ISLAMIC SCHOOL
12.6K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 2⃣0⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal


        እኔም ቀጥታ ወደ ቤት ሄድኩኝ.......እቤቴም ደረስኩኝ ዙበይር ሲደዉልልኝ ስልክ አላነሳሁም ነበር....መልሳ ፊርዶስም ደወለች ግን ለእሷም ማንሳት አልፈለኩም መረጋጋት ስላለብኝ እንባየን ጠረኩኝ እና እቤቴ ቁርአኔን ቀርቼ ኢሻን ሰግጄ ተኛሁኝ፡፡  ከሱብሂ ቡሀላ ትንሽ ጋደም እንዳልኩኝ ጠዋት ላይ የፊርዶስ ስልክ ተደወለ ግን ማንሳቱን ፈራሁ ለምን ማታ ወንድሟን አስቀይሜዋለሁ.......ከአሁን ቡሀላ ከእኔ ተስፋ ቁረጥ ብየዋለሁ ግን እኔ ዙበይር ጠልቸዉ አይደለም በፊት የሰራሁት ስራ እኔን የበታች አርጌ ስለማይ እንጂ......
   ለፊርዶስ ደግሞ እንደነገራት እርግጠኛ ነኝ ለምን ለእሷ ምንም ነገር አይደብቃትም እና....ፊርዶስ ደግማ ስደዉል ...አላስችለኝ አለ ለምን ፊርዶስ የኔ ምርጥ ጓደኛየ ባለዉለታየ ሀሳቤን ያካፈልኳት የሀሳቤ ተካፋየ ነች...ከዛም ስልኩን አነሳሁት ሰላማታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ፊርዶስ እየቀለደች አሁን ስልክ አላነሳም ያልሽኝ እቤትሽ አካባቢ መሆኔን አይተሽኝ ነዉ እንዴ አለችኝ
እኔም ወላሂ በይ ሰፈራችን መጥተሻል እንዴ አልኳት
....እሷም እኔ ግቢያችሁ በር ላይ ነኝ መቆርቆሩ ደብሮኝ ነዉ መጥተሽ ክፈችልኝ አለችኝ
...እኔም ምንም ጊዜ ሳልፈጅ ሂጄ የግቢዉን በር ስከፍተዉ ፊርዶስ ቁማለች ...ከዛ የተራራቁ ዘመዶች ይመስል ተቃቀፍን  ወደ ቤት ገባን እናቴ ጋር ሰላም ከተባባሉ ቡሀላ  ቁርስ አልበላሁም ነበር እናቴ ቁርስ አዘጋጅታ አብረን በላን...

ቁርስ በልተን ከጨረስን ቡሀላ እናቴ ወደ ዉጭ ስትወጣ  ፊርዱም እየቀለደች ትናንት የት ለመድረስ ነዉ ያን ያህል እሩጫ እኔ ደግሞ ሂክማ የመቶ ሜትር ሩጫ አለባት እንዴ  እስከምል ድረስ የት ለመድረስ ነዉ እኔ መቼም አንደኛ ወጥተሽ ተሸልመሽ እንደሆነ ሽልማቱን ለማየት ነዉ የመጣሁት አለችኝ እየቀለደች፡፡
ወይ ፊርዶስ ቀልዷ በጣም አሳቀኝ እኔ የጠበኩት ለምን ዙበይርን እንደዛ ጥለሽዉ ተናግረሽዉ ትሄጃለሽ ብላ የምትቆጣኝ መስሎኝ አይኗን ለማየት እየፈራሁ ነበር፡፡ እኔም ሳቅ ብየ ዝም አልኳት ጥሩም ክፉም አልተናገርኩም.....መቼም ዙበይር እንደሚነግራት አልጠራጠርም...

ፊርዶስም ሂክማ አንቺም እህቴ ነሽ ክፉሽን አልወድም ጥሩሽን ነዉ የምወደዉ...ዙበይር ወንድሜ ነዉ የእሱንም ክፉንም አልወድም ስለሆነም ትናንት የተፈጠረዉን ነገር ነግሮኛል ...የአንቺን ጉዳት አቃለሁ እሱ ደግሞ አንቺን ወዶሻል በዚህ የሚቀጥል ከሆነ  ከአንቺ በላይ እንደሚጎዳ ነዉ የሚታየኝ  ወንድሜ ደግሞ በፍቅር ሲንገላታ ሲያለቅስ ማየት አልፈልግም ....አንቺን መዉደዱን እንኳን  እናቴ ታቃለች ዙበይር በህልሙም ሂክማ ሲል ነዉ የሚያድረዉ፡፡ እናቴ ለምን አታገባም ብላ ጠይቀዋለች ..
....መስመር ላይ ነኝ ዱአ አድርጊልኝ ነዉ ሁሌ መልሱ  ፡፡ እናቴም ቀን በቀን ስትጠይቀዉ አንቺን እንደሚወድ እና አንቺን ማግባት እንደሚፈልግ ነግሯታል፡፡ የትናንትናዉ የምሳ ግብዣ እናቴ ሂክማን ማወቅ አለብኝ አንቺን ለማወቅ ጓጉታ ሂክማን አስተዋዉቂኝ የወደፊት የልጄን ሚስት ብላኝነዉ..ስለሆነም አንቺም ወንድሜን ተረጂዉ እየወደደሽ አንቺን ቢያጣ አሁን ባለበት ሁኔታ ወንድሜ ሰዉ አይሆንም፡፡ ለወንድሜ እኔ እመሰክርለታለሁ ሴትን ልጅ ቀጥ ብሎ የማያይ ዲን ያለዉ ሰዉ አክባሪ ነዉ ..ስለሆነም ሁለታችሁም ተግባቡ ሂክማ ...አላህ ፅፎላችሁ ይሆናል ስለሆነም ወንድሜ ጋር አብራችሁ ብትኖሩ ደስ ይለኛል አንቺ ለኔ የልብ ጓደኛየ ለወንድሜ ደግሞ የትዳር አጋሩ ስትሆኝ ደስ አይልም እንዴ አለችኝ፡፡ ደግሞ ስለአለፈዉ ማንነትሽ ያቃል ስነግረዉ አዝኖ የብስ ፍቁሩ ጨመረበት ሂክማ አለችኝ.......

      ካልደበረሽ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ሂኩ አለችኝ..
.....እኔም እሺ ጠይቂኝ አልኳት
...በእስከአሁኑ ቆይታችሁ ዙበይርን ትወጅዋለሽ አትወጅዉም አለችኝ
......እኔም የምመልሰዉ አጣሁ በእርግጥ ዙበይርን ወድጀዋለሁ ግን ለወደፊት አብረን የምንሆን ስለማይመስለኝ እሱን ልርቅ ወስኛለሁ ለምን በሀይደር የሴትነቴን ክብር አጥቻለሁ በዙበይር ደግሞ ሁለተኛ ፍቅር በሚባል መጎዳት አልፈልግም ብየ ወስኛለሁ፡፡
.....ፊርዶስም መልሽልኝ እንጂ አለችኝ
........እኔም አዎ እወድዋለሁ ግን....ስል ወሬየን አቋረጠችኝ

ሰባራ ነው ልቤ~

በፍጹም ቅንነት ከልብህ ቀርበኸኝ
የ ሃሳብ ተካፋይ እህትህ አድርገኸኝ
የሆዴን ብሶት በዝርዝር ስነግርህ
ቁስልህ ስለሆነ ቁስሌ አመመህ
ብዙ አይነት ፈተና ቢፈራረቅብኝም
ያን ሁሉ መከራ ችየ አሳልፌም
ግማሹን ታሪኬን በአፌ ስነግርህ
ያለፍኩትን ዘመን ዳስሼ ሳወራህ
ድንገት ሳላስበው ብሶት አስለቀሰኝ
መሆኑ ሳይገባህ በአንተ ህይወት ውስጥ እራሴን አጊቼ
አብሽሪ አልከኝ ማልቀሴ ቢመስልህ ላንተ ተከፍቼ
በጥርሴ ደብቄ የያስኩት ሚስጥር
ታሪኬ ሰፊ ነዉ ገብቶ ሲመዘብር
ያለፍኩትን ህይወት ብነግርህ በዝርዝር
እንዴት እንደሆነ ሰውን አምኖ ማጣት
ቁልጭ ብሎ ታየኝ የልቤ ስብራት
የኔ ነገር ብዙ ነው አንዴ ላጫውትህ
ያንጀቴን የሆዴን ውስጤን ልንገርህ
እናትና እህትህ ባለቤት ልሁንህ
ሰባራውን ልቤን ከሰባራው ልብህ ልገጣጥመውና
አንተም በኔ ድነህ እኔም ልሁን ደህና
ሃሳቤን ዘርዝሬ ልነግርህ አልኩና
ተመልሼ ተውኩት ደግሞ ፈራሁና
ምን አልባት ምን አልባት ህልሜ ይከሽፍና
ማገገሚያ ባጣስ በሰባራው ልቤ ዳግም እጎዳና


.......እኔ የምፈልገዉ እሱን መዉደድሽን ብቻ ነዉ ..ሌላ ምክንያት አልፈልግም አለችኝ... ከተመቸሽ ዛሬ የምንሄድበት ቦታ አለኝ ፍቃደኛ ከሆንሽ እቤት ስራ ከሌለሽ እንሄድ አለችኝ....እኔም እሺ አልኳት ፊርዶስ የት ትወስደኝ ይሆን ??? አብረን በቀጣዩ ክፍል እናያለን

#part 2⃣1⃣

ይ.............ቀ...............
.........ጥ...............ላ.......................ል

4 another channal👇
             @Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
   
  T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
👍1
🍃 #ሜጀር #ጀኔራል ፋጡማ ህሚንገር ትባላለች፡፡ አስራሁለተኛ የአሜሪካ የአየር ሀይል አዛዥ ናት፡፡ የመጀመሪያ ሴት ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያ ሙስሊም ሴት የተዋጊ ጀት አብራሪ መሆኗ ብዙዎችን አስደንቋል፡፡
የአሜሪካ አይነኬ ቦታዎች በሙስሊሞች እየፈራረሱ ነው አላህ ለእኛ ሀይል እና እውቀት ይስጠን፡፡

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
ከእንስሳቶች ሁሉ እጅግ በጣም ቂመኛ የምትበላው ግመል ናት፡፡ ግመል እንድ እንስሳ ወይም ሰው ቢተናኮላት ለሰባት ዓመት ያህል ቂም ትይዛለች፡፡ በዚህ መሐል በዳይዋን ካገኘች ከመበቀል ወደ ኀላ እትልም፡፡
✿ ግመል የሐሞት ከረጢት የላትም
✿ የግመል የጀርባ እጥንት ቀጥ ያለ ነው፡፡ ጎባጣ ሆኖ የሚታየው ሻኛዋ ነው፡፡
✿ ውኃ ለግመል የበረሃ "ነዳጇ" ነው፡፡ ለረጅም ጉዞ እንዲያገለግላት ውሀውን የምታጠራቅመው በሆድዋ እና በሰውነቷ ውሰጥ ባሉ የቅባት ሴሎች ነው፡፡
✿ ግመል በሻኛዋ ውሰጥ ውኀ ታጠራቅማለች ብለው ብዙዎች ያምናሉ፡፡ ነግር ግን በትክክለኛው ጥናት ግመል በሻኛዋ ውሰጥ ውኀ እንደማታጠራቅም ታውቋል፡፡
✿ ግመል እጅግ በጣም ከፍተኛ የሙቀት መጠን ባለው ጭው ምድረበዳ ውሰጥ ያለ ውኀ ለ17 ቀናት መቆየት ትችላልች፡፡ በቆላማና ወይናደጋማ የእየር ንብረት ደግም እሰከ 2 ውር ያለ ውኃ የመቆየት እቅም እላት፡፡
✿ የግመል መክሳትና መወፈር የሚለካው በሻኛዋ የይዘት መጠን ነው፡፡

