ISLAMIC SCHOOL
12.6K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
😔እኛ የመሬት ነን እንጂ መሬት የኛ አይደለችም

😔ይቺ ሀገር የኔ ናት ይሄ መሬት የኔ ነዉ ከማለትክ በፊት ቆም ብለክ አስብ መሬት የማንም አይደለችም.......

😔መሬት የማን እንደሆነች ለማወቅ ከፈለክ የቀብር ቦታዎችን ሄደህ ተመልከት!
ያኔ እኛ የመሬት እንጂ መሬት የኛ እንዳልሆነች ይገለፅልሀል!
ቀናችን ሲደርስ በእቅፏ አስገብታ ከአፈሯ ጋር ትቀላቅለናለች!
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
😔በግብፅ በግፍ ከተገደሉት መካከል አንዱ ለልጁ የፃፈላት ደብዳቤ አህመድ ዋህዳን
አንቺ የልቤ ማረፊያ የተወደድሽ ልጄ ሆይ… እወቂ። አባትሽ ምንም አይነት ወንጀልን አልተሸከመም ። አሳቤ ሰፋፊ እስርቤቶች ያሉባትን ሀገር ሳይሆን አንቺን እና መሰሎችሽን መጠበቅ የምትችል ሀገርን መፍጠር ነበር።
የልቤ ማረፍያ የተወደድሽ ልጄ ይቅርታሽን…? በእቅፌ ውስጥ ሸጉጬሽ ንፁህ ግንባርሽን አልሳምኩም ግና በዚያ መለያየትና ስንብት በማይታወቅበት በጀነት በር ላይ እጠብቅሻለሁ!!😢
Ahmed Wahdaan Shaheed (Egypt)
Before being Hanged ,He leaves a letter for his Innocent Daughter !
He writes , " Dear Love (My Laila), I didn't committed any crime , neither any offence for which I am being Hanged. Dear , I'm sorry , I couldn't do anything for you !
But , I'll be waiting for you at the Door of Jannah ! Where No one will separate us ! Fee Amanillah My love !
Successors of Hassan Al Banna still kiss the gallows with a Smile on their face !

´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
          `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science


☑️ ሼር በማድረግ ለጓደኞዉ ያካፍሉ
#ስለ_ልጆች_አስተዳደግ_ዶ/ር ምህረት እንዲህም አሉ


✔️ልጅን በባህሪ ማከም አስቸጋሪ የሚያደርገው ብዙ ጊዜ በሽታው ወላጅ ላይ ስለሆነ ነው። ወላጆች ደግሞ ችግሩ የነሱ መሆኑን ተረድተው ለመቀበል ብዙ ጊዜ ይቸገራሉ።

✔️ የወላጅ ትልቁ ኃላፊነት ልጅን ጨዋና ጎበዝ ተማሪ አድርጎ ማሳደግ ብቻ ሳይሆን ብልጥና ጠንቃቃም ማድረግ ነው። ይህንን ለማድረግ ደግሞ ልጆችን እየተሳሳቱ እንዲማሩ ዕድል መስጠት ያስፈልጋል።

✔️ በትክክል ያላደጉ ልጆች እንዴት ጥሩ ወላጅ ሊሆኑ ይችላሉ? ሠዎች
☞ሙዚቃና ስፖርት፣
☞እጅ ሥራና እርሻ ከልጅነታቸው ሲማሩ፤ ወላጅነትንና የትዳር አጋርነትን ግን በግምትና በመላምት የሚገቡበት መሆኑ አስገራሚ ነው።
⭐️አውሮፕላን አብርሮ በማያውቅ ፓይለት በሚበር አውሮፕላን ውስጥ ማንም አይሳፈርም። ብዙ ልጆች የሚወለዱት ግን ትዳርና ቤተሰብ እንዴት እንደሚመራ በማያውቁ አዲስ ለማጆች ባቋቋሙት ቤት ውስጥ ነው።

✔️ሴት ልጅ ከአባቷ ተወዳጅነትንና አፍቃሪነትን፤ ከእናቷም ወዳጅነትንና ወላጅነትን ትወርሳለች ይባላል።
የራሳቸውን ውድቀት ደብቀው በልጆቻቸው ስሕተት ላይ አለንጋ የሚመዙ ወላጆች የራሳቸውን ስህተት በልጆቻቸው ይደግማሉ።

# ምንጭ :- "የተቆለፈበት ቁልፍ" በዶ/ር ምህረት ደበበ


# በማንበባችን_እጥፍ_ብናተርፍ_እንጂ_ከቶ_አንከስርበትም

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
እዉነተኛ ታሪክ
          😷 #የታፍነ #ጩኸት 😰
#ክፍል4⃣



