ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.43K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
💎💎💎ፍቅር💎💎💎:

"እምነት ፣ተስፋ ፣ፍቅር የሰው ልጅ ህልውና መሰረት ናቸው . . .
በህይወትህ ከሶስቱ አንዱን ያጣህ ሰአት ለመኖር ከባዱ ግዜ ይሆናል . . . ፍቅር ከሁሉም የፀና ነው፡፡"

❤️❤️❤️ፍቅር ይስጠን❤️❤️❤️
#መልካም_ቀን
@Simetin_Begitim
#አሜን በሉ

🌼🌼ፈጣሪ በአዲሱ አመት🌼🌼
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

ታሞ ከመማቀቅ፣
በብድር ከመሳቀቅ፣
ተፈትኖ ከመዉደቅ፣
የምንወዳትን ቺክ ከመነጠቅ፣
ይሰዉረን !
🌼
ከሰዉነት አንሶ እንስሳ ከማከል፣
የራስ እያረረ የሰዉ ከማማሰል፣
ለዘር ለጎጠኝነት ዱላ ከማቀበል፣
በቸልተኝነት ጉዞ ሚስኪኑን ከመበደል፣
ይሰዉረን !!
🌼
ፈገግ ብለዉ ከሚገሉን፣
ጀነን ብለዉ ከሚያዋርዱን፣
ደንዘዉ ከሚያደነቁሩን፣
እሱ ይሰዉረን! 🙏
🌼
ሀብታም ሆኖ ሰገጤ፣
ድሃ ሆኖ አራዳ፣
አዕምሮ ይዞ ዘረኛ፣
ሀብት ይዞ ጎጠኛ፣
ከመሆን ይሰዉረን!! 🙏
🌼
ከባለሃብት ቋጣሪ፣
ከእነቅልፋም ታታሪ፣
ከበጥባጭ መሪ፣
ከወንድ ፈሪ፣
ከሴት አስነዋሪ፣
ይሰዉረን! 🙏
🌼
ከመሪ ሸረኛ፣
ከሴት ነገረኛ፣
ከወንድ ጉረኛ፣
ከማህፀን በረኛ፣
ይሰዉረን! 🙏

#መልካም_አዲስ_አመት
ሳምሶን
@Simetin_Begitim
#እውነቱን ተናግሮ አሳዳሪ ማጣት

እውነቱን ተናግሮ
የመሸበት ማደር
እያለ ሲሰብከኝ ፣ የመሸበት ሀገር
ስሰማና ሳምን ፣ ቆይቼ ሰንብቼ
በድንገት መሽቶብኝ ፣
አንቺ ጋር ለማደር ፣ ከቤትሽ መጥቼ
እወነቱን ብናገር ፣ ባልሽ ግን ጠመደኝ
እንኳን ሊያሳድረኝ
መዋያ አሳጣኝ ፣ ቀን እያሳደደኝ

ዳሩ ብሳደድም
እውነቱን ተናግሮ
በነጋበት መሸሽ ፣ እንዳለ አልዘነጋም
እውነቴም አንቺው ነሽ
ስትሔጅ መሽቷል ፣ ካልመጣሽ አይነጋም

