ISLAMIC SCHOOL
12.5K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
Facebook እና telegram ላይ 😃😃

🌻ረዥም ስትፅፍ → «አሳጥረው»
🌻አጭር ስትፅፍ → «አብራራው»
🌻ምንም ካልፃፍክ → «ዳዕዋ/ፆለት አድርግ እንጂ?»
🌻ዝም ስትል → « ምከረን እንጂ»
🌻ሐቅ ስትፅፍ → « ለምን ፃፍከው!»
🌻ከተሳሳትክ → «ድሮም‘ኮ ..»
🌻ክረምት ሲሆን → «ወየው ብርዱ»
🌻በጋ ሲሆን → «አረረ ሙቀቱ»
🌷ካላገባህ → « መቼ ነው የምታገባው? »
🌷 ካገባህ → « መቼ ነው ልጅ የምትወልደው?»
🌷ሁለት ልጅ ካለህ→መቼ ነው ሶስተኛ የምትደግመው?»
🌷ትዳርህ ጥሩ ካልሆነ→ፍቺ እያለ ለምን እንዲህ ትሆናለህ
🌷ከትዳር አጋርህ ስትፋታ⇄ ምነው ትንሽ ታግሰህ በነበረ?
- ጥብቅ ሰው ከሆንክ → « ምነው ከሰው አትቀላቀልም? »
- ከሰዎች ተቀላቅለህ ስትጨዋወት → « ምነው ወሬ አበዛህ?»
- ቁምነገረኛ ሰው ከሆንክ → « ምን አይነት ሻካራ ሰው ነህ?»
- በጥቂቱ ቀልደኛ ከሆንክ → «ቁምነገር የለህም»
- አንዳንዴ ቁምነገረኛ አንዳንዴ ቀልደኛ ስትሆን → «የምትጨበጥ ሰው አይደለህም»
በቃ ሁሌም ማውራት ነው!
ስትወፍር → ያወራሉ
ስትከሳም → ያወራሉ
ረዥም ከሆንክ → ያወራሉ
አጭር ከሆንክ → ያወራሉ
መካከለኛ ከሆንክ → ያወራሉ
ደደብ ከሆንክ → ያወራሉ
ጎበዝ ከሆንክ → ያወራሉ
ድሃ ከሆንክ → ያሾፉብሃል
ሃብታም ከሆንክ → ይቀኑብሃል
ስራ ከሌለህ → ይንቁሃል
ስራ ስትሰራ → ያሙሃል
ሰዎች ሁሌም ሙሉ በሙሉ እርካታ አይሰማቸውም!
ሰውን እርሳውና #ፈጣሪህን አስደስት!

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
የጓደኝነት የፍቅር ጥግ
💚💛
ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል፡፡
አለቃውም 'መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ
ህይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም'
በማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡ ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡ ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል ፤
አለቃውም 'ይሞታል ብዬህ አልነበረም?
ለሚሞት ሠው ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ፤' በማለት ይወቅሰዋል፡፡
ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበር ፡፡
አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም
ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሸበት ያለኝን ብነግርህ ትረዳኝ ነበር ፣
አለቃውም 'ምን አለህ?' ሲለው
ወታደሩም
' # እንደምትመጣ_እርግጠኛ_ነበርኩ '፡፡
❖ እውነተኛ ጓደኛ ማለት ሁሉም ሠው ሲሸሽህ እሱ ግን የሚፈልግህ ነው!
ሼር
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
#ምርጥ የአፍሪካዊያን አባባሎች"(ከ ቃረምኩት)

🎖"በችግር ጊዜ ብልህ ሰው ድልድይ ሲገነባ፤ ሞኝ ደግሞ ግድብ ይገድባል!!"(ናይጄሪያዊያን)

🎖 "ሀብት ሲጠቀሙበት እያለቀ ይሄዳል፤ ትምህርት ግን እየተጠቀሙበት በሄዱ ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል!!"(ታንዛኒያውያን)

🎖"እውነቱን ላለማየት ዓይናችንን የምንጨፍን ከሆነ ልንማር የምንችለው ከአደጋ ይሆናል!!"(ኬንያዊያን)

🎖 "ከማሸነፍ ይልቅ በመሸነፍ ወቅት ብዙ ትምህርት ይገኛል!!"(ጋቦናዊያን)

🎖" ሞኝ ጨዋታውን በሚለምድበት ጊዜ ተጨዋቹ ይበተናል!!"(አሻንቲዎች/ጋና)

🎖" ምክር ልክ እንደ-እንግዳ ነው። የሚቀበለው ካገኘ ያድራል፤ የሚቀበለው ካጣ ግን የዚያኑ ቀን ተመልሶ ይሄዳል!!"(ኮንጎዎች)

🎖 " አዋቂዎች በበዙበት ቦታ የአዳማጭ ዕጥረት አለ!!"(የስህዋሊ አባባል)

🎖 " በአንበጣዎች መካከል የሚደረግ ፀብ ለከብቶች መዝናኛ ነው!!"(ቦትስዋናዊያን)

🎖" ትልቅ ወንበር ብቻውን ንጉሥ ሊያደርግ አይችልም!!"(ሱዳናዊያን)
10፦ " በረሮ ዶሮዎችን የመምራት ሃሣብ ካለው፤ ቀበሮን ጠባቂው አድርጎ መቅጠር ይኖርበታል!!"(ሴራሊዮናዊያን)

🎖 " ቤተሰብ ልክ እንደ-ደን ነው። ከሩቅ ሲያዩት ጥቅጥቅ ያለ ሲሆን፤ ሲገቡበት ግን እያንዳንዱ የየራሱ ቦታ አለው!!"(ዛየራዊያን)

🎖" የገንዘብ ስልት ከጦር ስልት ይበልጣል!!"(ካሜሮናዊያን)

🎖" ገንዘብ ማውራት ባይችልም፤ ውሸትን እውነት የማድረግ አቅም ግን አለው!!"(ደቡብ አፍሪካዊያን)

🎖" ከገንዘብ ውስጥ ስንወጣ አዋቂ እየሆንን እንሄዳለን!!"(አይቮሪኮስታዊያን)

🎖" እስኪያወራ ድረስ እያንዳንዱ ሰው ውብ እና ቆንጆ ነው!!"(ዙምባቤዎች)

🎖" ያለሰዓቱ የሚጮኽ ዶሮ መንጋቱን ሳይሆን መታረዱን ያውጃል!!"(ኢትዮጵያዊያን)
የትኛው ተራ-ቁጥር ላይ ያለውን አባባል ወደዳችሁት!? እራሳችሁ ለራሳችሁ መልሱት

Forward ማረግ የሰከንዶች ስራ ነዉ share

Join👇👇
@Islam_and_Science
        @Islam_and_Science
                   @Islam_and_Science
🦋እዉተኛ ታሪክ
😔 #ማን_ነዉ_ጥፋቸኛ 🤔

#Part 6⃣
#ፀሀፊ ☞ ከባለታሪኩ ያለምንም ማስተካከያ የተጨመረ የተቀነሰ ሳይኖረዉ ባለታሪኳ እንደላከችልኝ የቀረበ ታሪክ፡፡

🎖በISLAMIC UNIVERSITY ቻናል የቀረበ

ጊዜው እየሄደ ነው።ስለ ሀሚድ ለ እህቴ ለሀዉለት እነግራታለሁ።2006 6ተኛ ወር ገባ። አንድ ቀን እኔና ቤቴልሄም በ ሀሚድ ጉዳይ በጣም ተከራከርን። ይወድሻል አይወደኝም እያልን ተከራከርን።በመሀል ቤቴልሄም አንድ ሀሳብ አመጣች .......
.........ሌሎች ወንዶች ላይ እንደምናደርገው ለምን የውሸት አንጠይቀውም ??? አለች  እኔም ወዲያው ተስማማሁ። ግን ብር እናሲዝ ተባብለን እኔ አይወደኝም ብየ ቤቲ ይወድሻል ብላ በ50 ብር አሲያዝን
ደብዳቤውም ተፃፈ ጁመአ እለት እንደወትሮው ከ ትምህርት ቤት ስወጣ ሀሚድ ቁሞ የሚጠብቀኝ ቦታ ሄጄ ሰጠሁት። ግን የማልክደው ነገር ቢኖር ለሱ ያለኝ አመለካከት እየተቀየረ መጥቷል ሀሚድን እወደዋለሁ በህልሜ ለራሱ ሀሚድን ሳላይባቸዉ የማይነጉ ለሊቶች የሉም ...ሀሚድ እኔን ባይወደኝ መድረሳ በር አይጠብቀኝም ነበር ብየ አስባለሁ እወድሻለሁ ብሎ ባያቅም ሀሚድ እንደሚወደኝ አልጠራጠርም።