የአይዳ የማነ አሳዛኝ እውነተኛ ታሪክ😢😥
   ተጨንቆል ዶክተር ምክሩን ይቆይልኝ ውጤቱን ብቻ ንገርኝ አልኩት ይገርምሻል ውጤትሽ እንደጠበቅነው አይደለም አለ ማለት ስለው ኤች አይቢ አለብሽ ሲለኝ ደነዘዝኩ በጀርበየ ውሀ ሲወርድ ይታወቀኛል እንዴት እንዴ ይሆናል የደፍኝ አጎቴ ሴቶችን ያንቆሽሻል ይንቃቸዋል ቫይሩሱን ከየት አመጠው አልኩት ዶክተሩ እንደዚህ ስለሚል አጎትሽ ከሌላ ሴት ጋር አይተኛም ለማት ይከብዳል አለ እህትሽ እንድታውቅ ከፍለግሽ ትግባ ሲለኝ ትግባ አልኩት እህቴን ጠራት ገባች የተፍጠርውን ሲነግራት ፍዝዝ ብላ አይናይኔን ታየኛለች ሚስጥሩ ከሶስታችን መውጣት የለበትም አሁን መዳኒቱን መጀመር አለብሽ ሁሌም ከጎንሽ ነኝ በማንኛውም ሳሀት አብሪሽ ነኝ በራስሽ ላይ መጥፎ ውሳኔ እንዳትወስኝ ብሎን ወደቤት ሄድን በጣም አዘንኩ ተከፍው የህይወቴ መመሰቃቀል ምክኔት እናቴ ናት አምርሬ ጠለዋት ምንም ነገር አያስደስተኝም
     እህቴ እኔን ለማስደሰት የምትችለውን ታደርጋለች ለብቻየ ክፍሌ ውስጥ ሳለቅስ አብራኝ ታለቅሳለች እሁድ ቀን የእናቴ ዘመዶች መጡ ሳሎን ተሰብስበው እህቴ ሊያወሩሽ ይፍልጋሉ ብላኝ ሳሎን ሄድኩ ቁጭ በይ ተባልኩ ቁጭ ስል ይቅርታ ሊጠይቁኝ ነው ብየ ስብቅ አያቴ የእናቴ አይነት ጨካኝ ናት አልወዳትም ምን መሰለሽ የተፍጠርው አንዴ ተፍጥሯል ስለዚህ ሌላ ሌገባሽ የሚፍልግ ሰው አለ አግቢ ሀብታም ነው ሚስቱ ሙታበት ብቻውን ነው የሚኖር ድንግል አለመሆንሽን ያውቃል ስለዚ ጥሩ አጋጣሚ ነው አለች
      እናቴ ዛሬም ስለገንዘብ ስለክብር ነው የምታስቢ በቁሜ ገለሽኛል እርሽኝ ብየ በተቀመጡበት ጥያቸው ከግቢ ወጥቸ በአስፓልት ስሄድ በtve የማውቀው ታዋቂ ስለ ኤች አይቪ የሚስተምርውን ሰውየ ስልክ እያወራ አውት ቀርብኩት ስልኩን ሲጨርስ ሰላም አልኩት ምን ልርዳሽ አለኝ ላወራህ እፍልጋለሁ ቤተሰቦቸ ያዩኛል ሌላ ቦታ እንሂድ ስለው እሽ መኪናውስጥ ግቢ አለኝ ገብቸ ቁጭ አልኩ የሆነ ፀጥ ያለ ቦታ መኪነውን አቁሞ ምን እንድርዳሽ ፍልገሽ ነው ሲለኝ በአጎቴ ተደፍሪ አርግዥ ፅንሱ እንደተቋርጠ እና ኤች አይቪ በደሜ ውስጥ መኖሩን ሁሉንም ነገርኩት ህፃን ነሽ ይህን ሁሉ እንዴት ችለሽ አሳለፍሽ ብሎ አዘነልኝ
    እናቴ በቫይርሱ መያዜን አታውቅም ለሌላ ሰው ልትድርኝ ነው እኔ ማግባት አልፍልግም ሰውየውንም በሽታ ላስተላልፍበት አልፍልግም እልኩት እያለቀስኩ እንች ካልፍለግሽ ማንም አያስገድድሽም እኔ አለው ከጎንሽ ነኝ አለኝ ስልኬን ያዥው እንደዋወል ብሎኝ ወደቤት ተመለስኩ ለእህቴ ስነግራት ብዙም አላስደሰታትም ሰውየው ታዋቂ ስለሆነ ከሱጋር ከታየሽ ኤች አይቪ እንዳለብሽ ሁሉም ያውቃል አለች እኔ በዚህ ሳሀት የምፍልገው ችግሬን ሰምቶ መፍትሄ የሚሰጠኝ ሰው ነው ስለሌላ አልጨነቅም አልኮት ለሰውየው በቤት ስልክ ደወልኩለት ስራ ቦታ ነይ አለኝ እየድርጅት ሀላፊ ነው ሄድኩ እንደ አባት ቀርብኩት
    ሰውየው ሚስቱ ሙታለች ሰራተኛ አለችው ከእናትሽ ቤት መውጣት ከፍለግሽ እኔ ቤት ሁነሽ ስራ ድርጅታችን የሰራተኛ እጥርት አለ ስራ ትገቢለሽ አለኝ በጣም ደስ አለኝ እናቴን ልገላገላት ነው እሰይ አልኩ ሻንጣየን እህቴ ደብቃ አወጣችልኝ የዥ ሰውየው ቤት ገበው ለሰውየው ያለኝ ስሜት የአባትነት ስሜት ነው ጧት ሰውየው ከእንቅልፊ ቀስቅሶ ሻወር ውሰጅ አለኝ እኔ ሻወር ስወስድ ሰራተኛዋ ቁርስ አቀራርበች አብርን በላን ስንጨርስ ልብስ ቀይሪ ናዝሪት ልንሄድ ነው ብሎኝ ወጣ ልብሴን ቀይሪ ተከተልኩት ናዝሬት ስንደርስ ከአስፓልት ገባ ብሎ መኪና መንዳት ትችያለሽ አለኝ አወ ከአባቴ ጋር ክፍለ ሀገር ስንዞር አስለምዶኛል አልኩት እሽ ቦታ እንቀያየር ነይ ልጅ ብሎ ሰጠኝ በጣም ደስ አለኝ አሱ መንገዱን እያመላከተኝ ስንጎዝ የሆነ ግቢ ስንደርስ እዚጋ አቁሚው ደርሰናል አለኝ ወርደን በር አንኳኳ ወዲው እሚምር ቆንጅየ ልጅ አድሜው በግምት 23 ይሆናል በሩን ከፍተ
    ልጁን ሳየው የሆነ የማላውቀው ስሜት ተሰምቶኛል ያሬድ አባላለሁ ብሎ እጁን ለሰላምታ ዘርጋልኝ አይዳ ብየ ሰላም አልኩት እንድንገባ በሩን ለቀቀልን ስንገባ የልጁ እናት አባት እና ታናሽ እህቱ ሰላም ብለውን ተቀመጥን ምሳ ቀርበ ብዙ አይነት ምግብ ነበር ስንበላ ይቃለዳሉ ቅልል ይሉ ቤተሰብ ናቸው ስንጨርስ ከአዲስ አበባ የወሰደኝ ሰውየ ሶደሬ እንሄድ ተነሽ አለኝ ያሬድ አብሪችሁ ልሂድ ብሎ አብርን ሄድን ያሬድ ጋር ተቀራርበናል ምግብ ስንበላ አብርን ሁሉን ነገር አብርን ያሬድ አያዳ በጣም ቆንጆ ነሽ ጌታ ላንች ያዳላ ይመስላል አለኝ አንተም ቆንጆ ነህ አልኩት ወድጀሻለሁ ሲለኝ ደነገጥኩ
   ወንዶችን እጠላቸው ነበር ግን ለያሬድ የተለየ ስሜት ተሰምቶኛል ያሬድ በጣም ቀርቦኛል እኔ የምጠጠውን ውሀ አንስቶ ያጠጣል ከዚህ ካለፍ ያሬድ የእኔ ኤች አይቪ የሚተላለፍበት መሰለኝ ሳሳውለት ሁሉንም ልነግርው ይገባል ብየ ወሰንኩ ምሽት ወክ እናርግ ብሎኝ ስንወጣ ሁሉንም ነገርኩት አልደነገጠም አውቀሽ እንድርቅሽ ፍልገሽ ነው ሲለኝ የህክምና ወርቀቱን አሳየውት አለቀሰ አዘነልኝ ትንሽ እኮ ነሽ ላአንች ይህ አይገባም ብሎ ሲያለቅስ እንበውን ሳይ እኔም አለቀስኩ አንበየን በሸሚዙ ጠርገልኝ ቤት ተመለስን
   በጧት ወደ a/a ተጎዝኩ ሰውየው ቤት ሄድኩ ሰውየው እድሜው ትልቅ ነው ልክ እንደአባቴ ጥሩ ሰው ነው አሱ ሶፋ ላይ ይተኛል እኔ ምኝታ ቤት እተኛለሁ በዚሁ ቀጠልን ከእናቴ ቤት ከወጠው ዛሬ 20 ቀን ሞላኝ በመውጣቴ ነፃነት ተሰምቶኛል ሳለቅስ አብራኝ የምታለቅሰው እህቴ ናፍቃኛለኝ አንድ ምሽት ሰውየው ደውሎ ዛሬ እራት ውጭ ነው የምንበላ በዚውም የማወራሽ ጉዳይ አለ ሹፌሩን እልከዋለሁ ተዘጋጅተሽ ጠብቂው ብሎኝ ስልኩን ዘገው ብዙም ሳይቆይ ሹፌሩ መጣ መኪና ውስጥ ገብቸ ሆቴል ደርስን በር ላይ ሰውየውን አገኘውት ውስጥ ገብተን እራት እዞ እየበላን ......ምን መሰለሽ አይዳ እንደምታይኝ ሜስት የለኝም ላገባሽ እፍልጋለሁ ሲለኝ አፌ ውስጥ የነበርው ምግብ ትን አለኝ ውሀ አጠጣኝ ልቤ ሲመለስ እንተ እና እኔ አንተኮ አባቴ ነህ ትልቅ ነህ በዛ ላይ ለእንደዚህ አይነት ነገር ዝግጁ አይደለሁም አልኩት እሱ ግን ምንም የእኔ ስሜት አላስጨነቀውም ምን አይነት እድል ነው ያለኝ አዘንኩ ተነሽ ወደቤት እንሂድ አለኝ እንደምንም ተነስቸ መኪና ውስጥ ገበው ስንሄድ መኪናው ቢገለበጥ እና ብሞት ብየ ተመኘው ቤት ስንደርስ😢😢

#part 5⃣

ይ..........ቀ.................
........ጥ............ላ....................ል

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
👍1
🌐🌐ይህች ኡማ ትታመማለች እንጂ አትሞትም፤ ታንቀላፋለች አንጂ አትተኛም! ተስፋ አትቁረጡ!
ወደ ጌታችሁ ተመልሳቹህ ማንነታችሁን ስታስተካክሉና ወንድሞቻችሁን ስትረዱ ያኔ ልቅናችሁን ትመለከታላችሁ!"