በላይ በቀለ ወያ
#መልካም የትምህርት እና የስራ ቀን ውብ ሰኞ ተመኘንላችሁ፡፡

@Simetin_Begitim
Fikre Z Bhere Ethiopia©
ይህቺን ነገር የሚሻማን ልጅ ነበር። ብሬ! በየቤቱ እየዞረ ስልቅጥ
ነው!
ለነገሩ ያኔ በግ የቤት እንስሳ ነበር! ቢያንስ በሰፈራችን አብዛኛው
ሰው ስለሚያርድ።
የበጎች ድምጽ ከጠፋ ታርደዋል ማለት ነው....
ያንኳኳል.......
" ምነው በደህና ነው ልጅ ብርሃኑ? "
" ጋሼ! እንኳን አደረሳችሁ! " ይላል ወደግቢው እያጮለቀ።
በሰፈሩ ሁሉም ስለሚያውቀው ያዘጋጅለታል። ገና አብስለው
ሲሰጡት እንደ ድመት አይኑን ጨፍኖ ያነክተዋል....
" ፍቅርሻ! "
" አቤት "
" ተዘጋጀልኝ?"...( እንዳስቀመጠ )
" ያውልህ! "
የሰፈሩ አባቶች ልጆቻቸውን ( በተለይ ወንዶቹን ) ለማብላት
ይሞክራሉ
" ልጅ ብርሃኑኮ ጀግና ነው! "
" እንዴት? "
" የበግ ቆ** ይበላል ቢያንስ!..አንተ እሳት ዳር ቁጭ ብለህ ጉበት
ጥበስ ረኸጥ! "
"...ወንድ ልጅ የበግ ቆ** ሲበላነውንጂ!!!....." ይባላል።
ጥቅሙን ሲያስረዱ.....
" በተለይ አንተ ( እኔን ነው ) ይሄ ውሻና ሸረሪት ስታይ
የምትበረግገው ነገር ይለቀሃል ".....እርፍ!
አንድ ቀን እትዬ ሻሼ ቤት ሄደ ብሬ....
.....በጉኮ አልታረደም! ድምጹ ስለጠፋ ብርሻ ከች!...
" ሳይታረድ እንደ ቲማቲም ከላዩ ላይ ልትቀነጥስበት ነውንዴ? "
አሉ እትዬ ሻሼ
" ሲታረድ ልምጣ? "
" ሳር አብላውማ! ጎሽ..."
በጉ አመጸኛ ነገር ነበር። ብሬ ጠጋ ሲለው ሊወጋው
ተንደረደረ!.....ብሬ እንደዛ ተፈናጥራ አታውቅም!
እማማ ሻሼ.....
" ያን ኩሉ የበግ ቆ** ሰልቅጠህ እንደ ፌንጣ መዝለል?
ሆ!ሆ!ሆ...እኛው እንበላዋለን ከዛሬ ጀምሮ "
" ለሴት አይሆንምኮ እትዬ ሻሼ "
" ለምን ሲባል!? ምን እንዳይቀንስብኝ ነው? "
...እውነታቸውን ነው..
ብሬ ታዲያ ከፍ እንዳለ ቀበሌያችንን ወክሎ ቦክሰኛ ሆኖ ነበር።
የሁላችንም ውጤት አይደል?
የሚያሳዝነው ሁሌም ይሸነፋል!
እሱ በዝረራ በተፈነደሰ ቁጥር ቤቱ ሄዶ መጠየቁ ታከተን!
አንድ ቀን እትዬ ሻሼ ሊጠይቁት ሄዱ
" ተረፍክ ልጄ? "
" ደህና ነኝ እትዬ "
" አቤት.. አቤት.. አቤት! ጭካኔ! አንተ ለነገሩ ለምደኸው ነውንጂ
ሌላ ሰውማ ይሞታል! "
እያዘኑ ቆዩና...ጠጋ ብለው
" ያኔ እየዞርሽ ሃሞት ጠጥተሽ ቢሆን....."

#መልካም_ትንሳዔ
#Stay_Home
#Stay_Safe
በትላንት መበሳጨት ለነገ መጨነቅ ዛሬን ማበላሸት ነው!
#መልካም_ቀን
#ከሙሉ_ጤና_ጋር
ተመኘንላችሁ፡፡
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
ዕንባህን ባረገኝ

© ሰሊና

ከውስጥ ስሜትህ ከልብህ ፈልቄ
የአጉል ኩራትህን ሽፋኑን ፈልቅቄ
የዐይኖችህን ብሌን በዕንባ ሞልቼ
ቅል ባሳክላቸው በዕንባ አሳብጬ
ደም ባስመስላቸው ስሜትህን ገልጬ
ሲቃ ብሆንብህ ድምፅህን ዘግቼ
ጉንጮችህን ባርስ በመንታ ወርጄ
ከዛም...
ይህን ሁላ ሄጄ ሁሉን አቋርጬ
ብገኝ እመርጣለሁ ከንፈርህ ላይ ሞቼ

