ISLAMIC SCHOOL
12.5K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
ሲሳካልህ

ከፍ ብለህ በቁሰ በጊዜያዊ ነገር
በውድ ጌጣጌጥ ሰትዋብ ዘወትር
ሳለህ በምቾት ገንዘቡ ሞልቶልክ
በወዳጅ ዘመዶች ዙሪያህን ታጅበክ
ባላወከው ጉዳይ ያልገባህ በቅጥ
እንዲሁ በወኔ አሰተያየት ብትሰጥ


አንተን ተጋፍጦ ሰህተትህን የሚነግር
ድፍረትን አግኝቶ ከአንጀቱ የሚመክር
ነብሱን አሸናፊ ለህሊናው የሚያሰብ
ማደር የሚመርጥ ጥሬ በመጠግብ

ጥፋት አሰታዋሸ ጥቂት ነው ሰነግርክ
ከልቡ የሚቆጣ ያለጥቅም ወዶክ
እንደ ባህላችን ሰውን ለማሰታረቅ
ጥንዶችን ለመዳር ወጉን በመጠበቅ
እድሜያቸው የገፋ ነበር የሚመረጥ
ገንዘብ ሆኗል ዛሬ ክብር የሚያሰጥ


አፍላ ወጣት ሆነህ አንሰህ በእድሜ
ለፍቅር ለቁጣ ሲያሰፈለግ ሸማግሌ
አዋጅ ሳይጎሰም ደንቡ ይለወጣል
ሰለ አንተ ሲባል ሁሉም ይቀየራል
ሲሳካልህ ወንድም በቀኝ እና በግራ
ወቃሸህ አንሶ ዝናህ ግን የሚያወራ
ብዙ ነው ወዳጄ ምንም አትጨነቅ
አለም እንዲ ናት በሞቀበት ምትሞቅ



@Islam_and_Science @Islam_and_Science
🎖አስተሳስብህ ካለባበስህ የበለጠ ሲያምር

☞መልካምነትህ ከምትቀባው ሽቶ የበለጠ ሲያውድ

☞ስነ ምግባርህ ከመልክህ የበለጠ ሲያምር

☞የዝነጣ ጣሪያ ላይ ደርሰሀል ማለት ነው።ከምር!
ላመነን ሰው መታመን ከህሊና ወቀሳ መዳን ነው
.ለፍቅር የገባነውን ቃል መጠበቅ ጀግንነት ነው

💐እውነት ሁል ጊዜ እውነት ናት
የሰው ልጅ መልክ ማማር ሀብት ንብርት ሳይሆን ውበቱ

💐ግልጽነቱና ቅን መሆን እራሱ ውበት ነው ውስጣዊ ማንነቱ።
ቅናነትን ያድለን!

ISLAM AND SCIENCE
══ •⊰✿🍃✿⊱• ══

🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😔 #ተስፋ #ያጣች #ሴት😢
እውነተኛ ታሪክ
#ክፍል 3⃣
...
#የእንጀራ አባቷ ቴድሮስ በስካር መንፈስ ሀናን ሊደፍራት
ሲታገል የውጪው በር መንኳኳቱን እንኳ አልሰማም ነበር ሀናም
የሚያንኳኳው ሰው በሩን ከፍቶ እንዲገባ በልቧ እየፀለየች
አይኗን ወደ በሩ ተክላ ቀረች ቴድሮስም ስሜቱን መቆጣጠር
#አቅቶት እሷን መታገል አቁሞ ልብሱን ለማውለቅ ሲነሳ ሀና
ካለችበት ተነስታ አልጋው ላይ ቆመችና ያለ የሌለ ሀይሏን
ተጠቅማ ገፈተረችው እሱም በመጠጥ ስለዛለ እዛች ጠባብ
ክፍል ውስጥ በጀርባው ወደቀ ሀናም ሮጣ ለመውጣት ካልጋው
ወርዳ ጫማዋን በማድረግ ላይ ሳለች #የሀና እናት አፀደ በሩን
ገፋ አድርጋ ገባች ሀናም ልክ ሰርቆ እንደተያዘ ሰው ክው ብላ
ደርቃ ቀረች ... አፀደም በድንጋጤ ምን እንደተፈጠረ ስትጠይቅ
ሀና ግን ምን እንደምትመልስ ግራ ስለገባት ዝምታን መረጠች
... የአፀደን መምጣት ስላየ እየሳቀ ነገሩን አስቀየሰ
...
ቴድሮስ ከዛ ግዜ ጀምሮ ሀናን እንደ ጠላት ያያት ጀመር ሁሌም
ሀና አንድ ነገር ስትናገር ለሱ አይጥመውም አፀደም ልጇን
እጅግ ስለምትወዳት ያ ቀን ተሸፋፍኖ ቢያልፍም ከዛ ቡሃላ ግን
ማታ ማታ ብቻቸውን ትታቸው #አትሄድም ... ይህ በንዲህ እንዳለ
ሀና የዘጠነኛ (9ኛ) ክፍል ትምህርቷን ጀመረች ይሄኔ አንድ የሴት
ጓደኛ ያዘችና አብረው መሄድና መምጣት እንዲሁም እረፍት
ሲሆኑም መገናኘት ጀመሩ የሀና ጓደኛ #ሶፊያ እጅግ በጣም ፀባየ
ሰናይ የምትባል ልጅ ነበረች በዚህም ነው ሀና ዱርዬ ጓደኞቿን
ትታ ሶፊያን መምረጧ...
አንድ እለተ ሀሙስ ሀና ከትምህርት ቤት ስትመለስ እናቷ
ከእንጀራ አባቷ ጋር በጣም ሲጨቃጨቁ ደረሰች ይሄን ስታይ
በጣም ተጨነቀች ደግሞ ሁሌም ቢሆን #አፀደና #ቴድሮስ
የሚጣሉት በሷ መሆኑን ታውቃለች ስለዛም " ደሞ ምን አረገች
ብሎ ይሆን?" ብላ መጨነቋን ቀጠለች ሀና የሚያሳስባት ነገር
ቢኖር እናቷ ስትበሳጭ ወይንም ስትናደድ በጣም ትታመማለች
ለዚም ነው ይሆዷን በሆዷ ይዛ የምትሰቃየው ... ሀናም እቤት
ገብታ ዩኒፎርሟን እየቀየረች የጭቅጭቃቸውን መንስኤ ለማወቅ
ማዳመጥ ቀጠለች ይሄኔ ነበር የገባት ትላንት ምሽት አምሽታ ስትመለስ አንድ የሰፈራቸው ጎረምሳ ሀናን
ሰላም ይላታል ይሄን ቴድሮስ ተመልክቶ ስለነበር ነው ለአፀደ
"ልጅሽን ስትንዘላዘል አየኋት ለምን አትቀጫትም...ወዘተ " እያለ
ይነዘንዛት የነበረው ... ሀናም ይሄን ስትሰማ ሽምቅቅ አለች ሀና
እንኳን ከወንድ ጋር ልትንዘላዘል ወንድ ጓደኛ እንኳን የላትም!
ይሄ "ልጅሽ ተንዘላዘለች..." የሚለው ወቀሳ ሲበዛባት አፀደ
ሀናን ለመምከር ቴድሮስና ትንሹ የሀና ወንድም የማይኖርበትን
ሰአት መረጠች ... ከዛም ለሀና ያዳለፈቻቸውን ችግሮችና የሀና
አባት ልጅ እያለች ደፍሯት ሀና እንደተረገዘች ...በመንገር ሀና
እንድትቆጠብና ያለድሜዋ አጉል ቦታ እንዳትወድቅባት
ማስጠንቀቂያ አዘል ምክር እንባዋን እያዘነበች ሰጠቻት ሀናም
ከመቼውም በላይ ለእናቷ ያላት ፍቅርና ሀዘኔታ ጨመረ እናትና
ልጅ ተቃቅፈው አለቀሱ...
ሀናም "እማዬ እርግጠኛ ነኝ አንድ ቀን አኮራሻለው" አለቻት
እናትም በስስት እያየቻት "ሀና ልጄ ያንቺን ስኬት አይቼ ብሞትም
ቅር አይለኝም"... አለቻት
ሀና የአስረኛ ክፍል ትምህርቷን ልትጀምር ጥቂት ወራት ሲቀራት
እናቷ ኑሮን ለማሸነፍና ባሏን ለማገዝ ሻይ #መሸጥ #ጀመረች
ይሄኔ ሃናም እናቷን ለማገዝ ከትምህርት መልስ አብራ ሻይ መሸጥ
ጀመረች ይሄኔ ቤታቸው ሻይ ለመጠጣት ስበብ የዱርዬ መአት ይመጣ ጀመር ... በዚም
ሀና ትምህርቷን በስርአት መማር አልቻለችም በዛ ላይ ደግሞ
በተደጋጋሚ የእንጀራ አባቷ መነዝነዙን ቀጠለ...
አንድ ቀን ሀና ብቻዋን ቤት ስትጠብቅ ሻይ የሚጠጡ 7
ጎረምሶች መጡ ይሄኔ ሀና ሁሌም እንደምታደርገው ሻይ  ቀድታላቸው ተቀመጠች እነሱም ሻያቸዉን ጠጡ ሻይ ከመጠጣታቸዉ 6ቱ በፊት አስካሪ መጠጥ ጠጥተዉ ነበር፡፡ ሀናንም ለመድፈር ይጠቃቀሱና ይተናኮሏት
ጀመር ጀመሩ ሀናም በጣም ፈርታ እንዲወጡ ትነግራቸዋለች
አለቻቸው እነሱም  ዉጡ ካልሽን ሻይ የጠጣንበትን አንከፍልም አሉ፡፡ በዚ
መሃል አንከፍልም ክፈሉ ሀና ያላቅሟ እያለቀሰች እናቴ ትቆጣኛለች ከፍላችሁ ዉጡ እያለች ስትሟገት
ከመሃላቸው አንዱ አባብሏት ብሩን በሙሉ ከፍሎ እንዲወጡ
አረጋቸው ከዛ ቡሃላ ሀናም ልጁ ላይ ቀልቧን ጣለች እሱም
እሷን ብሎ መመላለስ ጀመረ ምንም ሳይባባሉ ባይናቸው
ያወራሉ እጇን እንኳን ሳይነካት በፍቅሯ ክንፍ አለ እሷም ለሱ
#የተለየ #ስሜት ይሰማት ጀምሯል...