🍃🍃የዚህ ድንቅና ብርቅ ንግግር ባለቤት ማን እንደሆኑ ታውቃላችሁ?
ያ! የኢስላም ልጅ፣ የእውቀት ባለአባት፣ የዲኑ ባለአደራ፦ የ"ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ ቢን ዓብዲል‘ላህ ቢን ባዝ" ረሂመሁ ሏህ ንግግር ነው።
በርግጥም አኚህ ሸይኽ ገናና ዓሊም፣ ዓለምን ጉድ ያስባሉ የኢስላም ሊቅ ናቸው! እስቲ ከመዓት የህይወታቸው ክፍል የወጣትነት እድሜአቸውን በደፈናው ቀንጭቤ ላስታውሳችሁ፦
🍃🍃🍃በህይወታቸው መጀመሪያ ላይ ዓይነ ብሩህ ነበሩ፤ እንደ ሂጅራ አቆጣጠር [በ1316] 16ኛ ዓመታቸው ላይ እያሉ ሁለቱም አይናቸው በህመም ምክንያት እየደከመ መጣ! 20 ዓመት ገደማ ላይ አይናቸው ሙሉ ለሙሉ
ጠፋ! ይህ ከባድ ክስተት ግን ከእወቀት ፍለጋ አላገዳቸውም፤ ከዓላማቸው አላሰናከላቸውም፤ ቆራጥነታቸውንም አላደበዘዘባቸውም።
ማነው ግን ከዚህ ውድ ንብረቱ መጥፋት ቡኃላ የዓላማ ብርሃኑየማትጠፋ? አዎን!
በሂወታቸው መነሻ ላይ ትላልቅ የኢስላም ጠበብቶች አዎንታዊ ተፅዕኖ አሳድረውባቸው፣ ለምጥቀት ጎዳና ከፍተኛ ጉጉት እንዲላበሱ ኮትኩተዋቸው፣ በመልካም ስነምግባርም አንፀዋቸው ነበርና መቼም ቢሆን
ከእውቀት ፍለጋ አልታከቱም።

⭐️⭐️⭐️ጥበበኛው አሏህ ዓይናቸውን ቢነሳቸውም ከዚህ በስተጀርባ ግን ብዙ
ሚስጥራዊ ፋኢዳዎችን ለግሷቸዋል።
ለምሳሌ ያህል፦
▶️ ከማወቅ ባሻገር ትልቅ የመሸምደድና የማስታወስ ብቃትን ተችረዋል።ይነበብላቸዋል በዚያው ቅፅበት ይሸመድዱታል፤ ከ'ኩቱብ አስ-ሲታህ' አንድ
ሀዲስ ሲጠየቁ ብዙጊዜ ነገሩን በቅጡ ለማስቀመጥ አይቸገሩም ነበር! የዘመኑ "ሃፊዝ አል-ሀዲስ" (የሀዲስ ጠባቂ[ሸምዳጅ]) ተብለው
ተጠርተዋል።

▶️ የመልካም ምንዳና የታላቅ አጅር ባለቤትነትን ተጎናፅፈዋል፦ በሀዲስ አል-ቁድሲይ ላይ አላህ እንዲህ ይላል፦"ባሪያዬን በሁለት ውድ(ዓይኖቹ) ፈትኜው ከታገሰ በነርሱ ምትክ ጀነትን
እለግሰዋለሁ።" [ቡኻሪ ዘግበውታል]

▶️ የዚህችን ዓለም ጌጥና ፈተና በመራቅ ልቦናቸው ሙሉ ለሙሉ ወደ አኼራ አዘንብለዋል።

❤️አላህ ይዘንላቸው ለጀነት ካጫቸው መልካም ባሮቹም ያድርጋቸው!አሚን

አንብበን ዝም ማለት አይቻልም ሼር ይደረግ።

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 1⃣7⃣
ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ

እኔ ከተቀመኩበት ስነሳ ፊርዶስ አብራኝ ተነስታ .......
እንባየን ከጉንጬ እየጠረገች ሂኩየ አንቺኮ አሁንም ንፁህ ሰዉ ነሽ ወንጀል ሸይጧን አሳስቶሽ ልሰሪ ትችያለሽ ግን ወደአላህ ተመልሰሽ ማረኝ እያልሽ እያለቀሽ ነዉ፡፡ አላህ መሀሪ ነዉ የወንጀል ጉዳቱ ወንጀል መሆኑን እያወቁ እዛዉ ያለተዉበት በዛዉ ወንጀል ላይ ሁኖ ሳይቶብት መቼ እንደምንሞት ሳናቅ ዛሬ ወይ ነገ እቶብታለሁ እያልን ወይም ሀዲስ ስንሰማ መስጊድ ስንገባ ደአዋ ስናዳምጥ አልቅሰን ወንጀሎኞች ነን ከአሁን ቡሀላ ወደ ወንጀል አልሄድም ብለን እንቶብታለን ግን ወይ ከመስጊድ ስንወጣ ወይ ደአዋዉ ሲያልቅ የቶበትነዉን እንረሳዉና ወደ እዛ ወንጀል እንሄዳለን ይሄ አይነት ደግሞ መቶበት ሳይሆን በራስ ጭንቅላት ላይ ጌም እንደመጨዋት ነዉ...አሁን ብዙ ሰዉ ጋር የሚታየዉ ጥርት ያለ ተዉበት ሳያረጉ  አላህ ጋር መገናኘታቸዉ ነዉ፡፡
........ሂኩየ አንቺ ከእነዚህ ሰዎች ትለያለሽ ወንጀል ሰርተሽ  ወደ አላህ ነዉ እያለቀሽ ያለሽዉ እንጂ ወንጀል አብራችሁ ወደ ሰራሽዉ ሰዉ አይደለም ስንት እህቶቻችን ይህን ወንጀል ሰርተዉ ወንጀል ከሰሩት ሰዉ ጋር ተጣብቀዉ አንተዉ ቅብረኝ እሞታለሁ መርዝ እጠጣለሁ የሚሉ የፈጠራቸዉን ጌታ የረሱ አሉ አይደል፡፡ አንቺ እኮ የምታለቅሽዉ ወደ ፈጠረሽ ጌታ ወደ አላህ እንጂ ወደ ሀይደር አይደለም ስለሆነም አንቺ ከሌሎቹ ሴቶች ልዩ ነሽ፡፡
ጥራት የሚገባዉ አላህ ጌታችን አሏህም እንዲህ ይላል፦ የባሮችን ጉዳይ ተውልኝ እስኪ ከነሱ ወደኔ የተመለሰ (የተፀፀተ) እኔ ወዳጁ ነኝ። እኔኮ እናት ለልጇ ከምታዝነው በላይ ለባሮቼ አዛኝ ነኝ። ከነሱ ወደኔ ተፀፅቶ የተመለሰ «አንተ ተውበት አድራጊ ሆይ
እንኳን ደህና መጣህ ብየ ከርቀት እቀበለዋለሁኝ ።ወንጀል ሰርቶ ከኔ ለሚሸሸው ደግሞ፦ ወደርሱ ቀርቤ ፦ ባርያዬ ወዴት ነው የምትሄደው ከእኔ ውጭ ሌላ ጌታ አገኘህን፤ ከኔ ውጭስ ሌላ
አዛኝ የሆነ ጌታ አገኘህን የምትሸሸኝ »በማለት እጠራዋለሁኝ።
እናንተ ስንዝር ስቀርቡኝ በእርምጃ እቀርባችሇለሁ ....በእርምጃ ስቀርቡኝ እኔ በሩጫ በፍጥነት እቀርባችሆለሁ  ብሏል ሂኩየ ስለሆነም ከአሁን ቡሀላ የአንቺን ለቅሶ ሳይሆን የምፈልገዉ ደስታሽን ነዉ ሂኩየ አንቺ ከአሁን ቡሀላ የረከሽ ወንጀለኛ አይደለሽም ልታለቅሺ ሳይሆን የባሰ አለ ብለሽ ልታመሰግኚ ነዉ የሚገባዉ  አንቺ ልታለቅሺ አይገባም አላህ መሀሪ አዛኝ የሆነ ጌታ ነዉ ብላ አንገቴ ስር ጥምጥም አለችብኝ፡፡ ከዛም ወደ ቤቴ ልሂድ ብላኝ ሸኝቻት ተመለስኩኝ፡፡

