ISLAMIC SCHOOL
12.6K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY via @like
#ከሸኽ #ኻሊድ #አልራሺድ #የህይወት #ገፅ
#ክፍል☞ ሁለት
በIslam is university channal
#ሸኽ ኻሊድ ዳኢ ብቻ አልነበሩም ። የጥበብ ሰው ናቸው። ግጥም ይዋጣላቸዋል። #ኹጥባ ሲያዘጋጁ በመሃል ካነሱት ርዕስ ጋር የሚገናኝ ምርጥ ግጥም ሳያካትቱ ታዳሚ ፊት አይገኙም … ተራኪም ናቸው። በሳቸው የተነገረ ታሪክ ይመስጣል። የሚያሳዝን ከሆነ እስኪያስለቅስ፣ የሚያስደስት ደግሞ እስኪያስፈነጥዝ ያዋዙታል ። ባጭሩ መተረክ ይችሉበታል ።
#እንደ ጋዜጠኛም ናቸው። በአንድ ጉዳይ ላይ ደእዋ ለማድረግ ካሰቡ በጉዳዩ ዙርያ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተዘዋውረው ስለ ሁኔታዎች ይጠይቃሉ። ሀሳብ ያደምጣሉ፣ ገጠመኞቻቸውን ይቀበላሉ ከዛም ወደ ህዝብ ለማድረስ ይመጣሉ። #ርእስ አመራረጥስ ቢሆን… እስኪ እሳቸው የሚያነሱትን ርእስ ሌሎች ዳኢዎች ጋር ፈልገው አታገኘውም።
…ወደ ጀመርነው ከህይወት ገፃቸው የተወሰኑ ገፆችን ወደ መግለፅ ስንመለስ…
#ሸኽ #ኻሊድ ሙሃመድ አልራሽድ ኳስ ተጫዋች እንደነበሩ በክፍል አንድ ተመልክተናል። የእግር ኳስ ጊዜያቸው የህይወታቸውን አንድ ሶስተኛ ስለሚይዝ በቀላሉ ምናልፈው አይደለም።
አዎ ተጫዋች ነበሩ… ያውም የቀኝ ክንፍ ጎበዝ ተመላላሽ «ጎል ማግባት ለኔ ብዙም የማስበው አይደለም» ይላሉ…ሸኹ ስለ አጨዋወታቸው ሲያወሱ ማጠፍ እወዳለው ፣በኳስ መራቀቅ ደስ ይለኛል። #ሲሉ #ይናገራሉ
ትምህርት ቤት ሜዳ ስንጫወት የአልቃዲሲያ ክለብ አሰልጣኝ ከሽቦ በስተጀርባ ሆኖ ያየኝ እንደነበር አስታውሳለው ከዛም ለአልቃዲሲያ ክለብ እንድጫወት ሲያናግሩኝ… ትንሽ ግራ ተጋባው ይላሉ… እንዴት ሰው ሀፊዘል ቁርአንም ኳስ ተጫዋችም ሊሆን ይችላል ብዬ ራሴን እጠይቅ ነበር ። ለናቴ አማከርኳት « ቃዲሲያ የሚባል ክለብ እንድገባ አናገሩኝ» አልኳት ።
#እናቴ #ተቆጣች
በፍፁም አለችኝ ።
እግር ኳስ እቤት አዎ
ትምህርት ቤት አዎ
ነገር ግን በክለብ ደረጃ ላ!
አልፈቀድም አለችኝ ። አባቴም አይሆንም አለኝ።
#እኔ ግን ቤተሰቦቼን ተደብቄ ተመዘገብኩ ይላሉ…
ከዛ በቃ በኳስ ጨዋታ ሆነ ስራዬ ቤተሰቦቼ ሳያውቁ… የቁርአን ሀለቃ ላይ ኻሊድ የሚባል ሰው መገኘት አቆመ ። ያ ጎበዝ ተማሪ ያ የበታቾቹን ቁርአን ሲያስቀራ የነበረ ሰው ከቁርአን ሀለቃ ጠፋ… የአል ቃዲሲያ ክለብ ተጫዋች ሆኖ ቀረ…
#ሸኽ #ኻሊድ ሲናገሩ በኳስ ጨዋታ በወር እስከ አንድ ሺ አምስት መቶ ይሰጡን ነበር ይላሉ በጣም አነስተኛ ክፍያ ነበር ። በዛ ወቅት ኳስ እንዳሁኑ አልነበረም ። ታኬታ እንኳ ይቀየርላቹሃል ስንባል እንደሰት ነበር ። እንኳን ያንን ከፍለውን ቀርቶ ሲሉ ይናገራሉ።
ዛሬ ለአንድ ተጫዋች አምስ ሚሊየን ሪያል ይከፈለዋል። ሸኹ የሳቸው የኳስ ዘመን ባአሁኑ ሰአት ባለመሆኑ አልሃምዱሊላህ ይላሉ… በዘመኑ ከሚታየው የእግር ኳስ አጀብ በማምለጣቸው እየተደሰቱ።
ሸኽ ኻሊድ ስለ ታሪካቸው ሲቀጥሉ « የኳስ አሰልጣኞቼ በተስፋ ይሞሉኝ ነበር … አንተ ጎበዝ ኳስ ተጫዋች ትሆናለህ ጋዜጣ ላይ ትወጣለህ…ወ ዘ ተ እያሉ ተስፋ ይሰጡኝ ነበር።
#ከዚህ #ቀደም ትምህርት በጣም በመቅረቴ ዳይሬክተሩ ጠርቶ አንተም ክለብህም አስቸግራቹሁናልና ሌላ ትምህርት ቤት ፈልግ ብሎ አባሮኝ …ሌላ ትምህርት ቤት ገብቼ ነበር ሁለተኛ ትምህርቴን የጨረስኩት። እሱም ከባድ ነበር… የትምህርት ማጠናቀቂያው ማትሪክ ፈተና እና የክለባቸው ግጥሚያ አንድ ቀን ተገጣጠመ… ክለቡ ጨዋታውን የሚያደርገው ጀርመን ሀገር ነበር። ታድያ ምን ተሻለ?
ፈተናውን ይፈተኑ ወይስ ጀርመን ሄደው ኳስ ግጥሚያ ያድርጉ?
#ፈተናውን ትቼ ጀርመን ሄድኩ ይላሉ…
ነገር ግን እንደተመለሱ «የትምህርት ሚኒስተር ብቻዬን ፈተነኝ» ሲሉ ይገልፃሉ
።የትምህርት ውጤታቸውም ምንም አይልም ነበር ። «ሂሳብ የሚባል ትምህርት አይሆንልኝም እኔ የምወደው ስነ ፅሁፍ ታሪክ» ወዘተ ነበር ይላሉ።
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ሳጠናቅቅ ጓደኞቼ ወደ ዩንቨርስቲ ወይም ኮሌጅ ሲገቡ እኔ ወደ ኳስ ሜዳዬ ዘወተርኩ ። #በኳስ #ጨዋታ ላይ ቆይተው ሁለት አመት እንዳስቆጠሩ እግራቸው ላይ አደገኛ መሰበር ደረሰበት … ጉዳታቸው ከፍተኛ ነበር አንድ አመት ሙሉ እግራቸው መሬት ሳይረግጥ በክራንች ተጓዥ ሆኑ… #ታድያ ያኔ ይላሉ ሸኹ… አብሮኝ የተማሩት ከፊሉ ስራ ይሰራል ከፊሉ ትምህርቱን ያሻሽላል እኔስ? እኔ ብቻዬን ቀረው ። ያለ ስራ ያለ ሰርተፍኬት ያለ ምንም…የእግር ኳስ ክለቤም ቢሆንም አይፈልገኝም ምንም ስለማልሰራለት… ኳስ በሰጠሃት ልክ ትሰጥሃለች አንተ ከቆምክ እሷም ታቆምብሃለች የያኔው ጉዳቴ በወር በሁለት ወር የሚድን አልነበረም አንድ አመት ከግማሽ ማገገም ያስፈልገኝ ነበር።
#አንድ #ቀን ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ተቀምጠን አንድ ሀሳብ አቀረበልኝ ይላሉ«ያ ኻሊድ ትምህርት ያጠናቀቀው ስራ እየሰራ ነው… ኳስ የሚጫወተውም እየተጫወተ ነው እኔ እና አንተ ብቻ ቀረን ምን ይሻላል? አለኝ ከዛም ድንገት ለምን መኪናችንን ሽጠን አሜሪካ አንሄድም አለኝ ምን እንሰራለን አልኩት ትምህርት እንማራለን አለኝ ሸኽ ኻሊድ ይላሉ ትምህርት ቤት እያለው የጦር ጀነራል መሆን እፈልግ ነበር… እሱን ለመማር ፖሊስ ማሰልጠኛ እንዳልገባ ትምህርቱን አመት ሁለት አመት ያቋረጠ ሰው አያስገቡም ነበር ። #ስለዚህ ጓደኛዬ አለኝ ለምን አሜሪካ ሄደን ተምረን እዚህ መጥተን አንቀጥልም? ሲል ተስማማው እሺ አልኩት በዛ ሰአት መማከር ማሰብ የለም ነበር ይላሉ አዲስ ሆንዳ መኪና ነበረችኝ ሸጥኳትና ለመሄድ ስነሳ ጓደኛዬ ገና ለመሄድ አልተሰተካከለም ችግር ገጠመው በመሃል ስለዚህ እኔ ብቻዬን ተነስቼ ሄድኩ ይላሉ ከዛ አሜገሪካ ኢንዲያና የሚባል ኤርፖርት ደረስኩ ይላሉ… ከኛ በፊት የሄዱ ጀመአዎች ነበሩና ለነሱ ደወልኩላቸው ከቆይታዎች ቡሃላ ተቀብለውኝ አሜሪካ ገባው… ኑሮውን ተለማመድኩት ኮሌጅም ተመዝግቤ ትምህርቴንም ጀመርኩ ይላሉ… #ሸኻ #ኻሊድ አሜሪካም ሄደው የኳስ ፍቅር አለቀቃቸውም እግራቸውም ተሽሏቸው የኮሌጁ ምርጥ ተጫዋችሆኑ… ሸኹ በአንደበታቸው ሲናገሩ አሜሪካ ያኔ እግር ኳስን አያቋትም ነበር ይላሉ እነሱ የእጅ ኳስ ነበር ሚጫወቱት በቃ ብራዚል ሆንባቸው ይላሉ ፈገግ እያሉ… የኛ ኮሌጅ ከየትኛውም ኮሌጅ ጋር ተጋጥሞ አይሸነፍም ነበር… እኔ ስሜ ተቀይሮ በአንድ የብራዚል እግር ኳስ ተጫዋች ስም ነበር የምጠራ ይላሉ በሳቅ በፈገግታና ጥበብ በተሞላ አነጋገራቸው።
አንድ ቀን ታላቅ ወንድማቸው ከሳውዲ ይደውላል ወደ ትምህርት ቤቱ ዃሊድ እንዴት ነው እየተማረ ነው ሲል «ያ ኳስ ተጫዋቹን ነው? »ሲሉ ይጠይቁታል ።ያ አላላላላህ አሁንም እዛም ሄዶ ኳስ?
#ይቀጥላል
ሸኹ አስቸግረዋል የኳስ ህይወታቸው ሊለቃቸው አልቻለም ።
አሜሪካ ምን ያህል ግዜ ቆዩ?
ፂማቸውን ተላጩ ያላቸው ማነው?
ሲጋራ ማጨስ እንዴት አቆሙ?
በሚቀጥለው ክፍል ኢንሻአላህ
#Part 3⃣

