲዮ መስቀል ሲመጣ
አሲዮ ደምቆ ደመራ
ሁሉም በደጁ ችቦ ሲያበራ
በልጅ ባዋቂው ደምቆ ጭፈራ
በልልታ ሎጋ ደምቆ ሲደራ
ከብረው ይቆዩን በሚል ጨዋታ
የልጅ ምርቃት ያባት ስጦታ
እያለ ይቀጥልና ስለ ገና ጨዋታው ፣ ስለ ጥምቀቱ ፣ ስለ ፋሲካው ያነሳሳና ወዲያ ተሸግሮ ስለ ሐምሌና ነሐሴ ዳመናና ሰብል ብሎም ስለ ቀጣዩ ቡሄ ዳግመኛም ስለ መስከረም እንዳሻው በሰጠው ድምፅ እንዳሻው ዓመቱን ያስሳል…..ኑሯችንን ይቃኛል፡፡

ዛሬ ጥላሁንን ማውጋት ፣ ጥላሁንን መፃፍ ፣ ጥላሁንን መተረክ የፈለኩት ልደቱ ስለሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ጥላሁንን ለማንሳት ደግሞ ምን ምክንያት ያስፈልጋል…..እሱን ለማንሳት ምክንያት ፈለግን ማለት ስለ ኢትዮጲያ ለማውራት ሰበብ ፈለግን እንደማለት ነው……በኔ እምነት ሀገርን ለመተረክና ስለሃገር ለመወያየት ሰበብ አያስፈልገንም…ጥላሁንም እንዲያ ነው ለኔ፡፡
እንደሱ ያሉትን ምልክትና አድባር የሆኑ ሰዎች አብዝተን ብናስታውስና ብንዘክር ዘወትር እንደሚባለው መሰል ዜጎችን ለማፍራትም ሁነኛ መላ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በአንድ ወቅት በዚሁ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ስለ ጥላሁን በተፃፈው ፅሁፍ ውስጥ እንዲህ የምትል አረፍተ ነገር አንብቢያለሁ…..” ዘፈን ለጥላሁን የእንጀራ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ቁስል ማከሚያ መድኃኒት መሆኑንም በታሪኩ ውስጥ እናያለን፡፡ ምናልባትም ከብዙ አድናቂዎቹ በላይ በዘፈኖቹ ስሜቱ የሚነካው ጥላሁን ራሱ መሆኑን ስናነብ ፣ ጥላሁንን እንደ አዲስ የማወቅ ስሜት ይሰማናል” ትላለች፡፡
ጥላሁን ኢትዮጲያዊ ስሜቱን ለማከም ተፈጥሮ በሰጠችው ተሰጥኦ በትንፋሹ ሲታገስና ሲያባብል የኖረ ይመስለኛል፡፡ ህማሙንና ቁስሉን ፣ ማዘንና መደሰቱን ሁሉ በሀገሩ ስር ሆኖ በሃገሩ ቃል ሀገርን እየጠራ አንጎራጉሮላታል፡፡ የሚዘፍናትን ኢትዮጲያ ለማለት ብቻ የሚላት ሳይሆን ሆኖ የሚተውናት ናት፡፡ ጥላሁንን ማስታወስ የክፍለ ዘመናችንን ሙዚቃ መዳሰስ ነው…..ብንጠቅሰው ብንዘረዝረው አያልቅም ፣ ትንፋሹ ያረፈባቻውና የሱ ድምፅ በኪነት ያባበላቸው ሃሳቦች የትየለሌ ናቸው…ሁሉም እንደየመረዳቱ መጠን የተለየ አተያይ የሚመዝባቸው ስራዎቹም በርካታ ናቸው፡፡ ጥላሁንን ለመግለፅ ሻለቃ ክፍሌ የደረሱለትን ዜማውን እራሱ ጥላሁን ያሰናዳውን አንድ ምርጥ ስራ ልጥቀስ …..
“በአካል ሳይፈተን በአካል ሳይነካ
የማን ምንነቱ ግብሩ ሳይለካ
እርግጥ በተፈጥሮ በወል ስም ይጠራል
በቁም ነገር መድረክ ሰው ከሰው ይለያል”
ይህ ስራው መልሶ እራሱን ጥላሁንን የሚገልፅልኝ ድንቅ ስራው ነው…….ጥሌ ጥሩ ሃሳብ ሲያገኝ ዜማውን በሚፈልገው መንገድ እራሱ የመስራት ልምድም እንዳለው ባለሙያዎች ሲናገሩ ሰምቻለሁ….በቁም ነገር መድረክ ሰው ከሰው እንደሚለይ ጥላሁን እራሱን ማየት በቂ ነው፡፡ ሀገራችን ውስጥ እንደነ ኤፍሬም ታምሩ ፣ ቴዲ ታደሰ ፣ ሂሩት ፣ ሙሉቀን መለሰ ፣ ነዋይ ደበበ ፣ አለማየሁ እሸቴ ፣ ሚኒሊክ ወስናቸው ፣ አስቴር አወቀ ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ እጅጋየሁ ሺባባው ፣ ቴድሮስ ካሳሁን ፣ እዮብ መኮነን ፣ ዘሪቱ ከበደና የመሳሉት ብዙ የሙዚቃ ሰዎች አሉን ይሁንና ከሁሉ በላይ ከፍ ባለ ስሜትና ጥልቀት….