   ዉይ ለፊርዶስ ከነገርኳት ቡሀላ ይህ ሚስጥር ተሸክሜዉ እንዳታሳርፊ የተባልኩ ይመስል ቅልል አለኝ የሆነ የደስታ ስሜት ተሰማኝ ልተኛ ስል ፊርዶስ ደዉላልኝ በቃ በደስታ አወረሇት ..
.....እሷም ሂኩ ምን ተገኘ ስትለኝ
.ምንም አልተገኘ ግን ቅልል ብሎኛል የደስታ ስሜት ተሰማኝ አልኳት ብዙ ነገሮችን አወራን ስንጨርስ በስልክ ተሰነባብተን ወደ መኝታየ አመራሁ
ለመጀመሪያ ጊዜ ሳልጨናነቅ ደስተኛ ሁኜ አደርኩ፡፡ የመጀመሪያ የደስታ ሂወት የጀመርኩ ይመስለኛል አልሀምዱሊላህ ተገላገልኩ ዙበይር ከአሁን ቡሀላ ተስፋ ይቆርጣል ፊርዶስ እዉነቱን ትነግረዋለች ወደ እኔ በጭራሽ አይደርስም ብየ እራሴን አሳመንኩት፡፡
    ሳስበዉ የቸገረን ማንኛዉም ሰዉ አንድ የልብ ጓደኛ ያስፈልገዋል በደስታዉም በሀዘኑም ከጎኑ የሚሆን ሀሳብ ሲያስብ የማያማክረዉ በሀሳቡ ገንቢ አስተያየት መስጠት የሚችለዉ  ሰዉ ነዉ ለሰዉ መድሀኒት ነዉ ፡፡ ተማክረዉ የፈሱት ፈስ አይሸትም አይደል የሚባለዉ የልብ ጓደኛ ወሳኝ ነዉ፡፡ ጓደኛ ማለት በክፉም በደስታም በሀዘንም አብሮ መግባባት ሲቻል ነዉ፡፡ መጠንቀቅ ያለብን ሴቶች ማንኛዉም ነገር እስከ ዚና መስራት ወንጀል ድረስ የሴት ጓደኛ ተፅእኖ ግፊት ነዉ ጥሩ ሴቶች እየተበላሹ ያሉት፡፡ 
       የአሁን ጓደኝነት ስታማክረዉ ወይ ሚስጥርህን ለሌላ ያሳልፈዋል ወይም በቀኝ ጆሮዉ አዳምጦ በግራ ጆሮዉ ያፈሰዋል፡፡ ጫት ማን አስጀመረህ ጓደኛየ..የቱርክ ልብስ ማን ልበሺ አለሽ ጓደኛየ....የያሽዉ የወንድ ጓደኛ ማን አስተዋወቀሽ ጓደኛየ...ሶላት አልሰገድሽም የት ነበርሽ?? ጓደኛየ ቤት....ሜካፕ ሊፒስቲክ ኮስሞቲክስ ማን እንድትቀቢ አስለመደሽ ጓደኛየ.......ዚና እንድሰሪ ማን አስተዋወቀሽ ጓደኛየ...ነዉ መልሳችን አሁን የያሽዉ የሴት ጓደኞችሽ ከስንት አንድ ካልሆነ ከነዚህ ዉጭ ያሉት ብዙዎቹ ሴቶች የሚሸወዱት የሚበላሹት በሚይዙት የሴት ጓደኛ ስበብ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡
     ሴትን ለሴት እሾህን ለሾህ አይደል የሚባለዉ በጓደኛ አመራረጥ ቢያንስ እንደፊርዶስ አይነት ጓደኛ መያዝ መቻል አለብን፡፡
አሁን ላይ ትዉልዱ ከቤተሰብ ቁጥጥር ዉጭ ሁነናል ጊዜዉ የተራቀቀ ነዉ በፊት ቤተሰብ ይቆጣጠረን ነበር አሁን ግን በስልክ ሁኗል ስራዉ በስልክ ያልቃል ወንጀል ለመፈፀም አንቺ እሱ እና ጌታሽ ብቻ የሚያቃቸዉ ብዙ የዚና መስሪያ ቦታዎች ምን ይሰራ ማን ይግባ ማን ይዉጣ የማይታይበት የወንጀል መስሪያ ቦታዎች በሁላችንም የመኖሪያ ሰፈሮች ቦታዎች እናገኛለን ፡፡  የሂክማ ነገር አላለቀም
                  #እስኪ #ፈገግ #እንበል
 .....አንዷ ሁሌ ላይብረሪ እያለች ትሄዳለች አቧቱ ሲጠይቃት ሁሌ ላይብረሪ እያለች ስታስቸግር ..አንድ ቀን አባቷ ማታ ስትመጣ በብትር ይገርፋታል የት ነዉ የምትሄጅዉ ሲሏት ላይብረሪ ስትል...አባቷ አልተማሩም ነበር ላይም ብረሪ ታችም ብረሪ የሄድሽበትን ብቻ ተናገሪ እንዳሉት አባት ትክክለኛ መሆን መቻል አለብን፡፡
 መቼም ቀን በቀን ይፈራረቃል አንድ ቀን ባሳለፍን ቁጥር ወደ ሽምግልና እየሄድን እና ወደ ሞት እየተጠጋን መሆኑን እረስተናል፡፡ ነጋ ፊርዶስ ጋር ተገናኘን ከበፊቱ በበለጠ ፍካቷ እየጨመረ ለኔ ያላት አመለካከት እየጨመረ ሄደ ፡፡ በቃ ምን ልበላችሁ እስከዛሬ በመደበቄ እኔ ስጨናነቅ እንደኖሩኩ አወኩኝ ቢሆንም አልሀምዱሊላህ አሁንም እፎይ ማለቱ በጣም ደስታ ፈጠረልኝ፡፡
ፊርዶስ እኛ ቤት እየመጣች አንድ ላይ እንሆናለን ፡፡ አንዴ እናቴ ለፊርዶስ ምንድን ነዉ አታገቡም እንዴ ፊርዱ ሴት ልጅ ትዳር የሚያምረዉ በልጅነት ነዉ እኔ ያገባሁት በ19 አመቴ ነዉ እኮ፡፡ ከሁለት አንዳችሁ አግቡ እና በሰርጋችሁ እንልፋ አለችኝ፡፡
.....ፊርዱም ኢንሻ አላህ አይቀርም እኔ የማመቻቸዉ ስላለ ነዉ እንጂ በቤተሰብ የመጣ አለ ታጭቻለሁ  ሆነም ቀረ የሂክማ ይቀድማል ተዘጋጂ አለች
.....እናቴም ማሻ አላህ ብያለሁ ለድግሱ ልዘጋጃ ብላ ቀለድ አረገች፡፡ telegram ...Facebook ...ከገባሁ በጣም ቆየሁ ቻት የሚባል አቁሚያለሁ፡፡ ከሰለሙ ስልም ነዉ ከከፈሩ እንክፍርር ነዉ ይባል የለ፡፡ እኔም አላህ ተዉበቴን እንዲቀበለኝ ወንጀል ወደሰራሁበት ቦታ መመለስ ማየት ማስታወስ ጥሩ የወደፊት ጥሩ ህልም አያሳካም፡፡ ማታ ኢሻን ሰግጄ ቁርአኔን እየቀራሁ .....የማላቀዉ ቁጥር ተደወለብኝ እኔም ሳላነሳዉ ቀረሁ፡፡ መልሶ ተደወለ ሁለተኛ መቼም በዚህ ሰአት ሰዉ ያለምክንያት ሁለቴ አይደዉልም ብየ አሰብኩ፡፡ ከዛም ስልኩን አነሳሁት የወንድ ድምፅ ነዉ፡፡ ድምፁም የማቀዉ ድምፅ ነዉ፡፡ ስልኩን እንደያዝኩት ደንግጬ  ቆምኩ...የደወለልኝ.....

#Part 1⃣8⃣
ይ........ቀ.......ጥ.......ላ......ል
👇
@IslamisUniverstiy_public_group
............
ታምር በሞላባት በዚች ወሬኛ አለም
ዘረኛ እንደ መሆን የሚያሳፍር የለም
...........
በዚች ትንሽ ሜዳ በዚች ግብዝ አለም
የጊዜ ነው እንጂ..የሰው ጀግና የለም
..
በዚች ትንሽ ሜዳ በዚች መናኛ አለም
ያልተቀበረ እንጂ ያልሞተ ሰው የለም
......
በዚች ከንቱ ምድር ሳለሁ በዚች አለም
☞እንደ ባዶ አዕምሮ ከባድ ነገር የለም
...........
በዚች ከንቱ ምድር በዚች ቧልተኛ አለም
ውሸት እውነት ንጂ እውነት ውሸት የለም
...............
..
የእናቱ ልጅ አብዱል ከሪም
.
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
.. ISLAMIC SCHOOL CHANNEL.. 💠
🏷    @Islam_and_Science 🔗 JOIN US 
⭐️የራስህን ህይወት በፍፁም ከማንም ጋር አታወዳድር ።
ምክንያቱም የምታገኘው ውጤት ከዛ ሰው የተሻልክ ከሆነ ኩራት ሲሆን....
ከዛ ሰው የምታንስ ከሆነ ደግሞ ቅናት ነው ሚሆነው ሁለቱም
ውጤቶች መጥፎ ናቸው...

