#KALTUBE
15.6K subscribers
1.21K photos
443 videos
203 files
1.29K links
ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ። ዩሐ1÷ 14
" Daily Spiritual Feeding"
በዚህ ያገኙናል👉 @Kaltube_bot

የዩቲዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ👇
https://youtube.com/c/KALTUBEOfficial

ዘጠነኛ ቃልኛ ዲጂታል መፅሔታችን👇
https://t.me/KALTUBE/9618
Download Telegram
💐የመንፈሳዊ ህይወት እድገት

➤መግቢያ
➤መጽሀፍ ቅዱስ
➤ጸሎት
➤ህብረት
➤የእድገት ተግዳሮቶች

መግቢያ

እድገት በህይወት ያሉ ነገሮች ህይወትን በውስጣቸው ስለመያዛቸው ማረጋገጫ መንገድ ነው። ይህ እድገት ከወቅት ወደ ወቅት እየጨመረ የሚሄድ ነው።

ነገር ግን አንድ ነገር ተወልዶ ከአመት አመት ለውጥ የማይታይበት ከሆነ አንድ ችግር አለበት ማለት ነው። መንፈሳዊ ህይወትም እንደዚሁ ነው በክርስቶስ ኢየሱስ ዳግም ከተወለድንበት ሰአት ጀምሮ እድገት በመንፈሳዊ ህይወት መጨመር በእኛ ህይወት ውስጥ ይጠበቃል።

ለዚህም ነው የበለስ ወቅት ሆኖ ጌታ በዛች በለስ ላይ ፍሬ ሲያጣ የረገማት ምክንያቱ ደግሞ እድገት ከዛች በለስ ይጠበቅ ስለነበር ነው። አንድ ነገር ከተወለደ ማደግ አለበት የተወለደው ነገር እየጨመረ እየፋፋ ፍሬ እያፈራ መቀጠል አለበት

የእድገት መገለጫ መሓል አንዱ እኛ እራሳችን በብስለት በመረዳት እያደጉ ከመምጣት ባሻገር ከራስ አልፎ ለሌላው መትረፍ ይኖርብናል።

የዕብራውያን ጸሀፊ በዕብራውያን መልዕክት ላይም አማኞች ወተት ከመጋት ወጥተው ስጋ ወደ መብላት ማደግ እንዳለባቸው የሚያሳስበው እድገት ከአንድ አማኝ የሚጠበቅ ተግባር ስለሆነ ነው።

እስቲ ሁላችንም ይህን ቀን ስለ መንፈሳዊ ህይወታችን እድገት እያሰብን ለማደግስ ምን እያደረግን እንደሆነ ራሳችንን እየጠየቅን የምናስልፈበት ማለዳ እና ቀን ይሁንልን።

ይህን ሳምንት ለመንፈሳዊ ህይወት ማደግ ዋናውን አስተዋጾ የሚጫወቱ መርሆች አንስተን እየተነጋገርን አብረን እንቆያለን

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐የመንፈሳዊ ህይወት እድገት

➤መርህ አንድ - መጽሀፍ ቅዱስ

በአሁኑ ዘመን የምንኖር አማኞች ከመቼው ጊዜ በበለጠ የተዘናጋን እንደ ሆንን አስባለሁ። ምክንያቱ ደግሞ የህይወት እንጀራ ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የምናስበልጣቸው፣ ቅድሚያ የምን ሰጣቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ።

እስቲ እነዚህን ጥያቄዎች ራሳችንን እንጠይቅ የእግዚአብሔርን ቃል ካነበብን ስንት ጊዜ ሆነን ቀን ሳምንት፣ ወር? እሽ ቃሉን ጊዜ ሰጥተን ካጠናንስ ስንት ጊዜ ሆነን? በተከታታይ እያነበብን ነው?

ቃሉን የማንበብ ልምዳችን ምን ይመስላል? ጤናማ እድገት ካስፈለገ ጤናማ የሆነ አመጋገብ ( ተከታታይነት ያለው የቃል ጥናት ጊዜ ያስፈልገናል)

እድገትና ምግብ የተያያዙ ነገሮች እንደሆኑ ምንም የማያሻማ እውነት ነው። ማደግ ካስፈለገ መመገብ አለበት ጌታ በምድረበዳ በተፈተነ ጊዜ "ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ጭምር እንጂ" እንዳለ እንዲሁ ማደግ ካለብን ቃሉን መመገብ ይኖርብናል

በዚህ ምድር ስንኖር እኛ እንግዶች ነን እንግዳ ደግሞ እንዴት መኖር እንዳለበት የሚያሳየው የሚመራው ያስፈልገዋል።


➤ ክፍል ሁለት

ይህ መሪ የጌታው የአምላኩ ድምጽ ነው (ቃሉ) ከዚህ ቃል የተፋታ ኑሮ የምንመራ ከሆነ አቅጣጫ ስተን እንጠፋለን። የፂዮንን መንገድ ሚያሳየን እርሱ ጌታችን እግዚአብሔር ነው። በቃሉ አማካይነት እየመራ መንገድ የሚያሳየን።

