ISLAMIC SCHOOL
12.5K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
~" የእቆቅልሺ አለም ቅኔው ያልተፈታ
በሃሳብ መብሰክሰክ ከጧት እስከማታ
ደግሞም ሌሊት አለ ቶሎ እማይገታ !
ይች አታላይ አለም ሚዛኗ እማይሞላ
ላንዱ ምኞት ሆና ለሌላው ተድላ !
ያሰቡት ላይሞላ ምኞት ላይሳካ
በብዕር ይፃፋል የህይወት ትረካ
ማለቂያ የሌለው የህሌና ሙግት
በትንፋሽ አይወጣ በእንፋሎት መገፋት
ሲደሰቱ አይቼ ዉስጣቸው ሲፈካ !
የኔስ ቢሆን !ብየ ተመኘሁ በፎይታ
የነሱ ተመልካች ሆኘ በትዝታ !…
~~ ለራሴው😔😔😔
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
😔 #ዋ_ነብሴ
#ገጣሚ  ☞ ሀያት ሁሴን


ዋ ነብሴ . . .

አንቺ አኼራን የረሳሽ ለአዱንያ የሞትሽ
ለዚች ጠፊ አለም እራስሽን የሸጥሽ
ነብሴ ቓመጥሽላት ዱንያ መሆኇን ዘንግተሽ
ረህማንም ብሎሽ ይች አለም ጠፊ ናት
ታዲያ ለምን ይሁን እዲህ የወደድሻት
በምን ምክንያት ይሁን ቦታ የሰጠሻት

ዋ . . . . . ነብሴ ፈራሁልሽ

ለዚች ጠፊ አለም በፍቅሯ ወድቀሽ
ማጠቅምሽ ማትጎዳሽ የማትበጅሽ
ንቂ ዕጂ ነብሴ አትቃዢ ቁመሽ
ይች አለም ከንቱ ናት የማታዛልቅሽ

ዕናማ . . . . .

እናማ አድምጪው ፋጣሪሽን
አታወላውዪ ታዘዢው ጌታሽን
አዎ አታመንቺ ተግብሪ ያለሽን
ሠላም ትገቢ ዘንድ አኼራ ቤትሽን

ነብሴ . . . . .

እሱን ልትገዢ እሱ ፈጥሮሽ
ልትድኚ ላትከስሪ ኢስላምን መርጦልሽ
እና ለምን ይሁን የምታመነቺው
አኼራን ትተሽ ዱንያን የልሽው
እባክሽን ሩሄ ተገዢው ጌታሽን
ከአላህ ታገኚው ዘንድ ሰላምሽን ።

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
እዉነተኛ_ታሪክ

🦋 #ርዕስ☞ለአላህ ብሎ አንድን ነገር የተወ…
           #ክፍል 3⃣
#የመጨረሻዉ_ክፍል
#ፀሀፊ ☞ ራህመት ቢንት ሙሀመድ


አላረፍኩም …አሮጊቿን አፈላልጌ አገኘሁ
በአምስት መቶ ዲናር እንጂ ፍፁም አታገኛትም። ካልሆነ በፍቅሯ ተቃጥለህ መሞት ትችላለህ። ብላኝ ልትሄድ ስትል በሁሳቧ ተስማማሁ።ሱቄንና ሸቀጤን ሁሉ ለመሸጥ ቆረጥኩኝ ለእሷ ስል…አዎን ለእሷ ስል። ሁሉን ነገር ሽጬ 5መቶ ዲናሩን ለመስጠት ወሰንኩ።
በዚህ ሁኔታ ዉስጥ እያለሁ አንድ ክርስቲያን የሆነ ሰዉዬ ገቢያዉ ዉስጥ እየሄደ ሲያዉጅና ሲለፈልፍ ሰማሁኝ።

<እናንተ ሙስሊሞች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል የነበረዉ የስምምነት ጊዜዉ አልቋል። እዚህ ላሉት ነጋዴዎች አንድ ሳምንት ሰጥተናቸዉ ነበር።…> ይላል።
ያለኝን ንብረት ሰብስቤ የሻምን ሀገር ለቅቄ ወጣሁ። ዛሬም ዉስጤ ስለሷ ያስባል። በፍቅሯ ልቤ ይነዳል። ፈፅሞ ልረሳት አልቻልኩም።
ቀጥሎም ሌላ የንግድ ስራ ዉስጥ ገባሁ። ሴት ባሮችን ለገበያ ማቅረብ ስራዬ አድርጌ ያዝኩኝ።ያፈቀርኳትን ሴት ለመርሳት ብዬ ሌት ተቀን እራሴን በስራ ጠመድኩ ቀናቱ ነጎዱ። በዚህ ሁኔታ ሶስት ዓመታት አለፉ።
ቀጥሎ ታላቁ የሒጢን ጦርነት በሙስሊሞች በክርስቲያኖች መካከል ተካሄደ። ሙስሊሞች ቆላማዉን አካባቢ አስመለሱ። ንጉሱ ሴት ባሪያ እንድፈልግለት ትዕዛዝ ሰጠኝ። ቆንጆ የሆነች ባሪያ ነበረኝ። በመቶ ዲናር ተስማማን። ዘጠናዉን ዲናር ሰጡኝ። አስር ዲናር ቀረባቸዉ።ንጉሱ <ሴት የፈረንጅ ምርኮኞች ወደታጎሩበት ቤት ዉሰዱት። በቀረዉ አስር ዲናር አንዲት ፈረንጅ መርጦ ይዉሰድ።> በማለት ለወታደሮቹ ትዕዛዝ ሰጠ።
የቤቱ በር ሲከፍቱ ከተማረኩት የፈረንጁ ሴቶች መካከል ያችን ያፈቀርኳትን ሴት አየሁ። ወስጂያት ቤት ገባሁ ቤት ስንደርስ አወቅሽኝ ወይ ብየ ጠየኳት።
እንዳላወቀችኝ ነገረችኝ። እኔ እኮ ነጋዴዉ ነኝ። የሆነ ጊዜ መጥፎ ነገር አስቤ እንዲህ እንዲህ ብር ሰጥቼሽ ነበር አልኳት።
ወዲያዉኑ አሸሀዱን አን ላ ኢላሀ ኢልለላህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሃመደን ረሱሉላህ። በማለት በሽሀዳ በመመስከር ሰለመች። ኋላም እስልምናዋ ያማረ ሆነና ጠንካራ አማኝ ሴት ሆነች።
አገባኋት። ብዙም ሳይቆይ እናቷ የሆነ ሳጥን ላከችላት። ከፍተን ስናየዉ ያኔ የሰጠኋት ሁለት ከረጢት ዉስጡ አገኘሁ። በአንደኛዉ ዉስጥ መቶ ዲናር በሁለተኛዉ ዉስጥ ሁለት መቶ ነበር። ያኔ ለብሳ የማያት ልብስም እንዲሁ ዉስጡ ነበር።
በመጨረሻም ትረካዉን እንዲህ ሲል ቋጨልን…የነዚያ ዉብ ነጫጭ ልጆች እናት እሷ ናት። እሷ ናት እራት የሰራችላችሁ።