Like🤙🤙
#share #share #share

👇👇👇
@IslamisUniverstiy_public_group

join👇
@IslamisUniverstiy_public_group
😁ለፈገግታ ፈገግታ ሱና ነዉ

አንድ ኢትዮጵያዊ ከህንዳዊ ጀለሱ ጋርስለ ሙታን እያወሩ ነው....
;
;
ሀበሻው:-"እናንተአገርሰውሲሞትእንዴትነውሚቀበረው?"
ህንዳዊው:.-"የምን መቅበርነው?ማቃጠል ነውጂ!?
ሀበሻው:-"የናንተ ባህል ጥሩነው፥ እኛ አገር ሰው የሚቃጠለው በቁሙ ነው።"
😂😂😂😂😂

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
#ታውቃለህ ( ? )
🌾🌾🌾_________
አንዳንዴ ደስታ ፣ ተድላ ፣ መረጋጋትና ሰላም እንደሳሙና ሙልጭ እያሉ አልያዝ ሊሉህ ይችላሉ ፡፡ በምትኩ ሀዘን ፣ ችግር ፣ ትካዜና መረበሽ ያንተ የተባሉ ይመስል ከጀርባህ እንደ መዥገር ተጣብቀው እንደ ጥላህ በሄድክበት ሁሉ ሊከተሉህ ይችላሉ ፡፡
ከሌላው በተለየ መልኩ እንቅልፍህን አጥተህ ብትሰራ የማያልፍልህ
ሰዎችን ለማስደሰት ብለህ ጥቅምህን አሳልፈህ ብትሰጣቸውና ውለታ ብትውልልላቸው እንኳ የሚክዱህና ተመልሰው ጠላት የሚሆኑህ
ስህተቶችን አውቀህ በዝምታ ብታልፍ እንደሞኝ የምትቆጠር አይነት የልፋትና የስቃይ ሰው ልትሆን ትችላለህ ፡፡
°
🌾🌾በተመሳሳይ

