በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 9
ምሥጢሩ THE MYSTERY
“ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው።” — ቆላስይስ 1፥27
➢በብሉይ ኪዳን የነበሩ ታላላቅ አባቶቻችን፣ እጅግ የላቀ አገልግሎት ያገለገሉ መጪውን ዘመን በጥልቀት ይመረምሩ የነበሩ ሊቃውንትና ጠቢባን እንዲሁም ዘመን አዋቂዎች፣ ነቢያት ሳይቀሩ ምስጢር ሆኖባቸው ያለፈ አንድ ምስጢር ነበር። ይህ ምስጢር አባቶች ከሩቅ አይተው የተሳለሙት የአዲስ ኪዳኑ በግ፣ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ፣ ህግን በፀጋ የሻረው፣ሰማይን ከምድር ያስታረቀ፣አልፋ ኦሜጋ መጀመሪያ መጨረሻ፣ለእድሜው መነሻና መድረሻ የሌለው፣ሁሉን የሚገዛው፣ ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስም ባለቤት፣ በሰማይ ከብሮ ለዘላለም በአብ ቀኝ የተቀመጠው አሁን ግን የተገለጠልን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሃሌሉያ!! 🔥
➢በህግ ቀንበር ስር ሆነው የኖሩ፣በሚያስፈራ እና በሚጤስ የሲና ተራራ ክብር ውስጥ ሆነው ያገለገሉ የሞት አገልጋዮች— 2ኛቆሮ 3፥7
ህጉ እለት እለት የሚወቅሳቸው የብሉይ ቅዱሳን በእምነት መፅደቃችን፣በኮርማ ደም ሳይሆን በልጁ ደም መታጠባችን፣ ወደ ሲና ተራራ ሳይሆን ወደ ፂዮን ተራራ መድረሳችን፣ “የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም መድረሳችን — ዕብ 12፥24 ይህ ሁሉ ለብሉይ ቅዱሳን ከአዕምሮ በላይ የሆነ ሊገመት የማይችል ታላቅ የእግዚአብሔር የማዳን አጀንዳ ነው።
➢ይህ “ምሥጢር” ተብሎ የተጠቀሰው ቀደም ሲል ተደብቆ የነበረ ነገር ግን አሁን ''በአዲስኪዳን በእግዚአብሔር የተገለጠው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
የክብር ተስፋ በእኛ ዘንድ መሆኑ
THE HOPE OF GLORY IN US
ቀድሞ ምሥጢር የነበረው አሁን የተገለጠው፣ ክርስቶስ በእኛ ውስጥ የወደፊቱ የክብራችን ተስፋ ነው።
➢በብሉይ ኪዳን፣ መንፈስ ቅዱስ ለአገልግሎት ኃይል እንዲሰጣቸው በተወሰኑ ሰዎች(በካህናት፣በነገስታት፣በነቢያት ላይ ብቻ ይወርድ ነበር። ከዚያ በኋላ ተመልሶ ይሄድ ነበር።እኛ አማኞች ግን መንፈሱ በቋሚነት በሁላችንም ስለሚያድርብን የአዲስ ኪዳን አማኞች እጅግ ብሩካን ነን።ለአዲስ ኪዳን አማኞች የተሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ቋሚ ማደሪያ መሆናችን ለብሉይ ኪዳን ቅዱሳን “ምሥጢር” ነበር።
➢መንፈስ ቅዱስ ለቤዛ ቀን አትሞናል (ኤፌ 4፡30)።በሌላ አነጋገር፣ የመንፈስ በልባችን መገኘት የመጨረሻውን ድኅነታችንን ዋሰትና ነው። እግዚአብሔር እኛን ፍፁም አድርጎ እስኪያጠናቅቅ ድረስ በእኛ ውስጥ መስራቱን ይቀጥላል (ፊል 1፡6 )። ይህ ወደ ፊት የሚመለከት የፍጽምና ዋስትና “ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ያለው፣ የክብር ተስፋ” ምልክቱ ነው።
ይህ የክብር ተስፋችን:--
1ኛ የክብር ተስፋችን ትንሣኤያችንንም ይጨምራል፡- “ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ ምክንያት ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል። ሮሜ 8፡11)።
2ኛ ይህ የክብር ተስፋችን ሰማያዊ ውርሳችንን ይጨምራል፡- “በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋ፣ ለማይጠፋ፣ ለማይጠፋና ለማይጠፋ ርስት በታላቅ ምሕረቱ አዲስ ወለደን። ይህ ርስት በሰማይ ተጠብቆላችኋል” (1ጴጥ1፡3-4)።
3ኛ ይህ የክብር ተስፋችን በውስጣችን ያለው የክርስቶስ መንፈስ “የእኛ ርስት መያዣ” ነው (ኤፌ1፡14)።
አሜን!!!
✍ መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
ክፍል 10 ይቀጥላል
👇💐👇💐👇💐👇💐
@KALTUBE

ክፍል 10
በክርስቶስ አሸናፊዎች
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።ሮሜ 8፡37
➢አሸናፊነት ማለት ባላንጣን ተቀናቃኝን ወይም ጠላትን የማሸነፍ ብቃት ነው።የመግቢያ ጥቅሳችን ላይ እንዳነበብነው በወደደን በእርሱ (በክርስቶስ)ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
➢እንደ አማኝ በዚህ የምድር ቆይታችን የተለያዩ ፈተናዎችን በምንጋፈጥበት ጊዜ በክርስቶስ አሸናፊዎች መሆናችንን በመረዳት በእምነት ልንፀና ያስፈልጋል።የኛ ድል በፈተናዎች ውስጥ የተረጋገጠ ነው።በዚህ ሁሉ የአንድ አማኝ ድርሻ በክርስቶስ አሸናፊ መሆኑን አውቆና ተገንዝቦ በዚያ ንቃተ ህሊና እምነት መመላለስ ነው። ምክንያቱም የድልም ይሽንፈትም ጅማሬ ሀሳባችን ላይ ስለሆነ። “ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።”— 1ኛዮሐ 5፥4
➢በብሉይ ኪዳን ሙሴ የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ የላካቸው ሰላዮች ሰልለው ሲመለሱ ይዘውት የተመለሱት ሪፖርት የጠላቶቻቸውን የበላይ መሆን፣ግዙፍ ኔፍሊም እና አስፈሪ መሆናቸውንና፣በነሱ አይን እንደ አንበጣ መሆናቸውን ነበር። ይህን ሪፖርት ለእስራኤላውያን ሲያሰሙ መላው ህዝቡ ምነው ከግብፅ ባልወጣን ብለው እግዚአብሔር ላይ እንዲያጉረመርሙ ዳርጓቸው ነበር።ይህን ታሪክ ስናነብ የተሻናፊነት መንፈስ ከራስ ተርፎ ለሌላውም የወድቀትና የፍርሀት ምክንያት ሲሆን እናያለን።
➢ይህ ብቻ አይደለም እስራኤላውያን ትተው ወደመጡበት ወደ ግብፅ ለመመለስ አለቃ ለመሾም ምክክር ሁሉ ጀምረው ነበር።( ዘኍ 13፥17--33) ይህን ክፍል ሳነብ የሚገርመኝ እስራኤላውያን ግን ምን አስበው ነው?? ያን ሁሉ ተአምራት አይተው ለ40 አመታት በነፃ ከሰማይ መና እየተመገቡ፣በምድረበዳ ከጭንጫ አለት ውሃ ፈልቆ እየጠጡ፣ በደመናና በእሳት ታጅበው ፣ቀይ ባህርን በተአምር ተሻግረው እዚህ ከደረሱ በኋላ እንደገና ወደ ግብፅ ለመመለስ የውይይት ስብሰባ ለማድረግ ማሰባቸው ይደንቀኛል።
➢በተቃራኒው ግን ኢያሱና ካሌብ የአሸናፊነት እና የድል አድራጊነት መንፈስና ስነልቦና ስለነበራቸው በአምላካቸው በእግዚአብሔር ታምነው እንዲህ አሉ
''ምድርን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤
ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም ናት። እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል። ነገር ግን በእግዚአብ ሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው።”
ዘኍል 14:6-9
➢በአሸናፊ የክርስትና ህይወት ለመመላለስ እምነት እጅግ አስፈላጊ ነው በወደደን በክርስቶስ የትኛውም ችግር ተሸናፊ መሆኑ በቃሉ ተረጋግጧል። እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው ፍቅር ታላቅ ነው።አሸናፊነት የአማኞች እጣ ፈንታ ነው።
ሃሌሉያ!!