     ጁምአ የዉሸት የፍቅር ደብዳቤዉን ሰጥቸዋለሁ ሁለቱ ቀናቶች ቅዳሜ እና እሁድ እንደምንም አለፉ ሰኞ ደረሰ።ትምህርቱ ምንም አልገባ አለኝ ምክንያቱም የማስበው ሁሉ ስለ ሀሚድ ነው ምን ይለኝ ይሁንን? ልቤን አስጨንቆታል።አይደርሱ የለ ደረሰ እንደተለመደው መድረሳ ሄደን ስንመለስ እዛው ቦታ ላይ ቆሞ አየሁት።ምንም ሳላናግረው ልሄድ አሰብኩ ግን ቤቴልሄም አይሆንም እኔ ወይም አንቺ ማሸነፍ አለብን ...ይወድሻል አይወድሽም የሚለዉን ዛሬ መመለስ አለበት  አለችኝ።
.......እሺ ብዬ ሄድኩ ደፈር ብየ በእጄ ሰላም አልኩት ሰላም አለኝ። በነገራችን ላይ ይሄ ሁሉ ቀን ሰላምታ ስንለዋወጥ አንድም ቀን ተነካክተን አናቅም ሰላምታችን ባይን እና በ አፍ ነው። ሰላምታው ከተለዋወጥን በኋላ በመሀላችን ዝምታ ሰፈነ።
........መተያየት የለ መነጋገር የለ እሺ የለ እንቢ የለ ዝምምምምም እዛው እንደቆምን 20 ደቂቃ አለፈ.....30 ሆነ። ቤቲ በጣም ተናደደች እናም ድምፅዋን ከፍ አርጋ ምንድነው ሲሀም አፍጥኚው አለችኝ።
..........ከዛም ቀና ብዬ ምን አሰብክ ልለው ስል.............. እሺ አለኝ። እእእ ብዬ እንዳልሰማ ስሆን እሺ እወድሻለሁ ብሎ ደገመው።ዞር ብዬ ሳላየው መልስም ሳልሰጠው ወደ ቤቲ ሮጥኩ።በጣም ደንግጫለሁ ልቤ ይመታል።
ቤቲም ምን አለሽ ??ምን አለሽ ?? እያለች ታስጨንቀኛለች።
......እውነቱን ነገርኳትና ማብሸቁን ተያያዘች።አሸነፍኩ አሸነፍኩ እያለች ትጨፍራለች። ሀምሳ ብሩን ቤቲ አሸነፈች ግን 50 ብር መበላቱ ትዝም አላለኝ ግን በሀሚድ መወደዴ እወድሻለሁ የሚለዉ ከአፉ መዉጣቱ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
        ልቤ በጭንቀት ተሞላ ሀሳቤ ሁሉ ሀሚድ ሆነ። ደሞ ሰቃይ ተማሪ ነው ብርቀው ትምርቱ ላይ ተፅእኖ ያመጣል ብዬ ሰጋሁ። ዉሸት ነው ብር አሲዘን ነው የጠየኩህ ልለው ፈራው።ቀና ብዬ ሳየው የሚያበራው ኑሩ የሚጠፋ መሰለኝ ኢማኑ የሚቀንስ መሰለኝ እናም ዝም ብዬ ቀጠልኩ።ሳላስበዉ ፍቅረኛው ሆንኩ።ፍቅረኛውም ሆኜ እንደ ሌሎች ወንዶች ሊያቅፈኝ አለመሞከሩ በጣም ይገርመኝ ነበር።ምን አይነት ኢማን ቢኖረው ነው ብዬ አስባለው። ሁሉ ነገሩ እየማረከኝ መጥቷል። አለባበሴንም አስቀይሮኛል ሂጃብ አስለብሶኛል። በጣም እያፈቀርኩት መጣሁ። ሁሉ ነገር ለሱ ብዬ ተውኩ። አላህ ሊክሰኝ ነው ብዬ አሰብኩ።
   
    ስሜታቸውን ሊያረኩብኝ የፈለጉት ወንዶች ቂም እንድራሳ የአጎቴ ልጅም ሊደፍረኝ የሞከረዉን እንድረሳ አደረገኝ።ለካ እንደዚህ አይነት ጥሩ አመለካከት ያላቸዉ እንደ እነ ሀሚድ ሰውም አለ ብዬ አሰብኩ። ከማንም እና ከምንም በላይ አፈቀርኩት ሁሉ ነገሬ ለእርሱ አደረኩት በሂወቴ ደስተኛ ሆንኩ። ለ እህቴ ለሀዉለት ስነግራት ደስተኛ ሆነችልኝ።
ስ እንደዚህ እያልኩ ሀሚድ ጋር አልፎ አልፎ ሰላም እየተባብልን  በስልክም እየተደዋወልን ፍቅራችንን እየቀጨን ነዉ፡፡ ሚኒስትሪን ተፈትኜ ትምህርት ጨርሰን ፡፡ ትምህርት ተዘጋ ሀሚድ በትምህርት ደረጃዉ አንደኛ ወጣ፡፡ መድረሳ መቅራቴን አልተዉኩም ሀሚድ ጋር በአካል የምገናኘዉ መድረሳ ስሄድ ብቻ ነዉ ከዛ ዉጭ የምንገናኘዉ በጎረብት ስልክ ደዉሉልኝ እያልኩ ነዉ ፡፡  እኔም የሚኒስትሪ ዉጤቴ መጥፎም ጥሩም የማይባል ነበር ወደ ዘጠነኛ ክፍል አለፍኩ፡፡ ደግሞ በክረምት ቁርአኔን አከተምኩኝ በጣም ደስተኛ ሁኛለሁ ወንድሜም ተደስቷል፡፡ ግን አባቴ ምንም አልመሰለዉም አንቺ ብሎ ዲነኛ እያለ ሞራሌን ይነካኛል፡፡
      ዘጠነኛ ክፍል ደረስኩ 16 አመቴ ሆነ። በዚህ አመት ብዙ ነገር ተለወጠ። ለ 5 አመታት ስማር የቆየሁበት የግል ትምርት ቤት  ቃለ ሂወት የሚያስተምረው እስከ 8ተኛ ክፍል በመሆኑ ዘጠነኛ ክፍልን አማኑኤል አካባቢ የሚገኘው ድላችን ሁለተኛ ደረጃ ትምርት ቤት ገብቻለው።
    ሌላው ደሞ በድብቅ ከአባቴ ደብቄ ስልክ ገዛሁኝ ..ለሀሚድ ማዉሪያ ብየ ይህንን የምናቀዉ እህቴ ሀዉለት ታቃለች ለአባቴ እንዳትናገሪ ብየ አስጠንቅቂያታለሁ፡፡  መድረሳ የምሄደው ሀሚድን ለማግኘት ሁኗል። ምክንያቱም መድረሳ ከቀረው ሀሚድን አላየውም። በጣም አፍቅሬዋለው ከመጠን በላይ። ያለሱ ማስበው ነገር የለም።እናቴ እኳን የሱን ያክል አትናፍቀኝም ። ሰላትም ወቅቱን ጠብቄ መስገድ ጀምሬያለው።በጣም ውድ የሆነች የምወዳት አዲስ ጋደኛም ሰሚራን ይዣለው ። ከቤቴልሄም ጋር ያው ተራርቀናል። ምክንያቱም ዘጠነኛ ክፍልን school of canada ሚባል ትምርት ቤት ገብታለች።
      facebook መጠቀም ጀምሬያለው።ዘጠነኛ ክፍል ሁለተኛ መንፈቅ አመት ተጀመረ። ሀሚድም በማላውቀው ምክንያት ካሁን በኋላ እንዳደውይልኝ አለኝ። እኔም ደነገጥኩ ምነዉ ይሄን ወሬ ባልሰማሁ አልኩ ስልኩን ጆሮ ላይ እንደያዝኩ ደርቄ ቀረሁ..........

ሀሚድ ለምን ይሆን እኔዳደዉይ ያላት ??? በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን

#Part 7⃣

ይ..........ቀ.............,
.......ጥ..........ላ.....................ል


JOIN👇👇👇

4 another channal👇
@Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
እውነተኛ አጭር ታሪክ
…….. አንድ ሀብታም ሰው ዘመናዊ መኪናውን አቁሞ ለጉዳዩ
ገባ ይላል ጉዳዩን ጨርሶ ወደ መኪናው ሲመለስ የአንዱ
ጎማው 4 ብሎኖች ተፈተው ተወስዶበት ያያል ይህኔ
ይበሳጭ እና አከባቢው ላይ ዞር ዞር ብሎ ብሎን ፈልጎ
ያጣል::
ያኔ መኪናውን ተደግፎ በጭንቀት ቆዝሞ ሳለ አከባቢው
ላይ ያለ አንድ " #እብድ" ነገሩን ተከታትሎ ኖራል

🍃ምን ሆነህ ነው ይለዋል ሰውየውም በንቀት አይን አየት
እያደረገ
" የጎማዬ ብሎኖች ተፈተው ተወስዶብኝ ነው እንዳልገዛ
አከባቢው ላይ የለም "።
ይለዋል በብስጭት ስሜት
ይህኔ " እብዱ ነው እንዴ ታዲያ ለምን ከ3 ጎማዎች
አንድ አንድ ብሎን ፈተህ አራተኛውን ጎማ አታስርም "
አለው::
ሰውየውም በመገረም ሀሳቡ በጣም አስደሰተው
እንዳለውም አደረገ
ግን " እብዱ " ዘዴውን ነገሮት ሊሄድ ሲል
ሰውየው
" ቆይ አንተ "#እብድ "አይደለህ እንዴ አንዴት ይህ ሀሳብ
ሊመጣልህ ቻለ ይለዋል "
"እብዱም" ቀበል አድርጎ
"ታዲያ እኔ " እብድ ነኝ እንጂ #ደደብ አይደለሁም"
ብሎ ይመልስለታል ፡፡
ዝቅ በል ዝቅ ስትል ከፍ ትላለህ ተናነስ ራስህን አትቆልል
ሁሌም እኔ አዋቂነኝ አትበል፡፡👌👌

SHARE

🍃ISLAMIC SCHOOL CHANNAL🍃

       `JOIN`
@Islam_and_Science
         @Islam_and_Science
             @Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎖🎖ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ስለ እስር ቤት ያሳለፈዉ እያሳቀን ሲተርከዉ እንዴት ደስ ይላል😂😂 ተወልጄ ያደኩት ደሴ ከተማ ነዉ፡፡ በበፊቱ መንግስት አሸባሪ ነበርኩ አሁን ግን አልሀምዱሊላህ፡፡ ማንዴላም አሸባሪ ነበርክ ተብሏል ግን ለመሀበረሰቡ ለሀገሩ ግን ታጋይ ነዉ፡፡እኔ ማእከላዊ ያሰቃዩኝን አዉፍ ብያለሁ
📌በሒወታችን በሚገጥሙን ፈተናዎች ማለፍ መታገስ መቻል አለብን፡፡

4 ወር ጨለማ ቤት ዉስጥ ነዉ ያሳለፍኩት ይለናል ፡፡ ዉዱ ኡስታዛችን አቡበከር አህመድ ሁሌም ቢሆን እንወድሀለን ፈገግታህ ቀልድህ በጣም ያስደስተናል አቡኪ፡፡

✔️ባለፈዉ Arts tv ላይ ተጋብዞ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት ሙስሊሞችም ክርስቲያኖችም በተሰበሰቡበት ስለ እስር ቤት ስለ ሂወት ተጠይቆ የመለሰዉ መልስነዉ፡፡ ወላሂ ሙሉዉን program በArts tv አይቸዋለሁ ወላሂ ክርስቲያኖቹ ለራሱ በአነጋገሩ ሲገረሙ ነበር፡፡ ክርስቲያን ወንድሞቻችን እኛ ሙስሊሞች አርአያ ከሆን ወደ ኢስላም የማይመጡበት ምንም ምክንያት የላቸዉም፡፡
ሁላችንም እናዳምጠዉ አቡበከር አህመድ እያሳቀ እየቀለደ ነዉ የሚያስተምር ነዉ እንጂ እንደ አንዳንድ ኡስታዞች እየተሳደበ እያንቋሸሸ አይደለም ..
📌 አሁን አንዳንድ ኡስታዝ ከቅርብ አመት በፊት የመጡ እንኳን ክርስቲያኑን ወደ ኢስላም ሊያመጡ ቀርቶ ኢስላም ወንድማማቾች አንድ እንዳንሆን እየተሳደቡ በተከታዩ ኡማ ላይ ብዥታ ፈጥረዋል፡፡ ሙስሊም ወንድምህን ስደብ ያለዉ ማን ነዉ ከየትኛዉ ሀዲስ ቁርአን የተገኘ ነዉ ???ኢስላም የተስፋፋዉ ሙስሊሞች በሚያሳዩት ጥሩ ስነምግባር እንጂ ወገኑን እየሳደበ እያንቋሸሸ አይደለም፡፡👌👌👌 አርባ አራት ነጥብ፡፡

