#KALTUBE
15.1K subscribers
1.23K photos
448 videos
203 files
1.31K links
ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ። ዩሐ1÷ 14
" Daily Spiritual Feeding"
በዚህ ያገኙናል👉 @Kaltube_bot

የዩቲዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ👇
https://youtube.com/c/KALTUBEOfficial

ዘጠነኛ ቃልኛ ዲጂታል መፅሔታችን👇
https://t.me/KALTUBE/9618
Download Telegram
💐ከባለ-ህልመኛው ዮሴፍ ምን እንማር ?

        DAILY DEVOTION -DAY 5

ክፍል 6- ጠላትን በመልካምነት ማሸነፍ

➤ እንደተደረገብን መክፈል ከእኛ አይጠበቅም። ይልቁንም መልካም በማድረግ ማሳፈር ነው እንጂ። ያለፈ ጠባሳን እያነሱ...... ሰዎችን መበቀል ጥቅም የለውም ምክንያቱም በቀል የእግዚአብሔር ነው። ይህንን ትተን ለጠላቶቻችን ከመልካምነታቸን እናቋድሳቸው ዘንድ ይገባል።

ክፍል 7  ለትውልድ መዳን እኛ በመከራ አናልፋለን

ዮሴፍ በመልካምነቱ ራሱን ለወንድሞቹ ገለጠ። አንዳንዴ ለሌሎች እረፍት ምክንያት እንሆን ዘንድ በብዙ መከራ እና መፈተን ውስጥ እናልፋለን። የእግዚአብሔር  መንገድ እንዴት እንደሆነ ባናውቅም በሚመራን ሁሉ እሱ ለእኛ አዋቂ ነውና በመጨረሻም በከፍታ ማማ ያወጣናል፣ ለጠላቶች መዳን መንስኤ ያደርገናል።

መልካም  ቀን ይሁንላችሁ 💜

#Daily #Devotion #Kaltube #W5

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
📖ከነገ ጠዋት 1:00 የመንፈሳዊ ህይወት እድገት በሚል ርዕስ ለተከታታይ  5 ቀናት የእግዚአብሔር ቃል ከወንድማችን ሳም(Youth Focus) ጋር የምናጠና ይሆናል  ዘወትር ጠዋት ከ1:00  ጀምሮ የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

💐ጥናቱ ላይ ሀሳብ ወይም አስታያየት እንዲሁም ጥያቄ በComment Section እና በ @Kaltube_bot የምንቀበላችሁ ይሆናል ።

መልካም  ሳምንት ይሁንላችሁ 💜

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐የመንፈሳዊ ህይወት እድገት

➤መግቢያ
➤መጽሀፍ ቅዱስ
➤ጸሎት
➤ህብረት
➤የእድገት ተግዳሮቶች

መግቢያ

እድገት በህይወት ያሉ ነገሮች ህይወትን በውስጣቸው ስለመያዛቸው ማረጋገጫ መንገድ ነው። ይህ እድገት ከወቅት ወደ ወቅት እየጨመረ የሚሄድ ነው።

ነገር ግን አንድ ነገር ተወልዶ ከአመት አመት ለውጥ የማይታይበት ከሆነ አንድ ችግር አለበት ማለት ነው። መንፈሳዊ ህይወትም እንደዚሁ ነው በክርስቶስ ኢየሱስ ዳግም ከተወለድንበት ሰአት ጀምሮ እድገት በመንፈሳዊ ህይወት መጨመር በእኛ ህይወት ውስጥ ይጠበቃል።

ለዚህም ነው የበለስ ወቅት ሆኖ ጌታ በዛች በለስ ላይ ፍሬ ሲያጣ የረገማት ምክንያቱ ደግሞ እድገት ከዛች በለስ ይጠበቅ ስለነበር ነው። አንድ ነገር ከተወለደ ማደግ አለበት የተወለደው ነገር እየጨመረ እየፋፋ ፍሬ እያፈራ መቀጠል አለበት

የእድገት መገለጫ መሓል አንዱ እኛ እራሳችን በብስለት በመረዳት እያደጉ ከመምጣት ባሻገር ከራስ አልፎ ለሌላው መትረፍ ይኖርብናል።

