ISLAMIC SCHOOL
12.6K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
#ጠቃሚ_#የህይወት #ስንቅ
(ሙሉን ያነበበ ሰው ፣ የሆነ ነገሩ ይቀዪራል)

ማንበብ ያደልባል
👉ሁላችንም የቻልነውን በመቋጠር እንለወጥ

#ያለፈ #ነገር #አይቀዪርም ፣ ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው ፣ ካለፈው ነገርህ ተማር

እንጅ በፍፁም አታማርር ፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም
የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነትአይገልፅም ፣

#ማንነትህ #አንተ #ውስጥ #ነው #ያለው ፣ መልካም አድርግ ሌላውን
እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣
ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና ለሁሉም ጊዜ አለው ።


#መኪና #ገዛ #ብለህ "እኔስ" አትበል ጊዜህ ሲደርስ
መኪናዎች ወይም ‘ፕሌን’ ትገዛለህ ፣ ያውም
ለመኖር አስፈላጊ
ከሆነ ፣ ደግሞም እንዴት እንደገዛው የት
ታውቃለህ ?
ተወው በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው ።

#በሰዎች #ደስታ #ደስ #ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ
እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣
ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት
አይደለም ። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ
ከተጎዳው ሰው ጋ
ሁን ፣ አስተውል ።


#ጊዜ #የማይፈውሰውና #የማይቀይረው #ነገር #የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣
በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውና
የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት
ስራ መስራት
ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤
አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው
፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ #አንተም #ጥቂትም sብትሆን
ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ምንድነው? #ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው ፣ የድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን)
እየሰሩ መኖር ነው ፣ ምንድነው ??? #እባክህ #ፈልገው አጎልብተው ጀምረው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣
በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው ።
:

አስተውል ፣ #መልካም #ነገር #ሁሉ #ከፈጣሪ #መጥፎ
#ነገር #ሁሉ #ደግሞ #ከሰይጣን #አይደለም#ፈጣሪ #መጥፎን #ወደ #መልካም
#የመቀዪር #ብቃት #አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ
ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ።

መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር
እንዲገጥምህ ማመቻቸት
ነው ፣ መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም ።
:
#የሰራኸውና #የምትሰራው #ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ
ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "#ሰው #የዘራውን
#ያጭዳል" የሚለውን ስታውስ ፣
ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣

#ራስህን #አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ
አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም
የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ ።


ለራስህ ስትል መልካም ሁን ፣ በጎውንም አስብ።
#ለራስ #ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም ።
#አትፍረድ ፣ የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም ። #ፍርድ #የአላህ #ነው፣ ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል ፣ ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ
ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት ። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል ።
:
ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣ አበረታታው ፣ እንደማይጠቅም አትንገረው ፣
ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ
አትሁን ። #መልካም #ጓደኛ #ከፈጣሪ #የሚሰጥ #ጸጋ #ነው ። መልካም ጓደኛ ፣ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል ታድለሃል ። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ
መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ።

#ያለ #መጠን #ማሰብ #ጭንቀትን#ሀዘንን
#ያስከትላል
ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ ፣
መመለስ በማትችለው
ነገር ላይ አትወጠር ፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ
። አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ ።

ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር ።ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው ፣ "ያስከፍላል"ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ
#ደግ #ሁኑ ፣ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ
በረከታቸው ሰላማቸው ልክ የለውም ።

ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ ፣ ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ
ሲርቅ ወይም
ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል ። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ
ናቸው ። በራስህ በአፈጣጠርህ ደስ ይበልህ ፣ውለህ
በመግባትህ ደስ ይበልህ ። በአለህ ትንሽ ነገር ደስ ይበልህ ።

ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ
አይኑርህ ። #በመውደድ #የተጠመደ #ሰው
ለመጥላት ጊዜ የለውም።

#እድሜህን #በተመለከተ ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው ።
ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳዪኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።
:
#የምናማርረው #የተሰጠንንና #የሆነልንን#ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ
ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ።
#ሰላምና #ጤና ፣ ከመልካም አስተሳሰብና በጎ
ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ።
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

⚠️የምንፓስተውን በዝምታ እያነበባቹ ሼር የማታደርጉ አስሉ ወይ አስነጥሱ ብቻ የሆነ ነገር አድርጉ....ደህንነታቹ ሀሳብ ሆኖብናል አለን በሉን 😉
👍ሼር


Join👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
👍1
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY via @like
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሙስፊር ታሪክየአምስት አመት ህፃን..የሚሰግድን ሰዉ አላህ ይወደዋል ሲባል ሰጋጅ እና አንደኛ ሶፍ ሰጋጅ ሆነ..ከእለታት አንድ ቀን ሙስፊር በጣም ታመመ ..ግን መስጊድ አትሂድ ሲባል..እሄዳለሁ ለምን አላህ ያድነኛልምክንያቱም አላህ የሚሰግዱትን ይወዳል #ኻሊድረሻድ
@IslamisUniverstiy_public_group
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
#ወቅታዊ #መረጃ