       JOIN
@Islam_and_Science
         @Islam_and_Science
  
የህልም ባሌን አኘሁት የሚለዉ አስተማሪ የሆነ የፎዚያ ሙሀመድ በቻናል ተፓስቷል ግን የተፓሰተዉ ብዙ ተከታታይ በሌለበት ጊዜ ነበር፡፡

ይፓሰት አላነበብኩትም🤙🤙🤙

አንብበንዋል አይፓሰት👌👌👌

አሁኑኑ ድምፅ ይስጡ፡፡
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

            #ክፍል 1⃣

#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal
         ኢማን እባላለሁ ተወልጀ ያደኩት በኮምቦልቻ ከተማ ነው ለቤተሰቦቼ የመጨረሻ ልጅ ነኝ አባቴና ታላቅ ወንድሜ ሷልህ በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል እናቴ የቤት እመቤት ነች ቤተሰቦቿን መንከካከብ ከስራወች ሁሉ በላጭ ነው ለእናቴ ቤት የመጨረሻ ልጅ በመሆኔ ሁሉም ይሳሱልኛል የምፈልገው ምንም ሳይጓደል ይሟላልኛል አባቴ ኢማኔ የኔ ኢማን ብሎ ይጠራኛል ወንድሜ ትንሻ እናቴ ደግሞ ስስቴ ብላ ትጠራኛለች፡፡
      ........ብቻ ሁሉም በራሳቸው ፍቅራቸውን በሚገልፅላቸው ቃላት ይጠሩኛል እኔ በባህሪየ ተጫዋች እና ተግባቢ ነኝ ኩርፊያ ብሎ ነገር አልፈጠረብኝም ሁሌም መሳቅ አመሌ ነው ነገሮችን በቀጥታ አመጣጣቸው አምኘ እቀበላለሁ ሰው ይጎዳኛል መጥፎ ነገር ያደርገኛል ብየ አላስብም፡፡ ሁሉንም ሰው በአንድ አያለሁ እናቴ ታዳ እባክሽ ሰው አትመኝ እንደራሰሽ አድርገሽ አታሥቢ ሰው አይታመንም ትለኛለች እኔ በውስጤ ክፋት ከለሌ ከክፉ ነገር ጠባቂ አሏህ አለኝ እላታለሁ፡፡
       .......እናቴም አላህ ይጠብቅልኝ  ስትል ዱአ ታደርግልኛለች ሰወችን ተግባቢ ብሆንም ከሁሉም አብልጨ የምወዳቸው ጓደኞች አሉኝ ኢክራም ነቢያትና ሀያት ይባላሉ፡፡ ኢክሩ ጋር አንድ ላይ ነው ያደግነው ከልጅነታችን ጀምሮ አንዳይነት ልብስ አንዳይነት ምግብ በልተን ነው ያደግነው ኢክራም እዚህ ቀረሽ የማትባል ሁሉን አሟልቶ የሰጣት ቆንጆ ነች ,,,,,,,,,የተስተካከለ ተክለ ቁመና ያላት የፊቷ ጥራትና ቅላት ሊፈርጥ የደረሰ እንኮይ ይመስላል ከመልከ መልካምነቷ ባሻገር ደግሞ የመልካም ሥነምግባር ባለቤት መሆኗ ውበቷን የጎላዋል እንካን በወንዶች በሴቶችም ዘንድ ተወዳጅ ነች፡፡ ኢክሩ ለቤተሰቦቿ ሶስተኛ ልጅ ነች ከሷ በታች ታናሽ ወንድም አላት አይመን ይባላል አይመን የ5አመት ልጅ እያለ የኢክሩ አባት ሞተ አባቷም እንደሞተ እናቷ ወ/ሮ መሬማ የዋዛ አልነበረችም ለልጆቸ  ችግርን አላሳይም በሚል ቁርጠኛ አቃም የበረሀ ተመላላሽ ነጋዴ ሆነች ልጆቿን ያለምንም ችግር ፍለጎታቸውን አሟልታ አሳደገቻቸው ኢክሩ እናቷ በርሀ በምትሄድበት ሠአት አይመንን መንከባከብ የሷ ድርሻ ነበር በዚህም ምክንያት አይመንን እጅግ በጣም ትወደዋለች እሱም ከእናቱ አብልጦ ኢክራምን ይወዳል፡፡     
     ሁለተኛዋ ጓደኛየ ደግሞ ነቢያት ትባላለች፡፡
ነቢ ከቆንጆወች ተርታ የምትመደብ የቀይ ዳማ የፊት ቀለም ያላት ረዘም ያለች እንስት ነች ብዙ ሰወች እየና ነቢን በመልክ ያመሳስሉናል ነቢ ወግ አጥባቂና ተጠራጣሪ ነች ለትንሹም ለትልቁም ነገር ትኩረት ሰጥታ ትመረምራለች በቸልተኝነት ነገርን ማለፍ አይሆንላትም ለምን እንዴት ሆነ ብላ መጠየቅ ታበዛለች የነቢ አባት የፍርድ ቤት ዳኛ ነው ምናልባት ከአባቷ ተጣብቆባት  ይሆን አናውቅም ለሁሉም ነገር ምክያትና ማስረጃ ትፈልጋለች ፡፡
      ሶስተኛዋ ደግሞ ሀያት ትባላለች ሀዪ እናት የላትም እናቷ በልጅነቷ ነው የሞተችው አባቷ ነው እናትም አባትም ሆኖ ያሳደጋት እንደ አይኑ ብሌን ይሳሳላታል ምንም ነገር ፈልጋ አያሳጣትም ሀዪም ለአባቷ ልዪ ፋቅር አላት ህይወትን የሰጠኝ በዚች ምድር የሚኖርልኝ የምኖርለት አባቴ ብቻ ነው ትላለች የሀያት አባት ይማም የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ አለው የእለት ገቢ ስለማያጣ ጥሩ ኑሮ ይኖራሉ፡፡ ሀዪ ሲበዛ   ለሰው አዛኝ ሩህሩህና የዋህ ልብ አላት ሰወችን ያለአንዳች ጥቅም ለአሏህ ብላ መውደድ ትችላለች ግን ተፈጥሮዋ ሁኖ ስታወራ በጣም እየጮኸች እና እየፈጠነች ነው በዚህም የተነሳ እስኪ ዝም በይ ድምፅሽን ቀንሽ  የተባለችበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡   
      አስታውሳለሁ የ12ተኛ ክፍል በተማሪወች ሆነን በስፖርት ክፍለ ጊዜ ዬናስ ከማባል ልጅ ጋር አትጬሂብኝ ብሎ ሰድቧት ተጣሉ መምህሩ ተቆጥቶ አባረራቸው እኛም ከመምህሩ  ጋር ለማስታረቅ ልመና ጀመርን ወላጅ ሳታመጣ አትገባም ብሎ እምቢ አለ እክራም እንደምንም ለምና አስታረቀቻቸው እና ወደ ክላስ ስንሄድ ኢኮኖሚክስ መምህራችን ብርሀኑ ገብቶ ማስተማር ጀምሯል እሱ ከገባ በኃላ በር አንኮኩቶ መግባት የማይታሰብ ነው፡፡    
    ገና ቀድሞ ክላስ ከመጀመሩ በፊት አስጠንቅቆናል ከገባሁ በኃላ ማንም እንዳይመጣ በዛው ይቅር ብሎ አስጠንቅቆናል ስለዚህ ክፍለ ጊዜው እስከማያልቅ ውጭ ላይ መቀመጥ ግዴታ ነው ነቢ ጎበዝ ተማሪ ነች በትምህርት ቀልድ አታውቅም አሁን ክላስ ባለመግባቷ ትምህርት እያለፋት ስለሆነ ተናዳለች ምናለ ባትጮሂ ዝም ብትይ ኖሮ ይሄው ለኛም ተረፍሽ እያለች ስታጉመተምት በቃ እሥኪ ዝም በይ 40 ደቂቃ አይደል 25 ደቂቃ ቀረው ብየ ዘወር ስል......

#Part 2⃣

ይ.......
..........ቀ..........ጥ
......ላ........................ል

SHARE


       JOIN
@Islam_and_Science
         @Islam_and_Science
             @Islam_and_Science
1
ልብ የሚነካ ክስተት...
ሳይክል ሲነዳ መሬት ላይ የነበረችን ወፍ የገጨው ይህ
ህፃን በአቅራቢያው ወደ ሚገኛው ሆስፒታል ወስዶ ኪሱ ውስጥ የገኘውን ገንዘብ ሰጥቶ ዶክተሩን አክማት ብሎታል።
ዶክተሩም በአይኔ ያየሁት እጅግ ምርጡ ድርጊት ሲል
ተናግሯል።
ይህ ደግ ህፃን ክብርም ፍቅርም ይገባዋል

 ምንጭ:-Mufti Menk fan Reminders
ንፁህ ልብ የህፃናት ሰውነት ውስጥ በብዛት ይገኛል..