ስለዚህም ከቃሉ የተለየ ኑሮ እና ህይወት ካለን እድገት የለንም ዛሬም ልጆች ህጻናት ነን ማለትን ነው። ይህ ደግሞ በመጨረሻ ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን እንደተሰጣት ማስጠንቀቂያ ሞቃት ወይም በራድ ባለመሆናችን መተፋት እንዳይሆንብን።

ተከታታይነት ያለው የቃል ጊዜ ይኑረን፣ በቀን ውስጥ የምናሰላስለው ነገር በቲክቶክ የተመለከትነው ቀልድ.... ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል ይሁን። ይህን ማድረግ ስንለማመድ ያለጥርጥር እድገት ይኖራል።

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
ዛሬ ምሽት 3ሰዓት

#revealed_Gospel #kaltube #seifu
EP 8 - ውስጣዊ ኪዳን
RG - Seifu Zerihun
.          ልዩ የትምህርት ጊዜ
        | ውስጣዊ ኪዳን|
         Revealed Gospel
        With Seifu  Zerihun
Season -01 EPISODE 08
Amazing Preaching Program
sнαяє💐ѕнαяє💐ѕнαяє💐
          @KALTUBE
          @KALTUBE
          @KALTUBE
💐የመንፈሳዊ ህይወት እድገት

➤መርህ ሁለት ጸሎት

ፀልይ ከመባል ፊልም እይ፣ ጓደኞችህን አግኝ፣ ካፌ ቁጭ በል ብንባል እንመርጣለን ይህ ደግሞ ለጸሎት የሰጠነውን ቦታ ያሳያል።

ስንቶቻችን ነን በከንቱ ነገር ስንባክን የምንገኝ? በቀን ውስት 24ሰአታት አሉ ነገር ግን እስቲ ራሳችንን እንጠይቅ ምን ያህሉን ለጸሎት እናወለዋለን? ምን ያህሉንስ ለጓደኛ፣ ፊልም፣ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ እናውለዋለን ይህን በጥንቃቄ ብንመረምር እንዴት ባለ መዘናጋት ውስጥ እንደምኖር እናያለን።

ጸሎት አምላካችንን የምናናግርበት ብቸኛ መንገድ ነው። ጥያቄያችንን፣ የልብ ሀዘናችንን፣ ትካዜያችንን፣ ምስጋናችንን፣ ፍርሀቶቻችንን ብቻ ሁሉ ነገራችንን በአምላካችን ፊት የምናቀርብበት መንገድ ነው ጸሎት።

በድብቅ ጸልየን በአደባባይ ከእርሱ እጅ እንቀበላለን፤ በብዙ ነገር ተጨንቀን ግራ ተጋብተን ጥያቄ ተሞልተን፣ በፊቱ በጸጋው ዙፋን ፊት ስንሆን ግን ጥያቄዎቻችን ሁሉ ረስተን ፊታችን በርቶ እንመለሳለን።

ጸሎት መበርቻ፣ ጸጋ መቀበያ፣ ነፍሳችንን ማፍሰሻ ቦታ ነው። በቀን ውስጥ የጥሞና ጊዜ ያስፈልገናል ለጥቂት ደቂቃዎች ከአለም ጫጫታ ርቀን የእርሱን ድምጽ የምንሰማበት በጸሎት በፊቱ የምንሆንበት። ይህንንም በተከታታይነት የምንተገብረው ከሆነ ማደግ ይሆንልናል። ሰአቱ 5 ደቂቃ፣ 10 ደቂቃ .... ሊሆን ይችላል ዋናው ነገር በቀን ውስጥ ከአምላካችን ጋር መገናኘት መቻላችን ነው።

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐የመንፈሳዊ ህይወት እድገት

➤መርህ ሶስት ህብረት

“ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።”
መዝሙር 133፥1

መጽሀፍ ቅዱስ የወንድሞች ህብረት እጅግ ይደግፋል እንዲሁ ያበረታታል በህብረት ስንሆን አንዳችን አንዳችን እናንጻለን፣ እናበረታለን፣ እንማማራለን፣ ለአንዱ ያልተገለጠ ለሌላኛው ይገለጣል፣ አንዱ ያልተረዳውን ሌላው ይረዳል በህብረት በሆንንበት ቦታ ጌታም በዛ ስፍራ ከእኛ ጋር ይሆናል።