#ፕሬዚዳንት #ኢሳያስ #አፈወርቂ ለጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል

⭐️ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።
#ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

☞ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ወደ ተግባር ከተሸጋገረ ጊዜ አንስቶ ጥልቀት እያገኘ በመጣው በሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ተናግርዋል።

#በተጨማሪም በንግድና ልዩ ልዩ ትብብሮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያካሂዱም ነው ሀላፊው የተናገሩት።
ለሁለት አስርት ዓመታት ግንኙነታቸውን አቋርጠው የቆዩት ሁለቱ ሀገራት፥ በወራት ውስጥ ግንኙነታቸውን አድሰዋል።

☞ሀገራቱ በጦርነት ምክንያት ተዘግቶ የነበረውን ድንበራቸውን ከመክፈት ጀምሮ የዓየርና የየብስ ትራንፖርትን ጀምረዋል።
በየዋና ከተሞቻቸውም ኤምባሲዎቻውን ከፍተው መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ጀምረዋል።

🔰🔰 ለኢሳያስ አፈወረቅ #ደሴ# ከተማ ምን አስተዋፅኦ አርጋለች፡፡

#ደሴ #ከተማ እና #ኢሳያስ #አፈወርቄ

☞ የኢሳያስ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቂ #የደሴ #ማዘጋጃ ቤት ሰራተኛ ነበሩ።

☞ኢሳያስ አፈወርቂ የሀይስኩል ትምህርቱን የተማረው #ደሴ #ወይዘሮ #ስህን
ትምህርት ቤት ነው።

#ደሴ ወ/ሮ ስህን ት/ቤት የ1960ዎች የኢትዮጵያ ፖለቲካ አድባር ነበረች።
ብርሃነመስቀል ረዳ ፣ ነገደ ጎበዜ ፣ ዋለልኝ መኮንን ፣ ጥላሁን ግዛው እና
ኢሳያስ አፈወርቂ አ ነዚህ ሁሉ ጂያንትስ የአንድ ዘመን የወ/ሮ ስሂን
የፖለቲካ ፋብሪካ ውጤቶች ናቸው።

💫 በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ወ/ሮ ስህን
ያለ ጉዶችን የፈጠረ ት/ቤት እግራችሁ እስኪዝል ድረስ ብትፈልጉ
አታገኙም ።

☞ወ/ሮ ስህን ዝም ብሎ ስትገልጡት ብትውሉ የማያልቅ
መፅሀፍ ማለት ነው።

☞ ለኢሳያስ በኢትዮጲያ ለነፍሱም ለስጋውም የሚቀርበው #ደሴ ከተማ ናት።
☞ ዶ/ር አቢይ አህመድ በዚህ ጉብኝት ደሴን የጉብኝቱ አካል ባያደርጉት ደስ ይለናል፡፡ #ደሴ ከተማ ለሱ ባለ ውለታዋ ነች።👌

💠 ለማንኛውም ደሴ ከተማ ወ/ሮ
ስህን ለኢሳያስ አፈወርቂ እጅግ በጣም ባለውለታው ከተማና ት/ቤት
ናቸው። #ምናልባትም #ኢሳያስ #አፈወርቂ #ደሴ ወ/ሮ ስህን ት/ቤት ባይማር
ኖሮ #ፕሬዚደንት #መሆኑ ቀርቶ አንድ ተራ መሀንድስ ሆኖ ሊቀር የሚችልበት
እድሉ ሰፊ ነበር።

┏━ 🍃 ━━━━ 🍂 ━┓
✒️ islam is universtiy🖋
┗━ 🍂 ━━━━ 🍃 ━┛
#share #share #share

Join👇👇👇
@IslamisUniverstiy_public_group

@IslamisUniverstiy_public_group
ሴት ልጅን ሂጃብሽን አዉልቂ ማለት

🔽ንግስትን ከላይሽ ላይ ዘዉዱን አንሺው እንደ ማለት ነው።

የሴት ልጅ ውበቷ ሂጃቧ ነው::

ውዷ እህቴ የተለያዩ እውቀቶችን መቅሰም ትፈልጊያለሽ
እንግዳውስ ጆይን በማለት አጫጭር እና ጣፋጭ መልእክቶችን ውሰጅ::

👇👇👇👇

Join us 👉ለውዷ ሙስሊሟ እህቴ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#መጥፎና #ጋጠወጥ $ከሆኑ #ጓዶች #ጋር #ስትገጥም

