ISLAMIC SCHOOL
12.5K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

          🍃  #ክፍል 🔟

#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal
      አይነጋ የለምና ነግቶ ወደ ክላስ ሄድኩ አሁንም ግን ከሀሳቤ ጨርሶ አልፀዳም፡፡ አሁን አሁን ኡስማንን ለማግኘት እየጓጓሁ ነው ዋትሳፖ እና telegram ለመግባት ዳታየን የማበራው ልክ እንደበፊቱ አሁንም እናወራለን ግን ስለ ትምህርት ስለ ውሎ ገጠመኝ እንጅ ስለ ግል ህይወታችን አውርተን አናውቅም፡፡
.......ኡስማን ክላስ የምገባበትን ረፍት የምሆንበትን ሰአት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ከዶርም ልጆች ጋር ተግባብተናል ከሁዳ ውጭ ሌሎቻችን ተከባብረን ተጋግዘን እየተማርን ነው ያች ከኔ በላይ ማን አለና እያለች ስታቅራራ የነበረችው ሁዳ ዛሬ በሁሉም ዘንድ ተንቃ ለንግግሯ አድማጭ ለጥያቄዋ መልስ የሚሰጣት አታለች እንደዛ ታስበረግጋት የነበረችው አስማረች እንካን ዛሬ ከመጤፍ እንካን አትቆጥራትም እንደውም ዛሬ ላይ በትችት አነጋገር "አንች ሁዳ የሚሉሽ ግን እሱን ቀሚሳችሁን ዝም ብለሽ ነው የለበሽው? ይሄው እንደነሱ አንድ ቀን እንካን ስትሰግጅ አይቸሽ አላውቅም ኧረ ወይ መከረራየ ማስመሰል ብቻ አርገሽ አስጠላሽኝ"" አለቻት፡፡

      አላህ በኛ ላይ ግዴታ ያደረገብንን ነገር በአግባብ መፈፀም ስንችል በአላህ ዘንድ ውዴታን እናገኛለን ልቦች ሁሉ በእጅ የሆነው ጌታችን ሰወችም እንዲወዱን በማድረግ ተወዳጅ እንሆናለን፡፡ ከዛ ተቃራኒ ከሆን ደግሞ ውርደት እንጅ ክብርን አናገኘም
...........በአስማረች ንግግር  ይህን ሀዲስ አስታወስኩ ""ወመን  ተሀወነ ቢሶላቲ  ወየኩኑ  ባጊደን ፊቁሉቢ ናስ""( በሶላቱ የታከተ ሰው በሰወች ዘንድ የተጠላ ይሆናል) የአላህን አማና ያልተዋጣን ሰው ለኔ ይሆነኛል ብሎ ማን ይቀበለዋል አምሳያው ቢሆን እንጅ ለመወደድ ለመመሳሰል ብለን የምናደርገው ነገር እንዳችም ትርፍ አያስገኘንም ውርደት ቢሆን እንጅ ለአላህ ብለን በኢህላስ ስራወችን ስንሰራ አላህ ወዶ ያስወድደናል እና ስለ ሰወች ይሉኝታ ሳይሆን በኢስላም ህግጋቶች እንኑር፡፡
 
     የግማሽ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና በመድረሱ ሁላችንም ጥናቱን ተያይዘንዋል፡፡ ለውጤ እኔን እራሴን አስገርሞኛል ያች ገና ደብተር ስትገልጥ እንቅልፏ የሚጥላት ኢማን ዛሬ ላይብረሪን መዋያ ማደሪያዋ መሆኑን ላየ ሰው ለማመን ይከብዳል 12ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ የቢዝነስ መምህራችን ጀማል "ለትምህርት ያልተፈጠረ የለም ለትምህርት ያልነቃ ቢሆን እንጅ" ያለውን ንግግሩን አስታወስኩ " አወ አልሀምዱሊላህ ዛሬ በአላህ ፈቃድ ነቅቻለሁ" ከትናን ዛሬ የተሻልኩ ሁኛለሁ ሰው የፃፈውን ከመፃፍ ይልቅ የምፅፈውን ማወቅ ጀምሬያለሁ በዚህም ደስተኛ ነኝ!!
        ፈተና በመድረሱ ሰበብ ከኡስማን ጋር እንደበፊቱ አንገናኝም፡፡ የማያነብ   ተማሪ አይኖርም ኩረጃ በዚህ ሰአት አይታሰብም ምክንያቱም ማን ጎበዝ ማን ሰነፍ ነው የሚለው የሚታወቀው ከሴሚስተር ውጤት በኃላ ነው አሁን ሁሉም ራሱን ይዞ ለመውጣት ግብግብ ላይ ነው ከፈተና ጎን ለጎን በፈተናው ቀን እንድናስገባ የ ICT መምህራችን አሳይመንት ሰጠን......... ኡስማን ያለኝን አስታወስኩ " የፈተና ወቅትን አስታከው የሚሰጡ አሳይመንት በአብዘሀኛው መልሰው ፈተና ላይ ይመጣሉ በዚህ ጊዜ አሳይመንቱን የሰራ ተማሪ መልሱን ያገኘዋል"" ብሎ የነገረኝን አስታወስኩ አሳይመንቱን መስራት አለብኝ ብየ አሰብኩ የሚያግዘኝ ሰው ግን ያስፈልገኛል፡፡
,,,,,,,,,,,በዚህ ጊዜ እኔ የ ኮምፒውተር ሳይንስ 3ኛ አመት ተማሪ አውቃለሁ ብላኝ ከነኢማ ጋር ወደ ዋናው ጊቢ ሄድን እና ነኢማ ለጓደኛዋ ደወለችላትና መታ አስተዋወቀችን  ኢላሀም ቆንጂየ ልጅ ነች ቶሎ ሰው ትለምዳለች ባህሪያችን ተመሳሰለና ከረጅም ጊዜ በፊት የምንተዋወቅ ይመስል ቶሎ ተላመድን በአንዴ ተዋደድን አሳይመንቱን ሰርታልን አስረድታን እኔና ነኢማ ስንመለስ ስለጥሩ ባህሪዋ ተማርኬ እያወራኃት ነኢማም ስለሷ ታወራኝ ጀመር
      " ኢልሀም የደሴ ከተማ ልጅ ናት በወሬ በወሬ መቼም ሴት ለሴት ከተገናኘ ወሬዉ መቼም ስለወንድ እና ስላለፈ ሒወት አይደል .....ኢልሀምም እንደዚህ አለችኝ.....መድረሳ አንድ ላይ ነው ቁርአን የቀራነው እኛ ቁርአን ስንቀራ ኪታብ የሚቀሩ የሚዋደዱ የማይለያዩ ጓደኛሞች ነበሩ ኡስማን፡ አንዋር፡ ከማል፡ አቡበከር እና ሙስጠፍ ይባላሉ ሁሌም አይለያዩም የትም ቦታ ላይ አንድ ላይ ናቸው በጣም ነው የሚያስቀኑት ፍቅራቸው ብላ ስትነግረኝ ስለጓደኝነታቸው ጥንካሬና ቆይታ ተረዳሁ አስከትላም
.........ታዳ ኢልሀም ኡስማን የሚባለውን አፍቅራ ብዙ ተሰቃይታለች እንደውም በረኪና ሁላ ጠጥታ ነበር አሁን መቸም እንደዚህ ሁና አይጨክንባትም ስንል ጭራሽ ራስሽን የመግደል ስልጣን ማን ላንች ሰጠሽ ብሎ የበለጠ ፊት ነሳት" እንዲህ እያለች ስታወራኝ በምሰማው ነገር ተደነባበርኩ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,," ኡስማን ማለት መነሀሪያ አካባቢ ኤልክትሮኒክስ መሸጫ ሱቅ ያለው?" ብየ ለማረጋገጥ ያህል ጠየካት " አወ እሱ ብዙ ሴቶች ይወዱታል እንዴት እስካሁን እንዳላገባ አላውቅም ቢፈልግ ግን እንካን አንድ አራትም አያጣም " ስትለኝ...... ከየት መጣ የማልለው የራስ ምታት ግጥም አድረጎ ያዘኝ ምንም መናገር አልፈለኩም ወይም አልቻልኩም......ደነገጥኩ

#part  1⃣1⃣
ይ...........ቀ
.......ጥ........ላ......ል

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
📚❤️📚 አንድ ፈረሰኛ  ወደ አንድ ከፍተኛ ተራራ ይጓዝ ነበር፡፡ ወደ ተራራው ወገብ ላይ ሲደርስ አንድ ምስኪንና አንድ እግሩ ሽባ የሆነ ሰው እንዳቅሙ ቋጥኙን እየቧጠጠ ለመውጣት ሲፍጨረጨር ያገኛል፡፡
ፈረሰኛው፤
"ወዳጄ፤ ይህን የሚያህል ተራራ እንዲህ ተንፏቀህ የሚገፋ አይደለም፡፡ ስለዚህ እንደምንም ፈረሴ ላይ ላውጣህና አፈናጥጬ ዳገቱ ጫፍ ላይ ላድርስህ?"
ሰውዬው፤
"አመሰግናለሁ ! ግን ሥጋቴ እንዳላጣብብህ ነው፡፡ ለማፈናጠጥ ይበቃል ብለህ ነውን?"

#ፈረሰኛው
"እንደምንም ተጣበን እንወጣዋለን እንጂ በዚህ ሁኔታ በፍፁም ጥዬህ ብሄድ ግፍ ይሆንብኛል፡፡ ሰው እንኳ ባይኖር ተራራውም ይታዘበኛል፡፡ ስለዚህ ና ውጣ ግዴለህም፡፡"
#ሰውዬው
"ፈጣሪ ምስክሬ ነው፤ ለእኔ የተላክ ውድ አዳኝ መልዐክ ነህ፡፡ አምላክ ውለታህን ይክፈልህ!"
#ፈረሰኛው ተሸክሞ ፈረሱ ላይ አስቀመጠውና ተራራውን ተያያዙት፡፡ ጥቂት እንደሄዱ ግን፤
ሰውዬው
"ወዳጄ፤ ቅድም እንደፈራሁት በጣም ተጣበናል፡፡ ብወርድልህ ይሻላል፡፡"
ፈረሰኛው፤
"እንደሱማ አይሆንም፡፡ ባይሆን የተወሰነውን ዳገት እኔ በእግሬ ልሞክረው፤ አንተ ፈረሱን ያዝ" አለውና ፈረሱን ሰጥቶት ወረደ፡፡ ሰውየው እየጋለበ ዳገቱን እየወጣ እየራቀ ሄደ፡፡

🍃🍃🍃ፈረሰኛው በእግሩ ዳገቱን ተያያዘው፡፡ ሆኖም ባለፈረሱ እየራቀ ሄደ፡፡ ፈረሰኛው ሥጋት እየገባው በተቻለው ፍጥነት ሊከተለውና ሊጠጋው ቢሞክርም ሰውዬው ፈረሱን ይብስ አፈጠነው፡፡
ፈረሰኛው መጣራት ጀመረ፡፡ ወይ የሚለው ግን አጣ፡፡ ሰውዬው ፈረሱን ይዞ ሊጠፋ መሆኑ ለፈረሰኛው ገባው፡፡

🤔“አንተ ሰው፤ ግዴለም ፈረሱን ይዘኸው ትሄዳለህ፡፡ ግን አንድ ነገር ቆም ብለህ ስማኝ እባክህ፡፡ እንደማልደርስብህ ታውቃለህ፡፡ ጆሮህን ብቻ አውሰኝ?” ሲል ለመነው፡፡
ሰውዬው ርቀቱን በደንብ ካረጋገጠ በኋላ፤
“እሺ ምንድነው ልትነግረኝ የፈለከው?”
ፈረሰኛውም፤

‼️‼️‼️“ወዳጄ፤ መቼም አንድ ቦታ ወርደህ ከሰው መቀላቀልህ አይቀርም፡፡ አደራህን ይሄን አሁን እኔን የሰራኸኝን ነገር ለማንም ሰው እንዳትነግር፡፡ አለበለዚያ ደግ የሚሰራ ሰው ይጠፋል!”