የዕብራውያን ጸሀፊ በዕብራውያን መልዕክት ላይም አማኞች ወተት ከመጋት ወጥተው ስጋ ወደ መብላት ማደግ እንዳለባቸው የሚያሳስበው እድገት ከአንድ አማኝ የሚጠበቅ ተግባር ስለሆነ ነው።

እስቲ ሁላችንም ይህን ቀን ስለ መንፈሳዊ ህይወታችን እድገት እያሰብን ለማደግስ ምን እያደረግን እንደሆነ ራሳችንን እየጠየቅን የምናስልፈበት ማለዳ እና ቀን ይሁንልን።

ይህን ሳምንት ለመንፈሳዊ ህይወት ማደግ ዋናውን አስተዋጾ የሚጫወቱ መርሆች አንስተን እየተነጋገርን አብረን እንቆያለን

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐የመንፈሳዊ ህይወት እድገት

➤መርህ አንድ - መጽሀፍ ቅዱስ

በአሁኑ ዘመን የምንኖር አማኞች ከመቼው ጊዜ በበለጠ የተዘናጋን እንደ ሆንን አስባለሁ። ምክንያቱ ደግሞ የህይወት እንጀራ ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የምናስበልጣቸው፣ ቅድሚያ የምን ሰጣቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ።

እስቲ እነዚህን ጥያቄዎች ራሳችንን እንጠይቅ የእግዚአብሔርን ቃል ካነበብን ስንት ጊዜ ሆነን ቀን ሳምንት፣ ወር? እሽ ቃሉን ጊዜ ሰጥተን ካጠናንስ ስንት ጊዜ ሆነን? በተከታታይ እያነበብን ነው?

ቃሉን የማንበብ ልምዳችን ምን ይመስላል? ጤናማ እድገት ካስፈለገ ጤናማ የሆነ አመጋገብ ( ተከታታይነት ያለው የቃል ጥናት ጊዜ ያስፈልገናል)

እድገትና ምግብ የተያያዙ ነገሮች እንደሆኑ ምንም የማያሻማ እውነት ነው። ማደግ ካስፈለገ መመገብ አለበት ጌታ በምድረበዳ በተፈተነ ጊዜ "ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ጭምር እንጂ" እንዳለ እንዲሁ ማደግ ካለብን ቃሉን መመገብ ይኖርብናል

በዚህ ምድር ስንኖር እኛ እንግዶች ነን እንግዳ ደግሞ እንዴት መኖር እንዳለበት የሚያሳየው የሚመራው ያስፈልገዋል።


➤ ክፍል ሁለት

ይህ መሪ የጌታው የአምላኩ ድምጽ ነው (ቃሉ) ከዚህ ቃል የተፋታ ኑሮ የምንመራ ከሆነ አቅጣጫ ስተን እንጠፋለን። የፂዮንን መንገድ ሚያሳየን እርሱ ጌታችን እግዚአብሔር ነው። በቃሉ አማካይነት እየመራ መንገድ የሚያሳየን።

ስለዚህም ከቃሉ የተለየ ኑሮ እና ህይወት ካለን እድገት የለንም ዛሬም ልጆች ህጻናት ነን ማለትን ነው። ይህ ደግሞ በመጨረሻ ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን እንደተሰጣት ማስጠንቀቂያ ሞቃት ወይም በራድ ባለመሆናችን መተፋት እንዳይሆንብን።

ተከታታይነት ያለው የቃል ጊዜ ይኑረን፣ በቀን ውስጥ የምናሰላስለው ነገር በቲክቶክ የተመለከትነው ቀልድ.... ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል ይሁን። ይህን ማድረግ ስንለማመድ ያለጥርጥር እድገት ይኖራል።

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐የመንፈሳዊ ህይወት እድገት

➤መርህ ሁለት ጸሎት

ፀልይ ከመባል ፊልም እይ፣ ጓደኞችህን አግኝ፣ ካፌ ቁጭ በል ብንባል እንመርጣለን ይህ ደግሞ ለጸሎት የሰጠነውን ቦታ ያሳያል።

ስንቶቻችን ነን በከንቱ ነገር ስንባክን የምንገኝ? በቀን ውስት 24ሰአታት አሉ ነገር ግን እስቲ ራሳችንን እንጠይቅ ምን ያህሉን ለጸሎት እናወለዋለን? ምን ያህሉንስ ለጓደኛ፣ ፊልም፣ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ እናውለዋለን ይህን በጥንቃቄ ብንመረምር እንዴት ባለ መዘናጋት ውስጥ እንደምኖር እናያለን።