ማደግ ከፈለግክ በህብረት ከወንድሞች ጋር መሆን ነው።

➤ክፍል ሶስት

አንበሳ ወይም ነብር መንጋን ሊያጠቃ እንደማይችል ስለሚያው መንጋውን መበትን እንደ ስልት ይጠቀማል ጠላትም እንደዚሁ ነው መንጋውን ማጥቃት ስለማይችል በመጀመሪያ ሰው ከህብረት እንዲወጣ ነው የሚያደርገው ከዛም ብቻውን ሲያገኘው ለማጥቃት ይመቸዋል።

መዝሙር 133
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።
³ በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና።

በህብረት ውስጥ ከጌታ የታዘዘልን በረከት አለ ይህን በረከት ለማግኘት ለማደግም በህብረት አብሮ መሆንን አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው።

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐የመንፈሳዊ ህይወት እድገት

የመንፈሳዊ ህይወት እድገት ተግዳሮቶች  መቼም መልካም ነገር ለማድረግ ሲፈልግ ሲነሳም ያንን ማድረግ እንዳይችል የሚቃወም አይጠፋም በመንፈሳዊ ህይወታችን ማደጋችን ለሰይጣን መንግስትም ይሁን አገዛዝ ስለማያመቸው የእኛን መዘናጋት እና መደንዘዝ ይፈልገዋል።

ህጻንን ልጅ ለማታለል ብልጭልጭ እና አይንን የሚስብ ነገር በማሳየት ለመማረክ እንደምንሞክረው ሁሉ ጠላትም እኛን ለማስተኛት ለማታላል በህይወት ማደግ እንዳይሆን ብዙ መንገዶችን ይጠቀማል።

በማስፈራራት እንዳይመስላችሁ በማባበል ነው ከእውነት ከህይወት የሚያስወጣን እስቲ ቆም ብለን እናስብ ከእውነተኛ አምላክ ጋር እንዳንገናኝ ምን ፈተና እንደሆነብ እንይ። ለምሳሌ በእጃችን ላይ ያለው ስልክ አንድ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው ሰው በቀን ውስጥ ስልኩ ላይ ለ9 ሰአት ያህል ጊዜውን ይጠፋል በአብዛኛው ቲክቶክ ፌስቡክ እና ዮቲዮብ በመጠቀም እስቲ ካፌ፣ ባስ፣ ታክሲ፣ ትምህርት ቤት፣ አሁንማ ቤተክርስቲያን ፕሮግርራም ሁሉ ላይ ሳይቀር ሰው ስልኩን ከፋቶ ከላይ የጠቀስናቸውን ማህበራዊ ሚዲያዎች የጠቀማል፣ ሰዎች ተቀጣጥረው አብረው ከሚያወሩት ከሚጫወቱበት ጊዜ ይልቅ ሁሉም አንገቱን ቀርቅሮ ስልኩ ላይ የሚያጠፋው ጊዜ ብዙ ነው።
ታዲያ መፍትሄው ምን ይሆን? ራስን መግዛት ማደግ ከፈለግን ዋጋ መክፈል አለብን ምቾቶቻችንን መተው የራስ ደስታና ፍላጎትን ትቶ የእርሱን የጌታን መሻት እርሱም በፊቱ መሆን ነው መጨከንን መማር አለብን በቀን ውስጥ ለሰውነታችን የሚያስፈልገንን እንደምናደርግ ሁሉ ለመንፈሳዊ ህይወታችን አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ማድረግ መጸለይ ቃሉን ማንበብ በህብረት መሆን።

እግዚአብሔር አምላክ ይህን ማድረግ እንድንችል ጸጋን ይስጠን።

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
ሰይጣን የተሳካለት ክርስቲያኖችን በመግደል ሳይሆን ክርስቲያኖችን በማጋደል ነው ።

#Q0 #Kaltube  #ሰይፉ_ዘሪሁን

“ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።”
          ገላትያ 5፥15

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐በእርሱ ላይ አትጨምር፥ ከእርሱም ምንም አታጕድል


📖“እኔ የማዝዝህን ነገር ሁሉ ታደርገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእርሱ ላይ አትጨምር፥ ከእርሱም ምንም አታጕድል።”

           ዘዳግም 12፥32


የምናመልከው አምላክ ፍፁም እና እንከል አልባ ነው። እርሱ ይህን ባደረኩ ኖሮ ብሎ አይፀፀትም። ስህተትንም ሰርቶ የማያውቅ ሁሌም ትክክለኛ ነው። ይህ ሁሉ በሁሉ የሆነው አምላክ የሰው ልጅ ሊሄድበት የሚገባውን ትክክለኛውን ስርዓት ሰጠ። በዚህ ስርዓት እና መርህ ውስጥ ብቸኛው ተጠቃሚ የሰው ልጅ ቢሆንም እግዚአብሔር አምላክ ዝቅ በማለት ፍቅሩን ገለጠ።