#ምንጭ:- "ታሪክና ምሳሌ" ከክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
|| በቅንነት ሼር በማድረግ አዳርሱ
ምንጭ ☞ /Dr.Mehrat.Debebe

⭐️«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»⭐️
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
⭐️«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::⭐️»
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ #ማን_ነዉ_ጥፋተኛ የሚለዉን ታሪክ ጨርሰናል ከታሪኩ ትኩረት ማረግ ያለብን አጭር ነጥቦች፡፡
ጥፋቱ ከእሷም ከእሱም አለ..ግን መጀመሪያ ጥፋቱ የእሷ እንደሆነ እኔ ይሰማኛል በእኔ አስተያየት እስኪ እሱ እንዲጨክን ያረገዉን እንይ
➡️መጀመሪያ ላይ የአክስትሽ ልጅ መሆኑን አዉቃ ማዉራት የለባትም ነበር፡፡ ለምን ፍቅር የት እንዴት መቼ ይይዘኛል ተብሎ የሚወሰን አይደለም ...
➡️እሷን ለመበቀል ቢያስብ አልሆንለት ሲል ..ግን ምንም የማያቁ ሴቶች የእሱ ሰለባ ሆኑ ማለት ነዉ..መጀመሪያ ላይ እሷ ባታጀዝበዉ ፍቅር ባታሲዘዉ ኑሮ በእሷ የተነሳ  አሁን ድረስ ብዙ ሙስሊም እህቶች ሂወት እየተበላሸ ነዉ..እኛ ያቃተን የአሁኑን ሳይሆን ለወደፊት ምን ይፈጠራል ብሎ ማሰብ ነዉ፡፡
➡️ታሪኩ ላይ በክርስቲያን ጓደኛዋ ጋር ብዙ ወንዶች እንደምታጀዝብ እንደምጀነጅን ተናግራለች ..ታዳ በዚህ ሰለባ የሆነ ወንድ ልጅ ለሴት ልጅ ክብር ይኖረዋል ወይ ??? ሴቶች እባካችሁ ግን የምታወሩበትን ምክንያት ታቃላችሁ??
    >ዚና ለመስራት ነዉ ??
    >ወይስ መደበሪያ ነዉ ??
    >ወይስ ካርድ ለማስላክ ነዉ ??
    >ወይስ በፍቅር አጥምጄ ያገባኛል ነዉ ??
ጭራሽ እኮ ምን እንደምታስቡ ግራ ነዉ የሚያጋባዉ..ወንድን አዉርተሽ ጀንጅነሽ ምን ትጠቀሚያለሽ ?? ስለሆነም ሴቶች እባካችሁ በቀኝ ጆሯችሁ አዳምጣችሁ በግራ ጆሯችሁ አታፍሱት..አንቺ እኮ ትምህርት ቤት ነሽ እናትሽ ተንከባክባ ያሳደገችሽ እኮ አንቺም እናትነትን እንደምትሆኝ ስለምታቅ ነዉ፡፡ ለወደፊት በአንቺ መሀፀን የወጣዉ እኮ የዲኑ ጠባቂ ..ሀፊዘል ቁርአን.. ፕሬዝዳንት..ሊሆን ይችላል ታዳ አንቺ የወንድ ስሜት ማብረጃ ሁነሽ የምታስቢዉ ጊዜያዊ ስሜትሽን እየተከተልሽ የማንም ወንድ መደበሪያ ሳይደዉልልሽ አንቺዉ ናፈከኝ የት ነህ ብለሽ ሂደሽ የእሱ ስሜት ማብረጃ ሁነሽ እንዴት አንቺ ልጅ ወልደሽ ማሳደግ ትችያለሽ ?? የእናትሽን ህልም አበላሸሽ ማለት ነዉ..እናትሽ ተንከባክባ አሳድጋሽ ብዙ ህልም እያላት አንቺ ተደብቀሽ የርካሽ ስራ ትሰሪያለሽ ..በራስሽ ጊዜ ለቅራጫ የቀረበ በሬ ይመስል የማንም ተራ ወንድ ስሜት ማብረጃ ሳይሆን..ወንዶችን አንገታቸዉን የምታስደፊ መሆን አለብሽ፡፡
➡️አሁን ዘመን ላይ አጎቴ ነዉ የአጎቴ ልጅ ነዉ .የአክስቴ ልጅ ነዉ ምንም አይፈጠርም ..ልጁ አንገት ደፊ ነዉ ሚስኪን ነዉ ምንም አያረገኝ ማለት አይቻልም ለምን ስሜት ነዉ ምን እንደሚፈጠር አናቅም ቡሀላ ከመለደም ከማልቀስ መጀመሪያ መጠንቀቅ ነዉ የሚሻለዉ፡፡ ብታለቅሺ አልቅሰሽ ትቀሪያለሽ፡፡
ግን እህቴ ሴት ልጅ ብዙ ነገሮችን ተቋቁማ ወደ ትዳር አለም ትገባለች ያንን እንዴት ነዉ ፈተናዉን ማለፍ ያለብሽ ..ሴቶች ተማሪዎች አብረሽ መደበኛ ትምህርት ስትማሪ ሁሉምንም ትምህርት ሂሳብ እንግሊዝ አማረኛ civics ወ.ዘ.ተ ዉጤትሽ ጥሩ ሊሆን ይችላል ግን ከትምህርት ዉጤትሽ በላይ የአንቺ የሂወት ዉጤትሽ ጓደኞችሽ ሲሆኑ  የጓደኞችሽ ግፊት አንቺን ወደ ማፈልጊዉ አለም ትገቢያለሽ ...ስምንት ማትሪክ ስትፈተኝ ጥሩ ዉጤት አመጣሽ ወደ ዘጠኝ አለፍሽ ከዛስ አስርም አለ ማትሪክን ስትወስጅ ከዘጠኝ እና ከአስረኛ ክፍል ከበፊቱ ምን ለዉጥ አለኝ ቂርአት ላይ ጥሩ ነኝ ወይስ መጥፎ የሴት ጓደኞች አሉኝ ወይስ በሀራም ከወንድ ጋር እንደ አባይ ግድብ የማይጨረስ ፍቅር ጀምሪያለሁ ወይ ወ.ዘ.ተ ??? የሚለዉን አንቺ እራስሽ ለራስሽ ጥያቄዉን አቅርበሽ መመለስ አለብሽ

ከዛስ ማትሪክ ተፈተንኩ ትምህርቴን ካለፍኩኝ 11 ክፍል ስገባ አላማየ ምን መሆን አለበት ከ10 ብወድቅስ ? በDiploma የግል ኮሌጅ እገባለሁ እዛ ላይ እኔ ዲኔንም ቢክራየንም ጠብቄ የወደፊት ባሌን እንዴት ነዉ ማግኘት የምችለዉ ብለሽ ማሰብ ይኖርብሻል፡፡

እህቶቼ አራት አመት ፈተናዉን ማለፍ መታገስ ከቻላችሁ የወደፊት የእናንተ ከአላህ ጋር የአርባ አመት ፕላናችሁ መስተካከል ይችላል ፡፡ ግን አራት አመት ላይ ግን የምትሸወዱ ከሆነ በሀራም ከአጂ ነቢ ጋር ግንኙነት ከጀመራችሁ ለአንድቀን ለዛዉም 20 ደቂቃ ለማይሞላ ስሜት የ40 አመታት ፕላናችሁን ታበላሻላችሁ ማለት ነዉ፡፡ እነዚህ አራት አመታት እነማን ናቸዉ ካልን ከዘጠነኛ ክፍል እስከ 12 ክፍል ያሉትን አመታት ፋየር ኤጅ ሁሉም አለሁ አለሁ ከሰዉ በላይ ነኝ የሚባልበት እድሜ ነዉ ስለሆነም እነዚህ የትምህርት አመታት የወደፊት ሂወታችሁ ወሳኝ ናቸዉ፡፡ University በምገቡበት ጊዜ እናንተ የአራት አመቱ ምርት ዉጤት ናችሁ አራት አመቱን በመጃጃል ያሳለፍሽ ከሆነ university ከቤተሰብ ቁጥጥር ዉጭ ነሽ ለቤተሰብም ለሀገርም ለአንቺም አጠቅሚ ትበላሻለሽ ወንዱ ግን ተጠቃሚ ነዉ ሀራምም ቢሆን ስሜቱን ያበርድብሻል ሊያገባ ሲፈልግ የቤት ልጇን ቢክራዋን ፈልጎ ያገባል፡፡ ግን አራት አመታቱን ጥሩ ስነምግባር ካለሽ university ገብተሽ ዲንሽንም ቢክራሽን ዲግሪሽን ይዘሽ ትወጫለሽ አንቺን ለማግባት ትምህርት እስከ ምጨሪሺ ሲጠብቁ የነበሩ ወንዶችuniversity በነበርሽበት ሰአት ሲከታተሉሽ ነበር እና ለትዳር በሰልፍ ይመጣሉ
አንቺም በመስሪያ ቤት ገብተሽ የሙስሊም ሴቶች አርአያ ሁነሽ አላህን በመፍራት የአገር አለኝታ ሆንሽ ማለት ነዉ፡፡

➡️ወንድ እና ሴት ሁኖ አንድ ላይ ተቀምጠዉ ወይ እየሄዱ እኔ ወንጀል አልሰራም እጠነቀቃለሁ ማለት ቤንዚን ወይም ነጭ ጋዝ ላይ እሳት ተጥሎበት አይነድም ብሎ እንደማሰብ ይቆጠራል፡፡ስለሆነም እኔ እሱ ጋር ሁኜ ስሜቴን እጠነቀቃለሁ ማለት አይቻልም 44 ነጥብ👌
 