ጸሎት አምላካችንን የምናናግርበት ብቸኛ መንገድ ነው። ጥያቄያችንን፣ የልብ ሀዘናችንን፣ ትካዜያችንን፣ ምስጋናችንን፣ ፍርሀቶቻችንን ብቻ ሁሉ ነገራችንን በአምላካችን ፊት የምናቀርብበት መንገድ ነው ጸሎት።

በድብቅ ጸልየን በአደባባይ ከእርሱ እጅ እንቀበላለን፤ በብዙ ነገር ተጨንቀን ግራ ተጋብተን ጥያቄ ተሞልተን፣ በፊቱ በጸጋው ዙፋን ፊት ስንሆን ግን ጥያቄዎቻችን ሁሉ ረስተን ፊታችን በርቶ እንመለሳለን።

ጸሎት መበርቻ፣ ጸጋ መቀበያ፣ ነፍሳችንን ማፍሰሻ ቦታ ነው። በቀን ውስጥ የጥሞና ጊዜ ያስፈልገናል ለጥቂት ደቂቃዎች ከአለም ጫጫታ ርቀን የእርሱን ድምጽ የምንሰማበት በጸሎት በፊቱ የምንሆንበት። ይህንንም በተከታታይነት የምንተገብረው ከሆነ ማደግ ይሆንልናል። ሰአቱ 5 ደቂቃ፣ 10 ደቂቃ .... ሊሆን ይችላል ዋናው ነገር በቀን ውስጥ ከአምላካችን ጋር መገናኘት መቻላችን ነው።

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐የመንፈሳዊ ህይወት እድገት

➤መርህ ሶስት ህብረት

“ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።”
መዝሙር 133፥1

መጽሀፍ ቅዱስ የወንድሞች ህብረት እጅግ ይደግፋል እንዲሁ ያበረታታል በህብረት ስንሆን አንዳችን አንዳችን እናንጻለን፣ እናበረታለን፣ እንማማራለን፣ ለአንዱ ያልተገለጠ ለሌላኛው ይገለጣል፣ አንዱ ያልተረዳውን ሌላው ይረዳል በህብረት በሆንንበት ቦታ ጌታም በዛ ስፍራ ከእኛ ጋር ይሆናል።

ማደግ ከፈለግክ በህብረት ከወንድሞች ጋር መሆን ነው።

➤ክፍል ሶስት

አንበሳ ወይም ነብር መንጋን ሊያጠቃ እንደማይችል ስለሚያው መንጋውን መበትን እንደ ስልት ይጠቀማል ጠላትም እንደዚሁ ነው መንጋውን ማጥቃት ስለማይችል በመጀመሪያ ሰው ከህብረት እንዲወጣ ነው የሚያደርገው ከዛም ብቻውን ሲያገኘው ለማጥቃት ይመቸዋል።

መዝሙር 133
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።
³ በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና።

በህብረት ውስጥ ከጌታ የታዘዘልን በረከት አለ ይህን በረከት ለማግኘት ለማደግም በህብረት አብሮ መሆንን አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው።

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐የመንፈሳዊ ህይወት እድገት

የመንፈሳዊ ህይወት እድገት ተግዳሮቶች  መቼም መልካም ነገር ለማድረግ ሲፈልግ ሲነሳም ያንን ማድረግ እንዳይችል የሚቃወም አይጠፋም በመንፈሳዊ ህይወታችን ማደጋችን ለሰይጣን መንግስትም ይሁን አገዛዝ ስለማያመቸው የእኛን መዘናጋት እና መደንዘዝ ይፈልገዋል።

ህጻንን ልጅ ለማታለል ብልጭልጭ እና አይንን የሚስብ ነገር በማሳየት ለመማረክ እንደምንሞክረው ሁሉ ጠላትም እኛን ለማስተኛት ለማታላል በህይወት ማደግ እንዳይሆን ብዙ መንገዶችን ይጠቀማል።

