ISLAMIC SCHOOL
12.6K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
አይርቅህ አይችልም የኔ የዋህ ልቤ
ፍቅርህ አንዴ ገብቶ ሰርስሮ በደሜ
አሁንስ ጠናብኝ እያደር ህመሜ
እዴትስ ልቻለዉ ኧረ በምን አቅሜ፣
የሄዱት ሲመጡ የመጡት ሲሄዱ
የተጋቡት ሁሉ አረግዘዉ ወለዱ
እኔ አንተን ስከተል ግዜቶች ነጎዱ፣
ወራቶች ተቆጥረዉ አመታት አለፉ
……ባየህዉ መቅፈፉ
ከዛሬ ከነገ ይገባሀል እያልኩ
በትግስት ይፈታል እራሴን አሳመንኩ፣
አንተ ግን አይገባህ ለምን ወደዴችኝ
ይሄን ሁሉ ግዜ ለምን ጠበቀችኝ፣
ዛሬም ነገም ያዉ ነህ ልክ እደትላቱ
አንተ ግን እደዛዉ እየሄዴ ወቅቱ፣
እናም አንተ የኔ የእልም እጀራዬ
እኔ ጋ ያለህዉ አላት መጠሪዬ
ከግዲህስ በቃ ልጀምር ጉዞዬ፣
እኔመች አማረኝ አለሁሽ የዉሸት
እኔን የናፈቀኝ…
አንድ ጎጆ ሰርተን በአንድት ጣራ ሰር
ልክ እደምመኘዉ ሳንለያይ መኖር ፣
ነበር የኔ ምኞት ቢሰምር ሀሳቤ
መኖር እደቅማችን ሳትርቅ ካጠገቤ፣
ታዳ ምን ያደርጋል የኔ ብቻ ምኞት
የህልም እጀራ ነዉ የአንድ ሰዉ ህይወት፣
እናልህ የኔ አለም ከግዲ በኋላ
መጠበቁ ደክሞኝ
ሄጃለሁ ረቄ እዳትፈልገኝ፣

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

          🎧  #ክፍል 2⃣1⃣

#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal
ከቆምኩበት ሳልንቀሳቀስ አጠገቤ ደርሶ "እንካን ደህና መጣሽልኝ! የኔውድ"ብሎ የያዘውን አበባ ዘረጋልኝ፡፡ በስስት አይን አይኑን እያየሁ በፍቅር ስሜት ታጅሜ በፈገግታ ተቀበልኩት፡፡ " በቃ እንቀሳቀስ ኮ/ቻ መቼም ናፍቃሻለች ዞር ዞር እንበል አይሻልም?" አለ ሷሊህ ጥሩ ሀሳብ ነው! በሀሳቡ ተስማምተን መንገድ ጀመርን፡፡ ሷሊህ ወደኔ ዞሮ " ወዴት መሄድ ትፈልጊያለሽ?" አለኝ፡፡ ኮ/ ቻ ናፍቃኛለች ስለዚህ "ወደ ሚጢ ቆሎ እንሂድ?" አልኩት ቁልቁል ሙሉ ኮምቦልቻን ለማየት እንድችል  " አሁን ቀን ነው ማታ እወስድሻለሁ በጨለማ ስትታይ ነው ኮ/ቻ ውበቷ የሚጎላው!" አለኝ " እሽ በቃ አንተ ደስ ወደሚልህ ቦታ ውሰደን" ብየ በሀሳቡ ተስማማን፡፡ በመሀል "አለሜ ለምን ግሪን አንሄድም? እዛ አሪፍ  አየር አለ" ሲል በሱ ምርጫ ወደዛው አመራን፡፡ ግሪን ቦታው በራሱ ምትሀታዊ የሆነ ውበት አለው ድብርትን በአዲስ መንፈስ የመቀየር ሀይል አለው፡፡
ብዙ ሰው ለብዙ አላማ ይጠቀሙበታል፡፡ የከፍው ከሀዘኑ ይደበቀበታል መዝናናት መንፈሱን ለማደስ የሚመጣም አለ ከሚወዱት ሰው ጋር ቁም ነገር ለማውራት ሙሉ ቤተሰቡን ይዞ ለመናፈስም ይመጣሉ፡፡ እሁድ እሁድ ደግሞ መኪና ማቆሚያ የእግር መረገጫ እስኪጠፍ ድረስ ሙሽሮች የሰርግ ፕሮግራማቸውን በዚሁ መናፈሻ ውስጥ ያከብራሉ፡፡ ዛሬ እኛም ንፁህ አየር እየተቀበልን ዘና ፈታ ለማለት ተገኝተናል፡፡ ለወንዙ አቅራቢያ የሆነ ቦታ መርጠን ተቀመጥን የወንዙ ድምፅ በራሱ ልዩ የሆነ ውበት አለው! ሷሊህና አለሜ በሚያወሩት ነገር እንዲሁ እንዳሳቁኝ ጥርሴን ሳያስከድኑኝ እናቴ ደወለች፡፡ " ምነው እስካሁን ቀራችሁሳ? ምን ሆናችሁ ነው?" ብላ ሷሊህን ጠየቀችው፡፡
በቃ አለሜ እንዲህ ነው ከሱ ጋር ስሆን ሁሉን ነገር ረሳለሁ! በደስታ ባህር ውስጥ ሰምጨ እጠፍለሁ! ገና ከተገናኘን 10 ደቂቃ የቆየን ሳይመስለኝ ሰአቱ 6 ሰአት ሆኖ እናቴ ደወለች፡፡ አለሜ አብረን ወደ ቤት እንዲንሄድ እኔም ሷሊህም ብንለምነው በፍፁም ብሎ እምቢ አለ፡፡ ብዙ ብለምነውም ግን ላሸንፈው አልቻልኩም፡፡ " በቃ እሽ መነሀሪያ ድረስ አብረን እንሂድ" አለ ሷሊህ፡፡ አለሜን ሸኝተን ወደቤት አመራን፡፡ ደስታ ተደራርቦ ልቤን አስጨነቃት ሀገሬን አለሜን ቤተሰቦቼን  በሰላም በፍቅርና በደስታ አገኘኃቸው! አልሀምዱሊላህ በጣም ተደሰትኩ! እህቶቼ አግብተው ከኛ ርቀው ስለሚኖሩ በስልክ እንጅ በአካል የምንገናኝበት ጊዜ በቁጥር ነው ወይም በምክንያት ሰርግ ምናምን ብቻ የሆነ ለየት ያለ ፕሮግራም ሲኖር ይመጣሉ፡፡
እኔም ይሄን ስለማውቅ ለኔ ሰርግ እንደሚመጡ እና ቤታችን እንደበፊቱ ሙሉ እንደሚሆን አስባለሁ፡፡

ቤት እንደደረስኩ ያየሁትን ማመን አቃተኝ እናቴ አባቴ እህቶቼ ከነልጆቻቸው ቤቱን ሞልተውታል፡፡ ማንን ቀድሜ ማቀፍ እንዳለብኝ መምረጥ አልቻልኩም በቆምኩበት ለሁሉም እጀን ዘረጋሁ ሁላቸውም ከበው አቀፉኝ እኔ መሀል ገባሁ፡፡ የቀረበኝን ቀድሜ እየሳምኩ ሁሉም ጋር በመተቃቀፍ ናፍቆቴን ካስታገስኩ በኃላ ተቀመጥን ግን አንድ ያልሳምኩት ሰው አየሁ የእህቴ ልጅ ዲራር በማናለብኝ በነፃነት አጆቹን ግራና ቀኝ ተርግቶ ተኝቷል የኔውድ በተኛበት እየሳምኩ ስነካካው ፊቱን እንደማኮሳተር እያለ ፊቱን እጅ ጋር አፍተጋቸው፡፡ እኔ ስሄድ ገና የ2 ወር ልጅ ነበር በእናቱ እቅፍ ሆኖ ስታጠባው ጠብቶ ስታስተኛው ይተኛ የነበረ ዛሬ ላይ ረባሽ ሆኖ እንቅልፉ ሆኗል ረፍቷ፡፡ " ተይ እንዳይነሳ ለምኘ ነው ያስተኛሁት ብታይው 1 ልጅ እንዳይመስልሽ የ10 ያህል ነው" አለችኝ በተማረረ አነጋገር፡፡ እናቴ ከእቅፏ እንድርቅባት አልፈለገችም፡፡ አቅፍኝ ፀጉሬን እየደባበሰች ታወራኛለች፡፡ ከወትሮው ሁኔታዋ ተለየብኝ በፊት ሷሊህን ነበር እንዲህ ስታደርግ የማውቃት፡፡ ታዳ ዛሬ ምን ተገኘ ስለናፈኮት ነው ወይስ ላገባ እንደሆነ አስባ ሆድ ብሷት? አላውቅም ብቻ የእናቴ እቅፍ ለኔም ናፍቆኛልና ተመችቶኛል፡፡ እዛው በተሰባሰብንበት ሰለ ሰርጉ ወሬ ጀመሩ፡፡
ዝም ብየ ወሬያቸውን ማዳመጥ ጀመርኩ፡፡ ሀፍረት ተሰማኝ፡፡ እኔን አንዳንድ ሀሳብ ሲጠይቁኝ " እናንተ እንዳላችሁ" እያልኩ ወሬ አሳጥራለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማውራት የምፈልገው ጏደኞቸ ጋር ነው፡፡  ዛሬ ቀኑ ሰኔ 28 ነው ነሀሴ 4 ሰርጋችን ነው፡፡ ኦኦ የኢክሩ ሰርግ ጊዜ የነበረ ውጥረት አስታወስኩ፡፡ ጨነቀኝ ያኔ አራታችን ነበርን አሁን ሀዩ የለችም ኢክሩም የልጅ እናት ሆናለች እንደበፊቱ አብራን ተፍተፍ ማለት አትችልም እኔና ነቢ ብቻ ቀርተናል፡፡ ነቢም ገና አልመጣችም ኡፍፍፍ! ነቢ ከ3 ቀን በኃላ ትመጣለች፡፡ እስከዛ ድረስ ብቻየን ምንም መወሠን አልፈለኩም፡፡ 