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
ISLAMIC SCHOOL CHANNAL
💐 POST💐


ሁሌም ቢሆን…
"🦋 ስቀልድ ነበር " ከምትለዋ ቃል ጀርባ
ትንሽ እውነታ አለች
🦋" አረ ችግር የለውም " ከምትለዋ ቃል ጀርባ
ትንሽ ስሜት/ህመም አለች
🦋" ምንም አልፈልግም " ከምትለዋ ቃል ጀርባ
ትንሽ ፍላጎት አለች…
🦋"መሄዴ ነው"ከምትለዋ ቃል ጀርባ የመቅረት
ፍላጎት አለች
🦋. . . . . . . . .ነገር ግን ከዝምታ ጀርባ ብዙ ብዙ
ቃላቶች አሉና ቃላቶችን ብቻ ሳይሆን ስሜቶችንም
ለመረዳት ሞክሩ!!. . . .
መልካም ቀን ፍቅር ይብዛላቹ,

።።።።።።።።።።።።።።
@Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
።።።።።።።።።።።።።።

🚫 Share it now
👍1
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 2⃣1⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal


.
  ወደ አምስት ሰአት አካባቢ ከቤት ልብሴን ቀያይሬ ፊርዶስ ጋር አብረን ጉዟችንን ቀጠልን ..ፊርዶስም ዛሬ ምሳ እኔ ነኝ የምጋብዝሽ ብላኝ መገናኛ አካባቢ የሚገኝ  ኢስላም ሬስቶራንት(ምግብ ቤት ) ገባን ስንገባ ግን ያየሁትን ማመን አቃተኝ አሁንም ዙበይርን ነበር ያገኘሁት፡፡ ፊርዶስም ዛሬ እስኪ ምሳ አንድ ላይ ሁነን ልጋብዛችሁ ብየ ነዉ አለችን፡፡
...... ምሳችን አዘን በላን....ከዛም ምሳ በልተን ከምግብ ቤቱ ወጣን ፡፡ ሶስታችን ከመገናኛ ተነስተን እግራችን ወደ አመራን እየተጓዝን ነዉ...ትንሸ እንደሄድን ዙበይርም  ፊርዶስን እስኪ ሁለታችን የምናወራዉ ወሬ አለን አየር ትለቂልናለሽ አላት
...ፊርዱም ከእኔ ደብቀህ የምታወራዉ አለ ዙበይር እሺ ካልክ እገነጠላለሁ ብቻ የህዝብ ተወካዮች የፓርላማ ዉይይት እንዳታረጉት ብላ ገንጠል አለች
    እኔ እና ዙበይር ብቻ ቀረን ሁለታችንም ተፋፈርን በዝምታ ብዙ መንገዶች ተጓዝን ማን ወሬ ይጀምር የተባባልን ይመስል አንዳችን የወሬን መጀመሪያ መክፈቻ ዙበይር ተነፈሰ ..
....... የዛሬዉ ምሳ እንዴት ነበር አለኝ
.......እኔም አሪፍ ነዉ አላህ ይስጣት እህትህ ጋበዘችን አልኩት
.....እሱም ግን እኔ መኖሬን ብታቂ  ፊርዶስ ብነግርሽ ትመጪ ነበር???? ብሎ ጠየቀኝ
....እኔም እንጃ ግን እህትህ የምትለኝን እሰማለሁ ፊርዶስን የማያት እንደ እህቴ ነዉ፡፡ ስለሆነም ፊርዶስን ያለችን እንቢ የምልበት ድፍረት የለኝም አልኩት፡፡
.......ማሻ አላህ እህቴን እኔም አንቺም እንወዳታለን ፊርዶስ በቤተሰብ የመጣ ትዳር አለ ግን ሁሌ የምትለዉ እኔ ከማግባቴ በፊት ወንድሜን ዙበይርን ደግሼ ድሬዉ ነዉ የማገባዉ ትላለች የእኔ እና እሷ አስተዳደግ የተለየ ነዉ ተከታታይ ስለሆን ተዋደን ነዉ ያደግነዉ ..አሁንም ድረስ ወንድሞቼን ሁሉንም በአንድ አይን ብታይም እሷ ግን እኔ ጋር አስተዳደጋችን የተለየ ስለሆነ በጣም ነዉ የምንዋደደዉ ሚስጥር አደብቀኝም እኔም አልደብቃትም አለኝ፡፡
......እኔም ፊርዶስን እንደ እህቴ ነዉ የማያት የምደብቃት የለኝም አልኩት፡፡
አሁን መፈራራት የለም ሁላችንም ግልፅ ሁነን እያወራን ነዉ፡፡ ዙበይርም ግን ይሄን  ጥሩ ፀባይ  ይዘሽ እስከአሁን እንዴት ነዉ እንደ እኔ በፍቅር የወደቀ አላስቸገረሽም እንዴ አለኝ እየቀለደ ....
      እኔም ለዙበይር ምንም ላልደደብቀዉ ወስኛለሁ፡፡ እኔም የፈነዳ የመኪና ጎማ ይመስል ኡፍፍፍ ብየ #የት #ይደርሳል #የተባለዉን #ዛፍ #ቀበሌ #ቆረጠዉ፡፡ አልኩት፡፡
ዙበይርም ማለት አልገባኝም አለኝ
.....እስከ አሁን የት እደርስ ነበር ግን በመሀል ዛፍም ያድጋል ብለሀዉ ሲቆረጥ ማደጉ ያቆማል ይደርቃል  የኔም ሂወት እንደዛ በለዉ አልኩት
..ዙበይርም እንዴ እንደ እሱ አይደለም ዛፍ ሲቆረጥ ሌላ ያወጣል ያቆጠቁጣል አለኝ
...እኔም የኔ አቆራረጥ እንዳያቆጠቁጥ ነዉ ብቻ በሂደት ያንን ማስረሻ እህትህን ሰጠኝ አልሀምዱሊላህ አልኩት
...እሱም በአላህ ተወኩል ነዉ አላህ ያለዉ ነዉ የሚሆነዉ ደግሞ ያሰብሽበት ግብ ለመድረስ የትናንት ትናንት ነዉ አሁን ያለሽዉ አሁን ላይ ነዉ ያለፈ ትዝታ ትርፉ ቁጭት ነዉ፡፡ የወደፊት ራዐይ ግን ተስፋ ነዉ አለኝ፡፡
.....እኔም ኢንሻ አላህ ግን እስከ አሁን አንተ ለምን አላገባህም ???? ማስተዳደሪያ ብርም አለህ ነጋዴ ነህ መኖሪ ቤትም አለህ አከራይተህ ነዉ የምትኖረዉ ለምን እስከ አሁን አላገባህም??? አልኩት
    እሱም እኔ የምመኘዉ ዱአየ አላህ የምወዳትን ልጅ መጀመሪያ የወደድኳትን የትዳር አጋሬ አርግልኝ ነበር የምለዉ .....ግን ብዙ አመታት ማንም ሴት ልቤ ዉስጥ ገብቶ አያቅም ነበር....ግን ከትንሽ ወራት በፊት አንዲት ልጅ ወደድኩኝ ግን ምን ዋጋ አለዉ ፍቅሩ እኔ ጋር ብቻ ሆነ የአንድ ሰዉ መዉደድ ማለት በአንድ እጅ እንደማጨብጨብ ነዉ ዱአ አርጊልኝ ልጅቱ እንደምወዳት እንድትረዳኝ አለኝ፡፡
......እኔም እንደዚህ ሲለኝ እንዴ እኔን ነዉ ወይስ ሌላ ናት ብየ ተወዛገብኩ ለምን እንደሚወደኝ አቃለሁ ደግሞ እኔ ጋር ሁኖ ስለ ሌላ ሴት ያወራኝ መሰለኝ
....እኔም እስከ አሁን ስትወድ የመጀመሪያህ የሆነችዉን ለማግባት ወስነሀል ማለት ነዉ?? አልኩት

እሱም አዎ ወስኛለሁ ልጅቱን እኮ ታቂያታለሽ አለኝ፡፡
...እኔም ማን ናት አልኩኝ ፈጠን ብየ
እሱም ገሞች አለኝ
እኔም መገመት አልችልም አንተዉ ንገረኝ አልኩት
....እሱም ሂኩ አንቺ ነሽ ለምን አትረጂኝም አንቺ በፍልጥ ካልሆነ በፈሊጥ አይገባሽም ማለት ነዉ?? አለኝ ፈገግ እያለ.....
     ግን አንተ እኔን የወደድክብኝ ምክንያት መስፈርቱ ምንድን ነዉ ዙበይር እንዴት የትዳር አጋርህ እንድሆን መረከኝ አልኩት...
_____እሱም ሂኩ እኔ ከሆነሉም የወደድኩሽ ግልፅነትሽ እና ዲን ስላለሽ የዛሬወን ሳይሆን የነገዉን ሂወት የምታስቢ ፊርዶስ በጣም ትወድሻለች ታከብርሻለች ፊርዶስ የወደደችዉ ለኔ የወደፊት ትዳሬ ከሆነ ደስተኛ ነኝ ፍቅር መቼ የት እንዴት ከየት ወደ የት የማይባል ግዑዝ ነገር ነዉ አላህ ፍቅሬን በሀላሉ አድርጎ የትዳር አጋሬ ብትሆኝ እድለኛ ነኝ ሂኩ
......እኔም የደስታም የሀዘንም እንባ ከየት መጣ ሳይባል በአይኔ እንደምንጭ ዉሀ ኩልል እያለ ወረደ .... ሳለቅስ ዙበይር ደነገጠ ምን ሆንሽ መናገር የለብኝም ነበር እንዴ ምን ላርግ ተቸግሬ ነዉ ሂኩ አለኝ፡፡
ያለቀስኩት በእሱ መወደዴ የደስታ እምባ ሲሆን በተዘዋዋሪም እኔ ደግሞ ለትዳር ብቁ አይደለሁም ዙበይርን እኔም እወደዋለሁ ግን የኔ እንደማይሆን በማሰብ በዉሸት መዉደድ ጉድ የሰራኝ ሀይደር እዉነተኛ እኔን የሚወድ ሳገኝ  የተደበላለቀ ሁለት ስሜት ያለዉ እምባ ነዉ፡፡
    ግን ዙበይርን ልዋሸዉ አልፈለኩም፡፡ ልነግረዉ ወሰንኩ እሱም አረ በፈጠረሽ አታልቅሺ አታስጨንቂኝ ይለኛል ዙበይር፡፡
.....እኔም እምባየን በክሪሜ አበስ አድርጌ ዙበይር እኔ ለአንተ አልሆንህም ሌላ ፈልግ እኔ አንተን ባገባህ ደስ ይለኝ ነበር ግን ....ብየ ልቀጥል ስል ...ሂክማ አሁን ያለነዉ ዛሬ ጋር ነዉ ሁሉንም ፊርዱ አስረድታኛለች ......እምባሺን ጥረጊ ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በእጁ እምባየን ጠረገልኝ......አይን አይኔን እያየ ሂኩ ብቻ ዉደጅኝ አንቺን ማጣት አልፈልግም
ዛሬ ቁርጤን ንገሪኝ ሂክማ እኔ እወድሻለሁ..እኔ እስከማንነትሽ ተቀብየ አንቺ ጋር ጥሩ የፍቅርሽ ተካፋይ የትዳር አጋሪ ልትሆኝ ዝግጁ ነሽ ...የአንቺን ልብሽ ዉስጥ ያለዉን ስሜት ንገሪኝ ...ዛሬ ዉሳኔሽን አሳዉቂኝ አለኝ....