SHARE


       JOIN

         @Islam_and_Science
             @Islam_and_Science
🦋እዉተኛ ታሪክ
😔 #ማን_ነዉ_ጥፋቸኛ 🤔

#Part 7⃣
#ፀሀፊ ☞ ከባለታሪኩ ያለምንም ማስተካከያ የተጨመረ የተቀነሰ ሳይኖረዉ ባለታሪኳ እንደላከችልኝ የቀረበ ታሪክ፡፡

🎖በISLAMIC UNIVERSITY ቻናል የቀረበ

     facebook መጠቀም ጀምሬያለው።ዘጠነኛ ክፍል ሁለተኛ መንፈቅ አመት ተጀመረ። ሀሚድም በማላውቀው ምክንያት ደዉሎ ከአሁን በኋላ እንዳደውይልኝ አለኝ።ስልኬን በጆሮየ እንደያዝኩት ደንግጬ ቀረሁ.......
.......እንዴ ምን አጠፋሁ ምን አረኩህ ሀሀሀሚድ አለውኩኝ እየተንተባተብኩኝ
........እሱም በቃ ነገርኩሽ ከአሁን ቡሀላ እንዳደዉይ ብየሻለሁ ከአሁን ቡሀላ አንቺን አልፈልግሽም ከሒወቴ ዉጭልኝ ትደዉይ  እና  ከባድ ፀብ ነዉ የምንጣላዉ እንደዚህ በአለንበት በሰላም እንለያይ ብሎ ስልኩን እጆሮየ ላይ ጠርቅም አርጎ ዘጋብኝ፡፡
    ከሀሚድ ተለያይቶ መኖር ሞት መሰለኝ ማመን አቃተኝ። ስልክ እየደወልኩ መለማመጥ ማልቀስ ጀመርኩ። ቢያንስ እንኳ ምክንያቱን እንዲነግረኝ እያለቀስኩ  ለመንኩት ምንም መልስ አላገኘሁም። ለሀሚድ አልፈልግሽም እንዳደዉይ ስላለኝ ያለቀስኩት እምባ ለጌታየ አሏህን ፍራቻ ባለቅስበት እንኳን የኔን ለሌላ ሰዉ ጌታየ እንዲምረው የሚበቃ እንባ ለሀሚድ አፈሰስኩ፡፡ አዲሷ ጓደኛየ ሰሚራም ከጎኔ ሁኗ ታፅናናኝ ይዛለች...... አላህ ላንቺ አስቦ ነው ፍቅረኝነት ምን ያረጋል?? ሀራም ነው ይቅርብሽ እንዳውም ተገላገልሽ ...እሺ እሰቢዉ እስኪ ሀሚድ ጋር ሁነሽ ዚና አልሰራሽም አላህ ጠበቀሽ ታዳ አንቺ እኮ እድለኛ ነሽ፡፡
እድለኝነትሽ አንድ ከሀራም ቦይ ፍሬንድ ተገላገልሽ
ሁለት ደግሞ እሱ ጋር ዚና ሳሰሪ ሳትሳሳሚ ወደ መጥፎ ቦታ ሳትሄጂ አላህ ሲጠብቅሽ ነዉ...አንቺ ማልቀስ የለብሽም ተስፋ መቁረጥ የደካሞች ነዉ ......ሀሚድ ቢሄድ አንቺ ዲን ካለሽ ስነ ስርአት ካለሽ አንቺ ለወደፊት ለትዳር ብቁ ነሽ እያለች ሞራል ሰጠችኝ።

      ሰሚራ በጣም ኢማን ያላት ልጅ ናት ጅልባብ ትለብሳለች ዝሁርም በጀመአ እንዳያመልጠን ይዛኝ መስጊድ ትሄዳለች።ብቻ በ ሂወቴ ትልቅ ሚና ተጫውታለች።እነ ቤቴልሄም ቢሆኑ ወይ እንሸዉደዉ ወይ እንበቀለዉ እያሉ የተለያዩ ወንጀሎችን ልሰራ እችል ነበር የጓደኛ ጥሩ መሆን ዲነኛ መሆን በጣም ጠቀሜታ አለዉ እኔም ጓደኛየን ሰሚራን መምሰል ጀመርኩ፡፡ አሁን ላለሁበት ሁኔታ ሚናው የሰሚራ  ነው።
      ሀሚድን ለመርሳት ወሰንኩ። እሱን ላለማየት ስል መድረሳም አቆምኩ። በትምርቴም ደህና ነበርኩ። አልሀምዱሊላህ በ ሰሚራ ምክንያት የሱና ፆም ሰኞ እና ሀሙስ በተረፈም የተለያዪ የሱና ፆሞችን መፆም ጀምሬያለው ፡፡ ሰሚራን ከአገኘሁ ቡሀላ በአስተሳሰብም በዲንም በአመለካከትም  ተለውጫለሁ

   ግን በሀሚድ የተነሳ ወንድን መበቀል ደስ ይለኛል የወደፊትም ሀሳቤም አላማየም ነዉ።
  የፈተና ሰአት ደረሰ ዘጠነኛ ክፍል አይደለሁ ፈተና ተፈተን ፡፡ ዉጤት ስቀበል በጣም ጥሩ ዉጤት ነበር ለሰሚራ አሳይቻት በጣም ተደሰተች፡፡ ካርድ መቀበያችን ደረሰ ትምህርቴን አልሀምዱሊላህ በጥሩ ዉጤት ነበር ወደ 10 ክፍል የተዘዋወርኩት፡፡ በክረምት ሰፈር የሚገኝ ኪታብ የሚቀሩ ልጆች ጋር አብሬ በመቅራት አሳለፍኩ ሰሚራ ጋር አልፎ አልፎ በአካል እንገናኛለን በስልክ እናወራ ነበር፡፡ 

   2008 ሆነ 17 አመቴ የ 10ኛ ክፍል ተማሪ ሆንኩ። ግን ፀባዬ እየተበላሸ መጥቷል። ሀሚድ ትዝ ባለኝ ቁጥር እናደዳለሁ ወንዶች ሁሉም እንደ ሀሚድ ናቸዉ ብየ እራሴን አሳመንኩት፡፡
     ሰሚራ ሳታየኝ ሳሰማ የቀራሁት ኪታብ ሊያግደኝ አልቻለም ....ብዙ የክላስም እኛ ትምህርት ቤት የሚማሩ ወንዶችን  እቀርባቸዋለሁ ፍቅር ለማስያዝ እሞክራለው በፍቅር ወንድን ልጅ ለማጥመድ ለኔ ቀላሌ ነበር፡፡ በእኔ ፍቅር መያዛቸዉን ሳረጋግጥ ከዛም ሀሚድን እኔን እንዳደረገኝ አልፈልጋችሁም አንተን እኮ እንደወንድሜ ነዉ የማይህ እንዴት እወድሻለሁ ትለኛለህ እያልኩ በፍቅር አሻቸዉ አሰቃያቸዉ ነበር ። እኔዉ ቀርቤ እኔዉ ፍቅር አሲዣቸዉ እንደገና የማይህ እንደወንድሜ ነዉ እኮ እያልኩ ብዙ ወንዶችን መበቀል ጀመርኩ፡፡  በዚህ ጉዳይ ከሰሚራ ጋር ሁሌ እንጣላለን።
.... አንቺ አላህን ፍሪ እንደዚህ አታድርጊ ብትለኝ አረ በጭራሽ የአሁን ወንዶችንማ በፍቅር እያፍተለተሉ እንደ ቁንጫ አሽቶ መጣል ነዉ እላታለሁ፡፡ የ10 ክፍል ቆይታየ ወንዶችን ፌክ መስራት በፍቅር አሲዞ እምቢ ማለት ሁኗል ስራየ፡፡
     የ ብሄራዊ ፈተና መፈተኛ ጊዜ አቅራቢያ አካባቢ በሆነ ስልክ በማላቀዉ ተደወለልኝ።
ሄሎ....አቤት?  ይቅርታ አላወኩህም.......ግን ድምፁ አዲስ አሎነብኝም......

እእእእእ አንተ አለህ እንዴ? ዛሬ በምን ትዝ አልኩ? ይገርማል....... ብዙ ካወራን ቡሀላ ወሬው አለቀ ስልኩ ተዘጋ።

ለሲሀም ማን ይሆን የደወለዉ ??? በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን
#part 8⃣
ይ..............ቀ......
.........ጥ............ላ..............ል

ዉድ የቻናል አባሎቻችን ምን ያህል ሰዉ እንደሚከታተል ለማወቅ እና ቀጣዪን ክፍል አሁኑኑ ቶሎ ለማግኘት በማያስከፍለዉ Like(ላይክ)🤙🤙 በማረግ አሁኑኑ ይግለፁ


4another channal👇
@Islam_and_Science

JOIN👇👇👇
@IslamisUniverstiy_public_group
@IslamisUniverstiy_public_group
#አስደናቂ_እውነታዎች_ስለ_እርግዝና

➊. አንዲት ሴት በእርግዝናዋ አጋማሽ ከበፊቱ ከነበራት የሰውነት ደም መጠን ከግማሽ በላይ ይጨምራል፡፡
ከዚህም ጋር የልብ መጠን እንዲሁም የእግር ቁመትም እንዲሁ ይጨምራል፡፡

➋የእርጉዝ ሴት ማህፀን ዘጠነኛ ወር ሲደርስ ከእርግዝና በፊት ከነበረው መጠን 500 እጥፍ ይጨምራል፡፡

➌ ጨቅላ ህፃናት እናታቸው ማህፀን ውስጥ ሆነው ያለቅሳሉ፡፡ ነገር ግን የሽንት ውሃ ውስጥና ብዙ የቅባትና የጡንቻ ክፍል ስላለ ወደ ወጪ አይሰማም ::

➍. እርጉዝ ሴት በእርግዝና ጊዜዋ ቃር ወይም የጨጓራ ማቃጠል ከበዛባት የምትወልደው ልጅ ፀጉር በጣም ብዙና
ወፍራም ይሆናል፡፡ ይህ የሚሆነው ፀጉር የሚያበዛው ሆርሞን የጨጓራ ቱቦንም ስለሚያላላ የጨጓራ አሲድ ወደ ላይ
እንዲመለስ ስለሚያደርግ ነው፡፡

➎. አንድ የተረገዘ ህፃን ገና የ5 ወር እርግዝና ላይ አይነምድር ማምረት ይጀምራል፡፡ ነገር ግን ወደዉጪ ሳያስወጣ እስኪወለድ ድረስ
ይቆይና ከተወለደ በኋላ በ1-2 ሰዓት ውስጥ ያስወግዳል፡፡

➏. ጨቅላ ህፃናቶች ገና እናታቸው ማህፀን ውስጥ ሳሉ እናታቸው የምትበላውን ምግብ ጣዕም መቅመስ ይችላሉ በተደጋጋሚ
አንድ ነገር ከተመገበችም ከተወለዱ በኋላ ያንን ምግብ የበለጠ ሊወዱ ይችላሉ፡፡

➐. ይህ ብቻ አይደለም ከተረገዙ ወደ ሰባት ወር ላይ ሲደርሱ ማሽተትም ይችላሉ፡፡ እንደውም የሽንት ውሃ ውስጥ ስላሉ በተለይ
መጥፎ የሆነ ሽታ ሊረብሻው ይችላል፡፡