ሲሀም ቀድማ በያዘችው ፕሮግራም መሰረት ለምሳ ወደ ቤተሰባቸው መቀላቀልና መተዋወቅ ግድ ሆኗል! እናም ከጧት ሂጄ ሰአቱ እስኪደርስ ኢክሩ ጋር ለመቆየት  ሄድኩኝ፡፡ የኢክሩ ልጅ በጣም ታሳሳለች!! ማንም ሰው አይቶ ሊያልፍት አይችልም፡፡ ውፍረቷና ቅላቷ ከልጅነቷ ጋር ተደምሮ ልብን ትሰርቃለች!! እኔ ልጆችን በተኙበት ማጫወት እንጅ ማቀፍ አልችልም እንዳይወድቁብኝ እፈራለሁ፡፡  እዛው በተኛችበት እያወራሁ ሳጫውታት ኢክሩ በአግራሞት ታየኛለች! " እኔኮ እንዳንች አላጫውታትም አጥብቸ ነው የማስተኛት በአላህ በይ ጨዋታ አስለምደሽ ቡሀላ እንዳታስለቅሽብኝ" እያለች እየሳቀች ታየኛለች፡፡ "እንደኔ ማጫወት ነዋ ታዳ" ብያት ጨዋታየን ቀጠልኩ፡፡ ምሳ ግቦዣው እነ ኢክሩም እንደተጠሩ ስትነግረኝ ሌሎቹም ጏደኞቹ እንደሚጠሩ አሰብኩ ኢክሩ አብራኝ ስላለች በመጠኑም ቢሆን  ፍርሀት ቀነሰልኝ ግን ደግሞ ሙስጠፍ አዲስ አበባ ስለነበረን ቆይታ አስታውሶ በነሱ ፊት እንዳይዘባርቅ ፈርቻለሁ፡፡

አለሜና አንዋር እኛን ለመውሰድ ሲመጡ ኢክሩ መዘጋጀቷን ረስታ አፍ ለአፍ ገጥመን ወሬ ይዘናል፡፡ ኢስላማዊ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ  አንዋር " ሀቢብቲ ገና ነሽ እንዴ?" አለ " ውዴ 10 ደቂቃ ብቻ ታገሰኝ" ብላ ወደ ሻወር ቤት ገባች፡፡ እኔም ከሰኪና ጋር ጨዋታየን ቀጠልኩ፡፡ በመሀል ራባት መሰል ለማልቀስ መነጫነጭ ጀመረች፡፡ " ኢክሩ ልታለቅስ ርቧታል" ብየ ድምፄን ከፍ አድርጌ ነገርኮት፡፡ " አንሻት" አለችኝ፡፡ ጨነቀኝ እኔ ልጅ 6 ወር በፊት አቅፌ አላውቅም፡፡" አንዋር እቀፍት እኔ አልችልበትም እፈራለሁ" አልኩት " አረ ያንችን ልጅ ማን ሊያቅፍ ነው ታዳ መቼም ኡስማን አትይኝም" አለ እየሳቀብኝ ልጅን ለማቀፍ ወደኔ እየመጣ፡፡ አለሜም ቀጠል አለና " እናትነት እንዴት ያምርባታል ትችልበታለች ብየ ተናግሬ ሳልጨርስ ማቀፍ አልችልም ብለሽ አሳፈርሽኝኮ" አለኝ፡፡ " እና በራሴ ልጅ ነዋ የምለማመደው የሰው ልጅ ቢወድቅብኝስ!?" አልኩኝ፡፡ በንግግሬ አንዋር ከት ብሎ ሳቀ፡፡ አለሜ "ቆይ እኔ ላሳይሽ እንዴት እንደሚታቀፍ" ብሎ ሚጣን ከአባቷ ተቀብሎ ወደኔ ይዟት መጣ፡፡ አስተቃቀፍ እንዴት ቻለበት? አልኩኝ በውስጤ በቅፅበት ሰኪና የኛ ልጅ የሆነች መሰለኝ፡፡ በእቅፉ ውስጥ መልካም አባትነቱን ፈለኩ፡፡ በፍቅር አይን አይኑን ተመለከትኩት እሱ ግን አይኑ ሰኪና ላይ ስለነበር አላየኝም እንኮንም አላየኝ፡፡ ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ ለማቀፍ እጀን ዘረጋሁ " ተነሽና እቀፊያት" አለኝ
#part 2⃣2⃣
ይ ቀ ጥ ላ ል
JOIN👇👇👇
@IslamisUniverstiy_public_group
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😔 የእስራኤል ወታደሮች አሁንም ለሰዉ ክብር የላቸዉም አለምን ጉድ የሳዘነ video ይመልከቱ፡፡ በሽማግሌ ሰዉ ላይ በሶሪያ ዜጎች የሚያደርሱትን እንግልት ይመልከቱ ፡፡

አላህ ሆይ ሶሪያን ይህን ስቃይ እንግልት በቃ በላቸዉ፡፡

ሁላችንም ዱአ እናድርግላቸዉ፡፡

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💙#ትዳር #በነብዩ ስ.ዐ.ወ ሱና💙

😎 #ያገቡ #ሰዎች› ና ‹ያላገቡ ሰዎች› በእነዚህ ሰዎች መካከል
የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አለ ቢባል አይከብድም፡፡

#የእነዚህ ሰዎችን ልዩነት በአንድ ርእስ ብቻ መግለፅ
ቢከብድም አጠር ባለ መልኩ ኢን ሻ አላህ ለማቅረብ
እንሞክራለን፡፡

💟 (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ ሲከተል ያላገባ ሰው ትልቅ የሆነውን
ሱና ተነፍጓል፡- ከመጀመሪያው ቀጥሎ ትልቁ ልዩነታቸው
#ያገባ #ሰው ትልቅ ሱናን ሲከተል ያላገባ ሰው ደግሞ ትልቁ
ሱና አምልጦታል፡፡
☞ ሰይዱል ሙስጠፋ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ
ብለዋል፡- “…የእኔን ሱና የማይከተል ከእኛ አይደለም፡፡››

💟 #ያገቡ #ሰዎች ከብዙ ሀራም ሲጠበቁ ያላገቡ ሰዎች
ሀራም ላይ የመውደቅ እድላቸው ይሰፋል፡-
☞ያገቡ ሰዎች
አይናቸው ይሰበራል፣
☞ብልታቸው ከዝሙት ይጠበቃል፣
☞ቀልባቸው ይረጋጋል፡፡
☞ያላገቡ ግን ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ
ተጠቃሚ አይሆኑም፡፡

💐#ታላቁ #ነብይ(ሰ.ዐ.ወ) ‹በሁለት
እግሮቹና በሁለት ከንፈሮቹ መሀል ያሉትን ስጋዎቹን
የጠበቀ እኔም ጀነትን ቃል እገባለታለሁ፡፡› ብለዋል፡፡
#ያገባ
ሰው ከሁለቱ ነገሮች የመጠበቅ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ ያላገባ
ግን….