✍ መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
ክፍል 11 ይቀጥላል

ክፍል 11
በኢየሱስ ስም አጋንንት
የማስወጣት ስልጣን
ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ ማር 16:17
➢ የኢየሱስ ስም የመለኮት ስም ነው። የኢየሱስ ስም ስልጣንና ኃይል ያለው ስም ነው። የኢየሱስ ስም ክቡር ስም ነው። የኢየሱስ ስም ሁሉ የሚሰማውና ምላሽ የሚሰጠው የመጨረሻው ከፍተኛ ባለስልጣን ስም ነው። የኢየሱስ ስም የሚታዩና የማይታዩ ፍጥረታት ሁሉ ገዢ ስም ነው። የኢየሱስ ስም በሰውና በአጋንንት ባለስልጣናት ሁሉ ላይ የበላይ ሰም ነው።
ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠ ው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ ኤፌ1 : 20-21
➢ የኢየሱስ ስም የሰማይ ፈውስ ምንጭ፣ የዘላለም ህይወት ማግኛ መንገድ፣ የሰላምና የደስታ ሁሉ ጥቅል ነው። የኢየሱስ ስም ከስሞች ሁሉ የሚበልጥና ስም ያላቸው ነገሮች ሁሉ የሚገዛ ስም ነው። ኢየሱስ በሚለው ስም ውስጥ የመለኮት ኃይል፣ክብርና ስልጣን ይታያል። ጌታ ኢየሱስ ለአማኞች የሰጠን አንዱ ትልቁ ስጦታ ስሙን የመጠቀም መብት ነው።
➢ስሙን ጠርተን አጋንንት እንድናስወጣ፣ የታመሙ እንድንፈውስ፣በስሙ ስልጣን ሁሉን እንድንገዛ የኢየሱስ ስም በእምነት በኩል በሆነ ህጋዊ መንገድ ለእኛ ተፈቅዷል።
➢ ዳግም ሳይወለዱ ይህን ስም ለመጠቀም የሚጠሩ ብዙዎች ይገኛሉ። በከንቱ ስሙን የሚጠሩ ሰዎች ግን የስሙ ስልጣን፣ሃይልና ክብር አይገለጥባቸውም።
አንዳንድ ሰዎች ጠንቋይ እንኳ ኢየሱስን ሲጠራ ተአምራት የሚሆን ይመስላቸዋል።ነገር ግን ስህተት ነው።ስሙ የሚሰራው ማንም ላይ ሳይሆን ስሙን በትክክል ባመኑ፣በዳኑ አማኞች እና ስሙን የመጠቀም መንፈሳዊ መብት ለተሰጣቸው ሰዎች ነው።
➢የኢየሱስ ስም ህገወጥ በሆነ መንገድ ይሰራል ብሎ ማመን ስህተት ነው።ኢየሱስ ስሙን በከንቱ እንድንጠቀም ለማንም ውክልና አይሰጥም።ይህን ጉዳይ በተመለከተ በሐዋርያት ስራ መጽሐፍ ላይ አንድ አስተማሪ ክስተት እናነባለን።
አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች። ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት።ክፉው መንፈስ ግን መልሶ። ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው። ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም። የሐዋር 19 : 12--16
➢ የኢየሱስን ስም ሳያምኑና ዳግም ሳይወለዱ ስሙን በአጋንንት ላይ በጠሩ ጊዜ አጋንንቱ ለቆ አልወጣም። ምክንያቱም ስሙን የመጠቀም መለኮታዊ መብት አልነበራቸውም።
አጋንንቱ የጠየቀውን ጥያቄ እናስተወል
......ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው
➢ይህ አጋንንት ሐዋርያው ጳውሎስን ያውቅ ነበር። ይህ ማለት ለጳውሎስ ይገዛ ነበር።
➢ የኢየሱስን ስም ጠርቶ ተፅዕኖ ማምጣት ለአማኞች ብቻ የተፈቀደ ነው። ስለዚህ ስሙን ጥሩት።ስሙን መልመድ የለብንም። ስሙን ለእግዚአብሔር መንግስት ማስፋፍያ ፣ለወንጌል ምስክርነት፣ለድልና ለስኬት፣ ለሚያስፈልገን የሰማይ ሃይል ሁሉ እንጥራ።
የኢየሱስ ስም ብርቱ ነው። የኢየሱስ ስም ኃያል ነው። የኢየሱስ ስም መንፈሳዊ ውጊያን የምናሸንፍበት ትልቁ ቁልፍ ነው።
ክብር ለስሙ ይሁን።
ኢየሱስ ጌታ ነው!!