➑. ጨቅላ ህፃናት ማህፀን ውስጥ የእናት አባታቸውን ድምፅ መለየት ይችላሉ፡፡ ከፍ እያሉ ድምጾች ሊያስደነግጣቸው ይችላል፡፡

➒. አንዲት ሴት የመውለድ ወሯ ሲገባ የጡቶቿን ጫፎች በማሸት ምጧ እንዲመጣ ያለውን እድል መጨመር ትችላለች ይህ ጡትን
ማሸት (oxitosin) የተባለውን ሆርሞን ስለሚጨምር በዝያውም ምጥ ስለሚያመጣ ነው፡፡

➓. እርጉዝ ሴቶች ወደ ጭንቅላታቸው የሚደርሰው ኦክስጅን መጠን ለህፃኑ ስለሚካፈልና በመጠን ስለሚቀንስ የመርሳት ችግር ሊያጋጥማት ይችላል፡፡

➊➊. Progestrone የሚባለው በእርግዝና ጊዜ በብዛት የሚመረት ሆርሞን አንዲት እርጉዝ ሴት ብዙ ስራ አንዳትሰራና የተረገዘውን
ህፃን በንጥረነገርም ሆነ በብዙ እንቅስቃሴ እንዳትጫጫነው እንቅልፍና መደካከም እንዲበዛ ያረጋል፡፡

➊➋. አንዲት እርጉዝ ሴት ምግብ ስትበላ ምግቡ ተጣርቶ ቀድሞ ህፃኑን ከበላ በኋላ ነው ንጥረነገር ለሷ የሚደርሰው፡፡ ስለዚህ እሷ ብትመገብም መጀመሪያ የሚጠቀመው ህፃኑ ነው፡፡

➊➌. እርጉዝ ሴቶች ፀሃይ ቆዳቸውን ሲነካቸው ቶሎ ያጠቋቁራቸዋል፡፡ ስለዚህ ከፀሀይ እራሳቸውን ቢከላከሉ ይመረጣል፡፡ ነገር ግን vitamin D የሚባለውን ከፀሀይ የሚገኘውን ንጥረነገር ከወተት እና እንቁላል ማግኘት ይገባቸዋል፡፡

➊➍. ብዙ ያልተለመደ ቢሆንም አንዳንድ ባሎች ሚስታቸው በእርግዝና ጊዜ የሚያጋጥማት ህመሞች ሊሰማቸው ይችላል፡፡ አንደ የሆድ መወጠር, ወደ ላይ ማለት, እንዲሁም ሆድ ቁርጠትን ጨምሮ ሚስታቸው ብዙ የሆነ progestrone መጠን ስለምታመርት
እንዲሁም ይህ በቆዳ ሊተን ስለሚችል ወደሱ ስለሚተላለፍ የሚከሰት ነው፡፡

➊➎ ጨቅላ ህፃናት በእርግዝና ጊዜ ህልም ያያሉ፡፡ ምን አይነት ህልም እንደሚያዩ ማወቅ ባይቻልም (REM) የሚባለው የእንቅልፍ የመጀመሪያው ክፍል ፍጥነት ያለው የአይን እንቅስቃሴ ስለሚታይ ህልም አንደሚያዩ ያረጋግጣል፡፡

➊➏ ብዙ እርጉዝ ሴቶች የተለየ የምግብ አምሮት ቢኖራቸውም አንዳንዴ በተለየ ሁኔታ ምግብ ያልሆኑ እንደ ቀይ አፈር፣ ሳሙና፣አመድ እና አሸዋ ያሉ ነገሮች ማሽተትና መብላት ሊያምራቸው ይችላል፡፡ ይህ ሲከሰት ዶክተሮትን ማማከር ተገቢ ነው፡፡

➊➐ አንዲት እናት በምጥ ከወለደች በኋላ አስከ አንድ ቀን ድረስ ምጡ ላይቆም ይችላል፡፡ ከእናት እናት መጠኑ ቢለያይም የማህፀን መድማትን ለመከላከልና ማህፀን ቦታው እንዲመለስ ለማድረግ ምጡ ከወለደች በኋላ ለጥቂት ጊዜያት ሊቆይ ይችላል፡፡

➊➑ የጨቅላ ህፃናት መስሪያ ክፋዩች(Cells) በእርግዝና ጊዜ ወደተለያዩ የእናት ክፍሎች ይሄዳሉ ወደ ልቧ፣ኩላሊት፣ቆዳ፣ጡንቻና ሳምባዋ ገብተው እሷንም ይጠግናሉ፡፡ ስለዚህ የእያንዳንዱ ልጆቿ ቅሪት ክፋዩች ውስጧ በህይወቷ ሙሉ ይኖራል ማለት ነው፡፡
ምንጭ ☞ የዶክተር አለ8809ቴሌግራም ገፅ:

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

            #ክፍል 2⃣

#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal
      እሥኪ ዝም በይ 40 ደቂቃ አይደል 25 ደቂቃ ቀረው ብየ ዘወር ስል ቢንያም ወደኛ እየመጣ አየሁት ሳላስበው ቢንያም ብየ ድምፅ አወጣሁ ሁላቸውም ደንግጠው አይኔን ተከተሉ ቢንያም ማለት ፈረቃ መሪ ነው ምን እንዳደረግነው ባናውቅም ግን በኛ አብሮነት ይናደዳል ከ9-12 አንድ ክፍል መማራችን ለሱ ህመም ሆኖበት ለማለያየት ያልሞከረው ነገር አልነበረም ስላልተሳካለት እንጅ ዛሬ በግላጭ ሥ፡ስላገኘን ደስ ብሎታል እየሳቀ ወደኛ መጣ እሽ ጎረምሶቹ የሚያረጋችሁን አሳጣችሁ አይደል ብላችሁ ብላችሁ ክላስ ዘግታችሁ መቀመጥ ጀመራችሁ ብሎ አፈጠጠብን ፡፡
        ......ኢክራም ምክንያታችንን ነገረችው
...........እሱ ግን እጀ ገባችሁ አለቀላችሁ ብሎ ወላጅ ሳታመጡ እንዳትገቡ ብሎ አባረረን የባስ አለ አገርህን አትልቀቅ ማለት ይሄ ነው ነቢ ለ1 ክፍለ ጊዜ ሲያንገበግባት ጭራሽ ቀሪውንም ላትማር ነው
...... ነቢ አስተዛዝና መናገር ሞገረት ግን እዝነትን ሳይሆን ስድብን አተረፈች ዘልዛላ ፍላጎት ቢኖርሽማ እዚህ አትዘፈዘፊም ነበር ዱርየ ስለሆንሽ እንጅ ብሎ ሲናገር ነቢ ተናዳ ዱርየ አለመሆኔን ካንተ ውጭ ማንም ይመሰክራል አንተም ታውቃለህ ማመን አትፈልግም እንጅ ብላ እሷም በተራዋ አፈጠጠችበት .......በንዴት ፊቱ ተለዋወጠ ሁኔታው ስላላማረኝ በቃ ቦርሳችንን እናምጣ ብየ መራመድ ጀመርኩኝ አወ ተከተሏት እጀ ገብታችኃል ማን እንደሚያስጥላችሁ እናያለን ብሏ ዛተብን ..........
          ፓርሳችንን  ይዘን ከግቢ ወጥተን ወደነ ሀዩ ቤት ሄድን አባቷ ሱቅ ስለሚውል ቤት ማንም የለም ምሳችንን በልተን ስንጫወት ውለን በትምህርት መውጫ ሰአት ወደየቤታችን ሄድን በሚቀጥለው ቀን ክላስ ገባን ግን ገና 
...... በ1ኛው ክፍለ ጊዜ መጣና ወላጅ ሳታመጡ አትገቡም ብሎ አባረረን የኢክሩ እናት በርሀ ሥለሆነች ወደ ሱቅ ሄደን አባቴን ወላጅ ተብለናል ብየ አብረን ወደ ትምህርት ቤት ተመለስን ቢሮ ገብተን መምህሩ ስለኛ የማይታመን ነገሮችን ለአባቴ ይነግረው ጀመር አባቴ በንዴት ፊቱ ሲቀላ ይታየኛል   
       እናቴ ለካ ሠው ሁሉ እንዳንች አይደለም ያለችኝ እውነቷን ነው ውሸቱስ ከየት ነው የሚመጣለት የምሰማው የውሸት ዜና አፌን አስከፍቶ አድርቆኝ ቀረ፡፡
......አባቴ ንዴቱ ጣራ ነካ በጥፊ መታኝ አይኑን አፍጥጦ ወደ ኢክራም ዞረ በቃ አደጋችሁ የእድገታችሁ ፍሬ ይሄ ነው!!!ለኛስ የልፍታችን ዋጋ ክፍያው ይሄ ነው!!! እያለ ይጮሀል ኢክሩ የምትናገረው ጠፍባት አንገቷን ደፍታ ዝም አለች እኔ ከአይኔ እንባ ያለማቆረጥ ይፈሳል አባቴ ለመጀመሪያ ጊዜ መታኝ ያስለቀሰኝ ግን ከጥፊውም በላይ አባቴ እኔን አለማመኑ ነበር ......የተነገረውን አምኖ እኔን መታኝ እንባ መልስ ይሰጥ ይመስል ከመናገር ይልቅ ማልቀስን መረጥኩ እንደዛ ሁኜ ሲያየን ደስታው ፊቱ ላይ ያስታውቃል ፡፡
      አሁን አትነፍረቂ ቀድሞ ነበር መጠንቀቅ ተመልከች ባንች አባትሽ ምን ያህል አንገቱን እንዳስደፋሽው አሳፍሪ አለኝ ........ያአሏህ የሠው ልጅ እንዴት በውሸት ይኖራል ልቤን አመመኝ ውሸቱ አንገሸገሸኝ
,,,,,,,,,,,,,በዚህ ሁኔታ ነቢያት ከአባቷ ጋር መጣች ግቡ አንችም አመጣሽ ያችኛዋስ የት ቀረች አለና ቁጭ በሉ ብሎ የውሸቱን ዜና ለነቢ አባት ለመንገር ሲያኮበኩብ በር ተንካካ ሀዩም አባቷን ይዛ መጣች አሁን አራታችንም አንድ ላይ ነን ለሀዩና ለነቢ አባት ለአባቴ የነገረውን ደገመላቸው በጣም ዱርየና አስቸጋሪወች ናቸው ትምህርት አይማሩም በተደጋጋሚ መክረናቸው ከአቅም በላይ ሆነዋል ሁሉም መምህር በነሱ ተማሯል በመምህር ላይ ይሳለቃሉ  ከመማር ይልቅ የነሱ ስራ መምህርን ማሸማቀቅ ነው ከቅማችን በላይ ሁነዋል ፡፡
       አሁን እናንተ ሀላፊነት ወስዳችሁ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ፈርመው ድገሜ ከተገኘ ያለምንም እርህራሄ ይባረራሉ ብሎ ነገራቸው የሀዩ አባት የአባቴ ንዴት ተጋባበት ከጎኑ ብትሆን ኖሮ የኔ እጣ እንደሚደርስባት አልጠራጠርም
............የነቢያት አባት ቆይ ቆይ እስኪ አንዴ እንነጋገር አለና እኛኮ ልጆቻችንን ትምህርት ቤት የምንልከው በናንተ ጥበቃ ስር ናቸው ብለን እንጂ እንዲህ መረን ለቀው ሲጠፉ እናንተ ለምን ቀድማችሁ አላስጠራችሁንም አሁን እያልክ ያለከው ከአቅም በላይ እንደሆኑ ነገርገከን ይሄ ደግሞ እናንተን በጠያቂ ያደርጋችኃል ምክንያቱም ትግሩን ከልጆቻችን ጋር መክረን መፍትሄ እንዳንፈልግ በጊዜ ማሳወቅ ሲገባችሁ ከረፈደ መጨረሻ ላይ ሲደርሱ ተጠራን
.......ለነዚህ ልጆች መጥፍት ትምህርት ቤቱ ተጠያቂ ነው ብሎ ሲናገር ያ ውሸትን እያቀላጠፈ ሲናገር የነበረው ምላሱ አሁን ድመት በላችበት መሰል ዝም አለ ለጠላትህ አርቀህ ጉድጓድ አትቆፍር አንተም ልትገባበት ትችላለህና የሚለው አባባል እውነት ነው አሁን ተራው የሱ ሆነ አይኑ ፈጠጠ ውሸቱ ገባቸው ውሸታምነቱ ስለተጋለጠ ደስ አለኝ መመታቴ ግን አስቆጥቶኛል
..........,.አባቴ አሁን እውነቱ ሲገባው ተፀፀተ አቀፈኝና ወደደረቱ አስጠጋኝ እንዳኮረፍቱት እንዲያውቅ እጅን አንስቸ ከእቅፍ ወጣሁ አባቴ ዝም ብሎ አየኝ  ኢማኔ አለኝ ስሜን ሲጠራኝ ኩርፊያዬ ብን ብሎ ጠፋ
    ..... ልጅ አባቱን አያኮርፍምኮ አለኝ አንተ ያሳደካትን ኢማን ማወቅ ነበረብህ የኔ ኢማን እንደዚህ አይደለችም ሳትል የነገረህን አምነህ መታኸኝ ከጥፊው በላይ ያመመኝ እኔን አለማመንህ ነበር ብየ እቅፉ ውስጥ ገባሁ
............ይቅርታ አድርጊልኝ ብሎ ግንባሬን ሳመኝና አባቴ ጋር ታርቀን ወደ ክላስ ገባን ተማርን ፡፡ ከትምህርት ቤት ስንወጣ