ሂክማ የመጨረሻ ዉሳኔ ትሰጣለች ምን ትወስን ይሆን ?? በሚቀጥለዉ ክፍል እናያለን

#part 2⃣2⃣

#ይ.............#ቀ...............
.........#ጥ.............#ላ...................#ል

4 another channal👇
             @Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
   
  T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
👍1
እንዲህም ትመራለህ!
ከላይ የምታዯት ፋጢማህ የምትባል በእንግሊዝ አገር የምትገኝ ደሃ ሱማሊያዊት ነች።ከስር የምታዩት ደግሞ በአላህ ክዶ የነበረ ሙልሂድ እንግሊዛዊ ዶክተር ኤቴይስት ነው።ከለታት ባንዱ ቀን እህች እንስት ራዲዩ ላይ ገብታ ደሃ እንደሆነችና ሚረዳት እንደምትፈልግ ትናገራለች።
ሰውየውም ድህነቷና ዲኗ ላይ ሊያላግጥ ፈልጎ፣ከጣቢያው ስልኳን ይዞ ባንዲት ፀሃፊው ምግብና የሚያስፈልጋትን ነገሮች አስይዞ ላከላት።ለፀሃፊዋም ስትደርሺ ከማን ነው የተላከው ካለችሽ “ከሰይጣን ነው!” በያት በማለት ይነግራታል።ፀሃፊዋም መልክቱን አድርሳ ስታበቃ፣ይህች እንስት ማን እንደላከላት ስላልጠየቀቻት ‘ማን እንደላከልሽ ማወቅ አትፈልጊም?’ በማለት ጠየቀቻት።እህች ታላቅ እንስትም ይህን ሙልሂድ እንዲሰልምና ስሙንም ከቲሞሲ ወደ አብዱልሃኪም እንዲቀይር ያደረገውን ታላቅ መልስ ሰጠቻት።
መልሷ አጭር ነበር...
“ማን እንደረዳኝም ሆነ እንደላከልኝ ማወቅ አልፈልግም።
የኔ አላህ አንድ ነገር ማድረግ ከፈለገ
ሸይጣኖችም ቢሆኑ ይታዘዙታል።”
አላሁ አክበር!!
በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ሆነሽ እሱን እንዳትረሺ
ላደረገሽ ታላቁ አላህ ታላቅ ምስጋና ይገባው!!

´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
          `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science


☑️ ሼር በማድረግ ለጓደኞዉ ያካፍሉ
አፍሪካ ውስጥ በደዕዋ ባሳለፈቸው 29 አመታት ውስጥ....
☞11 ሚሊየን ሰው በሱ እጅ ሰልሟል።
☞5700 መስጂዶችን ገንብቷል።
☞15000 የቲሞችን አስድጉዋል።
☞አፍሪካ ውስጥ ውሀ በሌለባቸው አካባቢዎች 9500 ቦታዎች ላይ የውሃ ፓምፕ ገንብቷል።
☞860 መድረሳ፣4 ዩኒቨርስቲ፣204 ኢስላማዊ ማዕከላትን ገንብቷል።
የዚህ አይነት ጀግኖች ምንም እንኲን ታሪካቸው በወርቅ መፃፍ ቢኖርበትም አብዛኛዎቻችን እኚህን ሰው አናውቅም።
ሸይክ/ዶክተር፦ አብዱረህማን አሱመይጥ ይባላሉ።አላህ ይርሀማቸው አላህ ከይር ጀዛቸውን አባዝቶ ይክፈላቸው፣ቀብራቸውንም ኑር ያድርግላቸው
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናችሁ በየአላችሁበት ሰላምታየ ይድረስ ብያለሁ፡፡ አዲስ ታሪክ በቅርብ ቀን ልንጀምር ነዉ ርዕሱም
😰 #የባከነ #ሕይወት በሚል የተዘጋጀ አስተማሪ አሳዛኝ አስለቃሽ እንዲሁም እናንተ ትምህርት እንድወስዱበት የተዘጋጀ ታሪክ ልናቀርብ ነዉ፡፡ ታሪኩ የሚዳስሰዉ
☞ ስለቤተሰብ ቤተሰብ ሳይስማማ ትዳር ይፋታሉ መፋታታቸዉ ለልጆች አስተዳደግ ተፅእኖ እንደሚያሳድር
☞ በቤተሰብ ተገደዉ የሚያገቡ ሴቶች አሉ ካገቡ ቡሀላ እንደማይስማሙ እና አገበዋለሁ ብለዉ በፊት አሰቡት ጋር አልፎ አልፎ እንደሚደዋወሉ ለትዳርም ክብር አይሰጡም ወደ ፍች ይሄዳሉ
☞ አጉል ወንድሜ ነዉ እህቴ ነዉ ማለት መዘዙን አብሮ ይዳስሳል፡፡ ብታነቡት በጣም ይማሩበታል፡፡
😉ታዳ ከእኛ ምን ያስፈልጋል ያላችሁ መሰለኝ
የሚያስፈልገዉማ ቢያንስ ለሶስት ሰዉ ሼር share በማድረግ ቤተሰብ መሆናችሁን ግለፁ ..ደግሞ መስማማታችሁን በማያስከፍለዉ Like 🤙🤙🤙🤙 በማድረግ አሁኑኑ ይግለፁ ፡፡
መልካም ንባብ ይሁንላችሁ🤙

።።።።።።።።።።።።።።
@Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 2⃣2⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal

        እምባሺን ጥረጊ ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በእጁ እምባየን ጠረገልኝ......አይን አይኔን እያየ ሂኩ ብቻ ዉደጅኝ አንቺን ማጣት አልፈልግም ..እኔ እስከማንነትሽ አንቺ ጋር ጥሩ የፍቅርሽ ተካፋይ የትዳር አጋሪ ልትሆኝ ዝግጁ ነሽ አለኝ......
ዙበይር እኔ እኮ ....እንዳጨርሺዉ ጨረስን እኮ እኔ የምፈልገዉ ፍቅርሽን ዲንሺን እንጂ ደምሽን አይደለም ሸይጧን አሳስቶሽ የሰራሽዉ ወንጀል ተዉበት አርገሻል...... ኢነሏሀ ዩሂቡ ተዋቢነ ወዩሂቡ ሙተጦሂሪን ተብሎ የለ አንድ ሰዉ ወንጀል ይሰራል ይሳሳታል ነብዩሏህ አደም ዐ.ሰ ተዉ ይሄን ፍሬ አትብላ ተብሎ በልቶ አይደል ከጀነት የተባረሩት....ሸይጧን በፊት ስሙ አብዱረህማን አልነበር አርሽን ሁሉንም ሰግዶበታል ስንዝር ያልሰገደበት አይገኝም ግን ኩራት ይዞት ከጌታዉ ተጣልቶ ሰዎችን ለማሳሳት ተነስቷል፡፡
       ስለሆነም ሂክማ ወንጀል እንደሆነ እያወቅሽዉ ትሸወጃለሽ ስንት ሰዉ በአለበት ወንጀል ሳይቶብት በሰራዉ ወንጀል ሲመፃደቅ እየኖረ አይደል?? ስለሆነም አንቺ ቶብተሽ ወደ አላህ ተመልሰሻል ማታ ማታ ስታለቅሺ ዱአሽ እኔም ዱአ ሳደርግ የዱአ ዉጤት አላህ እኔ እና አንቺን አገናኘን ስለሆነም እኔ አንቺን በማሰብ መርካቶ በቅጥረኛ ሰራተኞች ነዉ ልብሱ ሲሸጥ የሚዉለዉ እሺ በይኝ እና እኔም ወደ ስራየ ጥቅልል ብየ ገብቼ ስራየን ልስራ አለኝ፡፡
......እኔም የደስታ እምባ እያነባሁ እሺ ዙበይር እኔም እወድሀለሁ አፈቅርሀለሁ የወደፊት ሚስትህ ከአላህ ጋር እሆናለሁ አልኩት ...አላቅፈዉ አልስመዉ ገና ነዉ የእኔ እና እሱ ነገር ለመተቃቀፍ ለመሳሳም ኒካህ ያስፈልገናል፡፡ ዙበይር በጣም ደስ አለዉ የሚሆነዉ ጠፋዉ በደስታ ከእኔ ፈጠን እያለ መሄድ ጀመረ እንደገና ከሄደ ቡሀላ ቁሞ ጠበቀኝ ፡፡ እሱም አይስመኝ አያቅፈኝ ገና ነዉ ግድ ኒካህ ማረግ አለብን...
ዙበይርም ይሄን ደስታየን ለፊርዶስ ልደዉልልላት አለኝ፡፡
እኔም አዎ ደዉልላት አልኩት
ለፊርዶስ ደዉሎ ዛሬ ደስተኛ ነኝ ተሳካ እኮ አላት.... ፡ፊርዶስም ዙበይርም በጣም ተደሰቱ የሚያስቀኑ እህት እና ወንድም በጣም ደስ ሲሉ....