🔰 #የመጀመሪያ #ሰሞን

↘️ የሚሠሩትን አትሠራም
↘️ የሚሠሩትን ትጠየፋለህ
↘️ መጥፎ ተግባራቸውን
ትቃወማቸዋለህ፨

🔰#በቀጣይ #ሰሞን

↘️ የሚሠሩትን አትሠራም
↘️ የሚሠሩትን ትጠየፋለህ
↘️ ነገር ግን ተቃውሞህን ትተዋለህ፨

🔰 #በሚሠልሠው #ሰሞን #ደግሞ
🔁 የሚሠሩትን አትሠራም
🔁 መጠየፉን ትተዋለህ
🔁 ተቃውሞውም ቀርቷል

🔰 #በመጨረሻም
↪️ የሚሆኑትን አብረህ ትሆናለህ
↪️ መጠየፉም
↪️ ተቃውሞውም ሙሉ በሙሉ ይቀራል


💢 #ጠንካራ #ነኝ ኢማን አለኝ በራሴ እተማመናለሁ ብለህ
መጥፎ ስብስቦችን ደፍረህ አትቅረብ።

💢 #ያለችህን አንዲት ኢማን የጓደኞችህ ሸይጣኖች
ነፍሲያዎችና ሁኔታዎች ተደማምረው ኢማንህን ድባቅ
ይመታሉ።


💠 #አላህ_ሷሊሕ_ጓደኞችን_ይምረጥልን!!

AMIN

Join👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
#እውነተኛ #ፍቅር
#ክፍል 2⃣

#የተከበረችው ኸድጃ በዝሆኖች አቆጣጠር ከ15 አመት ቀደም ብላ ከአባቷ ኩወይሊድ ኢብኑ አሰድ አብድልዑዛ ከእናቷ ፋጡማ ቢንቱ ዛኢዳ ተወለደች፡፡ #ከድጃ ስሩ ከጠለቀ ጫፉ ከዘለቀ ከተከበረ ነገድና ቤተሰብ የተገኘች ናት፡፡ #ከህፃንነቷ ጀምሮ የነገሮችን እውነታ የመከታተልና የማወቅ ጉጉቷ ከዕድሜዋ የላቀ ነበር፡፡ ስለ ንግድ አባቷ ከወንድሞቿ ጋር ሲወያዩ በአትኩሮት ትከታተል ነበር፡፡
ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ብዙ የጋብቻ ጥያቄ ይቀርብላት ጀመር፡፡ #እሷ #ግን በስሜት ተገፋፍታ ለምርጫ አልቸኮለችም፡፡ #ጉዳዩን በጥልቀትና በስፋት በመመርመር ለምትወስደው አቋም ሚዛናዊ መለኪያዎችን መፈለግ ተቀዳሚ ተግባሯ ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን አቡሀላህ ኢብኑዚራራህን አገባች፡፡ #ከሱም ህንድና ሀላህ የተባሉ ልጆችን አገኘች፡፡ ከድጃ ከአቡሀላህ ጋር ጥቂት አመታት እንደቆየች በሞት ተለያት፡፡ ከዚያ አቲቅ ኢብኑል ኩዘይምን አገባች፡፡ ከሱም አንድ ልጅ ከወለደች በኋላ አቲቅ በሞት ተለያት፡፡ #ሀብትና #ንብረቱን ወርሳ ተቀመጠች፡፡
ከባሏ ሞት በኋላ የተለያዩ ሰዎች ለጋብቻ ቢጠይቋትም ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ የወንድ አይነት እየተግተለተለ በተለያየ አቀራረብ ደጅ ቢጠናትም ስሜት አልሰጣትም፡፡
#አላህ #በረቀቀ ጥበብና ማንም በማይደረስበት ሚስጥሩ የማንነት መለኪያ የትልቅነት መገለጫ ሆነው ከቀረቡት ነገሮች ሁሉ እጅግ ብልጫ ያለውን መልካም ነገርን ሁሉ አጠቃሎ የያዘ ሰው አዘጋጅቶላት እንደነበር አስባውም አታውቅም፡፡
#ከድጃ #ጣኦት አላመለከችም፡፡በጃህሊያ ከጣኦት አምልኮ እንድትቆጠብ ያደረጋት ለአጎቷ ወረቃ ያላት ቀረቤታ ነው፡፡ ወረቃ ኢብኑ ኑፈይል የነሳራዎች መፅሀፍ ከቅድመ አያቶቹ ስለተሰጠው ይህንን መከተል መርጦ ስለነበር ብዙ ዕውቀቶችን ወደተለያዩ አገሮች ሄዶ ተምሮ ብዙ እውቀት ስላገኘ ከድጃ የባዕድ አምልኮ እንዳትከተልና እንድትጠላ አድርጓታል፡፡ #የተረጋጋች በሳል ተፈጥሮዋ የሰከነ በመሆኑ ሰዎች "ጧሂራ"(ንፅህት) በሚል በልዩ የማዕረግ ስያሜ ይጠሯታል፡፡ #ይህን #ስያሜ ከእስልምና በፊት ያገኘችው ነው፡፡
#አንድ ወቅት ከቁረይሽ ሴቶች ጋር ሆና በጃህሊያ ጊዜ አመታዊ በዓል በሚያከብሩበት የክብር ቦታ ቁጭ ብላ ሳለ አንድ ሰው ሴቶቹ አጠገብ ሲደርስ "እናንተ የመካ ሴቶች በናንተ ከተማ ነቢይ ሊመጣ ነው #ስሙ #አህመድ ይባላል፡፡ ከናንተ የቻለ ያግባው " ሲል ይጮሀል፡፡ #ሴቶቹና ሌሎች ሰዎች ጭምር በድንጋይ እየደበደቡት አባረሩት፡፡ #የተከበረችው #ከድጃ #ስትቀር
.
#part 3⃣
.........ይ...........
.......ቀ
.....................ጥ
ላ...........
........ል