_ #ክፍል 4⃣

.....ይ
.........ቀ
..............ጥ
...................ላ
.........................ል

ሼር ማረግ አንዘንጋ

telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science






ዝለቋት😉👉Read more.......
👍1
#ሶላት #የማይሰግድሰው #አንገት #እንደሌለውነውእሚቆጠረው

💚ነብዩ ሙሀመድ(ሰ.አ.ወ)
ሶላትን የመተው አደጋው
የአደምልጅ ሆይ
☞ስትወለድ ጆሮህ ላይ አዛን ይባልብሀል
☞ስትሞት ሶላት ይሰገድብሀል
☞በዱኒያ ላይ ሂወትህ ከአዛን እስከ ሶላት እንዳለው ጊዜ ነው ስለዚህ ሳይሰገድብህ ስገድ ጊዜህን በማይጠቅምና
❖ባልባሌ ቦታ አታሳልፍ
❖መቆያህን መስጅድ መረጋጊያህን ቁርአንን አድርግ።

💠አላህ ሱብሀነሁወተአላ ሶላትን ደንግጓል።
የኢስላምም ምሰሶና አስኳል አድርጎታል።
ነቢዩ ሙሀመድም( ) እንዲህ ብለዋል ፦ የነገሩ ሁሉ ራስ ኢስላም ነው።ሶላት ምሰሶው ነው። ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ጂሃድ ደግሞ ጣራው ( ሻኛው) ነው።
ከኢባዳዎች ሁሉ በቅድሚያ ግዴታ የተደረገው ሶላት ነው።

⭐️ነቢዩ ወደ ሰማይ ባረጉበት ሌሊት ።አዎ በዚያች በተከበረችወወ ሌሊት ያለማንም አገናኝ ( መልእክት አስተላላፊ) አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ ነቢዩን የሶላትን አስፈላጊነትና ግዳጅነት በቀጥታ አሳወቃቸው ። ለዚህ ነው ሶላትን ሆን ብሎ የተወ ሰው ወደ ክህደትና ጥመት ደረጃ ደርሷል ወይም ከሃዲ ነው የሚል ብይን የሚሰጠው ።
🌙🌙በርግጥ ከሶላት የራቀ ሰው

☞ከኢስላም ርቋል ፤
☞ጌታውን አስቆጥቷል ፤
☞ራሱንም ለጥፋት ዳርጓል ፤
☞መልካም ስራውንም አውድሟል ።

💚የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ፦ በአንድ ሰውና በክህደት መካከል ( መለያ የሚሆነው) ሶላት መተው ነው።
ኢማሙ አህመድ እና ሌሎችም ቡረይዳ( ረ ዐ) የተባሉትን ሰሃባ ( ረ ዐ) ጠቅሰው እንደዘገቡት ነቢዩ እንዲህ ብለዋል ፦ በኛና በነርሱ ( በከሃዲዎች) መካከል ያለው ልዩነት ሶላት ነው ። ሶላት የተወ ሰው በርግጥ ክዶአል ።

🌙አብደላህ ኢብን ዑመር ( ረ ዐ) እንዳወሩት የአላህ መልእክተኛ ( ) ስለ ሶላት የሚከተለውን ብለዋል ፦ ሶላትን የጠበቀ ለርሱ ብርሃን ማስረጃና ነፃ መውጫ ይሆነዋል ።
▶️ሶላትን ያልጠበቀ ለርሱ ብርሃን ፣

ማስረጃና ነፃ መውጫ አይኖረውም ። በእለተ ትንሳኤ ከቃሩን፣
ከፊርኦውን እና ከኡበይ ኢብኑ ኸለፍ ጋር ይሆናል ( ይጎዳኛል) ።

🌙አላህ ተከሳሪወች አያድርገን ከጀሀነም ቅጣትም እሱው ይጠብቀን አንተ አዛኝ ነህና እዘንልን የአላህ


┏━ 🍃 ━━━━ 🍂 ━┓
🎖ISLAM AND SCIENCE🎖
┗━ 🍂 ━━━━ 🍃 ━┛


T..➳ telegram.me/Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/Islam_and_Science
👍1
👩‍❤️‍💋‍👩 #ባለቤትሽን #አመስግኚ!

💐ባለቤትሽን ስለ መልካምነቱ ማመስገንሽ ፍቅራችሁን ከማጎልበቱና እሱን ለበለጠ መልካምነት ከማበረታታቱ ባሻገር አላህን ማስደሰት ነው!!
قال صلى الله عليه وسلم : (لا ينظر الله إلى امرأة لا تشكر لزوجها و هي لا تستغني عنه) رواه النسائي و صححه الألباني في الصحيح 289
💚የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «ከባሏ የማትብቃቃ ስትሆን ባሏን የማታመሰግን ሴት፣ አላህ በእዝነት አይኑ አይመለከታትም።” ኢማሙ ነሳኢ ዘግበውታል፤ አልባኒም ሰሒህ ብለውታል


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😁ለፈገግታ ወቅታዊ ጉዳዮች
#የትናንቱ #መግለጫ #ፉገራወች

ፉገራ ዘ ሜቴክ

😁ወይ ሜቴክ ሀገር በቀል ነው ያሉህ !ለካ ሀገር ነቀል ነህ....

😁አቃቤ ህግ ስለ ደህንነት መስሪያ ቤቱ ጭካኔ መግለጫ ሲሰጥ ሰይጣን
እንኳ ገርሞት ማስታወሻ ሲይዝ ነበር።

😁ለካ ስብሰባው በፕላዝማ ይሁንልን ያሉት ይችን ስለሚያውቁ ነው!!

😁እስኪ ሁላችንም ኩላሊታችሁ መኖርና አለመኖሩን አረጋግጡ እኒህ ሰዎች
እኮ የቀራቸው የለም ??

😁የስርቆታ ስርቆት ኮርፖሬሽን!
ሜቴክ!

😁ህዝቤ ሆይ በጠፋው ኮንዶሚንየም አትገረም የጠፋም አውሮፕላን አለና!!

😃አዉሮፕላን መጣ እየገሰገሰ
METEC እንዳይሰርቀዉ ዞሮ ተመለሰ

😃ልጅ፦ አባዬ ስልኬ ፓኬጅ በጣም እየበላብኝ ነው
አባት፦ ስልኩን ከ ሜቴክ ነው እንዴ የገዛከው?

😄8100 A ብለው ይላኩና አባይን ይገድቡ ምናምን እያሉ ለሜቴክ
አስበልተውን የተቦጨቀላቸው አርቲስቶች ግን ሃብታቸው አሁንም የህዝብ ፍቅር
ነው አደል!?