እያንዳንዱ ሰው አውቆትም ይሁን ሳያውቀው የሚመራበት የህይወት መርህ ይኖረዋል። ራሱን በዚህ መርህ ስር ለማስተዳደር ይጥራል። መርሁን የቀየረ ለት ማንነቱን ወዲያ አሽቀንጥሮ በመጣል ሌላ ሰው ለመሆን ይኖረጣል። ይህ ማለት ራስን ከማጣት ያልተናነሰ ጉዳይ ነው። በተመሳሳይ መልኩ እግዚአብሔር የሰጠው መርህ ሲጣስ ክርስትናችን ውሃ ይበላዋል። ለዚህ ነው “እኔ የማዝዝህን ነገር ሁሉ ታደርገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእርሱ ላይ አትጨምር፥ ከእርሱም ምንም አታጕድል።” (ዘዳ 12፥32) በማለት የሚናገረው።


ሰይጣን ቃሉን እኛ እንደሚመቸን አድርገን እንድንኖር ይፈትነናል። ህይወታችንም እንደ ቃሉ ይመራ ዘንድ አይፈቅድም። ቃሉንም ሸራርፎ፣ ሰርዞ እና ደልዞ በማቅረብ በዓለም ላይ መርዙን ለመርጨት ተግቶ እየሰራ ይገኛል። ስለዚህ ወዳጆቼ፣ በቃሉ ላይ ያነጣጠረውን የጠላት ጥቃት በቃሉ ልንመክተውን እና ድል ልንነሳው ይገባል። “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።” (ኤፌ 6፥11)


ስለዚህ "ምንም በእርሱ ላይ አትጨምር፥ ከእርሱም ምንም አታጕድል" ማለት በቃሉ አንፃር ራስን እንደ ቃሉ መምራት ማለት እንደሆነ እንገነዘባለን። እንደ ቃሉ ስንኖር፣ በማህበረሰባችን የተገነቡ የጥላቻ፣ የዘረኝነት፣ የቅናት፣ የበቀል ግድግዳዎች በሙሉ ይፈርሳሉ። ቃሉ መርሃችን ሲሆን ህሊናችን ፍፁም በሆነው እረፍት ይጎበኛል። እርስ በእርሳችንም በሰላም፣ በፍቅር እና በመተሳሰብ እንኖራለን። “ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን፤” (1ኛ ዮሐ 2፥5)


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ አንተነትህን ይበልጥ አውቅ ዘንድ ቃልህን ስለሰጠኸኝ አከብርሃለሁ። ከሰጠኸኝ ከዚህ እንቁ ስጦታ አንዳች እንዳልጨምር፣ ከእርሱም ምንም እንዳልቀንስ፣ ይልቁን እንደ ቃልህ እኖር ዘንድ ፀጋህ ይርዳኝ። አሜን።


Bible Club~ BT
በተወዳጁ ቻናል | KALTUBE
  "Daily Spiritual Feeding"
👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
            @KALTUBE
            @KALTUBE
            @KALTUBE
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Read Bible

“አቤቱ፥ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፥ ሁልጊዜም እፈልገዋለሁ።”
       መዝሙር 119፥33

#read #bible #kaltube #saka
💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐በተለያዩ መንፈሳዊ ጉዳዮች ጥያቄ የሆነባችሁን እና በመፅሐፍ ቅዱስ ዙርያ  ያልተረዳችሁትን ሀሳብ ሰብስበን መልስና ማብራሪያ የምንሰጥበት ልዩ ዝግጅት።

💐ያላችሁን ማንኛውም መንፈሳዊ ጥያቄ በ👉 @kaltube_Bot እስከ ነገ ግልፅ አድርጋችሁ ላኩልን።

መልስና ማብራሪያዎች
ነገ ምሽት LIVE |  3 ጀምሮ ይቀርባል

💐እንዲሁም የአዲስ ኪዳን እውነት በሚል ርዕሰ የጀመረውን ትምህርት ላይ ያላችሁን ጥያቄ በ @kaltube_bot መላክ ትችላላችሁ ።

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
Live stream scheduled for
🖐ሰላም ተወዳጆች ዛሬ ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ #የLive ፕሮግራም አለን አሪፊ ቆይታ ከሰይፉ እና ከሜርሲ ጋር የሚኖርን ይሆናል በተጨማሪም የእናንተም የተለያዩ ጥያቄዎችን በLive እንቀበላለን ይጠብቁን ።

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
Live stream started
Live stream finished (34 minutes)
Live stream started
#KALTUBE
#KALTUBE
Live stream የመጀመሪያው 30ደቂቃ አልሰራ ላላችሁ

መልስና ማብራሪያዎች
Live ላይ አሁን መጠየቅ ይቻላል
Live stream finished (1 hour)