ክፍል 12 ይቀጥላል

ክፍል 12
በክርስቶስ ያገኘነው ነፃነት
¹⁷ ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። (2ቆሮ 3:17)
➢በክርስቶስ፣ ከህግ ጨቋኝ ስርዓት እና ከኃጢአት ቅጣትና ኃይሉ ነፃ ወጥተናል።የኛ የክርስቲያኖች ከህግ ነፃ መውጣት ለኃጢአት ፈቃድ መስጠት ማለት አይደለም። በክርስቶስ ነፃ ወጥተናል፤ ነገር ግን በሥጋ ፈቃድ ለመኖር እንደፈለግን ለመኖር ነፃ አይደለንም፡-
“ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋ ልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ።”ገላትያ 5፥13
➢አማኞች ኃጢአትን ለመሥራት ነፃ አይደሉም፣ ነገር ግን በክርስቶስ ቅዱስ ሕይወት ለመኖር ነፃ ናቸው። እንደ አማኝ በክር ስቶስ ኢየሱስ አምነን ከዳንን በኋላ በስነ ስርዓ ት መኖር የምንችለው ህግን ከፀጋ ጋር በቀላ ቀለ አስተሳሰብ ሳይሆን ፀጋን በትክክል በመረዳት ነው።
➢ሰው በህግ አስተምሮ ሊቀየር አይችልም፣ የሰውን ልጅ ነፃ ሊያወጣው የሚችለው የፀጋ ትምህርት ብቻ ነው። ይህ የብሉይ ዘመን አይደለም፤ይህ የአዲስ ኪዳን ዘመን ነው። ሰዎች ወደመዳን እንዲመጡም ሆኖ ከዳኑ በኋላ እንዲፀኑ የሚረዳቸው ፀጋ ብቻ ነው። ፀጋ ኃጢአትን ማስካድ የሚችል የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችን ን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃ ኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ (ቲቶ 2:12-13)
➢ቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሰዎች ስለ ፀጋ ማስተማር ለኃጢአት ነፃነት መስጠት ነው ብለው ስለሚያስቡ ህግን መስበክ ደስ ይላቸዋል። እንዲያውም አንዳንድ አስተማ ሪዎች ለምዕመናን ቆንጠጥ ያለ ትምህርት ያስፈልጋል ሲሉ ይደመጣሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ፀጋ ፀጋ እያሉ ምዕመኑ መንገድ ሳተ የሚሉ ንግግሮች መስማት ተለምዷል። ነገር ግን አንድ ጥያቄ መጠየቅ አለበት። ለመሆኑ ፀጋ ሰዎች እንደፈለጉ እንዲሆኑ ያደርጋል የሚለው አስተሳሰብ ከየት ነው የመጣው??
➢ይህ አስተሳሰብ መ/ቅዱሳዊ ሊሆን አይችልም።ሰዎች ሀጢአት እንዳይሰሩ በህግ በማስፈራራት ሳይሆን ሀጢያትን የሚያስክ ደውን ፀጋ ብናስተምራቸው በክርስቶስ ነፃ ይወጣሉ። ዋ! ወዮልህ! እሳት ይበላሀል፣ ትሞታለህ! ሲዖል ሲዖል ! እያልን ሰዎችን ፍርሀት ውስጥ መክተት ኩነኔ ውስጥ እንጂ በክርስቶስ ኢየሱስ ህይወት ውስጥ እንዲመ ላለሱ አቅም አይሰጥም። የኛ ቁጣ የእግዚአ ብሔርን ፅድቅ እንደማይሰራ ማወቅ አለብን። ቁጣ ቁጣ ሲለን በብሉይ ኪዳን ያነበብነውን የቅጣት ታሪክ እየመዘዝን ሰዎችን የምንወግር ከሆነ ገና ፀጋ አልገባንም።
ሰዎች ፀጋን አለአግባብ እና ከመ/ቅዱሳዊ አስተምህሮ ዉጪ ለስጋ ነፃነት የሚሰጥ አድርገው ከሰበኩ ብቻ ነው የፀጋ ትምህርት አላማውን ሊስት የሚችለው።
➢ በአዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር ቁጣ በልጁ በኢየሱስ በመስቀል ላይ ሳለ ወርዶ አልቋል። አሁን ምህረት ዘንቧል።ቁጣው በርዷል፣ፍቅሩ ተገልጧል። እግዚአብሔር አብ በልጁ ደስ ተሰኝቷል።
➢የስብከታችን ርእስ የሰዎች ኃጢአተኛ መሆን ሳይሆን የኢየሱስ አዳኝነት ነው ሊሆን የሚገባው።ተወርቶ ፣ተነግሮ፣የማይጠገበው እግዚአብሔር በአንድ ልጁ ላይ የጨከነበት እና እኛን የወደደበት አጋፔ ፍቅሩ ነው።
➢ፀጋ ለሀጢአት ያለንን መሻት በመግደል ለስጋ እድል ፈንታ እንዳንሰጥ የሚያስተምረን አስተማሪ ነው። ከፀጋው ውጪ ክርስትና፣ድል፣ አሸናፊነት፣እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይታሰብም።የእግዚአብሔር ፀጋ የአዲስ ኪዳን ህይወት ማዕከላዊ የክርስትና ህይወት ምስጢር ነው።
ሃሌሉያ!!
ክፍል 13 ይቀጥላል
✍መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)

መሥዋዕት!
ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን! መሥዋዕት ቁጥር 4 አልበም በዚህ ሳምንት ይለቀቃል!እስከዚያው ከአልበሙ ውስጥ"በማለዳ"በተሰኘው አዲስ ዝማሬ ተባረኩ!
https://youtu.be/binGZ6i8-yI?si=kcGoXx-QIYBNh9Hz
https://youtube.com/@hannatekleofficial?si=Vu4U3C8z-QtxX1jV

YouTube
1.በማለዳ//Bemaleda//Hanna Tekle//Nov'2024
በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 13
በክርስቶስ ያገኘነውን ነፃነት መጠበቅ
በገላትያ 5፡1-15፣ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ክርስቲያናዊ ነፃነት ምንነት ሲናገር፣ “ክርስቶስ አርነት ባወጣን ነፃነት ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።(ገላትያ 5:1)ይላል
➢አንድ ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ ከዳነ በኋላ ዳግም ወደ ህግ እስራት እንዲመለስ የሚዳርጉ ነገሮች