👉ከቤተሰቦችህ መሃል አንዱን ሞት ነጥቆህ ይሆናል .....
👉 የተንበሸበሸውና የታጨቀው ካዝናህና ስራህም እንደ ንፋስ ውል ብለው ጠፍተውብህና ከስረህም ሊሆን ይችላል ......
👉ምን አልባት ታመህ ወራትንና አመታትን በአልጋና ቤት ውስጥ አሳልፈህ ይሆናል ....
👉ምን አልባትም ከምትወጂው ባልሽ ጋር ተፋተሽ ይሆናል .....
👉ምን አልባትም ሚስትህ ሚጥሚጣ ሆና ኑሮህን ባጠቃላይ አቃጥላው ሊሆን ይችላል .....
🍀🍀🍀እኚህ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ከየአቅጣጫው እንደንብ መንጋ ወረው ሊነድፉህ ይችላሉ ፡፡ ነገር ግን የሆነው ሁሉ ሆኖ አሁንም አልሏህን ልታመሰግንበት የሚገባ ትልቅና በቃላት የማይገለፅ ውድ ፀጋ አለህ
°
🔰🔰🔰ይህ ታላቅ ፀጋ ምን እንደሆነ #ታውቃለህ ( ? )
°
እኛም ሆነ ሌሎች ፍጥረታቶች የተቸሩት ቃላት የማይገልፀው ትልቁ ፀጋ .... #ፈጣሪያችን_አልሏህ መሆኑ_ነው !
ወልሏሂ ጌታዬ አልሏህ መሆኑን ባሰብኩ ቁጥር መረጋጋትና ሰላም ከውስጤ ይገባል ፡፡

ጌታዬ አልሏህ በነገራቶች ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑንና ልመናዬን የሚቀበል መሆኑን ሳስተውል ብቸኝነቴ ይወገዳል የችግሮቼም ግዝፈት ቀልሎና ተዋርደው ይታየኛል ፡፡
ምክንያቱም ጌታዬ ማድረግ የማይችለው የለም ፡፡ እርሱም ደግሞ ልመናዬን የሚቀበል አዛኝና ቅርብ ነው ፡፡ እና ምን ስሆን ልዘን ? ምንስ ሆንኩኝ ስል ልተክዝ ?


🌹🌹🌹ጌታዬን እያሰብኩ እሩቅ ወደ ሆነ የደስታ ሰፈር በእመነትና በተስፋ ሰረገላ መገስገስ ነው እንጂ
°
ለዚህም ነው ታላቁና አዛኙ ጌታዬና ጌታችሁ አልሏህ በማይሰለቸው ቃሉ ተከታዩን ያለው ....
'
ﻗُﻞْ ﺑِﻔَﻀْﻞِ ﭐﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺑِﺮَﺣْﻤَﺘِﻪِۦ ﻓَﺒِﺬَٰﻟِﻚَ ﻓَﻠْﻴَﻔْﺮَﺣُﻮﺍ۟ ﻫُﻮَ ﺧَﻴْﺮٌۭ ﻣِّﻤَّﺎ ﻳَﺠْﻤَﻌُﻮﻥَ
'
🍁🍁« በአላህ ችሮታና በእዝነቱ ( ይደሰቱ ) ፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው » በላቸው ፡፡
[[ ሱረቱ አል ዩኑስ 58 ]]
°
ውዶቼ ዛሬ ላይ ሀብት ኖሯችሁ በሃብታችሁ ብትደሰቱ ነገ ከነገ ወዲያ ትከስሩና ደስታችሁ ይበንናል ፡፡
በቤተሰቦቻችሁ ብትኮሩና ብትደሰቱ የሆነ ጊዜ ላይ ይሞቱባችሁና ደስታችሁን ይዘው ይቀበራሉ ፡፡


🌴🌴ነገር ግን ..... አንድዬውንና የማይሞተውን አዛኝ ጌታ ወዳችሁ ከተጠጋችሁ እናንተ ደስታን ፍለጋ መሄድ አይጠበቅባችሁም ፡፡ ደስታ የተባለ በሙሉ ያላችሁበት ድረስ መጥቶ ያንበሸብሻችኀል !
°
ውዶቼ ተወዳጁ ጌታችንን እንወቀው ለርሱ ፍፁም ስንሆንም እንውደደው ፡፡ ወልሏሂ ጌታዬን እወደዋለሁ ፡፡ በዚህም ሁሄም ደስተኛ ነኝ ፡፡ አልሃምዱሊላሂ !
ﺃﺣﺒﻚ ﺭﺑﻲ


ለበለጠ ኢስላማዊ መረጃ እና ጠቃሚ እዉቀት በዚህ ይከተሉን

Joinnn
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
#ወቅታዊ #ዜና
┈┈┈•••┈┈┈
.
☞ ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በጦላይ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ #1174_የአዲስ አበባ ወጣቶች ተለቀቁ።
.
☞ አቶ ታገሰ ጫፎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው ተመረጡ።
.
☞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በመጪው ሳምንት የመጀመሪያውን የአውሮፓ ጉብኝት በፈረንሳይና በጀርመን ሊያደርጉ መሆኑን ተዘገበ።
.
☞ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ዴንማርክ አቀኑ።
.
☞ ባለፈው ዓመት ከኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን ቦረቻ ወረዳ ተፈናቅለው የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆች አካባቢው ሰላም በመሆኑ ወደ መጡበት እንዲመለሱ ሽኝት ተደረገላቸው።
.
☞ መንግሥት ባለበት ተደራራቢ የበጀት ጫና ምክንያት ዘንድሮ ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ ሃሳብ እንደሌለው ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ አሳወቁ።
.
☞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በሚገኘው አማሮ ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት እንዳደረሱ የወረዳው አስተዳዳሪ ገለፁ።
.
☞ በሂንዱይዝም እምነት መሰረት የወር አበባ የሚያዩ ሴቶች "ንፁህ" እንዳልሆኑ ተደርገው የሚቆጠሩ ሲሆን፤ ሳብሪማላ የተባለው የአምልኮ ቦታም ዕድሜያቸው ለአቅመ ሔዋን የደረሱ ሴቶች በሙሉ እንዳይገቡ ከልክሏል ተባለ።
======
#ምንጭ: ማህበራዊ ሚድያ

JOIN💫 @Islam_and_Science
@Islam_and_Science
⭐️ #ሚሰጥርህን ለሁለቱም ተው

☞ለጌታህና
☞ለራስህ

⭐️ምድር ላይ ሁለት ሰዎች እንዲወዱህ ጣር
☞እናትና
☞ አባትህ

⭐️ #ሁለት #ሃይለኛ ነገሮች ላይ. ዘውትር
☞ሰላት እና
☞ ትዕግስት

⭐️ሁለት ነገሮችን አትፈራ
☞ርዝቅ እና
☞ሞትን ለምን ሁለቱም በአላህ እጃ ስለሆኑ

⭐️ሁለት ነገሮችን ምንም አታስታውሳቸው
☞ለሰዎች የዋልከው በጉ ነገር እና
☞ሰዎች አንተ ላይ ያደረጉት መጥፎ ነገር ሁለት ነገሮችን ምንም አትርሳቸው