😄እኛ ሲሰረቅ እምናቀው መኪና ምናምን ነው ከዛ ታርዶ ወደ ሰማሌ ተራ
እነሱ እቴ
ክሬን አውሮፕላን መርከብ ጋር ናቸው
የምን ሱማሌ ተራ ሱማሌ ኤርፖርት እና ሶማሌ ወደብ ላይ ናቸው!!

😄ሜቴክ ያልዘረፈው ቅኔ ብቻ ነው!!

😃አይ ንቢቱ ያልነደፈችው አበባ የት አለ?

😃 ቢሊየን ዶላር ዝርዝር ሳንቲም እንዲመስለኝ ላደረጋችሁኝ የሜቴክ
ጀነራሎች አመሰግናለሁ!!

😁"ሰባት ድብቅ እስር ቤቶች በአዲስ አበባ ተገኝተዋል።"......OMG ሰውየው
ጓንታናሞ እላለሁ ብሎ
ነው በሉኝ!!

😁"ሌብነት ስራ ነው... እስካልተያዝክ ድረስ" የሜቴክ God father !
That was the beginning !!

😃ተሰረቀ፡ቢሉኝ፡ግድቡ ነው ብየ ? ተዘረፈ ቢሉኝ ባቡሩ ነው ብየ ተዘረፈ ቢሉኝ
መርከቡ ነው ብየ ተዘረፈ ቢሉኝ ስኳሩ ነው ብየ
ተዘረፈ ቢሉኝ ሲሚንቶው ነው ብየ
ተዘረፈ ቢሉኝ አውቶቢስ ነው ብየ
ፕሌንም ተዘርፎአል እረ እናንተ ሆየ ።😂😂😂😂😂😂


😉ፈጣሪ ይህን ሁሉ ጉድ እያየ ዝም እንደሚለው እንደ # ሃይለማርያም
ደሳለኝ ያለ ልብ ስጠኝ!!


😉😉ማጠቃለያ

 ልጅ ,,,, አባየ #ጅብ ይበላል እንዴ ???
.
.
.
.
.
#አባት ,,,, አየ ልጄ መበላቱ ቀርቶ #መባላቱን ባቆመልን
#ለቀን_ጅቦች_መታሰቢያ

ገና በዶክተር አብይ ብዙ ነገሮች እንሰማለን ኢንሻ አላህ ፡፡

JOIN👇👇👇

telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
1
#ተስፋ #ያጣች #ሴት
#ክፍል 4⃣

#ሀና ምንም እንኳ ወንድ ልጅ ብትጠላ ባለፈው ስታለቅስ
ያዘነላትና ከጓደኞቹ ይልቅ እሷን መርጦ ከጥቃት ያዳናትን ወንድ
ከልቧ ቦታ ሰታዋለች ከትምህርት ቤት መልስ ወደቤት ስትመለስ ሻይ ሊጠጣ በመጣ ቀን ልጁን እስክታየው ትጓጓለች ከሱ ጋር መተያየት
#ብቻ ደስ ይላት ነበር። #ምናልባት እንኳ ልጁ ከሴት ጋር ስልክ
ካወራ ውስጧ የቅናት መንፈስ ሲሰማት ይታወቃታል ... ልጁ
ኪሩቤል ይባላል የሀብታም ቤተሰብ ልጅ ሲሆን መልኩም እጅግ
በጣም ቆንጆ ነው ሀና እንኳ አይኗ እያየ ሴቶች ሲጣሉበት
#አስተውላለች ግን ይህም ሆኖ ይህችን ተስፋ ያጣች ምስኪን
ታዳጊ ሴት ለውበቷ ቀርቶ ለነገዋ የማትጨነቅ ሀናን ማፍቀሩ
ለሃና ህልም ሆኖባታል በርግጥ ዱርዬ ነው ትምህርቱን ትቶ
ከሰፈሩ ልጆች ጋር የተለያዩ ሱሶችን ሲጠቀም ነው የሚውለው
ግን ከአባቷ አልፎም ከእንጀራ አባቷ ያላየችውን ፍቅርና እርህራሄ
እሱ አይኖች ውስጥ ታነባለች...
#አንድ #ቀን ሀና የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመሆኑ ከትምህርት
ቤት በቶሎ ተመለሰች ግን ያየችውን ማመን አቃታት እናቷ
አፀደና ቴድሮስ ተጣልተው ጎረቤት ተሰብስቧል በጣም ደንግጣ
ስትገባ እናቷ ታለቅስ ነበር ሀናም አብራት እያለቀሰች ከጎኗ
ተቀምጣ የሚሆነውን ማየት ጀመረች ቴድሮስም ለሽማግሌዎቹ
"ይሄን ሻይ መሸጥ  ካላቆመች በፍፁም አብረን አንቀጥልም"
ይላል እናቷም "ታድያ ምን ልስራ ተቀምጬ ያንተን እጅ
ስጠባበቅ ልኑር?" ትላለች በርግጥ ስራው እናቷን ቀርቶ ሀናንም
ጎድቷታል ግን ደግሞ ባታቆም ደስ ይላታል ምናልባት ከኪሩቤል
ጋር መገናኘታቸው ስለሚያበቃ ሀና የእናቷን ሻይ መሸጥ
ትደግፈዋለች ...: #በዛ መልኩም ብዙ ከተጨቃጨቁ ቡሃላ
ሽማግሌዎቹ እሷ እንድታቆም ወስነው አስማሟቸው....
ይህ ከሆነ ከ2 ወር ቡሃላ ሀና የ10ኛ ክፍል ማትሪክ ውጤት
ልትቀበል ወደ ትምህርት ቤት ሄደች የእንጀራ አባቷ በርግጥም
አሁን እንዳለፈው ግዜ "ካልደፈርኩሽ" አይልም ነገር ግን እሷ
ያለፈውን መርሳት ፈፅሞ አልቻለችም በዛ ላይ አሁን ከአባትነት
ወግ ያለፈ ቁጥጥር ያደርግባታል ... ሀና ውጤት ስላልመጣላት
እጅግ በጣም ተናዳ እያለቀሰች ወደ ቤት ስትመለስ ሶፍያን
ከአንድ ቆንጆ ወጣት ጋር ቆማ አገኘቻት ሶፊም አቅፋት
#እያባበለቻት መከረቻት ከሶፍያ ጋር የነበረውም የአብስራ
የሚባለው ልጅ ይሄ የሷ ብቻ እድል እንዳልሆነ በመግለፅ ከዚ
ቡሃላም ጠንካራ ሆና እንድትማር ነገራት ... ሀና የአብስራን
በአይን ብታውቀውም ስለሱ ግን ምንም የምታውቀው ነገር
አልነበረም ሶፊያና ያብስራ ሀናን ሰፈሯ ድረስ ከሸኟት ቡሃላ ሶፍያ
" #መጣው" ብላቸው ወደሱቅ ጎራ አለች ያብስራም ሀናን ፈራ ተባ
እያለ "ሀኒ አላት ሀናም እንደመደንገጥ ብላ ቀና ብላ አየችው
ያብስራም ከኪሱ የተጣጠፈች ወረቀት አውጥቶ በእጁ ይዞት
የነበረው /ፍቅር እስከ መቃብር/ ልቦለድ መፅሃፍ ውስጥ
ከተተውና " #ቅድሚያ ይሄን መፅሃፍ አንብቢው ከዛም ስጨርሺ
ወረቀቱን አንብቢው" አለና ሶፍያ ወዳለችበት ሄደ ....
ሀናም ግራ በመጋባት ምን ሊሆን እንደሚችል እያሰላሰለች
ወደኋላ ዞር ስትል ቴድሮስ ከፊለፊቷ ቆሞ ሲመለከታት አየችው
በጣም ነበር የደነገጠችው እሱም ከግር እስከራሷ ከገላመጣት
ቡሃላ በፍጥነት ወደቤት ተራመደ ሀናም ገብቶ እናቷን አንድ ነገር
#እንደሚላት እርግጠኛ ሆና ተከተለችው ...ልክ ስትደርስ ልክ
እንደገመተችው እየጮኸ ነበር ሀናም አንገቷን ደፍታ በር ላይ
ቆመች #ቴድሮስም መፅሃፉን ከጇ ላይ በመንጠቅ ይሄውልሻ
ደብዳቤ ከመፃፃፍም ደርሰውልሻል በዛላይ ሰው አጥር ስር
... #እነዚ ስዶች አለና ዞር ብሎ ሀናን እንዴት ወንድም እህቱን
አፈቀርኩ ይላል ከስጋሽ ጋር እንዴት ትንዘላዘያለሽ ብሎ በጥፊ
መታት ሀናም ፊቷ በርበሬ መስሎ እንባዋ መንታ መንታ እየወረደ
" #ወንድም" የምትለዋን ቃል ደገመቻት ይሄኔ የሀና ወንድም
"እማዬ" ብሎ ጮኸ ዞር ሲሉም አፀደ #በድንጋጤ #ወድቃለች...
#part 5⃣