➡️አሁን ላይ ሴቶች ከትንሽ ከተማ ከወረዳ ወደ ትልቅ ከተማ መጥተዉ ከ10 ወይ ከ 12 ክፍል ወድቀዉ በግል ወይ በመንግስት ወደ ትልቅ ከተማ ማለትም አዲስ አበባ....ደሴ...ጎንደር...ባህርዳር...ድሬድዋ ወ.ዘ.ተ በግል ትምህርት ለመከታተል በdiploma ለመማር ከተለያዩ ከተሞች ይመጣሉ ፡፡ ግን የመጡበትን አላማ ይረሳሉ ፡፡ ወደ እነዚህ ትልቅ ከተሞች ሲመጡ ቤት ይከራያሉ 3 ሴቶች አንድ ቤት ወንዶቹም እነደዚሁ ይከራያሉ፡፡ ያለዉ ማህበረሰብ ለመመሰል ፋሽን ተከታይ መሆን የወንድ ጓደኛ ለመያዝ ወንዱም ፑል ቤት መግባት .ፀጉሩን መፍተል..ሴት መጀንጀን የከተማ ልጅ ያስብላል ብለዉ ያስባሉ፡፡ የተከራዩበት ቤት ከመኖሪያ አልፎ የዚና መስሪያ ቤት እየሆነ የምናስተዉለዉ ነዉ፡፡ ግን ቤተሰቦችሽ በወር ትማርያለሽ ብለዉ በወር የትምህርት እየከፈሉ..የምግብ ወጭ የቤት ኪራይ ከፍለዉ ሴቶች እህቶቻችን በሀራም መንገድ ወንድ ጋር ሲጃጃሉ እያየን ነዉ፡፡ግን እስከ መቼ የከተማ ልጅ ማለት ፋሽን ተከትሎ ጊዜዉ ነዉ እያለ የትም የሚተኛ ነዉ ማለት ነዉ ??
አንድ ተማሪ ተምራ ከተማ ላይ ተወልዳ ግን ፋሽን እየተከተለች ሲትጃጃል ኑራ ከዛ ትምህርቷን ተመረቀች ስራ ያገኘችዉ ግን ገጠር ዉስጥ ነዉ እንበል...አንዲት የገጠር ልጅ ተምራ በዲን ተኮትኩታ አድጋ ዩኒቨርስቲም የገባችበትን አላማ ሳትረሳ ተመረቀች ስራ የተቀጠረችዉ ግን ከገጠር ወጥታ ትልቅ ከተማ ላይ ነዉ፡፡ አሁን የከተማዉ ልጅ ማንናት ከከተማ ገጠር የገባችዉ ናት ወይስ ከገጠር ወደ ከተማ የገባችዉ፡፡ የከተማ ልጅ ተብሎ የዜግነት ሲከፈል አላየንም መንግስት የተወልድክበትን ቦታ ለህንፃ መስራት ሲፈልገዉ እትብትህን በግሬደር ቆፍሮ በሲኖትራክ ጭኖ የትም ይደፈዋል፡፡ ስለሆነም የከተማ ልጅ ማለት በአስተሳሰቡ በስሎ የጊዜያዊ ስሜት ተከታይ ሳይሆን ዛሬ ሁኖ የወደፊቱን ሂወት ፕላን ማዉጣት ሲችል ነዉ፡፡👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👆👆ሁላችሁም አንብባችሁ አስተያየት ስጡ Forward አርጌ ለባለታሪኳ እደርሳለሁ፡፡ ወይም እሷን መርዳት ማናገር የምፈልጉ ሴቶች እህትች ብቻ የinbox አድራሻዋን ከፈለጋችሁ እሰጣችሇለሁ፡፡ በbot ጠይቁኝ
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

          ✔️  #ክፍል 1⃣1⃣

#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal
         ከተመለስን በኃላ ለብቻ ሁኘ ብዙ ማሰብ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ ለኡስማን ምን አይነት ስሜት ነው ያለኝ? ለምን እሱ ጋር ሳወራ ደስተኛ እሆናለሁ? ለምንስ ካላገኘሁት ይከፍኛል ይናፍቀኛ? ብየ የጥያቄ ጋጋታ  አቅርቤ ራሴን  በራሴ ጠየኩ የውስጤ ምላሽ ግን ኡስማንን እንደወደድኩት አስገነዘበኝ፡፡ እሽ ኡስማንስ ለኔ ምን አይነት ስሜት አለው ብየ ጥያቄየን አከልኩ የተፃፃፍናቸውን ሜሴጅ ገብቸ ማንበብ ጀመርኩ ያኔ " ገና እንዴት ነሽ ኢሙ" ብሎ ሲለኝ ለኔ ትልቅ የደስታ ስሜት ይፈጥርልኝ የነበረው ሜሴጅ ዛሬ ትርጉም አልሰጥሽ አለኝ አንዴ

        ሁሉም ምክር ነበር ለካ ፍቅር ፍቅር የሚሸቶ አንድ ቃል እንካን አጣሁ  " አይዞሽ በርች እንዳትታለይ መማር አለብሽ" በቃ ይሄ ቃል በብዛት ተደጋግሟል ግን አንድ እንካን እወድሻለሁ የሚል ቃል የለም በጣም አዘንኩ የተሸናፊነት ስሜት ተሰማኝ ሳላስበው ኡስማን ተቆጣጥሮ አሸንፎ እጅ አሰጥቶኛል፡፡ ........እንዴት ይሄን ያህል ብቻየን ርቄ ተጓዝኩ በሱ ፍቅር? ለምን በርግጥ ኡስማንን ማንም ሴት ባሏ እንዲሆን የምትመኘው አይነት ወንድ ነው በሱ ለፍቅር መውደቅ አያስገርምም ስለወደድኩት የተሸናፊነት ስሜት ተሰማኝ እንባየ ከአይኔ ፈሰሰ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ተረጋግቸ ማሰብ አቃተኝ
..............እስከዚህ ሰአት ድረስ በፍቅሩ መውደቄን አላወኩም ከሱ ጋር ደስተኛ እንደሆንኩ እንጅ ዛሬ ስለ ኢልሀም የሰማሁት ነገር ወደራሴ መልሶ ሀሳቤን ሰረቀኝ፡፡
ኢልሀም እዚህ ቀረሽ የማትባል ቆንጆ የወንዶችን ልብ በቀላሉ ልትቆጣጠር የምትችል ሁሉም የራሱ ለማድረግ የሚቆምጥላት እንስት ነች፡፡ የኡስማን ልብ በሷ ሳይሸነፍ በኔ ይሸነፍል ማለት እንደ ዘበት ሆኖ ታየኝ፡፡ መረጋጋት አቃተኝ ኡስማን ሀሳቤን ሠርቆ ሁለተኛ ከባድ ፈተና ሆነብኝ ዛሬ ሶስተኛ ቀናችን ከኡስማን ጋር ካወራን ድንገት አንድ ሀሳብ መጣልኝ ለምን ደውየ አልነግረውም ብየ ስልኬን አነሳሁ ግን
..............ከምን ጀምሬ ምን እንምለው ሳስብ ፍርሀት ወረረኝ አፌ ሲኮላተፍ ለራሴ ታወቀኝ ይቅርብኝ ብየ ያነሳሁት ስልክ ላስቀምጥ ስል ስልኬ ጠራ ኡስማን ነበር ሁኔታየን በቅርብ ሆኖ ያየኝ እስኪመስለኝ ድረስ ደነገጥኩ የልቤ ምት ፈጠነ ትንፋሼ ሲቆራረጥ ለራሴ ያስታውቀኛል ስፈራ ስቸር ስልኩን አንስቸ ወደ ጆሮየ አስጠጋሁ በለሰለሰ ድምፅ " አሰላሙአለይኪ ኢሙ" ድምፅን ስሰማ ልቤ በአፌ ልትወጣ መሰለኝ  ቃል ማውጣት ከብዶኝ " ወአለይኩምሰላም ኡስሚ ደህና ነህ" አልኩት  ናፍቆት ባደከመው ድምፅ እንባ እየተናነቀኝ
........" ኢሙ ድምፅሽ ልክ አይደለም ምነው ችግር አለ?""
......." አረ ምንም የለም ያው ፈተና ደርሶ የለ ንባብ አድክሞኝ ነው"
........." አወ ፈተና እንደደረሰ አውቃለሁ ይቅር በይኝ አላስችል ብሎኝ ነው ስትናፍቂኝ አንድ ደቂቃ እንካን ድምፅሽን ልስማ ብየ ነው" ይሄን ሲለኝ ከየት መጣ ሳልለው ጉሮሮ ላይ ሳግ ተሰንቅሮ ቃላት እንዳላወጣ ከለከለኝ፡፡ ዝምታየ በዝቶ ያስጨነቀው
.......ኡስማኔ "ኢሙ የት ሄድሽ አይሰማም" ይላል
.......እንደምንም ብየ " ይሄን ያህል ለምን ናፈኩህ?" ብየ ጠየኩት....... እእእ ብሎ ለሰከንዶች ያህል ዝም አለ "ኢማኔ ውሳኔሽ ምንም ይሁን ምን አከብራለሁ በምነግርሽ ነገርም እንዳትቀየሚ ምናልባት አንች እኔን እንደወንድምሽ አይተሽ ይሆናል የቀረብሽኝ ብቻ ብዙ ማውራት ብፈልግ እንካን አልችልም አፍቃሪ ተብታባ ነው ይባል የለ" ይሄን ስሰማ "እእእእ" የሚል ድምፅ አሰማሁ
" ኢማኔ ለአንች ያለኝን ስሜት እንዴት መግለፅ እንዳለብኝ  እንካን አላውቅም በቃ አንችን እንደወደድኩሽ እና የወደፊት የሂወት አጋሬ እንድትሆኝ እንደምፈልግ እወቂ" ንግግሩን ጠጠር አጠር አድርጎ ጨረሰ፡፡
......ከደቂቃወች በፊት በፍቅሩ እንደተሸነፍኩ ገብቶኝ የማደርገው ግራ ገብቶኝ በሀሳብ የታመምኩመት ኡስማን ስሜቴ ስሜቱ ሆኖ ይሄን ዜና ሲያበስረኝ አፌ ቃል ከማውጣቱ ቀድሞ አይኔ የደስታ እንባ ማንባት ጀመረ ለቅሶየን ማቆም አልቻልኩም ደስታየ ልቤን አፍኖ አስጨነቀኝ የለቅሶ ድምፅ ሲሰማ ኡስማን ደነገጠ የሚናገረው አጣ አፍ ተንተባትቦ "አስቀየምኩሽ አይደል" አለ ሀዘን በተቀላቀለበት ድምፅ አሁንም ሞከርኩ ግን ጉሮሮየ ታፍኗል
,,,,,,,,,,,,,,ከዚህ በላይ ላሳዝነው አልፈለኩም ስልኩን ዘጋሁት እና " ኡስማኔ በአንተ መመረጤ እድለኝነት ነው ጥያቄህን በደስታ ተቀብያለሁ ደስታ አስክሮኝ ልሳኔን ተዘጋ ለዛ ነው ስልክ የዘጋሁት እወድሀለሁ አንተን ለኔ ላደረገህ አላህ ምስጋና ይገባው" ብየ የፅሁፍ መልእክት ላኩለትና በጀርባየ ተዘርሬ.....