💟 #ያገባ #ሰው ዘሩን ሲቀጥል ያላገባ ግን ዘሩን የመቀጠል
እድል የለውም፡-

#ዘር #በኢስላም ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ‹ብዙ
ተባዙ፡፡
☞ነገ የውመል ቂያማ ከሌላው ነብይ የእኔ ኡመቶች
በዝተው እንዲታዩ› ብለው ነግረውናል ታላቁ ነብይ፡፡ እናም
ልጆችን የምንወልደውና የልጆችን ደስታ የምናገኘው
በትዳር ውስጥ ነው፡፡
☞ ያላገባ ሰው ይህን ኒዕማ ማግኘት
አይችልም፡፡

💟 #የገባ #ሰው ሪዝቁ ይሰፋል፣ የልብ መረጋጋትን ያገኛል
☞ያላገባ ሰው ግን ይህን ነገር አያገኝም፡- ‹ሪዝቁ
እንዲሰፋለት የፈለገ ሰው ያግባ› ሲሉ ሰለፎች
ይመክሩናል፡፡
☞ያገባ ሰው ልቡ መረጋጋትን ያገኛል፣ ቀልቡ
ማረፊያን ታገኛለች፡፡
☞ያላገባ ሰው ግን እንደተጨናነቀ ነው
እድሜውን የሚጨርሰው፡

💐💐💐 እስኪ የአገባችሁ ይህ ሁሉ ኒእማ ላይ ስለሆናችሁ ዱአ አርጉልን🌿🌿

❤️ #አላህ ላላገባን የሚበጀንን የትዳር አጋር እና ይወፍቀን

💚 #አሚን ያረበል አለሚንንንንንንን💚

✔️ #እስኪ ላላገቡት ጓደኛችሁ ሸር ያድርጉት አይታወቅም ጀምሮ ከሆነ ይህን ኒእማ ሲያነብ እስከ አሁን ተጎድቻለሁ ወይ ብሎ 😉 አባወራ ሊሆን ይችላል😉


🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
🔊 #የአደም #ልጅ #ሆይ!

💚 #የተሰጠህ ቀን እንግዳህ ነውና በመልካም ሁኔታ አስተናግደው፡፡

💜 #በመልካም #ሁኔታ
ካስተናገድከው አምስግኖ ይሄዳል፡፡

❤️ #በመጥፎ_ሁኔታ ካስተናገድከው ይወቅስሃል፡፡
[ ሐሰን አልበስሪ ረ.ሂ ]

﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
ሽንኩርት ሲልጡ ለምን ያለቅሳሉ?
...
አንዳንዶች ሽንኩርት ሲልጡና ሲከትፉ ያነባሉ፡፡ ሽንኩርት በሚከትፉበት ወቅት በሽንኩርት ሴል ውስጥ የሚገኙ #ኢንዛይሞች (Enzymes) ከተለያዩ ኬሚካሎች ጋር ሲደባለቁ ጋዝ ይፈጠራል። ይህ ጋዝ በአይን ውስጥ በሚገባበት ወቅት ሱልፈኒክ አሲድ ይፈጥራል።
.
የዚህ አሲድ በአይን ውስጥ መፈጠር ደግሞ ለማቃጠሉ፣ ለመቆጥቆጥና ለማስለቀስ ዋንኛ ምክንያት ነው፡፡ ታዲያ ሽንኩርት እንዴት አንዳንዶችን ሲያስለቅስ ሌሎችን ምንም አያደርጋቸውም ለሚለው ጥያቄ በዊስከንሳን ማድስን የሆርቲካልቸር ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አርዊን ጎልድመን ሲመልሱ ምናልባት የአይናችን ኬሚስትሪ የተለያየ ሲሆንና ለሱልፈኒክ አሲድ የሚኖርን ምላሽም ከሰው ሰው ሊለያዩ እንደሚችል ጠቁመው አንዳንዶች ላይ ከፍተኛ የሆነ መቆጥቆጥና ማስለቀስን ሲፈጥር ሌሎች ደግሞ ይህንን አሲድ የመቌቌም ብቃት ስላላቸው ምንም አይነት ሁኔታ እንደማይፈጠርላቸው ገልፀዋል፡፡
.
ይህንን ችግር ለመቅረፍም ዶ/ር ጎልድማን እንደሚሉት ሽንኩርቶቹ ከመከተፋቸው በፊት በደንብ #ማቀዝቀዝ የኢንዛይሞችን የመልቀቅ ሂደት ስለሚያዘገየው ችግሮቹንም በተወሰነ መልኩ ይቀንሰዋል፡፡ ባለሞያው አያዘውም ከላይ #ከቀጭኑ_ጫፍ በኩል መላጥና መክተፍ መጀመር ሌላው አማራጭ መሆኑን ገልፀው እነዚህ ኢንዛይሞች በብዛት የሚገኙት በወፍራሙ ጫፍ በኩል በመሆኑ ይህንን ማድረጉ ችግሩን በተወሰነ መልኩ ያቃልለዋል ብለዋል።
.
አንዳንዶች ሽንኩርትን ለመክተፍ በጣም የተሳለ ቢላዋን መጠቀም ሴሎቹ እንዳይጎዱና ኢንዛይሞችን እንዳይለቁ ስለሚያደርጋቸው ጥሩ መፍትሔ እንደሆነ ይጠቁማሉ። በተጨማሪም በውሃ ውስጥ ሽንኩርትን መክተፍ የሚለቀቀውን ጋዝ ለማፈን ስለሚረዳ ማስለቀሱን እንደሚቀንስ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ፡፡
.@ ምንጭ: Ethiopian Drug information Network
የፍቅር ህይወትህን መጨረሻውን በትዳር ማታሳምረው ከሆነ ባትጀምር ይሻላል ፥ በአንድ ካልፀናህ ሁሉን እየጀመርክ ምተው ከሆነ በሁሉም የተናቅ ትሆናለህ!!

«:::::::::::»
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
«::::::::::::»
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

          🎧  #ክፍል 2⃣2⃣

#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal

ከተቀመኩበት ሳልነሳ ለማቀፍ እጀን ዘረጋሁ " ተነሽና እቀፊያት" አለኝ አሱ ሰኪናን በስስት ያያል እኔ ደግሞ እሱን በፍቅር አየዋለሁ፡፡ በዚህ መሀል ኢክሩ ጨርሳ ወጣች " ልጀን መጫወቻ አደረጋችኃት አይደል" ብላ ልጇን ተቀብላ " የኔ ፍቅር ሲለማመዱብሽ ዝም ትያለሽ አታለቅሽም?" እያለች ልታጠባት ይዛት ገባች፡፡

አራታችንም ተያይዘን ሄድን በየመሀሉ የሲሀም የት ደርሳችኃል የሚል በስልክ ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ቤታቸው ደርሰን ጊቢ ስንገባ ፍርሀት ወረረኝ እስካሁን ድረስ አባቱን በድምፅም ይሁን በአካል ተገናኝተን አናውቅም፡፡ ወደ ኢክሩ ተጠግቼ ጠበቅ አድርጌ ያዝኮት፡፡ አይዞሽ ብላ ኢክሩ አጀን ጠበቅ አረገችኝ ወደ ቤት ስንገባ ያረፈድነው እኛ ብቻ ነን ሁሉም ጏደኛሞች ከሚስቶቻቸው ጋር ተገኝተዋል ብቻውን የመጣው አብበከር ብቻ ነው፡፡

ገና ወደ ቤት ስንገባ ሙስጤ ድምፁን ከፍ አድርጎ " ማዘር ምራትሽ መታለች ተዋወቂያት" አለ መጅሊሱ ላይ የተቀመጡት አባቱ እንደሆኑ ገምቻለሁ፡፡ ወዴት ልሂድ ምን ልበል ጨነቀኝ ባለሁበት ቆሜ ቀረሁ! "የኔ ቆንጆ ልጅ መጣሽልኝ" ብላ ሮጣ መታ ተጠመጠመችብኝ እናቱ ለኔም እናቴ ነች፡፡ አንቱ እያልኩ ላላርቃት እናቴ ብየ እንድጠራት ቀድማ ቃል አስገብታኛለች፡፡ ስለዚህ ልክ አለሜ አለሜ እንደሚጠራት እኔም እማ ብየ ጠርቸ አቀፍኮት፡፡ አቅፍኝ እየሳመችኝ ብዙ ቆየች፡፡ " አረ እኔም ተራ ይድረሰኝ" የሚለው የሂሀም ድምፅ አለያየን፡፡