ይቀጥላል____


telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
እዉነተኛ ታሪክ

የታሪኩ ርዕስ
💧 #ማን #ከማን #ያንሳል 💧

#ክፍል 1⃣

#ፀሀፊ#አሚር
በIslamic university channal
          
ህይወት እኔ እንደጠበኳት ብትሄድልኝ ምንኛ በጣም ደስተኛ ነበርኩ ፡፡ ሰዉ ምን ይለኛል ብየ የምሰራዉ ስራ ልቤን ሸርሽሮ እስከ አሁን በሂወቴ ጠብሳ ጥያለሁ ግን አልሀምዱ ሊላህ .ሁሉም ለበጎ ነዉ፡፡
...... እስከ ከስሜ ልጀምርላችሁ ስሜ ሰአዳ ይባላል የምኖረዉ እናቴ ጋር ነዉ መርሳ በምትባል ትንሸ ከተማ ነዉ ፡፡ እናትን እና አባቴ ገና ነፍሰጡር እንደሆነች ነበር አባቴ ጋር የተፋቱት፡፡ የአደኩት እናቴ ጋር ነበር የሂወት ዉጣ ዉረድ በእኔ እና በእናቴ ላይ ብዙም ባይባል አሳልፈናል፡፡ ለእናቴም ለአባቴም አንድ ፍሬ ልጅ ነኝ ፡፡ አባቴ ከእናቴም ጋር ቢለያዩም አንዳንድ አስቤዛዎች ይረዳን ነበር፡፡
.......የእናቴ የወደፊት ህልሟ እኔ ነኝ ሌላም ልጅ የላት በዲኔ ጠንክሬ በትምህርቴም ጎበዝ ሁኜ እንድታየኝ ምኞታ ነበር፡፡ እናቴ ቁርአን አልቀራችም .......,ሰአዲ እኔ ቁርአን ባለመቅራቴ አሁን ድረስ እቆጫለሁ ልጄ አንችዉ ነሽ ያለሽኝ ቁርአንገቀርተሽ እንድታከትሚ ብላ ቃል አስገባችኝ
.........በትምህርቴም በጣም ጎበዝ ባልባልም ሰነፍ ከሚባሉትም አይደለሁም ብቻ ተስፋ አለኝ ፡፡ ከአንድ ጀምሬ የተማርኩት እዛዉ መርሳ የሚገኝ ትምህርት ቤት ነዉ፡፡   እድሚየም 17 አመቴ ነዉ፡፡

.......... የምነግራችሁ እዉነተኛ ታሪክ ሰባተኛ ክፍል እንዳለሁ የተጀመረ ነዉ፡፡ #የሴት ጓደኞቼ ከ 5 ክፍል ተማሪ እያለሁ  ጀምሮ ጀሚላ ሀይባ ሀያት ብርቱካን እና ቢንስ  5 ያላነሱ ጓደኛ ነበሩኝ በጣም የምንዋደድ ጓደኛ ነበርን ግን የምንዋደደዉ ለአላህ ብለን ሳይሆን እንደ ክላስ ጓደኝነት እና የሰፈር ጓደኝነት የፌክ ነዉ ፡፡

.....ትምህርት ስንሄድ ወሬያችንም እከሌ የእከሌ ፍቅረኛ ናት የእናትና ጓደኛ እንትና ናት ዛሬ እሱ እንደዚህ አረገ እሷም እንደዚህ አረገች ወ.ዘ.ተ ስለሆነም በቃ እኛም ጓደኛ መያዝ አለብን ፡፡ መቼ ድረስ ፋራ እንሆናለን እያሉ ወሬያቸዉ በቃ የወንድ ጓደኛ ይዘን የአራዳ ልጅ መባል አለብን ብለዉ አሰቡ ሰባተኛ ክፍል ስንደርስ የመጀመሪያ አላማችን የወንድ ጓደኛ መያዝ ነዉ ብለዉ ለራሳቸዉ ቃል ገቡ ይገርማል ሰዉ በትምህርቴ እጠነክራለሁ ዉጤት አሻሽላለሁ ይላል እንዴት ሴት ሆኖ የወንድ ጓደኛ መያዝ አለብን ይባላል ?፡፡ ሀያእ ጠፍቷል ለነገሩ ቁርአን ቅሩ ሲባሉ እምቢ ነበር የሚሉት
.
.....አስበዉ ብቻም አልቀሩም ሰባተኛ ክፍል ሲደርሱ  አላማቸዉ ጓደኛ መያዝ ስለነበር ቀመር መቀመር ጀመሩ ፡፡ ይች አለም ላይ ስንኖር ከተለያዩ ልታይ ልታይ ዝንባሌዎች እራሳችንን ማራቅ አለብን ፡፡ እኔ አረ ተዉ ይቅርባችሁ ብላቸዉ ፡፡ አንቺ ነሽ ሁሌም ፋራ ነሽ አንቺ አይገባሽም ጊዜዉ ጋር አብረሽ መጓዝ አለብሽ ፡፡ አለዛ አንቺ መቼም ቢሆን ወንድ አይፈልግሽም ፡፡ሰዉ በአለፈዉ ሂወቱ መኖር የለብትም አንድ እስቴፕ ከፍ ማለት አለብን ብለዉ አኔን እንደፋራ ያዙኝ እነሱ እንደ አራዳ እራሳቸዉን ቆጠሩ ፡፡ እኔስ ቁርአኔንም እየቀራሁ ስለ ነበር ስለዲኔ አቃለሁ ብመክራቸዉ በመከርኳቸዉ ቁጥር ስድባቸዉ ፉገራቸዉ አላስቀመጡኝም ነበር፡፡
....... ወይ ስልጣኔ ለሰዉ ብሎ የሚኖር ህዝብ ... ከዛም ወንዶችን ተማሪ በተለያየ ዘዴ መቅረብ ጀመሩ.... እነሱ ጋር መፎጋገር መቀላለድ መበሻሸቅ ጀመሩ፡፡ ቦይ ፍሬንድ ለመያዝ  ከትምህርት ስንሄድ ስንመለስ መቀመር ጀመሩ ፡፡ የአሁን ወንዶች እንኳን ቀርበናቸዉ ወደ እነሱ ሂደን ሳንሄድ እንኳን ሴቶችን ለማጥመድ ቆርጠዉ ተነስተዋል ያስብላል፡፡
......በሂደት ጓደኞቼ ፍቅረኛ ያዙ እኔ በፋራ ተያዝኩ፡፡ #ጓደኞች መጀመሪያ ፍቅረኛ የያዙት እኔ በጣም የምቀርባቸዉ ጓደኞቼ  #ሀይባና #ጀሚላ ነበሩ እነሡ የወንድ ጓደኛ ሲይዙ  #እኛን እየራቁ መጡ ከዛ ቡሀላ የቀሩትም ጓደኞቼ ማን ከማን ያንሳል በመባባል #ሁሉም የየራሳቸወለን ምርጫ ያዙ ጓደኞቼ ጋር የወንድ ጓደኛ ያልያዘ ፋራ ተባለ ሁሉም ፍቅረኛ ያዙ 

        #ከዛ እኔ ቀረሁ እኔ በቃ ለመያዝ እንኳ አስቤ አላቅም ነበር፡፡ ለምን የእናቴኝ ህልም ለማሳካት አልም ነበር ዲኔንም አስወቅሳለሁ አላህ ጋርም እጣላለሁ በኢስላም ዘመድ ካልሆነ ወንድ ልጅ ጋር መቀራረብ ሀራም እንደሆነ አቃለሁ ፡፡  ዱአ ማረግ አለብን ዋናዉ ለሰዉ ልጅ ወሳኙ ጥሩ ጓደኛ ነዉ፡፡ የኔ ጓደኞች ግን ያልበላቸዉን የሚያኩ ስልጣኔን ከወንድ   ፡ጓደኛ ይጀምራል የተባሉ ነዉ የሚመስሉት፡፡         