በማስፈራራት እንዳይመስላችሁ በማባበል ነው ከእውነት ከህይወት የሚያስወጣን እስቲ ቆም ብለን እናስብ ከእውነተኛ አምላክ ጋር እንዳንገናኝ ምን ፈተና እንደሆነብ እንይ። ለምሳሌ በእጃችን ላይ ያለው ስልክ አንድ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው ሰው በቀን ውስጥ ስልኩ ላይ ለ9 ሰአት ያህል ጊዜውን ይጠፋል በአብዛኛው ቲክቶክ ፌስቡክ እና ዮቲዮብ በመጠቀም እስቲ ካፌ፣ ባስ፣ ታክሲ፣ ትምህርት ቤት፣ አሁንማ ቤተክርስቲያን ፕሮግርራም ሁሉ ላይ ሳይቀር ሰው ስልኩን ከፋቶ ከላይ የጠቀስናቸውን ማህበራዊ ሚዲያዎች የጠቀማል፣ ሰዎች ተቀጣጥረው አብረው ከሚያወሩት ከሚጫወቱበት ጊዜ ይልቅ ሁሉም አንገቱን ቀርቅሮ ስልኩ ላይ የሚያጠፋው ጊዜ ብዙ ነው።
ታዲያ መፍትሄው ምን ይሆን? ራስን መግዛት ማደግ ከፈለግን ዋጋ መክፈል አለብን ምቾቶቻችንን መተው የራስ ደስታና ፍላጎትን ትቶ የእርሱን የጌታን መሻት እርሱም በፊቱ መሆን ነው መጨከንን መማር አለብን በቀን ውስጥ ለሰውነታችን የሚያስፈልገንን እንደምናደርግ ሁሉ ለመንፈሳዊ ህይወታችን አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ማድረግ መጸለይ ቃሉን ማንበብ በህብረት መሆን።

እግዚአብሔር አምላክ ይህን ማድረግ እንድንችል ጸጋን ይስጠን።

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W6

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
📖ከነገ ጠዋት 1:00  ጀምሮ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ መኖር በሚል ርዕስ ለተከታታይ  5 ቀናት የእግዚአብሔር ቃል ከወንድማችን ሳም ጋር የምናጠና ይሆናል  ዘወትር ጠዋት ከ1:00  ጀምሮ የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

💐ጥናቱ ላይ ሀሳብ ወይም አስታያየት እንዲሁም ጥያቄ በComment Section እና በ @Kaltube_bot የምንቀበላችሁ ይሆናል ።

መልካም  ሳምንት ይሁንላችሁ 💜

#Daily #Devotion #Kaltube #W7

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ መኖር

መግቢያ

ሰው በተፈጥሮ በእኔነት የተሞላ ነው የትኛውም ነገር ላይ ራስ ተኮርና በራስ ፈቃድ እና ሀሳብ ተራማጅ መሆንን ይፈልጋል ነገር ግን ይህ አካሄዱ ብዙ ሩቅ ሲያስጉዘው አንመለከትም። አዳም እና ሔዋን የወሰዱት የራስ የሆነ እርምጃ ይኸው ዛሬ ለእኔ እና ለእናንተ መዘዝ አትርፎልናል። ምድራችን ላይ ያለውንም ቀውስ ተመልክተን ሰው በራሱ መንገድ መጓዙ ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል፣ እያስከፈለውም እንዳለ መታዘብ እንችላለን።

ከዚህም ጋር ተያይዞ የተፈጠርነውስ እንዴት ልንኖር ነው እንደው ዝም ብለን የራሳችንን ፈቃድና ፍላጎት በመፈጸም ራሳችንን ደስ እያሰኘን እንድንኖር ወይስ የተፈጠርንበት ሌላ ምክንያት አለ?

ይህንን ሳምንት አብረን እንድናይ ያሰብኩት ከዚህ ጋር የተያየዘ ጉዳይ ነው። እንዲሁም ስለ እኛ ፈቃድ እና ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ በዛም ውስጥ መኖር የሚሰጠውን ጥቅም አብረን እንመለከታለን። ብዙ ጌታ እንደሚያስተምረን ተስፋ አደርጋለሁ።

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W7

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐የእኛ ፈቃድ

የእግዚአብሔር መንግስት አሰራር እጅግ ያስደንቀኛል ምኑ እንደሚገርመኝ ታቃላችሁ እኛ ከምናስበውም ከምናቅደውም እኛ ከምናየው እጅግ ሩቅ እና ፍጹም የተለየ በመሆኑ። ለእኛ ውብ ማራኪ ለእርሱ ግን በውስጡ ሞት እና ጥፋትን ያረገዘ ነገር ነው።