በመሰጠት ሙዚቃን መስሎ ሳይሆን ሆኖ በመኖር ፣ አያሌ ቁምነገሮችና ሀገራዊ አተካራዎችን አሳምሮ በማንጎራጎር ፣ ሲሻው እንደ አርበኛ በል ሲለው እንደ ተዋናይ ባስቀመጡት መድረክ ልክክ ብሎ አምሮ በከፍታ በመስራት ጥላሁንን በቁምነገር መድረክ ሰው ከሰው ይለያል ብንለው….ጎልቶ መለየቱን ብንነግረውና ዛሬም በምናብ ብናወጋው ስህተት እንደማንሰራ አውቃለሁ፡፡
ጥላሁን በተጠየቀበት መድረክ ሁሉ እንጉርጓሮ ህይወቱ መሆኑን ያለ እንጉርጓሮ መኖርም ማሰብም እንደማይሻ ሲናገር ብዙ ጊዜ አድምጠናል፡፡ የሱ እንጉርጓሮዎች ሁሉ ጌጦቻችን ፣ ትንፋሾቹ ሁሉ እስትንፋሳችን ሆነው ስሜታችንን በመኮርኮራቸው ምህኛት ይህ ሰው ትክክለኛው የሙዚቃ ወዳጅ ብቻ ሳይሆን ጥላሁን ማለት ሌላው የሙዚቃ ስሟ ነው ብለን ቁጭ ብድግ ብለንለታል….ለዘመናት በስሜት ትውልድ ተቁነጥንጦለታል፡፡
ጥላሁን ኢትዮጲያ በምትፈልገው ቦታ ሁሉ አቤት ብሎ ያልተሰለፈበት ቦታ ቢገኝ ከህይወት ካለፈ በኋላ ነው፡፡ እንጂ ኢትዮጲያ ስትራብ….
ዋይ ዋይ ዋይ ሲሉ
የርሃብን ጉንፋን ሲስሉ
እያዘንኩኝ ባይኔ አይቼ
ምንላድርግ አለፍኳቸው ትቼ
ሲል በእንባ ታጅቦ ወቅቱን በሚገባ በሚችለው ተሰጥኦው ከትቧል…ስሜቷን ስሜቱ አድርጎ ለአለም በድምጡ አውግቷል፡፡ በጦር ሜዳ ውሎ እነ ዘማች ነኝን ፣ እነ አጥንቴም ይከስከስ ፣ እነ ወደፊት በሉለት
ስንታየሁ:
ይለይለትን ፣ ለውዲቷ ሀገሬን የመሳሰሉትን በመጫወት ከወታደሩ ጎን መሆኑን ፣ ሀገር የሁላችን አድባር የሁላችን አለኝታና መከታ
መሆኗን ሲያንጎራጉር ኖሯል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥላሁን በሴት መስሎ በፍቅር አምሳል የተጫወታቸውንም ስራዎቹን ብናይ ትንፋሹ ሊገልፅና ሊወክል የፈለገው ሀገርን እንጂ አንዲትን ኢትዮጲያዊ ሴት ላለመሆኑ ግልፅ ነው…..ለምሳሌ የጠላሽ ይጠላ ሲል ፣ እኔ ልሁን እንጂ የማልጠቅም ርካሽ ሲል ፣ እዩአት ስትናፍቀኝ ሲል በዚያ ገፀ ባህሪው ኢትዮጲያ ናት….ቁስሉና ርሃቡ ሀገር ናት፡፡ ከመጀመሪያ ስራው ጥላ ከለላዬ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ስራው ቆሜ ልመርቅሽ ድረስ ሀገር በትንፋሹ ስትነግስ ፣ በድምፁ ስትከብር ኖራለች፡፡
በቀጣይነት ጥላሁንን እንደ አርበኛ ፣ እንደ ሙዚቀኛ ፣ እንደ ተዋናይ ምን ሰርቶ እንዳለፈ ፣ ምናችን እንደነበረ እንቃኘዋለን፡፡ ብሎም ብዙ ሊተነተኑ የሚችሉ ሙዚቃዎቹን እያስተነተንን በምናብ ከርሱ ጋር እናወጋለን …በመልክት ለቀጣይ ተተኪ የቤት ስራ እናኖራለን….በግርምት በስራዎቹ እንደሰታለን ብዬ አስባለሁ፡፡
‹‹ትንፋሼ ተቀርጾ ይቀመጥ ማልቀሻ
ይህ ነው የሞትሁ’ ለት የኔ ማስታወሻ››
ብሎ ነበር ንጉሳችን፡፡ በእርግጥ እሱ እንዳለው ትንፋሹ ነው ማስታወሻችን ብለን ከሃሳቡ መስማማት እንችላለን…በትንፋሹ ውስጥ የገለፃት ኢትዮጲያ ነችና…..በውስጣችን ለዝንታለም ትንፋሹ ትንፋሻችን ኆኖ ዘልቋል ይዘልቃልም፡፡