🌿አላህን እና የመጨረሻይቱን ቀን🌴
☞ከፈጣሪህ ብዙ ስትርቅ፥ በፈጠራቸው ፍጡራን ክፉኛ ትፈተናለህ
👍
:::ላራህማኑ ጥራት ይገባው ምስጋና
ሙስሊም አርጎ ለፈጠረን ለረቡና
ከቶ አናፍርም እምነታችነው እስልምና
ቁርአን ነው የኛ የህይወት መመርያ!!
وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ
(إبراهيم)
ISLAM AND SINCE CHANNAL
POST

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
#ምላሳችን #ከእርግማንና ከስድብ እንቆጥብ!
"ሙስሊም ተሳዳቢም ሆነ ተራጋሚም አይደለም"

💫 አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦
"ነቢዩ( ﷺ) ተሳዳቢ፣አስቀያሚ ንግግርን ተናጋሪ ሆነ ተራጋሚ አልነበሩም።"
��【ቡኻሪ ዘግበውታል】

💐 የአላህ መልክተኛ( ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦
"እኔ ተራጋሚ ሆኜ አልተላኩም…።"
【ሙስሊም ዘግበውታል】

💐የአላህ መልክተኛ( ﷺ) እንዲህም ብለዋል፦
"አንድ የአላህ ባሪያ አንዳችን ነገር በሚራገም ግዜ ፦እርግማኗ ወደ ሰማይ ከፍ ብላ ትወጣለች፣ ከዚያም የሰማያት በር ይዘጉባታል፣ከዚያም ወደ ምድር ዝቅ ብላ ትወርድና በሮች በሙሉ ጥርቅም ብለው ይዘጋሉ፣ከዚያም ወደቀኝና ግራ ትመለከታለች ፣ መግቢያ ስታጣ ወደ ተረጋሚው ትመለሳለች ለእርግማን ተገቢ ከሆነ እርግማኑ ይደርስበታል፣ ካለሆነ ግን ወደ ተራጋሚው ትመለሳለች።"
��【አቡ ዳዉድ ዘግበውታል】


💫💫"አንድን አማኝ መርገም ነፍሱን እንደ ማጥፋት ይቆጠራል።"

【ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል】

Join
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
https://t.me/joinchat/AAAAAE38duUeOAlrjpHmUw

☝️ጆይን በሏት ትወዷታላችሁ😉
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✔️✔️ #እውነታ
#ጥቁር #አዝሙድ #ዘይት #ጥቅም""!

🎖 #ለካንሰርና #እባጮች
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከ አንድ የሻይ ማንኪያ የተፈጥሮ ማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ ግማሽ ሠዓት በፊት ይጠቀሙ።

🎖 #ለስኳር #በሽታ
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከተፈጥሮ ማር ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። ካርቦሃይድሬት ያላቸውን ምግቦች በመጨመር ስኳርን በማቆም የአመጋገብ ለውጥ ያድርጉ።

🎖 #ለተቅማጥ
አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ኩባያ እርጎ ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ።

🎖 #ለደረቅ #ሳል
ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከቡና ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። ጀርባዎና ደረትዎን በዘይት ይሹት።

🎖 #ለጆሮ #ህመም
በስሱ የተቆላ አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ይውሰድ ከዚያም ጥቂት የኦሊቭ ዘይት ጠብታዎች በመጨመር በደንብ ይቀላቅሉት። ሰባት ጠብታ በሲሪንጅ ውስጥ ይክተቱ ከዚያም ጠዋት እና ማታ ጆሮዎ ውስጥ ይጨምሩ።

🎖 #ለዓይን #ህመም እና #ለእይታ #ችግር
ወደ መኝታ ከመሄድዎ ከግማሽ ሠዓት በፊት የአይን ቆብዎን በጥቁር አዝሙድ ዘይት ይሹት። ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ኩባይ የካሮት ጭማቂ ጋር በመቀላቀል ይጠጡ።

🎖 #ለፊት #ፓራሊሲስ
አንድ የሻይ ማንኪይ ዘይት ለብ ባለ ውሃ ውስጥ በመጨመር እንፋሎቱን ይታጠኑ።

🎖 #ለጉንፋን እና ፍሉ
አንድ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ በፊት ይውሰድ። በእያንዳንዳቸው የአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ጥቂት ጠብታዎች ይጨምሩበት።

🎖 #ለሃሞት #ጠጠር እና #ለጉበት #ጠጠር
አንድ ትልቅ ማንኪያ የጥቁር አዝምድ ፍሬ ከማር ጋር በብርጭቆ ውስጥ ይቀላቅሉት ጥቂት ለብ ያለ ውሃ ይጨምሩበት። በመጨረሻም በመጨረሻም አንድ የሻይ ማንኪያ ዘይት ይጨምሩበት ይህን ውህድ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ይጠጡ።

🎖 #ለአጠቃላይ #ጤንነትና #ደህንነት
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከአንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል በየቀኑ ይጠቀሙ። ወይም ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ዘይት ከማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ በፊት በየቀኑ ይጠቀሙ።

🎖 #ለፀጉር #መሳሳት እና #ያለ #ዕድሜ #ሽበት

በመጀመሪያ ፀጉርዎን ይታጠቡ ከዚያም በቂ የሆነ የኦሊቭ ዘይት ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር በመቀላቀል ይቀቡት። ከአንድ ሠዓት ቆይታ በኋላ ያለቅልቁት ወይም ይታጠቡት።

🎖 #ለራስ #ህመም እና #ማይግሬን

ከግንባርዎ ግራ ክፍል ትንሽ ዝቅ ብሎ ወይም ቴምፕል በሚባለው የጥቁር አዝሙድ ዘይት በመቀባት ይሹት። ጥቂት ጠብታዎች በአፍንጫዎ ቀዳዳ እና ጭንቅላትዎ ላይ ያድርጉ። በቀን ሁለት ጊዜ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬና ማር ይብሉ።

🎖 #ለማስታወስ #ችሎታ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል በቀን ሶስት ጊዜ ይመገቡ።

🎖 #ለአፍ #ኢንፌክሽን #ቫይረስ
ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬ በአፍዎ ውስጥ ከ 10 – 15 ደቂቃ ይያዙት።

🎖 #ለጡንቻ #ህመም
አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ከማር ጋር በመቀላቀል በቀን ለሶስት ጊዜ ይውሰድ። የቅልጥም መረቅ በየቀኑ ይጠጡ። የቻሉትን ያክል ዘቢብ በየቀኑ ይመገቡ።