#Part 3⃣

,,,,,
,,,,,,,,,,ይ
,,,,,,,,,,,,,,,,,ቀ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ጥ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ላ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ል
@Islam_and_Science
         @Islam_and_Science
             @Islam_and_Science
💐💐💐
ችግርክን ለሰዉ ለማስረዳት አትሞክር ምክናየቱም ሰዉ የሚረዳህ የችግርህን ጥልቀት ያክል ሳይሆን የመረዳት አቅሙን ያክል ነዉ።

‼️ሰዉ ስለችግርህ ደጋግመህ ብታወራዉ ይሰለችሀል ወይም ይታዘብሀል፡ ደግሞም ሁሉም የራሱ ችግር እንዳለበት አትርሳ። ይሄን ስልህ ግን ችግርህን ደጋግመህ ብትነግረዉ ደስ የሚለዉ ደጋግመህ ብትጠይቀዉ በደስታ የሚሰጥህ ስትጠይቀዉ ሳይሆን ሳትጠይቀዉ ብትቀር የሚቆጣ ሌትም ቀንም የቸገረህን ለምነኝ እሰጥሀለሁ የሚል በችግርህ ጥልቀት ልክ የሚረዳ አምላክ እንዳለህ አስታዉስ

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
🦋እዉተኛ ታሪክ
😔 #ማን_ነዉ_ጥፋቸኛ 🤔

#Part 8⃣
#ፀሀፊ ☞ ከባለታሪኩ ያለምንም እንደተላከልኝ የቀረበ ታሪክ

   እእእእእ አንተ አለህ እንዴ? ዛሬ በምን ትዝ አልኩ? ይገርማል....... ብዙ ካወራን ቡሀላ ወሬው አለቀ ስልኩ ተዘጋ።

ሀሚድ ነበር እንደዛ ስሰድበው እና ስረግመው በሱ የተነሳ ወንዶችን መበቀል የጀመርኩት የነበረው ሀሚድ ደውሎ ሲያወራኝ ሁሉ ነገሬ ተቀየረ።
    
  አደዉይ ያልኩሽ እኔ በፍቅርሽ ተጨንቄ የምሆነዉ ሳጣ እንቅልፍ ሲነሳኝ ነዉ ፡፡ አላስቻለኝም ተረጂኝ እወድሻለሁ ስልክ መደዋወል ካቆምንባቸዉ ቀናቶች ቡሀላ ድምፅሽን ስላልሰማሁ በጣም ጨነቀኝ ብሎ በዛ በዚህ ብሎ አሳመነኝ ፡፡ እኔም አዝኜ ይቅርታ አረኩለት ሀሚድ ደስ አለዉ፡፡
  ሀሚድ ጋር እንደበፊቱ መደዋወል ጀመርን...ከመደዋወላችን ብዛት ተጣልተን የታረቅን አይመስልም፡፡ ፍቅራችንን እንደ አዲስ አደስን ሀሚድን ለማግኘት የሚመቸኝ መድረሳ ስለሆነ ያቋረኩትን መድረሳ መሄድ ጀመርኩ። አሁን አላህ እኔን ሲጠይቀኝ ለቂርአት ነዉ ወይስ ሀሚድን ለማግኘት ብየ ብጠይቀኝ የምመልሰዉ መልስ የለኝም፡፡  ግን ደግሞ ሀሚድ ጋር ስንገናኝ መጨባበጥ ጀምረናል ግን እጅ ለእጅ ብቻ ነዉ መሳሳም ምናምን የለም፡፡ ሀሚድ ደግሞ ሀይለኛ የቡና ሱስ አለበት .......
 
    የሆነ ቀን በ ፌስቡክ እያወራን ምን እየሰራሽ ነው ሲለኝ
.......ቡና እያፈላሁ አልኩት።እውነትም ቡና እያፈላሁ ነበር።እኔና እህቴ ሀዉለት ለብቻችን እየጠጣን ነበር።
.......ከዛም ቀጠል አርጎ ልምጣ? ሲለኝ ምን ችግር አለው ና አልኩት። አይ ዛሬ ይቅርብኝ ነገ እመጣለው አለኝ።ለካ እሱ የምሩን ነው።
    ደንግጬ ለሀዉለት  ነገርኳት ምን ችግር አለው ይምጣ እናፈላለታለን አለችኝ።
እኔ ማትሪክ ለመፈተን እየተጠባበኩ ነው ሀዉለት ማትሪክ ወድቃ ቴክኒክና ሙያ አይቲ እየተማረች ነው።