በአንቺ ክሶኛል
በ ዘ አዶኒ ባርኮት
‹………………..….......…›
አሁን ደስ ብሎኛል ተደስቻለሁ
የልፋቴን ዋጋ ምላሽ አጊቻለሁ
ከከበረው ሁሉ ትበልጭብኛለሽ
ከቶ አልችልም ተመን ላወጣልሽ
ወጥቴ ወርጃለሁ ብዬ ፍቅርሽን
ግን አልተቻለኝም ማሸነፍ ልብሽን

ቢደከምልሽ የሚገባሽ ፍጥረት
ፀባዬ ሰናይ  ነሽ በእውነት
ስሜቴን አክብሬ ሳልጎዳ ስሜትሽን
ፍቅርን ፍለጋ ጠንቻለሁ ደጅሽን
ሃሳቤ ነጉዶ ልቤ ብሎ አንቺን
ዓይኖቼ ናፍቀው ለማየት ዓይንሽን
ተስፋ አድርጌ አምኜው ፍቅርሽን
ስጠብቅ ነበረ መምጫ ቀንሽን

ዛሬ ግን ተሳካ ቀን ወጣልኝ
በሩን ከፈተና ልብሽ ልቤን ታደገልኝ
አሁን ደስ ብሎኛል ተደስቻለው
ያ ሁሉ አለፈና ሰላም አጊቻለው
ፍፁም የነፃ በደል ያልቆጠረ
ከወርቅ ከአልማዝ እጂግ የከበረ
ቸርነትን የሚያደርግ የማይሰስት
የማያስመስል የሚጠላ ወረት

የልቤን አይቶ ጥማት ረሃቤን
አንቺን አመጣሽ አዝኖ ሃዘኔን
እውነተኛ ፍቅር ፅናት ይጠይቃል
በለሷን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል
እድለኛ ነኝ እኔ አምላክ የረዳኝ
ጥማቴን አይቶ አንቺን የሰጠኝ
ተደስቻለሁ ፍቅሬ አሁን ደስ ብሎኛል
ያከበርኩት ፍቅር ባንቺ ክሶኛል፡፡

ሂኩ ከአሁን ቡሀላ ጊዜ መስጠት አያስፈልግም እኔ እቤት ላሳዉቅ ነዉ አንቺምለቤተሰቦችሽ  አሳወቂ አለኝ ፡፡ እኔም እሺ አሳዉቃለሁ መቼ እናሳዉቅ?? አልኩት
...እሱም እኔ እንኳ እናቴ ታቃለች እናቴን በፊት አማክሪያታለሁ በህልሜ ሂክማ ስል አይደል የማድረዉ አለኝ ...ሁለታችንንም ተሳሳቅን.... አንቺ አሳዉቂ ለኔ ቀላሌ ነዉ ተባብለን ወደ ገርጂ የሚሄድ ታክሲ አስይዞኝ ተለያየን፡፡ በሒወቴ እንደዛሬዉ ቀን ተደስቼ አላቅም ዙበይር በጣም ወደድኩት ለካ ሁሉም ወንድ አንድ አይደለም...እያልኩ፡ሁሉንም ወንድ አንድ ነዉ እያልኩ ተስፋ ቆርጬ ነበር ግን እንደነዙበይር አይነት ወንዶች እንዳናገኝ እንደ ሀይደር ያሉ ወንዶች ግርዶ ሽፋን ይሆንብናል..እኔ ሂወቴ የሚስተካከል አይመስለኝም ነበር..ግን በዙበይር እንደገና ህልሜ ሊሳካ ሆነ አልሀምዱሊላህ... ታክሲ ላይ ሁኜ ሀሳብ ገባሁ የዛሬዋ ቀን ለኔ ተስፋ የሰነቀች ቀን ናት፡፡

   መቅሪብ አካባቢ እቤቴ  ደርስኩ ስገባ እናቴን ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጥቼ ገብቼ ግንባሯን ሳምኳት፡፡ መቼም እናቶች በኛ ፊት ላይ ደስታን እና ሀዘንን ማንበብ ይችላሉ
........እንዴ ልጄ ዛሬ ምን ተገኘ ደስተኛ ትመስሊያለሽ አለችኝ
 .....እኔም እናቴ መንገድ ላይ ዙበይር ጋር ያየችኝ መሰለኝ ፍርሀት ተሰማኝ ፊቴ በደስታ አብርቷል ገና እናቴን ሳልነግራት በፊቴ አወቀችዉ......
  እኔም እንዴት አወቅሽ??? አልኳት
.....እናቴም ዛሬ ልጄ የተገኘ ነገር አለ ማለት ነዉ ቀርበሽ እንደ እናት አዉርተሽኝ አታቂም እኮ ስገቢም ግንባሬን ከሳምሽኝ ቆየሽ ከመታመምሽ በፊት ነበር እኮ ግንባሬን የምስሚኝ ..... እስኪ ዛሬ የተገኘዉን ታጫዉችኛለሽ እርግጠኛ ነኝ አዲስ ነገር አለ ማለት ነዉ አለችኝ፡፡
ለነገሩ ዛሬ እቤት አገባቤ በጣም በደስታ ስለሆነ እናቴ ፊቴን አንብበዋለች ግን ዛሬ የደስታ ቀኔ ነዉ ዙበይርም ጋር ዛሬ እቤት እናሳዉቅ ተባብለን ነዉ የተለያየነዉ፡፡
.....እናቴን እሺ መቅሪቢን ሰግጄ አንድ የማማክርሽ ጉዳይ አለ እናወራለን ብየ መኝታ ክፍሌ ገብቼ መቅሪቢንሰግጄ ወደእናቴ ጋር ሳሎን ተመልሼ እናቴ ጎን ቁጭ አልኩኝ፡፡
....እናቴም ፀጉሬን እየሻሸች ዛሬ ምን ተገኘ ልጄ??? አለችኝ
.....እኔም ዝም ብየ ቀረሁ አፌ ላይ ወሬዉ እያለ መተንፈስ ተሳነኝ
....እናቴም አይዞሽ ወይ እኔ ልጀምርልሽ እንዴ አለችኝ
እኔም
......... እሺ ጀምሪዉ አልኳት
......የትዳር ጥያቄ የመጣልሽ መሰለኝ ባልሳሳት አለችኝ
....እኔም እንዴ ማን ነገረሽ አልኳት
.....እናቴ ሳቀች  ማንም አልነገኝ ግን ስመጪ ፊትሽ የደስ ደስ ይዞ ነበር የገባዉ ፡፡ ደግሞ ባለፈዉ በተከታታይ  አዳሬን ጥሩ ህልም አይቸልሻለሁ...
ዛሬ  አዳሬንም ጥሩ ህልም አየሁ ህልሙ ተደጋገመብኝ....ያየሁትን ህልም  ዛሬ ማታ እነግርሻለሁ እያልኩ የእናትሽ ህልም አንቺዉ መጥተሽ ሳልነግርሽ ህልሙን ፈታሽዉ አለችኝ፡፡
እኔም እናቴን እቅፍ አርጌ ሳምኳት ...እናቴ በደንብ አዳምጪ ሁሉንም ልነግራት ጀመርኩ ስለ ዙበይር እናቴ ዙበይር የሚባል ልጅ እንድንጋባ ጥያቄ አቅርቦልኛል ....... ዙበይር ማለት .......

#part 2⃣3⃣

#ይ.............#ቀ...............
.........#ጥ...............#ላ.......................#ል

4 another channal👇
             @Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
   
  T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
👍2
#አስመሳይ #አግብቼ

አስመሳይ አግብቼ ግራ ከምጋባ፣
ተደብቄ ልኑር ልቅር ሳላገባ።
ተመሳሳይ ኮፒ በመቅረቷ አልባባም፣
እምነት አሰዳቢ ፍፁም አላገባም።
የአላህን ትዕዛዝ ሂጃቧን አድርጋ፣
ከተጨማለቀች ከአጂነብይ ሰው ጋ፣
እሷን አላገባም ከቶ ቁሜ ልቅር፣
በብቻየ አለም ውስጥ ተደብቄ ልኑር።

አቂዳየ እያለ ምን አለው ካለችኝ፣
እስልምናየን ይዤ ድሃ ካረገችኝ፣
መስፈርቷ ከሆነ ቤት ና መኪና፣
ኒቃቢስትም ብትሆን ብትሄድ ተሸፍና፣
ትቅርብኝ ይች ልጂ እኔ አላገባትም፣
ኪታቤን አዝየ ሄዳለሁ የትም።

እውቀት ፍለጋየን አቀጣጥላለሁ፣
እምነት አሰዳቢ ለምን አገባለሁ።
ጀግና የጀግና ልጂ በመንሀጂ ያደገች፣
በሰለፎች አሰር አምራ የደመቀች፣
አላህ ከገጠመኝ ውብ ትዳር ፈላጊ፣
አስተዋይ መካሪ ንደት አረጋጊ፣
የሙብተዲ ጥላት ጦረኛ ተዋጊ፣

ሽርክን አፈራራሽ የተውሂድ ምርኮኛ፣
የቢድአ ካንሰር የሱና ሱሰኛ፣
እምነቷ ሲደፈር የሚያንዘረዝራት፣
ከእግር እስከ ራሷ ንደት የሚወራት፣
በአቂዳዋ ታጋይ ጀግና አርቆ አሳቢ፣
የእህቶቿ ሞደል በሂጃብ ተዋቢ፣

ከመጥፎ ከልክላ በመልካም ላይ አዛዢ፣
ውዲ ባልተቤቷን በፍቅር አደንዛዢ።
ለረጂሙ ጉዞ ስንቋን የሰነቀች፣
በተውሂድ በሱና በሀቅ የደመቀች።
ከመንሀጀ ሰለፍ ሁሌ የማትለወጥ፣
ያወራ ቢያወራ ልቧን የማትሰጥ።

ይህችን መሳይ ሞደል ታስፈልገኛለች፣
እህትም ፣ባልተቤት እናት ትሆናለች።
ችግሩ እሷ ግን የት አለች የት አለች፣
ልፈልግ በዱኣ ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም፣
እምነት አሰዳቢ አልለማመጥም፣
ተውሂድ ያልገባት ልጂ አርፋ አትቀመጥም።


ያ አላህ
እኔንም አድርገኝ ከነጓደኞቼ፣
ቀጥ ብየ የምሄድ አንተኑ ፈርቼ።
ሀቅ የምገልፅበት ስጠኝ እምቅ ወኔ፣
ተውሂድ ላስተምረው ይጠቀም ወገኔ።
ጀግናይቱ የት አለች ለባሽ ጥቁር ካባ፣
ብቸኝነት ይብቃኝ አትፈትነኝ ላግባ።