#ሼርርርርር

Join👇👇🤞
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
🍃🍃 #ምርጥ_ጓደኛ🍃🍃


🎖 #ገሣጭህ #ነው ፥ የሰዎችን ውድቀት ይጠቁምሃል

🎖 #መካሪህ #ነው ፥ የሥኬታቸውን ምስጢር ሹክ ይለሃል

🎖ካንተ ጋር በሚኖረው ቆይታ አይሰለችም ፡፡

🎖 ካንተ ርቆም አያሴርም ፡፡ ከታላላቅ የዓለም ምሁራን ጋር
ያስተዋውቀሀል ፤ ከጥበባቸው ማዕድ ትቋደስ - ዘንድ ያስችለሃል ::

🎖 #የግለሰቦችን የሕዝቦችን ውድቀት
ወይም ምጥቀት ምክንያት ያትትልሃል ።

🎖 #ያልኖርካቸውን የጥንት ዘመናት በአይነህ ህሊና ኖረሃቸው ትማርባቸው ዘንድ እድል ይሰጥሃል ፡፡
~

↘️ #ምርጥ #ጓደኛህ #ነው ፤ ካንተ አንዳችም ጥቅም
አይፈልግም ፡፡

↘️ #ምርጥ #ጎረቤትህም #ነው ፤ ባንተ ላይ አንዳችም ችግር አይፈጥርም፡፡

↘️ #ያጋጠመህን #ችግር
አማክረኸው መፍትሄ ሳይጠቁም እንዲሁ አይተውህም ፡፡ ህልምህን አጋርተኸው የሥኬት ጎዳናን ሳያመላክትህ አይቀርም ፡፡
🎖 #ግለሰባዊና -ቤተሰባዊ ሕይወትህን አወያይተኸው የማበልፀጊያ ዘዴውን ሳይዘይድ ቸል አይልህም ::

🎖 #የሀገርህ ድህነትና ሗላ ቀርነት ሲያብከነክንህ የማስመንደጊያ ንድፉን ሳያስጨብጥህ ዝም -
አይልህም ::

🎖 #የዘመናት #የሰው #ልጆች እምቅ ዕውቀት
በውስጡ ያቀፈ በመሆኑ በርካታ የመፍትሄ ሃሳቦች ተሞልቷልና ::

💠💠 #ይህ #ምርጥ #ጓደኛ ሌት ከቀን ካንተ ላይለይ
ፈቃደኛ ነው ::

🎖 #ነዋሪም ሁን መንገደኛ ካንተጋር መሆን ያስደሰተዋል ::

🎖 #እንቅልፍ #ቢያዳፋህ እርሱ
እንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር እስከምትነቃ ይጠብቀሃል ::

🎖 #ተሰላችተህ #ብትወረውረው ዳግም እስክታነሳው
ይታገሰሃል ;

🍃🍃 #ቸር #ነው ፤ ያለውን ሊሰጥህ ዝግጁ ነው ፡፡

🍃🍃 #ትጉህ #ነው ፤ ያለማቋረጥ ቢያስተምርህ
ይወዳል ፡፡ ነፃ ነው ፤ ማንነትህ አያሳስበውም ፡፡

💢 #ሐብታም #ብትሆን ወይም ደሃ ፣ ደስተኛ ብትሆን ወይም የተከፋህ ፣ ብቸኛ ብትሆን ወይም ባለ ብዙ ጓደኛ ፣ ባለሥልጣን ብትሆን ወይም ተርታ ሰው ፡
ለርሱ ግዱ አይደለም ፡፡


💠 #ይልቁንስ #ሐብታም ከሆንክ ገንዘብ አያያዝና
አጠቃቀም ያስተምረሃል ፡፡

💠 #ድሃ #ከሆንክ የብልፅግና መንገድ ይጠቁመሃል ፡፡

💠 #ብቸኛ #ከሆንክ ጓደኛ - ይሆንሃል ፡፡

💠 ባለ ብዙ #ጓደኛ #ከሆንክ ከሰዎች ጋር በመኖር ጥበብ ይክንሃል ::

💠 #ባለሥልጣን #ከሆንክ
ያመራር ችሎታ ያላብሰሀሃል :: መልካም ልቦና ይኖርህ ዘንድ ይመክረሃል ::

💠 #ተራ #ሰው #ከሆንክ ደግሞ የታላቅነትን ማማ ትቆናጠጥ ዘንድ የሥኬት ምስጢር ያስተምረሃል ::