#part 1⃣2⃣
ይ.......ቀ......
.....ጥ........ላ...................ል

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
👍1
የቶማስ ኤዲሰን እናት! ለልጇ ያበረከትችዉ ወሳኝ ነገር ሁላችንም ለልጆች አስተዳደግ ቤተሰብ ወሳኝ ነዉ👇👇
#የቶማስ_ኤዲሰን_እናት!
ተዛማጅ ትርጉም።

⭐️ታዳጊው ቶማስ ኤዲሰን ከዕለታት አንድ ቀን ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲሄድ አንድ ወረቀት ለእናቱ ሰጣት።
''እማዬ መምህራችን ይህን ወረቀት ሰጠኝና ለእናትህ ብቻ ስጣት አለኝ'' አላት።
እናቱም ደብዳቤውን አንብባ በፍርሃት ተሸብባ፤ ዕንባ 😢😢በዓይኖችዋ ዙሪያ ግጥም አለ።
ነገርግን ድምጽዋን ከፍ አድርጋ ለልጅዋ ደብዳቤውን አነበችለት።

📌''ልጅሽ የሚገርም ክህሎት ያለው ብልህ ልጅ ነው። አሁን የሚማርበት ትምህርት ቤት ለእሱ በጭራሽ አይመጥነውም ያንሰዋል። የተሻሉ ጎበዝ መምህራን ያሉበት ትምህርት ቤት ቢገባ ይሻለዋል። ምክንያቱም እሱን የሚመጥነው ትምህርት ማግኝት ስለማይችል እባክሽ እራስሽ ልጅሽን ቤት ውስጥ አስተምሪው...!'' ይላል አለችው።

#እናቱ ከሞተች ከብዙ ዓመታት በኋላ ቶማስ ኤዲሰን በአሜሪካ ታላቁ የክፈለ ዘመኑ የፈጠራ ሰው ሆነ። ከእለታት አንድ ቀን የድሮ የቤተሰቡን ቁምሳጥን ሲከፍተው አንድ ተጣጥፎ የተቀመጠ ደብዳቤ አገኘ። ከፍቶ ሲያየው መምህሩ ልጅ እያለ ለእናቱ ብቻ እንዲሰጥ ያዘዘው ደብዳቤ ነበር።
ወዲያውኑ ደብዳቤውን ከፍቶ ማንበብ ጀመረ '' #ልጅሽ_የዓእምሮ_በሽተኛ_ነው። ለማንኛውም እዚህ ትምህርት ቤት እንዲማር አንፈቅድለትም። ስለዚህ ካሁን በኋላ ከትምህርት ቤቱ ተሰናብቷል።'' ይላል መልእክቱ።

✔️ቶማስ ኤዲሰን በስሜት ተመስጦ ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ በኋላ የግል ማስታወሻ ደብተሩ ላይ እንዲህ ብሎ አሰፈረ።
''ቶማስ አልቫ ኤዲሰን የዓእምሮ ህመምተኛ ታዳጊ ሕጻን ነበር። እናቱ ግን የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ሊቅ እንዲሆን አስቻለችው።''

📌ግብረገብ - የእናቶች ፍቅርና ማበረታታት ለልጆች መጻኢ ስኬታማ ሕይወት መሰረት ነው። በተፈጥሮዋቸው በተለይ እናቶች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸው ቅርበታቸው ከፍተኛ ነውና ሕጻናትን በሞራል በመደገፍ ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለአገራቸው እና ለዓለም የሚበጅ ስራዎችን ትተው የሚያልፍ ፍሬዎች እንዲሆኑ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው።

አትችልም፣ አትሞክሪ፣ የኔ ልጅ እኮ አይሆንለትም ወዘተ... መሰል ሞራል ገዳይ አሉታዊ ስሜት ንግግሮች ከማድረግ ይታቀቡ። በአንፃሩ ልጆችን ስሜታቸውን መረዳት፣ በእንክብካቤ መያዝ፣ ሳይታክቱ ምላሽ መስጠት፣ ትኩረት ሰጥቶ ማዳመጥ ይገባል።
ስወዳችሁ በብዛት!😍

😘😘 #ክብር ለእናቶች ሁሉ ይሁን!

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
ም/ጠ/ሚ ዶ/ር ደመቀ መኮንን ይናገሩታል. . .
#ዛሬ የኢሕአዴግ ምክር ቤትን ያንቀጠቀጠ ንግግር!!!

የአማራን_ህዝብ_ስነልቦና_በትክክል_የወከለ_መሪ!!!

'እኔ የምጨነቀው!' አሉ ጀግናው ሰው. . .

ዛሬም እኔ የምጨነቀው በኔ ዘመን ለመፍረስ እየሮጠች ስላለች ሀገር ነው!!!

ከዛም ቀጠሉ...

አንዳንዶች ለብሔራቸው ሲሮጡ እኛ ደግሞ ለኢትዮጵያ ስንሮጥ እነሱ እኛን ያሸነፉን ይመስላቸዋል። ነገር ግን መታወቅ ያለበት ትልቅ ጉዳይ፣ በዚህ የማይረባ ጨዋታ ማንም ማንንም አያሸንፍም!!!

በዚህ አላበቁሙም ስለ ወከላቸው የአማራ ህዝብ የሞራል ልእልናም እንዲህ አሉን. . .

የትኛውም ብሔር ጥቅምና ዝና እንደሚፈልግ ሁሉ፣ የኔም ብሔር ይሄንኑ ይፈልጋል ነገር ግን ከሌሎች የተለየ ተጠቃሚ እንሁን የሚል ብሔር አይደለም!!!

እኛን ወክሎ እዚህ ያደረሰን፤ አብረን እንጠቀም! አብረን እንኑር! ተከባብረን ተዋደን ያገኘናትን ቁራሽ አብረን እንብላ የሚል ሕዝብ ነው!!!

ም/ጠ/ሚ ዶ/ር ደመቀ መኮንን
10-08-2011
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

            #ክፍል 1⃣2⃣

#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal

       የደስታ እንባ አነባሁ ከኡስማኔ ጋር ስለሚኖረኝ የወደፊት ህይወት እያሰብኩ በደስታ ማእበል ሰምጨ ጠፋሁ ከገባሁበት ደስ የሚል ሰመመን የኡስማን የስልክ ጥሪ አባነነኝ ስልኩን በፍጥነት አነሳሁት በደስታ ብዛት እንደኔ ሰክሮ "የኔ ንግስት ደስታየን በቃል ልገልፀው አልችልም አንች ልዩ ስጦታየ ነሽ ሁሌም የምሳሳልሽ የምኖርልኝ ህይወቴን ትርጉም ሰተሽ ደስታየን የምታበዠልኝ ሁለንተናየ የኔ የምልሽ ንግስቴ አንች ነሽ በዚህም ደስታየ ወደር የለውም" ሲለኝ ልቤ በሀሴት ተሞልታ ጮቤ ስትረግጥ ይሰማኛል
..........ለኡስማን የትኛውንም የፍቅር ቃል ብጠቀም ስሜቴን አይገልፀውም ከቃል በላይ እምቅ የሆነው ፍቅሩ ልቤን ያሞቀዋል ኡስማን ሁሉ ነገሬ ሆኗል ስለዚህ "አለሜ" ብየ እጠራዋለሁ፡፡
.......አሁን  ህይወት ከሌላው ጊዜ በበለጠ ታጓጓኛለች አለሜ ብርታት ሆኖኛል ለሱ ብየ እበረታለሁ ለካ የኔ የምንለው ሰው ሲኖር ህይወት ትርጉሟ ይቀየራል ደስታኛ ነኝ አብረን የምንኖርበትን ቀን በጉጉት አጠብቃለሁ የአለሜ ኩራቱ ለመሆን ቆርጨ ተነሳሁ ፈተና ደርሷል የማንበብ ፍላጎቴ ከፍ ብሏል ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የአለሜን ደስታ ማየት ህልሜ ሆነ ሳልታክት ንባቤን ተያያዝኩት አልደክም አልሰለችም፡፡
       ፈተና እንደጨረስኩ የእረፍት ጊዜየን አዲስአበባ ከሀዩ እና ነቢያት ጋር ለማሳለፍ ቀድመን ተነጋግረናል አሁን ግን ልቤ ለሁለት ተከፈለ ወደ ኮምቦልቻ ሂጀ አለሜን ማግኘት ፈለኩ ግን ደግሞ ቀድሜ ለጓደኞቸ ቃል ገብቻለሁ ሀሳቤ ለሁለት ተከፈለ፡፡ ዛሬ ፈተና የመጨረሻ ቀን ነው ከዚህ በሆላ አንድ ቀን እንካን ጊቢ ማደር አልፈልግም ደግሞ የት ወዴት መሄድ እንዳለብኝ አልወሰንኩም ፈተናም አለቀ ነቢ 10 ሰአት ላይ ደወለችልኝ
....." ማሬ ልንገናኝኮ ዛሬ ብቻ ቀረን ወላሂ እንዴት እንደናፈቅሽኝ" አለችኝ
.......እኔም በጣም ናፍቃኛለች ግን በዚህ ሰአት ከአለሜ በፊት ቅድሚያ የምሰጠው ማንም የለም ጨነቀኝ "ኢንሻአላህ እንገናኛለን የኔውድ እኔም ንፍቅቆቅ ብለሽኛልኮ ደግሞ ሁሌም እንደምወድሽ እንዳትረሽ እሽ" አልኩኝ ቃሌን ሳጥፍ እንዳትቀየመኝ በመስጋትም ጭምር ነበር ንግግሬ ከነቢ ጋር ንግግሬን ጨርሸ ስልኩን እንደዘጋሁ አስከትሎ አለሜ ደወለ ሰላምታ ከበለዋወጥን በኃላ
....... " ሀቢብቲ ከነገወዲያ ትመጫለሽ አይደል" አለኝ
......" ኢንሻአላህ አስቢያለሁ"
......." እሽ የኔ ንግስት በሰላም ነይልኝ  አዲስ አበባ የምሄድበት ጉዳይ ነበረኝ አንች ከመጣሽ ግን ላንች ቅድማያ እሰጥሻለሁ ከአንች በላይ ጉዳይ የለኝም" ሲለኝ አንዳች ሸክም ከትከሻየ ላይ ሲነሳ ተሰማኝ ደስ አለኝ በጣም " ውዴ በቃ አዲስ አበባ መተህ እንገናኝ ወላሂ ጨንቆኝ ነበር እነ ሀዩ ጋር እረፍትን ለማሳለፍ ቃል ገብቸ ነበር አሁን ግን ቃሌን አጥፌ አንተን መርጨ ለነሱ ምን እንደምል ጨንቆኝ ነበር" ስለው ቅድሚያ ስለሰጠሁት ደስታው ጣራ ነካ እናም አዲስአበባ  ለመገናኘት ተስማማን፡፡
ምን_ልስጥሽ.. ..
.
እሺ ምን ላርግልሽ ??
ስጦታ የሚሆንሽ...ላንቺ የሚገባ
ምን ልስጥሽ አለሜ ላንቺ የሚረባ
ካንቺ ጋራ ስሆን እኛን የሚያግባባ
ፍቃድሽ ከሆነ
የሀገራችንን መብራት
ሃይልን ልስጥሽ
ይቅርብሽ አልሰጥሽ
ግድ የለም ይቅርብሽ
.
ይጠፋል
ይመጣል ላንቺ መች ሊጠቅም
ቁጣሽን አብዝቶ
ጨጓራሽን በልቶ ላጣሽ አልፈልግም
ቴሌን እንዳልሰጥሽ ስልክ ቤታችንን
እሱም መከራ ነው ታቂያለሽ ኔቶርኩን
እሺ ምን ላምጣልሽ
በምን ላስደስትሽ ?
.
እውነቱ ግን ውዴ
የቧንቧ መክፈቻ....ልሰጥሽ አስቤ
እየከበደኝ ነው....በጣም ፈራ ልቤ
ያልታከመ ውሀ ብጠጪ እንኳ ለጥም
ሀተት ታመሽብኝ..ላጣሽ አልፈልግም
.
ከሰማሽኝ ውዴ
ቁስ ተራ ነገር ነው ግዴለም አልስጥሽ
ፍቅር ብቻ ወስጅ ሁሌም ላስደስትሽ
,
].,,[ .አ..ከሪም የእናቱ ልጅ. ]
.
      ጠዋት ሁለታችንም  ጉዞችንን ወደ አዲስ አበባ አደረግን፡፡ ከነቢ እና ከሀዩ ጋር በአካል ለመገናኘት በቃን አልሀምዱሊላህ " ያለሰው ይገናኛል ካልሞተ በስተቀር"  ሶስታችንም ተሰባስበን የሆድ የሆዳችንን ስናወራ አደርን ስለ ኡስማን ስነግራቸው ሁለቱም ሳቁብኝ፡፡ ሳቃቸው ግራ አጋባኝ ከኔ ቀድመው የሚያውቁት ነገር ያለ መሰለኝና ምን አሳቃችሁ ብየ በጥያቄ አፍጠጥካቸው ሀዩ አይኗን ወደ ነቢ ወርወር አደረገችና  "አይ ነቢ ቀድማ አውቃው ነበር" አለችኝ ንግግሯ ይበልጥ ግራ አጋባኝና አልገባኝም በሚል እይታ ገርመም አረኮቸው
....."ባክሽ ገና ያኔ በኢክሩ ሠርግ ላይ ነው የምላሹ ቀን ሁለታችሁን አንድ ላይ ከኃላ ሳያችሁ ጥምረታችሁ ያምራል እና ለሀዩ ተመልከቻቸው ቢጋቡ አያምሩም ብየ ንግግሬን ሳልጨርስ ያ ኮስታራና ጥርሱ በዋዛ የማይገለጠው ኡስማን ላንች ግን ጥርሱን ገልጦልሽ በፈገግታ ሲያወራሽ ሳይ ጥርሱን ብቻ ሳይሆን ልብንም ከፍቶ እንደሚያስገባሽ እርግጠኛ ነበርኩ ይሄው ዛሬ ቀን ጠብቆ ከእጅ አስገባሽ" ብላ ንግግሯን ቆጨች፡፡
......በንግግሯ ተገረምኩ ያኔ ምናልባት አላስተዋልኩ ይሆናል ያኔም ፈገግ ብሎ አናግሮኛል ግን እኔ መሳቅ አመሌ ነውና ለፈገግታየ አፀፍ ምላሽ ለመስጠት ፈገግ የሚል እንጅ የመሰለኝ ነቢ በተመለከተችው ምልከታ አላየሁትም ነበር፡፡