@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
#ጥላሁን_ገሰሰ እና #ፍሬው ሀይሉ @Simetin_Begitim
የፍሬው ሀይሉና የ ጥላሁን ገሠሠ አስገራሚ ትውስታ
# ኢዮብ ዘለቀ
''ከፍሬው ሀይሉ ጋር ስንግባባ ጊዜ አልፈጀብንም ፤ ፍሬው
ጨዋታ ወዳድና ለጋስ ሰው ነበር ፤ ሥራውን ያከብራል
፣ሰው ይወዳል ፤ሰውም ይወደዋል ግን እንደኔና እሱ
በጔደኝነት ፍቅር ያበደ አልነበረም ።ከእብደታችን ሁሉ ግን
አንድ ቀን የሰራነውን አልረሳውም.።ከሀገር ፍቅር ጀርባ
ቁልቁለቱ ላይ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ቤት ነበር ። በዚያ
በኩል ስናልፍ ነጋድራስ ግቢ ውስጥ በጣም የሚያስጎመጅ
የኮክ ዛፍ አየንና ቀስ ብለን ገባን ።ወዲያው ኮኩ ዛፍ ላይ
ወጥተን እየተሻማን ፍሬውን ስንለቅም የኮኩ ዛፍ ቅርንጫፍ
ተገነጠለና ከአንድ ደሳሳ ቤት ጣራ ላይ ተያይዘን ወደቅን
።ለካስ የቤቱ ቆርቆሮ በጢስ የተበሳሳና ሆድ የባሰው ጭስ
ቤት ኖሮ ተያይዘን የወደቅነው ምጣዱ ላይ ነው።ድንገት
ዱብ ያልንባት ሰራተኛም በጣም ከመደንገጧ የተነሳ የሆነ
መአት ከሰማይ የወረደባት እንጂ የኮክ ፍሬ ለመልቀም
ወጥተን ለአደጋ የተጋለጥን ልጆች ስላልመሰልናት እንደ
ብራቅ በሚሰቀጥጥ ድምጽ አካባቢውን በጩህት
አደባለቀችው ። በመውደቃችን ሳይሆን በጩህቷ
የደነገጥነው እኔና ፍሬው ኃይሉም ሮጠን ከማምለጥ
ይልቅ በድንጋጤ እንደ ጅብራ ተገትረን ቀረን ።ወዲያው
ነጋድራስ ተሰማም ቤተሰባቸውም ግልብጥ ብለው ወጡና
ለምን እንደመጣን ከተጠየቅን በሁዋላ በቁንጥጫና
በኩርኩም ዋጋችንን አገኘን ።''
(ጥላሁን ገሠሠ እንደተናገረው ...)

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
" #መኖር ማለት አለመሞት ከሆነ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እየኖረ ነው። ግን መኖር ማለት #እራስን መሆን፣ #ለዓላማ መቆም፣ #ህሊናን አለመዘንጋት፣ #ፍርድን አለማጓደል፣ ለራስ ብቻ ሳይሆን #ለሌላው እራስን መስዋዕት ማድረግ ብሎም #አርአያ የሚሆን ነገር ጥሎ ማለፍ ከሆነ ስንቶቻችን ነን በህይወት ያለነው?"
#ኗሪዎች እንሁን ሠናይ ቀን ሠናይ ውሎ
© #ዶክተር_ምህረት_ደበበ

@Simetin_Begitim
የኔ ውብ ከተማ
(በአሉ ግርማ)
ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር
ካለ ሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር?
የኔ ውብ ከተማ
ህንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር
የኔ ውብ ከተማ
መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር
የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር
የሰው ልጅ ልብ ነው
የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር።

@Simetin_Begitim
መቃብሬ ላይ 'ሚጣፍ
ኑረዲን ኢሳ
.
.
ጥብቅ ማሳሰቢያ ሸክላን ለምትሰሩ
እዚህ መቃብር ላይ አፈር አትዝገኑ
ሲነድ ሲቃጠል ሲጨስ በመኖሩ
ሲቃጠል ለሚኖር
ለጀበና መስሪያ አይሆንም አፈሩ::

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
እኛ አድነቀናል እናንተስ?