እኛ በጣም አስበንና ተጠበን ያደረግነው የወሰነውን ሞኝነት ለእኛ ትልቅ ዋጋ የሰጠነው ነገር በእርሱ ዘንድ ደግሞ እርባን የሌለው ሆኖ እናገኘዋለን። ለምሳሌ ያህል ሎጥ ከአብርሀም ጋር ሲለያዩ አብርሀም ምርጫ ሰጥቶት እንደነበር እናስታውሳለን። አንተ ግራ ብትሄድ እኔ ቀኙን አንተ ቀኙን ብትሄድ እኔ ደግሞ ግራውን ብሎ ምርጫ ሰጥቶት ነበር ሎጥም አይኑን አንስቶ ለአይን የሚማርከውን ለምለም የሆነውም ውብ የሆነውን ስፍራ መረጠ።

የእርሱም ፈቃድ በዛ ስፍራ መኖር ነበር እንደ ሰው ስታስቡትም ትክክል ነው የመረጠው ማናችንም ብንሆን ይህንን ነው የምንወስነው። ነገር ግን ከሚታየው በስተጀርባ ስላለው ነገር ምንም አላወቀም ቢያውቅ ኖሮ በእሳት ዲን የምትጠፋውን እጅግ ዘግናኝ የሆነ ክፋት የተሞላ የሰዶም እና ጎሞራ ከተማን አይመርጥም ነበር።

🔍እንዲሁም አዳም እና ሔዋንን ማንሳት እንችላለን ስታየው ለመብላት የሚይጎመጅ እንደሆነ ጥበብ የሚሰጥ እንደሆነ ነው ለእርሷ የታያት ከዛ በስተጀርባ ስላለው ነገር እምብዛም አላሰበችም ብታውቅ ኖሮ ከእርሷ አልፎ እስከ አለም መጨረሻ ድረስ የሚወለዱትን ትውልድና ዘሮችዋን ዋጋ የሚያስከፋልን ምርጫ አትመርጥም ነበር።

🎯የእኛ እይታ የቅርብ የቅርቡን ብቻ ነው ትልቁ ትኩረታችንም የዛሬን ችግር መፍታት ላይ ብቻ ነው አሻግሮ መመልከት አንችልም ያየንም ሊመስለን ይችላል ነገርግን እውነታው እኛ የቅርቡን ብቻ ነው የምናየው።

👁 እይታችን የቅርብ ብቻ ከመሆኑ የተነሳ
ለዘለቄታው ለእኛ የሚሆነንን አናቅም ጅማሬውን እንጂ አሻግረን ፍጻሜውን አናየውም።

🔹ጊዜ አይበቃንም እንጂ ብዙ ምሳሌዎችን ማንሳት እንችል ነበር። በዋናነት በዚህ ቀን ላይ የእኛ ምርጫ ዋጋ ቢስ እንደሆነ እንድናስብ በትህትና ልጠይቅ ወዳለሁ ለዚህም ዞር ብለን ትላንታችንን ማየት  በቂ ነው !

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W7

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐የእርሱ ፈቃድ

🫂አባት ምን ጊዜም ለልጁ ምርጥ ምርጡን ነው የሚያስበው ለወለዳቸውም ልጆች እጅግ ጠቃሚ የሆነውን እና አስፈላጊ የሆነውን ነገር ነው የሚያደርግላቸው።

💡ጌታ ኢየሱስ እናንተ ክፍዎች ሆናችሁ መልካም ማድረግ ካወቃችሁ እንግዲያውስ የሰማዩ አባታችሁ እንዴት አብልጦ አያደርግላችሁ ብሎ ነው ያስተማረን እኛ ክፋ ሆነን መልካም ካሰብን ለልጆቻችንም መልካም ካደረግን ጌታ ደግሞ እጅግ መልካሙን ነው የሚያደርግልን።

🖊በእርግጥ ብዙውን ጊዜ እኛ የራሳችንን ፈቃድ ለመፈጸም እንሮጣለን ፈቃዱንም ለመጠየቅ ጊዜ የለንም እንጂ እርሱ ለእኛ የሚያስበው ሀሳብ እጅግ መልካም ነው። በወቅቱ ባይመስልም ነገሩ እኛ የምንፈልገው አይነት ባይሆንም ጫማ ስንገዛ በሚገባ የሚሆነን አይተን እንደምንገዛው ሁሉ እርሱም ለእኛ ግጥም የሚለውን ልክ የሚሆነን ነው የሚሰጥን የሚያረግልንም።

