LearnEthiopia(ExitExam/EntranceExam/NationalExam-G8/JobExam/GATExam)
10.5K subscribers
941 photos
5 videos
8 files
1.19K links
Ethiopian Universities Entrance Exam/Exit Exam & GAT Exam/Jobs Exam/National Exam. Largest Harmonize E-Library, Jobs and Scholarship Portal.
Download Telegram
#HawassaUniversity

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 መውጫ ፈተና ምን ያህል ተማሪ እንዳለፈ ይፋ አደርጓል።

መረጃው ከሀዋሳ የተማሪዎች ህብረት የተገኘ ነው።
የ2016 ሀገር አቀፉ የሬሜዲያል ፈተና ይፋ ተደርጎ ተማሪዎች በኦንላይን ውጤታቸውን በመመልከት ላይ ይገኛሉ።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ነው እየተመለከቱ ያሉት።

ድረገጹ በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ተማሪዎች እየሞከሩት ስለሆነ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ።

ደጋግሞ በመሞከር ውጤት መመልከት ይቻላል።
Remedial ተማሪዎች አሁን የምታዩት ውጤት ከ 70% ነው። የግቢው 30% ተጨምሮ ከግማሽ በላይ ካመጣችሁ አልፋችኋል።

🔖ለ Natural Science ከ 70% (350) + 30% (150) =500 ስሆን 250 እና ከዛ በላይ ያመጣችሁ አልፋችኋል።

🔖ለ Social Science ከ 70% (280) + 30% (120) =400 ስሆን 200 እና ከዛ በላይ ያመጣችሁ አልፋችኋል።

📍ውጤት ለማየት ያስቸገራችሁ VPN ተጠቀሙ።
Jigjiga University

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የተቋሙ ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ገልጿል

ዩኒቨርሲቲው ያስፈተናቸው ተማሪዎች ውጤት በተቋሙ ሬጅስትራር አማካኝነት ይፋ መደረጉንና ተማሪዎችም ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ አሳውቋል።
#HawassaUniversity #89%

የ2016 ዓ.ም ሃገርአቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓም የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተመራቂ ተማሪዎች መካከል #ከ89% በላይ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል::

ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ 👏👇

"ውድ ተመራቂ ተማሪዎቻችን:-
ሁላችሁም የሃገራቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ የዓመታት ልፋታችሁን የመጀመሪያ ምዕራፍ በድል ስላጠናቀቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

ውድ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን እና አመራሮች እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች:-
የተማሪዎቻችን ስኬትም ሆነ ውድቀት ከራሳቸው ከተማሪዎቹ ትጋትና ቁርጠኝነት በተጨማሪ በእናንተ ያላሰለሰ ጥረትና ድጋፍ ላይ የሚወሰን በመሆኑ በልጆቻችን ጥሩ ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ!

በዚህ ዙር የማለፊያ ውጤት ያላገኛችሁ ተማሪዎች ደግሞ ለሚቀጥለው ዙር ፈተና በተሻለ ዝግጅት ራሳችሁን እንድታበቁ አደራ እላለሁ!"

ዶ/ር አያኖ በራሶ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት
                  
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የተቋሙ ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ያስፈተናቸው ተማሪዎች ውጤት በተቋሙ ሬጅስትራር አማካኝነት ከሰዓታት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።
#WolloUniversity

የመውጫ ፈተና የወሰደችሁ የወሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ከአሁኑ ስዓት ጀምሮ ውጤታችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑን ግቢው አሳውቋል።

እንደ ኢንስቲትዩት ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ካምፓስ ከተፈተኑት ተማሪዎች 75% ተማሪዎች ማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል።

👉Software Engineering 100% pass
👉Industrial Engineering 100% pass
👉Architecture 100% pass


ምንጭ፡ የኮምቦልቻ ካምፓስ የተማሪዎች ህብረት
#WerabeUniversity

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን  የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከወሰዱት የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2016 የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተመራቂ ተማሪዎች መካከል ከ84% በላይ  ተማሪዎች  የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል::
#MizanTepiUniversity

የ2016 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። በዚህም መሰረት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለፈተና ከተቀመጡት ተማሪዎች ዉስጥ 74% ማሳለፍ ተችሏል።

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት በተመራቂ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና የተገኘዉን ዉጤት አስመልክተዉ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዶ/ር ዋቆ ገዳ (ፕሬዚደንት)
#PrivateCollege #ExitExam

የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ከትምህርት ሚኒስቴር ለተቋማቱ በመላክ ላይ መሆኑን ሰምተናል።

የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ሲደረግ እናሳውቃቹሃለን።።

የመውጫ ፈተና ውጤት ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ቀድሞ የተላከ ሲሆን ተማሪዎችም ውጤታቸውን በተቋማቸው በኩል በማየት ላይ ይገኛሉል።
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ካሉት 51 የቅደመ-ምረቃ ፕሮገራሞች በ50 ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ያስፈተነ ሲሆን በመደበኛ መርሀ-ግብር 85.07% በማሳለፍ በ2015 የነበረውን ከፍተኛ ውጤት በሰፊ ልዩነት ወደ ላቀ ደረጃ አሻሽሏል።

በተከታታይ ፕሮግራም የተፈተኑት ተማሪዎችን ጨምሮ የ2016 አማካይ ውጤቱ 82% ሲሆን በ10 ፕሮግራሞች ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ(100%) ማሳለፍ ችሏል።
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች #83% የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል።
#BongaUniversity

4ኛው ትውልድ የሆነው ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 87.47% ተማሪዎቹን በመውጫ ፈተና አሳለፈ!

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ላይ 869 ወንድና    400 ሴት 1269 ተማሪዎችን አስፈትኖ 773 ወንድና 337 ሴት በድምሩ 1110 (87.47%) ተማሪዎችን ማሳለፍ ችሏል፡፡
#SalaleUniversity

በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች #86% የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል።
#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ዕጩ ተመራቂዎች መካከል 87.47 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ካስፈተናቸው 1,269 ተማሪዎች 1,110 (87.47 በመቶ) ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል፡፡