           ተፈፀመ።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

አዎን ለአላህ ብሎ አንድን ነገር የተዉ ሰዉ አላህ ይተካለታል። አንድ ሰዉ ከሰዉ  ዓይን ተደብቆ የፈለገዉን መስራት ይችል ይሆናል ከአላህ( ሱ.ወ) እይታ ግን
 በፍፁም…።
ከዚህ ታሪክ ሁላችንም ብዙ ትምህሮቶችን እንደምንወስድ ተስፋ አለኝ

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ፡፡ በየአላችሁበት ሰላምታየ ይድረስ ብያለሁ፡፡ ነገ እሮብ 5⃣ ኛዉ ዙር የግጥም ዉድድር ስላለ ሁላችሁም ተወዳዳሪዎችን ድምፅ በመስጠት እንድታግዙን እንላለን፡፡
ጠቀም ያለ ሽልማት ያለዉ ነዉ፡፡

ግጥም በbot የላካችሁ ሁላችሁንም በየተራችሁ እናወዳድራለን፡፡ ግን አንዳንድ ለዉድድር የላካችሁ ጥራቱን ያልጠበቀ ግጥም እኔ ለቻናሉ አይመጥንም ያልኳቸዉን ግጥሞች አለወዳደርኳቸወም፡፡

⭐️ነገ ስድስት ተወዳዳሪዎችን ስድስቱን ግጥሙን ካነበባችሁ ቡሀላ አንዱን ብቻ በመምረጥ Like ትሰጣላችሁ፡፡

‼️ ተዋዳዳሪዎች የተወዳደሩት ግጥሙ ከቻናል copy የተደረገ ወይ እናንተ የፃፋችሁት ከሆነ በአስተያየት መስጫዉ bot ሹክ ይበሉን☺️፡፡ ግጥሙ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል👌 የተዋቀረ አጣሪ ኮሚቴ ግብረ ሀይል አለን ግጥሙን የሰዉ መሆኑን የሚከታተሉ😉

⚠️ ከተወዳዳሪ ብዛት ብዙ የሚወዳደሩ ግጥሞች ስላሉን ከአሁን ቡሀላ ተወዳዳሪዎች ለተወሰኑ ጊዚያት ማንኛዉንም ግጥም አንቀበልም፡፡ ግጥሙን አዘጋጅታችሁ አስቀምጡ ላኩ በምንላችሁ ጊዜ ትልካላላችሁ ፡፡ አሁን ግን ብዙ ተወዳዳሪዎች ስላሉ አዲስ መቀበል አንችልም ፡፡
🎖የ➊ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞ ሀኒ

🎖የ➋ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞ፎዚያ ሙሀመድ

🎖የ➌ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞አብዱሰላም ኢብራሂም

🎖የ➍ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞ አብዱ

🎖 የ➎ኛዉ ዙር አሸናፊ ☞ነገ እናንተ በምሰጡት ድምፅ ይወሰናል፡፡

አሁን የሚቀረን አንድ ዙር ብቻ ነዉ ስድስተኛ ዙር ማለት ነዉ፡፡የሁሉንም ዙር አሸናፊ በመጨረሻ አወዳድረን የተዘጋጀዉን ሽልማት እናስረክባለን፡፡

ነገ ለዉድድር የምቀርቡ ተወዳዳሪች ለማሳወቅ ያህል
➊ ረያን ☞ፊዳከ
➋ ሒክማ ☞ ለምን አትሰግድም
➌ ሀያት ሁሴን ☞ ያረብ
➍ ረያን ሀሰን ☞አልሀምዱሊላህ
➎ ኑርየ ንጉስ ☞ አቅሷ
➏ ኸዲጃ ☞ አይዘለቅም ቢከተብ
በሚል ግጥሞች ነገ ይሳተፋሉ፡፡

💐💐መልካም ዉድድር ይሁንላችሁ፡፡ የቻናል ቤተሰቦችም መልካም የግጥም ምርጫ☺️ ይሁንላችሁ፡፡
አብሽሩ አንብባችሁ መጨረሻ ላይ 👍👍👍 ይሄን መንካት እጅ አያሳምም 😉

ለግጥሙ ዉድድሩ ነገ ጠዋት ጀምሮ ሙሉቀን እንገናኝ በገባችሁ ሰአት ብቻ አንብቦ Like መግጨት ብቻ ነዉ፡፡
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
አሰላሙ አለይኩም 5⃣ዙር ግጥምዉድድር ነዉ👍ምርጫ ማለት ከባድ አማና ነዉ ከላይ ያሉትን #ስድስት ግጥሞች አንብባችሁ የወደዳችሁትን የሚያስመርጠዉ አንዱን ብቻ ስለሆነ ከታች ባሉት ምርጫዎች ይምረጡ፡፡ ስትመርጡ ስድስቱንም ግጥም አንብባችሁ መሆን አለበት ፡፡ 🎖🎖ከታች ባሉት የገጣሚዎች code አሁኑኑ ላይክ👍 በማድረግ vote ይስጡ፡፡ በግጥም ዉድድሩ ድምፅ ስለሰጡ ከልብ እናመሰግናለን👍👍
public poll