🎖 #ለሪህና #ጀርባ #ህመም
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ሞቅ በማድረግ የሚያምዎትን ቦታ ይሹት። በየቀኑ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ እና ማር ይመገቡ።

🎖 #ለሆድ #ህመም
በአንድ ትልቅ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከማር ጋር በመቀላቀል ይጠቀሙ። ጥቂት የፔፐርሜንት ሻይ ይጠጡ ከዚያም የረሃብ ስሜት ከተሰማዎት የተቀቀለ ሩዝ ውሃ ይጠጡ።

🎖 #ለጥርስ #ህመምና #ድድ #ኢንፌክሽን

በኩባያ የሎሚ ጭማቂ በማድረግ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ይጨምሩበት ከዚያም ያፍሉት። ከዚያም የፈላው ሎሚ ቀዝቀዝ ሲል በዚህ ውህድ ፈሳሽ አፍዎን ይጉመጥመጡበት/ይታጠቡበት።

🎖 #ለሆድ #ትላትል
ሁለት የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከግማሽ ኩባያ ሎሚ ጋር በመቀላቀል ይህን ውህድ ያሙቁት። ከዚያም ቡርሽ ወይም ሌላ ነገር በመጠቀም የሆድና ጉበትዎን አካባቢ ይሹት።

አንብበው ሲጨርሱ #Share አይርሱ ።

Join👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
#እዉነተኛ #ፍቅር
#part 7⃣

#አቡጣሊብ ወጣቱ ያለውን ባለማመን እንዴት ብለው ጠየቁት፡፡ መሀመድም "የጋብቻ ጥያቄ አቅርባልኝ ሽማግሌ እንድልክ ተስማምቼ ነው የመጣሁት "
አቡጣሊብም "አትሸንገል የከድጃ ንግግር እጅግ ሚስጥር ያለው ነው" አሉ፡፡ መሀላቸው የነበረው አቡለሀብም " #የወንድሜ #ልጅ ሆይ አንተ ከድጃን ማግባት አትችልም አትመጥንህምና የአረቦች መሳለቂያ አታድርገን" አለ፡፡
ሌላኛው አጎታቸው አባስም እንደመቆጣት ብሎ "ለምንድነው የምትዘላብዱት ወላሂ መሀመድ በመካ ውስጥ እጅግ በጣም ውብና ጥሩ ስነምግባር ያለው በህዝቡ ዘንድ መሀመዱልአሚን የሚል ስም የተሰጠው ታማኝ ልጅ ነው ታድያ ከድጃ ለእሱ በምኗ ነው የምትከብደው ንግግርን ማጥላላት ምንም የሚጠቅም ነገር አይደለም፡፡ ተነሱ ሄደን የከድጃን ወላጅ እንጠይቅለት" አሉ፡፡
#መሀላቸው ፀጥታ ሰፈነ አክስታቸው ሶፊያ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ከድጃ ቤት ሄደች፡፡ እንደደረሰችም በሩን በዝግታ አንኳኳች በሩን የከፈተችው ከድጃ ነበረች፡፡ ከዚያም አርሂቡ ብላ በፈገግታ ወደ ውስጥ እንድትገባ ጋበዘቻት #የሚቀመስ #ነገር ለማምጣት መነሳቷን ባወቀች ጊዜ ሶፊያ እንዲህ አለቻት
"እኔ ምግብ ፈልጌ አልመጣሁም ወንድሞቼ እየጠበቁኝ ነው፡፡ በርግጥ አንቺ ጋር የመጣሁት የሰማሁት ጉዳይ እውነት መሆኑን ላጣራ ነው " አለቻት፡፡ ከድጃም (ረዐ) "የመጣሽበት ወሬ በርግጥ እውነት ነው፡፡ #ከፈለጋችሁ በአደባባይ ማውራት ትችላላችሁ እኔው ነኝ ጥያቄውን ለመሀመድ ያቀረብኩለት የፈለገው ቢመጣ መሀመድን ከማግባት የሚያግደኝ ማንም የለም" አለች፡፡
ሶፊያም በከድጃ ንግግር ተገረመች፡፡ ከዚያም " #ከድጃ #ሆይ እውነት አለሽ መሀመድን የመሰለ ውብ ሰው በመውደድሽ የሚያጋጥምሽ ነውር የለም" አለቻት፡፡
#ከድጃም በሶፊያ ንግግር ተደስታ ወደ ጓዳ በመግባት ውድ ቀሚስ አምጥታ አለበሰቻት ደስታውን መቆጣጠር እስኪያቅታት ድረስ እቅፍ አድርጋም ሳመቻት፡፡ ከዚያም ብስራቱን እንድትናገር ወደ ወንድሞቿ ሸኘቻት፡፡ ሶፊያ ቤት እንደደረሰች ዠወንድሞቿና የመሀመድ (ሰዐወ) ፊት በፈገግታ ተቀበላት ሁሉም ጥሩ ዜና ይዛ የመጣች መሆኑን ያወቁት በውድ ልብስ አሸብርቃ መመለሷን ሲያዩ ነው፡፡ ወንድሟ አቡጣሊብም "አንቺ እውነተኛይቱ ልጅ ሆይ በምን መጣሽ" አሉ፡፡
#ሶፊያም "ከድጃ እውነቷን ነው በመሀመድ ፍቅር ወድቃለች በርሷ በኩል ያለው ጣጣ አልቋል፡፡ አሁን የሚቀረው አባትየውን መጠየቅ ብቻ ነው፡፡ ከከድጃ የምትሻል ሌላ ሴት ለማግኘት ሊከብድ ይችላል " አለቻቸው፡፡
#የመሀመድ #አጎቶች ደስ አላቸው ፤ አቡለሀብ ሲቀር ፣ ወድያው ምርጥና የክብር ልብስ ለብሰው መሀመድን (ሰዐወ ) ከኋላ አስከትለው ወደ ኩወይልድ ቤት አመሩ፡፡
#እግረመንገዳቸውን አቡበከር (ረዐ) ወደ እነሱ ሲመጣ አገኙት፡፡ ከዚያ አቡጣሊብ
" #የአቡቀሀፉ ልጅ ወዴት እየሄድክ ነው" አሉት ፤ አቡበከርም (ረዐ ) "የአብድልሙጠሊብ ልጆች በርግጥ ወደ እናንተ ለጉዳይ እየመጣሁ ነበር" አሉ፡፡
#አቡጣሊብም "ጉዳይህ ምን ነበር " ሲሉት አቡበከርም "ማታ ህልም አይቼ ነበር እናም ፍቺውን ልጠይቃችሁ መምጣቴ ነበር " አሉ፡፡ ህልሙ ምን እንደሆነ ጠየቁት፡፡
#አቡበከርም "ከአቡጣሊብ ቤት አንዲት ኮከብ ወደ ሰማይ ትሄድና ከሌሎች ኮከቦች ጋር ትደባለቃለች ከዚያም ተመልሳ ወደ ሁለት ቤቶች ትገባለች፡፡ አንደኛው ቤት የከድጃ ቤት ነው አንዱ ደሞ የሱዩዋን ቤት ነው፡፡ "
#አቡጣሊብም "እኛ አሁን ወደ አልካቸው ቤት ለጉዳይ እየሄድን ነው ህልምህ ጥሩ ብስራት አለው፡፡ ኩወይልድ ፍቃደኛ ከሆነ ለመሀመድ አሚን ከድጃን ለጋብቻ ልንጠይቅለት ነው፡፡ #ኮከቡ መሀመድ ነው የገባበት ቤት ያው እንዳየኸው የከድጃ ቤት ነው" በማለት #ህልሙን #ፈቱለትና #መርቀውት