.ሲሁም ተጠመጠመችብኝ እኔም አጥብቄ አቅፌ ሳምኮት ከወንድሙ ጋር በቃላት ሰላምታ ተለዋውጠን ተዋወቅን፡፡ "እስኪ ነይ የኔ ልጅ ልሳምሽ" የሚል ድምፅ ሰምቸ ወደ መጅሊሱ ሄድኩኝ አባቱ ትልቅ ሸህ ናቸው ፊታቸው በሻሻ የማያስፈሩ ኑራቸው የሚያበራ ናቸው፡፡
.....,,አጠገባቸው ሂጀ ተንበርክኬ ተቀመጥኩ፡፡  ዚያራየን እንደ ጨረስኩ ትንሽ ተረጋጋሁ ፍርሀት ቀነሰልኝ፡፡ ሲሀም ከጎኔ ተቀምጣ እያወራች ፍርሀቴን አባረረችው፡፡ 

"አሁን የምሳ ሰአት ነው ተሰብሰቡ" ተብሎ ሴት ለብቻ ወንድ ለብቻ  ተሰብስበን ማአድ ከበን በልተን እንደጨረስን ቡና ፈላ በዚህ ሰአት ሁሉም ከየራሱ የሂወት ገጠመኝ የሚያስቃቸውን ነገር እያወሩ ቤቱ በሳቅ ተሞላ ሙስጤ ሲቀልድ ለዛ አለው " ማዘር እእ እንዴት ነች ኢማን አገኝቷታል ነው ወይስ  አጊንታዋለች የሚባለው ብሎ ድንገታዊ ጥያቄ ጠየቀ"
....,ጥያቄው ድንገታዊ ሆኖ እንዳስደነገጣት ንግግሯ ያስታውቃል "አይ ቆንጆ ናት ምን ይወጣላታል ግን የኔም ልጅ ጨዋ ነው ስርአት አለው ሰው አክባሪ ነው" እያለች አንዳችንን ከአንዳችን አስበልጣ እንዳንቀየማት በሚመስል አነጋገር ሁለታችንምም መረጠች፡፡ በዚህ ንግግሯ አለሜ ሳቁን ለቀቀው "በቃ ጠበቃየኮ ነሽ እማ!" ብሎ አቅፎ ሳማት፡፡  ሙስጤ አሁንም አላረፈም በአይኑ ዞር ዞር ብሎ ሲመለከት ሁሉም ጥንድ ጥንድ ሆነው አቡበከር ብቻውን ተቀምጦ የፈንድሻ ሰሀን አቅፎ ሲበላ ተመለከተው " አወ አግብተህ ወልደህ አትቀፍና ሰሀን አቅፈህ ሆድህን ሙላ" ሲል በንግግሩ ሁሉም ሳቁ! አቡበከር መብላቱን አቁሞ ሰሀኑን ከሱ አራቀው፡፡
........" ተው ሙስጤ በቃ አንድ ቀን ያገባል" አልኩኝ " እንዳይከፍው ብለሽ ነው? ይሄ መቼም አይሰማውም እስኪ ቆጭቶት አሁኑ ያግባ ሴት አቶ መሰለሽ ስላልፈለገ እንጅ" አለኝ
......በዚህ ጊዜ አቡበከር በምሬት መናገር ጀመረ " እውነት እኔ እንደናተ አግብቼ መውለድ የማልፈልግ ይመስላችኃል እንዴ!!? እእእ እስኪ ንገሩኝ በማሰብና በመፈለግ ቢሆን ኖሮ ከማናችሁም እቀድም ነበር ግን ሴት ሁሉ ሚስት መሆን አይችልም! አላህን የምትፈራ የሆነችን አምጥታችሁ ወይም ጠቁማችሁኝ አላገባም ብያለሁ!!?? እእእ ንገሩኛ! እምቢ ብያችኃለሁ? በቃ እኔ በራሴ ፈልጌ አጣሁ! ምን ልሁን? ለአላህ ትእዛዝ ተገዥ የሆነች ከገንዘብ ይልቅ እኔን የሞታስቀድም የሆነች ካለች አምጡዋት ዛሬ ነገ ሳልል አገባለሁ!!" ንግግሩን በመሀል ዝምታን አሰፈነ፡፡
የሸህ አህመድ ንግግር ዝምታውን አስወገደ " ልጀ ንግግርህን ሰማሁህ ጥሩን ለጥሩ ነው አላህ የወፈቀው ኢንሻአላህ ልምከርና በዚህ ሳምንት ውስጥ አሳውቅሀለሁ በአላህ ፈቃድ አንተም እንደጓደኞችህ ታገባለህ አብሽር ልጀ ሁሉም ለከይር ነው መፈተንህን አትጥላው አላህ የተሻለን ይዞልህ ነው ወርቅ በስንት አሳት ተፈትኖ አይደል እኛ ጋር ውድ የሆነው ኢንሻአላህ በዱአ በርታ" አሉት ይሄን ሲናገሩ አቡኪ ፊቱ ላይ የተስፍ ብርሀን ፈንጥቆ ደስታ ይነበብበታል፡፡ ሌሎቹ ግን አለሜን ጨምሮ የሸህ አህመድ ንግግር ግራ ያጋባቸው ይመስላል፡፡ ሁሉም ተያዩ ማንን ሊድሩት ነው?
#part 2⃣3⃣

,,,,,,,,,,ይ
,,,,,,,,,,,,,,,,,ቀ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ጥ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ላ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ል

ሼር የማታረጉ የቻናል ቤተሰቦቻችን ደህንነታችሁ ሀሳብ ሁኖብናል😉 ለጓደኞቻችሁ ሼር በማድረግ አለን በሉን☺️

4 another channal👇
@Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
👍1
😂 #ፈገግታ ሱና ነዉ ፈገግ በሉ

አንዱ አባ ወራ የፓምፐርስ ወይ አስመርሮት

#ጓደኛዉ እንዴት ነህ ይለዋል

#እሱም ደህና

#ልጅህ እንዴት ነዉ ሲለዉ


ምን ቢል ጥሩ ነዉ
😳





😳




😳



ብር ላይ እየሸና ምን አለበት 😂😂😂
ብለህ ነዉ 😉😉
ብሎት እርፍ

#ፓመፕርስ ወጭ እንዲህ ያሰለቻል ማለት ነዉ😉


JOIN👇👇👇

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
በረከት ሰምዖን ታሰረ
*#ኡስታዝ_አህመድን_ጀበል በፌስቡክ ገፁ ያስቀመጠዉ መልእክት👇
የአቶ በረከት ስምኦንን መታሠር ዜና እውነት መሆን አስደሳች ነው።አልሀምዱሊላህ ። አቶ በረከት ከታደሰ ካሳ ጋር ታስረዋል። አቶ በረከት በኢትዮጵያውያን ላይ ብዙ መከራ ያደረሰና ያስደረሰ ግለሰብ ነው። የእርሱና ቀደም ብሎ ከወራት በፊት የታሰረው የአቶ ደርበው ደመላሽ መታሰር በመጅሊስ አከባቢ ለዓመታት ሲደረግ የነበረውን የሀጅ ገንዘብ ዝርፊያ፣ የመጅሊስ መሪዎችን በትዕዛዝ መዘወር እና ባለፉት ዓመታት በህዝበ ሙስሊሙ ላይ አህባሽን በግድ ለመጫን የተደረገውን ሰቆቃ እውነቱን ለማውጣት ያግዛል። ምናልባትም የመጅሊሳዊ ሜቴክ አበላትና ስራውን በዝርዝር እንሰማ ይሆናል። አቶ ደርበው ደመላሽ ቀደም ብሎ በደህንነት መስሪያ ቤት የሀይማኖት ክፍል ሀላፊ የነበረ በቀጥታ ከደህንነት መስሪያ ቤት ተወክሎ ሲያሳስር፣ የመጅሊስ መሪዎችን ሲለዋውጥ፣ የአህባሽን ስልጠና ሲመራ የነበረ ነው። ጌታቸው አሰፋ፣ ዶ/ር ሀሺም ተውፊው፣ ዶ/ር ሺፈራው ተክለማርያም፣ አቶ ሙሉጌታ ዉለታው፣ እና ሌሎችም ያቀራሉ። ከዶ/ር አብይ እነኘህን ጨምሮ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ በደል የፈጸሙት ላይ ራሱን የቻለ ምርመራ ማድረግና እውነቱን ለህዝብ ይፋ ማድረግ እንዲሁም አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንዲያገኙ ማስደረግን እንጠብቃለን።

@Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
የታሪኩ ርዕስ

💖 #የህልም #ባሌን #በአገኘሁት 💐

          🎧  #ክፍል 2⃣3⃣

#ፀሀፊ#ፎዚያ #ሙሀመድ
በIslamic university channal

23
ለሲሀም ግብዣ ምስጋናን ለግሸ ሰለነበረን ቆይታ ደስታየን ገልጨ ተሰናብቻቼው ከቤት ወጣን፡፡ ሙስጠፍ፣ ከማል እና አንዋር ሚስቶቻቼውን ይዘው ወደ ቤታቼው ተመለሱ፡፡ እኔ አለሜና አብኪ ብቻ ቀረን፡፡ አቡኪም ከስራ ቦታ ተደውሎለት "በቃ ሸኛትና ወደ ሱቅ ና" ብሎት ሄደ፡፡
     አለሜ የቤተሰቦቹ ቤት ደሴ ከተማ ላይ  አገር ግዛት ነው ወደ መነሀሪያ ለመሄድ ቁልቁል መንገድ ስንጀምር " ሁቢ እዚህ ከመጣሽ ለምን ቤታችንን አታይውም? ያልወደድሽው ነገር ካለ አይተን እናስተካክላለን" አለኝ፡፡  በሀሳቡ ተስማምቼ ወደ ተከራየው ኮንዶሚኒየም ቦታዉም ደሴ ከተማ በሚገኘዉ ተቋም ከመድረሳችን ተርሚናል በሚባለዉ  የኮንዶሚኒየም ቤቶች በሁለት ብር ታክሲ ትራንስፓርት አመራን፡፡ ቤት ገብቸ የእቃ ምርጫውንና የአቀማመጣቼው ፎርም ለራሴ ገረመኝ፡፡ በእኔ ምርጫ የተገዙ ነው የመሰለኝ ግን ደግሞ ምርጫየን ጠይቆኝ አያውቅም፡፡ ምናልባት ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳል ነውና ሚባለው ምርጫየ ምርጫው ይሆን?አላውቅም ብቻ!  ከሳሎን ወደ መኝታ ቤት ገባሁ፡፡
......ዋው! ነጭ አልጋ ነጭ ቁምሳጥን "ቆይ ይሄን ሁሉ ባንተ ምርጫ ነው!?" ብየ በአግራሞት ጠየኩት " አይ በኢክራም ምርጫ ነው የሆነው" አለኝ፡፡ የኔ ውድ ጓደኛ ምርጫየን ጠንቅቃ ታውቃለች! ስለመልካምነቷ እያሰብኩ  ፈገግ አልኩኝ፡፡ ከአልጋው ጎን እራቅ ብላ ወደተቀመጠችው የመዋቢያ ጠረንጼዛ ተራመድኩ፡፡
      ራሴን በመስታወት እየተመለከትኩ " እድለኛ ነሽ ኢሙ!" አልኩኝ ለራሴ፡፡ ራሴን በመስታወት ቁሜ ስመለከት አለሜ ከኃላየ አቀፈኝ፡፡ እጆቹ ትከሻየ ላይ ሲያርፍ ሰውነቴን ነዘረኝ ደርቄ ቀረሁ፡፡ ፊቴን ወደራሱ አዙሮ አቀፈኝ፡፡ ደረቱ ላይ ተለጠፍኩ የልብ ምቱ ድው ድው እያለ ሲፈጥን ጆሮየ እንደ ማግኔት ተጣብቆ ይሰማል፡፡ የልብ  ምቱ በጆሮየ ለልቤ መልክ የላከ መሰለኝ የልቤ ምት ሲፈጥን ለራሴ ይታወቀኛል፡፡ እሱ እንዳቀፈኝ እኔም በማቀፍ አፀፍውን መለስኩለት፡፡ መሳሳም ጀመርን፡፡ በስሜት ቅልጥ ብለን ጠፍን፡፡
......የአንዋር የስልክ ጥሪ ከገባንበት የስሜት ማእበል ቀሰቀሰን፡፡ በፍጥነት ተነሰቼ ቦርሳየን ይዠ ሮጨ ወጣሁ፡፡ ምን እየሆንኩ ነው? እንዴት እንደዚህ ሊሆን ቻለ? እያልኩኝ በራሴ እያፈርኩም እየተናደድኩም መንገዴን ጀመርኩ ቆይ አንዋር ባይደውል ኖሮ ምን ሊፈጠር ነበር? አኡዙቢላህ! ኢማን ደካማ፡፡ ነሽ! የማትረቢ ማፈሪያ ነሽ! እያልኩኝ ራሴን ስወቅስ አለሜ  ደወለ ግን ማንሳት አላሰኘኝም ድምፅን አጥፍቸ ተውኩት፡፡
  መነሀሪያ ደርሸ ጉዞ ከደሴ ከተማ ወደ ኮምቦልቻ ጀመርኩኝ፡፡ አሁንም ግን መደወል አላቆመም፡፡  እኔም ስልኩን አይቸ ድምፁን አጠፋለሁ፡፡ አንስቸስ ምን ልለው? ምንም እንዳልተፈጠረ ማስመሰል አልችልም ስለዚህ ዝምታን ምርጫየ አረኩ፡፡
......."እኔ  በጣም ባለጌ ሰው ነኝ! ይቅር የማይባል ስህተት ነው የሰራሁት! በፍፁም አንችን የስሜቴ ማስታመሚያ አድርጌ አስቤሽ አላውቅም! ዛሬ በተፈጠረው ነገር አፍሬያለሁ! ተሳስቸ አንችንም አሳሳትኩሽ፡፡ ይሄ ይፈጠራል ብየ አላሰብኩም፡፡ ሁሉም የኔ ጥፍት ነው!!! ይቅር በይኝ የማለት ድፍረት ባይኖረኝም ግን አላህ የውሰጤን ያውቃል የተፈጠረው ነገር እንዲፈጠር አልፈልግም ነበር  ወደ ቤትም ስወስድሽ ፍፁም ይሄን አስቤ አይደለም ግን በቃ ሸይጧን አሳሳተኝ" የሚል መልእክት ላከልኝ፡፡
       በርግጥ አለሜ የብልግና ባህሪ እንደለለበት ጠንቅቄ አውቃለሁ! አላህ የሩቅ ሚስጥር አዋቂ ነውና የሚሆነውን ቀድሞ ስለሚያው ነው በመሀላቸው ዝምድና የሌላቸውን ሁለት ተቃራኒ ፆታ ብቻቸውን እንዳይቀማመጡ የከለከለው፡፡ ዛሬ እና አላህ ካሰመረልን መስመር አልፈን በራሳችን መሄዳችን የስሜታችን ባሪያ የሸይጧን መናገሻ ሆነናል፡፡ ጥፍቱን ወደሱ ብቻ አስጠግቸ እሱን አልኮንንም " ሁለታችንም ጥፍት አጥፍተናል
.........አንተ ቤት እንሂድ ስትል እኔ እሽ ብየ ስከተልህ ነው የተሳሳትነው፡፡ ለአሁን ወንጀላችን አላህ ይማረን ከዚህ በኃላ ግን ኒካህ እስከምናስር ድረስ ብቻችንን በአካል አንገናኝም፡፡" ብየ ለመልእክቱ መልስ ላኩለት፡፡ "ሀሳብሽ ሀሳቤ ነው" በሎኝ ተስማማን፡፡