1ኛ-ሰው በፀጋ ከዳነ በኋላ በራስ መልካምነ ትና መልካም ስራዎች ላይ መደገፍ ሲጀምር (ኤፌ 2:7)
2ኛ- ፀጋ ላይ ከመደገፍ ይልቅ በህግ ወይም በራስ ፅድቅ ላይ ትኩረት ማድረግ (ኤፌ 2:8)
3ኛ የተለያዩ አይነት ግራ የተጋቡ መምህራንንና ትምህርቶችን በመስማት ከእውነተኛው የፀጋ ትምህርት ፈቀቅ ማለት።(ገላቲያ 3)
4ኛ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፀጋ ከሚያስተምረው አስተምህሮ ዉጪ የተለጠጠና የተጋነነ እንዲሁም ፅንፍ የረገጠ ፣ስጋ ተኮር አስተምህሮዎችን መከተል፣ (ሮሜ 6:1)
5ኛ ፀጋና ህግን የደባለቀ (HYBRID) አስተሳሰብ።ክርስትና የሁለቱ ጥምረት ውጤት ሳይሆን የፀጋ ብቻ ውጤት ነው። ( ገላቲያ 3)
6ኛ ቀድሞ የሰማነውን እውነት ከጊዜ በኋላ ትኩረት አለመስጠት እና አለመፅናት(ቆላሰ2:7
7ኛ በአዕምሮ አስተሳሰብ አለመለወጥ።(ሮሜ 12:3)
8ኛ ከጊዜ የተነሳ አስተማሪ መሆን ሲገባ እንጭጭ ሆኖ መቅረት(ዕብ 5:12) እንደ ምክንያት መነሳት ይችላሉ።
➢በክርስትና ህይወታችን የምንሰማቸው ትምህርቶች ወይ እምነታችንን ከፍ ያደርጋሉ አሊያም ይበርዛሉ። በተለይ በደህንነታችን እና በፀጋ ዙርያ የምንሰማው ትምህርት የህይወታችን ማዕከል ስለሆነ በተረዳነው እውነት ፀንተን ልንኖር ያስፈልጋል።
➢ህግን የቀላቀሉ፣የተምታቱ እና ወደ ክርስቶስ ሙላት የማያስጠጉ የትምህርት ነፋሶች ይዘውን እንዳይሄዱ በአለቱ ላይ ቤታችንን መስራት አለብን።
“አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤”— 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥14
✍መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
ክፍል 14 ይቀጥላል

ክፍል 14
በመንፈስ መመላለስ
በመንፈስ መመላለስ ሶስት አይነት ገፅታዎች ያለው ሲሆን የመጀመርያው በመንፈስ ፍሬ መመላለስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት መመላለስ ነው ሶስተኛ እንደ እግዚአብሔር ቃል መመላለስ ነው።
1ኛ በመንፈስ ፍሬ መመላለስ
➢የመንፈስ ፍሬ ሲባል ፍቅርን፣ ደስታን፣ ሰላምን፣ ትዕግሥትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ ታማኝነትን፣ የውሃትን፣ ራስን መግዛት ተብለው የተጠቀሱት ናቸው። (ገላ 5፡24)
1. ፍቅር፡እግዚአብሔርንና ሌሎች ሰዎችን መውደድ ነው።
2. ደስታ፡ የመንፈስ እርካታ እና መረስረስ ነው።
3. ሰላም፡ ከጭንቀት እና ከጭንቀት ነፃ መሆን ነው። (ፊልጵ 4፡6–7)።
4. ትዕግስት፡ ንዴትን የመቆጣጠር ብቃት ነው።
5. ቸርነት፡ የሌሎችን ፍላጎት እና አሳሳቢ ጉዳዮች ትኩረት መስጠትና ረጂ መሆን ነው።
6. በጎነት፡ ተግባራዊ ቅድስና ነው።
7. እምነት፡- ፈተናዎችን እና መከራዎችን ስንጸና እግዚአብሄርን አንተወውም ወይም ጀርባችንን አንሰጥም።
8. ገርነት፡ የትህትና መንፈስ ነው።
9. ራስን መግዛት፡ በኃጢአት ግፊት አለመሸነፍ ነው። ከላይ የተጠቀሱት 9ኙ የመንፈስ ፍሬዎች በመንፈስ የሚመላለስ ክርስትያን መገለጫዎች ናቸው።
2ኛ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት መመላለስ
በዮሐንስ 10: 27: በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ ተብሎ ተፅፏል። በመንፈስ የመመላለስ ሌላው ገፅታ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት መመላለስ ነው። ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስን በቀጥታ በመታዘዝ መመላለስ ነው።መንፈስ ቅዱስ በተለያዩ መንገዶች እንደሚናገር ቅዱስ ቃሉ ያስተምረናል።
እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ሰው ግን አያስተውለውም።በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥ በዚያን ጊዜ የሰዎችን ጆሮ ይከፍታል፥በተግሣጹም ያስደነግጣቸዋል፥ ኢዮብ 33:14-16
3ኛ እንደ እግዚአብሔር ቃል መመላለስ
የእግዚአብሔር ቃል የክርስትና ህይወት አዉራመንገድ ወይም ሃይዌይ ነው። ቃሉ የህይወታችን መሪ እና አቅጣጫ ጠቋሚ ነው።
ህይወታችን ከተፃፈው ቃል ጋር ተስማምቶ የሚጓዝ ከሆነ በመንፈስ የመመላለስ መገለጫ ነው።
“ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። (ማቴ 7:24)
➢በመንፈስ ለመመላለስ ራሳችንን በፈቃዳችን ለእግዚአብሔር ልናስገዛ ያስፈልጋል።መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳን እራሳችን ከሀይለኛው በታች ዝቅ እናድርግ። ብቃትችን መንፈስቅዱስ መሆኑን ተረድተን በእርሱ ላይ እንደገፍ። በድካማችን ወደ ሚራራልን ጌታ እንቅረብ፣ በፆምና በፀሎት ፊቱን ሁልጊዜ እንፈልግ። ቃሉን እናንብብ፣ እናጥና ፣እናሰላስል!
ክፍል15 ይቀጥላል

ክፍል 15
በአዕምሮ መታደስ
➢እንደ አማኝ ካመንበትና ከዳንበት ቅፅበት ጀምሮ በአስተሳሰብ ለውጥ ውስጥ እንድንመላለስ የእግዚአብሔር ቃል ያዘናል።
የመንፈሳችን መዳን ምንም እንኳ ቅፅበታዊ