🦋 #ተወዳዳሪ ቁጥር 3⃣ ☞ ሀያት ሁሴን – 64
👍👍👍👍👍👍👍 22%

🦋 #ተወዳዳሪ ቁጥር 2⃣ ☞ ሒክማ – 62
👍👍👍👍👍👍👍 21%

🦋 #ተወዳዳሪ ቁጥር 1⃣ ☞ ረያን – 55
👍👍👍👍👍👍 19%

🦋 #ተወዳዳሪ ቁጥር 6⃣ ☞ ኸዲጃ – 52
👍👍👍👍👍👍 18%

🦋 #ተወዳዳሪ ቁጥር 5⃣ ☞ ኑርየ ንጉስ – 36
👍👍👍👍 12%

🦋 #ተወዳዳሪ ቁጥር 4⃣ ☞ ረያን ሀሰን – 25
👍👍👍 9%

👥 294 people voted so far.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ዉድ የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ የሶስተኛዉ ዙር አሸናፊ 204 ሰዉ በግጥም ዉድድሩ ተሳትፎ ለሀያት ሁሴን ➍➑ ድምፅ በማግኘት አንደኛ ሁናል ፡፡ ሀያት ሁሴን እንኳን ደስ ያለሽ
🥇በአንደኛዉ ዙር Hani
🥈በሁለተኛዉ ዙር ፎዚያ ሙሀመድ
🥉በሶስተኛዉ ዙር አብዱ ሰላም ኢብራሂም
🎖በ➍ኛዉ ዙር ☞ አብዱ

🎖በ➎ኛዉ ዙር ☞ሀያት ሁሴን
ለፍፃሜዉ ዉድድር አልፈዋል፡፡


‼️ የመጨረሻዉ ስድስተኛዉ ዙር እሮብ ይኖረናል ማለት ነዉ፡፡

⭐️ ደግሞ ዉድድር ስለሆነ ያላሸነፋችሁ የተመቸኝን ግጥም በቻናል እንደምፓሰተዉ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፡፡

➋0➍ የቻናል ቤተሰቦች ግጡሙን አንብባችሁ በዉድድሩ የተሳተፉትን ስለመረጣችሁ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

ከአላህ ጋር ለመጨረሻዉ ዙር እሮብ እንገናኝ ፡
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
እስራኤል ፍልስጤም ላይ የምታደርጋቸው ጥቃቶች ውጤታቸው እንዲህ ነው የሚታየው! የአለም መንግስታት መሪ ነን የሚሉ ሀገራት የውሸት ሰላም ፈላጊ ነን እያሉ ሙስሊሞች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ባላየ ያልፋሉ። ታላቁ ቁርዓን እንዲህ ይላል...

"ወደ እስራኤልም ልጆች በመጽሐፉ ውስጥ (እንዲህ በማለት) አወረድን። በምድር ላይ በእርግጥ ሁለት ጊዜ ታጠፋላችሁ። ትልቅንም ኩራት ትኮራላችሁ። ከሁለቱ (ጊዜያቶች) የመጀመሪያይቱ ቀጠሮ በመጣም ጊዜ ለእኛ የኾኑን ባሮች የብርቱ ኃይል ባለቤቶች የኾኑትን በእናንተ ላይ እንልካለን። በቤቶችም መካከል ይመላለሳሉ፤ (ይበረብሩታል) ይህ ተፈጻሚ ቀጠሮም ነበር። ከዚያም (በኋላ) ለእናንተ በእነሱ ላይ ድልን መለስንላችሁ። በገንዘቦችና በወንዶች ልጆችም ጨመርንላችሁ። በወገንም የበዛችሁ አደረግናችሁ። መልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ። መጥፎንም ብትሠሩ በነርሱ (በነፍሶቻችሁ) ላይ ነው፤ (አልን)። የኋለኛይቱም (ጊዜ) ቀጠሮ በመጣ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፣ መስጊዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት ሊገቡ፣ ያሸነፉትንም ሁሉ (ፈጽመው) ማጥፋትን እንዲያጠፉ (እንልካቸዋልን)።"
(ኢስራ 4-7)

አላህ ሰላም ያጡትን ሀገራት በሙሉ የኛን ሀገር ጨምሮ ሰላም ያርግልን! አሚን!
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
ኢስላም ብርሀን ነው!! ባለቤቱም አላህ ነው። ማንም ሰው
ሊያጠፋው ይቅርና ሊያደበዝዘው አይችልም ።
♡ ጣፋጭ ነው
♡ ውብ ነው
♡ አይሰለችም
♡ አይጠገብም
♡ መካሪ ዉ
♡ የሙዕሚኖች አብሳሪ ነዉ
♡ በርግጥም ተዐምር ነዉ
☞አል__ቁርዐን ካላሙ ረቢ

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
ርዕስ ከእናንተ . . . >>
( ( ( 🇪🇹አራጋው ሙሃመድ ) ) )
አደም ሆኖ ሳለ የሁሉ መገኛ
ዘር እንቆጥራለን ሱስ ሆኖብን እኛ
ባላንጣ ፍለጋ ዘር ከቆጠራችሁ
እኔ ግን እንደኔ ስሙኝ ልንገራችሁ
.
የ'ናቴ ልጅ ሁሉ አይደለም ወንድሜ
ሠውነት ብቻ ነው ወዳጁ የደሜ
ቅንነት ከሌለው ቢወለድ ካ'ባቴ
አይደለም ወንድሜ የለም ከኔነቴ
እህቴን ከ'ናቴ መች እጠብቃለሁ
በፍቅር አምጬ እኔ እወልዳታለሁ
.
ለሠዎች አሳቢ ከሆናችሁ መልካም
በ'ናንተ ነው እንጂ በዘሬ አልመካም
ስለዚህ ግዴታ ዘር መንጥር ካላችሁ
የነፍቅርን ዘር የነደግነትን ኑ! ልቁጠርላችሁ::🇪🇹🇪🇹🇪🇹
.
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════••🇪🇹🇪🇹•••════•
#አይ__አንች___አለም//
ታዘብኩሽ አንች አለም በጣም አዘንኩብሽ
አንዱ ቤት ደስታን አንዱ ቤት ሀዘንን ለምንታስገቢያለሽ
እስኪ በይ ንገሪኝ ለምን ታዳሊያለሽ
ለሌላው ብርሀን ቀን ከሌት አብርተሽ
ለኔ ቢጤ ድሀ ሁሉን አጨልመሽ
አንጀት ጠብ የማይል የህልም እንጀራ አብልተሽ
መልስ ስጭኝ ልጠይቅሽ እኮለምን እንድህ መስራትሽ
ዘላለም ባንች ውስጥ ማንም ላይኖርብሽ
................አይ አንች አለም
አይአንች አለም ስንቱንበደስታ እያቀማጠልሽው
ሌላውን በሀዘን አንጀቱን ገረፍሽው
ተስፋ ትሰጭና መንገድ አስጀምረሽ
እዳር ታስቀሪያለሽ ቃልሽን አፍርሰሽ
በቃ ምን ልበልሽ አንች ፈተና ነሽ
ስንትና ስንት አሉ እጅግ ያዘኑብሽ
እስኪ በይ ንገሪኝ ለምን ታዳሊያለሽ
ዘላለም ለማይኖር ደፋ ቀና እያለ
እጅግ የተከፋ በውስጥሽ ብዙ አለ
..........አይ አንች
መጥፋትሽን ባወቅሽ መሆንሽን ከንቱ
ታስደስችው ነበር ሁሉን በየቤቱ
ቀንሽ ይደርስና አንችም ትጠፊያለሽ
ግን እስከዛው ድረስ ታስተዛዝቢያለሽ
ከወደዱት ሸር ያርጉት 😞😞😞
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
አፄ ሀልስላሴ لاعنتلله اليه በተባበሩት መንግስታት የመሪዎች ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስሊም ካለው ህዝብ ብዛት ከመቶው 10% ፐርሰንት ብቻ ናቸው እነዚህንም በቅርብ ግዜ ውስጥ ወደ ክርስትና እንጠምቃቸዋለን ሲል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት አቅርቦ ነበር ይሄው አልሀምዱሊላህ እሱ የሚለው ከእውነት የራቀ ቢሆንም አሁን በዕጥፍ በዝተን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ብዛት በአፍሪካ 3ኛ በአለም 9ኛ ደረጃን ይዘን እንገኛለን።
የኢስላም ታሪክ ተመራማሪው
#ረዳት_ፕሮፌሰር_አደም_ካሚል_ከተናገረው