ነቢም ትምህርት ጨርሳ መጣች፡፡ አልሀምዱሊላህ! አሁን ብቻየን አይደለሁም፡፡ ነቢ ፍላጎቴን ገና ከአይኔ አይታ መረዳት የምትችል ጓደኛየ ብቻ ሳትሆን ለኔ የሚሻለኝንም መራጭ ጓደኛየ ነች፡፡  አሁን ያለን ጊዜ አንድ ወር ብቻ ነው፡፡ ሲሁም ከኛው ጋር ብዙ ጊዜዋን ማሳለፍ ጀምራለች፡፡ ከወንድሟ ሰርግ እኔን ቅድሚያ ሰታ ስለመረጠችኝ ደስ ብሎኛል፡፡ ሚዜም እንደምትሆነኝ ነግራኛለች፡፡ ኢክሩ ከኛ ጋር ብዙ ጊዜ እንዳታሳልፍ ልጇ ገና አልጠነከረችም ቢሆንም ግን ሁሉንም ነገር በስልክ ሀሳብ  በመስጠት ድጋፍ አልተለየችንም፡፡
     ነቢ በሰርጉ  ሰበብ እኛ ቤት ውላ የምታድርባቸው ቀናቶች በዝተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከሷልህ ጋር ከበፊቱ በበለጠ ተግባብተዋል፡፡ የሷሊህን ስም ደጋግማ ስትጠራ እሰማታለሁ፡፡ እሱም እንደዛው አብዝቶ ስሟን ይጠራል፡፡ እኔ ጋር ካላደረች ለምን ብሎ መጠየቅ ጀምሯል ሁናታው አልጥምሽ ብሎኛል፡፡ ነቢም እኛ ቤት ማደሩን ወዳዋለች ግን እኔን ብላ ብቻ አይመስለኝም፡፡ የሁለቱንም ሁኔታ በጥልቅ መመርመር ይዣለሁ፡፡

     ሀይስኩል ተማሪ እያለሁ ሁሌ ማታ ማታ ከሷሊህ ጋር ፊልም እናይ ነበር፡፡ ታዳ ብዙ ጊዜ በተኛሁበት እንቅልፍ እየወሰደኝ እኔን አቅፎ ወደ ክፍሌ መውሰድ ቢያሰለቸውም ግን አንድም ቀን ተነሽ ብሎኝ አያውቅም እሱ ቀድሞኝ ከተኛ እኔም ትቸው አልሄድም ከጎኑ ተኝቸ አነጋለሁ ብዙ ፎጣ ብቻ ለብሰን ያነጋናቸው ምሽቶች ነበሩ፡፡ እናቴ ይሄን ስታይ " የናንተ ነገር አይታመንም" እያለች ብርድ ልብስ ትደርብብናለች፡፡ ከዛም በኃላ እንደልምድ ሳሎን ፊልም እያዩ በዛው መተኛትን ልምዳችን አድርገን ነበር ያው ወደ ዩኒቨርስቲ ስገባ ቀረ እንጅ፡፡ አሁንም ሷሊህ ነቢ ስትመጣ ሳሎን ውስጥ ለብዙ ሰአት እናወራለን፡፡ አባቴ ኢሻን ከሰገደ በኃላ ብዙ የማምሸት ልምድ የለውም " በሉ ልጆች እኔ አርጅቻለሁ ወጣት ጋር አልቀመጥም ብዙ ረፍት ያስፈልገኛል" ብሎ ወደ መኝታ ክፍሉ ይገባል፡፡ እናቴ ትንሽ አወራርታን ብዙም ሳትቆም እሷም ትሄዳለች፡፡
      ያኔ እኔና ሷሊህ ብቻ እንቀር ነበር፡፡ አሁን ግን ነቢ ተጨምራ ሶስት ሆነናል፡፡ ደግነቱ እኔም ከአለሜ ጋር ስለሰርጋችን ሁኔታ እያወራሁ አመሻሁ እንጅ እንደ በፊቱ ቢሆን እንቅልፍ ሰለሚያሸንፈኝ እንተኛ በሚል ሰበብ ከነቢ ጋር ወሬያቸውን ሳይጨርሱ ባለያያቸው ሁለቱም ሳይረግሙኝ አይቀሩም፡፡ ነቢ ሷሊህን የማድነቅ ሰለሱ የማውራት አባዜ ይዟታል! ስለሱም የግል ሂወት ከኔ ማጣራት ትፈልጋለች፡፡ በተደጋጋሚ የሚወዳት ልጅ መኖር አለመኖሯን ለማጣራት በዘዴ ልታውጣጣኝ ሞክራ ወሬ አስቀይሻታለሁ፡፡
     በሷሊህ ሂወት ውስጥ ማንም ሴት እንደለለች አውቃለሁ ካለችም ደግሞ ራሷ ነቢ እንደምትሆን አምናለሁ፡፡

#የመጨረሻዉ #ክፍል

ይ..........ቀ........
.......ጥ.........ላ........ል

4another channal👇
@Islam_and_Science

JOIN👇👇👇
@IslamisUniverstiy_public_group
@IslamisUniverstiy_public_group
ሶስተኛው ፆታው

ወንዶች አሉ
እገሊት ሳይባል እንዲያው በጥቅሉ
ማንም ታማኝ የለም ከሄዋን ዘር ሁሉ
ከአፅናፍ እስካፅናፍ ብትታሰስ አለም
አጉል ድካም እንጅ የሴት ታማኝ የለም
..........................
ሁሉ ሴት አስመሳይ
ሁሉም ብር አምላኪ
የሃሰት ሊቅ ካህን የውሸት ሰባኪ
ጉዳቸው አያቅም ስንል ንውላለን
ከሴት ውጭ መኖር ከቶ ላይቻለን
............................
ሴቶች
የአዳምን ዘር ማመን ለካ ቂልነት ነው
ሞኝ መስሎ አካሉ ልቡ ግን እባብ ነው
ማር በሚያዘንብ አፉ ቃል የቀመረ
ዛሬ አንዷን ነገ አንዷን እየቀያየረ
ስንቱን የሄዋን ዘር በቁሙ ቀበረ
ሁሉም ፏፏቴ ነው ለስሜቱ አዳሪ
ታማኝ አዳም የለም እውነተኛ አፍቃሪ
ብለው ያወራሉ
................................
ታዲያ
ዘበት የማይነካው
የሚኖር ለእውነት
አጣምሮ የያዘ ፍቅር ታማኝነት
ከሁለቱም ጎራ ከሁሉም የማይሆን
ያ ሶስተኛው ፆታ ታማኙ ማን ይሆን
ፆታውስ ምን ይሆን
..................................
አብደል ከሪም የእናቱ ልጅ


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
"✔️💐 #የሕይወትህ #መርሆዎች በእነዚህ ላይ
የተመሰረቱ
ይሁኑ!"
❖አንብበዉ ሲጨርሱ # share ማድረጎን
እንዳይረሱ፡
.
⭐️ የፈለከውን ነገር ሁልጊዜ ላታገኝ ትችላለህ፡፡
ያገኘኸውን
ነገር መውደድን ግን ተለማመድ፡፡ መሻትህ ሁሉ
ላይኖርህ
ይችላል ያለህን መንከባከብ ግን አትርሳ፡፡
.
⭐️. ኑሮዬ ይበቃኛል ማለትን ተለማመድ፤ ኑሮዬ
ይበቃኛል
ማለት ስለ ግብህ ማሰብ አቆምክ ማለት
አይደለም፡፡
በዚህ ውሳኔ ማረፍ ቅሬታን ያርቅልሃል እምነት
ማጣትን
ያስወግድልሃል ተስፋ መቁረጥንና የተዛባ
አመለካከትህንም ያስተካክልልሃል፡፡
.
⭐️ አሳብህም ልብህም ሰፊ ይሁን፤
አመለካከቶችህ ሁሉ
ሁሉንም ነገር በቀናነት በመልካም ጎኑ
በመመልከትና
በማሰብ ላይ የተመሰረቱ ይሁኑ፡፡
.
⭐️ ሥራህንና ቃልህን ለማዛመድ ትጋ፡፡ ልብህና እጅህ
እርስ በእርሳቸው እንዳይጣረሱ ጥረት አድርግ፡፡
.
⭐️. ወሳኙ ነገር የምትኖርበት ቦታ ሳይሆን አኗኗርህ ነው፡፡
ከምታምንበት ነገርም በላይ ዋጋ ሊሰጠው የሚገባው ባመንክበት ነገር እንዴት ትኖራለህ የሚለው
ነው፡፡
.
⭐️. ሁላችንም በሕይወት ያለነው ደስተኞች
እንድንሆን
ነው፡፡ ለዚህም የፈጣሪን ድምጽ
አድምጥ፤ ለኑሮህ
ብልጥግና ፍቃዱን ተከተል፤ ስኬታማ ለመሆንም በእውነት ላይ ቁም፡፡
.
⭐️. እኛ ቀብረን የምናዝነውን ሀዘን ቆመው፣ እኛ ርቦን የምንሰቃየውን ስቃይ ጠግበው፣ እኛ አጥተን የምናነባውን
እንባ አግኝተው የሚያነቡት ብዙ ናቸው፡፡ ልዩነቱ እኛ ሁሉን
ለእርሱ ክብር ማድረጋችን ነውና ሁኔታዎችህንሁሉ ለእርሱ ክብር ማድረግን መልመድ ይገባሃል፡፡
.
⭐️ ማንም ሰው ከጠባቡ ግለኝነት ሕይወት ወደ ሰፊው ጠቅላላው የሰው ልጅ ምልከታ ከፍ እስኪል
ድረስ መኖርን ተማረ አይባልም፡፡ ማለዳ ማለዳ አዲስ ትርጉም ባለው
መንገድ ለመኖር ራሳችንንን ብቻ መመልከታችን
ወደ ፊት ከመመልከት ጋር ሊዋሐድ ይገባዋል፡፡
.
⭐️. ያለህን ስትሰጥ ጥቂት ሰጥተሃል፤ ራስህን ስትሰጥ ግን ያኔ በእውነት ሰጥተሃል እንደሚባለው የእኛን ብቻ
ሳይሆን እኛንም ለሌሎች ማካፈል አለብን፡፡ ለምሳሌ፦ ማየት
ለተሳነው ሰው መመልከት ቢችል ኖሮ
ሊያከናውን የሚችለውን እኛ ብናከናውንለት፣ መራመድለማይችል
ቢራመድ ኖሮ ሊሠራው የሚችለውን እኛ
በመራመድ ብንሠራለት፣ መናገር ለማይችለው መናገር
ቢችል ኖሮ የሚያስረዳውን አፍ ሆነን ብንናገርለት ይህ ራስን
ማካፈል ነው፡፡
.
⭐️. በፍቅር መግዛት በጥላቻ ከመግዛት፣
ብቸኝነትን ከመንከባከብ ሕይወትን ማጋራት አብዝቶ የተሻለ ነው፡፡
በትህትና ልንሠራው የምንችለውን መልካም ነገር በሸካራ ቃላቶች ልናውከው፣ በግለኝነት ልናፍነው
አይገባም፡፡