  እህቴ ሀዉለት  ወደ አዲስ አበባ ከመጣች በኋላ ብዙ ነገሬ ተቀይሯል ዘመዶቼን ታስተዋውቀኛለች። እኔ በልጅነቴ ስለሆነ ወደ አዲስ አባባ የመጣሁት ማንም አያውቀኝም እኔም አላውቅም።
     በነገራችን ላይ የአጎቴ ልጅ ራዉዳ ከ አባቴ ጋር ተጣልታ ከቤት ወታለች ተከራይታ ብቻዋን እየኖረች ነው።የ አክስቴ ልጅ ሀፍሷም ወደ ሻሸመኔ ያለችው እህትዋ ጋ ለ እረፍት ሄዳለች። ቤቱ ያለንበት እኔ ሀዉለት እና አባቴ ብቻ ሁነናል። አይነጋ የለ ነጋ አባቴም ስራ ቦታ ሄደ ሀዉለትም ትምርት ቤት ሄደች። ብቻዬን ቀረሁ።
     ቤቱን አፀዳድቼ ቁርሴን በልቼ ወጥ እየሰራሁ ሀሚድ ደወለ። እየመጣ እንደሆነ ነገረኝ። ረስቼው ነበር ለካ እሱ ቀጠሮውን አክብሯል።
......ቤቱን ማን ያሳይሀል ስለው እንደሚያውቀው ነገረኝ ለካ ተከታትሎኝ ቤታችንን አይቶታል። ከዛም ከጥቂት ደቂቃዎች ቡሀላ እኛ ቤት ደረሰ የጊቢውን በር ከፍቼ አስገባሁት።
.... እኔ ጉዴን አላቅም ቡና ላፍላ ብዬ ስነሳ አንቺን እንጂ ቡና ፈልጌ አልመጣሁም አለኝ።
 እኔም እሺ ብዬ ቁጭ አልኩኝ እናም ማውራት ቀጠልን።
   ሀሚድም ነይ አጠገቤ ቁጭ በይ ይለኛል ባልሰማ ሳልፈው እኔው ጋ ከጎኔ መጥቶ ቁጭ አለ። እቅፉ ውስጥም አስገባኝ ደስተኛ ነበርኩ ግን ሀሚድ  እኮ ሴት አይጨብጥም ምን ሆኖ ነው ብዬ ደነገጥኩ።
....እቅፉ ዉስጥ ሁኜ ወሬያችንን ቀጠልን ከወትሮ በተለየ እንደሚያፈቅረኝ ይነግረኝ ጀመር።
     ልቤ በሀሴት ተሞላ ሌላ አለም ያለሁ መሰለኝ። በሚወዱት ሰው መታቀፍ ደስታ ነው።ህልምም መሰለኝ።ግን ቀስ በቀስ ነገሮች እየተቀያየሩ መጡ።መላ ሰውነቴን ይደባብስ ጀመር እጁን እንደፈለገ ሰውነቴ ላይ ያንሸራትታል።ሁኔታው አላምር አለኝ ከዛም የማይነኩ ቦታዎችን መነካካት ሲጀምር ነው አላማው የገባኝ። .......ከእቅፉ ለመውጣት ታገልኩ እሱም ሀይሉን ጨምሮ አጥብቆ ያዘኝ። እንደ ሌሎቹ ስሜቱን ሊያረካብኝ ፈለገ ።ታገልኩት ታገልኩት..ሀሚድ እኔን በስሜቱ ዉስጥ አስገብቶኝ ይሳስመኝ ይዟል፡፡ በውስጤም ደስተኛ ልሆን አልቻልኩም ፡፡ የአጎቴ ልጅ ሊደፍረኝ የነበረዉ ጊዜ ፊቴ ላይ መጥቶ ድቅን አለ ፡፡ ሰሚራም ስመክረኝ የነበረዉ ምክር በሀሚድ ሞቃት በሆነ የስሜት ትንፋሽ ዉስጥ ሁኜ አስታወስኩ ፡፡አላህን ለምን ይሄ ሁሉ ስቃይ ብዬ ሀሚድ እቅፍ ሁኜ እጠይቀው ጀመር።
     እንደምንም ተፍተልኬ አላህ ብርታት ሰጥቶኝ ከዛ አሳማ መዳፍ አመለጥኩ ሮጬ በሩጋ ቆሜ ከቤቴ ውጣልኝ እያልኩ ጮህኩ ግን ግቢ ውስጥ ማንም ስለሌለ ሚሰማኝ የለም እሱም አላሳፈረኝም ጫማውን አድርጎ ወጣ።
    ማመን አቃተኝ ሰዎች ሁሉ እኔን የሚፈልጉኝ ለስሜታቸው ነው ብዬ አስብኩ። እንዴት ሀሚድ ጥሩ ሰዉ አንገት ደፊ ሴት ቀጥ ብሎ የማያይ አልነበር እንዴ ??? እያልኩ ቁጭ ብየ ማሰብ ጀመርኩ አልሀምዱሊላህ ለሶስተኛ ጊዜ ከአውሬዎች መንጋጋ ጎትቶ አወጣኝ።
    እሱ አላህ ጌታየ ታግሎልኝ እንጂ እኔ በምን አቅሜ እነሱን አሸንፍ ነበር? የዚን ያክል ቆንጆ አይደለሁ ፀባይ የለኝ መልክ የለኝ አቋም የለኝ ግን ለምን እያልኩ እራሴን መጠየቅ ጀመርኩኝ።
   ድንገት ጎንበስ ብዬ ደረቴን ሳየው በደም ተጨማልቋል። በጣም ስናደድ ይነስረኛል። ልብሴን ቀያይሬ ደሜን ታጥቤ ማሰላሰል ጀመርኩ። እንዳዲስ ሳስታውስ ውስጤ ይቆስላል ልክ እንደድሮው ተንሰቅስቄ ማልቀስ ሆነ ስራዬ አለቅሳለው አለቅሳለው ግን ለማንም ትንፍሽ አልልም።
   እንደድሮ የማማክረው ሰው አጥቼ ሳይሆን የለመድኩት ዝም ማለትን ስለሆነ አሁን ላይ ሰው ባገኝም ማውራት ግን ይከብደኛል። እህቴን ሀዉለትን የሆነውን ሁሉ ደበቅኳት። ግን የተዉኩትን ወንዶችን ማሰቃየት ፈለኩ። ወንዶችን በፍቅር ማሸት በሚል እንደገና ልጀምር ወሰንኩ፡፡ አሁን ከበፊቱ ከዲኔ ለዉጥ አለኝ ሀራም እና ሀራሙን መድረሳ በመቅራት ለይቻለሁ ግን ....ወንዶችን ለመበቀል ምንም የቀራሇቸዉ ኪታቦች ሊያግደኝ አልቻለም፡፡
     ብዙ ወንዶች ስለምቀርብ እነሱን ፍቅር አሲዞ ላሽ ማለት ሆነ ስራዬ ።ከነሱም መካከል ሲራጅ የዚህ ጥቃት ሰለባ ነው። ሲራጅ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሲሆን የ ወንድሜ ጋደኛም ጭምር ነው።በነገራችን ላይ ወንድሜ የዩኒቨርስቲ ትምርቱን ትቶ መጥቶ የራሱን ስራ እየሰራ ነው።
    እነ አቡበከር አህመድ የታሰሩ ጊዜ ሙስሊሞች ላይ የደረሰው ጫና መቼም አንዘነጋውም።ወንድሜም የዚህ ሰለባ ተጠቂ ነው።ሙስሊም በመሆኑ ብቻ መምህራኖች ተመካክረውበት ግሬድ አበላሽተውበት ሁሉ ነገሩን ለአላህ ትቶ መጥቷል። እኔ በቃ ነጋ ጠባ መጀናጀን ነው ስራዬ። እቤት ስልክ እንደያዝኩ አባቴ ካወቀ ቆይቷል ምንም አላለኝም፡፡ ማትሪክን ተፈትነናል የማትሪክ ዉጤት እየጠበኩ ነዉ ..የምዉለዉ እቤቴ ስለሚሆን ይደብረኛል ፡፡ፈታ ዘና የምለዉ በቻት በማዉራት ወንዶችን በመጀንጀን ነዉ፡፡
 ......ዘመድ ነው የለ ትልቅ ነው የለ ትንሽ ነው የለ አላቀውም የለ ከtelegram group ከwhatsap group profile እያየሁ ወማውራት ብቻ መጀንጀን ብቻ ሆነ ስራየ ብዙ ወንዶችን በፍቅር ክንፍ አረኳቸዉ።ቫይበር አይቀረኝ ኢሞ አይቀረኝ ፌስቡክ አይቀረኝ  ዋትሳፕ telegram አይቀረኝ መጀናጀን ነው ስራዬ።
   
     አንድ ቀን ማታ ላይ ስልኬ ካርድ ዘጋ።ውጪ ወጥቼ አልገዛ ምሽት ነዉ.....

#part 9⃣
ይ..............ቀ..........
........ጥ...........ላ.........,......ል

Join👇
T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
#በትውልድ_ሱማሊያዊቷ_በዜግነት_እንግሊዛዊ_የሆነችዋ_ጃዋሂር_ሮብለ_የመጀመሪያዋ_ሂጃብ_ለባሽ_እግርኳስ_ዳኛ 🎌
አስቸጋሪውን የስደተኝነት ህይወት ተቋቁማ አለም አቀፍ የእግርኳስ ዳኝነት መሆን የቻለችው የ24 ዓመቷ ጃዋሂር ከፍተኛ የአካል ብቃት የሚፈልገውን የዳኝነት ስልጠና በብቃት በመወጣት የፊፋ አለም አቀፍ የዳኝነት ሰርተፍኬት ማግኘት ችላለች።
እስከ ፈረንጆቹ 2014 ድረስ #ሂጃብ መልበስ ለቅጣት ይዳርግ የነበረው የFAው ህግ የተቀየረ ብሆንም አሁንም ጫናዎች እንዳሉ ትናገራለች እነዚህንም ጫናዎች ተቋቁማ ስኬታማ መሆን ችላለች
#በዚህም_የመጀመሪያዋ_ጥቁር_ሙስሊም_ሶማሊያ_እንግሊዛዊ_ሂጃብ_ለባሽ_ሴት_አለም_አቀፍ_የእግርኳስ_ዳኛ_በመሆን_ታሪክ_ሰርታለች 👍👍

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
👍1
የነጻነቱ ታጋይ #ኔልሰን_ማንዴላ ወርቃማ ንግግሮች ውስጥ ጥቂቶች
➊.ማንም ሰው ሌላውን ሰው በሁኔታዎች እና በቆዳው ቀለም፤ወይም በሃይማኖቱ እንዲጠላ ሆኖ አልተወለደም፤ ሰዎች መጥላትን ተምረውት ነው።
➋.የሰው ልጅ ጥላቻን ከተማረ፤ ፍቅርንም መማር ይችላል፤እንደውም ፍቅር ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው።
➌.ማናችንም ከዚህ ምድር ይዘነው የምንሄደው አንዲት ነገር የለም፤ ስለዚህ በጥላቻ ለምን ግዜያችንን እናጠፋለን፤ ይልቅ በፍቅር እና በስምምነት ብዙ ነገሮችን እንለውጥ።
➍.ጥላቻን ፈልገነውም ሆን ሳንፈልገው ተምረነው ይሆናል ፍቅርን መማር ግን ጥላቻን ከመማር በላይ ይቀላል እና ፊታችንን ወደ ፍቅር እንመልስ!