#መልካም_ቀን
ውብ ውሎ ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ!!
ቲቸር ቦጋለ፡ ሒሳብ ሊያወሩልን ሲገቡ
" መጡ ደግሞ! ስራ ሊያስፈቱን " እንል ነበር።
ማንም አይሰማቸውምኮ፡ ብቻቸውን ያወራሉ
.............One man show!.............
" ውይ! ልጆች ይሄን ፎርሙላ አሳሳትኳችሁ ይቅርታ! "
......ተሳስተው ቢቀሩስ ምናለበት?.....
" ምንም አይደል ".....Who cares!?
ስድባቸውስ
" ትኋን ሁሉ! "
......የዘንድሮ ፈላ የቻይና እቃ መስሎታል ይሄኔ.....
ያኔ ትኋን እንደልብ የሚገኝ ተባይ ነበር! አዬ ግርማ ሞገስ! አዬ
እርጋታው!
ከነከሳችሁ በኋላኮ አይሸሽም! እንደ ድፍን ምስር ተጎልቶ
ይጠብቃችኋል! እናንተም ለመያዝ መጣደፍ አያስፈልጋችሁም፡
ጠዋት ከነከሳችሁ ንዴታችሁ ካልበረደ ማታ መጥቶ አንስቶ
መወርወር ነው!
ጣ! ይላል ሲወድቅ ( ወለምታው መሰለኝ! )
ከትኋን የተረፈችውን ደማችንን ቀይ መስቀል እየቀዳት ነውኮ
አይናችን ብቻ የቀረው! ( እንደ ጉጉት! )
እሱም አይን ሆኖ ቲቸር ቦጋለን ነው የምናይበት!
የፈተና ውጤታችንን አይሰጡንም። እኛም አንጠይቅማ!
" ቀጥሎ የማን ክላስ ነው? "
" የፓርላማ! "......የክላሳቸው ስም!
" አይታመሙምንዴ አንዳንዴ? "
" ሲሚንቶ ነገር "
ፊዚክስ ቲቸር ይግደለኝ! እሱ ሁሌም ያመዋል
" ተማሪዎች ነገ የለሁም! አርሾ እሄዳለሁ " ይላል ሁሌ
ያማረበት እየመሰለው በተሰበሰብንበት
" አርሾ ሰገራ ስጥ ብለውኝ..." ብሎ ያወራናል
......ይድፋህ አቦ!.......
ሁልጊዜ አርሾ ሄጄ ሰገራ ሰጥቼ መጣሁ ይላልንዴ?
" ባለገ! ይሄ ሰው " ይላል ጌቱ
" ወይ ሽንት ቤት የለው ይሆናል "
የአስተማሪዎቻችን ትዝታ ብዙ ነው።
ኢለመንተሪ ላይ ቲቸር ጸጋዬ ትዝ ይሉኛል
" የፈሳውን ካላጋለጣችሁ በመደዳ ትገረፋላችሁ "
ይታያችሁ! በአንድ አቃጣሪ ቂጥ፡ ስንጠፈጠፍ
ቲቸር ጸጋዬ የሚታሙት የተማሪ ምሳቃ በማጫረስ ነበር
.......ምሳ እቃ ሰባሪ በሏቸው.....
ምሳ ሰአት ላይ አፍንጫቸውን አስቀድመው ከች ይሉና፡
" ማነው ጎበዝ! አጉርሱኝስኪ " ይላሉ
አጉርሱኝ ይላሉ ግን በኋላ እሳቸው ናቸው የሚያጎርሱን!