share 🔰share🔰
.
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸


👇Click & Join👇
══ •⊰✿✿⊱• ══
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science

ቤተሰብ ሼር አይዘንጉ
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
✔️አንተ ጠጥተህ በጣልከው #ሀይላንድ እግራቸውን የሚሸፍኑ ሰዎች ባሉበት አለም ውስጥ ሁነህ ለምን #ብራንድ ጫማ አልተጫማሁም ብለህ #አታማርር

✔️ልብ ብለህ ካሰብከውኮ ለውድ ጫማ የሚሆን በቂ #ገንዘብ ኑሯቸው ነገር ግን #እግር_የሌላቸው ሰወች ብዙ ናቸው ። ያለህን ነገር በአግባቡ ተጠቀም ባለህ ነገር #ደስተኛ እና #አመስጋኝ ሁን በተረፈ ለምታልመው ነገር መጣሩ አንጂ ማማረሩ መፍትሄ አይሆንም ።
አየህ #የሚጠቅምህ አሁን እጅህ ላይ ያለው ነገር እንጂ #አጣሁት ብለህ የምትማረርበት ነገር አይደለም ።

@Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
⚠️🚫 #ለሴቶች #ማስጠንቀቂያ🚫⚠️

🚫 #አንዳንድ #መደመር ሳይሆን መቀነስን ያነገባችሁ ሴቶች፡- እንደመር ስንላችሁ፡- አይሆንም፣አንፈልግም እያላችሁ ወንደ-ላጤ ሁነን እንድንቀር የፈለጋችሁ የአሸባሪን ጭንብል ያጠለቃችሁ ሴቶች ከዚህ እኩይ ተግባራችሁ ብትታቀቡ ይሻላል፡፡
😒😒
#የወንድን #መባከን የምትመኙ እድገቱን የማትሹ የዶላርና የብር ውድመት የሚስደስታችሁ ጥቂት የቀን ጅብ-ሴቶች☺️ ብትታቀቡ ይሻላችሀል 😉

⚠️ #ይሄ #የመጨረሻችን የወንዶች ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይችላል
#ከመጀናጀን_በሀላል_መደመር_ያዋጣናል

💟 #እኛ #ስንደመር
☞ቆንጆ ልጆች
☞ለኢስላም የሚጠቅሙ
☞ሰዉ የሚያከብሩ
ልጆች ይኖሩናል ኢንሻ አላህ

😳ግን ታዲያ፡-.........
የሽሮ የበርበሬ የዘይት የጨው እያላችሁ እየጎቸጎታችሁ መበቀላችሁ ልታቆሙ ይገባል #መበቀል #ትነሽነት #ነው፡፡

🚫 #በቀል #ትንሽ #ያረጋል ፡፡እኛ ትልልቆች ነን፡፡ ለዘዋጅ ደርሰናል😉

🚫 በቻት ብራችንን ከምንጨርስ በሀላል አላህ ባዘዘን መሰረት ለቤተሰቦቻችን አሳዉቀን በሀላል ትዳር እንደመር ይላሉ፡፡

😳እስከ አሁን በቻት የጨረስነዉ ብር አንድ ልጅ ወልደን እናሳድግበት ነበር😉

😍ግን ከአሁን ቡሀላ የማትስማሙ ከሆነ እኔ ጋር መደመር ወደ ምፈልገዉ ሂጃለሁ 🚶🚶

🙄አንዱ የኔ ብጤ ላጤ እንዲህ ብሎ በሳቅ ገደለኝ
ይኸው ስንት አመቴ፣
" #ያ አላህ! ሚስት ስጠኝ"
እያልኩ ዱዐ ሳደርግ!
አሁን ገና ነው ለምን እንደዘገየሁ የገባኝ!
ሚስቴ ኤርትራዊ ሳትሆን አትቀርም!
መታረቃችን እንዲሁ አጋጣሚ #አይመስለኝም!😂😂😂

🔊🔊እዚህ ቻናል ያሉትን ወንዶች ወክየ መልእክቱን እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያዉን አስተላልፊያለሁ፡፡