#part 8⃣

ይ.........
.....ቀ......
ጥ............
.......,ላ........
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ል


🎖SHARE🎖

JOIN👇👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
መጋቢት 1993 ዓም‹‹#ኬቨን #ካርተር››
የተባለ ደቡብ አፍሪቃዊ የፎቶግራፍ ባለሙያ ሱዳን ውስጥ ተከስቶ በነበረው ርሀብ ከተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ልኡክ ጋር ለበጎ አድራጎት ስራ ወደ #ደቡብ #ሱዳን ያመራል ፡፡ በአንዷ መከረኛ እለትም ይህቺን ከታች የምትመለከቷትን ምስል በካሜራው አስቀረ፡፡👇👇
✔️ #በጣም #ልብ #የሚነካ #ታሪክ

መጋቢት 1993 ዓም‹‹#ኬቨን #ካርተር››
የተባለ ደቡብ አፍሪቃዊ የፎቶግራፍ ባለሙያ ሱዳን ውስጥ ተከስቶ በነበረው ርሀብ ከተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ልኡክ ጋር ለበጎ አድራጎት ስራ ወደ #ደቡብ #ሱዳን ያመራል ፡፡ በአንዷ መከረኛ እለትም ይህቺን ከታች የምትመለከቷትን ምስል በካሜራው አስቀረ፡፡

💫💫‹‹ርሀብ አድቅቆት የገዛ ራሱን መሸከም ያቃተው ህፃን ልጅ እና ይህን ህጻን ለመብላት የቋመጠ ጥንብ አንሳ›› የረሀብን ክፉ ገፅታ ፣የድርቅን አሰቃቂ ሁነት፣የምስኪኖችን
እልቂት ፣ቃላት ሊገልፁ ከሚችሉበት አቅም በላይ በሆነ መንገድ በድንቅ ካሜራው ለአለም አስቃኘ፡፡

✔️‹‹ቀጫጫ እጆች እንኳን ለመሮጥ፣ለመቦረቅ ይቅርና የገዛ አካሉን ለመሸከም ያዳገተው እግር፣ መቆም የከበደው ገላ
እና በርሀብ በሞቱ ሰዎች የደለበ ፈርጣማ አሞራ!!››
*
ይህን ፎቶ ከወራት በኃላ በ 1993 ዓም ለኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ተሸጦ ታተመ፡፡ ምስሉ በመላው አለም ታየ፡፡ፎቶግራፈሩ፣ክብር እና ዝናን አተረፈ፡፡ ተሸለመ፣ተሞገሰ፡፡ዓለም ስለፎቶግራፈሩ አወራ፡፡
☞☞☞☞☞☞☞☜☜☜☜

💫ከዚህ ሽልማት በኃላ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በአንድ አስተዋይ ጋዜጠኛ የተወረወረች #ያልተጠበቀች #ጥያቄ ግን የህይወቱን አቅጣጫ እስከወዲያኛው ቀየረችው፤ አመሳቀለችው፡፡

⭐️⭐️‹‹ህፃኗ ልጅ እንዴት ሆነች….ታደግካት?!!>>
አይኖቹ ፈጠጡ….ላብ አጠመቀው………ቃላት ከአንደበቱ ጠፋ!!
……….. #በምናብ ወደ ደቡብ ሱዳንዋ የርሃብ መንደር ተሰደደ፡፡ ጠያቂው ግን ድጋሚ በጩኸት ጠየቀ ‹‹ #ህፃንዋን #ልጅ #ታደግካት ?? ነው ፎቶዋን ብቻ ነው ይዘኸው የመጣህ????››

#ካርተር #ጋዜጣዊ #መግለጫውን አቋርጦ ወጣ፡፡ ከወዳጅ ከዘመድ ሁሉ ተሰወረ፡፡ ከራሱ ጋር ተጣልቶ ለብቻው ውሳኔ አልባ ዶሴ ከፈተ፡፡ በገዳይዋ ፊት ጥሏት የሄደው የጎስቋላ ህፃን ነፍስ ለወራት እንቅልፍ ነሳው፡፡

✔️ካርተር ራሱን ወነጀለ፡፡የፎቶግራፍ ሽልማቱን ባሸነፈ #በሦስት #ወሩ በልጅነቱ ሲቦርቅ ባደገባት ‹‹ #ፓርክሞር›› በተባለች ለምለም ቀዬ በ33 አመቱ እራሱን ገድሎ ተገኘ፡፡ራሱን የሞት ፍርድ ፈረደበት ፡፡😔😔
*

💫💫በሞቱ ዋዜማ ላይ ሆኖ ለወዳጅ ዘመዶቹ ባስቀረው ማስታወሻ የሚከተለውን ፀፀት አሰፈረ ፤

✔️" #ካለኝ #ነገር ቀንሸ አልሰጠሁም፡፡ እኔን ለማኖር ስራየን ብቻ ሰራሁ፡፡ሚጡ ከርሀብ ጋር ስትታገል ጥንብ አንሳው በእሷ ጠግቦ ይሆናል፡፡ ሚጡዋ፣ #የአሞራው #እራት ስትሆን፣በሚጡ ርሀብ እኔ ተሸለምኩ፡፡ይህም እኔን ሚጡ ወዳለችበት የሞት ጎዳና እንድሄድ ፀፀቱ አስገደደኝ፡፡ደህና ሁኑ ዘመዶቸ፡፡
☞ሰው ሲራብ፣
☞ሲቸገር አትዮ፡፡ካያችሁም ከሌላችሁ ቀንሳችሁም ቢሆን እርዱ፡፡ የህሌና ቁስል መፈወሻ የለውም ፡፡
ራሳችሁን ከህሌና ቁስለት ታደጉ፡፡ "