        #ጓደኞቼ እንድይዝ የግድ ገፍፉኝ  በጣም ከመገፋፋታቸዉ የተነሳ ትንሽ ኢማን በልቤ አለች ያልኩትን ተፈታተነኝ ማን ከማን ያንሳል በሚል ወደ ማልወደዉ እልክ ዉስጥ አስገቡኝ ለምን እኔ ትምህርት ቤት ዉስጥ ብችኝነት ተሰማኝ፡፡እነሱ በቃ የሚሄዱት ቦይ ፍሬንድ ተብየዉ ጋር ሆነ ፡፡ ብቻየን እኔ ምን ያንሰኛል የሚል ጥርጣሬ እራሴን ጠየኩት ያዉ የሴት ነገር ከነሱ ብምን አሳለሁ በማለት እልክ አስያዙኝ፡፡ ያዉ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ በቃ አለሁ አለሁ የሚል ስሜት ተሰማኝ ፋየር ኤጅ አስቸጋሪ ሰአት ናት ፡፡ ይች ሰአት ለእኔ እና ለጓደኞቼ ለእናንተም ቢሆን አስቸጋሪ ሰአት ናት ለእኔም ሆነችብኝ በጓደኞቼ ግፊት ፈተና ዉስጥ ገባሁ፡፡
         ማንኛዉንም ነገር ላላሳልፍ ብየ ቃል ለራሴ ገባሁ ማን ከማን ያንሳል፡፡ የኔ የምኖርበት መኖሪያ ቤት ትንሽ ይርቃል ጓደኞቼ ጋር የምንገናኘዉ  ትምርት ቤት ነዉ እንጂ ሠፈራችን #ይራራቃል፡፡ በፊት የወንድ ጓደኛ ባልያዙበት ጊዜ ይሸኙኝ ነበር ፡፡ ከያዙ ቡሀላ ግን የእነሱን አለም እንጂ እንሸኝሽ የሚባለዉ ነገር ቀረ ብቸኝነት ተሰማኝ፡፡ ግን  ትምህርት ከመግባታችን በፊት ጓደኞቼ ጋር የምንገናኝበት የሆነ ትልቅ ዛፍ አለ እዛ የቀደመ እንገናኛለን፡፡ ስልክ ከጓደኞቼ ሁለቱ ነበር ያላቸወ ሌሎቻችን የለንም ነበር፡፡ ከዛ ትምህርት ቤት አብረን እንገባለን፡፡ ያዉ ወሬዉ መቼም ታቁታላችሁ ትናንት እንደዚህ ብሎኝ እንደዚህ አልኩት መቼም የኛንየሴቶች ባህሪ የታወቀ ነዉ ፡፡ ሴቶች ትረዱኛላችሁ ብየ አሳባለሁ፡፡
      ይህ ወሬ ሁሉም የትናንትናዉ ዉሎዉን አንደዜና ሲዘገብ እነሱ እየተጣሉ እኔ ላዉራ እኔ ላዉራ ነበር የሚሉት በቃ የኔ ቦይ ፍሬድ ከአንቺ ይበልጣል ሆነ ወሬዉ ፉክክር ገቡ እኔ ተገርምኩኝ ፡፡ እኔ ስለ ቤት ስራ ስለ አሳይመንት ሳወራ ይቺ  ፋራ ጀመረች እያሉ እድል ስለማይሰጡኝ ግድ የእነሱን ወሬ ማዳመጥ ሆነ ስራየ፡፡
         አንድ ቀን ጓደኞቼን እንደወትሮዉ እኔ ቀድሜ  ትልቁ ዛፍ ተቀምጨ እየጠበኳቸዉ እያለ ያላሰብኩት ነገር ገጠመኝ የሂወቴ ትምህርት የሆነኝ የመላቀዉ ሰዉ ከፊት ለፊት ከእኔ ትንሽ በእድሜዉ የሚበልጠኝ ወጣት

#Part 2⃣
......ይ
..........ቀ
...............ጥ
.....................ላ
...........................ል

የቃላት ስህተት ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ
4 another channal👇
@Islam_and_Science
Joinn

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
ምርጥ 10 የሀገራት አባባሎች!
:
1. "ድልድዩን ከመስበርህ በፊት ዋና እንደምትችል እርግጠኛ
ሁን" ኬንያ
:
2. "አዲሱ ባልዲህ ውሃ የሚይዝ መሆኑን ሳታረጋግጥ
አሮጌውን አትጣል" ስዊድን
:
3. "አንድን ሰው ልብስ ከመጠየቅህ በፊት መጀመሪያ ለራሱ
ምን ዓይነት ልብስ እንደለበሰ ልብ ብለህ ተመልከተው" ቤኒን
:
4. "ውሸት መላውን ዓለም ትዞራለች ፤ እውነት ደግሞ እቤቷ
ቁጭ ብላ የሚሆነውን ትጠባበቃለች" ፈረንሳይ
:
5. "ጠማማ ዕድል ያለው ሰው ወደ ወንዝ አትላከው" ይዲሽ
:
6. "በጓደኛህ ግንባር ላይ ያረፈውን ዝምብ ለማባረር ብለህ
መጥረቢያ አትጠቀም" ቻይና
:
7. "አይጥ በድመት ላይ ከሳቀች አቅራቢያዋ ጉድጓድ አለ ማለት
ነው" ናይጄሪያ
:
8. "ውሃ ውስጥ ሰምጠህ የመሞት ፍላጎት ካለህ በጎደለው
ኩሬ ውስጥ እየተንቦራጨክ ራስህን አታሳቃይ" ቡልጋሪያ
:
9. "ተኩላዎች ዳኞች ሆነው በተሰየሙበት ችሎት ላይ የበጎች
ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት
አያዳግትም" ይዲሽ
:
10. "እንቁላል የሞላ ቅርጫት ተሸክመህ አትጨፍር" ጊኒ
:

ሼር በማድረግ ለወዳጆዏ አስተላልፉ

💧══ •⊰✿💚✿⊱• ══💧


┏━ 🍃 ━━━━ 🍂 ━┓
🎖ISLAM AND SCIENCE🎖
┗━ 🍂 ━━━━ 🍃 ━┛

telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
😂ለፈገግታ ፈገግታ ሱና ነዉ

ለአንዳንድ_ሴቶች
*አናትሽ ላይ ከፈረስ ጭራ የተሰራ ኮፍያ ሰክተሽ፣
*ፊትሽ ላይ ሩብ ቶን ሜካፕ ጭነሽ፣
* ከንፈርሽ ላይ የቀለም መዓት ከምረሽ፣
* ከተነሳሽው 47 ፎቶ ውስጥ አንዱን በጥንቃቄ
መርጠሽ፣
*በጥንቃቄ አቀናብረሽ Fb ላይ እና በTelegram ትለጥፊና
*ከፎቶው ላይ ደግሞ "ውበት ማለት መልክ ሳይሆን መልካምነት
ነው!" የሚል ፅሁፍ ትጨምሪበታለሽ።
# My_Sister ሁላችንም እናውቃለን! መልካምነትሽ ለኮስሞቲክስ ሻጩ
ብቻ ነው፡፡😂😂😂😂

@Islam_and_Science @Islam_and_Science
ይብላኝላት!!
ሰሞኑን ደሴ ከተማ ላይ ህዝብ ያስቆጣውን የህፃኗን ልጅ ግድያ በተመለከተ ዛሬ

እዉነተኛዉ መረጃ ገዳያ እናቷ ሁና ተገኘች፡፡😭😭😭
« ልጄ ጫማ እንድገዛላት ጠየቀችኝ።እንደማልችል ነገርኳት።ደጋግማ
ስትጨቀጭቀኝ በስሜት አጠገቤ የነበረን ዘነዘና ወረወርኩት ከልጄ ደንደስ ላይ
አረፈ።ፀጥ አለች።😭
የማደርገው አጣሁ ሰው ልጇን ገደለች ይለኛል ብየ በኬሻ ጠቅልየ ገንዳ ውስጥ
ከተትኳት።
☞ሰውነቷ ተቆረጠ የተባለው ውሼት ነው።ሆስፒታል ወስደው
አሳይተውኛል።
😔ድህነት ልጄን አስገደለኝ።»
የገደለችዉ እናቷ ሴተኛ አዳሪ ናት።
ከዚህ ክስተት ሁለት ነገር ተማርኩ
1 ህዝቡ ገደለ እና ደፈረ የተባለውን ሰው ገድሎ ቢሆን ፀፀቱ…
2 በደቂቃ ስሜት ተሸንፈን የምንፈፅመው ስህተት የዘላለም እሳት ማትረፉን
3 ፈራጅ መሆን ያለብን ህግ ባስረገጠው እና እጅ ከፍንጅ በተያዘ ወንጀለኛ ላይ
ብቻ መሆን እንዳለበት።
ሌላውን ይብላኝ ለሷ እጇን በእጇ ለበላችው።የናትን አንጀት አውቀዋለሁና
መፍረድ አልችልም