✔️ሲለዚህ ወዳጄ ራስህን ከራስህ ጋር ብቻ ነው ማወዳደር ያለብህ
እመነኝ ያኔ ሰላምህን ታገኛለህ😉

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 1⃣8⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal



      ስልኩን አነሳሁት የወንድ ድምፅ ነዉ፡፡ ድምፁም የማቀዉ ድምፅ ነዉ፡፡ ስልኩን እንደያዝኩት ደንግጬ  ቆምኩ...የደወለልኝ. ዙበይር ነበር
አሰላሙ አለይኩም
....እኔም ወአለይኩም ሰላም አልኩት
...እንዴትነሽ እንዴትነህ ከተባባልን ቡሀላ በሰላም ነዉ መደወሉ?? አልኩት
...መደወል አይቻልም እንዴ ስልክሽን ከእህቴ ፊርዶስ ነዉ የተቀበልኩት አንዳንድ ወሬ አዉርተን ብዙም በስልክ በወሬ ሳንቆይ ቻዉ ተባብለን ስልኩን ዘጋሁት፡፡
ዙበይር በሂክማ ፍቅር ወድቋል፡፡

#ናፍቆት .
ናፍቀሽኛል ብዬ ቃላት እያወጣሁ
ናፍቆቴን ለመግለፅ ለናፍቆት ቃል አጣሁ
ገና ናፍቀሽኛል ብዬ ሳልጀምረው
ተሰማኝ ናፍቆትሽ ውስጤን ሲያሸብረው
እኔ የፍሬ ናፍቆት ፣ አንቺ የጥበብ ሸማ
ሲመታ አዳምጪው ያን የልቤ ዜማ
በናፍቆት አለንጋ
ደምቶ የማይረጋ
ብዙ ቅኔ ያለው ናፍቆት ሞልቶት ልቤን
ናፈቅሽኝ እላለሁ ላይገልፀው የውስጤን
የመናፈቄን ጥግ የጉጉቴን መጠን
የመውደዴን አቅም የናፍቆት ወሰን
ድንበሩን ለማየት መግለጥ ያሻው ዶሴ
ከምን ደርሶ እንደሆን ይለካ እስትንፋሴ ።

      ዙበይር እንዴት ሊደዉልልኝ ቻለ ፊርዶስ ሂወቴን ከላይ እስከታች ነግሪያት እንዴት ስልኬን ሰጠችዉ እያልኩ ተወዘገብኩ፡፡ የማይነጋ የለም ነጋ ፊርዶስ ጋር ተገናኘን ከዛ ስለማታዉ ጉዳይ ዙበይር ደዉሎልኛል ብየ አጫወትኳት እንዴት ለወንድምሽ የኔ ቁጥር ትሰጫለሽ ሂወቴን አጫዉቸሽ ነግሬሽ ወንድምሽ እኔን እንዲረሳ ማረግ ሲገባሽ ..ይባስ ብለሽ ስልክ ቁጥሬን ሰጠሽዉ ፊርዱ ጥሩ መስሎ አይታየኝም አልኳት፡፡
  ....ፊርዱም በመቆጣት ከአሁን ቡሀላ ስለ አለፈዉ ሂወትሽ ነግረሽኛል ተረድቸሻለሁ ጨዋና እና ሬድዮ ወሬ አይደጋግምም አይደል የሚባለዉ ..ወደ አላህ ተመልሰሻል ያለፈዉ አልፏል አሁን ያለነዉ ዛሬ ላይ ነን፡፡ ትናንት ያየዉን ህልም ሰዉ ዛሬ መድገም አይችልም  ሂኩ ከአሁን ቡሀላ ያለፈ ሂወት ብታነሽብኝ የምወድሽን ያህል እጠላሻለሁ፡፡ አንቺ ለኔም ለወንድሜም ለማንም ሰዉ ወንጀለኛ መጥፎ ሰዉ አይደለሽም እንደዉም ጠንካራ ጎበዝ ነሽ ፡፡ ሲደዉልልሽ ፊት አትንሽዉ ዙበይር ወንድሜ አንቺም እንደ እህቴም እንደ ጓደኛየም የማይሽ ነሽ ሁለታችሁም እንድትጎዱ አልፈልግም አለችኝ፡፡
.....እኔም እሺ ከአሁን ቡሀላ ያለፈ ሂወቴን ላነሳ ብየ ፊርዱ አንገት ስር ጥምጥም ብየ አለቀስኩኝ፡፡

ዙበይር ጋር በስልክ ሲደዉልልኝ ማዉራት ጀመረን ዙበይር እንደሚወደኝ አቃለሁ እኔም ትንሽ ለዙበይር ከሌሎቹ ወንዶች ለየት ያለ አመለካከት አለኝ ግን ያንን ጥያቄ ቢጠይቀኝ ምን እንደምመልስ አላቅም ግን ፊረዱ ያለፈዉ አልፏል አሁን ወደፊት እሰቢ ብላ አስጠንቅቃኛለች፡፡ ዙበይር እንደሀይደር ወደድኩሽ አበድኩልሽ ሳይሆን የጨዋ ወንድ አነጋገር ነበር የምናወራዉ፡፡እያደር ግን ስልክ አዉርተን ስንጨርስ ሂኩ እንደምወድሸ እንዳረሺ ማለት ጀምሯል፡፡ እኔም አረሳም ብየ እጥር ያለ መልስ እመልስለታለሁ፡፡
,
አንድ ቀን ፊርዶስ እሁድ ምሳ እኛ ቤት ጋብዠሻለሁ አንቺ እናትሽን አስተዋወቀሽኛል እናትሽ እኔን,, የምታየኝ እኔደ ልጇ ነዉ እኔ እኮ አላስተዋወኩሽም ብላኝ ስለሆነም እሁድ ምሳ ጋብዠሻለሁ ቤታችንን ስለማታቂዉ አብረን እንሄዳለን ተባባልን፡፡ እኔም እሺ ከማለት ዉጭ ምንም አላልኩም፡፡
   እሁድ ደረሰ ፊርዶስ እኛ ቤት መጥታ አብረን ወደ እነሱ ቤት ወደ  ጎሮ ሰፈር ሔድን ፡፡ ቤታቸዉ ደረስን ቤታቸዉ በጣም ያምራል አባቷ ነጋዴ ነዉ፡፡ ከዟም እናቷ ወይዘሮ ዚነትን አስተዋወቀችኝ ተነስተዉ ጉንጬን ሳሙኝ ሂክማ እኔ ልጄን ፊርዶስን በአሳታዋሽነቷ በጣም እወደታለሁ ደግሞ ፊርዶስ አንቺን ትወድሻለች ልጄ የወደደችዉን እኔም እወዳለሁ በአካል ዛሬ ስላወኩሽ ደስ ብሎኛል ደግሞም ቆንጅየ ነሽ ማሻ አላህ ብያለሁ አሉኝ ወይዘሮ ዚነት፡፡ እኔም አመሰግናለሁ ማዘር ብየ ግንባሬን ሳሙኝ፡፡ ምሳዉ በጣም ለየት ያለ ዝግጅት ነበር ምሳዉ ቀረበ ከዉጭ አሰላሙ አይኩም የሚል ድምፅ ሰማሁ ፡፡ ድምፁን አቀዋለሁ የዙበይር ነበር ድምፅ ነዉ ወደ ቤት አሰላሙ አለይኩም ብሎ ገባ ወአለይኩም ሰላም ምሳ ላይ ደርሰሀል ና ምሳ ብላ አሉት እናቱ
......እሱም እሺ ብሎ ታጥቦ እኛ ጋር ቀረበ ...እናቱም መቼ ይሆን አንተ ጎጆ መስርተህ ምሳ የምጠራን ዙበይር አሉት
.....ዙበይርም እማየ ዱአ አድርጊ መስመር ላይ ነኝ አላህ ያሳካልህ ብለሽ አለ፡፡
ፊርዶስም ከአፉ ቀበል አድርጋ እንዴ ትገርማለህ እኔ የማላቃት ያላስተዋወከኝ ከእህትህ ደብቀህ የማጠሀት ሚስትማ እኔ አልስማማም አለች ፊርዱ
....ዙበይርም ከአንቺማ ምንም አይደበቅ ፊርዱ እኔ እኮ ታናሽ እህቴም ብትሆኝ አከብርሻለሁ አንቺ የወደድሽዉን ነዉ የምወደዉ አላት ለፊርዶስ፡፡
በቃ ወሬዉ እናት ዙበይር ፊርዶስ እየተቀባበሉ ስለትዳር ነዉ የሚያወሩት እኔም የሚሉትን ሳዳምጥ ነገሮች ሁሉ ወደ እኔ ያመላከቱ መሰለኝ፡፡ እናቲቱ ማብቂያ ላይ ያሉት ንግግር ገረሞኛል መቼም ከፊርዶስ ጓደኛ ከሂክማ የበለጠ ቆንጆ አዲስ አበባ ብፈልግ አታገኝም ብለዉ ሁሉም ሲስቁ ነገሮች ሁሉ እኔን እንደሆነ ጠረጠርኩ፡፡ዙበይር እና ፊርዶስ  እኔ እና ዙበይር ለወደፊት አብረን ለመኖር መስመር እንደጀመርን እናታቸዉ ቅድምያ ነግረዋቸዋል ማለት ነዉ ?? ይሄ ነገር ባይሳካስ?? ለእናታቸዉ ተናግረዉ ይሆን እንዴ ???እያልኩ እዛዉ እነሱ መሀል ቁጥ ብየ በሀሳብ አለም ዉስጥ ተጓዝኩኝ....