#Part 1⃣3⃣
ይ..........,ቀ......
.........ጥ..........ላ.............ል

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
ለምን ትጽፋልህ??? ✍️
ባልጠበቅኩት ሰሀት ከመሬት ተነስተህ
ምንም ሳልበድልህ ሰማይ በኔ ደፍተህ፤
ስትሄድ ከደጃፌ በሀዘን ፊቴን ጥዬው
ራሴን ከሰው በታች በውርደት ቀብሬው፤
ከለመድኩኝ ኋላ ምን ቀርቶህ ወረቀት
የምትሞነጭረው ለሰበርከው አንገት
ምነው ባትነካካኝ ሰላም ብኖርበት!??
እፈታለሁ ብለህ ቂመኛው አንጀቴን
ብታሞጋግሰው ደምግባት ውበቴን፤
ደህና ሰንብች ብለህ በጨበጥከኝ መዳፍ
አይገባኝም ዛሬ ጥራዝ ምክንያት ቢጻፍ፡፡
እውነቱን ልንገርህ ከኔ ላንተ የቀረ
የፍቅርህ እንጥፍጣፊ ቅሪት ስለሌለህ፤
በብጣሽ ደብዳቤ ምህረት ተሸምቶ
የተከፋው ፊቴ ዳግም ላንተ ፈክቶ
ይታይ ይመስልሀል በግፍ ተጨራምቶ???
አንጀቴን ከቆረጥክ ከረሳሁህ በኋላ
ታሪክ ስለሌለኝ ጦማር የማይሞላ፤
በከሸንከው ቃልህ የሀሰት እጉርጉሮ
ብትጽፍ ብትቀኘው በውብ ቃላት ቋጠሮ፤
ልቤ አይደነንጥም ጠፍቶአል ተሰውሮ
ፊት አትንሺኝ አትበል ፊቴም ጠፍቶአል ድሮ፡፡

@Me-DAG

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
#የማይረሳው_ኮኮብ...!

✔️በህይወት እስካለህ ልትሳሳት፣ ልትወድቅ ትቸላለህ። ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ። ወይም ሃሳብህን ላይረዱህ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ። በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ። ሰዎች ሊጠሉህ፣ ሊያሙህ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ፣ አሊያም ሊስቁብህ፣ ይችላሉ።
.
.
.
✔️በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሃል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሃል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ፤ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሃል።
.
.
.
✔️ምናለፋህ በዓለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር። ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!
አንድ ነገር ልንገራችሁ!
:
በህይወት ማንንም አትውቀሱ!
ጥሩ ሰዎች ... ደስታን ይሰጡዋችኋል።
መጥፎ ሰዎች ... ልምድ ይሆኑዋችኋል።
ክፉ ሰዎች ... ማስጠንቀቂያ ይሆኑዋችኋል።
ምርጥ ሰዎች ... ትዝታ ይሆኑዋችኋል።
© ደራሲና ጋዜጠኛ ስብሃት

Join 👇👇👇
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

          🌼  #ክፍል 1⃣3⃣

#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal
       ምሽቱን ነግቶ እሱን ስለማግኘት እያሰብኩ ነገን በጉጉት በመጠባበቅ በአይኔ እንቅልፍ ሳይዞር ነጋ፡፡ አዲስ ቀን ብሩህ ተስፋ  ተሰባስበን ቁርስ ከበላን በኃላ አክረም ወደ ስራ ሄደ፡፡ አክረም መልካም ሰው ነው ለሀዩ ያለው ፍቅር የተለየ ነው በትዳራቸው ውስጥ ከልብ የመነጨ ፍቅር ጥልቅ የሆነ መተሳሰብና መከባበር ይስተዋላል፡፡ ፍቅራቸው እጅጉን ያስቀናል፡፡
......ሀዩ ስለ አክረም መልካምነት አውርታ አትጠግብም ትሳሳለታለች ወቶ እስኪመለስ ይናፍቃታል፡፡ ከተቀመጥንበት ሳንነሳ ኡስማኔ ደወለ የምንገናኘበትን ቦታ ነግሮኝ ስልኩ ተዘጋ፡፡ ሁለታችን ብቻ መገናኘታችን አላስፈላጊ ነገር ውስጥ ይከተናል ብየ ስላሰብኩ ከነቢ ጋር ለመሄድ ተስማማን፡፡     

        አለሜን ገና ከርቀት ሳየው ሮጠሽ ሂደሽ ተጠምጠሚበት የሚል ሀይል ውስጤን ተቆጣጠረው ግን ሀይማኖታችን በኒካህ እስካልተሳሰርን ድረስ እንዲህ አይነት ተግባርን ይከለክላልና ከስሜቴ ይልቅ ሀይማኖቴን አስቀደምኩ እነዚያ ውብ በፍቅር ገዳይ ጥርሶቹ ተገልጠው ሳያቸው የምገባበትን አጣሁ አይኖቸ አይኑ ውስጥ ሰጠሙ በሱ ውጭ ማንም አይታየኝ ፈዝዝ ብየ ቀረሁ " አረ እኛንም እይን" የሚለው የሙስጤ ድምፅ አባነነኝ አይገርምም እስከ አሁን ሰአት ድረስ ሙስጤን አላስተዋልኩም ድምፅ ወደሰማሁበት አቅጣጫ ስዞር ሙስጠፍ በትዝብት ይመለከተኛል እንደማፈር ብየ "
...... እእ ሙስጤ እንዴት ነህ" ብየ ሀፍረቴን በፈገግታ ለመደበቅ ሞከርኩ፡፡
.......ሙስጤ ተጫዋች እና የማያስፈራ ቀለል ያለ ሰው ነው፡፡ እኔም ለማዳ በመሆኔ ለመግባባት ጊዜ አልፈጀብንም፡፡

,.,,.ያኮስታራው ኡስማን ዛሬ ጥርሶቹ መሳቅ አላቆመም ፊቱ የደስታ ብርሀን ያበራል፡፡ እኔም ከሱ ጋር መሆኔ ደስታ ምቾትና ሰላምን ፈጥሮልኛል፡፡ ልቤ በደስታ ብዛት ሰክራ ትፈነጥዛለች፡፡ ከሚወዱት ሰው ጋር እንደመሆን ምን የሚያስደስት ነገር አለና፡፡ የቱንም ያህል የቆየን ሳይመስለን ሰአቱ ለካ ሂዷል፡፡ መለያየት ባንፈልግም ግዴታ እንለያያለን፡፡ ከፋኝ ደስታየ እንደጉም በኖ ጠፋ፡፡ ደስታየን እና ልቤን አለሜ ጋር ትቸ በድን አካሌን  ይዤ ተመለስኩ ገና ስለየው ይናፍቀኝ ጀመር ስንገናኝ ፍቅሩ ጨመረብኝ እንደከፋኝ ቤት ደረስን፡፡
      ሀዩ ፈራርሻ ብና አፍልታ ጠበቀችን እንደዚህ ተፈራርሾ ካየሁ ወራቶችን አስቆጥሬያለሁና ደስስስ አለኝ፡፡ ሀዩን ሳምኩና የፈንደሻ ሰሀኑን አቅፌ ተቀመጥኩ ፈንድሻ እንደምወድ ስለሚያውቁ ተያይተዎ ተሳሳቁ "ግን ዘይቱ ሲበዛ ልብሽን አያምሽም" ትለኝ ነበር ኢክሩ፡፡ ሰሀኑን ይዤ ስቀመጥ "አረ ትንሽ እንካን ስጭኝ" ብላ ነቢ ከጎኔ ተቀመጠች .
........"እሽ ውሎ እንዴት ነበር" አለች ሀዩ ለመስማት እየተመቻቸች፡፡ ስለውሎአችን ስነግራት በአይነ ህሊናኔ አለሜን እያየሁ እየተፍነከነኩ ተረኩላት፡፡ ንግግሬን ስጨርስ ነቢ ሳቆን ለቀቀችው "ውይ ኢሙ በቃ በፍቅር ተሸነፈች ያች ፍልቅልቅ የምትለው አይከፍሽ መሳቅ ማቆም የማይሆንላት ኢማን ዛሬ በፍቅር ወድቃ የደስታዋን ቁልፍ በኡስማን ተሰርቃ ህልውናዋ በሱ ስር ወድቆ ስሜቷ ከሱ ስሜት ጋር ተቆራኝቶ ደስታው የሚያስደስታት ሀዘኑ ህመም የሚሆንባት ፍቅሩ አቅም አሳጥቷት ሳይ የእውነት አዘንኩላት እስካሁንኮ ስንመጣ አኩርፋኝ ነበር አሁን ስለሱ ሲነሳ ተመልከች እንዴት ጥርስ በጥርስ እንደምትሆን" አለችና የፌዝ ሳቆን ለቀቀችው የፍቅርን ሀያልነት የሚያውቅ ያውቀዋልና "እስኪ ያንችም ተራ ሲደርስ እናይሻለን" አለች ሀዩ፡፡