ISLAM AND SCIENCE
══ •⊰✿🍃✿⊱• ══

🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
1⃣0⃣ #የሪዝቅ #መክፈቻ #ቁልፎች

⭐️ኢስቲግፋር እና ተዉባ፣

⭐️ እውነተኛ የሆነ የአላህ ፍራቻ፣

⭐️ መስፈርቱን ያሟላ ዱዓእና የተመረጡ አዝካሮችን ማብዛት፣

⭐️ ነቢዩን መውደድ እና በርሣቸው ላይ ሰለዋት ማውረድ፣

⭐️ ዘካን ማውጣት ሰደቃ መስጠት፣

⭐️ ለደካሞችና ችግረኞች መልካም መዋል፣

⭐️ እዉነተኛ መመካትን በአላህ ሱ.ወ. መመካት፣

⭐️ ለእናት አባት በጎ መዋል፣

⭐️ ለአላህ ሱ.ወ. ምስጋናና ዉዳሴ ማድረስ፣

⭐️ ኒካህ ማድረግ

💫💫ሰምተው ከሚተገብሩ። ያድርገን


ISLAM AND SCIENCE
══ •⊰✿🍃✿⊱• ══

🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌸 ት ዳ ር #ቀልድ #አይደለምና

✔️ ምርጫዎንና ሚዛንዎን ያስተካክሉ
ነቢዩ ﷺ ለሴቷ ቤተሰቦች እንዳሉት «ዲኑና ስነምግባሩን የምትወዱለት ሰው ሲመጣችሁ ዳሩት። ያለዚያ በምድር ላይ ብልሽትሽትን ታነግሳላችሁ።»


💐 #ለትዳር የምትመርጪው ሰው በዲኑ ላይ ትጉ የሆነና ስነምግባሩም መልካም የሆነ ሰው መሆን አለበት። ወንዱንም ሲመክሩ «ዲነኛዋን ምረጥ ያለዚያ እጆችህ ኣመድ አፋሽ ይሆናሉ።» ብለውሃልና አንተም በሌሎች አላፊ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ ትተህ ከትዳር ክስረት የሚያድንህን መልካም ሰበብ ተከተል።

⭐️ #በዚህም #መሰረት ለትዳር የሚሆን ጓደኛ ማግኘት ከባድ ከሆነና ማህበረሰቡ ተዳክሞ ትውልዱ ፈዝዞ ደህና የሚባል ወይም የምትባል ዲናቸውን በአግባቡ የሚከተሉ የታዳከመበት ማህበረሰብ መሃል ከተገኘን እንኳን ቢያንስ ቢያንስ የሙስሊምነታችን መሰረታዊ መለኪያ የሆኑትን አርካኑል ኢስላምን ከያዙት መሃል ልንመርጥ ይገባል።

✔️ #አሳዛኙ #ጉዳይ ግን ዛሬ ዛሬ ስንትና ስንት ለዲናቸው የተንበረከኩ ሸባቦች በሞሉበት ሀገር በርካታ ተጋቢዎች ሰላት የማይሰግድን ወይም የማትሰግድን ያለ ምንም እፍረት ሲያገቡ ይታያል። በአንፃሩ በሌላ ስነ ምግባሩ ወይም ስነ ምግባሯ ብልሹ የሆኑትን ካወቁ ግን ይጠየፏቸዋል። ተመሳሳይ ስሜት ከሌላቸው በስተቀር ይርቋቸዋል።

💫💫በዚህ ረገድ ታላቁ ሊቅ ሸይኹል ኢስላም ተቂዩ ዲን ረሂመሁላህ የሚመክሩንን ልጨመርላችሁ።

✔️✔️«ሰዎች ሁሉ አንድ ሰው ሌባ የሆነችን ሴት ወይም ዝሙተኛ የሆነችን ወይም አስካሪ ነገር ጠጪ የሆነችን ሴት እና የመሳሰሉትን ማግባቱን የሚቃወሙ እስከሆነ ድረስ #ሶላት የማትሰግደዋን ደግሞ ከዚህ በባሰና በከበደ መልኩ መቃወም የግድ ይላቸዋል። የኢስላም ሊቃውንት በጋራ አቋም እጅግ በከባዱ የሚቃወሙት ይህንን ነውና።