ቢሆንም የአስተሳሰብ ለውጥ ግን ሂደት ነው።
የአስተሳሰብ ለውጥ የህይወት ለውጦች ሁሉ መጀመሪያ ነው። አዕምሮ ሳይለጥ ምንም በህይወታችን የሚለወጥ እውነተኛ ነገር የለም።
''የእግዚአብሔር' ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።'' ሮሜ12:2
➢አዕምሯችን የህይወታችን ማዕከላዊ የለውጥ ስፍራ ነው። ለውጥ የሚጀምረው ከስራ፣ከትምህርት ፣ከአገልግሎት ሳይሆን ከአዕምሮ ነው።አዕምሮ በእግዚአብሔር ቃል ካልታደሰ የትኛውም የህይወት ክፍል እንደነበር ይቀጥላል።
➢ያልተለወጠ አዕምሮ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ አይችልም። የእግዚአብሔርን ቃል አለማወቅ ደግሞ የህይወት ምስቅልቅልና ጭለማ ውስጥ መኖር ነው።የአዕምሮ መታደስ የእድሜ ልክ የለውጥ ሂደት ነው።
➢የአስተሳሰብ ለውጥ አገልጋይ ስንሆን የሚያበቃ፣ድንቅና ተአምራት ስንሰራ የሚቆም የለውጥ ሂደት አይደለም።በየቀኑ በአዕምሮ መታደስ በመንፈሳዊ ህይወት ልቆ ለመኖር አስፈላጊ ነው።በአዕምሮ ስንታደስ ለእግዚአብሔር ስራ ምቹ እንሆናለን። አለበለዚያ የእግዚአብሔር አሰራር ተቃዋሚ ልንሆን እንችላለንን።
➢ስለዚህ በአዕምሮ ለመታደስ ትልቁ መሳርያ የእግዚአብሔር ቃል ነው። የእግዚአብሔር ቃል ህያውና የሚሰራ በመሆኑ በመንፈስ ስናነበውና ስናሰላስለው አስተሳሰባችን በቃሉ ይቃኛል። ይህ ሲሆን አዕምሮአችን ከእግዚአብሔር ቃል አንፃር ነገሮችን ማሰብ፣ማየት፣ ማመዛዘን፣ መወሰን ይጀምራል።
➢አናስተውል እግዚአብሔር በህይወታችን ያየልን ፍፃሜ ለውጥ ነው። ነገሮችን ሁሉ በቃሉ በተቃኘ አዕምሮ እንመልከት። በዚህ ጊዜ ህይወት ሌላ ትርጉም እንዳላት መረዳት እንጀምራለን። አሰልቺ፣ግራ አጋቢ ጉዳዮች ከህይወታችን ይቆረጣሉ።
በክርስትናችን ደስተኛ፣በተድላና በሰላም የተሞላ ህይወት ማጣጣም እንችላለን።
✍መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)
ክፍል 16 ይቀጥላል

♦አልቻልኩበትም♦
አልሆንልሽ አለኝ ዝምታ
አቅም'ም አጣሁ ለፀጥታ
ቸርነትህ በረታ ምህረትህም ገነነ
ስጦታህ በረከተብኝ ሆነ ያልተመጠነ
ሞላ ተትረፈረፈ የምቀበለው ከእጅህ
ስለሰጠኸኝ ያለልክ እንዳይቆጠር አድርገህ
የጠየኩህ ብዙ ነበረኝ እኔ ለእኔ ያሰብኩት
እፍኝ የማይሞላ ጥቂት ለቅርብ ቀኔ ያልኩት
ጩኸትም ልኬ ነበረ ወደ ማደሪያ ድንኳንህ
ቆይቼ ስጠናም ነበር እንዲከፈትልኝ ደጅህ
ሰማኸውም ጩኸቴን አደመጥከውም እዬዬን
ከአድማስ ያልተሻገረ ቅርብ ያደረ ልመናዬን
አባቴም ስለሆንክልኝ ስለምታውቀኝ ጠንቅቀህ
ውሃ ባያነሳም ጉዳዬ ሚዛን ባይደፋም በፊትህ
አልሳክብኝም ከቶውን አላልከኝምም ለዚሁ
እኔም ለኔ እንዳላውቅ ከምክር ቃልህ ተማርሁ
እንደምታውቅልኝ አንተ እንደሚበልጥም የአንተ
አወቀ ተረዳልኝ ልቤ ከልብህም ፍቅርን ሸመተ
እንድትሳሳልኝ በብርቱ እንድትራራልኝም በብዙ
እንዴትም እንደምትወደኝ ሳውቅ ሲበራልኝ ልኩ
ከድካሜ በሚልቅ ከስንፍናዬም በሚበልጥ
በእልፍ ም'ረትህ ስማር በይቅርታህ ስሰምጥ
ትከሻዬ እስካይችል ድረስ መሸከም እስከሚያቅተኝ
ባርኮትህ ዝም ብሎ ሲፈስስ ውለታህም ሲበዛብኝ
አልቻልኩበትም ዝምታ አልሆንልሽ አለኝ ፀጥታ
ሳይ'ገባኝ ስላደረከው ስላትረፈረፍከው ስጦታ
ለውድ አባቴ ለእግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታ
ባይመጥንህም ቃላቴ ባይደርስም ያንተን ከፍታ
ስላልቻልኩበት ፀጥታ ስላልሆነልኝ ዝምታ
ተመስገን ልበልህ እንጂ ምከፍልህ የለኝም ወሮታ
ተወደስ ልበልህ እንጂ ምሰጥህ የለኝም ወሮታ!!!
ምህረት ግርማ
💐SHARE💐SHARE💐SHARE💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
አልሆንልሽ አለኝ ዝምታ
አቅም'ም አጣሁ ለፀጥታ
ቸርነትህ በረታ ምህረትህም ገነነ
ስጦታህ በረከተብኝ ሆነ ያልተመጠነ
ሞላ ተትረፈረፈ የምቀበለው ከእጅህ
ስለሰጠኸኝ ያለልክ እንዳይቆጠር አድርገህ
የጠየኩህ ብዙ ነበረኝ እኔ ለእኔ ያሰብኩት
እፍኝ የማይሞላ ጥቂት ለቅርብ ቀኔ ያልኩት
ጩኸትም ልኬ ነበረ ወደ ማደሪያ ድንኳንህ
ቆይቼ ስጠናም ነበር እንዲከፈትልኝ ደጅህ
ሰማኸውም ጩኸቴን አደመጥከውም እዬዬን
ከአድማስ ያልተሻገረ ቅርብ ያደረ ልመናዬን
አባቴም ስለሆንክልኝ ስለምታውቀኝ ጠንቅቀህ
ውሃ ባያነሳም ጉዳዬ ሚዛን ባይደፋም በፊትህ
አልሳክብኝም ከቶውን አላልከኝምም ለዚሁ
እኔም ለኔ እንዳላውቅ ከምክር ቃልህ ተማርሁ
እንደምታውቅልኝ አንተ እንደሚበልጥም የአንተ
አወቀ ተረዳልኝ ልቤ ከልብህም ፍቅርን ሸመተ
እንድትሳሳልኝ በብርቱ እንድትራራልኝም በብዙ
እንዴትም እንደምትወደኝ ሳውቅ ሲበራልኝ ልኩ
ከድካሜ በሚልቅ ከስንፍናዬም በሚበልጥ
በእልፍ ም'ረትህ ስማር በይቅርታህ ስሰምጥ
ትከሻዬ እስካይችል ድረስ መሸከም እስከሚያቅተኝ
ባርኮትህ ዝም ብሎ ሲፈስስ ውለታህም ሲበዛብኝ
አልቻልኩበትም ዝምታ አልሆንልሽ አለኝ ፀጥታ
ሳይ'ገባኝ ስላደረከው ስላትረፈረፍከው ስጦታ
ለውድ አባቴ ለእግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታ
ባይመጥንህም ቃላቴ ባይደርስም ያንተን ከፍታ
ስላልቻልኩበት ፀጥታ ስላልሆነልኝ ዝምታ
ተመስገን ልበልህ እንጂ ምከፍልህ የለኝም ወሮታ
ተወደስ ልበልህ እንጂ ምሰጥህ የለኝም ወሮታ!!!