«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»
👍👍👍ውርደት ይሉሃል ኢሄ ነው! !
ፓውሊን ሃንሰን ትባላለች
የአውስትራሊያ ሲናተር ናት ቡርጋ(የፊት መሸፈኛ) በሃገሪቱ የሚከለክል ህግ እንዲወጣ ስለ ፈለገች የአረብ ቡርጋዓ ለብሳ ሙስሊሞች ምን ያህል ለአውስትራሊያ አደጋ እንደ ሆኑ ለማሳመን ብትቀርብም ገና አፏን ሳትከፍት ጆርጅ ብራንዲ (አቶኒ ጅነራል) የተባለ የፓርላማ አባል አፏን አዘጓት፣ የፓርላማው አባላትም ከመቀመጫቸው በመነሳት በጭብጨባ የጆርጅ ብራንዲስ ንግግር በማድነቅ የፅንፈኛዋን የወ/ሮ ሲናተር ፓውሊን ሃንሰን መርዘኛ አስተሳሰብ ተቃውመው ፓርላማ ውስጥ ኩምሽሽ ብላ ና በመጨረሻም አፍራና አንገቷን ደፍታ ከፓርላማው ለመውጣት ተገዳለች።
ሴናተር ጆርጅ ብራንዲስ (አቶኒ ጅነራል) የሴትየዋን መርዘኛ አስተሳሰብ በመቃወም ለፓርላማ አባላት ይህን ድንቅ ንግግር ተናግሮ አፏን አዘጋት፣አላማዋንም አከሸፈባት።
"ለመሆኑ ሙስሊሞች እነማን እንደሆኑ ታውቂያለሽ ? የሰው ክብር እና ሃይማኖት ለማቋሽሽ የምታደርጊው ያለ ድርጊት በጣም በጣም መጠንቀቅ አለብሽ ሁላችን አደጋ ላይ ሊጥለን መሆኑን በቅድሚያ ሊገባሽ ይገባል።በአገራችን ግማሽ ሚልዮን ሙስሊሞች የአውስትራሊያ ዜጎች ይገኛሉ በጣም ከሚገርሚሽ ላለፈው ለ4አመታት እኔ በተለያዩ የደህንነት የፀጥታ ተቋማት በሃላፊነት ደረጃ ስርቼአለሁ ባይገርምሽ የአንድ ወንጀለኛ ሙስሊም ፋይል አይቼ አላውቅም። የእስልምና እምነት ተከታዮች እጅግ ሲበዛ ስነ ስርአት ያላቸው ማህበረስብ ኮሚኒቶች ናቸው ተጠንቀቂ" በማለት ልኳን ነግረው አስቀመጧት።
ለጆርጂ ብራንዲስ አላህም ሂዳያ እንዲሰጠው ዱአችን ነው ።
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
>>>>>>>> #ከገባሽ_ስሚኝ_ልንገርሽ……<<<<<<<<<
*\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\*********
⭐️ውበትሽን አይቶ የተመኘሽ እና ውስጥሽን(ስብእናሽን)
አይቶ ያፈቀረሽ ሰው የተለያዩ ናቸው።
#ለምን ነገርከኝ እንዳትይኝ??? ምክንያቱም አስብልሻለዋ!!!
#እኛ ወንዶች ስንባል የፈለግነውን ነገር እስክናገኝ ድረስ ሴትን ልጅ ንግስት ማድረግ እናውቅበታለን። #ከልቡ ያፈቀረ ሰው ግን ተብታባ ነው። ውሸትን ለመግለፅ እንኳን አንደበት የለውም።

‼️ነገር ግን በውስጣዊ ማንነትሽ ተማርኮና እጅ ሰጥቶ የቀድሞ ማንነቱን ወዲያ አሽቀንጥሮ ጥሎ ሌት ተቀን አንችን በምናቡ ሲያወጣ እና ሲያወርድ ፣ ☞ያንቺን ህይወት ለማድመቅ የራሱን ሲያፈዝ ፣
☞ከሰው በላይ የነበረው ላንቺ ፍቅር ሲል መቀመቅ ሲወርድ ፡ ያኔ ላንቺ ያንስብሻል። ያኔ ላንቺ ተራ ሰው ይመስልሻል።

‼️ #እናም ፍቅርሽን ሳይሆን ገላሽን ለተመኘው ትሰጪና ዳግም ብትፈጠሪ እንኳን ዳግመኛ የማታገኝውን ንፁህ አፍቃሪሽን ልብ አንኮታኩተሽ እንዳይሽር እንዳይድን አርገሽ ትሰብሪዋለሽ።

😔 #እሱም ለዘላለም ልቡ ታሞበት እንደማቀቀ ፍቅሩን ተቀምቶ አዝኖ ቁርጡን አውቆ ይቀመጣል።
#አንቺ ግን ሳታውቂው ከፍቅር ፊልሞች ላይ ባየው አማላይ ቃላቶች ወይም ከፊክሽን መፅሀፎች ላይ በሸመደደው የሽንገላ ቃላቶች ያታለለሽ ሰው ግን ከአንድ ለሊት መኝታ በኋላ ለአይኑ እንኳን ይጠየፍሻል።

‼️ #በቃላት ድርደራ በስጦታ ጋጋታ ንግስት ያስመሰለሽ ሰው ያሻውን ፈፅሞ ሲያበቃ የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እንኳን ዋጋ አይሰጥሽም ፡ ከጥፍሩ ቆሻሻ እኩል እንኳን አይቆጥርሽም።

👌 #እናም ሄዋኔ ለዚህ ነው የተመኘሽ እና ያፈቀረሽ የተለያዩ ናቸው ያልኩሽ።99 ነጥብ።
* ጨ ፡ ረ ፡ ስ ፡ ኩ ፡ ***
>>>>>> ውጫዊ ውበት ቀልብን ይስባል <<<<<<<
>>>>>ውስጣዊ ማንነት ግን ልብን ያስገዛል<<<<<

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
👍1
🦋እዉተኛ ታሪክ
😔 #ማን_ነዉ_ጥፋቸኛ 🤔

#Part 1⃣
#ፀሀፊ ☞ ከባለታሪኩ ያለምንም ማስተካከያ የተጨመረ የተቀነሰ ሳይኖረዉ ባለታሪኳ እንደላከችልኝ የቀረበ ታሪክ፡፡

🎖በISLAMIC UNIVERSITY ቻናል የቀረበ
    
ስሜ ሲሀም ይባላል አሁን የ 20 አመት ልጃገረድ ስሆን ከ 9 አመቴ እስከ 20 አመቴ ያሳለፍኩትን ህይወት ነው ምፅፍላቹ። 2 ወንድም እና 5 እህት አለኝ። ሁላችንም በአንዲት የገጠር ከተማ ውስጥ ነው ተወልደን ያደግነው። አባታችን ግን ኑሮው አዲስ አበባ ሲሆን ለ አመትባል እና ለ አንዳንድ አስገዳጅ ጉዳዮች ብቻ ነው ወዳለንባት መንደር ሚመጣው። አንዱ ወንድሜም ያለንባት መንደር ከ 8ተኛ ክፍል በላይ ስለማያስተምሩ ለትምርት ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ሄዶ ኑሮውን ከአባቴ ጋር አድርጎታል እኔ በባህሪዬ በጣም ፈጣን እና ችኩል እንዲሁም ታዛዥ እና ጎበዝ ልጅ ስለሆንኩ አባቴ ከሁሉም ልጆቹ አስበልጦ ይወደኛል። ስለሆነም የ 1ኛ ክፍል ትምርቴን እንዳጠናቀቅኩ ማለትም የ 9 አመት ልጅ እያለሁ ወደ አዲስ አበባ ይዞኝ መጣ።
      አባቴ ለትምርት ያለው ፍቅር አውርቼው አያልቅም። በቃ ለሱ ትምርት ከምንም በላይ ነው።ታዳ ለሌላ ነገር ቦታ የለውም።ከስራ የሚመጣበትን ሰአት በጉጉት እጠባበቅ ነበር።አባቴን ከምገልፀው በላይ ነው ምወደው ከማንም በላይ።የምተኛው ሁላ ከሱጋ ነው።ሌላው ይቅርና ወደ አዲስ አበባ ሳልመጣ በፊት ለአመት በአል ወደ ሀገራችን ሲመጣ ግማሹን የግር መንገድ ተጉዤ ነበር ምቀበለው። እናም እንደነገርኳቹ አብሬው ነው ምተኛው።በነገራችን ላይ አባቴ ሀምር(መጠጥ) ይጠጣል እና አምሽቶ ሲመጣ እሱን ሳላይ እንቅልፍ አይወስደኝም።ጥዋትም ስራ ሲወጣ ግንባሬን ሳይስመኝ አይወጣም። ደሞ አብሮኝ ሚኖረው ወንድሜ ሁሉ ነገሬ ነበር ያጥበኛል ያለብሰኛል ያስጠናኛል........ከ እህት ወንድሞቼ ልዩ ፍቅር አለኝ ለሱ። ከዛም ሁለተኛ ክፍልን ካለንባት ሰፈር ከ መርካቶ ብዙም የማትርቀው  እናት ኢትዮጽያ ትምርት ቤት ቀጠልኩ። ኑሮዬም ከቤት ትምርት ቤት...ከትምርት ቤት ወደ ቤት ሆነ። ከጊቢ መውጣት ስለማይፈቀድልኝ የሚያጫውተኝ ጋደኛም የለኝም።
     እንዳውም አንዳንዴ እትብቴ የተቀበረባት መንደር እና እናቴን እያስታወስኩ ስቅስቅ ብዬ አለቅስ ነበር። እያለ እያለ አመቱ አለቀ እናም 3ተኛ ክፍልን ሌላ የግል ትምርት ቤት አስገቡኝ። ጌጃ ቃለ ህይወት ይባላል የሀብታሞች ትምርት ቤት ነው አብነት አካባቢ ጌጃ ሰፈር ይገኛል።እናም እዛ መማር ጀመርኩ ። እንደ እውነቱ ምርጥ ትምርትቤት ነው ከልብ ያስተምራሉ።ተማሪዎችንም ስነምግባር ያስይዛሉ።ትምርቴን ቀጠልኩ ብዙ ጋደኞችን አፈራሁ። ቤተሰባችን ላይም አንድ አካል ተጨመረ። ራዉዳ ትባላለች የ አጎቴ ልጅ ናት። በአንድ ዘመዳችን ቤት በጥገኝነት ትኖር የነበረ ሲሆን ስላልተስማሙ ሁሉንም ነገር ጥላ ወደ እኛ ቤት መጣች።
    አሁንም ቀጠለ 4ተኛ ክፍል ገባሁ። እስካሁን ድረስ አንድም የሰፈር ጋደኛ የለኝም።እንደተለመደው ከጊቢም አልወጣም።እድሜዬ 11 ደረሰ።አሁንም ድረስ ከ አባቴ ጋ ነው ምተኛው። ልጆች ሲጫወቱ ሳይ እቀናለው። እህህህህህ ብዬ ብሶቴን የምነግረው ሰው በማጣቴም አዝናለው። ትምርት ቤት ደሞ እኔ ብቸኛዋ ሙስሊም ሴት በመሆኔ ምክንያት ብዙም ልጆች አይቀርቡኝም።ትምርት ቤቱ የጴንጤ ነው። አራተኛ ክፍል ስደርስ ከ ወንድሜ ጋ ያለኝ ቀረቤታም እየራቀ መጣ ለኔ መጨነቅ ቀነሰ ምክንያቱም የ አጎቴ ልጅ ራዉዳ አለች።ብዙም ሳይቆይ ደሞ ሌላኛዋ የ አክስቴ ልጅ ተቀላቀለችን ሀፍሷ ትባላለች። ሁለቱ ሴቶች እኛን በመቀላቀላቸው ምክንያት ብዙ ዘመዶቻችን ወደ ቤታችን መጉረፍ ጀምረዋል። ከነዛም መካከል ሁበይብ አንዱ ነው። ሌላኛው የ አጎቴ ልጅ ነው.በጣም እወደዋለው።እንዳውም አንዳንዴ ጀሙን ደውይለት ና በይው እላታለው።
     አረፍት ደረሰ እናም እንደተለመደው አባቴ ለ አመት በአሉ ገጠር የሚጠብቁትን ልጆቹ ሚስቱ እና መላ ቤተሰቡ ለማስደሰት ሄደ። ወንድሜም እንደዛው። እኔ ራዉዳ እና ሀፍሷ ቀረን። እናም የሆነ ቀን ምሽት 5 ሰአት አካባቢ የሀፍሷ ስልክ ጮኸ..ሁበይብ ነው ሰክሯል ሙስሊም ሁኖ ይጠጣል የገጠር የወረዳ ልጆች አዲስ አበባ ሲገቡ መጠጣት ስልጣኔ ይመስላቸዋል አስተዳደጉ በዲን ያለደገ ከተማ ሲገባ ሰዉ ያረገዉን ለማረግ ይቸገራል ።  ሄሎ......አቤት?....በሰላም ነው በዚሰአት?.......
.....ልመጣ ነዉ
እሺ ና.....ችግር የለውም........
 ስልኩ ተዘጋ ፡፡ሀፍሷ ራዉዳን  ጠራቻትና ሁበይብ ሊመጣ ነው ብላ ነገረቻት። ምክንያቱም ስለሰከረ ቤት መግባት ፈርቶ እንደሆነ ትነግራትና ወሬውን ይቓጫሉ።
    ትንሽ ቆይቶ ሁበይብ መጣ.... ስለመሸ መኝታችን ተዘገጃጅቶ ነበር።እንደተለመደው ሀፍሷ እና ራዉዳ አንድላይ እኔ አባዬ ስለሌለ ለብቻዬ እና ከኔ ጎን ለ ሁበይብ ተዘጋጅቶ ነበር ፡፡ግን ሁበይብ አሻፈረኝ ብቻዬን አልተኛም አለ። 
.....ዝም ብለን ስንተኛ ተነስቶ እነ ሀፍሷ ጋ ሄዶ ይተኛል። ሲቆሙ ይቆማል።ሲጨንቃቸው በቃ ከሲሀም ጋ ተኛ አሉት እኔም አልተቃወምኩትም ምክንያቱም በጣም የምወደው የ አጎቴ ልጅ ነው።ልጅነትም አለብኝ። ውዱን የ አጎቴ ልጅ ስሩ ተሸጉጬ አቅፎው ተኛሁ። ለሌት ላይ አንዳች ነገር ተሰማኝ ህልም ይሁን እውን ይሁን ቅዠት መለየት አልቻልኩም....... እንደምንም ነቃሁ..... ሁበይብ የለሊት ልብሴን  ለማውለቅ ሲታገለኝ ነቃሁ።ማመን አቃተኝ ግን ምንም ያልኩት ነገር የለም ብቻ ልብሴን እንዳያወልቅብኝ እታገለው ጀመር ...አልቻልኩትም አወለቀብኝ.....ከዛም ልክ እንደ እንስሳ ወንዶች ይታገለኝ ጀመር........ያሻውን ሳይፈፅም በፊት ልቀድመው አስቤ ጮህኩኝ።
     ያኔ ራዉዳ እና ሀፍሷ ነቁና ደንግጠው ምንድነው ሲሉኝ ለማውራት አፍሬ ምንም አልኳቸው.ምክንያቱም የዚን ያክል የ እህትማማችነት ቀረቤታ የለንማ ምን ብዬ ልንገራቸው?
......ያኔ ተናደው ቅዠታም ነይ እዚጋ ተኚ አሉኝ ያኔ ሳላንገራግር አጠገባቸው ሄጄ ተኛሁ። አላህ በዚ መልኩ ከሁበይብ ጉድ አወጣኝ አልሀምዱሊላህ።ከዛን ጊዜ ጀምሮም ስተኛ ከቢጃማዬ ስር ሌላ ተጨማሪ ሱሪ ወይም ቁንጣ ሳላደርግ መተኛት አልችልም።እስካሁንም ድረስ ይህ ነገር አልተወኝም።.
     ይሄ ባህሪዬ ደሞ ከአባቴ ጋር ያጣላኝ ጀመር። እሱ ኩላሊቱን ስለሚያመው ሱሪ ወይም ላስቲክ ያለውን ልብስ ለመኝታ ሚጠቀም ሰው ይቆጣል። እኔ ደሞ የራሴ ምክንያት አለኝ ግን አይረዳኝም ለምን ብሎም አይጠይቀኝም። እንዳውም ከሱ ጋር መተኛትም እየቀፈፈኝ መቷል። በቃ ቀስ በቀስ እኔና አባቴጋ ያለን ቀረቤታ እየደበዘዘ መጣ

#Part 2⃣

ይ........ቀ..............ጥ.....
................ላ.................,.....ል

4 another channal👇
@Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
👍1
🕊🕊🕊🕊አንድ ግዜ አንድ ገበሬ አንድ ላባዋ በጣም የሚያምር ወፍ ያገኝና እንዲህ ይላታል

🕊🕊‹‹አንቺ ወፍ አንቺ እየበረርሽ ከምትለፊ እኔ ምግብሽን በየቀኑ ልስጥሽ አንቺም በየቀኑ አንድ አንድ ላባ ስጪኝ››
ይላታል
🕊🕊ወፏም በደስታ ትስማማና ሁሌ ላባዋን እየሰጠችው እሱ ምግብ ይሰጣታል ላባዋ በጣም ስለሚያምር ገበሬው ቤቱን ያስውብበታል ወፏም ለፍተው በሚያድሩ ወፎችን እያየች ትስቅባቸዋለች፡፡

🍃🍃ከዚያም ከጊዜ ቦሃላ ላባዋ ከላይዋ ላይ ያልቃል ከዚያም ብርዱን መቋቋም አቅቷት ትሞታለች፡፡
እንግዲህ የኛ #ኑሮም ይህ ነው፡፡
ከአለም ጋር በምን እንደምንደራደር ለይተን አናውቅም አንዳንዱ ከጫት ከመጠጥና ከሱስ ጋር ይደራደራል እንዲህ ብሎ ‹‹እኔ ጤናዬን ልስጥህ አንተ ትንሽ ፈገግታ ስጠኝ›› ይለዋል፡፡
🕊🕊🕊ለወፏ ምግብ እየሰጠ ላባዋን(ህይወቷን) እንደተቀበላትና ባዶ እንዳስቀራት ገበሬ
ጫቱም መጠጡም ጊዜአዊ የላይ ፈገግታ እየሰጠው ጤናውን ገንዘቡን አራግፎ ያለላባ ባዶውን ሲቀር የኑሮን ብርድ መቋቋም ሲያቅተው አንድ ቀን ስርአት ያለው ሳቅ ሳይስቅ የሚወራ ታሪክ ሳያስቀምጥ ሳይኖር ይሞታል ታሪኩም በሁለት መስመር ይቋጫል፡፡

እራሳችንን ሸቶ ከመድረቅ እንታደገው የጫት ትርፉ ላባን ሰውቶ ራቁት መግዛት ነው፡፡
መቼም በዚህ የግብይት አለም ፀሃይ እየሸጠ ጨረቃ የሚገዛ አትራፊ አይባልም
አንተም ጫት መጨበጥህ እንደ አትራፊነት ከተሰማህ 🌻ላባዎችህን አታስብላቸውም ማለት ነው፡፡
☞ ላባህ ጤናህ ነው
☞ላባህ ወዳጆችህ ናቸው
☞ ላባህ ቤተሰቦችህ ናቸው፡፡ እስካሁን የሰጠኸውን ላባ ተወው የዛሬዋን ቀን የላባዎችህ ማትረፊያ አድርጋት ላባዎችህን ጠብቃቸው ።

‼️አስብ ዛሬውኑ ከውሸተኛው የህይወት እንቅልፍህ ውስጥ እውነተኛ መባነን ባን ተነሳ ከዛሬ ጀምረህ እሩጥ!!

‼️"አስብ በባነነበት ሰአት የሮጠ በሙሉ ዘገየህ አይባልም"
ሁሉም በራሱ የህይወት መሮጫ ስለሚሮጥ ማለት ነው፡፡
Art Firaw//78

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
#ለሟቹ_ወዳጄ
😔 #ይሄው_ትላንትና

ያመንክባት ሚስትህ ባንተም የተመካች
ሙት አመትህ ሳይደርስ ፈጥና ሌላ ተካች።
የመስክህ አበቦች
አንተን ቢያጡ ጊዜ ጠውልገው ረገፉ
የልብ ወዳጆችህ
የሙት ደጃፍህን እያዩት አለፉ።
ግና ዛሬም ታምኖ
በናፍቆትህ ታሞ በቁሙ የሞተው
የቀድሞ ፍቅርህን መውደድህን ባይተው
ያ ታማኙ ውሻህ ሰው መልመድ አቃተው።😔😔
Ezana Mesfin