Fikre Z Bhere Ethiopia

#መልካም_ቀን_ሠናይ_ውሎ
ታጋቹ ማስታወሻ
( በእውቀቱ ስዩም)
ቀሳ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ቤቴ ውስጥ ያገኘሁት ምግብ ሩዝ ብቻ
ነው ፤ ሰኞ ሩዝ በቲማቲም- ማክሰኞ ሩዝ በጅንጅብል- ረቡእ ሩዝ
እንደወረደ፤ ወዘተ…ባጭሩ በሩዝና በሪዝ ተከብቤ ሰነበትሁ ማለት
ይቻላል፤ አንዳንዴ ምግብ የቀየርኩ እንዲመስለኝ የምበላበትን
ቦታ እቀያይራለሁ፤ ሳሎን ውስጥ ሁለት ማንኪያ እጎርስና
የተረፈውን በረንዳው ላይ ተቀምጨ እጨርሰዋለሁ፤
ሩዝ ጠዋት ማታ ከመብላቴ የተነሳ ወደ ማጅራቴ ሲሸሽ የነበረው
ፀጉሬ ተመልሶ ቅንድቤ ድረስ ግጥ—ም አለ ፤ የህንድ አክተር
ለመምሰል የቀረኝ በሱሪ ላይ ቀሚስ መደረብና ባየር ላይ የሚበር
ሞተር ሳይክል መንዳት ነው፡ ፡
የሆነ ግልገል ጉንዳን ጠረጴዛየ እምብርት ላይ ከተበተኑት የሩዝ
ቅንጣቶች መካከል አንዲቱን መርጦ ተሸክሞ ሲያዘግም
ተመለከትኩ ፤ኩንታል መሸከሙ ነው፤ አይ ጉንዳን! አሁን ጉንዳንን
የመሰለ ታታሪ ፍጡር በሚኖርበት አለም የሰው ልጅ የላባደሮችን
ቀን ያከብራል ? ልይዘው ሞከርኩ ፤የጣቶቼን ጥላ ሲያይ
ኩንታሉን እንደተሸከመ መሮጥ ጀመረ፤ አምልጠህ ሞተህል
ባክህ! !ባውራ ጣቴና በነገረኛ ጣቴ መካከል አጣብቄ ያዝኩት ፤
የሞተ መስሎ ፀጥ አለ፤ ለካ አስመሳይነት የሰው ልጆች ባህርይ
ብቻ አይደለም፤ ትወናውን አድንቄ በተሸከመው የሩዝ ቅንጣት ላይ
አንዲት የቲማቲም ፍሬ መርቄለት ለቀቅሁት፤
ባለፈው ለለውጥ ያክል የሱካር ድንች ለመቀቀል ሞከርኩ፤
የአሜሪካ የሱካር ድንች አንዱ ፍሬ የድሮ ካውያ ያህላል ፤ ችግሩ
በቀላሉ አይበስልም፤ እንዲያውም ካሜሪካ ሱካር ድንች፤
የኢትዮጵያ በሬ ሸኮና ቀድሞ ይበስላል፤ ቤት ጠርጌ ፤ምንጣፍ
ቀይሬ፤ ኮርኔስ ራሱ ቀይሬ ተመልሼ መጥቼ ሳየው፤ አልበሰለም፤
ምን ጉድ ነው! ከዛ ገላየን ተታጥቤ፤ ብብቴንና በስተራስጌ
የሚገኘውን ሁሉ ተላጭቼ ለባብሼ ሳበቃ ብረትድስቱን ከፈትኩት፤
ድንቼ መብሰሉን ለማረጋገጥ በሹካየ ወጋ አደረግሁት፤
እንዴየየየየ! የሹካው ጥርስ ተጣመመ፤ በጣም ተናደድሁና
አውጥቼ በመስኮት በኩል ወረወርኩት፤ ድው! የሆነ ሰውየ oh
Fuck! ብሎ ሲወድቅ አየሁት፤ ልጅ እያለሁ እናቴ “ ምግብ
መወርወር ጡር ነው “ ትለኝ ነበር፤ እረ ጦርም ነው እማየ ፤
ይሄው አንድ ምስኪን ፖስታ አመላላሽ ፈረንጅ ለትንሽ ገድየ ነበር!
በክቡር ዳኛ Frank Caprio ፊት ቀርቤ ፤የፈነከትኩት ሰውየ
እስኪሻለው ድረስ አልጋው አጠገብ ተቀምጨ በእንግሊዝኛ
እንዳስታምመው ፈረዱብኝ! ሁለት ወር ሙሉ ተጎድቼ
እንደከረምኩ ያወቅሁት በሆስፒታሉ ውስጥ የሚቀርበልኝን መኖ
ሳይ ነው-ቆስጣ፤ የወይን ዘለላ፤ በማር የተጠበሰ ዳቦ! ግሪክ
ሳላድ! እረ ወገን! ላስታማሚው እንዲህ አይነት ምግብ ከቀረበ
ለታማሚው ምን እንደሚቀርብ ኢማጂን እንግዲህ!
ባልተያያዘ ዜና ፤
እንደ ዶክተር አቢይ አህመድ ያለ ብልጥ ሰው ግን አለ? ፤
ሰልስትና (ከሶስት ቀን በፊት) ተቃዋሚዎችን ፓርላማ ውስጥ
ሰብስቦ ሲያወራ ማስኩን ካፍንጫው ሸርተት አድርጎ ከንፈሩ ላይ
አስቀምጦት አየሁ ፤ ብዙ ሰው ስትራቴጂ መሆኑ የገባው
አልመሰለኝም ፤የተፎካካሪ ፓርቲ ሊቀመንበሮች " አንተ ብቻ ነህ
እንዴ አፍንጫህን የማናፈስ ነፃነት ያለህ ?ብለው በእልህ
ማሳካቸውን ገለቡት ፤ አብቹየም ሁሉም አፍንጫውን ማጋለጡን
ከተመለከተ በሁዋላ ፈገግ ብሎ በልቡ፤ “ጎበዝ! እንግዲህ ይቺን
ቫይረስ እንቃመሳታ ፤ እኔ ጎልማሳ ስለሆንኩ አገግሜ እነሳለሁ ፤
ለእናንተም ደግሞ አካላዊ ርቀቱን ያስጠበቀ ቀብር አስከባሪ
ይዘጋጃል” ካለ በሁዋላ የምትከተለዋን ዘለሰኛ ማስታወሻው ላይ
አሰፈረ፤
ጎልማሶች ከመከራ ስንማር ፤
ለሼባዎች ነፍስ ይማር

#መልካም ዕሁድ
አይፍታህ!..(ልዑል ኃይሌ)