#part 1⃣9⃣

ይ.............ቀ...............
.........ጥ...............ላ.......................ል

4 another channal👇
             @Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
   
  T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
በሳውዲ አረብያ አንድ ግለሰብ ለ አይነ ስውር ወንድሙ ከመኖሪያ ቤቱ አስከ መስጊድ ያለውን መተላለፊያ መንገድ ገንብቶለታል ።
#ሱብሀንአላህ

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
✔️አንዳድንድ እህቶች ሂጃብ አስተካክላችሁ ልበሱ ሲባሉ ዋናው ኢማን በልብ ነው ይላሉ። እህቴ ሆይ ኢማን በልብሽማ ቢኖር አካልሽ ይህን ለመተግበር አይሰንፍም ነበር''

❤️ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ካደረገው ዳእዋ

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
ሜጀር ጀኔራል ፋጡማ ህሚንገር ትባላለች፡፡ አስራሁለተኛ የአሜሪካ የአየር ሀይል አዛዥ ናት፡፡ የመጀመሪያ ሴት ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያ ሙስሊም ሴት የተዋጊ ጀት አብራሪ መሆኗ ብዙዎችን አስደንቋል፡፡
የአሜሪካ አይነኬ ቦታዎች በሙስሊሞች እየፈራረሱ ነው አላህ ለእኛ ሀይል እና እውቀት ይስጠን፡፡
يُرِيدُونَ أَن يُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَيَأْبَى اللَّهُ إِلَّا أَن يُتِمَّ نُورَهُ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ
የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም፡፡ቁርአን 9:32

JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
          `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science


☑️ ሼር በማድረግ ኢስላማዊ ግዴታዎን ይወጡ
#ጀነት

በሰማይ ቀበሌ ያለችዋ ጀነት
አላህ ለሚፈሩት ለሙተቆች ናት
ሰብረኞች እጂ ማንም አይገባት
መታደል ነው መግባት የፀጋ አገር ጀነት
ይህንን ለማግኘት ዛሬ ነው መበርታት

የሳሊሆች ሰፈር የሙእሚኖች መንደር
በሷ ለገባማ የለውም መቸገር
ይህቺን ለማግኘት በጣአው እጠክር
ለሚመጣው አዛ በርትተን እሶብር

ኧረ ተይኝ ነፍሴ ይብቃ ክፋትሺ
ሀላሉ እያለ ሀራም መውደድሺ
ለፀፀት ለሀዘን ትዳረጊያለሺ
እሳት ውስጥ በመግባት ትቃጠያለሺ
ስለዚ ነፍሴ ሆይ ዛሬ ላይ ታገሺ
በአላህ ትእዛዝ ላይ ቀጥ ካልሽ ከታዘዝሽ
ጀነት ከሚገቡት አንዷ ትሆኛለሽ

ሸርጥ አላት መስፈርት ጀነት ለመግባት
ማመን ነው በአንድ አላህ ያለ ማጋራት
ባግባቡ ፈፅመው ፆም ዘካ ሶላት
ከቻልክም ዘይረው ሐጁሏሂል በይት
ረሱልን ውደድ ሱናቸው ተግብረው
ይህ ካደረክ ጀነቱ ላተ ነው
ነብዩ ውደጂ ሱናቸው ተግብሪ
ነገ በአኼራ አንቺም እንዳታፍሪ

ቁም ነገር የለውም መጥቆርና መቅላት
ሸርጡ አይሆኑትም ጀነትን ለመግባት
ዋናው ቁም ነገሩ አላህን መፍራት

(ከአብድል ቃድር ሻፊ ነፍሴ ተመለሺ ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ)

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 1⃣9⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal

     ከፊርዶስ ጓደኛ ከሂክማ የበለጠ ቆንጆ አዲስ አበባ ብፈልግ አታገኝም ብለዉ ሁሉም ሲስቁ ነገሮች ሁሉ እኔን እንደሆነ ጠረጠርኩ፡፡ ከዛም ምሳ በልተን ጨረስን ግን ሌሎቹን ሁለቱን የፊርዶስ ወንድሞች የሉም ይሄ program ለኔ እና ለዙበይር በዛዉም እናቲቱ እኔን እንዲያቁኝ የተዘጋጀ ዝግጅት መሰለኝ፡፡
   እስከ አሱር ድረስ እነሱ ቤት ፊርዶስ ጋር እና እናቷ ጋር እየተጨዋወትን ቆየን አሱር እነሱ ቤት ሰግደን ወደ ቤት ልሂድ ለነበረኝ የምሳ ግብዣ አላህ ይስጥልኝ ብየ ከቤት ልወጣ ስል  የዙበይር እና ወይዘሮ ዚነት ልጄ እስኪ አንድ ጊዜ ከመኝታ ክፍል እቃ ይዤ ልምጣ ጠብቂኝ ብለዉ ወደ መኝታ ክፍል ገቡ
እኔም እሺ አልኩኝ
.....ማዘር መጡ የሚያምር አበያ ሰጡኝ ልጄ ልበሽዉ የልጄ ፊርዶስ ጓደኛ አይደለሽ በትንሹም ቢሆን ማስታወሻ ይሁን ይሄን አበያ  ባየሽ ቁጥር እኔን እያስታወሽ ዱአ እንድታረጊኝ እና መጥተሽ እንድዘይሪኝ እፈልጋለሁ እኔ ከአንቺ ዝምድናዉን እፈልጋለሁ ብለዉ ግንባሬን ሳሙኝ፡፡
እኔም ማዘር አመሰግናለሁ ብየ ተቃቅፈን ተለያየን ፡፡ ፊርዶስ እና ዙበይር እኔን ሊሸኙ አብረዉ ከእነሱ ቤት ወጥተን ጉዟችንን ጀመርን ...እየሄድን ፊርዶስ አንድ የምታቃት ልጅ አግኝታ አሰላሙ አለይኩም ተባብለዉ ተዘያየሩ እዛዉ ቁመዉ ማዉራት ጀመሩ፡፡
 ፊርዱ እደርስባችሇለሁ እየሄዴችሁ ጠብቁኝ ከምቆሙ አለችን ፡፡ እኔና ዙበይር ብቻ ሁነን ወደ ፊት ጉዟችንን ቀጠልን ከአሁን አሁን ፊርዱ ትመጣለች ብየ ብዞር እዛዉ ቁማለች እርምጃ በተራመድን ቁጥር ፊርዶስን እየራቅናት መጣን እኔ እና ዙበይር ብቻችንን ሆንን ፡፡ ዙበይርን ወድጀዋለሁ ግን የበፊት ማንነቴ ያስፈራኛል ....እሱም እንደሚወደኝ አዉቃለሁ ግን ዉደታ ሙሉ የሚሆነዉ አብሮ በትዳር መዝለቅ ሲቻል ነዉ፡፡ ብቻ እኔም ቀጥ ስል አይን ለአይን እንጋጫለን ሁለታችንም አንገታችንን እንደፋለን፡፡