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
.....አስተዉሉ እህቶቼ...
ስንቶቻችን ነን ክብራችንን ምንጠብቀዉ??
ሼር
እናቴ (ዝሙት) መስራት እፈልጋለሁ...
.
አንዲት ወጣት እንስት እናቷን ዝሙት ትፈጽም ዘንድ ታስፈቅዳታለች።
.
እናትየውም በእርግጥም የፈለግሽውን ነገር ከመፈጸምሽ በፊት
ለአንድ ሳምንት የማዝሽን መፈጸም ይኖርብሻል ስትል አቋሟን
ታሳውቃለታለች።
.
እናትየውም እንዲህ ስትል ታዛታለች ወደ ንጉሱ ቤተ መንግስት ሂጂና
ልክ
ንጉሱ ከቤተ መንግስት ሲወጣ እራሱን እንደሳተ ሰው ውደቂ
.
ልጅየውም ልክ እንደተባለችው እራሷን ስታ ትወድቃለች ንጉሱም
እራሱ ከሰረገላው ላይ ወረደና ሙሉ
እንክብካቤ እንዲደረግለትና ቤቷ
እንዲያደርሷት አዘዘ
.
በሚቀጥለው ቀንም ንጉሱ ከቤተመንግስት ሲወጣ አሁንም
ራሷን ስታ ወድቃለች ንጉሱም ችላ
ብሎ አለፈ ዞር ብሎ እንኳን አልተመለከታትም
.
የንጉሱ ተከታይም ከወደቀችበት አነሳት በሶስተኛው ቀን እሱም
ይተዋትና የዘበኞች አለቃ ያነሳታል
.
በአራተኛው ቀን አለቃውም ትቷት አንድ ተራ ወታደር ያነሳታል
በሚቀጥለው ቀን ግን እሱም ቀርቶ ሰዎች እየገፉ ወደ ዳር ያወጧታል።
እንደተለመደው በመጨረሻው ቀንም እራሱን እንደሳተ ሰው ወደቀች
.
ይሄኔ ግን ፊቷን ከሚልሳት ውሻ ውጪ ምንም ነገር አላገኘችም
.
ከዚያም የእናቷ ተግባር የታከለበት ምክሯን እንዲህ ለገሰች
.
በማህብረሰቡ ውስጥ ክብሯን ያጣች ሴት ምሳሌም ይሄው ነው
በመጀመሪያ የተከበረች ሴት
በመሆኗ ሁሉም ይንሰፈሰፍላታል
.
ክብሯን ስታጣ ግን ፈላጊዋ ይጠፋል ሁሉም እንዳሻው ይጫወትባታል
በመጨረሻ ግን ማንም የማይፈልጋት ርካሽ እቃ ትሆናለች። ስትል
ልጇን
በጥበብ አስተማረቻት።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጣሪን መፍራት ጥበብ ነው! ከሀጢያት መራቅ ማስተዋል ነው።
አስተዋይ የሆነ ሰው ፈጣሪ መንግስት እንዳይለይ ራሱን ከአመንዝራ
ሊጠብቅ ይገባዋል።
በዚህ በአለንበት ዘመን ሰውን ያንበረከከ ትልቁ ሀጢያት
"ዝሙት" ነው

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
ምንም ብትሆን ምንም ብታደርግ ሰው
ስላንተ ተቃራኒ ማውራቱን አይተውም
* ………………………ቢሆንም
ካንተ በላይ ስላንተ የሚያውቅ ሰው የለም
* ያንተ ማንነት የሚለካው ሰውች
በሚሰጡህ ግምት አይደለም
………ያንተ ማንነት ያለው~
* ከማንም ሳይሆን ካንተ ውስጥ ብቻ ነው
* ማን ይወደኛል …?
* ማን ያከብረኛል…?
 እያልህ…
* ክብርህን ከሌሎች አትጠብቅ
* ሰው ስለሚልህ ነገር አትጨነቅ
* መጥፎ እንዳታደርግ ብቻ ተጠንቀቅ
* አንተነትህን ብዙ ለማስረዳት አትሞክር
ሰው እንደተረዳህ ሳይሆን አንተ
እንደገባህ፣ እንደመረጥከው፣
እንደሚያስደስትህ ኑር
* ለራስህ ምን እንደሚያስፈልግህ ካወቅህ
እራስህን ከተረዳህው በቂ ነው
*…………ዋናው እሱ ነው
* ሌላው አድርቅ ነው ተወው
*……… ማንም ምንም ይሁን

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 2⃣3⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal

    እኔም እናቴ ጎን ቁጭ ኡልኩኝ...ሁሉንም ልነግራት ጀመርኩ ስለ ዙበይር እናቴ ዙበይር ማለት .......የፊርዶስ ታላቅ ወንድም ስለ ፀባዩ እና እስከሚሰራዉ ስራ መርካቶ ሱቅ እንዳለዉ መኖሪያ ቤትም እንዳለዉ አከራይቶት እሱ ቤተሰብ ጋር እንደሚኖር ነገርኳት፡፡
     እናቴም ጥሩ ግን ፊርዶስ በጣም ጥሩ ልጅ ናት ማሻ አላህ የነ እሱ ዘር ጋር አንቺ መጋብትሽ ደስ ይለኛል፡፡ ግን ልጄዋ አለችኝ በስስት እያየችኝ የወደድሽዉ ብር ስላለዉ ሱቅ ስላለዉ መኖሪያ ቤት ስላለዉ ነዉ ወይ ?
.... አንቺ በብር አስበሽ ከሆነ አላህ ያይሻል አንቺ በብር የምትገዢ ሸቀጥ አይደለሽም እኔ የምፈልገዉ ኢማን ያለዉ አንቺን ወዶሽ በፍቅር ተሳስራችሁ ልጅ ወልዳችሁ የአንቺን ደስታ ማየት ነዉ እንጂ ገና እሱ ብር አለዉ ብለሽ አስበሽ የትዳር አጋር የመረጥሽዉ ከሆነ ልጄዋ ይቅርብሽ እኔ ዲን ያላቸዉ አብራችሁ ማደግ የምትችሉ ሁለት ሰዉ ቅርብ ቀን ልጅሽን ዳሪኝ ያሉኝ አሉ ልጄ እኔ የምፈልገዉ የአንቺን ደስታ እንጂ ወንድ ልጅ በብር ሀይል አግብቶሽ የሀብታም እስረኛ እንድትሆኝ አልፈልግም አለችኝ፡፡
.....እኔም እናቴን ምንም አላልኳት ወሬዋን አስጨረስኳት እዉነቷን ነዉ ትዳር ማለት ሁለተኛ ሂወት ማለት ነዉ እንጂ እንደ ሆቴል ገብቶ ተጠቅሞ የሚወጣበት ሂወት አይደለም፡፡ እናቴ ልክ ነሽ ግን ዙበይርን በብዙ ነገር ፈትኘዋለሁ እናቴ ብዙ ለአንቺ መንገሩ ጥሩ መስሎ ያልታዩኝ ሂወቶች ነበሩኝ..... ዙበይር ነዉ የተረዳኝ እሱ በብሩ የማይተማመን እኔ ለራሱ ይሄ ሁሉ እንዳለዉ የሰማሁት ቅርብ ቀን ነዉ ...የቀረበኝ ፍቅሩን ይዞ ትዳርን አስቦ እንጂ ይሄ ቤት አለኝ መርካቶ ሱቅ አለኝ ብሎ አንድ ቀን አዉርቶኝ አያቅም ማሚ በዲኑም ጎበዝ ነዉ ፡፡ የሚገርምሺ እንደ አንዳንድ ወንዶች አይደለም እናቱ ምሳ አዘጋጅተዉ ጠርተዉኝ አስተዋዉቆኛል፡፡ ለእናቱ የወደፊት ሚስቴ ናት ብሎ አሳዉቋል ማሚ እናቱም ወደዉኝ ስጦታ ሰጥተዉኛል ..ዙበይር የሚፈልገዉ እኔን ማጃጃል ሳይሆን ወደ በሀላል ወደ ትዳር ለመግባት ነዉ፡፡ እኔ ወድጀዋለሁ አንቺም ዉደጅልኝ ማሚ አልኳት፡፡
 
....እናቴም እኔ አንቺን እወድሻለሁ የወደድሽዉንም እወዳለሁ የምጠይዉንም እጠላለሁ ግን አንድ ፍሬ ልጄ ነሽ ጥሩ ትዳር እንዲኖርሽ እፈልጋለሁ ድል ባለ ሰርግ ነዉ የምድርሽ ዙበይርን አምነሽበታል አለችኝ
...እኔም አዎ እናቴ ዙበይር ነዉ ምርጫየ ብየ ብዙ ነገሮችን አጫወትኳት ያዉ የሚደበቀዉ ያለ ሁኖ መቼም እናቴ ናት እና ሀይደር ጋር ያሳለፍኩትን እና በዛ ነገር ሀኪም ቤት የተኛሁበትን ሂወት እኔም እናቴም እንድታስታዉሰዉ አልፈልግም........
በመጨረሻም እናቴ እሺ አለችኝ ..እኔም ደስ አለኝ ደግሞ ደስታየን እናቴ እንዲህ ብላ ጨመረችልኝ፡፡ ዙበይር አንቺን ለእናቱ ካስተዋወቀሽ በጣም ጎበዝ አስተዋይ ልጅ ነዉ እኔንም እሁድ ምሳ አዘጋጅተን ዙበይርን አስተዋዉቂኝ እሁድ ንገሪዉና ምሳ እንጋብዘዉ   እህቱ ፊርዶስም አብረዉ ይምጡ  ...እኔም ነገ ጠዋት ደዉየ ለአባትሽ እቤት እንደመጣ እነግረዋለሁ .. አባትሽም ይወቀዉ ነገ ከሰአት መጥቶ ከአባትሽ ጋር እንመካከርበታለን  ብላ እናቴ አስደሰተችኝ እኔም እናቴ ጋር ተቃቅፈን ሁለታችንም በጣም ደስ አለን ፡፡ እሁድ ለመድረስ ገና አራት ቀናቶች አሉ፡፡ እናቴ ለአባቴ ደወለችለት መምጣት የሚመቸዉ ቅዳሜ እንደሆነ ነገራት፡፡ ቅዳሜ አደራ እንዳቀር ለአስቸኳይ ጉዳይ ነዉ የምትፈለገዉ አለችዉ እናቴ...
.....አባቴም ለመስማት ጓጉቶ አሁን በስልክ ንገሪኝ ቢላት አይሆንም በስልክ ተነግሮ አያልቅም በአካል ስንገናኝ ነዉ የምነግርህ አለችዉ...
   ወዳዉ መኝታ ቤት በመግባት ለዙበይር ደወልኩለት ሁሉንም ነገር ነገርኩት እና እናቴ እሁድ ምሳ ትዉዉቅ እናድርግ  ብላኛለች እሁድ ይመቸሀል ከነእህትህ አልኩት
......እሱም በደስታ እንዴት አይመቸኝ ቤተቦችሽን ለመተዋወቅ ዝግጁ ነኝ አለኝ፡፡
.......ከዛ ለፊርዶስ ደወልኩላት ብዙ አዉርተን ...እሁድ ስላት
ወሬየን አቋርጣ ሂኩ ታዘብኩሽ አለችኝ
ምን ሆንሽ ፊርዱ አልኳት
እሷም የምሳ ግብዣዉን መጀመሪያ ለኔ ሳትነግሪ ለወንድሜ ነግረሽ ነዋ ከእኔ እና እሱ መጀመሪያ ያወቅሽዉ እኔን አይደል ብላኝ ተሳሳቅን፡፡

የማይደርስ የለም ነገ እሁድ ነዉ ዛሬ ቅዳሜ ላይ ነን ቅዳሜ ሙሉቀን ጀምረን እኔ እና እናቴ ለእሁዱ ባሌን የማስተዋዉቅበት የምሳ ፕሮግራም ደፋ ቀና እያልን ነዉ ..አባቴንም ሸዋ ሮቢት ስለሚኖር እሁድ እቤት ምሳ ተዘጋጅቷል ምክንያቱ ስትመጣ ይነገረሀል ብለን ቅድሚያ ስለነገርነዉ ቅዳሜ ማታ እቤት ገባ፡፡