ለማንኛዉም ጨዋዉ የደሴ ህዝቦች ለወደፊት ከስሜታዊነት እራሳችሁን ጠብቁ ፡፡ ሰዉየዉ ገድልሀል ተብሎ ሙቶ በነበር ፀፀቱ ከባድ ነበር👍

ግን የእናት ጨካኝ አረመኔ ያሳዝናል፡፡
@IslamisUniverstiy_public_group
# መለስ_ዜና
.
አንተ ከሞትክ ወዲህ
የቆመ አፓርታማ ቤት ጠፋ ተባልን
እኛም ለይስሙላ አምነን ተቀበልን

አንተ ከሞት ወዲህ
ስር የሌለው ህንፃ ሸገር ላይ በቀሉ
በረከት ቤት አጥቶ አቦይጋ ተጉላሉ
ሌብነት ስራ ነው
ከያዙህ ወንጀል ነው
ብለህ ስትናገር ሳይገባው ጠይቆ
ባልተያዘ ነበር.....ዛሬ ፕሌን ሰርቆ

እና ምን መሰህ
የማይሆን ሲሰራ ብዙ ዶላር ቢያልቅም
ሜቴኩ ጨዋ ነው መቼም ሰርቆ አያቅም
.
.
.. የእናቱ ልጅ አብዱል ከሪም ..


🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
😔 #ተስፋ #ያጣች #ሴት😢
እውነተኛና ልብ የሚነካ አሳዛኝ ታሪክ

#ክፍል 5⃣
... #የሀና እናት ሆስፒታል በቶሎ ባትደርስ ምናልባትም ህይወቷ
አደጋ ላይ ይወድቅ እንደነበር ዶክተሮቹ ተናግረው ሲያበቁ ሌላም
የምስራች ይሁን መርዶ ለሀና ያልገባትን ነገር አበሰሩ አፀደ
#እርጉዝ #ነች ሀና ምንም እንኳ እህት ወይ ወንድም ልታገኝ
መሆኑን ብታውቅም ከደስታ ይልቅ ጭንቀት ነበር የሚሰማት ያን
ግዜ ወደኋላ ተመልሳ አሰበችው የእንጀራ አባቷ አብሯት ሲተኛና
እስከዛሬ ከውስጧ ተፍቆ ሊወጣ ያልቻለው የህሊና ቁስሏ
ታወሳት በዛ ላይ እናቷ ስትወልድ ብዙ ትሰቃያለች ይሄ ሁሉ
ተደማምሮ ሀናን " #ህልም #በሆነ" ሲያስብላት የእንጀራ አባቷ
ቴድሮስ ግን በደስታ ፈነደቀ "ልጄ እህት ሊያገኝ ነው..." አለ
በምፀት ፈገግ ብሎ ሀና ይህን ንግግሩን በሰአቱ
ባታስተውለውም እያደር ግን እሷን ማግለል ፈልጎ እንዳለ
ስትረዳው ብቸኝነት ተሰምቷት ከልቧ ታነባለች...
#አፀደ #ከሆስፒታል ወታለች ይሄኔ ሀና ከ3 ቀን በፊት
ስለተፈጠረው እናቷን መጠየቅ ፈልጋ "እማ" አለች አንገቷን
ወለሉ ላይ እንደሰካች "ወዬ ልጄ" አለች አፀደ "ያአብስራ ምኔ
ነው ደግሞም ቴዲ እንዳለው አይደለም ምንም አላረግንም
አላውቀውም ነበር ዛሬ ከሶፊ ጋር መቶ..." እንባዋ እየቀደመ
ንግግሯን አላስጨርስ አላት አፀደም በልጇ የእውነቷን
እየተማመነችና የልጇን እንባ እየጠረገችላት " #ልጄ ይሄ የኔና
የአባትሽ ጥፋት እንጂ ያንቺ አይደለም ያብስራ ያባትሽ ልጅ ነው
ብዙ ወንድሞች አሉሽ እናም ልጄ እኛ ካላስተዋወቅናቹ ጥፋቱ
የኛ ነው!" አለችና በሻርቧ እንባዋን ጠራረገች ሀናም
#የምትመልሰው አታ የእናቷን ንግግርና ሁኔታ ብቻ ማጤን
ቀጠለች ዝምታዋ ያስፈራት እናት ልጇን ቀና አድርጋ አይኖቿን
ለማንበብ እየሞከረች "ልጄ ፍቅር #ይዞሻል ?" ብላ ጠየቀቻት ሀና
እንደዚ በግልፅ አውርታ ስለማታውቅ ልቧ ስንጥቅ አለ
"መልሺልኛ" አለች እናት ሀናም ድምፅጿ እየተቆራረጠ "እኔ
ወንድ ልጅ እፈራለው ሁሉም የሚደፍሩኝ ይመስለኛል..." አለች
#አፀደም #ደንገጥ ብላ ልጄ ያስገደደሽ ወይንም ሊደፍርሽ የሞከረ
ሰው አለ? ብላ ጠየቀቻት ሀናም በስሞት ከተቀመጠችበት ተነስታ
አዎ ስትል ቴድሮስ ኮቴ እንኳ ሳያሰማ ዘው ብሎ ገብቶ እናንተ
ምን እያወራቹ ነው አለ የወሬው እንቅፋት ለመሆን እንደሆነ
ዳያስነቃ አዲስ ወሬ ጀምሮ ያን ሰአት አረሳሳቸው ... ከዛም
ሀናን በዘዴ ካሶጣት ቡሃላ አንድ ቃል ትንፍሽ ብትል እናቷንም
እሷንም እንደሚገላቸው አስፈራራት...
ሀና ውጤቷ ለመምህርነት በቂ ስለነበር ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ
#ለመማር #ምዝገባ መከታተል ጀምራለች ሀና ብዙ የምታስባቸው
ነገሮች አሉ በእውነቱ ሀና እጅግ በጣም ውብ ነች ነገር ግን
ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች ውበቷን ሲያደንቁ እየቀለዱባት
እስኪመስላት ድረስ አታምናቸውም ይሁን እንጂ ሀና ልቅም
ያለች የቀይ ዳማ ከለር ያላት ውብ ነች በተለይ አሁን እያደገች
ስትመጣ አይቶ የማይመኛት የለም ... ሀና የኮሌጅ ትምህርቷን
በተመዘገበች በሳምንቷ የአብስራን #መንገድ #ላይ አገኘችው
ያብስራ ሲያያት በጣም ደስ አለው እሮጦም አቀፋት ሲያቅፋት
ሀና በጣም ነበር የደነገጠችው ... ያአብስራ ያፈቅራታል ግን
ደግሞ ወንድሟ ነው እሱ ይህን አያውቅም ... ሀና እንባዋ ዱብ
ዱብ አለ ያብስራም ግራ ተጋብቶ ምን እንደሆነች ሲጠይቃት
ትታው እሮጠች... ያን ቀን ስትሮጥ ድንገት ቤታቸው ሻይ በሚሸጡበት ጊዜ የተዋወቀችው ኪሩቤል ከጓደኞቹ ጋር በተለምዶ(ድድ
ማስጫ) የሚባለው ቦታ ተቀምጧል ሀና አላየችውም ስለያብስራ
እያሰበች እንባዋ ይዘንባል ነገሮች በሙሉ ድብልቅልቅ
ብለውባታል እድለ ቢስነቷን እያሰበች ፈጣሪዋን እያማረረች
ስታልፍ ኪሩቤል "ሀኒ" ብሎ ጠራት ዞራ ስታየው ደነገጠች
... #ኪሩቤልም እንባዋን እየጠረገ ምን "ሆነሽ ነው" ሲል ጠየቃት
ሀናም እንባዋ መውረዱ ሳያቆም ፈገግ ለማለት እየጣረች
"ምንም" አለችው ኪሩን ስታገኘው ውስጧ የማታውቀው ስሜት
ተሰምቷታል ይህ ስሜት የሀዘን እንዳልሆነ ደግሞ እርግጠኛ ነች
...
#ኪሩቤል እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አርጎ ሰፈር ድረስ ሲሸኛት
ሁለቱም አይነጋገሩም ነበር ሰፈር ደርሳም "በቃ ተመለስ
ደርሻለው" ስትለው "እሺ ሀኒ ግን ሳልነግርሽ አልሄድም በጣም
ደስ ትይኛለሽ ማለቴ..." #ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ #የእንጀራ
#አባቷ ከየት መጣ ሳይባል" አንቺ ስድ ለምን አንደኛሽን ሴተኛ
አዳሪ አትሆኚም ጭራሽ ከማንም  ዱርዬ ጋር " ሲል
ሁለቱም ቀልባቸው ተገፈፈ... ሀናም የኪሩቤልን እጅ አስለቅቃ
ወደ ቤት እሮጠች ግን በዚ አላበቃም ነበር ቴድሮስ ተከትሏት
ገብቶ ከእናቷ ፊት ከወረደባት ቡሃላ "እዚ ቤት ላይሽ አልፈልግም
ውጪ" ብሎ አሶጣት ሀናም ከመውጣቱ በላይ እየደረሰባት
ያለው በደልና የእናቷ ጉዳይ እያሳሰባት #ቤቱን #ለቃ #ወጣች...
ሀና ምንም ዘመድ የላትም መሄጃዋንም አታውቅም ብቻ የሷ
መፅናኛ እንባዋ ነውና እያነባች አንድ ጭር ያለ ስፍራ ሄደች ይሄኔ
የቴድሮስ ግፍና ስድቦች በእናቷ ላይ የማገጠው... ሲደፍራት
የኖረው እንዲሁም ዛሬ የተናገራት "...የትም ስትንዘላዘይ ቆይተሽ
መተሽ ልጄን HIV እንዳታስይዥው አንቺስ ጉዳይሽ" ያላት
አፀያፊ ንግግር አይምሮዋ ላይ ተመላለሰባት እናም እራስዋን
#ለማጥፋት #ገመድ #ማዘጋጀት #ጀመረች...