ዙበይር የዝምታዉን ድልድይ ለመስበር እየታገለ ነዉ........ሂክማ ተጨዋቺ ወሬ አምጪ ፊርዶስ እንደሆነች ወሬዋን ይዛለች እርቀናታል የምመጣ አይመስልም  አለኝ፡፡
......እኔም እሺ እጫወታለሁ እልኩት
.........ምሳ እንዴት ነበር አለኝ
.............አሪፍ ነበር ጀዛከሏህ አለኩት
አንድ አንድ እያልን በወሬ ተግባባን፡፡ ግን በመጨረሻ ከበድ ያለ ጥያቄ ጠየቀኝ፡፡ ሂክማ ግን ሰለፍቅር ምን ታስቢያለሸ አለኝ .....
....ይህን ንግግሩን ስሰማ በጣም ደነገጥኩ የምመልሰዉ ግራ ገባኝ፡፡ ዝም አልኩኝ
.......ሂክማ ምነዉ የማይጠየቅ ጥያቄ ጠየኩሽ እንዴ አለኝ
...... አኔም ካላስቸገርኩህ የጠየከኝ መጀመሪያ አንተ ነህ ግን ይህን ጥያቄ አንተ መልስልኝ ስለፍቅር ምን ታስባለህ መልስልኝ እና እኔም መልስ እሰጥለሁ አልኩት፡፡
እሱም ፍቅር ሳፈልጊዉ ጊዜ ሰአት ቦታ ሳይል የሚይዝ ነዉ ግን ችግሩ ያፈቀረዉ ሰዉ እንዴት እንደሚወድ ለተፈቃሪዉ ግልፅ አለመሆኑ ነዉ እኔ የወደድኩትን ያፈቀርኩትን የመጀመሪያየ የሆነችዉን ልጅ   እስከ ሂወት አጋሬ የልጆቼ እናት ብትሆን ደስ ይለኛል ....አንቺሰ ምን ታስቢያለሽ???? አለኝ
  ሀይደር ጋር ያሳለፍኩት ያጠባሳ ጊዜ ትዝ አለኝ፡፡ ........ዙበይር እኔ ለፍቅር ወንድን የምቀበልበት ልቤ ዉስጥ የማስቀምጥበት ቦታ በጣም ተጎድቷል አልኩት፡፡ አንተንም የቀረብኩህ የፊርዶስ ወንድም ስለሆንክ ነዉ አንተ ለኔ የጓደኛየ ወንድም ነህ ከዚህ ዉጭ እኔ ብዙ ያለፉ ሂወቶች የተበላሹ ማንነቶች አሉኝ እኔ ለእንደ አንተ አይነት ጥሩ ወንዶች አልገባም አልኩት፡፡ ምንም አማራጭ የለኝም እየፈለኩት የማጣት አይነት ስሜት ይሰማኛል፡፡
........ዙበይርም እኔ እስከዛሬ ደበኩት ግን መደበቄ ለኔ እንቅልፍ ነሳኝ ዛሬ ለአንቺ ልነግርሽ ዝግጁ ነኝ ሂክማ ይህን ስነግርሽ ከኔ ላትርቂ ላትሸሺ ቃል ግቢልኝ፡፡ ሂክማ እወድሻለሁ አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም እባክሽ ተረጂኝ እና ቀጥታ ወደ ትዳር እንግባ አግብቼሽ የወደፊት ሚስቴ እንድትሆኝ እፈልጋለሁ ከአንቺ  ልጆች መዉለድ እፈልጋለሁ፡፡የዛሬዉ ምሳ እናቴ የወደፊት እጮኛህን አስተዋዉቀኝ እያለች ስረብሸኝ አንቺን ስለመረጥኩ ነዉ ምሳዉ እናቴ ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ ነዉ ......አለኝ አንገቱን ደፍቶ

#እንዲህ #አድርጎኛል
ተፃፈ  በ ዘ አዶኒ

ፍቅርሽ እያቃዠ እንቅልፍ ያሳጣኛል
ከእህል ከውሃ ጋር ዘወትር ያጣላኛል
ሆዴን ባርባር እያለ ደርሶ ይጨንቀኛል
በዓለም ለብቻዬ የተተውኩ ይመስለኛል

በውድቅት ሰዓት ከቤት እወጣለው
ፍቅርሽን ፍለጋ ሌሊቱን እሄዳለው
ተጉዤ ሲደክመኝ ኮከብ እቆጥራለው
ለጨረቃ ሳልፈራ የሆዴን እነግራታለው
ጉልበቴን አዝሎ አቅም ነስቶኛል
ቅስሜን ሰባብሮ ወኔ አሳጥቶኛል
የፍቅር ቅጣት ህመሙ መሪር ነው
መጨረሻው ካማረ ሁሉም ለበጎ ነው

ግና እፈራለው ብኩን ሆኜ እንዳልቀር
አይሰምርም ይባላል የአንድ ወገን ፍቅር
ብቻ አለው ዛሬም እኔ እንዳለሁኝ
ህመሜን አይቶ ማንም ሳይጠይቀኝ
የሆንኩትን ሁሉ መግለፅ ቸግሮኛል
ፍቅርሽ በጥቂቱ እንዲህ አድርጎኛል፡፡

እኔም ዝም ብየ አንገቴን ደፍቼ የሚለኝን እየሰማሁ ነዉ ዙበይር መልኩ በእድሜም እኔን ቢበልጠኝ ሶስት አመት ነዉ ከዚህ በላይ አይበልጠኝም በጣም አይናፋር ሲሆን ስራዉም መርካቶ ላይ ደርዘን ልብስ ማከፋፈል ነበር፡፡ ግን እኔ ዙበይርን ማግባት አልችልም ለምን ቢጠይቀኝ መልስ የለኝም፡፡ እኔም አንገቴን እንደ ደፋሁ እንባየ ይወርድ ጀመር ....ዙበይርም ደነገጠ
እንዴ በነገርኩሽ ነገር አስከፋሁሽ እንዴ እኔም ተቸግሬ ነዉ ሂክማ እንድታለቅሺ ሳይሆን እንድትረጂኝ ነዉ ፡፡
እኔም ዙበይር ሌላ ፈልግ እኔ ለትዳር አልሆንህም .....እኔ እና አንተ አንድ ላይ መኖር አንችልም ብየ ከእሱ በተቻለኝ አቀም እየሮጥኩ ሄድኩኝ
ዙበይርም ሂክማ እያለ ሲከተለኝ፡፡ ዘወር ብየ እንዳትከተለኝ ብየ ተቆጣሁት..ዙበይርም ባለበት እንባዉ እየወረደ ቁሞ ቀረ.....

#part 2⃣0⃣


ይ.............ቀ...............
.........ጥ...............ላ.......................ል

4 another channal👇
             @Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
   
  T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
🎖ISLAMIC SCHOOL CHNNAL POST🎖

🌸 #ትክክለኛ #አማኝ #ሴት ልጅ ለትዳር መስፈርቷ ዲን ነዉ ዲን የሌለዉ ሀብታም ወንድ አትፈልግም እሷ የምትፈልገዉ ዲነኛ የእዉነት የሚወዳት ሁል ግዜ ከጎኗ የሚሆንን ወንድ ነዉ!
ስለዚህ ወንዶች እንድትመረጡ ዲነኛ ሁኑ
⭐️⭐️⭐️ደግሞ ከማግባትህ በፊት ከራስህ ጋር ተግባባ ለምን ብትል ትዳር ቀልድ አይደለችም ዛሬ ገብተህ ነጌ የምትወጣበት አይደለም ሴቶችንም ያካትታል ከራስሽ ጋር ሳትግባቢ እንዳታገቢ…ምክንኛቶች

💐የትዳርን ትርጉም ከመረዳትሽና ከመገንዘብሽ በፊይት በዲናችን ትዳር የተደነገገበትን አላማ ምንም ሳይገባሽ እንዳታገቢ

💐በትዳር ላይ ያለብሽን ግዴታና የባልን ቦታና ደረጃ ከማወቅሽ በፊይት እንዳታገቢ

💐ባልሽን እንዴት ማክበርና መንከባከብ እንዳለብሽ እንዲሆም ልጆችሽን እንዴት ማነፅ እንዳለብሽ ሳትረጂ እንዳታገቢ

💐በየተረትተረቱ የሚወራውን የፍቅር ታሪክ {በሙሰልሰል}የተመለከትሽውን አፍቃሪ የሚመሰለውን የውሸት ሰው ባልሽ የሚሆንልሽ መስሎሽ የምትጠብቂ ከሆነ
【احسن لك لا تتزوجي】

💐እውነተኛው ትዳር ደስታም ችግርም እንዳለውና መሳቅም፣ማልቀስም እንዳለበት ካለወቅሽ እንዳታገቢ

💐ትዳርን ለሙከራ ካሳበሺውና ባልሽ አንቺን የመቆጣጠር ሙሉ መብት እንዳለው በይ እንደውም ስትገቢ፣ ስትወጪ የግድ ፍቃድ መጠየቅ እንዳለብሽ ካልተዋጠልሽ እንዳታገቢ
ይህ ካወቅቅሽ ግን አህለንወ ሰህለን የባልሽ ሀቅ መጠበቅ ትችያለሽ ማለት ነው ወንዱም ልክ እንደዛዉ የሚስትህ ሀቅ ካወክ አህለን ወሰህለን ዳይ ወደ ትዳር ተብሎዋቹሀል

😊በላጤነት ዘመን ወጣ እንበል ኢሻላህ እናም የላገባቹሁ አላህ ሷሊህ ሷሊህ ዘወጀት እና ዘወጅ ይወፍቃቹሁ ያገባቹም አላህ ሷሊህ ትዳር ያርግላቹሁ አሚን ያረብ !!