ይህ ምርጥ ጓደኛ ጥሩ መፅሐፍ ነው ::

🔁ከመፅሐፍት ሁሉ የላቀውና ስህተት ያልጎበኘው ፣

🔁ዘመን የማይጥለው ፣ ሁሉንም የሕይወትህን ክፍል
አንዳች ሳያስቀር የሚዳስስ መመሪያ ፣ ያካተተ ፡
ተዓምሩ የማያልቅ ፣ ተደጋግሞ ቢነበብ የማይሰለች ፣ ሊቃውንት የማይጠግቡት ፣

💢💢ያለፉ ሕዝቦችን ታሪክ የሚዳስስ ፣ የዘመኑን ሕዝብ የሚዳኝ የሚመጣውን ዘመን ምንነት የሚተነብይ ፣ ከፊት ለፊቱም ይሁን ከበስተሗላው ደምሳሽ ተቀናቃኝ የሌለበት #ዘልዓለማዊ_መፅሐፍ ፡_


🌸🌸 #ቅዱስ_ቁርኣን_ነው ፡፡🌸🌸


ካመንክበት አስተላልፈው …SHARE

Join👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
✏️✏️ #በፍፁም #ለራሳችን #መንገር #የሌለብን 4⃣ #ነገሮች

የተለያዩ ችግሮች ውስጥ የምታልፉበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንድ
ጊዜ ለችግሮቹም ራሳችሁን ተጠያቂ ታደርጉ ይሆናል፡፡ በየትኛውም አይነት
ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ግን ደካማነታችሁን የሚያጎሉና ከሠዎች በታች
ሆናችሁ እንድትታዩ የሚያደርጉ ቃላትን መጠቀም የለባችሁም በማለት
#የሥነ-ልቦና #ምሁራን #ይመክራሉ፡፡
.
↘️ #እነኚህ #ቃላት አስተሳሰባችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የመፍጠር አቅማቸው
ከፍተኛ ነው። ለራሳችን የምንናገራቸው አሉታዊ ቃላት ከፍተኛ ጉዳት
እንዳላቸው ከሕይወት ልምዴ ተገንዝቤያለሁ የሚሉት የሥነ-ልቦና
ባለሙያው ማይክ ቡንድራንት በተለይ የሚከተሉትን ቃላት ለራሳችሁ ፈፅሞ
መንገር የለባችሁም ይላሉ፡፡
.
1⃣ #የማልረባ_ነኝ
ይህ በራስ መተማመናችሁን በቀጥታ የሚገድል አነጋገር ነው፡፡ የማትረቡ
ወይም አንዳች ዋጋ የሌላችሁ መሆኑን ለራሳችሁ መንገር አሉታዊ
አስተሳሰብ በአእምሯችሁ እንዲሰርፅ የማድረግ ኃይል ስላለው ቃሉን
መጠቀም ተገቢ አይደለም፡፡
.
2⃣ #አልችልም
አንዳንድ ነገሮችን በምትፈልጉት ደረጃ መስራት የማትችሉባቸው ሁኔታዎች
በሚፈጠሩበት ጊዜ አቅማችሁን ልትጠራጠሩ ትችላላችሁ። የምታደርጉት
ነገር ጥቅም እንደ ሌለው ለራሳችሁ መንገር ለሥራ ያላችሁን የተነሳሽነት
#ስሜት #ይቀንሰዋል#አቅማችሁን #ያሳጣችኋል፡፡ ይህ አነጋገር እውነታውን
ከመግለፅ በላይ ራሳችሁን መልሶ የማጥቃት አቅም አለው፡፡ አንድ ነገር
ከመሥራታችሁ በፊት እወድቃለሁ/አይሳካልኝም ከማለት ይልቅ ደጋግሞ
በመሞከር ለውጤት መብቃት እንደምትችሉ ማመን አለባችሁ፡፡
.
3⃣ #ሠዎች_አይወዱኝም
ሠዎች አይወዱኝም የሚለውን ስሜት በአእምሯችን ማስረፅ ሌሎች ከእኛ
የተሻሉ እንደሆኑ እንድናስብና ለራሳችን ጥረት ተገቢ ውጤት እንዳንሰጥ
ያደርገናል፡፡ #በሌሎች ያለመወደድ ስሜት ከተሠማን ደግሞ ለራሳችን
የምንሰጠው ክብርም ይቀንሳል።
.

4⃣ #ለውጥ_ማምጣት_አልችልም
አንድን ነገር ለመለወጥ አቅማችሁ ካልፈቀደ ራሳችሁን አታስገድዱት፡፡

↘️ፍፁም መሆንንም ከራሳችሁ አትጠብቁ፡፡በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ
የምትሰጧቸው ሀሳቦች የራሳቸው አዎንታዊ ተፅእኖ አላቸው፡፡ ስለዚህ
#ለውጥ #ማምጣት #አልችልም›› የሚለው ቃል ለራሳችሁ መንገር
ከሌለባችሁ አሉታዊ ቃላት መካከል አንዱ ነው፡፡
.