ምህረት ግርማ
💐SHARE💐SHARE💐SHARE💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል16
በክርስቶስ ኢየሱስ ያለ ስርአት
ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው። 1ጢሞ 3:15
ሐዋርያው ጳውሎስ በእግዚአብሔር ቤት ወይም እንደ ክርስትያን እንዴት መመላለስ እንደሚገባ የኤፌሶን ቤተክርስትያን ፓስተር ለነበረው ፓስተር ጢሞቲዎስ የፃፈውን ከላይ እንብበናል። ይህ በእግዚአብሔር ቤት ያለ ስነስርዓት የክርስትና ህይወት መገለጫ ነው።
ስነስርዓት ማለት "ብቁ ገጸ ባህሪን ወይም የባህሪ ዘይቤ ወይም የህይወት አካሄድ ነው።
ስነስርዓት የክርስቲያን ሕይወት ተፈጥሯዊ አካል ነው። በህይወታችን ውስጥ ምንም አይነት ትርጉም ያለው ነገር ያለ ስነስርዓት አይከናወንም።
➢የተለያዪ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ የስነስርአት አስፈላጊነት ሲወራ መንፈስን ማጥፋት ነው ብለው ያምናሉ፤ ስለዚህ እንደፈለጉ መሆን ደግሞ መንፈሳዊነትና በመንፈስ መነዳት እንደሆነ ሲናገሩ ይደመጣል።ስለዚህ ለእንደነዚህ አይነት ክርስትያኖች ስነስርዓት ያን ያክል አሳሳቢ ጉዳይ ስላልሆነ እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ:-
''ብቻ ቤ/ክ ውስጥ መንፈስ ካለ ህግ ምናምን አልሰማም'' ''የምን ማካበድ ነው??'' እያሉ መረን መውጣት፣
'''መንፈስቅዱስ በሰው ስርአት አይመራም' በሚል ሰበብ ቤ/ክ ላይ ማጉረምረም በትዕቢት መነፋት ፣
''እዛ ቸርች ስርአታቸው የኦሮቶዶክስ ያክል ነው'' እያሉ ስርአት አልባ መሆን፣
'' እዛ ቸርች ስርአታቸው የብሉይ ኪዳን ነው'' እያሉ ለቤ/ክ አሰራር አለመገዛተ፣
'''ክርስትና ፎርሙላ የለውም'' እያሉ ሊበራል መሆን እና ህይወትን እንደፈለጉ ለመኖር ሸነጥ የሚያደርጋቸው ጥቂት አይደሉም።
➢እንደ ክርስትያን ስነስርዓትን መገንባት እንድ ወታደር የውትድርናን ስርአት ለመገንባት የሚያደርገው ቆራጥነት ያስፈልጋል። አለማችን ላይ ከፍተኛ ስነስርዓት ከሚጠይቁ ሞያዎች አንዱ ውትድርና ነው።ይህ ሞያ የህይወት መስዋዕትነት ድረስ የሚያደርስና ከፍተኛ በሆነ ዲስፒሊን የሚገነባ ሞያ ነው። እንደ አማኝ ለስጋ ሞተን ለመንፈስ ህያዋን ሆነን ለመኖር ከስጋ ጋር የሞት ትንቅንቅ በማድረግ የመንፈስ ስርአትን በህይወታችን እና በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ልንገነባ ያስፈልጋል።እንደ አማኝ ሁላችንም ክርስቶስን አምኖ የእግዚአብሔር ልጅ በመሆን ደረጃ እኩል ነን። ነገር ግን የተሰራ እና ያልተሰራ ህይወት ሰፊ ልዩነት ይፈጥራል።ይህ ልዩነት በመጨረሻው ቀን የምንቀበለውን ሽልማትም ይወስናል። ምክንያቱም መዳን በፀጋ ቢሆንም ሽልማት ግን በመሰጠትና በክርስትያናዊ አኗኗር የሚመጣና የሚገኝ ነው።
➢ቤ/ክ ውስጥ የአምልኮ ስርአት፣የአነጋገር ስርአት ፣የአለባበስ ስርአት ፣የፀሎት ስርአት ፣ እና ሌሎችም አሰፈላጊ የሆኑ ስርአቶችን መገንባት መንፈስን ማጥፋት አይደለም። እግዚአብሔር ሁሉ ነገር በስርአት እንዲሆን የሚፈልግ አምላክ ነው ምክንያቱም የተተረማመሰ ነገር እናዝብርቅርቅ ያለ ነገር አይመቸውም።
➢እስቲ በምናባቹ አስቡት ሰማይ ቤት ያለውን ዲስፒሊን ??! እንዴት የተዋበ ይሆን?! እንዴት አስደናቂ ይሆን?!
➢ስነስርአት በሂደት የሚመጣ የተለወጠ አስተሳሰብ ውጤት ነው።በአንድ ሌሊት የሚመጣ ለውጥ ባይኖርም በአስተሳሰብ ለውጥ ይህን ስርአት መገንባት ይቻላል። (ቆላስ3፡9-10)።
➢ እንደ አማኝ በእግዚአብሔር ቤት ስንመላለስ አካሄዳችንን፣አምልኳችን፣ ፀሎቶቻን፣ቤ/ክ ለብሰን የምንመጣው አለባበስ ሳይቀር ፣አስተሳሰባችን፣ አነጋገራችንን ሁሉ የሚመዝን አምላክ ስላለ ለእሱ የሚገባውን ህይወት ለመኖር መትጋት አለብን።
➢የእግዚአብሔር ቤት እንደፈለግን የምንሆንበት ስርአት አልባ ቤት አይደለም።ቤቱ የእውነት አምድ እና የህያው እግዚአብሔር ቤ/ክ ነው።ቤቱ ባለቤት አለው?የቤቱ ባለቤት እግዚአብሔር የቤቱ ራስ ክርስቶስ ነው።
ክፍል17 ይቀጥላል

ክፍል 17
በክርስቶስ የሀሳብ ጦርነቶችን ማሸነፍ
የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። ኤፌ 6:17
ኃጢአትም ፅድቅም የሚጀምረው ከአስተሳሰብ ነው።ያላሰብነውን አናደርግም።ለምሳሌ አንድ ሰው ስርቆት ሲፈፅም መጀመርያ በሀሳቡ ይሰርቃል ከዛ ቀጥሎ በእጁ(በተግባር) ይሰርቃል።እያንዳንዳችን የሀሳባችን ተጠቂዎች ነን።ከሀሳባችን ማምለጥ አንችልም።ሀሳባችን እውነተኛው ማንነታችን ነው። የእግዚአብሔር ቃል በአስተሳሰብ እና በሀሳብ ስለመሻሻል ስለመለወጥ በተደጋጋሚ ያስተምረናል።ምክንያቱም እግዚአብሔርን የምን
መስለው በአስተሳሰባችን ነው። እንዲሁም መንፈሳዊ ውጊያዎችን ድል የምናደርገው በሀሳባችን ነው።
የሰው አዕምሮ የጦር ሜዳ ነው፤ሀሳብ ደግሞ የጦር መሳርያ ነው።
➢እንደ ክርስቲያን የተለያዩ አይነት ሀሳቦች ከሰይጣን እና ከስጋችን ወደ አዕምሯችን ሊወረወሩ ይችላሉ።አንድ ክርስትያን መቼም ቢሆን ከክፉ ሀሳብ ፍላፃ ነፃ ሊሆን አይችልም። ነፃ ሊሆን የሚችለው ወደ ጌታ ሲሄድ ብቻ ነው።
እዚህ ምድር ላይ እስካለን ድረስ የተለያዩ አይነት ክፉ ሀሳቦች ይወረወራሉ ነገር ግን በቃሉ ከመከትናቸው ይመክናሉ።