     እቤት እንደገባም ስለ ነገዉ እሁዱ የምሳ ፕሮግራም እናቴ ነገረችዉ ግን አባቴ እና እናቴ በነገዉ ምሳ ላይ የተስማሙ አልመሰለኝም ፡፡ አባቴ ጮክ ብሎ ይሄማ መቼም አይሆንም እኔ ፈቅጄ ልጄን አልሰጥም አንቺ እኔ ሳልፈቅድ ትድሪያት እንደሆነ አያላሁ...እዚህ ቤት ወንዱ ወይ አንቺ ወይ እኔ እንሆናለን አትሰቢዉ እኔን የጠየቁኝ ሰዎች አሉ እንደዉም ለአንዱ ቃል ገብቸለታለሁ ትምህርቷን ስጨርስ ብየ አሁን ከህመሟ ከሻረች እኔም አንቺን አማክርሻለሁ እያልኩ ነበር በስራ ተወጣጥሬ ነዉ እንጂ ዛሬ ላማክርሽም ነበር ለአስቸኳይ ስትይኝ ጭራሽ ልጄ ታገባለች ብየ ትዝም አላለኝ፡፡ ወደድሽም ጠላሽም እኔ መቼም አልስማማም እኔ ለመረጥኩት ሰዉ ነዉ ልጄን የምድረዉ ...የነገዉም ምሳ ፕሮግራም እኔ አልኖርም እንደፈለጋችሁ ማረግ ትችላላችሁ...ተስማምቼ እሱን እኔ አልተዋወቅም፡፡ እናተ እሱ እቤት መጥቶ ብትተዋወቁ እኔ እና አንቺ ፍች ነዉ የሚለየን...እኔ ከሀገር ሌላ ሀገር በመንግስት ስራ የቤተሰብ ፍቅር ሳላይ በግዥ በሁቴል ምግብ የምኖረዉ አንቺ እና ልጄ እንድትደሰቱ እንዳትከፉ እንጂ ለራሴ መኖር መች አቃተኝ...ስለሆነም ይሄ የትዳር ነገር መቼም የማይሆን ነዉ ሲል እዉጭ ሁኜ ሰማሁት፡፡ የኔ ፈተና ብዙ ነዉ እኔም ከቤት ዉጭ ሁኜ ደንግጬ ቆምኩኝ...የማወራዉ ጠፋኝ ነገ ምሳ ዙበይርን ጠርቸዋለሁ....ትዳር ቤተሰብ ስቆ መርቆ ሲሰጥ ነዉ አለመግባባት ቢኖር ተመልሰን የምንመጣዉ ወደ ቤተሰብ ነዉ፡፡ ቤተሰብ ለወደደዉ ስቆ ደስተኛ ሁኖ ካልሰጠ ቡሀላ የሆነ ነገር ቢፈጠር ሌላ የቤተሰብ ጫና ይፈጠራል፡፡

....የሂክማ ፈተና በዛ አሁን ደግሞ አባቷ እኔ ያልኩት ካልሆነ አታገባም አለ..ዙበይርም ምሳ ተጠርቷል ምን ይፈጠር ይሆን በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን

#Part 2⃣4⃣

ይ...........ቀ...........
.........ጥ..........ላ................ል
4 another channal👇
             @Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
   
  T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
👍2
💐💐 #ወንድሜ!እነዚህን አስር ነገሮች ለባለቤትክ መፈፀም ካልቻልክ በትዳር ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል ምክሬን ጠበቅ አድርገህ ለመያዝ ሞክር "!!
➊☞_ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት።
➋☞ሴት ፍቅርህን እንድትገልፅላት ትሻለች #ባገኘኸው_አጋጣሚ ፍቅርህን ከመግለፅ ወደ ኃላ አትበል።
➌☞ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ።ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ።አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር።
➍☞ #_ሴቶችን_መልካም_ንግግር_ውብ_ገፅታ_ንፁህ_ልብሶችና _ጥሩ_መአዛ_ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖርህ ጥረት አድርግ።
➎☞ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው።ቤቷ ስትሆን ዙፏኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል።በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባት ነገር እንዳትፈጵም ።ከንግስና ዙፏኗ ላይ ልታወርዳት እንዳትሞክር።ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ።
➏☞ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም።አንተን ከቤተሰቧ በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር ።ይህን ማድረግ ፋፃሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል።
➐☞ሴት ከጎንህ(ጠማማ አጥንት)መፈጠሯን አትዘንጋ።ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን አወቅ ።ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለው እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ።ስብራቷ ፍቺ ነው።ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት ።መካከለኛ ሰው ሁንላት ።
➑☞_ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል።ነገር ግን እንዲህ አደረገች ብቻ በማለት እንዳትጠላት።ይህን ባህሪዋን ባቶድላት ሌሎች ሚስቡህ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ።
➒☞ሴት አካላዊ ድካምና ስነ ልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል። #የአንተን_ፍላጎት_ለማሟላት_የሚከለክላት_ነገር_አለ፡፡ በዚህ ወቅት ከፍጥረታት ሁሉ የተጥራራዉ ጌታችን አሏሁ ሱብሐነሁ ወተዓላ የግዴታ አምልኮዎችን (ሶላትና ፆም)ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል። #በዚህ_ጊዜ_እዘንላት_ትእዛዝ_አታብዛባት
➓☞ #ሴት_አንተ_ዘንድ_ያለች_የፍቅር_ምርኮኛህ_መሆኗን_አትዘንጋ_ምርኮኛህን_በጥሩ_ሁኔታ_ያዛት_እዘንላት_በድክመቷ የምትፈፅመውን ስህተት እለፋት ።ምርጥ የህይወትህ አጋር ትሆንሀለች።

💐ትደር ላይ ላላችሁ በሙሉ ኑሯችሁ የጣፈጠ ይሁንላችሁ

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
😔#የባከነ #ህይወት 😢
#ክፍል 1⃣

#ፀሀፊ ☞ mahalet Ethiopiawt

ማርታ እባላለሁ ለቤተሰቦቸ የመጀመሪ ልጅ ነኝ ሁለት ታናናሽ ወንድሞች አሉኝ አባቴ በተለየ እኔን በጣም ይወደኛል እኔም በጣም እወደዋለሁ በ7 በአል ነበር አዲስ ልብስ አልተገዛልኝም ታጥቦ የተቀመጠ ልብሴን አውጥቸ ለብሸ ወደ  ስሄድ ሁሉም አዲስ ልብስ ለብሰዋል እኔም ልጅ ስለሆንኩ እያለቀስኩ ወደቤት ተመልሸ ሶፋው ላይ ኩርምት ብየ ቁጭ አልኩ
.......አባቴ ልጀ ምን ሆነሽ ነው ጨዋታውን አቆርጠሽ የመጣሽ ሲለኝ
......ሁሉም አዲስ ልብስ ለብሰው የኔ ብቻ አሮጌ ብየ አለቀስኩ አንችንማ እይከፋሽም ብሎ ወዲው ወጥቶ የሚምር  ልብስ ገዝቶልኝ መጣ ሲሰጠኝ በደስታ ስሜው ልብሱን ለብሸ እየሮጥኩ ጓደኞቸ ጋ ሄድኩ፡፡ ስፈር ስንጫወት  ውለን ተለያየን እናቴ አርቄ ታወጣለች አንድ ቀን  እናቴ ከቤት ወጣ ስትል እናቴን ላስደስታት ብየ ወጥ ሰርቼ ልጠብቃት ብየ ወጥ ሰራሁኝ፡፡ ወጡን ሰርቼ እንደጨረስኩ ወዲያው እናቴ መጣች ምድጃውን ስታይ እሳቱ ጠፋቶል ወጡ የታል ስትለኝ ሰርቼ አወጣሁት ስላት የታል ብላ ጮህች አሳየዋት ቀመሰችዉ....እንዴ እንዴት እንደዚህ አርገሽ ትሰሪያለሽ አበላሽተሻል እያለች ጮህች
......በጣም ደነገጥኩ በሩን ዘግታ በአለንጋ ቅጥቅጥ አርጋ ገርፈችኝ ሰውነቴ አበጠ አባቴ ሲመጣ ለመናገር መንገድ ላይ ቁጭ ብየ ስጠብቅ ምሽት 12 ሳዐት ሲሆን መጣ ገና ከሩቅ ሳየው ወደሱ እየሮጥኩ አባቴ ደንግጦ እሩጦ አቀፈኝ ምን ሆንሽ ሲለኝ እያለቀስኩ እማየ ገርፍችኝ ስለው ምን አጥፋተሽ ሲለኝ ነገርኩት
.....ቤት ገብቶ እናቴን ደበደባት እሶን አናዳኝ ስለነበር ደስ አለኝ የሆነ ፎቅ ላይ ወጥቸ እያየው እሰይ አልኩ ጎርቤት ደርሶ ገላገላቸው ፡፡አባቴ ልጄን ሁለተኛ ስራም እንዳታዥት አላት እናቴ ልጅቱ የእኔም ናት ብላ ጮህች ከብዙ ግርግር በኃላ ጎርቤቶች አስታርቆቸው እናቴ ስራ ማዘዝ አቆመች በትምህርቴ ጎበዝ ነኝ ሰፍር ትምህርት ቤት የትም ቦታ እረባሽ እና ተጫዋች ነኝ
    የሆነ ሰው ከሰደበኝ እደባደባለሁ በዚህ ፀባየ በጓደኞቸ አድናቆት ይሰጠኛል አንድ ቀን አንዶ ጓደኛየ እያለቀሰች ቤት መጣች ምን ሆነሽ ነው ስላት እራሄል ሰደበችኝ አለች እራሄል የሌላ ሰፍር ልጅ ነች ከእኔ ጋር ክፍላችን አንድ ነው በቃ አታልቅሽ ነገ እቀጠቅጥልሻለሁ ስላት ደስ ብሎት ወደቤቶ ሄደች ጧት ትምህርት ቤት ሂደን ክላስ ገብቸ ሳስብ የነበር እራሄልን እንዴት እንደ ምመታት ነበር መምህር ሲያስተምር ምንም አልሰማም ልንለቀቅ ትንሽ ደቂቃ ሲቀር ለመምህሩ ፍቀድልኝ እራሴን አሞኛል ብየ ወጠው እሩጨ ከትምህርት ቤት እራቅ ያለ ጎድጓዳ ነገር አለ ከዛ ገብቸ ተደበኩ እራሄል ብቸዋን ስትመጣ ማንም ሳያየኝ ጉድጓዱ ውስጥ አስገብቸ ቅጥቅጥ አደርኮት ሲበቃኝ ጥያት ሄድኩ .......የደበደብኩላት ጓደኛየ በጣም ደስ አላት ለአባቴ ብዙ ጊዜ ልጅህን አስተውልን የሚል ስሞታ ቢነገርውም እሱ ምንም አይለኝም
        ይህ የቤታችን ደስታ መቀጠል አልቻለም እናት እና አባቴ ሁሌ ይጨቃጨቃሉ አንድ ቀን አባቴ ሽማግሌ ሰብስቦ መፋታት እፍልጋለሁ አለ እናቴም በተመሳሳይ እቃ ሲከፋፍሉ ደና ደና እቃወችን መርጦ አባቴ ሳጥን ውስጥ ቆለፍ እናቴ ብትለምነው አልሰጥም አላት የሰጣትን ተቀብላ የታናሸን ታናሽ ወንድሜን ይዛ እኔን እና ታናሽ ወንድሜን ከአባታችሁ ጋር ሁኑ ብላን ሄደች ቤተሰቦቸ ልክ እንደ ህፃን ጨዋታ ጨዋታ ፍርሰ ዳቦው ተቆርሰ እንደምንለው ትዳራቸውን የበተኑን ለእኔ እና ለወድሞቸ ደግሞ የህይወት ምራፋችንን የቀየሩት በዚህ ጊዜ ነበር ዛሬም ድርስ ህይወቴ ባክኖ እንዴቀር የሚደርግ ጥፋት ያጠፋሁት…………