ክፍል 6⃣
ይቀጥላል____

ከተመቻችሁ Part 6⃣ ቶሎ እንዲለቀቅ እና ምን ያህል ሰዉ እንደሚከታተለዉ ለማወቅ 🤙🤙🤙 like አርገዉ ሼር አይዘንጉ

@Islam_and_Science @Islam_and_Science
👍1
#የሸህ #ኻሊድ #ረሻድ #የሂወት #ገፅ
#የመጨረሻዉ #ክፍል
በIslamic university channal

#እኔ አንድ ቀን ከሪያድ ወደ ደማም ለመሄድ ኤርፖርት ነኝ። መግሪብና ኢሻን ጀምዕ አድርጌ ሰግጄ ሳበቃ… አንድ ሰው መጥቶ ኻሊድ አራሺድ ነህ አለኝ አዎ አልኩት ጓደኛውን እየጮኸ እገሌ ብሎ ጠራውና ጓደኛው ዞር ሲል ይኸው ኻሊድ አል ራሺድ አለው…
ጓደኛውም የቱ ኻሊድ ሲለው «ያ… ጀመአን በታታኙ?» አለው።
ሸኹ ደገጡ አኡዙ ቢላህ አልኩ አሉ አረ #እኔ ጀመአን እስበስባለው እንጂ አልበታትንም ስላቸው… አይ የካሴትህ ርእስ ጀመአን በታታኝ ስለሚል ነው አሉኝ በወቅቱ (( مفرق الجمع)) ጀመአን በታታኝ የሚለው ስለ ሞት የሚናገረው ሙሀደራ ሀገር አዳርሶ ነበር ። አድናቂዎቹ በየደረሰበት አላንቀሳቅስ አሉት… ህፃናቶች ሲያዩኝ «من حال إلى حال» ሚን ሀል ኢላ ሃል ይሉታል…kkkk ይህም ሌላ የሙሀደራው ካሴት ነው ።
#ሸኽ ኻሊድ በመላው ሳውዲ ስሙ ናኘ ብሎም በአረቡ አለም ከፍተኛ ተቀባይነትን አገኘ… የማይሰለች ዳእዋው ህዝብን አንበረከከ ከ40 በላይ የሙሀደራ ካሴቶችን ሰራ… በ2008 አንድ የዴንማርክ መፅሄት የረሱል (ሰዐወ) ምስል አወጣ… #በአለም #ላይ ያሉ ሙስሊሞች ጉዳዩ በከፍተኛ ሁኔታ አስቆጣቸው… እንደ ሳውዲ ያሉ አረብ ሀገራት ከዴንማርክ የሚገቡ እንደ ኒዶ ወተት እና ቂቤ ሌሎችንም ምርቶች እንዳይገባ አገዱ… የሳውዲ እና የሌሎች ሙስሊም ሀገራቶች ምላሽ ያልተዋጠላቸው ሸኽ ኻሊድ «ያ አመተ ሙሃመድ» በሚል ርእስ ትልቅ ኹጥባ አደረጉ… በኹጥባቸውም… ይህ ነገር እንደዋዛ ካለፈ ኸይር አይጠበቅብንም ። ኒዶ አትግዙ ብቻ ሆነ ተቃውሞችን… ይሄኔ የሳውዲ ንጉስ ተሰድቦ ቢሆን ጦር በተንቀሳቀሰ ነበር… ረሱል ተሰድበውብን ምላሻችን ይሄ ነው? ኤምባሲያቸው ከሀገራችን ይውጣልን ። በሚል ተዋውሞ ሊያደርጉ ከስር በምትመለከተቱት መልኩ በአንድ መስጂድ ተገናኝተው #ተቃውሞውን #ቀጠሉ… ይህን ግዜ ሸኽ ኻሊድን የሳውዲ አቃቤ ህግ ከሰሳቸው… ለጂሀድ ሰው እያነሳሳ ነው በሚል ታስረውም የአምስት አመት ፍርድ ከተፈረደባቸው ቡሃላ ይግባኝ ጠይቀው ከዳኛው ጋር ባደረጉት ክርክር ዳኛውን ሰድበዋል በሚል ልባቸው በኩራት ያበጠው የሳውዲ ዳኞች እዛው ፍርድ ቤት ውስጥ ለ15 አመታት በይነውባቸዋል … #አላህ #ከእስር #ነጃ #ይበላቸው

ከኻሊድ ረሻድ የሂወት ገፅ የምንይዘዉ ማንኛዉም ሰዉ
☞ከአለበት ሱስ ተላቆ
☞እድሜ ሳይገድበዉ
☞ እኔ አልችልም ከማለት
☞ እኔ ኪታብ አልቀራሁም ከማለት ወደ ፊት ዲኔን ተምሬ ሰዉ መቀየር እችላለሁ
☞አንቺም አሁን ላይ በዘመናዊ ፋሽን ብትጠመጅ እኔ ተቀይሬ ሰዉ መቀየር እችላለሁ
☞አእምሮየን ማሰራት መቻል አለብን