የእረፍት ጊዜየን ከአለሜ ጋር አሳለፍኩ ግን ሁሌም ስንገናኝ ነቢና ሙስጤ ከኛ ጋር ናቸው፡፡ አለሜ የመጣበትን ጉዳይ ጨርሷል ግን እኔ እስክመለስ ድረስ አብሮኝ ለመሆን ወስኗል የኔም እረፍት ቀን አልቆ ሁለት ቀን ብቻ ቀርቶኛል፡፡ አቤት የጊዜው እሩጫ አንድ ቀን የቆየን ሳይመስለኝ 10 ቀናት አለፉ፡፡ ግን እስካሁን ለምን ጉዳይ እንደመጡ አልጠየኩም ነበር፡፡
       የመጡበትን ጉዳይ እንደጨረሱ ሲነግረኝ ነበር " ግን ለምን ነበር የመጣችሁት?" ብየ ጠየኩኝ ሙስጤ ሳቀብኝ "ለነገሩ አልፈርድብሽም ኡስማን ማሰቢያሽን ወስዶት ነው ቆይ ግን ምን ይሻላችኃል? ያለማሰቢያ እንዴት ትኖራላችሁ የሱንምኮ ማሰቢያ ሰርቀሽዋል የሚሰራውን አያውቅም ዝም ብሎ መጣ እንጅ ሁሉን በኔ ጥሏል፡፡ ኢማን ሁኗል ሀሳቡና ወሬው" ሲል ልቤ በደስታ ቀለጠች፡፡ ......." የመጣነው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቆም ለመክፈት አስበን እኔና ኡስሚ አንዳንድ ነገሮችን ከዚህ አስጨረስን አሁን ደግሞ ባህር ዳር ማስጨረስ ያለብን ነገር አለ" አለን "
.......እና አሁን ደግሞ ባህር ዳር ልትሄዱ ነው?" አልኩ "
.......... አይ ልትሄድ በይኝ እኔ ብቻየን ነኝ እሱ በድኑ ነው ያለው መስራት አቁሟል ብቻ ውክልና የተሰጠን ለሁለታችን ስለ ሆነ ፊርማው ስለሚያስፈልግ እወስደዋለሁ" ብሎ የኡስማኔን በፍቅር መውደቅ ታዝቦ በአሽሙር ተናገረ "አምስታችሁም ናችሁ በጋራ የምትከፍቱት?"
....." አወ ግን ሁለቱን ተያቸው ከማል በልጅ ፍቅር ተጠምዶ ለኛ የሚሰጠን ጊዜ አቷል ስራ ቦታ መዋል ራሱ ከብዶታል ከልጅ ጋር ውሎ ቢያድር ስምቱ ነው አንዋሬም ያው እክራም እርጉዝ ነች ብቻዋን ሊተዋት አይችልም ከአብኪ ይሄ ይሻላል ብየ ባመጣው እንደዚህ ያለ ልብ መወዝወዝ ሆነ ስራው" አለ     
        የሙስጤ አሽሙር  ስለበዛበት " ቆይ ግን አንተ የራስህ አይታይህማ  አንተ ከሪማን ወደህ ቀን ለሊት ማልቀስ አልነበር እንዴ ስራህ? እእ ለያዠ ለገናዠ አስቸግረስ ዛሬ አንተም በኔ ላይ ለመሳለቅ በቃህ?"ብሎ አለሜ ጥያቄ አዘል ንግግሩን ጨረሰ " አልቅሸም አብጀም አልቀረሁም አላህ ዱአየን ሰምቶኛል ታውቃለህ በቅርቡ ሚስቴ ትሆናለች ሚስቴ!!" ከንግግሩ  ሙስጤ ሊያገባ እንደሆነ ተረዳሁ፡፡ ከማል መንገዱን አሳያቸው አንዋር ተከተለ አሁን የሙስጤ ተራ ደረሰ፡፡
        ዛሬ የመጨረሻ ቀኔ ነው ከአሁን በኃላ አለሜን ለማየት ወራቶችን መጠበቅ አለብኝ፡፡ እንዴት ነው የምችለው ከጎኔ ሁኖ እየናፈቀኝ ጭራሽ ሳላየው ውየ ላድር ፍርጃ ሆኗል፡፡ ምነው ዛሬ ቀኑ ሳይመሽ የአመት ያህል በተለጠጠ ነገ የሚሉት ቀን ባይመጣ ብየ ተመኘሁ ግን ምን ዋጋ አለው ሰአቱ መቁጠሩን ሳያቆም ፀሀይ ቦታዋን ለጨረቃ ለመልቀቅ አኮበኮበች፡፡

#part 1⃣4⃣
ይ........ቀ........
........ጥ ................ላ........ል

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
#የቻይናው_ፕሬዝዳንት_ሺ_ጂንግ_ፒንግ

" #የአባቴ_ሦስቱ_ምክሮች"
የወቅቱ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንግ ፒንግ ጥሩ ስትራቴጂ አዋቂና የሀገር መሪ ብቻ አይደሉም፡፡ ጥሩ ወግ አዋቂ ጭምር እንጂ፡፡ በአንድ ወቅት እንዲህ ሲሉ ስለልጅነት ጊዜያቸው ተናገረዋል፡፡


📌“ልጅ እያለሁ፣ እጅግ በጣም ራስ ወዳድና ሁሉንም ነገር ለኔ ባይ ነበርኩኝ” ይላሉ ፕሬዝዳንተ ሺ ጨዋታቸውን ሲጀምሩ፡፡ ለግማሽ ክፍለዘመን ወደኋላ በትዝታ እያሰቡ ፕሬዝዳንቱ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡
ራስ ወዳድ ከመሆኔ የተነሳ ሁል ጊዜም ጥሩ ጥሩውን ለራሴ ነበር የምወስደው፡፡ ይህ ባህሪዬ ቀስ በቀስ ጓደኛ እያሳጣኝ መጣ፡፡ በመጨረሻም ጓደኞቼ ሁሉ ሸሽተውኝ ጓደኛ አልባ ሆንኩ፡፡ እኔ ግን ጥፋቴ ምን እንደሆነ አልገባኝም፡፡ ጓደኞቼ ስለሸሹኝ ኮነንኳቸው እንጂ ጥፋቴ ምን እንደሆነ ራሴን አልጠየኩም፡፡ ቢሆንም፣ አባቴ ሕይወትን በመልካም መንገድ እንዴት መምራት እንደምችል በተግባር አስተማረኝ፡፡


የአባቴ የሕይወት ትምህርት ሶስት ደረጃዎች ነበሩት፡፡
አንድ ቀን አባቴ፣ ለሁለታችን የሚሆን ምግብ አዘጋጀና በሁለት ሳህን ከፍሎ የምግብ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው፡፡ ምግቡ ፓስታ (ኑድል) በእንቁላል ነበር፡፡ አባቴ ፓስታውን ሲያስቀምጠው በአንደኛው ሳህን ከፓስታው በተጨማሪ የተቀቀለ አንድ እንቁላል ከአናቱ አድርጎበታል፡፡ በሌላኛው ሳህን ግን ከፓስታው በላይ እንቁላል የለም፡፡ ከዚያ አባቴ ወደ እኔ እየተመለከተ፣ “ልጄ የትኛውን ትፈልጋለህ? አንዱን ሳህን ምረጥ” አለኝ፡፡
በጊዜው፣ እንቁላል እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ ምግብ አይደለም፡፡ አዲስ ዓመት ካልመጣ ወይም ዓመትባል ካልደረሰ በቀር እንቁላል መብላት ዘበት ነው፡፡ ፈጥኜ እንቁላል ያለበትን ሳህን መረጥኩ፡፡ በሰዓቱ፣ ሳህኑን ሳነሳ ቅንጣት ታህል አላመነታሁም፡፡ ደስ እያለኝ መብላት ጀመርኩ፡፡
አባቴ ሁለተኛውን ሳህን አንስቶ መመገብ ሲጀምር አይኔን አላመንኩም፡፡ አባቴ ከሚበላበት ሳህን ውስጥ ሁለት የተቀቀሉ እንቁላሎች በፓስታው ተሸፍነው ኖሯል፡፡ ተቆጨሁ በጣም! ቸኩዬ በመወሰኔ ራሴን ወቀስኩት፡፡

🍃ይሄን ጊዜ አባቴ እየሳቀ፣ “የኔ ልጅ፣ አይኖችህ የሚያዩት ሁሉ እውነት እንዳልሆነ መቼም እንዳትረሳ! በሰዎች ላይ ብልጣብልጥ ለመሆን ስትሞክር ትጎዳለህ!!” አለኝ፡፡
በሌላ ቀን፣ አባቴ በተመሳሳይ ምግብ አዘጋጅቶ ሲያበቃ እንደተለመደው ፓስታውን በሁለት ሳህን አቀረበው፡፡ አንደኛው ሳህን አናት ላይ አንድ የተቀቀለ እንቁላል አስቀምጦበታል፡፡ በሌላኛው ግን ከላይ ምንም እንቁላል አላደረገበትም፡፡ ከዚያ እንደተለመደው አባቴ ወደ ምግብ ጠረጴዛው እየጠቆመ “ልጄ፣ ምረጥና የምትፈልገውን ሳህን ውሰድ” አለኝ፡፡

ካለፈው ስህተቴ በመማር በጥንቃቄ መምረጥ እንዳለብኝ አሰብኩና ቀልጠፍ ብዬ ከአናቱ እንቁላል የተደረገበትን ትቼ ሌላኛውን መረጥኩ፡፡ ከዚያ በፍጥነት ፓስታውን ገላለጥኩና ሳህኑን አየሁት፡፡ በጣም ደነገጥኩ! ሳህኑ ውስጥ አንድም እንቁላል የሚባል ነገር የለም፡፡
አባቴ በድጋሚ እየሳቀ፣ “ልጄ፣ ሁል ጊዜ በልምድህ ላይ ብቻ የምትተማመን ከሆነ ትከስራለህ፡፡ አንዳንዴ ሕይወት ራሷ ልታሞኝህ ወይም ቁማር ልትጫወትብህ ትችላለች፡፡ ዳሩ ግን፣ በዚህ ብዙ ልታዝን ወይም ልትቆጣ አይገባም፤ ትምህርት እንደሚሆንህ ቆጥረህ እለፈው፡፡ እንዲህ ያለውን እውቀት ከመማሪያ መፅሀፍት ላታገኝ እንደምትችል አስታውስ” ብሎኝ፣ ያ ቀን አለፈ፡፡
ለሶስተኛ ጊዜ አባቴ ምግብ አዘጋጀ፡፡ እንደተለመደው ፓስታ እና እንቁላል በሁለት ሳህኖች ቀርበዋል፡፡ በአንዱ ሳህን የተቀቀለው እንቁላል ከፓስታው በላይ ተቀምጧል፡፡ በሌላኛው ሳህን ደግሞ ፓስታ ብቻ…፡፡ የውስጡን አላውቅም፣ ከላይ ግን እንቁላል የለም፡፡ አባቴ የተለመደው ጥያቄውን አቀረበልኝ፡፡ ወደ ምግብ ጠረጴዛው እየጠቆመ፣ “ልጄ ምረጥ! የትኛው ሳህን ይሁንልህ?” አለኝ።
አሁን እኔ ከሁለት ሥህተቶቼ ትምህርት አግኝቻለሁ፡፡