✏️✏️በአጠቃላይ ስሜታችሁን የሚጎዱ እንዲህ ዓይነት ቃላትንና አነጋገሮችን
መጠቀም ትታችሁ አንደበታችሁን በመጠበቅ በየዕለቱ ለምታከናውኗቸው
ተግባራት ትኩረት በመስጠት #ውጤታማ #መሆን #ትችላላችሁ፡፡

Join
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science

@Islam_and_Science
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY via @like
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኡመቲ ተስፋ አትቁረጪ ...አቅሷ ላይ ብዙ ወንድሞቻችን እህቶቻችን ህፃናት ሴቶች እየተገደሉ ጠዋት እና ማታ አዉሮፕላን ሲጨፈጭፋቸዉ አላያችሁምን?እንደዚህ ሲሆን ስሜትህ ምንድን ነዉ ? #ሸህ #ኻሊድ #ረሻድ
@IslamisUniverstiy_public_group 😭😭
#እውነተኛ #ፍቅር

#ክፍል 3⃣

#የከድጃ ሀብት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ፡፡ በውክልና እሷ ዘንድ በኮሚሽን መቀጠር ከቻሉ ሰዎች መካከል ሙሀመድ (ሰዐወ) አንዱ ነበር፡፡ ወጣቱ ትሁት ሰው አክባሪ የሰውን ገንዘብ ያለ ሀቁ የማይፈልግ ታታሪ ቸር ስራውን ወዳድ በመሆኑ ከድጃ ጋር #ከተቀጠረ ጀምሮ ከመካ ከተማ ርቆ በመሄድ እየነገደ ገንዘቧን በእጥፍ አሳደገው፡፡ በዚህም ከድጃ በወጣቱ ኮርታበታለች፡፡ #ሙሀመድ ከድጃ ጋር የተቀጠረው እንዲሁ በአጋጣሚ አልነበረም፡፡ የሚያሳድጉት አጎቱ ጥሪት አነስተኛ በመሆኑ እንጂ፡፡
የሙሀመድ አባት አብደላህ ገና ሳይወለዱ ነበር የሞቱት፡፡ እናታቸውን ያጡት ደግሞ በ6 አመታቸው ነበር፡፡ ቢሆንም በአያቱ ዘንድ አደገ፡፡ አያቱ ሲሞቱ አጎቱ ተረከቧቸው፡፡
#መሀመድ አጎቱ ጋር መኖር ሲጀምር ፍየል በመጠበቅ ተግባር ተሰማራ፡፡ ግን ብዙም ሳይቆይ አጎትየው የገቢያቸውን መጠን ለማሳደግ ጥረት ማድረግ ጀመሩ፡፡
#አንድ #ቀን ከድጃ ወንዶችን ወደ ምድረ ሻም በመላክ እንደምታሰማራ ስላወቁ ነጋዴው ወደተባለው ሀገር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ ሳሉ ሙሀመድን አስጠርተው ስለሁኔታው ሊነግሯቸው ወሰኑ፡፡
"የወንድሜ ልጅ ሆይ እንደምታውቀው አንዳች የሌለኝ ደሀ ነኝ ፤ ግዜው ደግሞ በድርቅ ተመቷል፡፡ ከድጃ ሰው ቀጥራ እንደምታስነግድ ሰምቻለው በርግጥ የምትከፍለው ገንዘብ አነስተኛ በመሆኑ ደስ አያሰኝም፡፡ #እናም ስለዚህ ጉዳይ እሷኑ ባነጋግርልህ " ሲሉ አቡጧሊብ ጥያቄ ለመሀመድ አቀረቡ፡፡ ሙሀመድም እንዲህ አላቸው "አጎቴ ሆይ እንዳሻህ ማድረግ ትችላለህ ሀሳብህ የኔም ሀሳብ ነው መጭው አለም ከዱንያ አለም በላጭ ነው" አሏቸው፡፡
#አቡጧሊብ #ጊዜ ማጥፋት አልፈለጉም ወንድሞቻቸውን አስከትለው ወደ ኸድጃ ቤት አመሩ፡፡ እሷም ከሀር በተሰራ ባማረ ልብስ ተውባ በፈገግታ ተቀበለቻቸው፡፡
#አቡጧሊብም "የተከበርሽው ከድጃ ሆይ እኛ የመጣነው ለጉዳይ ነው ሰዎችን ገንዘብ እየከፈልሽ እንደምታስነግጂ ሰምቻለው፡፡ ለሌሎች በምትከፊይው ላይ ጨምረሽ ተመሳሳይ ስራ እንዲሰራልሽ መሀመድን አትቀጥሪምን? " አሉ
ከድጃም "እንኳንስ ለሚወደድ ለቅርብ ዘመድ ለማይታወቀውም ቢሆን ጥያቄዎ በኔ ዘንድ ተቀባይነት አለው" በማለት አስደሳች መልስ ሰጠች፡፡
#አቡጧሊብ አስደሳቹን ዜና ይዘው ወደ መሀመድ (ሰዐወ) ተመለሱ፡፡ ብስራቱን ከነገሩት በኋላ "ይህ ፈጣሪ ላንተ የላከው ሲሳይ ነው " አሉ፡፡
#ሩህሩሁ #አጎት መጪው ጊዜ ያረገዘውን ቢረዱ ይህ ለከድጃ ከሰማይ የወረደ ፀጋ ነው ባሉ ነበር፡፡ ሆኖም ከዚህ መልካም ዜና በስተጀርባ የሚመጣውን የላቀ ዕጣ የሚያውቅ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
#እድለኛዋ ከድጃ አቡጧሊብ ያቀረቡትን ጥያቄ በደስታ ተቀበለች ፤ ይህም ሙሀመድ (ሰዐወ) እና ከድጃ (ረዐ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁበት አጋጣሚ ፈጠረ፡፡ ጉዳዩ በመካ ነዋሪዎች ዘንድ ተዳረሰ፡፡ በየአጋጣሚው የታላቁን ሰው መልካም ትሩፋት እውነተኛነት ዘረዘሩላቸው፡፡ ከድጃም ይበልጥ ደስ አላት፡፡ #መይሰራ ከተባለው አገልጋይ ጋር ወደ ሻም እንዲሄዱ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አስታወቀች፡፡ ሙሀመድም የተሰጣቸውን አማና ተቀብለው ለንግድ ከመይሰራ ጋር ወደ ሻም አመሩ፡፡
.
#part 4⃣