✔️ምክንያቱም ያቺ የማትሰግደዋ ከዝሙተኛይቱም፣ ከሌቢቱም ሆነች ከአስካሪ ነገር ጠጪዋ የከፋች መጥፎ ነችና።»
[ጃሚዑል መሳኢል: 4/142]
[ ﺟﺎﻣﻊ ﺍﻟﻤﺴﺎﺋﻞ لابن تيمية - (ﺝ٤/ﺹ١٤٢) ]
አላህ ለልቦናችን ብርሃን ይስጠን። ጠቃሚ እውቀትንም ይለግሰን። የምንሰራበትም ያድርገን።
~~~~~~~~~

💧══ •⊰✿💚✿⊱• ══💧


┏━ 🍃 ━━━━ 🍂 ━┓
🎖ISLAM AND SCIENCE🎖
┗━ 🍂 ━━━━ 🍃 ━┛

🎖SHARE🎖

JOIN👇👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😁ለፈገግታ
#አብይን___ከነካህ :-
እድሜህ ከሚስ ኮል ይጠር
ኑሮህ ቫይብሬት ሞድ ላይ ይሁን
ችግሮችህ እንደ ኮንታክ ሊስቶቼ ይብዙ
ፎቶ አይዉጣልህ
የድሮ ቴሌ ያስተዳድርህ
ሽንት ቤት ለመጠቀም ስትሄድ ሰው አለ ይበሉህ
ፀጉር ቤት ስትሄድ 19 ሰው ይቀድምሃል ይበሉህ
በሰው በር ላይ ስታልፍ እጣቢ ይድፋብህ
እንራጀህ ጀሶ ይብዛበት
ወጥህ በጨው ብዛት የመረረ ይሁን
ቤትህን ኦርጅናል ሳይሆን የቻይና ዕቃ ይሙላው
ልጅ ለማጫወት ስታነሳ ፊትህ ላይ ይሽናብህ
ታክሲ ላይ ወራጅ ስትል 3 ኪሎ ሜትር አሳልፎ ያውርድህ
ኮንዶምንየም ተመዝግበህ ዕጣው ከሞትክ በኃላ ይውጣልህ
ዕቁብ የደረሰህ ቀን ሌባ ይዝረፍህ
አጥበህ ያሰጣህው ልብስ ይሰረቅ ( በወር 2 ግዜ)
እርግማኔ ይድረስህ
😁😁

JOIN👇👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
#እውነተኛ #ፍቅር
#ክፍል 8⃣

#ከድጃን ያፈራው ቤተሰብ በማህበረሰቡ ዘንድ ጥንታዊ ከበሬታ የነበረው ለህዝብ ግንኙነት የቅርብ ተጠሪና ነገር ቆራጭ የነበረ ነው፡፡ በቁሰይ አማካኝነት በካዕባው አቅራቢያ ዳረል ነድዋ በሚል ስያሜ በሚታወቀው #ታላቅ #አዳራሽ ውስጥ የነገዱ ታላላቆችና ነገር አዋቂዎች በህዝባዊ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጡ ናቸውና ይከበራሉ፡፡
#የመሀመድ (ሰዐወ) አጎቶች ኩወይልድ ቤት ደረሱ ፤ እንግዶቹ እንደሚመጡ በአገልጋዩ መልዕክት ደርሶት የነበረው የከድጃ አባትም በጥሩና በከፍተኛ ክብር ተቀበላቸው፡፡ ኩወይልድ እንግዶቹ የመጡበትን ምክንያት ባያውቅም ከድጃን ግን ለጋብቻ ይጠይቃሉ የሚል ግምት በጭራሽ የለውም፡፡
#እንግዶቹ ለመስተንግዶው ምስጋና አቀረቡ ከዚያም አቡጣሊብ እንዲህ አለ "ምስጋና ለአላህ ይሁን ኩወይልድ ሆይ እንደምታውቀው እኛ የአጎታሞች ጎሳዎች ነን፡፡ #አንዳችን ለአንዳችን ጋሻና መከታ ሆነን በቋሚነት በመሀከላችን ምንም መበዳደል ሳይኖር ተከባብረን በጨዋ ደንብ ኖረናል፡፡ #እናም ካንተ ጉዳይ አለን አንተ ደሞ ጉዳያችንን እንደምትቀበለውና እንደምትፈታው ባለሙሉ ተስፋ ሆነን ነው የመጣነው " #ሲሉት ኩወይልድ ጉዳያቸው ምን እንደሆነ ጠየቃቸው፡፡
"ልጅህን ከድጃ ለጋብቻ እንድትሰጠን ነው የመጣነው" አሉት፡፡
#ኩወይልድም "ለመሆኑ የሚያጫት ሰው ማነው"፡፡ አቡጣሊብም "ታማኙና ፀባየሸጋው መልከመልካሙ መሀመዱልአሚን ነው" አሉት፡፡
ቁረይሾች በሚጠሩት አጠራር ኩወይልድ የተጠራውን ስም ሲሰማ ፊቱን እንደማጨፍገግ አደረገና ከዚያም " #የአብድልሙጠሊብ ልጆች ወደ ኀላ ቀራችሁ ልጄ ከድጃ እንደምታውቋት የተከበረችና እድለኛ ሴት ናት፡፡ #ከቁረይሾች ሴቶችም ትበልጣለች ፤ አላህ በሀብት ያበለፀጋት እጅግ የተከበሩና በሀብታቸው አንቱ የሚባሉ ሹማምንቶች ለጋብቻ ጠይቀዋት ከነሱ የተብቃቃችና እንቢ ያለች ናት፡፡ ታዲያ ደሀና የቲም ለሆነ ሰው እንዴት ፍቃደኛ ትሆናለች አትሆንም " አላቸው፡፡
ለሽምግልና የመጡት የመሀመድ አጎቶች #ኩወይልድን በጥሩ አነጋገር ሊያሳምኑት ሞከሩ እሱ ግን ጭራሽ እንደማይሆን ነገራቸው፡፡ #መሀመድን ከከድጃ ጋር በንፅፅር እያቀረበ እንደማይሆን ገለፀላቸው፡፡ አቡጣሊብም በብስጭት
" #ኩወይልድ #ሆይ መሀመዱልአሚን ሚስት ፈልጎ ቢጠይቀን ኖሮ ከቁረይሽ ውስጥ ምርጧን እናቀርብለታለን ሀብት ፈልጎ ቢጠይቀን እኛ ዘመዶቹ አሱን ባለሀብት እናደርገዋለን" አሉት፡፡ ሀምዛም "ፀሀይንና ጨረቃን እኩል ማነፃፀርህ ጅልነት ነው" #በማለት በቁጣ ተናገረውና ወንድሞቹን አስከትሎ ከቤቱ ወጡ፡፡
ከድጃ የሽማግሌዎቹ መምጣት ቀድማ ታውቅ ስለነበር አገልጋይዋን ሁኔታውን እንድታጣራላት ልካት ነበር፡፡ አገልጋይዋም የኩወይሊድ እንቢ ማለት ነገረቻት፡፡ ወድያውኑ ከድጃ አጎቷ ወረቃ በአስቸኳይ ተጠርቶ እንዲመጣ ላኸችበት፡፡ አጎቷም መጣ፡፡ ከድጃ ቤት ሲጀርስ ከድጃ አንድ ስፍራ ትክዝ ብላ ቁጭ እንዳለች አያት አጠገቧ ቁጭ አለና
.
.
. #Part 9⃣
ይቀጥላል

JOIN👇👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
#ወርቃማ #አባባሎች 🔘
~
🔹ከልምዶች ሁሉ ጎጂ☞ጭንቀት
🔹የሚያኮራ ስራ. ☞ሰወችን መርዳት
🔹አስቀያሚ ባህሪ. ☞ራስ ወዳድነት
🔹መጥፎ ልማድ ☞መስረቅ
🔹ትልቅ የተፈጥሮ ሀብት☞ወጣትነት
🔹ትልቅ መሳሪያ ☞ ብርታት
🔹መጥፎ ፀባይ ☞ ይሉኝታ
🔹ቆንጆ ጌጥ ☞ፈገግታ
🔹አደገኛ ስብከት☞አሉባልታ
🔹ትልቅ ስጦታ ☞ምክር
🔹የሰዉ ልጅ እንቆቅልሽ ☞ኑሮ
🔹አደገኛ መሳርያ☞ ምላስ
🔹ራስን የመጉዳት ዘዴ ☞ማልቀስ
🔹በሀይል የተሞላ ቃል ☞እችላለሁ
🔹ልንፈታዉ የሚገባን ችግር ☞ፍርሀት
🔹ዉጤታማ የእንቅልፍ ክኒን ☞የአእምሮ እረፍት
🔹መጥፎ የዉድቀት በሽታ ☞ከስህተት ይቅርታን
አለመጠየቅ
🔹የህይወት ሀይለኛ ጉልበት ☞ አእምሮ
🔹ከህይወት ልምዶች የምድር ታላቅ ደስታ ☞መስጠት
⚂ወዳጀ ሆይ⚂
ትላንት ታሪክ ነዉና ተርከዉ
ዛሬ ቁምነገር ነዉና ተጠቀምበት
ነገ ምስጢር ነዉና ድረስበት
★ለመነሳት ከፈለክ መዉደቅህን አምነህ ተቀበል★
🔘
"መልካም ውሎ" ለወዳጅዎ "ሼር" አይርሱ

ISLAM AND SCIENCE
══ •⊰✿🍃✿⊱• ══

🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science
@Islam_and_Science