🍃“አባቴ አንተ የቤቱ አባወራ ነህ! ለቤተሰባችን ሰርክ የምትለፋ አባት ነህ፡፡ መጀመሪያ መብላት ያለብህ አንተ ነህ፤ ይገባሃልም፡፡ ስለዚህ ቅድሚያ አንተ አንሳ…” ስል መለስኩለት፡፡
አባቴ በጭራሽ አላቅማማም…፡፡ ከአናቱ እንቁላል የተቀመጠበትን ሳህን አንስቶ መብላት ጀመረ፡፡ እኔም ሁለተኛውን አንስቼ ፓስታዬን ለመብላት አቀረቀርኩ፡፡ እርግጠኛ ነበርኩ፣ ሳህኑ ውስጥ እንቁላል እንደማይኖር፡፡ ከፓስታው በታች ሁለት እንቁላሎችን ሳገኝ ግን አይኔን ማመን አልቻልኩም፡፡
ቀና ብዬ ሳየው፣ አባቴ ፈገግ ብሎ በፍቅር አይኑ እያስተዋለኝ ነበር፡፡ ከዚያም እንዲህ ሲል መከረኝ፤ “የኔ ውድ ልጅ! ለሌሎች ሰዎች መልካም መልካሙን ስታደርግ ተፈጥሮ ራሷ መልካም መልካሙን ወደ አንተ ታመጣለች! ይሄንን መቼም እንዳትዘነጋ” አለኝ፡፡
ከዚያን ጊዜ በፊትም ሆነ፣ ከዚያን ጊዜ በኋላ አባቴ ብዙ ጊዜ መክሮኛል… ገስፆኛል፡፡ አብዛኞቹን ማስታወሴን እጠራጠራለሁ፡፡ ነገር ግን፣ እነዚህ ሦስት ምክሮቹን በፍፁም አልረሳቸውም… እስክሞት ድረስ፡፡ እነሆ ሕይወቴም በዚህ ምክንያት የተስተካከለ ሆኗል፡፡ ከአባቴ ምክር በኋላ ስኬት መንገዷን ወደ እኔ አድርጋለች፡፡
አባቱን የሚወድ ሼር
#ምንጭ: Long Live Ethiopia

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
የት ብዬ ላግኝሽ...»
(አወቀ ካሳው)
....................
አልንድ ተራራውን መሬትን ገልብጬ
ወይ አንቺ አይገባሽ በጭንቀት ተውጬ
.
የለሽም ባገሩ በየጥሻ ሁሉ
ርቀሽ ሂደሻል ታይቶሽ መኮብለሉ
.
መናወዝ አይደክመኝ በፍለጋ መድከም
ብሶቴ ላይቀለኝ እግሬም አይታከም
.
የለሽም የለሽም ላይን ተሰውረሻል
እንደው እንደ ዘበት ይነጋል ይመሻል
ቢጨልም ቢመሽም ዐይኔማ ያይሻል
.
በየት ልፈልግሽ አድራሻሽ ወደየት ነው
የወደፊት ሚስቴ እየናፈኩሽ ነዉ
.
በየት ብዬ ልምጣ ካለሽበት ቦታ
ዕይሽን እንዳየው ምን መንገድ ይወሰደኝ
ካለሽበት አገር ካንቺ ጋር ያድርሰኝ
ይኸው ቁጭ ብያለሁ ሁሉ ተደናግሮኝ
.
መንገድ ዳር ቁጭ ብዬ ብጠብቅሽ የለሽ
በተመላላሹ ራስሽን ተክተሽ አንቺ ብቻ የለሽ
.
ሰው ሁሉ ይመጣል ይነጉዳል እንደ ጉድ
ያየሽ አላየሁም ሂዶ ባንቺ መንገድ
ይጎርፋል እንደ ጉድ ያልፈኛል ታዝቦ
ቅጭም ባለ ፊቴ ሀዘንታን ደርቦ
.
አንቺ ግን አታልፊም ዱካሽ አይታይም
በየት ልፈልሽ? ምንም ቢጨንቀኝም መፍትሄ የለኝም
...........
#ሼር #ላይክ በማድረግ ቤተሰብነታችን ይጠንክር

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
⭐️#አለመግባባትና_የአሮጌ_እይታ_ተጽእኖ

💐💐"ሰላም ማለት የአለመግባባት አለመኖር ሳይሆን በመሸማቀቅ መደበቅን ፣ አጉል ኃይለኝነትንና ጸበኝነትን የሚተኩ ትክክለኛ ምርጫዎችን የማምጣት ብቃት ነው"

#Dorothy_Thompson

ከልጅነታችን ጀምሮ ስንመለከት ያድግነው የሕብረተሰባችን አካሄድ በአለመግባባት ላይ ያለንን አመለካከት ቀርጾታል። ስለዚህም ከአለመግባባት ጋር አዛምደን የምናስባቸው ቃላት ጥሩ ስሜት የሚሰጡና ለመፍትሄ የሚያነሳሱ አይደሉም።
#ለምሳሌ ፣ ካለመግባባት ጋር የተያያዙ ቃላት የሚከተሉትን ያጠቃልላል። ጸብ ፣ ቁጣ ፣ ንዴት ፣ መቋሰል ፣ ጦርነት ፣ ፍጥጫ ፣ ውድመት ፣ ፍርሃት ፣ ገለልተኝነት ፣ ክስረት ፣ ቁጥጥር ፣ ጥላቻ ፣ መጥፎነት ፣ ክፋት ፣ በደለኛነት... እና የመሳሰሉት። እነዚህ ቃላት የተሸከሙት ሃሳብ አሉታዊና መፍትሄ-ቢስ ስሜትን የሚጭኑ ናቸው።

⭐️አንድ ሰው አለመግባባትን በበሰለ ስሜታዊ ብልህነት መመልከት ሲጀምር ግን አለመግባባት በራሱ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ገጽታ እንደሌለው መገንዘብ ይጀምራል።
⭐️በሌላ አባባል አለመግባባትን አያያዛችን ብቻ አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ገጽታ ሊሰጠው ይችላል እንጂ አለመግባባት በራሱ ከሁለት አንዱን ባህሪይ የያዘ ክስተት አይደለም። ለዚህ ነው ስሜታዊ ብልህነት ወይም በሌላ እይታ ፣ ማሕበራዊ ብልህነት በግንኙነትና በአለመግባባት ላይ ታላቅ ስፍራ አለው ብለን የምናምነው።

🍃በማንኛውም ግንኙነትና ማሕበራዊ ኑሮ ውስጥ አለመግባባት የማይቀር ጉዳይ መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው። የጉርብትና የእርቅ ሸንጎውና ማሕበራዊው ትስስር ፣ ሽምግልናው ፣ የሕግ ስርአቱና የመሳሰሉት የሕብረተሰባችን ሂደቶች የአለመግባባትን ቋሚነት አመልካች ናቸው።

🎖ስለዚህ ፣ አለመግባባት የማይቀር ክስተት ከሆነ ፣ ትክክለኛ የአያያዝ መንገዶችን ማዳበሩ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ይህንን ለማድረግ ደግሞ በስሜትም ሆነ በማህበራዊ ብልህነት መብሰሉ የመጀመርያው እርምጃ ሲሆን ፣ በመቀጠልም ባለመግባባት ላይ ያለንን አሮጌ እይታ በአዲስ እይታ መቀየር አለብን።

#ምንጭ :- "የስሜት ብልህነት" ገጽ 116-117 በዶክተር ኢዮብ ማሞ

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
⭐️በያንዳንዱ ሕፃን ልጅ ውስጥ አንድ ገና ያልተገለጸ ትልቅ ሰው አለ ፡፡ ይህም ጊዜን የሚጠብቅ ነው ። ለእኔ ግን ምንጩን መርምሬ በቅጡ ያልደረስኩበት በሄድኩበት ሁሉ የሚያጋጥመኝ በያንዳንዱ ትልቅ ሰው ውስጥ የሚወራጭ ሕፃን ልጅ ነው።

🍃 በተለይ 'ሕፃናት' ወላጆችንና አገር መሪዎችን ማየት በጣም ነው የሚያስፈራኝ።
በያንዳንዱ ሕፃን ውስጥ የተሰወረውን ትልቅ ሰው በትክክል ካላሳደግነው፡ ውሎ ዐድሮ በትልቅ ሰውነት ውስጥ የሚንፈራገጥ እንጭጭ ሕፃንን ማግኘታችን አይቀርም።

🍃በሕፃን ውስጥ የተሰወረውን ትልቅ ሰው ማሳደግ ደስታ ነው።በዐዋቂ ሰውነት ውስጥ ከተደበቀ ሕፃን ጋር መኖር ግን ከሁሉ የከፋ መከራ ይመስለኛል። "
ለሰው ልጅ ስብዐናው መሰረቱ ነው

ምንጭ ☞ ዶ/ር ምህረት ደበበ , የተቆለፈበት ቁልፍ ገፅ 45

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
🍃 #ሁለቱ_ወንድማማቾች
አል–በራዕ ኢብን ማሊክ አል–አንሷሪይ እና አነስ ኢብን ማሊክ
በትዕግስት አንብቡት

ኢስላም እንደ ሙሰይለማህ ቢን ሀቢብ(ሙሰይለመቱል ከዛብ) አይነት ቅጥፈተኛ የኢስላም ጠላት ገጥሞት አያውቅም። ይህ ሰው ራሱን ነብይ አድርጎ ነበር የሚጠራው። ከረሱል[ሰ•ዐ•ወ] ህልፈት በኋላ ጦር አደራጅቶ በሙስሊሞች ላይ ግልፅ ጦርነት አወጀ።
ሙስሊሞች በኻሊድ መሪነት ይህን የቅጥፈት ሰው ቢፋለሙትም ከትልቅ ግምብ ጀርባ በመሆን በአማኞች ላይ የቀስት ናዳ ያዘንቡባቸዋል። ብሎም በእሳት የጋለ ሜንጦ በመወርወር ሙስሊሞቹን ያሰቃዩ ጀመር።


🍃በዚህ መሀል የተወረወረ ሜንጦ አነስ ኢብን ማሊክን አንጠልጥሎ ይይዛቸዋል። ወንድማቸው አለ በራዕ ይህን ባየ ጊዜ በእሳት የጋለውን ሜንጦ በእጁ ይዞ ወንድሙን ለማስለቀቅ ይጥራል። የብረቱ ግለት እጁ ላይ የነበረውን ስጋ አቃጥሎ በአጥንት ቢያስቀረውም ወንድሙን ነፃ እስከሚያደርግ ድረስ አልለቀቀውም። ስቃዩን ችሎ ወንድሙንም ከሜንጦው ነፃ አደረገ።

ፍልሚያው ለሙስሊሞች የሚቋቋሙት አልሆነም። ከግምቡ ጀርባ የመሸጉት ሙሽሪኮች በምን ብልሀት ሊሸነፉ አንደሚችሉ ሲያስብ አል በራዕ አንድ ሀሳብ አፈለቀ። ሰውነቱ ቀጭን የሆነው ይህ ታላቅ ሰሀባ በወስፈንጠር ከግምቡ ጀርባ ይጥሉ ዘንድ ባልደረቦቹን አማከረ። "ከሞትኩም ሸሂድ ነኝ፣ ተሳክቶልኝ በሩን ከከፈትኩላችሁም ድል ለኛ ይሆናል" አላቸው። በሀሳቡ ተስማምተው አስፈንጥረው ወረወሩት።
መሬት ላይ እንዳረፈ አንድ እጁን እያስታመመ በሌላኛ እጁ በያዘው ሰይፍ የአላህን ጠላቶች ይፋለም ጀመር። ብዙዎቹን ጥሎ እርሱም ብዙ ቦታ ቆስሎ በሩን ይከፍትላቸዋል። በዚህ ታላቅ መስዋዕትነት በተከፈለበት ድርጊቱ ሙስሊሞች ለድል በቁ። በኡሁድ ዘመቻ ሀምዛን የገደለው ወህሽይ ዳግም በአላህ መንገድ ላይ ባደረገው ተጋድሎ ሙሰይለማህን ገደለው።
በዚህ የሞት ሽረት በተደረገበት ታላቅ ተጋድሎ ሁለቱ ወንድማማቾች ሸሂድ ሆኑ።

