ነገደ አምሃራ - Negede Amhara
6.83K subscribers
5.39K photos
1.06K videos
11 files
1.44K links
ነገደ አምሓራ - Negede Amhara.

ሃሳብና አስተያየት እንድሁም ጥቆማ ለመስጠት👇👇👇
@negedeforum
Download Telegram
ሰበር የድል  ዜና..‼️

የአማራ ፋኖ በወሎ የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር የአገዛዙን ጥምር ጦር እያደባዩት ይገኛሉ📌

የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ክንፍ የሆነው በመቅደላ ወረዳ የሚንቀሳቀሰው  #ሼህ_ሁሴን_ጂብሪል_ብርጌድ ትናንት እና ዛሬ  የአገዛዙን ጥምር ጦር እየለበለቡት መሆኑ ተገልጿል። በዚህም አውደ ውጊያ የአገዛዙ ጥምር ጦር ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱ ታውቋል። ስለሆነም በትናንትናው ዕለት ማለትም በቀን 21/12/2016 ዓ/ም ማክሰኞ ከጠዋቱ 12:00 ስዓት እስከ ምሽቱ 12:00 ስዓት ድርስ በ011 #ደቻ ቀበሌ ላይ በነበረው ትንቅንቅ  ለጠላት መረር ኮምጨጭ ያለ ሽንፈትን የተከናነበ ሲሆን ለወገን ኃይል ደግሞ አስደሳችና አመርቂ ድሎች ለማስመዝገብ ችሏል።  በጠላት ላይ የደረሰው ጉዳት 11ሙት ሲሆን #አጨብር_ማሪያም ቀብሮ መሄዱንና ከሰባት በላይ ቁስለኞችን ወደ መቅደላ ሆስፒታል በአንቡላንስ ማስገባቱን ከታማኝ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

    ከዚህም ጋር ተያይዞ በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 22/2016 ዓ/ም  የሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ በ031 ቀበሌ #ማታሜ ላይ ከባድ ፍልሚያ እንደነበረ ተገልጿል። በመሆኑም የጀግኖቹን ክንድ መቋቋም ያቃተው አራዊት ሰራዊቱ እግሬ አውጭኝ በማለት ማታሜዳን ለቆ ወደ ኮሬብ  መፈርጠጡ ታውቋል። 031 ቀበሌ ማታሜዳ በጀግኖች ቁጥጥር ስር መሆኗን ነው ምንጮች አክለው የገለፁት!!

#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪

22/12/2016 ዓ/ም