#Part 2⃣

ይ..............ቀ..............
...........ጥ..........ላ..................ል

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
👍1
#ህይወትህ_በደስታ ለማሳለፍ የሚጠቅሙ ምክሮች
➊• ቀንህን መጀመሪያ ሱብሂ ሶላትን በመስገድና (አዝካሩ ሰባህ) የጠዋት ዚክሮችን በማድረገ ጀምር ያንን ቀን ደስተኛ ሆነህ ታሳልፋለህ ምናልባት ችግር እንኳን ቢፈጠር አላህ ይረዳሃል።

➋• ሸይጣን እራሱን ማነቅ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ኢስቲግፋር አብዛ።

➌• ዱአ ማድረግህን አታቋርጥ ከጀሃነም የመትረፊያ ገመድ ነውና አይስጠኝም ብለህ ከአላህ ተስፋ አትቁረጥ አላህ አንተ ያደረከው ዱአ "3" በሶስት አይነት መንገድ ሊመልስልህ ይችላል
1⃣/ የጠየቅከውን ነገር ወዲያው ይሰጥሃል
2⃣/ የጠየቅከውን ነገር አዘግይቶ ከጠየቅከው በላይ በተሻለ ነገር ይሰጥሃል
3⃣/ ያደረከውን ዱአ ወደ አኼራ አስተላልፎልህ የውመል ቂያማ ይመነዳሀል ኢንሻ አላህ።

➍•የምትናገራቸው ቃላቶች ከቀኝና ከግራህ ያሉ መላኢካዎች እንደ ሚፅፉት ምን ግዜም አስታውስ

➎ የእጆችህን ውበት በነሱ ዚክር በማድረግ ጨምርላቸው።

➏• በጥቂት ገንዘብ የድሆችን ዱአ የምስኪኖች ውዴታ የየቲሞች ደስታንና የአላህ ውዴታ አግኝ።

➐ አንዲት በአላህ ፍራቻ የተደረገች ረዘም ያለች ስጁድ በአዱንያ ከምታያቸው ቤተ መንግሰታት እንደ ምትበልጥ እወቅ ።

➑• አንድ ቃል ከመናገርህ በፊት በደንብ አስብ ያቺ ቃል ብዙ ችግር ውስጥ ልታስገባህ ትችላለች።

➒• የበደልከውን ሰው ዱአ ፍራ የከለከልከው ሰው እንባ ተጠንቀቅ።

➓• መፅሀፎች ጋዜጣ ከማንበብህ በፊት ቁርአን ቅራ

➊➊• ነፍስህ ጥሩ ነገር እንድትሰራ ታገላት ነፍሳችን በተፈጥሮ መጥፎ ነገር አዛዥ ናትና።

➊➋• የወላጆችህ መዳፍና ግንባር ሳም የአላህ ውዴታ ታገኛለህ።

➊➌ የንጉሶች ንጉስ የሀብታሞች ሀብታም አንተ ለራስህ ከምታስበው በላይ ላንተ የሚያስብልህ #አላህ_ሱብሀነሁ_ወታአላ ምን ግዜም ካንተ ጋር መሆኑን አትዘንጋ

➊➍• በሚያጋጥምህ ሙሲባ እና ችግር ላይ አላህ እንዲያግዝህ በሶላት ወደሱ ተቃረብ።

➊➎ መጥፎ ጥርጣሬዎች ከራስህ አስወግድ ትርፋማ ትሆናለህ።

➊➏• የሁሉም ጭንቅ መጥፎ ሀሳቦች ምክንያት ከአላህ መራቅህ ነው ስለዚህ ወጀ አላህ ተመለስ።

➊➐ ቀብር አብሮህ ሊገባ የሚችለው ሶላትህ ስገድ።

➊➑• አንተን ያማህ ሰው ጥሩ ስራውን እያካፈለህ ስለሆነ አውፉ በለው አላህ ከሱ ጥሩ ስራ የበለጠ መልኩ ይመነዳሃል።

➊➒• የጀሃነም እሳት እንደምትጠብቀው ያወቀ ሰው ወንጀል ከመስራት እራሱን ይቆጥባል

➋0•ሶላትህን በአላህ ፍራቻ ስገድ የውመል ቂያማ መጀመሪያ የምትጠየቀው ስለ ሶላት ነው እሱ ከተስተካከለ ሌላው ነገር እንዳለ ይስተካከላል በአዱንያ ከምታረጋቸው ነገሮች በላይ አሳሳቢ አንገብጋቢ ሶላታችንን በወቅቱና በጀመአ መስገድ አለብን።

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
👍1
By mehbuba. B.A
<<<አድምጪኝ እህቴ>>>

አድምጪኝ እህቴ ምክር ልለግስሽ፣
እስከመቼ ድረስ ከፈጣሪሽ እርቀሽ፣
ሀራም ሳትተይ ከሀላል ታቅበሽ፣
ሀራም የተባለን ታግበሰብሻለሽ፣
በሰውላይ አማርረሽ አንቺት ሰሪያለሽ፣
ያንቺን ጥፋት ታዳ ለምን ትረሻለሽ፣
በፋሽን ተውበሽ ለብሰሽ እንዳለበሽ፣
ከሀጂነብይጋ እኽቲሏጥ አይርቅሽ፣
እስከመቼ ድረስ በወንጀል ታንፀሽ፣

ጌታሽን ቅረቢው ተውበትሽን አርገሽ፣
አሏህን ሚፈራ ለማግኘት ከፈለግሽ፣
አንቺ ሷሊህ ሁኒ ተስተካከይ ቀድመሽ፣
አንቺ ባልባሌ በቧልታ እየኖርሽ፣
ቤተሰብ አክባሪ እንደት ታገኛለሽ ፣

ለድኑ የሚኖር ፈጣሪውን ፈሪ፣
ከሀላል ሚመገብ በሸሪአ አዳሪ፣
የጌታውን ትእዛዝ ሀቁን የሚሞላ፣
በገንዘብ ታውሮ የማይሆን ተላላ፣
በአዱኒያ ፍቅር ተታሎ ያልቀረ፣
ወደጌታው ዞሮ በስቲግፋር ያደረ፣

ቀኑን በፆም ውሎ ሌቱን ሚሰግድ፣
ለእናት አባቱ በፍቅር ሚዋረድ፣
የቲምን የማይርቅ ደካማን የሚወድ፣
እንዲህ አይነት ሪጃልከሆነ ሀሳብሽ፣
አሏህን ተገዢ ሸይጧን አይወስውስሽ፣
ሷሊህ ሆነሽ አንቺ ለሰወች ልትረጂ፣
ከፈጣሪሽ ዘንዳ እንድትወደጂ፣

በዚች ጠፊምድር መማረኩ ይብቃን፣
አብረን የነበሩት እርቀው ከጎናቺን፣
ስንቱ ከፊታቺን ሲነጉድ እያየን፣
የኛ ችላ ማለት ከቶ ለምን ይሆን፣
እህቴ ልንገርሽ መታለሉ ይብቃን፣
ተውበት አድርጊና ልበሺ ሂጃብን፣
ሂጃብ ለሴት ልጆች ዋጂብ ነውና፣

አጥብቂው ከልብሽ ከሸይጧንራቂና፣
ለሙስሊም ወንድምሽ አትሁኒ ፊትና፣
ለሙስሊም ወንድምሽ አትሁኒ ፊትና።

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
😔#የባከነ #ህይወት 😢
           #ክፍል 2⃣