🕯የእርሱ ፈቃድ መልካምነት ያለበት ነው። በውስጡ ሀዘን እና ጸጸት አይገኝበትም። እኛ ለልጆቻችን፣ ለታናናሾቻችን የሚጠይቁንን ሁሉ አናደርግም ምክንያቱም የሚጠይቁት ለእነሱ ደስታ የሚሰጥ እንጂ በውስጡ የሚጠቅም ይሁን ጥቅሙሙ ዘላቂነት ያለው አይሁን አያውቁም። ብቻ ደስ ስላላቸው ይጠይቃሉ እኛ ግን ከነሱ ከፋ ስላልን ነገሮችን ስለምናገናዝብ ሁሉን እንሰጥም።

ልክ እንደዚሁ እርሱ ለእኛ ከእኛ በላይ ያስባልና ሁሉን አያደርግም የሚጠቅመንን ብቻ።

👉እስቲ ዛሬ "እኔ" የሚለውን ነገር ትተን የእኛን ፍላጎት ወደጎን አድርገን ፈቃዱን እንጠይቅ ። በስራችን፣ በትምህርታችን፣ በፍቅር ግንኙነት ምርጫችን ፈቃዱን እንፈልግ።

ይህን ቀን ስንውል የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈለግ የምንውልበት ቀን ይሁን።


መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W7

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
እኛ ለራሳችን ክፋዎች ነን!

🔹እኛ ለራሳችን ክፋዎች ነን ለራሳችን አናውቅበትም። የምናውቅ እንመስላለን ነገር ግን በራሳችን የተጓዝንባቸው መንገዶች በብዙ ዋጋ አስከፍለውናል በህይወታችን ላይ ጠባሳ አሳድረዋል የጸጸት ምክንያት ሆነውብናል።

🔹ከሁሉም አስቀድመን እኛ ለራሳችን አለማወቃችንን ማወቅ አለብን ለራሳችን የምናውቅ ሰዎች አይደለንም ይህንን በደንብ መገንዘብ አለብን እኛም ልክ እንደ ልጆቻችን ዝም ብሎ ስላስደሰተን ብቻ የምንጠይቀው፣ የምንፈልገው፣ የምንመርጠው ብዙ ነገሮች አሉ።

🔹ራሳችንን ለእረኛችን አሳልፈን መስጠት አለብን በህይወታችን በሚሆኑ ነገሮች ሁሉ እርሱ እረኛችን ስለሆነ መሪያችን ስለሆነ ከእኛ በላይ ለእኛ ስለሚያስብ በነገር ሁሉ ፈቃዱን መፈለግ አለብን።

#በሕይወታችን እኔ የእኔ የምንለውን ነገር አይኑር ምክንያቱም ዋጋ ስለሚያስከፍለን። ንጉስ ዳዊት እጅግ የሚገርም ማንነት ነበረው በነገር ሁሉ ፈቃዱን ይጠይቃል ጦርነት ሲገጥመው ጌታ ሆይ ልውጣን? ብሎይ ይጠይቃል ለሚወስነው ውሳኔም የአምላኩን ፈቃድ ይፈልጋል።

🔹ሚስቱ፣ ልጆቹ፣ ንብረቱ ተማርኮ እንኳን ልውጣ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ? ብሎይ ይጠይቃል እኛም እንደዚሁ እንድንሆን ጌታ ይርዳን በነገር ሁሉ ፈቃዱን የምንፈልግ፤ ድምጹን ሳንሰማ ውሳኔ የማንወስን ያድርገን።

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W7

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐በራስህ ማስተዋል አትደገፍ

ምሳሌ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤
⁶ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።

በዚህ ሳምንት በመጀመሪያ እንዳነሳነው የእኛ ማስተዋል እና ጥበብ ከንቱ ነው። የጌታ ቃልም ይህንን ያስረግጥልናል በራስህ ማስተዋል አትደገፍ እሽ ምን እናድርግ ብለን ስንጠይቅ በመንገዱህ ሁሉ እርሱን እውቅ ይህ ማለት እርሱን በነገር ሁሉ አስቀድም ፈቃዱን ጠይቅ የእኛ ችግር በራሳችን ማስተዋል መደገፋችን ነው ያ ደግሞ ይህው ከአዳም እና ሔዋን ጀምሮ ያመጣው መዘዝ አይተናል እግዚአብሔርም አምላክን ስለሁሉ መጠየቅ ማማከርን መልመድ አለብን እርሱ በምክሩ መርቶ ወደ ክብር ያወጣናል።

“በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዓይኖችህ በአዳም ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።”
— ኤርምያስ 32፥19

እርሱ በምክሩ ታላቅ ነው የእርሱ ምክር ለዘላለም ያቆማል በራሳችን አይን ተመልክተን ብቻ አንሩጥ ምናልባት መጥፊያችን ይሆን ይሆናል የምንጸጸትበት ምርጫ ይሆናል በእርሱ ፈቃድ ውስጥ ግን ሰላም አለ እረፍት አለ ችግሮች ቢኖሩም ቢፈጠሩም እርሱ ያለበት ስለሆነ ሁል ጊዜ ድሉ የእኛ ነው።

በመጨረሻ በዚህ አዲስ አመት የእኔን መንገድ ትተን የእርሱን መከተል የምንጀምርበት አመት ይሁንልን የእኛ መንገድ ጥፋት ስለሆነ ነገር ግን በፍቅር ምርጫ፣ በምንኖርበት መኖሪያ ምርጫ፣ በትምህርት፣ በስራ ብቻ በሁሉም ነገር የእርሱን ፈቃድ እየጠየቅም የምኖርበት አመት ይሁንልን

መልካም ቀን ተመኘሁ

#Daily #Devotion #Kaltube #W7

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
📖ከነገ ጠዋት 1:00  ጀምሮ የእግዚአብሔር ፍቅር (አጋፔ) በሚል ርዕስ ለተከታታይ  5 ቀናት የእግዚአብሔር ቃል ከእህታችን ያብስራ(ያቢ) ጋር የምናጠና ይሆናል  ዘወትር ጠዋት ከ1:00  ጀምሮ የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

💐ጥናቱ ላይ ሀሳብ ወይም አስታያየት እንዲሁም ጥያቄ በComment Section እና በ @Kaltube_bot የምንቀበላችሁ ይሆናል ።

መልካም  ሳምንት ይሁንላችሁ 💜

#Daily #Devotion #Kaltube #W8

💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
💐አጋፔ (የእግዚአብሔር ፍቅር )

መግቢያ

ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በጻፈው በአንደኛ መልእክቱ በ13ኛው ምዕራፉ ላይ የድርጊታችን ሁሉ መነሻ ፍቅር መሆን እንዳለበት፣ ደግሞም ፍቅር የራሱ የሆኑ መገለጫ ባህርያት እንዳሉት ካሳየ በኋላ .........

➥መሉ ለማንበብ  👉 ይጫኑ

➥ወይም ከምስሉ በታች ያለውን Instant View ይጫኑ
#Daily #Devotion #Kaltube #W8
የእግዚአብሔር ፍቅር በኢየሱስ!

ሐዋርያው ዮሐንስ በመጀመሪያ መልዕክቱ ኢየሱስ ከሁሉ የላቀ የፍቅር መገለጫ እንደሆነ ተናግሯል፡፡

"እግዚአብሔር ፍቅሩን በመካከላችን የገለጠው እንዲህ ነው፤ እኛ በእርሱ አማካይነት በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ፡፡ ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተሰረያ............

➥መሉ ለማንበብ  👉 ይጫኑ

➥ወይም ከምስሉ በታች ያለውን Instant View ይጫኑ
#Daily #Devotion #Kaltube #W8
💐እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን!

እግዚአብሔር መንፈስ ከመሆኑ የተነሣ ፍቅሩ ከስሜታዊነት ይልቅ መንፈሳዊ ነው። ይህ ምን ማለት ነው? መንፈሳዊ ፍቅር እውነተኛ ያልሆነ ወይም ግላዊ ያልሆነ ይመስላል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር ከማንኛውም ዓይነት ፍቅር የበለጠ እውነተኛ፣ ቋሚ እና አስተማማኝ ነው። እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እና ...............

➥መሉ ለማንበብ  👉 ይጫኑ

➥ወይም ከምስሉ በታች ያለውን  Instant View ይጫኑ

#Daily #Devotion #Kaltube #W8