የባጃጅ ቦቴ: የጉልበት ብዝበዛ ወይስ ምርጥ የስራ ፈጠራ?

Via Keybaher Tadesse/BCAA
@WalyasHood
@Simetin_Begitim
Forwarded from መባቻ © (Mickey) via @like
አፍ መፍቻ
----//----

መሰረቱ ሆኖ ፥ . .ግንዱን ካዘለ ሥር
በገንጣዮች ስለት ፥ ገዝፎ ሳይመተር
እንዳሜባ ቅንጣት...
ሁሉም በየጉልቱ ፥ .. . .ሳይራባ በዘር

የምላሱ ፍሬ
እንዳበደ ውሻ ፥ ሳያደርገው አውሬ
ካካሉ መቋሚያ
.…ከመሰሉ ጉያ
ፊደል ካራ ሆኖ ፥ ..ገንጥሎ ሳይለየው
ሳይከፈል ያ..ኔ ፥ የሰው ልጅ በቋንቋው
በለቅሶ ነበረ ፥. . . . . .አፉን የሚፈታው

«ሚኪ እንዳለ»

@MEBACHA
@MEBACHA
@MEBACHA
እንኳን ደስ አለን! ወርቅ እና ብር ለእናታችን ኢትዮጵያ !

1ኛ ሙክታር እድሪስ🇪🇹
2ኛ ሰለሞን ባረጋ🇪🇹

@Simetin_Begitim
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian pinned «" #መኖር ማለት አለመሞት ከሆነ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እየኖረ ነው። ግን መኖር ማለት #እራስን መሆን፣ #ለዓላማ መቆም፣ #ህሊናን አለመዘንጋት፣ #ፍርድን አለማጓደል፣ ለራስ ብቻ ሳይሆን #ለሌላው እራስን መስዋዕት ማድረግ ብሎም #አርአያ የሚሆን ነገር ጥሎ ማለፍ ከሆነ ስንቶቻችን ነን በህይወት ያለነው?" #ኗሪዎች እንሁን ሠናይ ቀን ሠናይ ውሎ © #ዶክተር_ምህረት_ደበበ @Simetin_Begitim»
#ውድ የኢትዮጵያዊ ወጎች ቤተሠቦች የቤተሠቦቻችንን ቁጥር ለመጨመር በምናደርጋቸው የማስታወቂያ ልውጦሽ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ድግግሞሽ እና ይዘት ፈፅሞ የቻናላችን አለመሆኑንን እንድታውቁልን እንላለን ፡፡
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian pinned «#ውድ የኢትዮጵያዊ ወጎች ቤተሠቦች የቤተሠቦቻችንን ቁጥር ለመጨመር በምናደርጋቸው የማስታወቂያ ልውጦሽ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ድግግሞሽ እና ይዘት ፈፅሞ የቻናላችን አለመሆኑንን እንድታውቁልን እንላለን ፡፡»
ያልወደደ አበደ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
በሰው የደረሰ...
በኔ ላይ እንዳይደርስ ፣ ስፈራና ስቸር
ወድጄሽ እንዳላብድ ፣ ስጠነቀቅ ነበር፡፡
ታድያ ምን ያደርጋል
በከንቱ ፍርሃት ፣ ባክኖ መጠንቀቄ
ዋናው እብደት ነበር ፣ ከመውደድ መራቄ፡፡

@Simetin_Begitim
ሽመላው ወለልቱ
__
ከብት አረቡ ወዳጆቼ
ፈረስ ያረቡ ነበር አያቶቼ
ልውረድ ከንግድያ ወደ ቆላው
ሞቃት መጋላ ግስ ላርባ
ያለመደብ የሚያብብ አበባ
(ወለሎ - ሰሎሞን ዴሬሳ)
@Simetin_Begitim
ለፈገግታ😂😂😂

የህንድ ፊልም ተፅእኖ ያደረበት ሰውዬ ልጁን ሲቆጣው...........

እንግዲህ አትረብሽ ክሪሽና ምስክሬ ነው እስከ ሰባት ትውልድ ማትረሳውን ኩርኩም ነው ምመታህ😡

@Simetin_Begitim
@WalyasHood