ወደ አዕምሯችን ክፉ ሀሳቦች መጡ ማለት እኛ ክፉ ነን ማለት አይደለም። ክፋቱ የሚጀምረው የመጣውን ክፉ ሀሳብ ማሰላሰል፣ደጋግሞ ማሰብ እና ለመጣው ሀሳብ አዎንታዊ ምላሽ የሰጠን ቀን ነው።
አንድ አማኝ እዚህ ምድር ላይ እያለ የሀሳብ ጦርነቶችን እየተዋጋ የተቀደሰውን ሀሳብ እየያዘ በድል እንዲኖር የእግዚአብሔር ቃል አስፈላጊ ነው።
➢ሰይጣን ጌታችንን በፈተነ ሰአት ሶስት የተለያዩ ሀሳቦችን አመጣበት፤ ነገር ግን ሶስቱንም የፈተና ሀሳቦች ያሸነፈው በሀሳቡ ሳይሆን በቃሉ ነበር። (ማቴ:4:1-5) ሰይጣን ወደኛ የሚወረውረውን ሀሳብ በእኛ ብልጠት ሳይሆን በቃሉ ብቻ ነው የምናሸንፈው። ምክንያቱም ሰይጣን ከእኛ በላይ ብልጥ ነው። የብዙ ሺህ አመት ልምድ እንዳለው መርሳት የለብንም። ለዲያብሎስ መምዘዝ ያለብን የቃሉን ሰይፍ እንጂ የራሳችንን ብቃት አይደለም።
➢ '''ከአናታችን በላይ የምትበረዋን ወፍ እንዳትበር መከልከል አትችልም፤ ነገር ግን ወፏ በአናትህ ላይ ጎጇዋን እንዳትቀልስ መከልከል ትችላለህ'' የሚል የቆየ አባባል አለ።
ሰይጣን፣ አለምና ስጋችን ወደኛ የሚወረውሩ ትን ሀሳብ ማስቆም አንችልም። ነገር ግን ሀሳባቸው አዕምሯችን ውስጥ እንዳይበቅል ማድረግ እንችላለን።
እግዚአብሔር እንድትሆኑ ኃይል ያላስታጠቃችሁን እንድትሆኑ አይጠይቃችሁም።
➢የሀሳብ ጦርነቶችን በድል ለመወጣት 3 መንፈሳዊ ምስጢራት አሉ :--
1- ቃሉ ( ኤፌ 6:17)
2- ፀሎት (ኤፌ 6:18)
3-የኢየሱስ ደም ራዕ 12:11
እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም። (ራዕ 12:11)
ክፍል 18 ይቀጥላል

ክፍል 18
በክርስቶስ በውስጥህ ያለውን የገደብ
ኃይል መሰባበር
BREAKING THE POWER OF INNER LIMITATIONS
የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለ ሽና፥ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና..(ኢሳ54:2)
➢የሰው ልጅ ሰው ሆኖ በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ ብቻ በውስጡ የተከማቸ በጎ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል ብቃት አለ።
ሰው በክርስቶስ አምኖ ሲድን ደግሞ ጌታ በውስጡ የሚያስቀምጠው ውድ የሆነ ስጦታ ፣ታለንት፣ራዕይ፣ የፀጋ ስጦታ እና የተለያዩ አይነት የመፍትሔ ሀሳቦች አሉ። እንደ አማኝ በዚህ ምድር ላይ ያለነው ለተልዕኮ ነው። ተልዕኳችንን ፈፅመን ለመሄድ ደግሞ በዚህ ምድር ላይ የምንጋፈጣቸው ተቀናቃኞች ኃይላት አሉ። ከእነሱ ውስጥ አንዱ የገደብ ኃይል ነው።
➢እንደ አማኝ ጌታ በውስጣችን ያስቀመጠው ን ብቃትና በጎ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም ልንነንቀው አይገባም።በእግዚአብሔር የተሰጠንን ማወቅ በራስ መተማመንን ከፍ ያደርጋል። ለራስህ ያለህ ግምት ከፍ ይላል።
በራስ መተማመን ማለት እግዚአብሔር አንተን በሚያይበት እይታ እራሰህን ማየትና እግዚአብሔር እንዳከበረህ እራስህን ማክበር ነው። እግዚአብሔር ላንተ ያለውን ፍቅርና አክብሮት ለራስህ እውቅና ልትሰጥ ይገባል ያኔ በውስጥህ ያለውን እንቁ ነገር አውቀህ ማውጣት ትጀምራለህ።
➢አዳማዊ ማንነት ገደብን ያስቀምጥብሀል፣
መንፈሳዊ ማንነትህ ግን ገደብን ሁሉ ይሰባብ ራል። አማኝ ስትሆን ወደ ተራ የሀይማኖት ቡድን አልተቀላቀልክም። የተቀላቀልከው ወደ አንበሶች መንጋ ነው። የመንጋው መሪ ደግሞ የይሁዳ አንበሳ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ለአንበሳ ዱር ውስጥ ያለው አራዊት ሁሉ ቁርስ፣ምሳና እራቱ ናቸው። አንበሳ የቱንም አራዊት አይፈራም።ሁሉንም የሚያየው ለመብልነት ብቻ ነው። ለዛ ነው የአራዊቶች ንጉስ የተባለው።ቃሉ ''ክፉ ሰው ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ነው።'' ይላል። ምሳሌ 28፥1
➢ ስለዚህ በዚህ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ላይ ቆመህ በውስጥህ ያለውን የገደብ አስተሳሰብ እና አላስፈላጊ ድንበር ስበረው።
''አንተ ኃጢአተኛ ነህ፣አትረባም፣አትጠቅምም፣ ተራ ሰው ነህ'' የሚል ድምፅ በውስጥህ ሲጮህ '' በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም'' ተብሎ ተፅፎልኛል ብለህ ለራስህ ንገረው።ሀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን አንደምትችል ለውሰጠኛው ሰው ንገረው።
በውስጥህ ያለውን የአትችልም መንፈስ
ለመስበር :-
1ኛ በክርስቶስ ማን እንደሆንህ ጠንቅቀህ እወቅ።(ከእግዚአብሔር ተወልደሀል፣የአለም ብርሀን፣የምድር ጨው ነህ)
2ኛ በክርስቶስ የተሰጠህን ብቃት(ፀጋ) እወቅ።
3ኛ በፀጋው ላይ ተማመን
4ኛ እለት እለት በአዕምሮ መታደስ ቁልፍ መሆኑን ተረዳ(ሮሜ12:2-3)
5ኛ የእግዚአብሔር መንግስት ጉዳይ ያሳስብህ
ክፍል 19 ይቀጥላል

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
New Album #Pastor_Endale
" እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል፡ ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።
በጌታ የተወደዳችሁ ቤተሰቦች ሰላም ይብዛላችሁ...