       JOIN
@Islam_and_Science
         @Islam_and_Science
            
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

            #ክፍል 3⃣
በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተደገፈ ታሪክ
#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal
     ከትምህርት ቤት ስንወጣ አሻግሬን ከሩቅ አየችው ሀያት ኑኑኑ! ይሄን ልጅ ዛሬ ተጋግዘን ካልመታን ጓደኞቸ አይደላችሁም አለች ቆጣ ኮስተር ብላ አሻግሬ ማለት ጤንነቱ የተቃወሰ ነው ጤነኛ ነው ብሎ ለማለት እንዳንችል ብዙ የእብድ ስራወች ባለቤት ነው ታዳ ይህ ልጅ ሀያትን ወደድኩ ብሎ ወሬው ተናፍሶ ሠው ጆሮ ደርሶ ሀያትን መሣቂያ መሣለቂያ አደረጓት በዚህም ስለተናደደች ልትቀጣው ወስና እርዳታ ጠየቀችን እንቢ ማለት አንችልም፡፡ ጥያቄዋ ድንገታዊ ሆኖ አስደንግጦናል ግን እንዳልሽ ብለን ተከተልናት እኔ በጣም ፈርቻለሁ
      ዛሬ ስትደበደቢ ዋይ ብሎኛል ጠዋት አባቴ አሁን ደግሞ ይሄ እያልኩኝ በውስጤ ልቤ እየቀረ እግሬ ተገትቶ አጠገቡ ደረስን ማን ይሆን የመጀመሪያ ጥፊ ቀማሽ ፊትለፊቱ ቆመን ሀዩ ንግግሯን ጀመረች ተናዳ ስለተማረረችበት ንግግሯ ጠጠር ያለ ነበረ ከአሁን በኃላ ስሜን ብታነሣ አ,ገ,ል,ሀ,ለ,ሁ!!!! አይኑ ውስጥ ልትገባ ምንም አልቀራትም በዚህ ጊዜ
.......አሻግሬ ማልቀስ ጀመረ ሁላችንም እርስ በርስ ተያየን ከደቂቃ በፊት በርቸ ልቤ ሲመታለት የነበረ ልጅ አሁን እሽ ምንም አላወራም አሁን ግን ምንም አታረጊኝ ብሎ ልመና ወደቀ ሀዩም ለዛሬ አልፍሀለሁ ሁለተኛ ወሬ ብሰማ ግን አላዝንልህም አሁን ሂድ ብላ አባረረችው ከሄደ በኃላ ሳቄን ለቀኩት ሁኔታው ሁላችንንም አሳቀን አሁን ሀዩ እፎይ አለች፡፡
       የግማሽ ሴሚስተር ፈተና ደርሷል አራታችንም ላይብረሪ ተገኝተናል ነቢ በትምህረቷ አትደራደርም ጎበዝ ተማሪ ነች ኢክሩም ለራሷ አታንስም ከሠው አጠብቅም እንደነቢያት ባትሆንም ጎበዝ ነች እኔና ሀዩ ደግሞ ትምህርት ብሎ ነገር አይሆንልንም ብቻ አላህ ነቢያትን ሠቶናል ከ50 ከነቢያት እየሰራን አጠራቅመን ፍይናል ብዙም አንጨናነቅም አሁን ማንበብ መልመድ አለባችሁ ቀጣይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ነው ስለዚህ አሁን ተለማመዱ ብላ ተቆጣችን ግን ማንበብ አለመደብኝ ነገር ጨነቀኝ ተቁነጠነጥኩ ........እናንተ ግብ ፊቴን ታጥቤ መጣሁ ድብርት እንዲለቀኝ   ብየ ወደ  ቧንቧ ስሄድ ሀዩ ጠብቂኝ እኔም ጠምቶኛል ብላ ተከተለች
.......... ኢክሩ ነገሩ ገብቷት ሳቀችብን ነቢ ግን ተቆጣች አወ ቀልዱ ዋጋ የምትከፍሉበት ቀን ቅርብ ነው ብላን ተያይዘው ኢክራም ጋር ገቡ እኔና ሀዩ ውጭ ቁጭ ብለን የቆጥ የባጡን ስናወራ ቆየንና በመሀል "" ራህማኮ ባሏ ጋር ተጣላች አለችኝ ራህማ ማለት የሀዩ አክስት ነች""
"" ምነው ምን ሆን አሉ""
""ሁለተኛ ሚስት አግብቶ""
""ምን!!? ምን አይነት ሰው ነው ግን ከሷ ምን ጎደለውና ሄደ ሲጀመርኮ አትመጥነውም ያችን የመሰለች ቆንጆ ሚስቱን ትቶ ሌላ አማረው?? አይ ወንዶች!!!!"""
""እንዴ እሷ እንካን ያንችን ያህል አልተናደደችም የተገባባት ምን አናደደሽ ደግሞ አቅም ካለው ቢያገባስ ምንድነው ችግሩ"""
"" ጭራሽ!!! አንችም ደገፍሽው እኔ ልብሴን ጫማየን ገንዘቤን ላጋራ እችላለሁ በባሌ ግን አልደራደርም ማንም እንዲጋራኝ አልፈቅድም!!!""
"" ኢሙ ግን በጣም ራስ ወዳድ ነሽ "" በክርክራችን መሀል የአሱር ሶላት ደርሶ እነ ኢክራም ወጡ፡፡
......ክርክራችንን ያየችው ኢክሩ ስታነቡ ያልገባችሁ ነገር ነዋ የሚያከራክራችሁ ብላ በአሽሙር ነካ አረገችን ወሬውን ለነሱ ነገርካቸው
.........ነቢም በዛ ላይ አስተያየቷን ሰጠች በርግጥ አላህ ፈቅዶለታል ፍትሀዊ መሆን ከቻለ ቢያገባ ችግር የለውም ግን በዚህ ጊዜ ፍላጎት እንጅ አቅሙ ያለው የለም ቢያገባ እንካን ከአንዷ አንዷን ያስበልጣል ይሄ ደግሞ እሱን ነገ በአሏህ ፊት ያስጠይቀዋል ስለዚህ በአንዷ ረግቶ ራሱን ከኪሳራ ቢጠብቅ የተሻለ ነው ለራሱ ሲል ግን አቅሙ አለኝ እችላለሁ ካለ ሚስቱ ብትፈቅድ የተሻለ ነው አንድም ባሏ በሀራም ሂዶ እንዳይባልግ ከሀራም ትጠብቀዋለች በዛ ላይ እነዛም ሙስሊም እህቶቿ ናቸው ፈሳድ ላይ ሳይወድቁ በሀላል እሷ እየኖረች ያለችውን ህይወት እነሱም እንዲኖሩ ብትፈቅድ እንደኔ ሀሣብ እና እምነት ጥሩ ነው ባይ ነኝ ብላ ንግግሮን ጨረሠች "
      በቃ አሁን አሱር ደርሷል እንስገድ አለችና ኢክራም አስነሳችን በኢክሩ ኢማምነት አሱርን ሰግደን በተቀመጥንበት ፎዚያ መጣች፡፡ ፎዚም የሰርግ ወረቀት ይዛ መጣች እኛም ማን ሊያገባ ነዉ ???? ብለን ጠየቅናት ፎዚም.......
#Part 4⃣
ይ .......ቀ
..........ጥ.........
....ላ......................ል
በislamic university channal የተዘጋጀ

▶️ ሼር አይዘንጉ
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
✔️ከስራ ፈተና ብትወድቅ ሌላ ስራ ትፈልጋለህ
ከዩኒቨርስቲ ብትወድቅ(ብትባረር) የምታርፈዉ ቤተሰቦችህ ጋ ነዉ

ልብ በል ከሲራጥ ላይ ከወደቅክ ግን ማረፊያህ አስከፊዋ ና ምህረት አልባዋ የጀሃነም እሳት ዉስጥ ነዉ*

✔️እኛ ሰወች ከመጀመሪያዉ ከሁለቱ ላለመዉደቅ ጥረት የምናደርገዉን ያክል ከሶስተኛዉ ላለመዉደቅ ብንተጋ ምን ያማረ አኗኗርና አሟሟት ይኖረን ነበር

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
🍃🍃🍃🍃🍃
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ፡፡ በየአላችሁበት ሰላምታየ ይድረስ ብያለሁ፡፡ ነገ እሮብ ከስድስቱም ዙር ያሸነፉት ነገ ሽልማቱን ለመዉሰድ ይወዳደራሉ፡፡ ነገ የግጥም ዉድድር ስላለ ሁላችሁም ተወዳዳሪዎችን ድምፅ በመስጠት እንድታግዙን እንላለን፡፡ ለምን ነገ አንደኛ የወጣዉን ሽልማቱን🏆🏆🏆 ላሸነፈዉ ተወዳዳሪ ነገ አይተን የሚኖርበት ሀገር ድረስ የምናደርስ ይሆናል ሽልማቱን እናሳዉቃለን፡፡


⭐️ነገ ስድስት ተወዳዳሪዎችን ስድስቱን ግጥሙን ካነበባችሁ ቡሀላ ከታች ባላዉ ምልክት 🤙🤙 መስጠት ትችላላችሁ፡፡
☞ለስድስቱም ተወዳዳሪ
☞ለተመቻችሁ ግጥም
☞እናንተ የፈለጋችሁትን ከስድስቱ ተወዳዳሪ like መስጠት ይቻላል

ከዛ በbot ላይ አንዱን ብቻ 👍 Like ትሰጣላችሁ፡፡ አሸናፊዉ በሁለቱ ድምር ተደምሮ አንደኛ ይወጣል ማለት ነዉ፡፡
ከግጥም ዉድድሩ ዉጤት ላይ ሀገራቸዉን እንገልፃለን፡፡ አሁን ግን ሀገር ብንገልፅ ሁሉም የሀገሩን ልጅ እንዳይመርጥ☺️☺️ ዘረኝነት እንዳይንፀባረቅ😉 የተወዳዳሪዎችን ሀገር እንገልፃለን፡፡

🏆የ➊ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞ ሀኒን መኑር
( #ጌታየ_ያለአንተ_ባዶነኝ፡) በሚል ግጥም

🏆የ➋ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞ፎዚያ ሙሀመድ( #የህልሜ_ላይ_ንጉስ)በሚል ግጥም

🏆 የ➌ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞አብዱሰላም ኢብራሂም( #ልኩራ_ወይስ_ልፈር)በሚል ግጥም

🏆የ➍ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞ አብዱ እንድሪስ( #የቲምነት_ህይወት)በሚል ግጥም

🏆የ➎ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞ ሀያት ሁሴን
( #ያረብ)በሚል ግጥም

🏆 የ➏ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞ ሒክማ ወለላዉ ( #ሁን_ያለዉ_ይሆናል) በሚል ግጥም፡፡
ነገ ሽልማቱን የሚረከቡበት ዉድድር ነገ ይወዳደራሉ ሁላችሁም የተመቻችሁን በመምረጥ እንድትተባበሩን በአላህ ስም እንጠይቃለን፡፡

💐💐መልካም ዉድድር ይሁንላችሁ፡፡ የቻናል ቤተሰቦችም መልካም የግጥም ምርጫ☺️ ይሁንላችሁ፡፡
አብሽሩ አንብባችሁ መጨረሻ ላይ 👍👍👍 ይሄን መንካት እጅ አያሳምም 😉

ለግጥሙ ዉድድሩ ነገ ጠዋት ጀምሮ ሙሉቀን እንገናኝ ወይም እንደተሳታፊዉ አይተን አንድ ቀን እንጨምርበታለን፡፡በገባችሁ ሰአት ብቻ አንብቦ Like መግጨት ብቻ ነዉ፡፡

ከአሁን ቡሀላ ሌላ ዙር አይኖርም ለምን ረመዷን እየቀረበ ስለሆነ እኛ ርዕስ እንሰጣችሇለን በርዕሱ ዙሪያ ፅፋችሁ ትልካላችሁ ከዛ ያሸነፈ ሽልማት ይኖረዋል፡፡ ይሄ ማለት በሳምንት አንድ ቀን ይኖረናል ማለት ነዉ፡፡ ግጥሙን ለማወዳደር ከሚወዳደርበት ሁለት ቀን ቀደም ብለን እናሳዉቃለን፡፡
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM