ISLAMIC SCHOOL
12.6K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
😔 #የባከነ #ህይወት 😢
           #ክፍል 3⃣

#ፀሀፊ ☞ mahalet Ethiopiawt


      ጎትቶ ሲረግጠኝ በድንጋጤ ብርጭቆውን መሬት ላይ ከሰከስኩት 😢ጮህቴን ለቀኩት ሰውየው ደንግጦ በሩን ከፍተው እሩጨ ስወጣ ሰራተኘዋ በሩ ላይ ምን ሆንሽ አለችኝ ምን ሆንኩ ስላት ጮህትሽን ሰምቸ ነው የመጣሉት ለምን ጮህሽ ስትለኝ በድንጋጤ እየተንቀጠቀጦኩ አልጮኩም ብየ ሽምጥጥ አርጌ ካድኮት እሽ ብላ ወደስርዋ ተመለሰች እኔም ህፃኑን ታቅፌ ምን ማድርግ እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል ሴትዮ ከሰማች ከዚህ ቤት ታባረርኛለች የታባቴ ነው የምሄድ ብየ እያሰብኩ
     ሰውየው ካለሁበት ልጁን ልየው ብሎ መጣ ስሚ ለሚስቴ አንድ ነገር ትንፍሽ እላለው ብትይ አንገትሽን እቆርጥልሻለሁ ብሎኝ ወጥቶ ሄደ ከትንሽ ቀን በኃላ ሻንጠውን ይዞ ወደ ስራው ሄደ እሱ እንደሄደ ሴትዮዋ ጠራችኝ ስሄድ በሩን ዝጊው እና ቁጭ በይ የምጠይቅሽ ጉዳይ አለኝ ስትለኝ ደነገጥኩ እንደምንም እራሴን አርጋግቸ ቁጭ አልኩ ባለፍው ምን ሁነሽ ጩሀሽ ብርጭቆም ሰብርሻል ማን አስደንግጦሽ ነው እውነቱን ንገሪኝ ባሌ ነው ያስደነገጠሽ ስትለኝ አይደለም ምንም አልሆንኩም አልጮኩም አልኮት እውነትሽን ከነገርሽኝ አዲስ አበባ ቤተሰቦቸ ጋር እንድትኖሪ እልክሻለሁ እዛ ህፃንም የለም ስትለኝ ባሏ ሊደፍርኝ ሲል መጮሄን ነገርኮት በጣም ተናደደች ይህ ወራዳ የ11 አመት ህፃን ለመድፍር ይሞክራል በገዛ ቤቴ ብላ ቀወጠችው እሽ አንችን እሱ ሳይመጣ ቀድሜ ወደ አዲስ አበባ እልክሻለሁ አለችኝ
    ቃሏን አክብራ ሰውየው ሳይመለስ ወደ አዲስ አበባ ቤተሰቦቾ እንዲቀበሉኝ ደውልኩላቸው በአውቶብስ አሳፍራ ላከችኝ አዲስ አበባ መናሀሪያ ሲደርስ የሰው የመኪናው ብዛት አራሴን አዞርኝ ሰወቹ ወደ ቤታቸው ወሰዱኝ ልጆቹ 3 ወንዶች ናቸው ሁሉም ጎርምሳወች ናቸው አንዲት ሰራተኛ አለች የእኔ የስራ ድርሻ ቤት ማፅዳት የልጆቹን ልብስማጠብ አልጋቸውን ማንጠፍ ነበር አንዱ ልጅ አስቸጋሪ ነው ለሰው ክብር የለውም ሰራተኛዋን ይማታል ሁሌ ማታ ፊልም ኳስ ያያሉ እና ይህ አስቸጋሪ ልጅ የሚተኛበትን ፍራሽ ሳሎን ወስጀለት እዛ ላይ ተኝቶ ፊልም ያያል እስከ ሌሊቱ 6 ሰአት ከዛም በለይ ያመሻሉ ሲጨርሱ ፍራሹን አንስቸ ክፍሉ ወስጀ አልገውን አነጥፍለታለሁ
     ሁሌ እነሱን በመጠበቅ እንቅልፍ ሳልተኛ ቁጭ ብየ እጠብቃለሁ አንድ ቀን ማታ በጣም እንቅልፍ ሲይዘኝ ክፍሌ ገብቸ ተኛው ልጅ ፊልሙን ሲጨርስ ሲጠራኝ አልሰመውትም ክፍሌ መጥቶ በሩን ደበደበው ከእነ እንቅልፌ እሮጨ በሩን ስከፍት ለምን እኔ ሳልተኛ ቀድመሽ ተኛሽ ብሎ ፊቱ ላይ ባገኘው ፍልጥ እንጨት ሲመታኝ ለመከላከል እጀን ስዘርጋ የፍልጡ ስንጣቂ እጀ ውስጥ ገባ እጀ ደማ ደሜን በጨርቅ ጠቅልሌ ከሳሎን ፍራሹን አንስቸ ክፍሉ ውስጥ ጥየለት ተመልሸ ክፍሌ ገበው
   እጄ እየደማ አይዞሽ የሚለኝ ሳጣ አባቴን አስታወሰኝ አባቴ ልጀ እኔ በህይወት እያለው ከአንች አይኖች የእንባ ዘለላ ሲወርዱ ማየት አልፍልግም ይለኝ ነበር አባቴ ናፍቀኝ በጣም ከፋኝ ሆድ ባሰኝ ሳለቅስ ሳልተኛ ቁጭ ብየ ሳለቅስ ነጋ ሰራተኘዋ ምን ሆንሽ አይንሽ አብጦል ልጁ መቶሽ ነው አለች አወ አንች ግን እንቅልፍሽ ምን አይነት ቢሆን ነው ሳለቅስ ያልሰማሽኝ ስላት እኔ ከተኘው ምንም አልሰማም አለችኝ
     ቤት ለማፅዳት እጀን በጨርቅ ጠቅልየ የልጁ እናት አይታ ዝም ብላ ወደስርዋ ሄደች ምን ሆነሽ ነው አለማለቷ በጣም አናደደችኝ ከዚህ ቤት መውጣት አለብኝ ብየ አሰብኩ ግን እንዴት እና ወዴት ነው የምሄደው ይህን ሀሳብ ሳወጣ ሳወርድ መሸ ሴትዮዋ ማታ ቡና አፍሊ ስትለኝ ክሰል የለም አልኮት ሱቅ ገዝተሽ ነይ ብላ 5 ብር ሰጠችኝ ክሰሉን ሳልገዛ በዚው ጠፋሁ አስፓልት ስጓዝ የሆነች ልች የተቀቀለ ድንች ቁጭ ብላ ትሸጣለች ቀርብ ብየ ሰላም ስላት ምን ልስጥሽ አለች አንድነገር ትተባበሪኛለሽ ስላት እሽ አለች የማድርበት ቤት የለኝም ከአንች ጋር አብርሽ አሳድሪኝ ስላት ችግር የለም ታድሬለሽ ግን ድንች ልጨርስ ብላኝ አብረን ድንቹን ሽጠን ወደቤቶ ወሰደችኝ
    ልጅቶ ጋር አድሬ በጧት ልጅቶን አመስግኘ ቻው ብያት ከቤቶ ወጠሁ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ብቻ የማያልቀው አስፓልት እየመራኝ ጉዞየን ቀጠልኩ መድርሻ የሌለው መንገዱ ስጎዝ በግምት ከጦቱ 4 ሰአት ይሆናል መንገዱ ፀሀዩ ውሀ ጥሙ ጉልበቴን አዛለው ከእስፓልት ወጣ ብየ የሆነ ትልቅ ግቢ አየሁ ቀርቤ በር ሳንኳኳ ጥቁር ሴትዮ በሩን ከፍተችው ጥቁርቷ በጣም አስደንግጦኝ ቃላት ለማውጣት ትንፋሽ አጠርኝ……

#Part 4⃣

ይ............ቀ............
...........ጥ............ላ,............ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
          `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science


☑️ ሼር በማድረግ ለሁሉም ያድርሱ
👍1
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 2⃣4⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal


    እኔም እናት እና አባቴ በዚህ ጉዳይ ሲጣሉ ሲቸካቸኩ አባቴ አይሆንም እያለ ሲጮህ ይህ ችክችክ ወደ ሌላ ወደ ቤተሰብ ፀብ እንዳይዞር እኔዉ እራሴ መፍታት ማስታረቅ አለብኝ ብየ ወሰንኩ ግን አባቴን ማሳመኑ አደራዉ እኔ ጋር እንደሆነ ተገነዘብኩኝ ...በራስ መተማመን ይዤ አባቴ የተናገረኝን ቢናገረኝ ላልቀየም ላላለቅስ የአላህ ቀድር ከሆነ በእኔ ምንም መለወጥ አልችልም ብየ አስቤ.. እራሴን አሳምኜ በሩን ስከፍተዉ እናት እና አባቴ መቸካቸካቸዉን አቁመዉ ሁለቱም ወደ እኔ ትኩረታቸዉን አደረጉ፡፡ ቤቱ ፀጥ አለ ማን ወሬ እንደሚጀምር አስፈራኝ ግን እኔ መጀመር እንዳለብኝ ተረዳሁ ...ወደ አባቴ ጎን ሂጄ ቁጭ አልኩኝ
    አባቴ ምነዉ እናቴ ጋር አለመግባባት ምን ተፈጠረ አልኩት ነገሮችን እንዳልሰማሁ ሁኜ
.....እሱም የምሰማዉ ነገር እዉነት ነዉ እንዴ??? አለኝ
.....እኔም እዉነት ቢሆን ለአንተ ደስ አይልህም እንዴ?? አልኩት
.....እሱም የጠየኩልሽን አጭር መልስ ንገሪኝ ከአፍሽ ልስማዉ አለኝ
...እኔም ከእኔ መነገሩ ጥቅም የለዉም እናቴም ነግረሀለች አዎ እዉነት ባቢ ዙበይርን ነገ እናንተን ላስተዋዉቅ ምሳ ጠርተነዋል ከነ እህቱ አልኩት
....አባቴም እኔ አባትሽ አይደለሁ እስከ አሁን እንዴት ሳትነግሪኝ እኔ የልጄን ሂወት መወሰን አልችልም ማለት ነዉ?? ቢሆንም ባይሆን እንዴት አንድ ቀን ሲቀረዉ ትነግሪኛለሽ ?? እኔ ከእናተ እርቄ የመንግስት መስሪያ ቤት የምሰራዉ አስተካክየ ቁርስ በልቼ ምሳ በቅጡ የማልበላዉ ለማን ብየ መሰለሽ ለአንድ ፍሬ ልጄ ለአንቺ ብየ እኮ ነዉ፡፡ በጣም ጥፋተኞች ናችሁ አዝናለሁ አለኝ፡፡
 አባቴ እዉነቱን ነዉ የቤተሰብ ፍቅር እርቆ  በአገኘዉ የወር ደመወዝ ነዉ የሚያስተዳድረን ግን ዙበይር ጋር እዚህ ደረጃ ለትዳር እንደርሳለን ብየ ትዝም ብሎኝ አያቅም..... ደግሞ ቀድሜ ብነግራቸዉ ይሆናል ብየ ባይሳካ ቤተሰቦቼ እኔን ምን ይጠረጥሩኛል ?? አጃጅሎ ተዋት ብለዉ ወይ እኔን አያምኑኝም ወይ እሱ ጋር ፀብ እንደሚኖር መዘንጋት የለብኝም፡፡
   አሁን ያለኝ አማራጭ አባቴ ያለኝን የጠየቀኝን ከመመለስ እኔ ይቅርታ ብለዉ የተሻለ መሰለኝ፡፡ ከአባቴ ጎን ተነስቼ  ከእግሩ ስር ተደፍቼ አባቴ ጥፋተኛ ነኝ ይቅር በለኝ እኔ እንደዚህ ይከፋሀል ብየ ትዝም አላለኝ ሰርፕራይዝ ላረግህ ነበር ሀሳቤ ይቅር በለኝ እኔ ይሄ ትዳር ይሆናል ብየ አላሰብኩትም ለእናቴ እንኳ የነገርኳት ከሶስት ቀን በፊት ነዉ እኔ ዙበይር የሂወት አጋሬ ይሆናል ብየ አስቤዉም አላቅ አዉፍ በለኝ ብየ አለቀስኩኝ አባቴ እግር ላይ ተደፍቼ፡፡
    አረ ልጄዋ አታልቅሺ እኔ የአንቺን ለቅሶ አልፈልግም ሀገር ለሀገር የምዞረዉ አንቺ ደስተኛ እንድትሆኝ ነዉ አዉፍ ብየሻለሁ ብሎ ግንባሬን ሳመኝ
እኔም በደስታ እሺ የነገዉን ምሳ ፕሮግራም እዚሁ ልትገኝ ተስማማህ?? አልኩት
   አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ አለኝ ለእሱ ብዙ ነገር ጠየቀኝ መለስኩለት የጓደኛየ ወንድምም እንደሆነ..እናቴ እንደጠየቀችኝ ሀብቱን አይተሽ እንዳይሆን አለኝ፡፡ እኔም በጭራሽ ይሄ እንዳለዉ ያወኩት ቅርብ ቀን ነዉ እኔ መስፈርቴ ብር አይደለም ነበር እኔ ማንነቴን አዉቆ ስለተቀበለ ነዉ የመረጥኩት አልኩት
    አባቴም ግን ልጄ እኔ የጠየቁኝ አሉ እሺ ከህመሟ ይሻላት እያልኩ መልሻለሁ  የነገዉን ምሳ ችግር የለም እንተዋወቃለን ፡፡ ግን ብትረጋጊ እና እኔ የጠየቁኝን ሰዎች አጥንተሽ ለምን መርጠሽ አታገቢም አለኝ
እኔም ሳቅ እያልኩ አባቴ የመጡልኝ እኮ ማንነታቸዉን አላዉቅም ፀባያቸዉን ከኔ ምን እንደሚፈልጉ የማቀዉ የለኝም ዙበይር እኮ ከኔ የሚፈልገዉ ፍቅሩን እና የትዳር አጋሩ እንድሆን ነዉ፡፡ አንተን የጠየቁህ ለክብራቸዉ ለዘራቸዉ ሊጨነቁ ይችላሉ ደግሞ መቀራረብ እንጠናና በሚለዉ እኔም የእሱን ፀባይ ልወቅ ስል እሱም የኔን ፀባይ ልወቅ ሲል መቀራረብ አላህ ብዙ የከለከሉ ወንጀሎችን ልንሰራ እንችላለን ፡፡አንተ አስተዋወከን  ቀርባችሁ ተዋወቁ ነዉ የምትለን ..ቀርባችሁ ተዋወቁ  ማለት ከዚህ የባሰ ምን ይፈጠራል አባቴ አልኩት
   እሱም ይሄ ቂርአት ብዙ አስተምሮሻል ብሎ እየሳቀ እሺ ይሁና ልጄ እኔ የምፈልገዉ አግብተሽም ደስታሽን ነዉ አለኝ ቤቱ በደስታ አባቴም እናቴም እኔም ተቃቀፍን የቅድሙ ጭቅጭቅ በጠረንቤዛ ዙሪያ ዉይይት በመሰለ አጀንዳ በሰላም በፍቅር ተፈታ ቤታችን በአንዴ ወደ ቤተሰብ ፍቅር ዞረ ፡፡
    ቤተሰብም ጋር ሳያለቅሱ ተረጋግቶ ማዉራት ጥቅም አለዉ፡፡ ግን አንዳንድ እህቶቼ ይዘሀኝ ጥፋ...እሱን ካልዳራችሁኝ እታነቃለሁ በሂወት አታገኙኝም የሚሉ አሉ ይሄ አግባብ አይደለም ማንኛዉም ቤተሰብ ለልጆቹ ክፉ አይደለም ብቻ የትዳር ሂወት ማለት ሁለተኛ ሂወት ስለሆነ ቤተሰብም በትንሹም ቢሆን ጣልቃ መግባቱ አይቀሬ ነዉ፡፡ ትዳር ጋር አለመስማማት ቢኖር ተመልሰን የምንመጣዉ ወደ ቤተሰብ ነዉ፡፡
   
እሷ እና ጠቢቡ

#እሷ👇
አምላክ ልጠይቅህ ፍቅር ግን ምንድነው
ያኛውም ይሄኛውም ወደድኩሽ የሚለው
የቱ ነው የወደደኝ የቱ ነው ያፈቀረኝ
አንተው መልስልኝ እኔስ ግራ ገባኝ

#ጠቢቡ👇
ልጄ ተባረኪ ጥሩ ጥያቄ ነው
መውደድ በጣም ብዙ ማፍቀር ግን 1 ነው
አንቺን የሚወዱሽ ተቆጥረው አያልቁም
ያፈቀረሽ ሰው ግን ከ 1 እንኳን አይበልጥም

#እሷ👇
እንዲ ከሆነማ አፈቀርኩሽ ያሉኝ
ከ 1 እኮ ይበልጣሉ መጥተው የጠየቁኝ
ከነዛ ሰው ሁሉ ተድያ እንዴት ልለየው
የእውነት እፍቃሪ ምልክት ምንድነው

#ጠቢቡ👇
በማስመሠል ዘመን ማመኑ ቢከብድም
የእውነት ፍቅርን ግን መለየት አያቅትም
ተወኝ ብትይውም ሊተውሽ ቢፈልግ
ልቡ ግን አይፈቅድም ይሄንን ለማድረግ

አንቺን እንዲተውሽ ፊት አንኳን ብትነሺው
ፊትሽን ይተውና ልብሽን ነው የሚያየው
አፈቀርኩሽ ብሎ ፅናቱ ካልታየ
የውሸት ፍቅር ነው እለፊው ባላየ
#ምንጭ_anu

 ቅዳሜ ተሻግረን እሁድን የወፎች ጫጫታ አስተጋባ ትናንት ጀምሮ እናቴ ጋር አብሬ ደፋ ቀና እያልን ነዉ ስድስት ሰአት ላይ ስራዉን አጠቃለልን ስድስት ተኩል ሲል ከፊርዶስ ስልክ ተደወለ.... ስልኩን አነሳሁት ..ፊርዶስም ማመን የማልችለዉን በስልክ ነገረችኝ.....
ምን ተፈጥሮ ይሆን ?? የሂክማ ነገር አንዱን ፈተና ስጨርስ ሌላ የማትወጣዉ ፈተና ይመጣባታል ...


   የሂክማ ታሪክ በመጨረሻዉ ክፍል እና በማጠቃለያ ፁሁፋችን ይጠብቁን ...

4 another channal👇
@Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
🥰1
💐ያለ ኒካህ የተጀመረ ፍቅር መጨረሻው ፀፀት ነው ።
በፍፁም ርካታ የለውም።

#ትሰማለህ
ከወጣቶች በነርሱ አሥተሣሰብ ለአንድ ሰሞን ቅምጥ ይይዙና እወዲሻለሁ እወዲሀለሁ ይባባላሉ።

ሞት ብቻ ነው የሚያለያየን ይላሉ

በቅፅበት ተለያይተው ሲተቻቹ ትሰማለህ እና ሞተው ነው እንበል??

ደግሞኮ በኒካህ የተጀመረ ፍቅር ሞትም ቢሆን አይለያቸውም።
ከሞት በኋላ ህይወት የለም እንደ
ያውም የተዋበ ጀነት ነዋ!

⭐️ችግሩ ጀነት የተዘጋጀው ለአማኞች እንጂ ለተጀናጃኞች አይደለም ንቃ አንተ ወጣት አደራህን

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#አጭር_ #ናት

⭐️የሙስሊሞች እና የፐርሽያን ወታደሮች የሰይፍ ትንቅንቅ ሊያደርጉ ሁለቱም በተንጣለለ ሜዳ ላይ ተሰልፈዋል። ከሁለቱም በኩል እሚታየው ትዕይንት ያስፈራል።
ግጥሚያው ከመጀመሩ በፊት ሁለቱም ቡድኖች ተርታቸውን ይዘው ለጥቂት ደቂቃዎች ከተዛዛቱ በኋላ ያለምንም ማስጠንቀቅያ ፐርሺያኖቹ የጦር አንበሳቸውን ወደ ሙስሊሙ ቀጠና ሰደዱ።
ድልብ #አንበሳውም የፐርሺያኖቹን ሰልፍ አልፎ እየጋለበ እና እያቧራ ወደ ሰሀቦች ሰልፍ መገስገስ ጀመረ።
🌿🌿🌿🌿ይህን የተመለከተ አንድ ሰሀቢይም የሙስሊሙን ሰልፍ ሰንጥቆ በመውጣት አንበሳውን ሊጋፈጥ ወደሱ አቀና።
ይህ ሲሆን የሁለቱም ሰራዊቶች ትዕይንቱን በዝምታ እየተከታተሉት ነው።ይህ ጀግና ካሄዱ አንበሳን ሊጋፈጥ ሳይሆን አንበሳው እሱን ሚጋፈጥ ነበር እሚመስለው።
አንበሳውም እየጋለበ ሰሀቢዩም እየረጡ እኩል ሜዳ ላይ ተጋጠሙ።ሰሀቢዩ ብልህ ጀግና ነበር'ና በአንበሳው ጀርባ ላይ ዘሎ በመውጣት በላዩ ቁጭ ብሎ በሰይፉ ይቆራርጠው ጀመር። በመጨረሻም እላዩ ላይ ሁኖ አንበሳውን አሰናብቶ ወደ አጋሮቹ ተመለሰ።

⭐️ይህን የተመለከቱ የፐርሺያ ሰራዊቶችም አንበሳ ከማይፈሩ ህዝቦች ጋር መጋፈጥ ቢከብዳቸውም ሰልፉን ትተው ከመሸሽ መጋፈጥን መርጠው ለሰሀቦቹ ሰይፎች እራት ሁነው አደሩ።(ሰሀቦቹ ድልን ተጎናፀፉባቸው)
በግዜው የሰሀቦቹ የጦር አዛዥ የነበረው ሰዕድ ኢብን አቢ ወቃስ ጦር ከተረጋጋ በኋላ አንበሳውን ወደ ገደለው ጀግና በመሄድ ግንባሩን ሳመው።
#ያጀግናም ከፈረሱ ወርዶ ዝቅ በማለት የጦር አዛዡን እግር በመሳም፦"ያንተ አይነቱ የኔን ግንባር ሊስም አይገባም" ብሎ ኢስላማዊ መተናነስን በታሪክ መዝገብ ላይ አሰፈረልን።


✔️ይህ ጀግና ስሙ hashim ibn utba ይባል ነበር። ታሪኩ እንደሰሃቦቹ አጥንት በፐርሺያ በረሀ ላይ መቅረት የለበትም ሼር እያደረጋችሁ አስትላልፉ።
_________________________

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
ዕንባ !!!
መከፋት ሲበዛ... በደል ሲጠራቀም ..መተንፈሻ ጠፍቶ
መገፋት ሲጨምር ....ብሶቱ ሲከፉ ..መታፈን በርክቶ
የስቃዩ ብዛት ..መድረሻ ሲነሳው ...ካቅም በላይ በዝቶ
እንኩዋንስ የሰው ልጅ... እንሰሳም ያለቅሳል.. ያውም እንባ አውጥቶ

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
⭐️⭐️
ሁላችንም በማያቀን ሰው ዘንድ ተራዎች ነን
በሚጠሉን ዘንድ የማንረባ ነን
በሚረዱን ዘንድ ምርጦች ነን
በሚወዱን ዘንድ ተቀዳሚ ነን
በሚመቀኙን ዘንድ መጥፎዎች ነን
ለሁሉም የራሱ ምልከታ አለውና ሌሎች ዘንድ
ምርጥነት ለማግኘት ብለህ አትድከም
የፈጣሪህ ውዴታ ይበቀሀል "

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
#ወሳኝ #መልእክት #ለወንዶች🕶
===================
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " مَنْ كَانَتْ لَهُ امْرَأَتَانِ فَمَالَ إِلَى إِحْدَاهُمَا ؛ جَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَشِقُّهُ مَائِلٌ ".
አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ
ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል
" ከእናተ ውስጥ ሁለት ሚስት ያለው ወደ አንደኛዋ የሚያደላ( የሚያዘነብል) ከሆነ የቂያማ ቀን አንድ ጎኑ ያዘነበለ (ያጋደለ) ሆኖ ይመጣል።
አቡ ዳውድ፣አህመድ፣ነሳኢ፣ቲርሚዚ እና ኢብን ማጃህ ዘግበውታል ሸይህ አልባኒ ሰሂህ (ትክክለኛ)
ብለውታል

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
😔 #የባከነ #ህይወት 😢
           #ክፍል 4⃣

#ፀሀፊ ☞ mahalet Ethiopiawt


    በር ሳንኳኳ ጥቁር ሴትዮ በሩን ከፍተችው ጥቁረቷ በጣም አስደንግጦኝ ከአንደበቴ ቃላት ለማውጣት ትንፋሽ አጠርኝ ሴትዮዋ በሁኔታየ ግራ ተጋብታ
...... ልጀ ቤትሽ ጠፍቶብሽ ነው አለችኝ አ አ አይደለም አልኮት እየተንተባተብኩ
.....ታዲ ምን ፍልገሽ ነው ስትለኝ ውሀ ውሀ ጠምቶኝ ስላት እኔን ይጥማኝ ነይ ግቢ ብላ እንድገባ የበሩን መንገድ ለቀቀችልኝ ወደውስጥ ስገባ ቤቱ የተዋበ ነው የሀብታም ቤት ይመሰላል ሴትዮዋ ወደሳሎኑ አስገብታኝ ሶፋ ላይ ተቀመጭ ብላኝ ሌላ ልጅ ተጣራች የተጠራችው ልጅ አቤት ብላ መጣች ለእንግደዋ ምግብ ከውሀ ጋር አቅርቤ አለቻት ሴትዮዋ እንደ  መልካም ሳትሆን አትቀርም አልኩ በልቤ
     ልጅቶ ምግቡን ስታቀርብልኝ በፍጥነት ስበላ ሴትዮዋ እያየችኝ እንደነበር ያወኩት ምግቡን ጥርግ አድርጌ በልቸ ቀና ስል ነበር ልጀ ከቤተሰብ ጠፍተሽ ነው አለችኝ አወ አልኮት ሀገርሽ የት ነው ስትለኝ ሀገሬን ነገርኮት  አዲስ አበባ ማን አመጣሽ ህፃን ነሽ ስትለኝ እንዴት እንደመጠው ዘርዝሬ ነገርኮት አዘነች እኔ አሳድግሻለሁ ከዛሬ ጀምሮ ልጀ ነሽ ልጅ የለኝም አሁን ምግብ ያቀርበችልሽ ሰራተኘየ ናት ስትለኝ በልቤ ፍጣሪየን አመሰገንኩ
    ከዚች ቀን ጀምሬ ሴትዮዋ ጋር መኖር ጀመርኩ አንድ ቀን ሴትዮዋ ጠርታ ለምጠይቅሽ ጥያቄ ሳትዋሽ ትክክለኛ መልስ ስጭኝ አለችኝ እሽ አልኮት የወር አበባ ታያለሽ ስትለኝ አላይም አልኮት ድንግል ነሽ የሷው ጥያቄ ነበር አወ አልኩ ፊቶ ላይ የደስታ ስሜት አየውባት ምን አስባ ነው አልኩ በልቤ በቃ ከዛሬ ጀምሮ ቡና የምታፍይልኝ አንች ነሽ የወር አበባሽ በመጣ ጊዜ ነገሪኝ ለእኔ ቡና የምታፍላልኝ ሴት የወር አበባ የማታይ እና ከወንድ ጋር የማትገናኝ ናት ታዳ ቡናው ከቀኑ 6 ሰአት አንዲት ደቂቃም ማለፍ የለበትም በይ አሁን 5:30 ሁኖል ቡና አቀራርቢ አለችኝ እሽ ብየ እንደታዘዝኩት ቡናውን ሳፍላ አንዲት ጓደኛዋ መጣች ወዲው አንድ ሰውየ ጫት  ይዞላቸው መጣ እኔ ቡናውን እያፍለው ይቅማሉ ያጨሳሉ ቤቱ በጭስ ታፍነ ፍጣሪየ ምን ጉድ ነው አልኩ በልቤ
     ኩሽና ሂጀ ሰራተኛዋን ሁሌም እንደዚህ ይቅማሉ ስላት አዎ የለት ከእለት ተግባራቸው ነው አለችኝ እኔም ቡና ማፍላት የእለት ከእለት ተግባሬ ሁኖል ሴትዮዋ ከቤት ወጥታ ስትመለስ ልብስ ጫማ ቁሳቁስ ገዝታ ታመጣልኛለች ጥሩ ናት ያልተመቸኝ ሲጋራ ጫት እና እምታጨሰው እጣን ያስጠላኛል እኔም ሰራ ለምጃለሁ እንጀራ እጋግራለሁ ወጥ እሰራለሁ ሁሉንም ስራ እችላለሁ
    አንድ ቀን ሰራተኘዋ እርፍት ወጣች ሴትዮዋ ስብሰባ አለብኝ ብላ ሁላቸውም ወጥተው ሄዱ ብዙ ስራ ነበርብኝ እሱን ስሰራ የ 6 ሳአቱን ቡና ሳላቀራርብ ሴትዮዋ 6 ሰአት ስትመጣ ምንም አላቀራርብኩም እንደእብድ ጮህች መሬት ላይ ወድቃ ስትፍራገጥ ደንግጨ እየሮጥኩ ጓደኛዋን ጠረሇት ከጓደኛዋ ጋር እየሮጥን ቤት ደርስን ሴትዮ አሁንም እየጮህች መሬት ላይ ትንከባለላለች ሁኔተዋ አስፍርቶኛል
... ......ጓደኛዋ ሻንጣ ከፍታ ሽቶ እጣን አምጣት ታጨሳለች ሽቶውን መሬት ላይ ደፋችው ቡና ቁይ ፍጠኝ አለችኝ ቡናውን ቆልቸ ጭሱን ታጠነችው ፍጣሪየ ምን ጉድ ነው ሴትዮዋ ሳይጣን ታመልካለች ለነገሩ መልኳም ጥቁረቷ ሰይጣን ነው የምትመስል አልኩ ለራሴ ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ተሽሎት ቡናውን ጠጣች ጫቶን ማድቀቅ ጀመርች
    ከዚች ቀን ጀምሮ ለእኔ ያላት ስሜት ቀነሰ ሂሳብ ስሌት ትችያለሽ ስትለኝ አወ ልኩ 3 ቦታ ሆቴል አለኝ ከአንዱ ወስጀሽ እዛ ሂሳብ ትቆጣጠሪልኛለሽ አለችኝ ደስ አለኝ ከዚህ ለእሷ ቡና ሳፈላ ከመዋል ልገላገል ነው አልኩ ሆቴሉ ስንሄድ ብዙ ሰራተኞች አሉ አንድ የሴትዮዋ የወንድም ልጅ አለ ተጠርቶ መጣ ለትውውቅ  ጌታነህ እባላለሁ ሲለኝ ማርታ አልኩት እሱ ነበር ሂሳብ ተቆጣጣሪ ከዛሬ ጀምሬ ሀላፊነተን ለአንች ሰጥቸሻለሁ አለች ሴትዮዋ ጌታነህ ተገላገልኩ ሂሳብ ጎደለ ብለሽ አተጨቃጨቂኝም ብሎ ወቶ ሄደ እኔም ሀላፊነቴን ተቀብየ በሚገባ መስራት ጀመርኩ
      ጌታነህ ስራ የለውም በፍለገበት ቦታ ሲዞር ይውላል ሴትዮዋ ደመወዝ አትከፍለኝም ወደ ቤተሰብ መሄድ እንደምፍልግ ስነግራት ሀገርሽ እሩቅ ነው ለመኪና 3000 ብር ያስከፍላል ስለዚህ ብዙ አመት ከሰራሽልኝ በኃላ እኔ ብሩን ከፍየ እልክሻለሁ እለችኝ እኔም እሽ ብየ እሰራለሁ አሁን 16 አመት ሞልቶኛል የቤቱ ከስተምሮች አደገች ልጅሽ ይሏታል ለሴትዮዋ ለእኔ ትድሪልኛለሽ ሲሎት አይ እሷን ውጭ ሀገር ነው የምልካት ትላለች እንዲህ ስትላቸው እኔ ደስ ይለኛል
    ከጌታነህ ጋር ቅርርባችን ጠንከር ብሎል ጌታነህን ሳየው ልቤ ይደነግጣል እሱም ከእኔ ጋር ማዉራት ይወዳል አንድ ቀን ማታ ሆቴሉን ዘጋግተን ሰራተኞቹም ክፍላቸው ገብተው ተኝተዋል እኔም ልተኛ ክፍሌ ገብቸ ሻወር ለመውሰድ ስዘጋጅ በሬ ተንኳኳ ማነው ስል እኔ ነኝ አለ ጌታነህ ነበር.....


#Part  5⃣

ይ............ቀ............
...........ጥ............ላ,............ል


JOIN ISLAMIC SCHOOL
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
          `·.
@Islam_and_Science          @Islam_and_Science
 

☑️ ሼር በማድረግ ለሁሉም ያድርሱ
👍1
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
#የመጨረሻዉ #ክፍል
   ፊርዶስ ደወለች ስልኩን አነሳሁት ...ምንም አልተፈጠረም ለወሬ አቸኩሉ 😊
  .....ፊርዶስ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ  አንድ ነገር ልጠይቅሽ ነበር አለችኝ
......እኔም ምን ነበር ፊርዱ አልኳት
........እሷም ምሳ የጠራችሁን ሁለታችን ነበር ግን አንድ ሰዉ አብሬ እናንተ ጋር ካልሄድኩ አለን ምን ትያለሽ ሂኩ
.....እኔም ችግር የለም እሄዳለሁ ያለዉን አብራችሁ ኑ አልኳት
....ፊርዱም የዛሬዉ ቀን እኮ ለ ዙበይር
 ታላቅ ቀን ነዉ ትናንት ቅዳሜ አዳር እንቅልፍ ሳይወስደዉ ነዉ ያደረዉ በደስታ ተባብለን ተሳስቀን ፊርዶስ አሁን ከቤት እየመጣን ነዉ ብላ ነገረችኝ፡፡ እኛም ተዘጋጅተን ነዉ እየጠበቅናቸዉ ያለነዉ...
      ከ30 ደቂቃ ቡሀላ እቤት ደረሱ ፡፡ ወደ ቤት ሲገቡ ያየሁትን ማመን አቃተኝ የፊርዶስ እናት አብረዉ መጥተዋል ቅድም ደዉላ አንድ ሰዉ ይዤ ልምጣ ያለችዉ እናታቸዉን እንደሆነ ተገለፀልኝ ፡፡ የእኔ እናት እና አባት ብድግ ብለዉ ተቀበሉ ፊርዶስ የእኔን እናት ከእሷ እናት አስተዋወቀች አባቴንም ..የፊርዶስ እናት  እና የእኔ ቤተሰቦች ሲያወሩ ዛሬ አዲስ የተገናኙ አይመስሉም ነበር በጣም ደስ አለኝ ፡፡
     ዙበይር ግን ፈርቶ ዝም ብሏን አባቴ አብሽር ተጨዋት አትፍራ እንጂ እያለዉ ነዉ፡፡
 ከዛም ምሳችንን በልተን ጨረስን ቡናዉ ተፈልቶ ተመራርቀዉ ቡናዉን ተጠጥቶ ከጨረሱ ቡሀላ የዙበይር እናት እስኪ የመጀመሪያ ስለሆነ ማስታወሻ  ብለዉ የተጠቀለለ ስጦታ ሰጡን ስጦታዉ ለእናቴ የሚያምር ድርኢና ጎጎራ እና የሚያምር ጫማ ሲሆን ለአባቴ ደግሞ ሽቶ የዙበይር እናት አበረክተዉ ለምሳዉ ፕሮግራም አመስግነዉ ተመራርቀዉ ተለያዩ  እናቴም አባቴም በጣም ተደስተዉ ከአሁን ቡሀላ ምን ቀረ እንግዲህ ልጄ ያሰብሽዉን አላህ ያሳካልሽ ብለዉ አባቴም እናቴም መረቁኝ፡፡
    ማታ ላይ ዙበይር ደወለልኝ ብዙ ነገሮችን አዉርተን ሂኩ መኖሪያ ቤቴን ያከራየሁትን ሰዎቹን ቤት እንዲፈልጉ ደዉየ ነግሪያቸዉ እሺ በቅርብ ቀን ለቀዉ እንደሚወጡ ነግረዉኛል ስለሆነም ተዘጋጂ ብሎ ነገረኝ፡፡
እኔም እሺ  አልኩት
ዙበይርም ሂክማ እወድሻለሁ አላህ ሀላሌ ስላረገኝ የአንቺ በጣም ደስተኛ ነኝ አለኝ፡፡
እኔም እወድሀለሁ ዙበይር አንተ ማለት የሂወቴ ብሩህ ተስፋየ ነህ ጥሩ ልጅ ወልደን በዲነል ኢስላም ገንብተን እንደምናሳድግ ይታየኛል ኢንሻ አላህ አልኩት፡፡ ብዙ ደቂቃዎች አዉርተን ተሰነባብተን ወደ መኝታየ አመራሁ፡፡ የእኔ እናት እና የዙበይር እናት በስልክ ማዉራት መቀራረብ ጀምረዋል በጣም ደስተኛ ነኝ
   ፊርዶስም እቤት መቼ ሽምግልና እንላክ ብላ ጠየቀችኝ ...ቤተሰቦቼን ጠይቄ የሚመችባቸዉን ቀን ቤተሰቦቼን ጠይቄ ለፊርዶስ ነገርኳት
ዙበይርም መኖሪያ ቤቱ አስለቅቆ የቤት እቃ እያሟላ ነዉ ፡፡ በስልክ ቀን በቀን እያወራን ነዉ አልፎ አልፎ በአካል እንገናኛለን ግን ተሳስመን አናቅም የወደፊት መሆን ያለባቸዉን ተወያይተን እንለያያለን....
   ሸምግልና የሚልኩበትን ቀን ቤተሰብ የሚመችባቸዉን ጠይቄ ለዙበይር ነገርኩት..... አስታዉሳለሁ ቅዳሜ ቀን የዙበይር አባትን አብሮ በመምጣት እስከ 10 የሚደርሱ ሽማግሌዎች መጥተዉ ልጅህን ለልጄ ተባብለዉ ለዙበይር ታጨሁ ...በዛዉም የሰርጉን ቀን ተቆርጦ ሽማግሌዎቹ ተመለሱ ....በጣም በሂወቴ ደስተኛ እየሆንኩ ነዉ የዙበይር የሰራዉ የመኖሪያ ቤት ሸጎሌ መንገድ 7 አካባቢ  ነዉ፡፡ ምን የራሱ ለወደፊት አብረን ልጅ ወልደን የምናሳድግበት ቤት ነዉ እንጂ
   የሰርጉ ቀን ደረሰ ሰርጋችንንም ..
ሁለታችንም ተነጋግረን ጦር ሀይሎች አካባቢ በሚገኘዉ  በኡማ ሆቴል ነበር ፡፡ ፊርዶስ ለኔ የመጀመሪያ ሚዜ ሆነች ሁለቱ ሚዜዎቼ ደሴ ከተማ ካሉት የአጎቴ ልጆች አረኩኝ  ..ፊርዶስ ለዙበይር መጀመሪያ የሱን ደስታ ያስቀደመች እህቱ ለእኔ ደግሞ የዲን እህቴም ጓደኛየም ..የወንድሟ ባለቤት(አይቷ)  ነኝ፡፡ ሰርጉ በሚያምር ዘመድ ጓደኛቼ በተገኙበት በአማረ ሁኔታ በኡማ ሆቴል ተፈፀመ፡፡ ፊርዶስ ጋር ከበፊቱ በበለጠ ከአገባሁም ቡሀላ ተቀራርበናል ደስ የሚል ሂወት እየመራሁ ነዉ፡፡

 አንተን ያወቅኩ ለታ
የዛን እለት ማታ
ትዝ ይልሀል ያኔ
ያወራሀኝ አንተ የወደድኩህ እኔ
ያን ምገዛውን ፈጣሪዬን ትቼ
ህጉን ተላልፌ ራሴን ሰዉቼ
      ትዝ ይልሀል ያኔ🤔
መዉደድህ ሲያሰክረኝ
ፍቅርህ እንዲያ ሲያንገላታኝ
መውደድህ የእውነት
ማፍቀርህ የእውነት
ማውራትህ የእውነት
ሁሉም ነገር እውነት መስሎ ያዘናጋኝ
ትዝ ይልሀል ያኔ
ከቤት  ተደብቄ ምክንያት ፈጥሬ
የውሸት  ጋጋታ  አውርቼ ደርድሬ
አንተ ጋር ለመምጣት ብዙ ቀባጥሬ
  ትዝ ይልሃል ያኔ
አሁን  አስብና ያን ሁሉ መሆኔ
ፈገግ  እላለሁ አወይ ስልጣኔ
  ለካ
ፍቅር የሚሠምረው
ፈክቶ  የሚጠነክረው
ከአላህ  ጋር ሁኖ የተመሠረተ ነው
በትላንቴ አፍራለሁ በዛኛው ዘመኔ
     ግና
መሀሪው ጌታዬ እስኪ ተቀበለኝ ፀፀት  ፍራቻዬን
አዲሱን ህይወቴን ካንተ ጋ ልጀምር
አንተ የገባህበት አያውቅም  ድንግርግር

    ፊርዶስ ከእኛ ሰርግ አራት ወር ቡሀላ ስለታጨች  የምታገባበት ቀን ደርሷል ......እኔም ዙበይር ጋር ጥሩ የትዳር ሂወት መኖር ጀመርኩ፡፡ ሁሉም ወንድ አንድ አይደለም ለምን ሁሉም ሴት አንድ ስላላይደል...አንድ ሰዉ የምንቀርበዉ የምንወደዉ ሰዉ ሲሸዉደን መጥፎ ስራ ሲሰራብን ጥሩ ሰዉን ማመን ስለሚያቅተን ሂወታችን ህልማችን ዳግም  አይሳካም በሚል እኔ ዙበይርን ላጣዉ ነበር፡፡ የሰዉ ልጅ ነን እና እንሸወዳለን ግን ከተሸወድን ቡሀላ በዛ ነገር ላይ ቋሚ ወንጀለኛ መሆን የለብንም ወደ አላህ መመለስ መቻል አለብን፡፡ ዙበይር ጋር በደስታ በፍቅር እየኖርኩ ነዉ .. በቅርብ ቀን ደግሞ ፊርዶስ ልታገባ ነዉ እኔም የመጀመሪያ ሚዜየ አንቺ ነሽ ተዘጋጂ ብላኝ ዝግጅት ላይ ነኝ፡፡

እህቶቼ  ብዙ ሴቶች በቻት የሚያወሩ አሉ ቻት እና የተለያዩ group እንደ እኔ እንደሚጎዱ ከመቶ አንድ የሚቆጠሩ እንደዙበይር ያሉ ወንዶችን ለማግኘት በቻት ሳይሆን በዱአ ነዉ እንጂ በቻት አይደለም ቻት የዚና መስመር ነዉ እንጂ የትዳር መስመር የሚጀመረዉ በኒካህ ነዉ፡፡ አንዴ በራስሽ ፍቃድ ሂወትሽን አበላሽተሽ ፈጣሪሽን አታማሪ ወንድንም አታማሪ መጀመሪያ ብልጥ መሆን ያለብሽ አንቺ ነሽ ሴት ልጅ ክብር ነሽ ..ክብርሽን በማያቁ ወንዶች ክብርሽን አትነፈጊ
  ታሪኬን እዚህ ላይ ጨረስኩኝ፡፡

#ተ........ #ፈ....... #ፀ....... #መ

እንዴት ነበር እኔ ከደሴ ከተማ ሁኜ በዚህ እዉነተኛ ታሪክ አዲስ አበባን በከፊሉ አካተናል፡፡ ብዙ የአዲስ አበባ ልጆች ለምን ስለደሴ ከተማ ትፅፋለህ እያላችሁ በbot የረበሻችሁኝ በዚህ እዉነተኛ ታሪክ የተደሰታችሁ የተማራችሁ ይመስለኛል፡፡ በመሀል በሆነ ምክንያት መጥቼ ታሪኩ የፃፍኩበትን ገርጂ ሰፈር ጎሮ  ጃክሮስ እስከ ሂክማ ትምህርት ቤት ቦሌ መድሀኒያለም ድረስ በአካል ተገኝቼ ስላየሁት ታሪኩን ለመፃፍ ተመችቶኝ ነበር፡፡  መፃፍ ቢያደክምም ይሄን ታሪክ ለእናንተ እስከማቀርበዉ ቸኩየ ነበር የመጨረሻየ ታሪክ መሰለኝ ከአሁን ቡሀላ በፁሁፍ የሚያግዘኝ እፈልጋለሁ፡፡

🌹ዉድ የቻናል ምርጥ ቤተሰቦችይህን እዉነተኛ ታሪኩን ጨርሰናል ማመስገን የምፈልገዉ ሁላችሁንም የቻናል ቤተሰቦቼ ታግሳችሁ አብራችሁ ስለጨረሳችሁ ሳቆይባችሁም በbot ስጠይቁኝ በንዴት ስሰድቡኝም የነበራችሁ እኔ አዉፍ ብያለሁ እናንተም ከልባችሁ አዉፍ በሉኝ ፡፡👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አስለቃሽ የቴሌግራም ፕሮፋይል የሚለዉን ጨርሰናል ከታች ያሉትን ፍሬ ሀሳብ እንድትይዙ ነዉ
➡️ሴቶች ማንኛዉም ከትዳር በፊት ያለ ግንኙነት ማቆም እንደአለባችሁ ያስተምራል፡፡
➡️ብዙ ሴቶች በተለያዩ የTelegram.. Whatsap..ላይ ኢስላሚክ እወቃታችሁን ለማዳበር ትገባላችሁ ግን ብዙ ቻት ይበዛባችሇል ቁጥሬን የት አገኘሀዉ ብላችሁ ስትጠይቁ መልሱ ከgroup ነዉ አይደል የምትባሉት ስለሆነም በጣም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡ የቴሌግራም ቻናል ከሆነ ከadmin ዉጭ ያለትን ተከታታዮች ማየት አይችሉም፡፡ ስለሆነም አንዳንድ ወንድም እና እህቶቼ ቶሎ ብላችሁ የtelegram group አትክፈቱ ኸይር እንሰራለን ብላችሁ የአጂ ነቢ ማዉሪያ የሀራም መንገድ መተዋወቂያ አታድርጉ፡፡
➡️አሁን ላይ ተማሪዎች የክላስ ልጆች ብቻ የሚያወሩበት group እየከፈቱ ማታ ማታ ጊዜ ሲፈጁ ሲያወሩ እየተስተዋለ ነዉ ይህ ሁላ ሙስሊሞችን አይወክልም ከዚህ አይነት group እራሳችሁን አግሉ፡፡
➡️ አሁን ላይ እየተስተዋለ ያሉ ነገሮች አሉ አንድ ሙስሊም ኢስላማዊ group ከፍቶ ሰዉ ይሰበስባል ግን በተሰበሰበዉ ተከታታይ ዉስጥ ክሪስቲያን ብዙም ለዲኑ የማይጨነቅ ሙስሊም ስለሚኖር በgroup ላይ
               >የሙዚቃ ቻናሎች ሊንክ
               >የባለጌ video ቻናሎች ሊንክ
               >የፎቶ ኤግዚቢዥን ሊንክ
                >የተለያዩ ከዲን የሚያዘናጉ ቻናሎች ማስታወቂያ ብዙ ሰዉ በgroup ላይ ይለቃል ፡፡ ሙስሊሞቹ ወደ እነዚህ ቻናሎች በመግባት የሙዚቃ የsex የተለያዪ ከዲን የሚያስወጡ ሱሰኛ ሊሆኑ ስለሚችሉ የWhatsap እና telegram group የምከፍቱ ከባድ ጥንቃቄ ያስፈልጋችሇል፡፡
➡️ከታሪኩ የምንረዳዉ ሴቶች መጀመሪያ ወንጀል  ላይ አለመዉደቅ ግን ሸይጧን አሳስቷችሁ ወንጀል የሰራችሁ ጥርት ያለ ተዉበት ወደ አላህ ተመልሳችሁ  ዱአ አድርጉ ከአላህ ምንም ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም፡፡
      በbot አስተያየት ስሰጡ የአንተን ታሪክ አንብበን ሂወታችን ጋር ይያያዛል አንብቤ ማታ ተዉበት አድርጌ ጠዋት ጓደኛቼ ጋር እና የወንድ ጓደኛየን ሳየዉ እረሳለሁ የሚል አስተያየት ብዙ ጊዜ የምታደርሱ እህቶቼ አላችሁ፡፡ ይሄ አመለካከት አስተያየት ምንም ተቀባይነት የለዉም ሲጀመር አልቶበትሽም ማለት ነዉ ፡፡ ማታ ቶብቶ አድሮ ጠዋት መርሳት " #ከፎቁ #ዉልቅ #እጭቃዉ #ጥልቅ" እንደማለት ነዉ ፡፡
እህቴ ጥርት ያለ ተዉበት ለማረግ ቢያንስ እነዚህ መስፈርቶች መሟላት አለባቸዉ
     >ወንጀል እሰራሽበት ቦታ እና ሰዉ አለመሄድ
     > ክፉ ጓደኞሽ ካሉሽ በተለያዩ ዘዴዎችመራቅ
     >ወንጀልሽን እያስታወሽ ከጌታሽምህረትመጠየቅ
     >ትክክለኛ ተዉበት መሆንሽን እራስሽን ማሳመን
     >ወንጀል የሰራሽበት ቀናቶች አለማስታወስ
     >ወደ ዲንሽ መመለስ መቻል አለብሽ
አሁን መቼም ብዙ ሴቶች ከጋብቻ በፊት እንጠናና ወንድም እህት እንሁን እየተባለ ብዙ ወንጀሎች እየተሰሩ ነዉ ፡፡ እህት ሁኚኝ ካለሽ ልትጠነቀቂ ይገባል ...አንቺ እቤትሽ ያሉት ወንድሞችሽ በቂ ናቸዉ አጂ ነብይ ጋር ወንድም ከምትባባይ sis
➡️ ሸይጧን አሳስቷችሁ ወንጀል የሰራችሁ ..አሁንም  በዚህ ዚና በሚባል ዱንያንም አኼራንም የሚያጠፋ ወንጀል ላይ ተጥዳችሁ ያላችሁ እህቶቼ የጠፋዉን ድንግልሽን የምታስመልሺዉ አንዴ ሂዷል ከትዳር በፊት እያልሽ ማንም ጋር በመተኛት ሳይሆን ..ጥርት ያለ ተዉበት አርገሽ አንቺ ላይ የደረሰዉን በሌላ እህትሽ ላይ እንዳይደርስ በመተባበር ወደ ዲንሽ ቂርአትሽ ከተመለሽ ፡ሴት ብቻ አይደለም ወንጀል የሚሰራዉ በአፍ በጅዶ ብሎ  ድንግል የሚወስደዉ ወንዱ ነዉ እሱም ሲቶብት ማግባት የሚፈልገዉ ወይ ድንግል ነዉ ወይ ወንጀል መሆኑን አዉቃ የቶበተችን ነዉ፡፡ ግን በዚሁ ስጃጃል እቆያለሁ ካልሽ እንኳን የሚያገባሽ ልታገኚ ለጥሙ ማርኪያ የሚፈልግሽ ወንድ እንኳ አረ ይቺን እነ እንትና ጋር ብዙ ወንድ ጋር አይቻታለሁ በሽታ ኤች አይቪ ሊኖርባት ይችላል ብለዉ እንደ እጅ ኳስ ተቀባብለዉ ይጥሉሻል፡፡ ጨዉ ለራስህ ስትል ጣፍጥ አለዛ ዲንጋይ ነህ ተብለህ ትወረወራለህ አይደል የተባለዉ አንቺም ለወደፊት ሂወትሽ ስትይ ለ30 ደቂቃ ስሜት ቦታ አትስጪ አንቺ ማለት አሁን ላይ እህት ለወደፊት እናት አላህ ቤት ጀነት ከእግርሽ ስር የሆነ የተከበርሽ ነሽ፡፡ ታዳ ይሄን ክብርሽን ማስከበር መቻል አለብሽ እንጂ ወንድ ሲደዉልልሽ ሲጠራሽ እየሄድሽ የሱ ስሜት መደበሪያ መጃጃያ እንድትሆኝ መፍቀድ የለብሽም፡፡
⚠️ እስኪ ትኩረታችን ወንድ ጨካኝ ክፉ አርገን የሴትን ሂወት የሚያበላሸዉ ወንዱ እያልን በብዙ ታሪኮች ላይ ወንዶችን አትመኑ ከትዳር በፊት እያልን ነዉ ...ግን ለምን ወንዱ ጨካኝ ሆነ ?? ለምን ወደ እዚህ ሂወት ሊገባ ይችላል ?? የሚለዉን በጥናት እራሴ ያረጋገጥኩት ከጓደኛቼ እና እዚሁ ቻናል ካሉ ወንድሞቼ መረጃ በመሰብሰብ ላይ ነበርኩ ግን ጥፋቱ የወንድ ብቻ ነዉ ወይ ?? የሚለዉን እስኪ አብረን እንየዉ፡፡
ወንድ ልጅ ምን ተፅእኖ ኑሮበት ነዉ የሴቶችን ሂወት ለማበላሸት የሚሄደዉ የሚለዉን እንየዉ
#ጓደኛ :- ጓደኛ ወሳኝ ነዉ እሱ የካፊር ጓደኛ ካለዉ ካፊሩ የሴት ጓደኛ ስለሚኖረዉ ግድ እሱም መያዝ ይኖርበታል ይይዛል በሴት ሂወት ይጫወታል፡፡
#ጓደኝነት ደግሞ ሰፋ አርገን ስናየዉ..ሙስሊም የሆነዉ ደግሞ መጀመሪያ አንዲት ሴት ይወድና ለቁም ነገር እያወራት እየወደዳት ከትዳር በፊት ሀራም አንሰራም ብሎ እሷም ቃል ገብታለት እስከ ጋብቻ የሚያፈርሱ ሴቶች ብዙ ናቸዉ ታዳ ይህ ልጅ በፍቅር ጎድታዉ የትዳር ሂወት አስቦ እሷ በጎን ሌላ ደርባ ስታባርረዉ መቼም አላህ በልብችን ፍቅርን አስቀምጧል በፍቅር ተጎድቶ ሌላ ሴት ሲጀምር የበፊቷን እያስተዋለ ለሴት ልጅ ክብር ይኖረዋል ወይ ??? ችግሩ ምንም የማያቁት ሴቶች በዚህ ምክንያት አብረዉ መጎዳታቸዉ ያሳዝናል
➋አንዳንድ ሴቶች ብር ያለዉን ወንድ ይቀርባሉ አብረዉ በልተዉ ጠጥተዉ ለትዳር ድረስ ተዘጋጅተዉ ለመጣላት ፈልገዉ በትንሽ ምክንያት ተለያይተዉ የወንድን ልብ የሚሰብሩ ብዙ ሴቶች አሉ ታዳ እሱ ለሴቶች ክፋት እንጂ ጥሩ ያስባል ወይ ??
➌ሴቶች በተንኮል በጣም የላቁ ናቸዉ .ለትዳር የፈለጋቸዉ ሲያወራቸዉ .መጀመሪያ
       >ጓደኛ የለኝም
       > እወድሀለሁ
       > የለአንተ መኖር አልችልም..
       >እሞትልሀለሁ እያለች ሳቀርባት ትቀርብሀለች አንተም ልብህ ይራራና የሴት ልጅ ለቅሶዋ አሳዝኖህ ትቀርባታለህ ግን ለምን እንደቀረበችህ ሳይገባህ አንተ ላይ የፍቅር ስሜት ጥላብህ ትክክለኛ ማንነቷን ትደብቃለች፡፡ ክፉ ሴት  ማለት ስትፈልጋት የማትፈልግህ ሳይሆን ሳትፈልጋት ፈልጋህ የመፈለግን ስሜት ፈጥራ የማትፈልግህ ሴት ናት ፡፡ ነብዩ ሙሀመድ ሰ ዐ ወ ነጋዴ በማለ ጊዜ እና ሴት ባለቀሰች ጊዜ አትታመንም ብለዋል በጣም ትክክል የሆነ ሀዲስ ነዉ፡፡ ስለሆነም ያቺ ያለቀሰችልህ ሴት ትክክለኛ መንነቷን ስታቅ እንደትቆጭ በሌላ ጥሩ ሴቶች ሁለተኛ አላምንም እንዳትል ሲርቁህም ጠፋህ በሰላም ነዉ እንደምትለዉ ሲቀርቡህም እንዴት ለምን ቀረበችኝ ብለህ ማሰብ አለብህ፡፡
➌መቼም ቢሆን የሩቅ ፍቅር አደራ አደራ አደራ አደራ አንዳትጀምሩ አንተ ወሎ የምትኖር ከሆነ ምርጫህን ወሎ ሸዋ ላይ ከሆንክ እዛዉ ሸዋ ሀሉም በየሀገሩ እድል መስጠት የሚገባዉ የቅርቡን ነዉ ለምን ትዳር ስለሆነ በቅርቡ ማጠናት መቻል አለብህ፡፡ የሩቅ ፍቅር ወደድኩህ አበድኩልህ  እያለች ብታለቅስ 👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ታላቅ #ምክር ***
ﻛﻔﻰ ﺑﺎﻟﻤﻮﺕ ﻭﺍﻋﻈﺎ መካሪነት በሞት በቃ
ﺇﻧﺎ ﻟﻠﻪ ﻭﺇﻧﺎ ﺇﻟﻴﻪ ﺭﺍﺟﻌﻮﻥ
☞ በሰሞኑ የአየር አደጋ ትምህርት ልንወስድ ይገባል ።
☞ እሱም ሞት ድንገተኛ ነው በመሆኑም ሁልግዜ ለአኼራችን ስንቅ
ከማዘጋጃት ልንሰንፍ አይገባም።

☞ ኑሮ ማለት የአኼራ ኑሮ ነው በመሆኑም ጥለናት ለምንሄዳት ዱንያ
ከምንጨነቀው የበለጠ ማሰብ መጨነቅ ያለብን ለአኼራ ነው ።

☞ስለሆነም አሁኑኑ ከሽርክ፣ከብድዓ፣ከዝሙት፣ከሰው ሀቅ፣ከሀሜትና መሰል
ወንጀሎች ተፀጽተን ወደ አላህ ልንመለስ ይገባል ።
( ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻋِﻨﺪَﻩُ ﻋِﻠْﻢُ ﺍﻟﺴَّﺎﻋَﺔِ ﻭَﻳُﻨَﺰِّﻝُ ﺍﻟْﻐَﻴْﺚَ ﻭَﻳَﻌْﻠَﻢُ ﻣَﺎ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺄَﺭْﺣَﺎﻡِ ۖ ﻭَﻣَﺎ ﺗَﺪْﺭِﻱ ﻧَﻔْﺲٌ ﻣَّﺎﺫَﺍ
ﺗَﻜْﺴِﺐُ ﻏَﺪًﺍ ۖ ﻭَﻣَﺎ ﺗَﺪْﺭِﻱ ﻧَﻔْﺲٌ ﺑِﺄَﻱِّ ﺃَﺭْﺽٍ ﺗَﻤُﻮﺕُ ۚ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻋَﻠِﻴﻢٌ ﺧَﺒِﻴﺮٌ )
(ሱረቱ ሉቅማን - 34)
((አላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ዝናብንም ያወርዳል፡፡
በማሕፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም ነገ
የምትሠራውን አታውቅም፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት
አታውቅም፡፡ አላህ ዐዋቂ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡))

⭐️ያ አላህ በሞት ከሚመከሩ መልካም ባርያዎችህ አድርገን

⭐️ያ አላህ መጨረሻችንን አሳምርልን
*ያ አላህ ሞታችንን በሸሃዳ አድርግልን

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
😔 #የባከነ #ህይወት 😢
           #ክፍል 5⃣

#ፀሀፊ ☞ mahalet Ethiopiawt


      እኔም ልተኛ ክፍሌ ገብቸ ሻወር ለመውሰድ ስዘጋጅ የክፍሌ በር ተንኳኳ ማነው ስል እኔ ነኝ አለ ጌታነህ ነበር ምን ፍልገህ ነው ስለው እራቴን አልበለውም ኩሽናው ተዘግቶል ማንም የለም በጣም እርቦኛል ነይ ስጭኝ ሲለኝ እስካሁን የታባህ አምሽተህ ነው እያልኩ በንዴት በሩን ከፍቸ በቆመበት ትቸው ወደ ኩሽና ምግቡን ለማቅርብ ሄድኩ ምግቡን በሳሀን አድርጌ ወጡን አሙቄ ጨምሬ የዥለት ስሄድ አልጋየ ላይ ቁጭ ብሏል ከክፍሌ ገብቶ የማያውቅ ጭራሽ አልጋየ ላይ ቁጭ ብሏል
 .......ድርጊቱ ሁሉ አዲስ ሆነብኝ አናደደኝ እዚህ ምን ትሰራለህ ይሀው ክፍልህ ወስደህ ብላ ስለው አልወጣም አለ ማለት ይህ የእኔ ክፍል ነው ስለው ብድግ ብሎ በሩን ቆልፎ ቁልፉን በኪሱ ከተተው ምን እየሰራህ ነው አብደሀል ከክፍሌ ካልወጣህ እጮሀለው ስለው ፊቴን በጥፊ ጮ አርጎ አልጋው ላይ ወርወርኝ እራሴን ለማዳን ታገልኩት ግን ጌታነህ ወንድነቱን ተጠቅሞ  የእኔን ጩኸት ከንቱ አርገው  ጌታነህ የፈለገዉን ነገር ካረገኝ ቡሀላ ባደርገው ነገር ሳያፍር በሩን ዘግቶ ጥሎኝ ወቶ ሄደ፡፡
     የእኔ ህይወት እንዲባክን የፍርዱት ቤተሰቦቸ ናቸው እነሱን እየወቀስኩ ሳለቅስ ነጋ😢😢 ጠዋት መነሳት አልቻልኩም ሰራተኞቹ ክፍሌ መጥተው ማርቲ እርፍዶል አትነሽም ሲሉኝ እራሴን አሞኛል አልኮቸው ወደስራቸው ተመለሱ ሴትዮዋ መጣች ሀኪም ቤት ልውሰድሽ ተነሽ ስትለኝ ሀኪም ቤት አልሄድም ፓናዶል ስጭኝ ይሻለኛል አልኮት እሽ ብላ ፋርማሲ ሂዳ አመጣችልኝ 5 ቀን ስራ ሳልሰራ ተኝቸ ሰነበትኩ በ6ኛ ቀኔ ስራ ገበው እንደዱሮው ፈጣን አይደለሁም ደነዘዝኩ ሁሉም ነገር አስጠላኝ ሰው የሚባል ፍጡር ማየት አስጠላኝ
     የቤቱ ደንበኞች ማርታ ምን ሁነሻል ፈዘሻል ይላሉ አሞኝ ነበር አሁን ተሽሎኛል አልኳቸው አንድ በጣም የምግባባው ባንክ ቤት የሚሰራ ልጅ አለ አሱ ለብቸየ ጠርቶኝ ምን ሁነሽ ነው ተደፍርሽ ነው? ሲለኝ አይደለም ቤተሰቦቸ ናፍቀውኝ አልኩት
..... ታዲያ ለምን ወደ ሀገርሽ አትሄጅም አለኝ ብር የለኝም ለመኪና ትኬት 3000 ብር ያስፍልገኛል ስለው ከት ብሎ ሳቀ ኢትዮጵያ ውስጥ 3000 ብር የሚስከፍል መንገድ የለም ሲለኝ ሴትዮዋ ነች ያለችኝ አልኩት ሴትዮሽ እንዳትሄጅባት ብላ ዋሽታሻለች የት ነው ሀገርሽ ሲለኝ ነገርኩት ቀርብ ነው የ50 ብር መንገድ ነው ሴትዮዋ ብር ካልሰጠችሽ እኔ እሰጥሻለሁ ብሎኝ ወደ ስራው ሄደ
    እኔም ሴትዮዋን ሄጀ ሀገሬ መሄድ እፍልጋለሁ 50ብር ብቻ ስጭኝ ስላት አትሂጅ ብላ ለመነችኝ እንደማልቀር አርጋገጥኩላት እሽ ብላ 100 ብር ሰጠችኝ ልብሶቸን አዘገጃጅቸ አደርኩ በጧት አውቶብስ ተራ ሄድኩ እርዳቱ ሲጠራ መኪና ውስጥ ገባሁ ጉዞ ወደቤተሰቦቸ🚐
     ከእኔ ጎን የተቀመጠ ወጣት ልጅ ነበር ያወራኛል ምንም አልሰማውም ልቤ የሚያስበው ስለቤተሰቦቸ ነበር ልቤ ደስታ ይሁን ፍርሀት አላውቅም በፍጥነት ይመታል መንገዱ እራቀብኝ መድርስ አይቀርም ደርስኩ ከመኪና ወርጀ ቤት ለመድርስ ትንሽ የእግር መንገድ ነበርው እሱን በሩጫ ከሩቅ ለሚየኝ ሰው ውሻ አያባረረኝ ይመስላል አሯሯጤ ቤታችን ስደርስ በር ሳንኳኳ የሆነች ጩጨ ልጅ ከፈተችው ወደውስጥ ስገባ ቤተሰቦቸ የሉም ሌሎች ሰወች ሁሉም አዲሶች ናቸው አላውቃቸውም አባቴ ቤታችን ሽጦት ነው አልኩ በልቤ
.........የአባቴ ቤት አይደለም ስላቸው ነው አሉኝ አባቴ እና ወንድሜ የት ሄዱ?? አልኩ ይመጣሉ አባትሽ ስራ ሂዶ ነው ወንድምሽ ት/ት አሁን ይመጣሉ ቁጭ በይ ብለው ወንበር ሰጡኝ እንደተቀመጥኩ አሻግሬ መንገድ መንገዱን ሳይ አብራኝ የተማርችው ጓደኛየ ከትምህርት ቤት ስትመለስ ከሩቅ አየዋት ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጠራት እየሮጠች መጣች ከተሳሳምን በኃላ እዚህ ምን ትሰሪለሽ ስትለኝ ቤቴ እኮነው አባቴን እየጠበኩ አልኳት ፊቷ ለይ የመደንገጥ ስሜት አነበብኩ ምነው ደነገጥሽ ስላት አልሰማሽም አለች የልጅቷ ድንጋጤ እኔንም አስደነገጠኝ ምንም አልሰመውም ቤተሰቦቸ ምን ሆኑ አባቴ ምን ሆነ ጥያቄየን ደርደርኩላት ቅዝቅዝ ባለ ድምፅ አባትሽ እኮ .………

#part 6⃣

ይ............ቀ...................
...........ጥ............ላ.............ል

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════••••••════•
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ዉድ የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ የአንደኛዉ ዙር አሸናፊ 305 ሰዉ በግጥም ዉድድሩ ተሳትፎ ለ Hani 87 ድምፅ በማግኘት አንደኛ ሁናለች ግን በፍቅር ግጥም መወዳደር አይቻልም ብለን ነበር የHani የፍቅር ግጥም ነበር ፡፡ ሁለተኛ የወጣዉ አብዱን 55 ሰዉ መርጦታል በሌላ ዙር ይወዳደራል ፡፡ 🏆🏆🏆Hani አንደኛ ሁናለች ለሌላ ቀን ግን ለፍፃሜዉ ዉድድር ግን ግጥሟን ቀይራ ነዉ የምትወዳደረዉ፡፡

‼️ በአንደኛዉ ዙር የተወዳደርሽዉ ሰአዳ ብታሸንፊ ቢሆን የአንቺ ማሸነፍ ለሌላ ተወዳዳሪ ይሰጥ ነበር ለምን የሰዉ ግጥም ነዉ የፓሰትሺዉ ከቻናል ነዉ copy ያረግሽዉ፡፡

‼️ ይሄ ዉድድር ተወዳዳሪ ስለበዛብን ቅዳሜን ጨምረን በሳምንት ሁለት ቀን አርገንዋል ፡፡ ስለሆነም ሁለተኛዉ ዙር ቅዳሜ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ ሁሌም እሮብ እና ቅዳሜ የግጥም ዉድድር ነዉ ማለት ነዉ፡፡
👍 ብዙዎቻችሁ መምረጥ የሚቻለዉ አንድ ስለሆነ እንደተቸገራችሁ ነግራችሁኟል ያዉ ዉድድር ስለሆነ ነዉ
⭐️ ደግሞ ዉድድር ስለሆነ ያላሸነፋችሁ የተመቸኝን ግጥም በቻናል እንደምፓሰተዉ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፡፡

🏆🏆🏆Hani የአንደኛዉ ዙር አሸናፊ ሁነሻል ግጥምሽን ቀይረሽ ፡፡ ለመጨረሻዉ ሽልማት ላለዉ የመጨረሻዉ የግጥም ዉድድር ግጥምሽን አዘጋጅተሽ በአንድ ሳምንት ዉስጥ እንድልኪልኝ ፡፡ ሁለተኛዉ ዙር የማጣሪያ ዉድድር ቅዳሜ ይጠብቁን፡፡ ግጥም ያላችሁ ላኩ በተራ እናወዳድራለን የተሸነፋችሁም በሌላ ግጥም መወዳደር ትችላላችሁ፡፡ 305 የቻናል ቤተሰቦች ግጡሙን አንብባችሁ በዉድድሩ የተሳተፉትን ስለመረጣችሁ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
😔 #የባከነ #ህይወት 😢
           #ክፍል 6⃣

#ፀሀፊ ☞ mahalet Ethiopiawt


     አባትሽ እኮ ከሞተ ቆየ ብላ አንገቷን ወደ ምድር አቀርቀርች 😥 .አባቴ ሞተ እኔ አላምንም ፍጣሪ ይህ እንዴሆን አይፍቅድም አባቴ እንደናፍኩት አይሞትም እያልኩ በጩሀት ሰፈሩን አደባለኩት የሰፍር ሰወች ጩኸቴን ሲሰሙ ሁሉም እየተሯሯጡ መጡ አኔን ለማርጋጋት ሁሉም በየአፉ የማጽናኔ ቃላት ይደርድራሉ ለእናቴ ደውለው ጠሯት ከወንድሞቸ ጋር እየሮጠች መጣች እነሱን ሳይ ይበልጥ አባቴ ናፍቀኝ እንደናፍቀኝ ላይመለስ ሄደ
     እናቴ ይህን ቤታችን አከራይቸ ሌላ ቤት ገዝቻለሁ ተነሽ ወደቤት እንሂድ ስትለኝ ዛሬ እዚሁ ማደር እፍልጋለሁ ስላት እሽ ብላኝ እሷም ከኔ ጋር አደርች ለሊት እንቅልፍ አልወሰደኝም ተኝቸ እያለቀስኩ ነበር ከሌሊቱ 10 ሰአት ሽንት ቤትመሄድ ፍልጌ ወደ ውጭ ወጣሁ ስወጣ ማንም አልተከተለኝም አባቴ ቢኖር ተከትሎኝ ይወጣ ነበር ግቢያችን ውስጥ የቡና ዛፍ አለ ከዚያ ቁጭ ብየ ብርድ እየቀጠቀጠኝ
     ነጋ ወደ እናቴ ቤት ሄድን እናቴ በብዙ ነገር ተቀይራለች አዲስ ባል አግብታ ዘመናዊይ ቤት ገዝታ ትልቅ ሆቴል ከፍታ ሀብታም ሁናለች ከትንሽ ቀን በኃላ ተርጋግቸ ለእናቴ ወደ አዲስ አበባ መመለስ እንደምፍልግ ስነግራት አትሄጅም እኔም ብቻየን ነኝ ከጎኔ ሁኝ እዚሁ ባል አግብተሽ እንድትኖሪ እፍልጋለሁ አለችኝ እኔም ዳግም ከቤተሰቦቸ መለየት አልፍለኩም ነበር በእናቴ ሀሳብ ተስማማው
    እናቴ የሆነ ሰው ልጅሽን አጋቢኝ እያለ ጨቅጭቆኛል ሰውየው ሀብታም ነው ልድርሽ ነው አለች ሰውየው አልሽ ትልቅ ሰው ነው እንዴ ?? ስላት አረ አይደለም ባይሆን በሀብቱ ትልቅ ነው አለች ሽማግሌ ተልኮ እናቴ እሽ ብላ ሰርግ እየተዘጋጀ አንዲት ጎርቤታችን ጠራችኝ ሄድኩ ቁጭ በይ የማወራሽ አለኝ አለችኝ ቁጭ አልኩ ድንግል ነሽ??? አለችኝ ያልጠበኩት ጥያቄ ነበር ደነገጥኩ ዝም አልኩ ምነው ደነገጥሽ ካልሆንሽ ችግር የለውም እንድጠይቅሽ እናትሽ አዛኝ ነው ምክንያቱም አንች ድንግል ከሆንሽ የሚገባሽ ባልሽ ለቤተሰቦችሽ የሚሰጠው ብር አለ እሱን ለማርጋገጥ ነው ስትለኝ
..........አይደለሁም አልኳት ችግር የለውም ካልሆንሽ ብላ መሄድ ትችያለሽ አለችኝ ወጥቸ ወደቤቴ ሄድኩ ባሌን ማወቅ ፍልጌ የሰፍር ጓደኛየን የሚገባኝን ልጅ ታውቂዋለሽ ስላት አወ ብላ ሳቀች .....ለምን ሳቅሽ ??አልኮት ሳቋ አበሳጭቶኝ ልጅ ስትይ ነዋ ሰውየ በይ አለች ንግግሯ ምንም አልገባኝም በቃ ምሽት ከእናንተ ሆቴል ይመጣል አሳይሻለሁ ብላኝ ወደቤቷ ሄደች በቀጠሯችን ሰአት ምሽት መጣች ከሆቴሉ በር ወጣ ብሎ ስልክ የሚወራ ሰውየ ስታይ እጇን እየጠቆመች ይህውልሽ ባልሽ አለች እየሳቀች ማለት ይህ ስልክ የሚወርው ጥቁር ጃኬት የለበሰው ስላት አዎ አለች
.......በፍጣሪ እናቴ አብዳ መሆን አለበት ለዚህ ሽማግሌ ልትድርኝ የምትዘጋጅ ብየ በፍጥነት ወደ እናቴ ሂጀ ስጮህባት ምን ችግር አለው አባትም ባልም ይሆንሻል አንዴ ቃሌን ሰጥቻለሁ መቀየር አትችይም ....የዘንድሮ ወጣት ኪሳቸው ባዶ ውሎ አዳራቸው ጫት ቤት ነው ለትዳር የሚሆን ወጣት የት አለ ብላ ወጣቶችን መሳደብ ጀመርች በእናቴ ብር መውድድ እየተገርምኩ ትቻት ወደ ጓደኛየ ቤት ሄድኩ
       ሰርጉ እንዲቀር ጎርቤቶቻችን ሳማክር ሰውየው ጥሩ ሰው ነው አግቢው እናትሽንም አታሳዝኛት አሉ ምርጭ አልነበርኝም አገባሁት ከሰውየው ጋር መኖር ጀምርን ፡፡
    በ4ኛ ቀናችን ሽማግሌወችን ሰብስቦ ቤት ይዞቸው መጣ ሽማግሌወቹ አንዴ ቁጭ በይ የምንነግርሽ ጉዳይ አለን አሉኝ እሽ ብየ ቁጭ አልኩ ደሞ ምን አጥፍቸ ነው ሽማግሌ ያመጣብኝ እያልኩ አብሰለስላለሁ ባሌ ተነስቶ ቆመ እኔ ገጠር ሌላ ሚስት እና ልጆች አሉኝ
......ሳይጨርስ እኔ ሁለተኛ ሚስትህ ነኝ ስለው ሳያፍር አወ እናትሽ ታውቃለች በዚህ ሀገር ሁለት ሚስት ማግባት የተለመደ ነው ስለዚህ 4 ቀን ካንች ጋር 4 ቀን ከዚችኘዋ ሚስቴ እሄዳለሁ አለ
        በእናቴ ተስፋ ቆርጥኩ ሁኔታዋ በሙሉ ገንዘብ ብቻ ሁኖል ሰውየውን በጣም እጠለዋለሁ የእናቴ ባል ቤተሰቦች ሀዋሳ ናቸው አጎቱ ሞቶ ለለቅሶ እኔ እናቴ የእናቴ ባል ሁነን ሀዋሳ ሄድን ሟቹን ቀብርን ወደ ሞቹ ቤተሰቦች ቤት ገባን ከተማውን የሚሳየኝ ሰው እፍልጋለሁ ስላቸው ቆይ የወንድሜ ልጅ አለ እሱን ልጥራልሽ አለኝ የእናቴ ባል ሲደውልለት ወዲያው መጣ
       ልጁም ቆንጅየ ነው አይኔን ከልጁ ማንሳት ተሳነኝ ምነው ተመሰጥሽብኝ የሚል ድምፅ አባነነኝ ልጅ ነበር ደሞ ቀልቃላ ቢጤ ነው
...አረ በፍፁም ባለትዳር ነኝ አልኩት በድንጋጤ አረ ሙድ አትያዥ ህፃን እኮነሽ ሲለኝ እሚገርመው ማግባቴ ብቻ አይደለም ሁለተኛ ሚስት መሆኔ ነው በዛ ላይ ትልቅ ሰውየ እናቴ እና ባሏ እየሰሙ ነበር ......እናቴን ለማናደድ ፍልጌ እሷ ምንም አላለችም
ልጁም አርጋጊው በይ ነይ ሀዋሳን ላሹፍሽ ብሎኝ እጀን ያዞኝ ከቤት ወጣን አስፓልቱን ስንጎዝ ስለእኔ ብዙ ነገር አወራሁት ከማትፍልጊው ሰው ጋር ለምን ትኖሪለሽ ፍቅር ደስ የሚለው ከእኩያሽ ጋር ሲሆን ነው .....ለማንኛውም አሁን ፈታ ማለት ከፍለግሽ የሆነ ቦታ ልውሰድሽ ትስማሚለሽ አለኝ
....አወ አልኩት ከአስፓልት ወጣ ያለ ግቢ ውስጥ ገባን ፍርሸው ሽሻ ሲጋራ ጫት የሚቅሙ ወጣቶች ሴትም ወንዶችም ተሰባስበዋል ልጁን ሲያዩን ጆኒ መጣ ብለው በየአፍቸው ጆኒ ዛሬ ይቀመቀማል አሉት ..ልጁ ጆኒ ነበር ስሙ ልክ እንደ እንጀራ ጫቱን ሁሉም አጎርሱት ቁጭ አልኩ ሞክሪ ብሎ ትንሽ ጫት ቀንጥሶ አጎርሰኝ በጣም ይመራል ከፊትለፊት ስኳር ተቀምጦ ነበር ብድግ አድርጌ ቃምኩት ምሬቱን አጠፋልኝ ሁሉም ትንሽ ትንሽ እያሉ ሲያጎርሱኝ እይኔ መፍጠጥ ጀመር ሰወቹ በዙብኝ ሲመሽ  ወተን ወደ ሆቴል ገባን  የመጀመሬው መጠጥ ሲመጣ አስታውሳለሁ ከዛ በኃላ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም
      ጧት ከእንቅልፌ ስነቃ የሆነ ሆቴል ውስጥ አልጋ ላይ ተኝቸ እራሴን አገኘውት በድንጋጤ ብድግ ልል ስል ከጎኔ .………


#Part  7⃣

ይ............ቀ............
...........ጥ............ላ,............ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
          `·. @Islam_and_Science          @Islam_and_Science
 

☑️ ሼር በማድረግ ለሁሉም ያድርሱ
#ማሻ_አላህ!
በግራ በኩል የምታዩት የሰው አንበሳ ሀሺም አምላ ይባላል። በአንድ ጨዋታ $500 (አምስት መቶ ዶላር) የካስትልን ቢራ ምልክት በቲሸርቱ ላይ ባለማድረጉ የሚያጣው ነው።
He is Muslim. so he does not use the logo of alcohol beer. I have heard that the fine is to count him for this reason.
Hashim Amla
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
😔 #የባከነ #ህይወት 😢
           #ክፍል 7⃣

     ከጎኔ ጆኒ ተኝቶል በድንጋጤ ከአልጋው ዘልየ መሬት ወርድኩ ጆኒ ጆኒ አንተ ጆኒ ተነስ ብየ በግድ አስነሳሉት
..... ምን ሆነሻል እቅልፌን አቋረጥሽኝ ብሎ ተነጫነጨ ማታምን ተፍጠር እንዴት እዚህ መጣን በጥያቄ አፍጠጥኩት ምንም አልተፍጠርም እኔም አንቺም አቅላችንን አናቅም ነበር ቤት ከሄድን ችግር ይፍጠራል ብለን እዚህ አልጋ ያዝን አልጋ አልቆ አንድ ብቻ ስለነበር ያው ካንችጋር አደርኩ አለ እና ምንም አልተፍጠርም
.... ይሄው ነው ስለው እምልልሻለሁ ምንም አልተፍጠርም ሱሰኛ ብሆንም ባለጌ አይደለሁም ብሎ ካልገው ወርዶ አሁን ፍጥነን ቤት መሄድ አለብን ብሎ ወጣ እኔም ተከትየው ወደ ቤት ሄድን እቤት ስንደርስ በጓሮው በር ከፍተን ገባን ሁሉም እንደተኙ ነበር በመጠጥ እና በጫት የደነዘዘው ሰውነታችን ለማፍታታት ሻይ አፍልተን ስንጠጣ እናቴ ተነሳች ምንም አላለች ፡፡
    ከጆኒ ጋር እየተደበቅን ጫት ቤት ሂደን እንቅማለን ጆኒ ቀለል ያለ ጭንቀት የማይወድ ፍታ ያለ ልጅ ነው ከሳምንት የሀዋሳ ቆይታ በኃላ ወደቤታችን ተመለስን ጆኒን ስለየው የማላውቀው ስሜት ውስጤን እየረበሸው ነበር ቤቴ መጥቸ ስራየ ጆኒን ማሰብ ሆነ ይባስ ብሎ በህልሜ ያመጣ ጀመር ሽማግሌው ባሌን ለአይኔ ጠለሁት
......ጆኒን አፍቅሬዋለሁ ፍቅሩን አፍኘ መያዝ አልቻልኩም አንድ ነገር አሰብኩ ወደ ጆኒ መመለስ 1000 ብር ይዤ እናቴ ሳታየኝ ወደ ሀዋሳ ጉዞየን ጀመርኩ መኪና ውስጥ ገብቸ ድንገት ስሄድ ጆኒ ምን ይለኝ ይሆን ይናደድብኛል ወይስ ደስ ይለዋል እያልኩ ይህኑ በሀሳቤ ሳወጣ ሳወርድ ሀዋሳ ደርስኩ .......የጆኒ ጓደኛ ሱቅ አለው አውቀው ነበር ከመኪና ወርጀ እየሮጥኩ ወደ ልጅ ሱቅ ሄድኩ ልጁ ሲየየኝ ደነገጠ
......ማርቲ ምነው ሲለኝ
........,ጆኒን ፍልጌ ነው እባክህ ጥራልኝ ስለው እሽ አሁኑኑ ይመጣል እዚጋ ቁጭ በይ ብሎ ወንበር ሰጠኝ ወዲያውኑ ጆኒ መጣ
.......ማርቲ ምን ሆንሽ ከእናትሽ ጋር ተጣላሽ ??ብሎ እቅፍ አርገኝ ደርቱ ላይ ተለጥፌ ጆኒ ናፍቀህኝ ነው ወደ ቤትሽ ተመለሽ እንዳትለኝ ካንተ ጋር መሆን ነው የምፍልገዉ አፍቅሬሀለው ለደቂቃወች ዝም ብሎ አዳመጠኝ
...... እሽ አሁን ተርጋጊ እና በኃላ እናወራለን ነይ ውስጥ እንግባ ብሎኝ ጓደኘው ሱቅ ውስጥ ገባን ምሽት እንደተለመደው ጫት ማድቀቅ ጀመርን ማታ ጆኒ አልጋ ይዘ አብርን አደርን ጦት ቁርስ በልተን ጆኒ ወደስራ ሄደ እኔ እዚሁ የሆቴል አልጋ ይዥ ዋልኩ በዚህ ሁኔታ ለተወሰነ ቀን ሰነበትን ለጆኒ ቤት እንከራይ እስከመቸ እዚህ እንቆያለን ብየ 800 ብር አውጥቸ ሰጠሁት ብሩን ይዞ ቤት እንዲፍልግልን ለደላላ ነግሮ ቤቱ ተገኘልን ትንሽ ጠባብ ቤት ገባን ምንም እቃ የለንም ምግብ ከውጭ እየገዛን እንበላለን
       ጆኒ ከስራ ሲመለስ ብረድስት ገዝቶ መጣ በሌላቀን ቡታጋዝ በየቀኑ አንዳንድ እቃ እየገዛ ቤቶን በእቃ ሞላት ምግብ ሰርቸ መብላት ጀመርን ደስ የሚል ህይወት በፍቅር ተጣመርን ከጆኒ ልጅ እንዲኖርኝ እፍልጋለሁ ......ሳማክርው በፍፁም አሁን ልጅ መውለድ የለብንም አለኝ ከእኔ ጋር መቀጥል አይፍልግም ብየ አሰብኩ ደግሞ የቤት እቃ ይገዛል ለወደፊት እቅድ ያወጣል ግራ አጋባኝ ኑሮችን ተሻሽሎል ጆኒ ስራ ይሰራል ገንዘብ ያገኛል
     አንድ ቀን ጠዋት እንደተለመደው ቁርስ ስሰራ ጆኒ እንደተኛ ነበር ጆኒ ተነስ ስራ እንዳይርፍድብህ ስለው ዛሬ ስራ አልሄድም አለ ደስ አለኝ ሁሌም አብሮኝ ቢውል ደስ ይለኛል ተነስቶ ፊቱን ታጥቦ ቁጭ አለ ፊቱ ላይ የጭንቀት ስሜት ይነበባል
.......ጆኒ ምን ሁነሀል ስሜትህ ተርብሾል ስለው አወ የሆነ ልነግርሽ የምፍልገው ነገር አለ አለኝ
..... እሺ ንገርኝ ብየ የምቆለውን ቡና አቁሜ ሳዳምጠው ዝም አለ ምነው ሎተሪ ደርሶህ ነው አልኩት ቀለል እንዲለው ፈልጌ እንጅ ፊቱ ላይ የደስታ ስሜት ሳይሆን መርዶ ነጋር ነበር የሚመስል ለመሳቅ እየሞከር
,ያልነገርኩሽ ነገር አለ ከአንች በፊት ትዳር ነበርኝ አንድ ወንድ ልጅም አለኝ ከሚስቴ ጋር የተለያየነው በሱስ ምክኔት ገንዘቤን ስጨርስ አልፍልግህም ብላኝ ተፋታን አሁን ልጃችን አብርን እናሳድግ እንታርቅ አለችኝ እናም አንች ወደባልሽ ተመለሽ እኔም ወደሚስቴ ልመለስ ነው አለ በድንጋጤ አፌ ተሳስሮ ጆኒ በህልምህ ነው ደግመህ ተኛ እንቅልፍህን አልጨርስክም አልኩት ውሸቴን ነው እንዲለኝ እየተመኘው ....ብድግ ብሎ ልብሶቹን ሻንጣ ውስጥ እያስገባ እውነቴን ነው ይህን በማድርጌ በጣም ይቅርታ ብሎ ሻንጣውን አንጠልጥሎ ከቤት ወቶ ሄደ ሳላስበው በጩኸት ግቢውን ቀወጥኩት አከራየ መጥታ ምንነው ምን ሆንሽ ስትለኝ እያለቀስኩ ሁሉንም ነገርኳት እናቴን እንዴት ብየ ነው አይኖን የማየው የታባቴ ነው የምሄድ ሀዋሳ ማንንም አላውቅም ጆኒን ፍቅሬን ብየ ነው የመጣሁት ስላት ተርጋጊ ገና ልጅ ነሽ በእዚህ እድሜሽ ተስፋ አትቁርጭ ገና ብዙ የህይወት ውጣ ውርዶች ይገጥሙሻል ስለዚህ ጠንካራ መሆን አለብሽ አሁን ደላላ ጋር ሂደሽ ስራ ፈግጉልኝ በይው በይ ተነሽ ፊትሽን ታጠቢ አለችኝ እውነቶን ነው ወደ እናቴ ከምመለስ ሰው ቤት ገብቸ ብሰራ ይሻላል ብየ ወሰንኩ ሀዋሳ ከሆንኩ ጆኒን መርሳት አልችልም ስለዚህ ሻሸመኔ መሄድ አለብኝ ጉዞየን ወደ ሻሸመኔ አደርኩ እዛ ስደርስ በሰወች ጥቆማ ደላላወችን አገኘው ስራ እንደምፍልግ ስነግራቸው የወታደር ካንፕ ውስጥ በወጥ ሰራተኝነት አስቀጠሩኝ ስራ ጀመርኩ ሙሉ ቀን ከሰው ጋር ስለምውል ጆኒ ማታ ስተኛ ብቻ ይናፍቀኛል ግን ለመርሳት እየሞከርኩ ነው ወታደሮቹ አብዛኞቹ አማርኛ በደንብ አይችሉም ቢሆንም ሲያወሩ ያስቁኛል አንድ ቆንጆ ልጅ አለ ስሙ ሰለሞን ይባላል ለየት ያለ ፀባይ አለው ስላም አይለንም ዝምተኛ ነው አይኔ ልጁ ላይ አርፎል ማርቲ ዛሬም በወንድ ልጅ ተስፋ አትቆርጭም አልኩ ለራሴው የሰለሞን አንዱ ጓደኛ ገመቹ ነው ለሱ ሰለሞንን እንደወደድኩት ስነግርው ሰለሞን የ4 አመት ፍቅርኛ ነበርችው ድንገት ያለምንም ምክኔት ሌላ አገባች እና በዚህ ምክኔት ሴትን አይቀርብም እሺ ካለኝ ቀርቦ እንዴወራሽ አደርጋለሁ ብሎኝ ተለያየን አንድ ቀን ሰለሞን የተጠቀለለ ወርቀት ሰጥቶኝ ወደስራው ሄደ ወርቀቱን ስገልጠው ዛሬ ከቀኑ 8 ሳዐት ካፌ እንገናኝ ይላል ቀድሜ 8 ሰአት እኔ ነበርኩ ቀድሜ የደርስኩ ሻይ አዘዝኩ ትንሽ ቆይቶ መጣ ሰላም ተባብለን ቁጭ አለ ማርታ ድጋሜ መጎዳት አልፍልግም በፍቅር የሚቀልድ አልወድም እርግጠኛ የምትወጅኝ እና የምታገቢኝ ከሆነ ነው ፍቅርሽን የምቀበል አለኝ እኔም በፍቅር መቀለድ እንደማልፍልግ እና ማግባት እንደምፍልግ አስረዳሁት  ሰለሞን ጋር መቀራረብ ጀመረን እሱኔ፡ን ስቀርበው የበለጠ መልካም አስታዋይ ሁኖ አግኝቸዋለሁ በጓደኞቹ ፊት ተንበርክኮ ቀለበት አርገልኝ ያኔ የተሰማኝን ደስታ በቃላት መግለፅ አልችልም በፍቅር አበድን ጌታየን አመሰገንኩት ዳግም እንድቆም አደርገኝ ወታደሮቹ በየጊዜው የኤች አይቢ ምርመራ ያደርጋሉ ሰለሞን አንችም መመርመር አለብሽ ብሎኝ አብርን ሄድን ደም ሰጥተን ውጭ ቁጭ ብለን ውጤት መጠባበቅ ጀመርን ከ2 ሰአትበኃላ ሰለሞን ተጠራ ውጤቱን ይዞ እየሳቀ መጣ ነፃ ነህ ስለው አወ ብሎ እቅፍ አርገኝ ቀጥየ እኔ ተጠርው ስገባ ዶክተሩ ፊቱ ጠቆርብኝ ምነው ችግር አለ ዶክተር አልኩት ሰለሞን ፍቅርኛሽ ነው አለኝ አወ አልኩት ውጤትሽን አብሮ እንዲሰማ ፍቃደኛ ከሆንሽ እናስገበው አለኝ እሽታየን ገለፃኩለት ውጤትሽ እንደሚሳየው ቫይርሱ በደምሽ ውስጥ ☞ @Islam_and_Scienc
ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የሆነውን ሁሉ አቀፍ የመስጂድ ዲዛይን ይፋ ሁኗል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በመሆን ሊያሠራው ያቀደውን በዘመናዊነቱ ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የሆነውን ሁሉ አቀፍ የመስጂድ ዲዛይን ዛሬ ይፋ ሆነ።
በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ኢብኑ ዑመር አል ኸጣብ መስጂድ በቦታው ስፋት ሃያ አራት ሺ ካሬ ሜትር በሆነ የመስጂዱ ህጋዊ ይዞታ ላይ ይሄ እጅግ ዘመናዊ የሆነ መስጂድ ለመስራት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በጋራ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠው እንደነበር ይታወቃል።

📚📚ይህ መላውን ሙስሊም ህብረተሰብ በባለቤትነት ስሜት እንዲሳተፍበት በማሠብ ታቅዶ እየተሠራ ያለው ትልቅ ፕሮጀክት ለመጀመር በርካታ የቅድመ ሁኔታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ዲዛይኑ በመስራት ላይ የሚገኙት ባለሙያዎች በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀርቦ ከፍተኛ አድናቆትን የተቸረው የወንዞች ዳርቻ የልማት ፕሮጀክት ዲዛይን ሠርተው ያቀረቡት ባለሙያዎች ቡድን መሪ በነበረው በአርክቴክቸር(አቤነዘር) የተመራ ቡድን ዛሬ መጋቢት 5/2011 ዓ.ል የመስጂዱ ዲዛይን ለአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ አባላት በይፋ ቀርቦ የመጀመሪያ ደረጃ ውይይት ተደረገበት። በቀጣይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ተጨማሪ ተከታታይ ውይይቶች ይደረጉበታል።
ይህ ሁሉን አቀፍ ዘመናዊ ግዙፍ የመስጂድ ግንባታ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የበላይ አስተባባሪነት እና በሙስሊሙ ሕብረተሰብ ባለቤትነት

የሚሠራው ሜጋ ፕሮጀክት
☞ወደ ላይ ባለ ሠባት ፎቅ
☞ባለ አራት ወለል
☞አራት ዘመናዊ ሚናራዎች
☞አራት ቁባዎች
☞አንድ እስላማዊ ዩኒቨርስቲ
☞አንድ ዘመናዊ ሆስፒታል
☞አንድ ትልቅ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል
☞ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የሠርግ አዳራሾች
☞የመዝናኛ መናፈሻ
☞የህፃናት መጫወቻ ስፍራ
እና ሌሎች በርካታ ነገሮች የሚያሟላ ሆኖ የሚሠራ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ፕሮጀክቱ የሚመራው ከተለየዩ አካላት ማለትም ከባለሐብቶች ከአካባቢው ነዋሪዎች ከሙህራን ከዳኢዎች ከባለሙያዎች ከሐይማኖት አባቶችና ለፕሮጀክቱ ያግዛሉ ከተባሉት አካላት በሙሉ የተውጣጡ አባላት ባሉት ቦርድ ይሆናል ።

⭐️⭐️ ይህንን ፕሮጀክት ለማሳካት ከሠባት መቶ ሚሊዮን እስከ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ በማብራሬያው ተጠቁሟል። ኢንሻአላህ ስለዚህ ፕሮጀክት በስፋት በሌላ ጊዜ የምንመለስበት ይሆናል። መስጂዱ ተሰርቶ ለማየት ያብቃን እቅዱም እንዲሳካ አላህ ያግዘን አሚን።

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
👍1