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
🦋እዉተኛ ታሪክ
😔 #ማን_ነዉ_ጥፋቸኛ 🤔

#Part 2⃣
#ፀሀፊ ☞ ከባለታሪኩ ያለምንም ማስተካከያ የተጨመረ የተቀነሰ ሳይኖረዉ ባለታሪኳ እንደላከችልኝ የቀረበ ታሪክ፡፡

🎖በISLAMIC UNIVERSITY ቻናል የቀረበ

    አመቱ አለቀ 5ተኛ ክፍል ደረስኩ እድሜዬም 12 ሆነ። የጉርምስና ምልክቶች እኔላይ ይታዩ ጀመር። ጡት አጎጠጎጥኩ ፔሬድ ማየት ጀመርኩ። ሁሉ ነገሬ ባንዴ ተለዋወጠ። እብደቱም ልታይ ልታይ ባይነቱ ባሰብኝ ከብዙ ሰዎች ጋር መግባባት ጀመርኩ። በባህሪዬ ደፋር ቀልደኛ ተጨዋች ስለሆንኩኝ አስተማሪዎችም ይወዱኛል። ብዙ ሰዎች ግልፅነቴን እና የዋህነቴን ይወዱታል። የትምህርት ቤት ዳይሬክተሬም ጭምር።
   እንዳውም 5ተኛ ክፍል ከገባሁ በኋላ በጣም ተግባብቼዋለው።ብዙ ጓደኛ ስለሌለኝ ቀርቦ ሀሳቤን የሚረዳኝ አይዞሽ የሚለን ስለለም ጭምር በ እረፍት ሰአትና ከምሳ በኋላ ቢሮው እየሄድኩ ያጫውተኛል የተለያዩ የሚበሉ የሚጠጡ ነገሮች ይገዛልኛል ይላፍኛል...አንዳንዴም ከአባቴ በላይ አንቺን ጥሩ ዉጤት ደርሰሽ ማየት ነዉ የምፈልገዉ እያለም ሞራል ይሰጠኛል... ልክ እንደ አባት ፀጉሬንም ያሻሸኛል። ልክ እንዳባቴ አስበዋለው። እንዳውም አባዬ ስለማያጫውተኝ ከሱጋ ስጫወት ከአባቴ ያጣሁትን ፍቅር ያገኘሁ እየመሰለኝ እደሰታለው።
      ታድያ አንድ ቀን እንደለመድኩት እረፍት ሰአት ላይ የዳይሬክተሬ ቢሮ ሄጄ መጫወት ጀመርኩ እንደሁልጊዜው እንቃለዳለን እንላፍለን ከዛም ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦኝ ያሎነ ያሎነ ቦታዬን መነካካት ጀመረ። ነገሩ አላምር ሲለኘ ለመነሳት ሞከርኩ ግን በምን አቅሜ? ደሞ ባመልጠው እኳን በሩን ቆልፎታል። መታገል ጀመርኩ ማምለጥ አልቻልኩም እታገላለው እታገላለው ግን ከመዳፉ ማምለጥ አልቻልኩም ምንም ማድረግ ሲያቅተኝ እንባዬ ይንቆረቆር ጀመር ይኒፎርሜን ገልቦ የፈለገዉን ሊያረገኝ ሲል የአላህ ነገር በሩ ተንኳኳ።
......ያኔ ሚሆነውን አጣ እንባሽን ጥረጊ ብሎ ቶሎ ብሎ ከ ጠረቤዛው አውርዶ ልብሴን አስተካክሎ ካቆመኝ በኋላ በሩን ሊከፍት ተነሳ። እኔ ደንዝዤ ቆሜ ቀረው አላህ አባቴን በሚያክል በትልቅ ሰዉ በዳይሬክተሩ ሳያበላሸኝ የላከልኝ መለአክ መስሎ ታየኝ
.....በሩም ተከፈተ ከ አስተማሪዎቼ አንዱ ነበር
 .......እንዴ በዚ ሰአት በሰላም ነው በር የቆለፍከው ብሎ ሲጠይቀው
......ዳይሬክተሩም እቺን እብድ እያጫወትኳት ነበር አምልጣ እንዳትወጣብኝ ብዬ ነው ብሎ በሳቅ መልክ ነገረው።
......መምህሩም አልጠረጠረም።እኔ ግን አሁንም ቆሜያለው መምህሩም እንዴ ሲሀም ተደውሏል እኮ ምን ሆነሻል ሂጂ ጊቢ ብሎ በያዘው ዱላ አባረረኝ።
     ተደውሎ ከትምርት ቤት እስክወጣ ድረስ ከ ከድንጋጤየ አልነቃሁም ነበር። ህልምም መሰለኝ የሚያስጠላ ህልም በቅዠት የተሞላ የማይመስል ነገር።አባቴ ብዬ ከማስበው ሰው ለዛዉም ትዉልድን ለመቅረፅ ሀላፊነት የተሰጠዉ ዳይሬክተር የመድፈር ሙከራ ደርሶብኝ እንዴት እነቃለው? ከትምህርት ቤት ስንለቀቅ በመንገድ ወደ ቤቴ እየሄድኩ አለቅሳለሁ አለቅሳለሁ ግን አንድም እንባዬን ሚጠርግልኝ የለም።
    እቤቴ ደረስኩ ለ አጎቴ እና ለ አክስቴ ልጆች ማለትም ለሀፍሷ እና ለራዉዳ ልነግርራቸው አሰብኩ እቅፍቸው ስር ሆኜ ማልቀስ ፈለኩ ግን አልችልም ምክንያቱም እንደዚ ቀረቤታ የለኝም ዝም ብሎ ማልቀስ ብቻ ልክ እንደ እናት ይሆነኝ የነበረው ወንድሜም ለእነሱ ትቶኛል።
     እህህህህ ብዬ ላባቴ እንዳልነግረው ስሜን እኳን የሚጠራው ለ ቁጣ እና ለመላክ ሁኗል። ያኔ የምር እናቴ አጠገቤ በሆነች ብዬ ተመኘው 
ሲመሽ ሲመሽ መሳቀቅ ጀመርኩ ካባቴጋ መተኛት ሞት መሰለኝ እሱም እንደነሱ ሚያደርገኝ መሰለኝ። ብቻየን ለሊት አለቅሳለሁ አለቅሳለሁ ግን ምን ሆንሽ የሚለኝ የለም።ከማልቀሴ ብዛት እነሱ ለመዱት ሳለቅስ እንዳውም ይስቃሉ ጂኒዋ ተነሳ መሰለኝ ይላሉ።   
   ሁሉንም ነገር መቋቋም አቃተኝ የአጎቴ ልጅም ይበልጥ ጠላሁት። ቤት ሲመጣም እንባዬ ይነጉድ ጀመር እያደር እያደር ልቤ ቂም አዘለ። እንዳውም ሰላም ሲለኝ ፊቴ ይቀያየር ጀመር

እንግዳ ብቶንም አያምንህም ልቤ
ዘመዴ ብቶንም አይወድህም ቀልቤ
እንዳልመልስህ ከበሩ አልፈሀል
እንግዳ ነኝ በለህ በሰላም መተሀል
ምንም ብቀየምህ ብጠላህ ከሆዴ
መቼስ ፈርዶብኛል ልሳለምህ አንዴ

ያኔ ለሱ የገጠምኩት ግጥም ነው፡፡ እንዴት ሰዉ የራሱን ዘመድ የአጎቴ ልጅ ነዉ እንዴት ለስጋዊ ስሜት ይፈልገኛል፡፡ ለነገሩ ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ወንድም እና እህቶች ተቃራኒ ፆታ በ15 አመታቸዉ መኝታቸዉን ለዩ ልጁቹ አስተዳደጋቸዉ ፈጣን ከሆነም 15 አመት መጠበቅ አያስፈልግም የተባለዉ ሀዲስ ትክክል ነዉ ስንት የምናቃቸዉ ከወንድሞቻቸዉ የወለዱ ሴቶች እያስተዋልን ነዉ፡፡ የአጎቴ ልጅ እና ዳይሬክተሩ የመድፈር ሙከራ አርገዉብኝ ህይወቴን የለቅሶ ሂወት አደረጉት.... አባቴም እኔን ሊረዳኝ አልቻለም ሶላት መስገዱ ይቅር እና ማታ ማታ እየጠጣ እየመጣ እኔንም አስቸግሮኛል፡፡ ለአባቴ ሀይማኖት ጌታን መገዛት ማለት ረመዷን ሲመጣ ፆም መፆም እና የተመቸዉን ሶላት መስገድ ነዉ ..ረመዷን ሲመጣ ከረመዷን ቡሀላ ላልጠጣ ይላል ግን ማታ ላይ ረመዷን ፆም ከተፈታ ቀጥታ ወደ መጠጥ ቤት ነዉ........ ያልፍ ይሆን ?????

ገና #part 3⃣
ይ .................ቀ.............
.............ጥ.................ላ...............ል

ቤተሰብ አስተማሪ ስለሆነ ሼር አይዘንጉ

4 another channal👇
@Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
#ልብ___በል

☞ሰወች ምክንያት እየፈለጉ ካኮርፉህ ለመራቅ
ምክንያት እየፈለጉ ነው ንቃ

☞ደስታ ከአየር የሳሳ ነው ተንከባከበው

☞ ፍቅር ከእውቅና የጠለቀ ነው

☞ ወዳጅነት ከዳይመንድ #የጠጠረ ነው

☞ስኬት ደግሞ #ከወርቅ ያብረቀርቃል

ንፁህ የሆነ ፍቅር ንፁህ ልብ ብቻ ይቀበለዋል
እውቀትን⚂ አዕምሮ ብቻ ይቀበለዋል
#ንፁህ እጅ ስጦታ ያበዛል
የልብ ወዳጅ ይህን መልዕክት ይቀበላል

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