የሚወክለዉ🤙🤙


JOIN👇👇👇

@Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
ከቂያማ ምልክቶች መካከል የተወሰኑት # የሚከተሉት ናቸዉ !!!
አጅብ በርግጥ ቂያም # ከመድረስም
# አፍንጫችን ሰር ናት !!!
1 ዝሙት ይስፋፋል
2 ወንዶች ሀር ይለብሳሉ
3 ሙዚቃ እንደሚፈቀድ ይነገራል
4 ሴቶች ዘፋኞች በአጫዋችነት ይያዛሉ
5 መጥፎ ቃላቶችን መለዋወጥ ይበዛል
6 ዝምድናን መቁረጥ ይበረክታል
7 ታማኝ ሰዉን እንደ ከዳተኛ መቁጠር እና መወንጀል
8 ከዳተኛን ማገዝ እና ማቅረብ
9 ድንገተኛ ሞት መከሰት
10 መስጅድን እንደ መተላለፊያ መንገድ መጠቀም
11 ጥሪያቸዉ ወይም ተልእኮአቸዉ ተመሳሳይ የሆነ ሁለት ቡድኖች
ይፋ ጦር ይማዘዛሉ(የአልይ ና የሙአዉያዉጊያን ያመለክታሉ
12 የዘመን መቀራረብ ወይም የጊዜ መፍጠን (በረካ ማጣት)
13 ፈተናዎች ይደራርሳሉ ፣ተንኮል ይስፋፋል
14 ኢልም ከህፃናት ይፈለጋል
15 የመሬት መንቀጥቀጥ
16 ሰዉነታቸዉን አግባብ ባለዉ ልብስ ያልሸፈኑ ሴቶች ይበዛሉ
17 እዉቀት የሌላቸዉ ሰዎች ህዝባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ
ይወስናሉ
18 ሰላምታ በትዉዉቅ ላይ ብቻ ይመሰረታል
19 ዉሸት መናገር ይስፋፋል::
20 የንግድ ቤቶች ተቀራርበዉ ይገነባሉ።
21 ለሰይጣን አገልግሎት የሚዉሉ ግመሎች ና ለሰይጣን
አገልግሎት የሚዉሉ ቤቶች ይገነባሉ። ማለትም 1 አንድ ሰዉ
ከሚጠቀምባቸዉ ዉጭ ያሉ ግመሎች በስድ ሲለቀቁ ሰይጣን
ይጋልባቸዋል። 2 ከመኖሪያ ቤት ዉጭ ያሉ ትርፍ ቤቶች ለረጅም
ጊዜ ሰዉ ሳይገባባቸዉ ከቆዩ የሰይጣን መኖሪያ ይሆናል።
22 ሰዎች በመስጊድ ዉበት ይፎካከራሉ_በዉስጡ ይመፃደቃሉ።
23 ሺበታቸዉን በጥቁር ቀለም የሚያጠቁሩ ሰዎች ይመጣሉ።
እነዚህ ሰዎች የጀነትን ሽታ እንኮአን አያገኙም።
24 ሰዎች አላህን የመታዘዝ ባህሪያቸዉ ይመነምናል።ለአኬራ
መስራትም ይቀንሳል።
25 ስስት ይስፋፋል፣ሁሉም ሰዉ ግለኛ ይሆናል፣አዋቂ እዉቀቱን
ለማካፈል ይሳሳል።
26 ሰዎች አላማዉን በማያዉቁት ዉጊያ ዉስጥ ይሳተፋሉ
(ይጋደላሉ።)"ነፍሴ በእጁ በሆነዉ ጌታ እምላለሁ በሰዎች ላይ ይህ
ዘመን ይመጣል።ገዳይ በምን ምክንያት እንደገደለ አያዉቅም-
ተገዳይ በምን ምክንያት እንደተገደለ አያዉቅም።
27 የህዝብ ገንዘብ ያለ አግባብ ይመዘበራል።
28 አማና (ታማኝነት) ይጎአደላል።
29 ባል ሚስቱን እየታዘዘ እናቱን ይበድላል።
30 በአባቶች ላይ እየተፌዘ (አባት ሳይከበር) ጎአደኛ ይከበራል።
31 በመስጅድ ዉስጥ ጩሀት ይበራከታል።
32 ተንኮሉ ተፈርቶ ሰዉ ይከበራል-ችሎታና ስነ-ምግር ግን
የለዉም።
33 ፖሊስ ይበዛል፤ይህም ማለት ወንጀል መበራከቱን
ያመለክታል።
34 አንድ ሰዉ በእዉቀቱ አናሳ ሆኖ እና በባህሪዉም ገና ያልተገራ
ሆኖ ሳለ ድምፁ የሚያምር ሆኖ በመገኘቱ ብቻ ሶላት እንዲመራ
(እንዲያሰግድ) ይደረጋል።
35 ሚስት ባሏን በንግድ እና በስራ ላይ ትጋራለች።
36 ብእር ይበራከታል፤ድርሰት እና ህትመት ይስፋፋል።
37 ልጅ መመኪያ መሆኑ ቀርቶ መተከዣ እና መቆጫ ይሆናል።
38 የዝናብ እጥረት ይስተዋላል።
39 መኪና ይፈለሰፋል። "ከኡመቶቼ መካከል ወደ መጨረሻዉ
የሚመጡት 'ሱሩጅ ወይም (መኪና) ላይ ይሳፈራሉ። የመጎጎዣ
አይነት ነዉ በመስጅድ በሮች ያቆሙታል (ይወርዳሉ) ሴቶቻቸዉ
ግን የለባሽ እርቃን ናቸዉ።
40 ፊትና በመብዛቱ ሳቢያ ሞትን መመኘት።
41 ኢራቅ ማእቀብ ይጣልባታል-ምግብ ና እርዳታ ትከለከላለች።
42 በመቀጠልም ሻም (ሶሪያ፣ሊባኖስ፣ዩርዳኖስ እና ፍልስጤም)
ምግብና እርዳታ ይከለከላሉ ማእቀብ ይጣልባቸዋል።
43 የነብዩ ሙሀመድ (ሶ.አ.ወ) ከዚህ አለም በሞት መለየት እንደ
አንድ የቂያማ ቀን መድረስ ምልክት ተወስዷል።
44 በይተል መቅደስ (እየሩሳሌም) በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር
መግባት።
45 በጅምላ ጨራሽ በሽታ ሆነ ጦርነት የሰዉ ህይወት
መጥፋት።
46 ሙስና፣ማጭበርበር እና የዋጋ ንብረት እያየለ መምጣት።
47 በአረቦችም ሆነ በሌሎች ወገኖች ቤት ዉስጥ ጣልቃ ገብነት
እና ፊትና(መከራ) ይስተዋላል።
48 በሙስሊሞች እና በሮማዉያን(አዉሮፓ እና አሜሪካ) የጋራ
ስምምነት ይፈረማል። አዉፍ ኢብን ማሊክ (ረ.አ) እንዳስተላለፉት
የአላህ መልእክተኛ (ሶ.አ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦
# የቂያማ ቀን ከመድረሱ በፊት # ስድስት ነገሮች # ይከሰታሉ
1 የኔ ሞት
2 ከዚያም በይተልመቅዲስ ይከፈታል
3 ከዚያም ሁለት ሞት እዉን ይሆናል
4 አንድ ሰዉ መቶ ዲናር ቢሰጠዉ እንኳን ምንም አይመስለዉም
5 ከዚያ በሁላ ደግሞ ፊትና ይከሰታል።
6 ከዚያም በናንተና በነጮች መካከል ስምምነት ይኖራል።
ይከዷችሁል ።
80 አላማ ይዘዉ ይመጣሉ እያንዳንዱ አላማ ደግሞ 12 ሺህ
(ንኡስ አላማ) አለዉ።
ያአላህ እዘንልን ከምናውቀውም

﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
የዑመር ኢብኑልኸጣብ (ረዐ) 20ምርጥ ምክሮች፤
.
1. ‹የምትጠላውን ሰው ተጠንቀቅ፤›
2. ‹ብልጥ ሰው የእለት ስራዎቹን ከራሱ ጋር ይተሳሰባል፡፡
3. ‹የዛሬን ስራ ለነገ አታሳድር፡፡›
4. ‹ከሰዎች ጥያቄ ተነስተህ አስተሳሰባቸውን መለካት ይቻላል፡፡›
5. ‹ለሌሎች ዳዕዋ በምታደርግበት ወቅት እራስህን አትርሳ፡፡›
.
6. ‹ከዱንያ ትንሽን ብቻ ስትፈልግ ይበልጥ ነፃነትን እያገኘህ ትሄዳለህ፡፡›
7. ‹ወንጀል አለመስራት ከፀፀት ይሻላል፡፡›
8. ‹ታጋሽ ሁን፤ ትዕግስት የእምነት ምሶሶ ነችና፡፡›
9. ‹አሏህን ፈሪ መሆን እድለኛነት ነው፤ ከዚህ ውጭ ያለው እድለቢስ መሆን ነው፤›
10. ‹ወደ አኺራ የሄዱ ሰዎችን ንግግር ጠብቁ፤ እነርሱ የተናገሩት አሏህ እንዲናገሩ ያገራላቸውን ብቻ ነውና፡፡
.
11. ‹አሏህን ፍራ፤ እርሱ ሁሌም ህያው፤ ከርሱ ውጭ ያሉ ሁሉ ጠፊ እና አላቂ ናቸውና፡፡
12. ‹ጥፋቴን በነገረኝ ሰው ላይ የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡
13. ‹እውቀትን ገብያት፤ ከዚያም ለሰዎች አስተምር፡፡›
14. ‹የተከበርክ፣ ታማኝ እና እውነተኛ ሁን፡፡›
15. ‹ትምክህተኛ ምሁር አትሁን፤ ትምክህተኛነት እና እውቀት አንድ ላይ አይሄዱምና፡፡
.
16. ‹ለዚህች አለም ፍቅር ያለው አዋቂ ባየህ ግዜ እውቀቱ አጠራጣሪ መሆኑን ተረዳ፡፡›
17. ‹ትንሽ አውርቶ ብዙ በሚሰራ ሰው ላይ የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡›
18. ‹ታማኝነት ማለት በምትሰራው፣ በተናገርከው እና በምታስበው ነገሮች ልዩነት አለመኖር ማለት ነው፡፡
19. ‹የሰው ልጅ ምንም እንኳ እንደ ቀስት ቀጥ ያለ ስራ ቢሰራ ተቃውሞ አያጣውም፡፡›
20. ‹አዕምሮህ እንዲሰፋ ከፈለግክ፤ ከፈሪሀ አሏሆች ጋር ተቀመጥ፤›
ወዳጆችዎን ሼር በማድረግ ያካፍሉ
በቴሌግራም ጆይን አድርገው በተለይ ጽሁፎችን ያግኙ
👇👇👇

﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