ማንኛቻንም የተሰጠንን አእምሮ ብንጠቀም እኛም ተቀይረን ሰዉ መቀየር እንችላለን፡፡

በታሪኩ አንብባችሁ እንደምንቀየር ባለሙሉ ተስፋ ነኝ

ጨርሰናል፡፡




JOIN👇👇👇

4 another channal👇
@Islam_and_Science
Joinn

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
እዉነተኛ ታሪክ

የታሪኩ ርዕስ
💧 #ማን #ከማን #ያንሳል💧

#ክፍል 2⃣

#ፀሀፊ#አሚር
በIslamic university channal

#አንድ ቀን ጓደኞቼን እንደወትሮዉ እኔ ቀድሜ  ትልቁ ዛፍ ተቀምጨ እየጠበኳቸዉ እያለ ያላሰብኩት ነገር ገጠመኝ አንድ ልጅ መጣ መልኩ ጠይም እረጅም ቀጠን ያለ ብቻ ለማንኛዋም ሴት የሚመች ወንድ ነገር ነዉ ፡፡ #በጣም የሚያምር ነገር አለዉ፡፡ 
        #መጣና አንቺ ተነሽ ማን ተቀመጭ ብሎሽ ነዉ የተቀመጥሽዉ  ??? አለኝ  መቼም ወንድ ልጅ መጀመሪያ ላይ ከሴት ለመግባቢያ ቃላት አላቸዉ፡፡ እኔን ተነሽ ሲለኝ በጣም በመናደድ ምን አገባህ የሚል መልስ ሰጠሁት ፡፡
........እሱም የቸገረ ያግባሽ እኔን ነዉ ምን አገባህ የምትይዉ ሲለኝ
........ #እኔም እና ቦታዉ የአንተ አይደለም ምን ያገባሀል የሊዝ አልከፈልክበት ወይ እንቁላል አልጣልክበት ብየ ገለማመጥኩት ፡፡
...... #እሱምእኔ እንደ አንቺ ክፉ አይደለሁም እንጂ በጥፊ ነበር ማለት ብሎ ጥሎኝ ሄደ፡፡
      #ኡፍ አልሀምዱሊላህ አልኩኝ እንደዚህ ቢናገረኝም ምንም አልመሰለኝ ብቻ የፈለኩት ከእኔ እንዲሄድ ነበር፡፡ ግን ከሄደ ቡሀላ በቃ አለ አይደል ልቤን ለመጀመሪያ ጊዜ ለእሱ ድንግጥ ብሏል ሁሉ ነገሩ ተመችቶኛል፡፡ ግን ይመለሳል የሚል ግምት የለኝም ነበር፡፡ ጓደኞቼ መጡ ወደ ትምህርት ቤት አብረን ገባን፡፡
       #በሁለተኛ ቀን ከዛዉ ተቀምጨ መጣ እንደ አጋጣሚ ጓደኞቼን ቀድሚያቸዉ ነበር፡፡ ከዛ ሳላስበዉ  የትናንትናዉ ልጅ መጣ  አሁንም እዚሁ ነሽ ?? አለኝ፡፡  #እሱ መሆኑን ሳቅ የሆነ የደስታ ነገር ተሰማኝ እና የደስታ ይሁን የቀልድ አላቅም  ሳኩኝ  ከዛም እና የት ልሂድ እዚህ የምቀመጠዉ ጓደኞቼን እየጠበኩ እስከሚመጡ ነዉ አልኩት፡፡
     #እሱም ወዴኔ እየተጠጋ ለምን አንተዋወቅም ብሎ እጁን ዘረጋ እና #ኑሩ እባላለሁ አለኝ፡፡ የሆነ ደስ ደስ ያለዉ ልጅ ነዉ በቃ የሆነ ነገሩ ደስ አለኝ፡፡
....... #እኔም እጁን ጨበጥኩት እና  ስሜን በመዋሸት #ሀያት #እባላለሁ አልኩት ፡፡ ግን የዋሸሁት እሱ ጋር ለወደፊት ጓደኛ አልሆንም ፡፡ አላህ ይቆጣብኛል ብየ ነበር ፡፡
....... #እሱም እኔ 12 ክፍል ተማሪ ነኝ አለኝ፡፡ #በዛን ሰአት #ስልክ አልነበረኝም  ነበር ስልኬን እድሰጠዉ ጠየቀኝ ስልክ እንዴሌለኝ ስነግረዉ የእሱን ከፖርሳየ ዴብተሬን አዉጥቶ ቁጡሩን ፃፈልኝ የምደዉይበትን ሰአት በተስፋ እገብቃለሁ አለኝ፡፡  እና ወደ ትምህርት ቤት ሄደ ፡፡
        #ኑሩ የሚማረዉ ሌላ ትምህርት ቤት ነበር፡፡ እዛዉ ዛፉ ስር ቁጭ እንዳልኩ  ጓደኞቼ መጡ ወደ ትምህርት ቤት እየሄድን ስነግራቸዉ የሌላ ነዉ የተደሰቱት፡፡ #በጣም #ደስ አላቸዉ ፡፡እኔን እስከ መሳም ደረሱ፡፡ አይ የሚገርም ነዉ  ለምን እንደሆነ አላቅም፡፡ መቼም ጥሩ ጓደኞቼ ቢሆኑ ከመደሰት ቢመክሩኝ ተይ ቢሉኝ ነበር፡፡ አህያ ጋር የዋለች ጊደር ፈስ ተምራ መጣች አይደል ተረቱ፡፡ጓደኛህ ማነው? ፣
ጓደኛሽ ማናት??
ከክፉ አውሬ እንደምትሸሸው ሁሉ ከመጥፎ ጓደኛሽ ሽሽ።
ከፍራፍሬ መልካሙን እና ምርጡን እንደ ምትመርጪዉ ሁሉ ከወዳጅችም መልካሙን ምረጭ።
መጥፎ ጓደኛ ከሚኖርሽ
ጭራሹኑ ባይኖርሽ
ይመረጣል።
ቀደምቶቻችን “ስለማንነትህ እንድነግርህ ከፈለግክ ስለጓደኛህ ንገረኝ “ የሚሉት ያለምክንያት አይደለምና፡፡

       #ይሄማ ካንች መዉጣት የለበት እያሉ መዛት ለኔ ተስፋ መስጠት ጀመሩ #እኔም እራሴን አሳመንኩት እና እንደተለመደዉ ወዴ ቤት ሄድን ሰአት ደርሶ ወደ ትምህርት ቤት  ስሄድ ሁሌ ከምቀመጥበት ከዛፉ ስር  እሱ ተቀምጦ አገኘሁት፡፡
     #እሱም ነይ ተቀመጭ አለኝ ጓደኞቼ እንዳያመልጥሽ ስላሉኝ እኔም የሆነ ነገሩ ስለተመቸኝ እንደ እነሱ ስታይል ለመመሳሰል እኔም የላ አንድ አፈረት አብሬዉ ተቀመጥኩ፡፡
....... #እሱምግን ታዘብኩሽ ለምን ትዋሻለሽ አለኝ ? 
 ...... #እኔም ምን ዋሸሁህ አልኩት
.. .. . #እሱም ስምሽን ለምን ሀያት አልሽኝ ሰአዳ አይደል እንዴ ስምሽ አለኝ ??
........ #እኔ ምንም መልስ የለኝም ዝም አልኩ ለምን ዋሽቻለሁ እና፡፡
ኑሩም  የእኔ#ታናሽ ወንድሜ እናንተ ጋር ይማራል ስሟ ሰአዳ ነዉ አለኝ ፡፡ ለምን ዋሸሽኝ አለኝ?? መልሴ አሁንም ዝምታ ነበር ፡፡
      ግን እኔ #ማወቁ #ግድ #አይሰጠኝም ዝምም ያልኩት ምንም ደንታ አልሰጠኝም እንቀጥላለን ብዬ ትዝም ብሎኝ አያቅም፡፡ኑሩም ለምን በጓደኞችሽ ስልክ Missd call  አታረጊልኝም እኔ እደዉላለሁ ዛሬ ስልክ እንደምደዉይ እርግጠኛ ነኝ አለኝ፡፡ ከዛ በይ ቻዉ ደህና ዋይ ብሎ ወደ ትምህርት ቤት ሄደ ፡፡

       #ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ጓደኞቼ መጡ ያለኝን ሁላ ነገርኳቸዉ፡፡ በጣም ተደሰቱ ፨ ምን አሸሽ ብለዉ በእረፍት ሰአት ቁጥሩን አምጪ ብለዉ ደወሉልኝ በስልክ እናወራ ጀመረ፡፡ የሚገርመዉ ከአሁን በፊት ለዘመዶቼ ደዉሉልኝ ስላቸዉ እምቢ የሚሉኝ ጓደኞቼ ለወንድ ጓደኛ ሲሏቸዉ ግን ምንም ሳያመነቱ እሺ ማለታቸዉ ይገርማል፡፡
       #ኑሩም በጣም መቀራረብ በጓደኞቼ ስልክ መደዋወል ጀምርን በሂደት ትምህትን እየዘጋ የትምህርት መዉጫየ ሲደርስ እየመጣ ሰፈሬ ድረስ ይሸኘኝ ጀመር ፡፡ መደዋወሉና ከትምህርት ስለቀቅ መሸኘቱ በቃ ተለመደ ስንለቀቅ ሳይሸኘኝ ሲቀር ዛሬ ምን ሁኖ ነዉ እያልኩ መጨነቅ ጀመርኩ፡፡
        #በቃ ኑሩ ብዙ ነገሮችን አስተማረኝ ስንሄድ የሚለኝ ማሬ ነበር ወይ ማር ...እሱ ጋር አብሮ መሄዱ ለኔ ኩራት ተሰማኝ ፡፡ ጓደኞቼ ተሳካላቸዉ ማለት ነዉ ያሰቡት ፡፡ እስኪ ስለ ኑሩ ልንገራችሁ፡፡ #ኑሩ #እንደ #እኔ #የደሀ $ልጅ #አይደለም ፡፡


ኑሩ ማለት እናት እና አባቱ ...በሚቀጥለዉ ክፍል እናየዋለን

Part 3⃣
....ይ
.........ቀ
..............ጥ
....................ላ
..........................ል


4another channal👇
@Islam_and_Science

JOIN👇👇👇
@IslamisUniverstiy_public_group
@IslamisUniverstiy_public_group
 
👍1