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የውጭ ፀሀፊወች ሀገራችንን ከውጭ ሆነው ክርስትያን ነገሥታቱን ብቻ በማየት፤ ከውስጥ ያሉትም ደግሞ ከራሳቸው መነጠር ብቻ በመነሳት በርካታ ሙስሊም ማህበረሰብ መኖሩን በመዘንጋት በጣፏቸው ማስታወሻወች ይኼን የእስልምና ተከታይ የዓድዋ ዘመቻ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር በዓድዋ ላይ ያደረገውን ተጋድሎ ለክርስትያን አገር የተከፈለ መስዋትነት በማለት ድሉን ለማጥበብ ይሞክራሉ።👇አድዋ የሙስሊሞች የሰሩት ስራ
ዓድዋና #ሙስሊሞቹ_የራስ_ወሌ ብጡል አዝማቾች
※※※※※※※※※※※※※※※※※
በ Brook Abegaz Aba Bona
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅
ዓድዋ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ተሳትፎ ነው፤ በዓድዋ ጦርነት ከበርካታ ነገዶች የተውጣጡ፣ የእስልምና፣ የክርስትና አልያም ሌላ አምልኮ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ከጠላት ጋር ተናንቀው ተነባብረው የወደቁበት ድልም ያገኙበት ነው። ራስ ወሌ ብጡል ከዓድዋ ጀግኖች መካከል በቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፤ ከየጁ፣ ከላስታ፣ ከራያ፣ ከዋድላና ደላንታ የተውጣጣ ከ3000 በላይ ጦርም አሰለፈዋል። በዚህ በእሳቸው ብርጌድ በልጃቸው በራስ ጉግሳ ወሌ ሥር ሆነው የሙስሊሙን ጦር የመሩት ሙስሊሞቹ የጦር አበጋዞች ሚና የማይናቅ ነበር።
.
ከእነዚህ ሙስሊም አበጋዞች መካከል ቀኝ አዝማች ሀምዛ አበጋዝ፣ ቀኝ አዝማች ሞሀመድ በረንቶ፣ ባላምባራስ ይማም አምቡሎ፣ ፊታውራሪ ዓሊ ይማም፣ ሼኽ ሞሀመድ ሚዐዋ ወዘተ የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የዋርካው የሼኹ የአባ ጌትዬ ተወላጆች ናቸው፤ የክርስትያኖቹ የእነ ራስ ወሌ ብጡል የእነ እቴጌ ጣይቱ ብጡል፣ የእነ ደጅ አዝማች አያሌው ብሩ ወዘተ የሩቅ ዘመዶች ናቸው። ሼኽ ሞሀመድ መሸሻ የዕድሜ ባለጠጋውን የሼኽ ሞሀመድ ሚዐዋ የዓድዋ ውሎ ሲያጫውቱኝ የሚከተለውን ብለውኛል
.
አባባ ሞሀመድ! ሙስሊም ጦር በመምራት በአምባላጌ፣ በመቀለ እና በዓድዋ ጦርነቶች ተካፍለዋል። ፈረሳቸው ደበላ አባ ጫጉ ይባል ነበር። ቀደም ብሎ በዓጤ ዮሀንስ የማጥመቅ ዘመቻ ጊዜ ከዓጤ ዮሀንስ አምስት አሽከሮች ጋር ተጋጥመው ከፈረሳቸው እንዳሉ በጎራዴ ሁሉንም አንጋለዋቸዋል፤ በጣም ኃይለኛ ፈረሰኛ ናቸው። እሳቸው ፈረንጅ የሚባል ነገር አይወዱም ነበር፤ በኋለኛው በማይጨው የጣልያን የ5 ዓመት ዘመን ከፊታቸው አያስቀርቡም ነበር። በመጀመሪያው የአምባላጌ ውጊያ ጀብዱ በመፈጸማቸው እና መሳሪያም መትረየስም ጭምር ማርከው ስለነበር ራስ ጉግሣ ወሌ በጣም ተደንቀውባቸዋል።
.
በዋናው የዓድዋ የጦር ግጥሚያ ጠላት ወገግ ሲል ንጋት ላይ አጥቂ ሆኖ ጦርነት ሲጀምር እነ ራስ ጉግሣ በዋዜማው ጠጅ ሲጠጡ አምሽተው እንቅልፍ ላይ ስለነበሩ እና ጠላት ሳይታሰብ ስለመጣ ከባላምባራስ ይማም አምቡሎ ጋር ሆነው የራስ ጉግሣ ወሌን ኃላፊነት በመያዝ ጦሩን ግፋ በል እያሉ የጣልያንን ጦር በግንባር ቀደምትነት ተዋግተው ጀብዱ ፈጽመዋል። በዚህ በዓድዋ ውጊያም በርካታ የጦር መሳሪያ መትረየስም ጭምር ስለማረኩ ራስ ጉግሣ “ይበሉ የመሳሪያ እና የሰው ምርኮዎትን ይዘው ለአባቴ ለራስ ወሌ ያቅርቡ እና ይሾሙበታል ግዛትም ይሰጠዎታል አላቸው።” እሳቸው ግን “እኔ ሹመት ምን ያደርግልኛል፤ አላህ የሾመኝ ይበቃኛል። አንተ ምርኮውን ወስደህ ተሾምበት፤ እኔ ነኝ የማረኩት ብለህ ተናገር” ብለው እንደመለሱለት ሰምተናል።
.
ትናንት እንዳልኩት የውጭ ፀሀፊወች ሀገራችንን ከውጭ ሆነው ክርስትያን ነገሥታቱን ብቻ በማየት፤ ከውስጥ ያሉትም ደግሞ ከራሳቸው መነጠር ብቻ በመነሳት በርካታ ሙስሊም ማህበረሰብ መኖሩን በመዘንጋት በጣፏቸው ማስታወሻወች ይኼን የእስልምና ተከታይ የዓድዋ ዘመቻ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር በዓድዋ ላይ ያደረገውን ተጋድሎ ለክርስትያን አገር የተከፈለ መስዋትነት በማለት ድሉን ለማጥበብ ይሞክራሉ።
ክርስትያኑ ንጉሥ ነገሥት በማርያም እየማለ ተከተሉኝ ያለውን የዘመቻ ጥሪ አዋጅ ተቀብሎ የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበው ለእናት ሀገሩ እና ለራሱ ክብር ሲል ከክርስትያን ወገኑ ጋር ተነባብሮ የተዋደቀው የእግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር የአገራችንን ዳይቨርስቲ ደመቅ አድርጎ ከሚያሳዩ ምንጊዜም ከማይረሱ ሁነቶች ውስጥ የሚመደብ ነው።
.
ጦር ይምጣ ጦር ይምጣ ለምን ትላላችሁ፣
እንደ ደጉ አደሜ እንደ ዓሊ ነጎደ ታስወስዳላችሁ።
.
(ዓድዋ ለቀሩ ለራስ ወሌ ብጡል አዝማቾች Dej Azimach Degu Ademe, Fitawurari Ali Negode የተገጠመ)
.
ከጠመንጃው ይልቅ ያይኑ መመልከት፣
አባ ጠጣው ወሌ የእነ ጉግሳ አባት፣
ሰላቶ አባራሪ ዳገት ለዳገት።

﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