JOIN 👇👇👇
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

          🎧  #ክፍል 1⃣4⃣

#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal

       መለያየታችን ቁርጥ ሲሆን ሆዴን ባር ባር እያለኝ አልቅሽ አልቅሽ የሚል  ስሜት ውስጤን ተቆጣጠረኝ፡፡ ለረዥም  ሰአት ዝምታ ሰፈነ ሁለታቾንም በየራሳችን በሀሳብ ፈረስ ጉዞ ጀመርን፡፡ በዚች በጥቂት ጊዜ ቆይታችን ስላሳለፍነው ጣፍጭ ጊዜያቶች እያሰብኩ በደስታ ማእበል ሰጠምኩ፡፡ እንደገና አሁን ልንለያይ መሆኑን ሳስብ ደስታየ እንደጉም በኖ ጠፍ፡፡ አሁን እንዴት ነው የምሰናበተው ጨነቀኝ ምናለ ሳላገኝህ ቀርቸ ቢሆን አይኖቸ በእንባ ተሞሉ እንባየን አይቶ እንዲባባ አልፈለኩምና አይኔን እንዳያይ አቀረቀርኩ፡፡
....... ነቢ " ኢሙ እየመሸ ነው " አለችኝ መሄድ እንዳለብን እየነገረችኝ መሆኑ ገባኝ፡፡ ቀና ብየ እንካን ሳላየው ከንግግሬ እንባየ እንዳይቀድም በመስጋት "በቃ ቻው" ብየ በአጭር ቃል ስንብት እርምጃየን ለመጀመር ፊቴን አዞርኩ " ኢሙ" የሚል ለጆሮ ጣፍጭ የሆነ ድምፅ ሰማሁ ባለሁበት ጀርባየን ሰጥቸው ቆምኩ፡፡

"ይሄን ቤት ስትደርሽ አንብቢው" ብሎ የታሸገ ፖስታ እና በትንሽ እቃ ተጠቅልሎ የታሸገ "ስጦታየ ነው እንደምትወጅው ተስፍ አደርጋለሁ" ብሎ ሰጠኝ የልቤ ምት ሲፈጥን ለራሴ ይታወቀኛል፡፡ በዚህ ሰአት አንገቱ ላይ ተጠምጥሜ ደረቱላይ ብለጠፍ እንዴት ደስ ባለኝ ግን አልችልም አልተፈቀደልኝም፡፡ እንዳሰብኩት ለመሆን በሀላል በኒካህ መጣመር አለብን፡፡ ስጦታየን ተቀብየ በእንባ በተሞሉ አይኖቸ አየሁት፡፡ አለሜም እንደኔ ከፍቶት ደስታ ርቆታል፡፡
 
ፍቺል

ወደ ዕሩቁ ሠማይ ወደ ላይ ከፍ ብሎ
አልያም ወደታች በምድር ተከልሎ
ቢያልፈው መልካም ነበር ሀዘንሽን አታሎ
ይሄ አፍቃሪው ልቤ ሞኝነቱ ጠንቶ
ሲያስብሸ እየዋለ ከ አካሌ ተጣልቶ
ከሁሉ አስበልጦ ለ ፍቅርሽ ተገዝቶ
ሲከፋሽ ያነባል መንታ ዕንባ አውጥቶ

ይሄ የዋህ ልቤ ይሄ ገራገሩ
ከስርሽ አይጠፋም ይታሠራል እግሩ
ሰትስቂ ይቦርቃል ይበረታል ፍቅሩ
የማይሠማኝ ልቤ ላንቺ ተገዝቶልሽ
የተከፋሽ ዕለት መንታ የሚያነባልሽ
ፈገግ ያልሽም ዕለት ጩሆ ሚስቅልሽ
እኔን ንቆ ትቶ ላንቺ ሚኖርልሽ
አማክሮሽ ከሆነ ለምንድን ነው አለሽ?

እኔ ስጠይቀው ዕንቆቅልሽ ብሎኝ
መመለስ ሲያቅተኝ ሀገር ተቀብሎኝ
ስቆብኝ ይሄዳል በቁሜ አደንዝዞኝ
ያሠረውን ቅኔ መፍታት ስላልቻልኩኝ
እቴ ልለምንሽ እስኪ አንቺ ፍቺልኝ
―――――――――――――

አየሁት አየኝ ግን አንዳችንም ቃል ማውጣት አልቻልንም፡፡
.......ነቢና ሙስጤ በሁኔታችን ያዘኑልን ይመስላሉ፡፡ ነቢ እንደ ሀውልት ከተገተርኩበት ጎተት አደረገችኝ፡፡ ከዚህ በኃላ እንባየን ልቆጣጠረው አልቻልኩም፡፡ እንደ ደራሽ ወንዝ ግልብጦ ብሎ መፍሰስ ጀመረ ፡፡ ነቢ እንደወትሮን ልትቀልድብኝ አላስቻላትም እሷም እንደኔ በእንባ ፊቷ ታጠበ፡፡ ሁለታችንም እየተላቀስን ቤት ደረስን ማንንም ማናገር አላሰኘኝም ሀዩም ሁኔታየን ስታይ ምንም መናገር አልደፈረችም ኢሻን ሰግጀ ወደ መኝታየ አመራሁ፡፡
      በጣም እየጓጓሁ የሰጠኝን ስጦታ ከፈትኩት  የሚያምር የብር ቀለበት በጣም ደስ ብሎኝ ተቻኩየ አጠለኩት፡፡ በጣም ያምራል ጣቴን ከወትሮው ተለይቶ ውብ ሆኖ ታየኝ፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቴ የአለሜ ቀለበት ነው፡፡ በደስታ እየሰከርኩ ፖስታውን ከፈትኩት፡፡

"የኔ ንግስት ይሄን ቀለበት ፊትሽ ተንበርክኬ በፍቅር አይኖችሽን እያየሁ በጠልቅልሽ ደስታየ ወደር አልነበረውም፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው የተከለከልሽ በለስ ሆንሽብኝ፡፡
 የኔንግስት ታውቂያለሽ ግን በልቤ ምን ያህል ቦታ እንዳለሽ ሳይሽ የልብ ምቴ ይፈጥናል የደም ስሮቸ ይነቃቃሉ ግን የማትበሊ ወፍ ሆንሽብኝ፡፡ የኔ ውድ ከዚህ በኃላ ግን በአይኔ ተቀብየ በአይኔ ልሸኝሽ አልፈልግም እጆችሽን መጨበጥ  ሰውነትሽን መዳሰስ እፈልጋለሁ፡፡ የኔ ውድ አግቢኝ ባልሽ ልሁን ወደፊት ብዙ ጣፍጭ የፍቅር ጊዜያት ይኖሩናል ብዙ ልጆችም እንወልዳለን፡፡ ጊዜ ሳናባክን ተጋብተን እንኑር፡፡ የኔ ልዩ ስጦታየ ነሽ ሁሌም ሳፈቅርሽ እኖራለሁ!!"
....... አንብቤ እንደጨረስኩ ደብዳቤውን ወደ ደረቴ አስጠግቸ አቀፍኩት ቀለበቴን አጥብቄ ሳምኩ፡፡ የደስታ እንባ አነባሁ፡፡  ደብዳቤውን እንዳቀፍኩ አንሶላየ ውስጥ ገባሁ፡፡  ጎኔ ቢጋደምም እንቅልፍ ግን ከኔ ርቆ ሂዷል፡፡ እኔና አለሜ ተጋብተን ስለሚኖረን ሂወት ስለምንወልዳቸው ልጆች እያሰብኩ የፈጅር (የንጋት) ሰላት ጥሪ ተሰማ፡፡ ነቢ ከጎኔ ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዷታሎ የኔ ውድ ጓደኛ በደስታየ ተደስታ በሀዘኔ ታነባለች፡፡ ልቀሰቅሳት አልፈለኩሞ በተኛትበት ሳምካት እና ተነስቸ ሱቢሂን ሰግጀ እዛው መስገጃየ ላይ እንደተቀመጥኩ ሀዩ ተነስታ ሩጣ ወደ ሻወር ስትገባ አየኃት ደህና አልመሰለችኝም ተከተልካት፡፡  ስገባ ሀዩን እያስመለሳት ነበር፡፡ #ደነገጥኩ ሀዩ! ብየ ሩጨ ልቧን ደገፍኮት፡፡
..... "ደህና ነኝ ውዴ ሰሞኑን ትንሽ እያመመኝ ነው" አለችኝ " ሀዩ በተደጋጋሚ ነው የሚያስመልስሽ?" ብየ ጠየካት
......" አወ ሰሞኑን ምቾት እየተሰማኝ አይደለም በቃ ወደ ነቢ ጋር ክሊኒክ እሄዳለሁ" አለችኝ እንዳረገዘች ጠረጠርኩ እጀን ወደ ሆዷ ልኬ "ሀዩ" ብየ አይን አይኗን ስመለከታት እንደማፈር ብላ እየሳቀች " አወ እኔም ይመስለኛል ግን ክሊኒክ ሂጀ ላረጋግጥ እና ለእሱም  አባት ሊሆን እንደሆነ አበስረዋለሁ"" አለችኝ " የኔቆንጆ እንዴት ደስ ይላል በአላህ ሁሌም ደስታሽን አላህ ያሳየኝ" ብየ አቀፍኮት፡፡
......ነቢ ከእንቅልፏ ነቅታ " እናንተ እዚህ ነው እንዴ ያደራችሁት?" እያለች አይኗን እየዳጠች ተጠጋችን " እንቅልፎ እስኪ ንቂ መጀመሪያ ከነቆራው በፊት" አለች ሀዩ " ነቢ ሲነጋ ሀዩን ክሊኒክ ይዘሻት ሂጅ እሽ" አልካት ነቢም ደንገጥ ብላ " ሀዩ አሞሻል እንዴ?" አለች  ሆዷን በእጀ ስይዝ ነገሩ ገብቷት ነቢ በደስታ ዘለለች፡፡

     ጠዋት ቁርስ ከበላን በኃላ ሀዩንና አክረምን ተሰናብቸ ከነቢ ጋር ጉዟችንን ወደ ቃሊቲ አመራን፡፡ እዛ ደርሰን መኪና ላይ አሳፍራኝ ነቢ ጋር ተሳስመን ተለያየን፡፡

መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር አለሜ የፃፈልኝን ደብዳቤ ማንበብ ጀመርኩ፡፡  አግቢኝ አግቢኝ አግባኝ የሚለው ቃል ደጋግሞ በውስጤ ያቃጭላል፡፡ አለሜ ለኔ ብርታቴ ሁሉ ነገሬ ነው በአዲስ መንፈስ ብሩህ ተስፍን ሰንቄ ከአለሜ ጋር አብረን ለመኖር የቀሩንን ቀናት አንድ ብየ ቆጠርኩ፡፡ አለሜ ፍቅሩ በልቤ ትዝታው በአምሮየ ላይጠፍ በደማቁ ተፅፏል፡፡   
       ያሳለፍናቸው ቀናት አብረን የምንኖርበትን ቀን እንድንናፍቅ አድርጎናል፡፡ ወደፊት ስለሚኖረን ሂወት እያሰብኩ በሀሳብ ሽምጥ ጋለብኩ፡፡ ጠረኑ አሁንም አፍንጫየ ላይ አለ ፈገግታው ፊቴ ላይ ነው ደስ በሚል የሀሳብ ሰመመን ያንን አሰልች ጉዞ ሳላውቀው ደረስን፡፡

#Part 1⃣5⃣

ይ.......ቀ....
.....ጥ...........ላ.........ል

▶️ቤተሰብ ሼር አይዘንጉ

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
🍃🍃🍃🍃