የኑሮዬ መስቀል የኑሮዬ ጥምጣም፤
የቄስ ማዕረግ ነጥቆት ተሳላሚ አያጣም፤
ፍታኝ ላለኝ ሁሉ
አልፈታህም ብለው ፈፅሞ አልቀጣም፤
.
ካላፊ ካ'ግዳሚው
እልፍ ሠው መካከል ቢሠለፍ ለፍትሃት፤
በነፍሰ ስጋዬ
ገለባ ልብ እንጂ መች አደለኝ ብልሐት፤
ከእንግዲህ በቅቶኛል
ፍታኝ ላለኝ ሁሉ አይፍታህ ነው መልሴ፤
እስር ቋጠሮውን
እንዴት እፈታለሁ ሳልፈ'ታ ራሴ፤
.
ማሕሌት ያልቆመ ልብ
አርምሞ አልባ ምኞት ሱባኤ-ቢስ ሐሳብ፤
ከደመና አያልፍም
በሠማይነቴ በሠውነት ቢሳብ፤
አ'ለምድም ከእንግዲህ
ከነ ሰባራ ሕልም ከኑሮ ጥምጣም ጋር፤
አሳልሜ አልፋለሁ
ላልተማረ ቀልቤ ክህደትና ችጋር፤
ተምሮ ይለፈው
ድኩም ማንነቴ የኔ ምዕመን ስጋ፤
አገኘሁኝ ብሎ
ፍፁም እምነት ይዞ ሠው እንዳይጠጋ፤
.
[ቅስና ለሌለው
'ሠው ነው!' የሚል ማዕረግ ምን ቢጠመጥሙ፤
ነፍስስ ምን ይረባል
ከወዳጅ ክህደት ጋር ልብ እያጣመሙ፤]
.
ለነፍሴ ውዳሴ
ለነፍሴ ቅዳሴ ቆሜ ማደርስበት፤
መቅደስ 'ሠውነቴ!'
እግዜር ያነፀልኝ የኔ ሕልም አለበት፤
.
ይሄ ፅኑ መቅደስ
የሠው ክብሪት ሐሳብ እንዳያቃጥለው፤
ክፋቱን ክህደቱን
ውስጤ ሳይደርስ ነው አርቄ 'ምጥለው፤
.
የሌላው መፈታት
ለሕልሜ ማሠሪያ እንዳያበጅለት፤
ነፍሴን እየመገብኩ
ራ'ቡን እንዲያስታግስ ስጋ ልጣልለት፤
.
የኑሮዬ መስቀል የኑሮዬ ጥምጣም፤
የቄስ ማዕረግ ነጥቆት 'ሚሳለም ባላጣም፤
ሕልሜን ለተጠማ
'ይፍታህ!' ብዬ አልፌ ራሴን አልቀጣም፤
23ኛው ሚያዚያ, 2012ኛው

#መልካም ቀን ውብ ውሎ ተመኘንላችሁ፡፡
79ኛው አርበኞች የድል በዓል እየተከበረ ይገኛል።

( አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ )

ቀደምት አባቶች ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት የመጣውን የጣሊያን ጦር ድል ያደረጉበት 79ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን እየተከበረ ነው:: በዓሉ በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሀውልት በመከበር ላይ የሚገኝ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ እና የአርበኞች ተወካዮች በሃውልቱ ስር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡

#መልካም_የአርበኞች_ቀን
ያነበብኩትን ላካፍላችሁ

*ቅናት*

ፍቅሬን ሜዳላይ ጥላ
ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ
እያልኩ እረግማታለሁ።

ዘወትር ሙሾ ታላዝን
የዕንባ ማዕበል ይጠባት።
ደስታዬን እንዳጨለመች
ደስታዋ ይጨልምባት።
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
ለዘራችብኝ ጥፋት።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የኮራችበትን ገላ
መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲን ይውረድባት
ጥጋት መሸሻ ትጣ።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የምድር የቀላይ ጥፋት
በላይዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲዖል ያድርገው
ስቃይዋን ያሳየኝ በዓይኔ።
እንደከዳችኝ ትከዳ
የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ ዓይኗን ያፈርጠው
ከውካዋ እግሯን ያልምሻት

እያልኩ እረግማታለሁ ።

ክንዷ በመጅ ይሰበር
ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓሬ ይሙላው
ፍራሹ የተኛችበት።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የሌላ ሆና ብትከዳኝ
አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለማተቤ ብጠየቅ
በዓለም ላይ ካለ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታ የለኝ
እሷን አምጡልኝ እላለሁ።
ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
እርግማኔና በረከቴ
ያለሷ ሕይወት የሌለኝ
ያሳበደችኝ ቅ ና ቴ ።

አበባው መላኩ

#መልካም ቀን ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ፡፡