#ፀሀፊ ☞ mahalet Ethiopiawt


     እናት እና አባቴ ሲፋቱ በጣም ከፋኝ ከማን ጋር ልሆነው ከእናቴ ወይስ ከአባቴ ግራ ተጋባሁ እናቴ የታናሸን ታናሽ ወንድሜን ይዛ እኔን እና ታናሽ ወንድሜን ከአባታችሁ ጋር ሁኑ ብላን ሄደች እናቴን በአይኔ ተከትየ ሸኘሆት እናቴ ከሄደችበት ቀን ጀምሮ አባቴ እራሱ ምግብ እየሰራ እንበላለን እኛን ትምህርት ቤት ልኮ እሱ ወደስራ ይሄዳል በሶስተኛው ቀን አባቴ ቤት አልነበርም እናቴ መጥታ ስማን እኔን ነይ ተከተይኝ የምኖርበትን ቤት ላሳይሽ ምግብ ሲርባችሁ መጥታችሁ እንድትበሉ ቤቴን ላሳይሽ ብላኝ ተከትያት ሄድኩ
     ከእኛ ሰፍር እራቅ ይላል ግቢ ገብተን ቤቱን አይቸ ተመለስኩ ከዛ በኃላ ሁሌም አባታችን ሳያየን ከታናሽ ወንድሜ ጋር እየሄድን ምግብ በልተን ተጫውተን እንመለሳለን በተለይ ትምህርት ከሌለን ውሎችን ከእናታችን ቤት ነው አባታችን ሙሉ ቀን ሰራ ስለሚውል ከእናታችን ጋር እንደምንገናኝ አያውቅም .
........አንደቀን እናቴ አንደ እምትወጅኝ ከሆነ አንድ ነገር አርጊልኝ አለችኝ
......ምን ነበር አልኮት አባትሽ ሳጥን ውስጥ የደበቀብኝን እቃ በጣም እፍልገዋለሁ የሳጥኑን ቁልፋ ፍልገሽ ከፍተሽ የምፍልጋቸውን እቃ እና ልብስ አምጭልኝ አለችኝ
..... እሽ ብያት ወደቤት ሄጀ የሳጥኑን ቁልፍ ብፈልግ ብፈልግ አጣሁት ከዛ በብርት ዘነዘና ሳጥኑን ሰብሬ ከፍትኩት ሁሉንም እቃ ልብስ የአልጋ ልብስ ሳይቀር ሰብስቤ ለእናቴ ሰጠዋት እናቴ ስታመጭ ማን አየሽ ስትለኝ ጎርቤታችን አይታኛለች ስላት ለአባትሽ ትነግርዋለች ግን እንኳን አመጣሽልኝ ብላ ደስ ብሏት እኔም ወደቤት ተመለስኩ
    ማታ አባቴ ከስራ ሲመለስ ልብሱን ስወስድ ያየችኝ ጎርቤታችን መንገድ ላይ ጠብቃ ነገርችው አባቴ በጣም ተናዶ መጣ ለምን እቃውን ለእናትሽ ሰጠሽ ከዛሬ ጀምሮ እናታችሁ ታሳድጋችሁ ብሎ ጮህብኝ እራት ሳንበላ ተኛን ጦትም አባቴ ቁርስ ሳያበላን ወቶ ሄደ በጣም እርቦናል
.....ወዲው ከወንድሜ ጋር ወደ እናታችን ቤት ሄድን ምግብ ለመብላት ቤቶ ስንደርስ ቤቱ ተዘግቶል አከራዮን ስንጠይቃት እናታችሁ እቀዋን ሰባስባ ሂዳለች አለችን በእናቴ ተናደድኩ እንዴ እንዲህ ታርገኛለች አባቴ እንደሚጣላኝ እያወቀች ወደቤት ተመልሰን በር ላይ ኩርምት ብለን ተቀምጠን
  አንዷ ጎርቤታችን መጣች ምን ሁናችሁ ነው ስትለን እራትም ቁርስም አልበላንም እራበን ስንላት በሉ ተነሱ እኔ ጋር ትበላላችሁ ብላ ቤቶ ወስዳ አበላችን አባታችን ማታ ሰክሮ እየተንገዳገደ መጣ ክፍሉ ገብቶ ተኛ በዚህ ሁኔታ ለሳምንት ቀጥልን ምግብ ጎርቤታችን ታበላናለች ትምህርታችን ተቆርጠ ምግብ የምታበላን ጎርቤታችን እኔን ጠርታ
>>>>>>>እስከመቸ በዚህ ሁኔታ ትኖራላችሁ አንች ሰው ቤት ግቢ ስራ ስሪ በደማወዝሽ ወንድምሽን ታግዥዋለሽ አለችኝ
>>>>///>>>ማን ይቀጥርኛል ስላት እኔ የማውቃት ሰው አለች ህፃን ልጅ አላት ህፃኑን የሚይዝላት ሰራተኛ ትፍልጋለች ከእሷ አስገባሻለሁ አለችኝ ደስ ብሎኝ እሽ አልኳት
......ቤት ገብቸ ለወንድሜ ስነግርው አትሂጅ እየራበንም ቢሆን አብርን እንኑር ብሎ አለቀሰ ሀሳቤን እንደማልቀይር ደጋግሜ ነገርኩት በጧት ጎርቤታችን ቤት መጥታ ተነሽ ልውሰድሽ ስትለኝ ያሉኝን ልብሶች ሰብስቤ ስወጣ ወንድሜ ጨርቄን ይዞ እህቴ አትሂጅብኝ ብቸየን ጥለሽኝ አትሂጅ ወይም እኔንም ውሰጅኝ እናቴ እና ወንድሜ ጥለውኝ ሄዱ አንች አትሂጅብኝ እያለ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል እኔም አብሬው እያለቀስኩ እንደምንም ብየ እጅን ከልብሴ አስለቅቄው ጥየው ሄድኩ
      ገና በ 11 አመቴ የሰው ቤት ሰራተኛ ሆንኩ እሩጠው ያልጠገቡ እግሮቸ በአንድ ግቢ ውስጥ ተቆለፉ ያልጠነከሩ እጆቸ ልጅ ታቅፍው መዋልን ተፈርደባቸው የገባሁባቸው ሰወች ልጆች አሏቸው እኔ ህፃኑን እይዛለሁ ሌላ አንዴት ሰራተኛ አለች ምግብ እና ፅዳት የሷ የስራ ድርሻ ነው የሰውየው ስራ ሌላ ሀገር ነው አልፎ አልፎ ለእርፍት ሲመጣ ከልጆቹ እኩል ስጦታ ያመጣልናል ትንሽ ሰንብቶ ያሄዳል፡፡
     ቤተሰቦቸ ይናፍቁኛል በተለይ ታናሽ ወንድሜ ስለየው ጥለሽኝ አትሂጅ እያለ ያለቀሰው እንባ ከሀሳቤ ለደቂቃ አይጠፋም ማታ ስተኛ ወንድሜን ሳስታውስ አይኖቸ እንባ ያፍሳሉ ጉንጮቸ በእንባ ይታጠባሉ በዚህ ሁኔታ ኑሮየን ጀምሬለሁ እንድ ቀን ህፃኑ ልጅ እኔ ሰራተኘዋ እና ሰውየው ቤት ነበርን ትልቆቹ ልጆች ትምህርት ቤት ሴትዮዋ ስራ ሂደዋል ሰውየው ክፍሉ ውስጥ ሁኖ ውሀ አምጭልኝ ብሎኝ አዘዘኝ ውሀውን ይዥለት ስገባ ወዳው በሩን ዘግቶ እጀን ጉትት ሲያርገኝ በድንጋጤ ብርጭቆውን መሬት ላይ ከሰከስኩት 😢

#part 3⃣
ይ.......,......ቀ...................
..........ጥ............ላ...................ል

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
👍1
😍 #የት_አለሽ_የኔዋ•••

የት አለሽ የኔዋ ያይኔ ማረፊያየ
የሂወቴ መብራት አልባሳት ጎጆየ
የጎኔ ፍልቅቃት የፍቅር ርስቴ
አንቺ የብቻየ ገንዘቤ ንብረቴ

የት አለሽ የኔዋ•••
ሜካፕ የማታቂ እንዳሁኑ ወጣት
ከቤት የምቶጪ በተፈጥሮ ቅባት
ሁነሽ የኔ ኩራት,,

የት አለሽ የኔዋ •••
ቴሌግራም ፌስቡክ ፈጠሽ የማታድሪ
እንደበዙት ሴቶች ማሬ ውዴ ብቻ የማቀባጥሪ
ፍቅርን ከወሬ አልፈሽ የምተገብሪ ,,

የት አለሽ የኔዋ •••
ባህል እምነትሽን ጠብቀሽ የኖርሽው
ለብጥስጥስ ፋሽን አይንሽን ያዞርሽው

የት አለሽ የኔዋ•••
ከውሸት ማስመሰል ከወረት የፀዳሽ
ገና ሳልናገር ውስጤን የተረዳሽ
ከሴትነት ወዲያ ሚስትነት የገባሽ

የት አለሽ የኔዋ •••
ሳላቅሽ ናፍቄሽ በምኞት የኖርኩሽ
የት አለሽ የኔዋ ውጪ ከምሽግሽ
እየጠበቀሽ ነው ውዱ ውሀ አጣጭሽ
#sean_wiz_y_lph

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••⭐️•••════•
┈ድንቅ ታሪክ ናት┈┉┅━

{በሙሳ ዐ.ሰ} በዘመን ነው ....
አንድ በጣም ድህነት ያጎሳቆላቸው ለዘመናት በችግር እና በረሀብ የኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ።
ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ዘመናት በሰብር አሳልፈዋል.።
እናም አንድ ቀን እቤታቸው ጋደም ብለው ሳለ
#ሚስት #ለባለቤትዋ፦"ሙሳ አላህን ማናገር የሚችል ነቢይ ነው አይደል?" ብላ ትጠይቀዋለች።
#እሱም፦"አዎን" ይላታል።
"ታዲያ ለምን እሱጋ ሄደን ስለ ሁኔታችን አንነግረውም አላህንም ስለኛ ያናግረው ሀብታም እንዲያረገን ቀሪ ህይወታችንን በድሎት እንድንኖርም ይጠይቅልን።" አለችው።

🍃🍃ባልም በሚስቱ ሀሳብ ይስማማና ሌሊቱ እንደነጋ ጉዞ ወደ {ሙሳ ዐ.ሰ} ቤት ጀመሩ።
{ሙሳንም ዐ.ሰ} አገኟቸው። ስለድህነታቸው ነግረዋቸውም በዚህ ጉዳይ እሳቸው አላህን እንዲለምኑላቸው ጠየቋቸው።
{ሙሳንም ዐ.ሰ} አላህን ለመኑላቸው።

#አላህም፦"ሙሳ ሆይ! እኔ እነዚህን ሰዎች በችሮታዬ ለአንድ አመት ያህል
ሀብታም አደርጋቸዋለሁ !
አንድ አመት ካለፈም ወደነበሩበት ድህነት እመልሳቸዋለሁ።
#ብሎ_መለሰላቸው
እሳቸውም ጥንዶቹ ጋ በመሄድ
#አላህ ዱዓቸውን #ሙስተጃብ እንዳደረገላቸው።
ሀብታምም እንደሚሆኑ ነግረዋቸው እናም ግን ለ አንድ አመት ቢቻ እንደሚቆይ አክለው ነገሯቸው።
እነዚህ ምስኪኖችም የሰሙትን ማመን ተሳናቸው።
በአጭር ግዜ ውስጥ ካለሰቡበት መንገድ ሀብታም መሆን ጀመሩ ማንም
ከሚኖረው የተሻለ ኖሮ መኖርም ጀመሩ።
እናም አንድ ቀን ይህች ብልህ #ሚስት #ለባሏ እንዲህ አለችው፦
"ይህ ፀጋ ይህ ድሎት ለአንድ አመት ብቻ እንደሚዘገይ ታውቃለህ አይደል? ስለዚህ በዚህ ንብረታችን
#አንድ_መልካም_ስራ_እንስራ
#ባልይውም በሀሳቧ ይስማማል።
ከዚያም በከተማዋ ግንባር ቦታ ላይ አደባባይ መልክ አንድ ትልቅ ቤት
ይገነቡና 7 በር አበጁለት።
ለሰውም መተላለፊያ ሰሩ።
ቤቱ ተገንብቶ ካለቀ በኋላ እዛ ቤት ውስጥ ምግብ እያዘጋጁ ለአላፊ አግዳሚ #ጠዋት #ማታ
ምግብ ይቀልቡ ጀመር...።
በዚህ ሁኔታ ሳሉ ወራት አስቆጠሩ።
#ሙሳም በትኩረት ይከታተሏቸው ነበር። ማይደርስ ቀን የለምና ያ የተወሰነላቸው ቀን ቀጠሮውን ጠብቆ ከች አለ።
እነሱ ግን የቀጠሮ ቀኑ ሁላ ትዝ አላላቸውም በስራቸው ተጠምደዋል።
ያ ቀጠሮ ቀናቸው አለፈ እነሱ ግን ያው ናቸው ምንም አልቀነሱም ብቻ በስራቸው
ተጠምደዋል....
{ሙሳንም ዐ.ሰ} ባዩት ሁኔታ ተገርመው፦
#ያ_ረብ_ቃል_የገበኽላቸው_ለአንድ_አመት_ሆኖ_ሳለ_እንዴት_እስካሁን_እልደኸዩም?"
#ብለው አላህን ጠየቁ።
እዚጋ እሳቸው ሰዎቹን ተመቃኝተው ሳይሆን #የአላህን_ሂክማ_ለማወቅ_ነው

የጠየቁት/ ቸር የሆነው #አላህም
#ሙሳ_ሆይ!
#ለነዚህ_ጥንዶች_ከፀጋ_በሮቼ_አንዲትን_በር_ስከፍትላቸው...
#እነሱ_ደሞ_7_በር_ከፍተው_ባሪያዎቼን_መቀለብ_ጀመሩ
#ሙሳ_ሆይ!
#እነሱ_ይሄን_ሲያረጉ_አይቼ_የከፈትኩላቸውን_በር_መዝጋት_ከበደኝ"አለው።
━┅┉┈ሱብሀን አላህ┈┉┅━

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