ከእኔ አቅምና ብርታ ሳይሆን ከእርሱ ምህረትና እርዳታ የተነሳ 23 ዝማሬዎችን የያዘው አልበም እነሆ ተጠናቀቀ
በሰማይ እና በምድር ክበር ለእርሱ ብቻ ይሁን🙌🙌ስለሆነም በ ሕዳር 21-2017 ቅዳሜ ከሰሃት ከ 8 ሰሃት ጀምሮ በአዲስ አበባ ቤተምህረት ቤ/ክ አምላካችንን ለቅድስናው መታሰቢያ እየዘመርን በማምለክ አልበሙን በይፋ እንለቃለን...አብራችሁን ጌታን ለማምለክ እንደ ጌታ ፈቃድ በዚያው እንገናኝ ያምላኬ መልካምነት ከፊታችሁ ይቅደም🙏🏾🙏🏾

Forwarded from KINGDOM MEDIA/Seifu Zerihun
"አስር የጣደች..."
አንዳንዴ የአበው አባባሎች ለሚሰማ ጆሮ ለሚያስተውል ልቦና ለሕይወት የሚጠቅም ስንቅ ሰንቀዋል ከነዚህ ቢሂሎች መካከል አንዱ "አስር የጣደች አንዱንም አታማስልም"ወይም ይሄንን የሚስለው "አስር የሚያባርር አንዱንም አይዝም " የሚል ነው። የብዙዎቻችን ችግር ሁሉንም ጉዳይ በአንድ ጀንበር ካልገደልን የምንል የማንችለውን የምንገጥም ተግባሮቻችንን በቅደም ተከተል እና በፕሮግራም የማንከውን ሰዎች መሆናችን ከትልልቅ ስኬቶች ላይ ካለመድረስ አለፎ ለተለያዩ ጨንቀቶች አጋልጦናል።
ያለን አቅም ችግሮቻችንን በአንድ ጀንበር እንድንፈታ የሚያስችለን አይደለም ስለዚህ የተወሰኑ እና ቅድሚ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ ግዴታ ነው። ያለዚያ ብዙ የምንጀምር አንዱንም የማናጠናቅቅ ብዙ የምንፎክር ግን ድል የማናደርግ እንሆናለን። አስር ድስት ጥደን ሁሉንም የምናሳርር ከመሆን አንዱን በትኩረት ሰርተን እጅ የሚያቆረጥም ወጥ መወጥወጡ የተሻለ ነው። ያለዚያ የምናሰበውን የማናደርግ ያሰብነውን ባለማድረጋችን የምንጨነቅ ብዙ ችግር ለመፍታት የምናስብ ነገር ግን ተጨማሪ ችግር የምናዋልድ እንሆናለን።
ወዳጄ ሆይ አንተ ግን ሁሉ ቦታ አትገኝ፤ ትኩረትህን መጥን፤ ሀይልህን አታባክን፤ ለድርጊትህ ከአላማ አንጻር ቅድመ ተከተል አኑር የጀመርከውን ነገር አድምተህ ስራ ይሄንን ብታደርግ ከጭንቀት እየራክ ለስኬት እየቀረብክ ትመጣለህ።
አገልጋይ ሰይፉ ዘሪሁን

ክፍል 19
በእምነት መመላለስ
መፅሐፍ ቅዱስ ስለ እምነት አስፈላጊነት እና በእምነት ድል ስላደረጉ ሰዎች እንዲሁም በእምነት ስለተደረጉ ታላላቅ ነገሮች ያስተምረ ናል።ክርስትና የእምነት ህይወት እንጂ የብል ሀት ውጤት አይደለም። እምነትን ከክርስትና ህይወት ነጥሎ ማየት አይቻልም።
➢ እምነት የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች እንደሚፈፀሙ እርግጠኛ መሆን እና የማይታየው ነገር እውን እንደሆነ መረዳት ነው።( ዕብ 11፥1)
➢መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ አባቶች የስኬት ምስጢር ብልጣብልጥነት ሳይሆን እምነት ነበር። አሁን ባለንበት በዚህ ዘመናዊ አለም ውስጥ ከእምነት በላይ ለዘመናዊነት የተለየ ግምት የሚሰጡ ጥቂቶች አይደሉም።
አንዳንዶች እምነት የማይሰራና ያልተረጋገጠ ( DISPROVEN BELIEF ) ነው በማለት የሚገልፁ ፕሮፌሰሮች ሊቃውንት አና ፈላስፋዎች እጅግ ብዙ ናቸው።
➢ነገር ግን አባቶቻችን በህይወታቸው፣ በጤንነታቸው፣ በትዳራቸው፣ በስራቸው፣ በራዕያቸው፣በአግልግሎታቸው እና በፈተናዎች ወቅት ምላሽ ይሰጡ የነበረው በእምነት ነበር።
እምነት በሰው ላብራቶሪ የሚረጋገጥ እና በሰው ረቂቅ ጥበብ የሚመረመር አይደለም።
--ድንግል በድንግልናዋ መፀነሷ በየትኛው ዶክተር ይመረመራል?!
-- የኤርትራ ባህር በእምነት ተከፈለ ብለን ስናምን የትኛውም የውሀ መሀንዲስ-መርምሮ ይደርስበታል ?!
--ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማይ ዐረገ ብለን ስናምን የትኛውም የፊዚክስ ሊቅ ሊተነትነው ይችላል?!
እምነት እጅግ አስፈላጊ ነው።
ምክንያቱም
1ኛ- ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም።
ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት። ዕብ 11፥6
2ኛ-ያለ እምነት የዚህን ዓለም ፈተናዎች ማሸነፍ አይቻልም።
ምክንያቱም ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ዓለምን የሚያሸንፈውም እምነታችን ነው።1ዮሐ5፥4
3ኛ-ያለ እምነት እንደ እውነተኛ አማኝ(ክርስቲያን)መመላለስ አይቻልም።
“ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሎ እንደ
ተጻፈው። ሮሜ 1፥17
➢ እግዚአብሔርን በማመን በእለት እለት ህይወትህ እንደ አሸናፊ ክርስትያን ለመመላለ ስ እምነትን መገንባት ያስፈልጋል።
እምነት ዘር ነው ማለትም የቃሉ ዘር። ይህ ዘር ይበቅላል፣ያድጋል፣ፍሬ ያፈራል። እምነትን ለመገንባት ፍርሀትን እና ጥርጣሬን ከሚፈጥሩ አሉታዊ ወሬዎችና ዜናዎች ጆሮህን መጠበቅ አለብህ። አለበለዚያ ፍርሀት የእምነትን ስፍራ ይዞ ግራ የገባው ክርስትያን ያደርግሀል።
እምነት በልብህ ውስጥ የሚመነጨው ቃሉን በመስማት ሲሆን እምነትህ ፀንቶ የሚቆየው ቃሉን እለት እለት በመስማት ስትፀና ነው።
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
ሮሜ:--10:17
✍መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
ክፍል 20 ይቀጥላል