ይቀጥላል


@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
💫 #ልጅቷን #ለምን #ሳምካት ?
,
#አስገራሚው #አጋጣሚ

💢በእድሜ የገፉ አባት ናቸዉ ከሁለት ወጣት ልጆቻቸዉ ጋር ሲኖሩ
ችግር ይገጥማቸዋል ::
#ወንዱን #ልጅ ስራ እንዲሰራ ይልኩታል ከመሔዱ በፊት ሊመክሩት
ፈለጉና

🍃🍃 #ልጄ #ሆይ ስለ #እህት ስትል አሏህን ፍራ አሉት::
#አልገባዉም እህቱ አብራዉ አትሔድ ..ምን ለማለት ፈልገዉ
እንደሆነ ሳይገባዉ ሳይጠይቅ ተሰናብቷቸዉ ሄደ ::
#ስራዉን #ጨርሶ #ሲመለስ አባት ልጄ ሆይ! #ለምን ያቺን ልጅ
ሳምካት አሉት ።
,
🔰 #አባቴ አረ ማንንም አልሳምኩም አላቸዉ በጭራሽ
ስመሃታል ብለዉ ሲያፋጥጡት አባቴ #ማንም #አላየንም #ጨለማ
#ዉስጥ ነበርን ከአሏህ ዉጪ ማንም አልተመለከተንም
#ማን #ነገረክ? ዋህይ(ራዕይ) ወረደልህ እንዴት አወክ ብሎ
ሲጠይቃቸዉ
,
📚📚በሩን ከፍቼ ቤት ዉስጥ ቁጭ ብዬ ነበር ዉሀ ቀጂዉ ዉሀ ይዞ
መጣ #እህትህ #ከፈተችለት ዉሃዉን ከገለበጠ በኃላ ሊወጣ
ሲል እህትህን ግጥም አድርጎ ሳማት
ያኔ #አንተም #የሰዉ #እህት #እንደሳምክ
#አወኩ ወደ ሌላ እንቅስቃሴ ብትገባ ዉሀ ቀጂዉም #ወደሌላ
እንቅስቃሴ ይገባ ነበር።

💢በሰዉ እህት ሚቀልድ በእህቱ ይቀለዳል

☞በሰዉ ልጅ ሚቀልድ በራሱ በልጁ ይቀለዳል

☞በሰዉ ሚስት ሚቀልድ በራሱ ሚስቱ ይቀለዳል

☞በሰዉ ልጅ በሰዉ ሚስት በሰዉ እህት ዝሙት የሚፈጽም
እዳዉን በቤተሰቡ ይቀበላል
#ዝሙት #እዳ #ነዉ ካበደርከዉ በቤተሠብህ ብድሩን
ትቀበላለህ።

ሁሉም ሰው የዘራውን ያጭዳል
በራስህ ላይ (በቤተሰብህ) ላይ ሊደረግ የማትፈልገውን
ነገር
#በሌሎች #ላይ #አታድርግ


💠💠 በሌላ ሴት ላይ የምሰራዉ ስራ አንተ ሳታቅ በእህትህ ላይ እንደሚሰራ እወቅ..የሌሎችን ሴቶች መብት ስትጠብቅ የአንተም እህት መብት ይጠበቃል፡፡



🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃

#እስቲ #ሁላችንም ከዚህ ፈተና አላህ ይጠብቀን አሚን በሉ

Joinnn👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
😁ፈገግታ ሱና ነዉ ፈገግ በሉ

እዚያ ሰፈር ያሉ ወንዶቺ ምን ቢሉ ጥሩነዉ 😅😅😅😅😅😅
.
.
.
.
.ተከተሉኝ ነገሩ አለበት ልምራቹሁ
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
።።።።።።።።።።።።
እድሜዋ 25 አመት በላይ የሆነችን ሴት ያገባ ወንድ ፥ለሷ ባሏ ብቻ ሳይሆን ባለ ውሌታዋም ነው።😅😅😅
ኤያዳድሺ ፈንሺን ፈልጊ ጪራሺ ባለዉለታሺ ሆነ እኮ
😂😂😂😂
Join
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፈገግታ ሱና ነው😊

እሱ ~ አይንሽን ጨፍኚ
እኔ ~ እሺ ግን ቶሎ በል
እሱ ~ በቃ ክፈቺ
እኔ ~ ስጦታው የት አለ
እሱ ~ የምን ስጦታ ሱሬን መቀየር ፈልጌ ነው አይ እኛ ሴቶች😅😄 ስጦታ ውስጣችን ነው

ውዷ እህቴ የተለያዩ ትምህርቶችን ለመከታተል ከፈለግሽ ወደዚህ👇👇 ቻናል ጎራ በይ

ለውዷ ሙስሊሟ እህቴ 👉play

ዘይነብ ቢንት ጃህሽ
#እውነተኛ #ፍቅር
#ክፍል 5⃣
ከሻም ጉዞ መልስ ከድጃ (ረዐ) #ለሙሀመድ (ሰዐወ) "ለአንተ እኔ ዘንድ ጥሩ ደስታና ስጦታ ተቀምጦልሀል ከሁሉም ሰራተኞች የበለጠ እጥፍ ተጨማሪ ገንዘብ ይከፈልሀል" አለችው፡፡ #ሙሀመድም (ሰዐወ) ከጉዞ መልስ አጎቱ ጋር ተመለሰ፡፡ #አቡጣሊብም አባት ለልጅ አቀባበል ከሚያደርገው በላይ በደስታ ተቀበሉት፡፡ ከዚያም እንዲህ አሉት
"#ልጄ #ሆይ ከድጃ ከፈለችህ"
ሙሀመድም "ከውሉ በተጨማሪ ትርፍ ገንዘብ ጨምራ እንደምትሰጠኝ ቃል ገባችልኝ " አለ
#አቡጣሊብም "ልጄ ሆይ የወላጆችህ አደራ አለብኝ እንደምታዬኝ አርጅቻለሁ የሞትም ምልክቱ እየታየብኝ ነው ስለዚህ አንተን ድሬ ወግ ማዕረግህን ማየት እፈልጋለሁኝ እናም ከቁረይሾች ጥሩ ሚስት ብፈልግልህና ብድርህስ " አሉ፡፡
#ሙሀመድም "አጎቴ ሆይ አንተ እንደፈለክ ማድረግ ትችላለህ እኔ ያንተን ትዕዛዝ ለመፈፀም ዝግጁ ነኝ " አለ፡፡
ከሻም መልስ በሁለተኛው ቀን ታላቁ ሙሀመድ (ሰዐወ) ገላቸውን ታጥበው አቡጣሊብ በገዙላቸው ልብስ ተውበው ወደ ከድጃ ሄዱ፡፡ ከድጃም እውነተኛ ፣ ታማኝ ፣ ፍትሀዊ ፣ አዛኝ ፣ መልካም ሰሪን ታላቁን ወጣት በውበቱ ላይ አዲስ ልብስን ተጎናፅፎ ስታየው ተደነቀች ከዚያም "#እንዲህ #አምረህ የመጣኸው ከኔ አንድ ነገር ፈልገህ ሳይሆን አይቀርም ምን ልታዘዝ ሀጃህ ምንድነው?" አለችው፡፡
"#ከአንቺ ዘንድ ያለኝን ገንዘብ ፈልጌ ነው " አላት፡፡
"#መሀመድ ሆይ ይህ ውዐትና ገንዘብ ይዘህ በንደዚህ ሁኔታህ ምን ልትሰራበት ነው" አለችው፡፡
"አጎቴ ከቁረይሽ የሆነችን ሚስት እድርልሀለው ስላለኝ ተስማምቼ ነው የመጣሁት " አላት፡፡
"#ሚስት ልታገባ አስበህ ከሆነ እኔ እጅግ ቆንጆ የሆነች ገንዘብ ያላት ለዘርህ ቅርብ የሆነች ሹማምንቶች ለጋብቻ ጠይቀዋት እንቢ ያለች በሰዎች ዘንድ የተከበረች አዕምሮዋ የተረጋጋና የሞላ አንተን እንጂ ከአንተ ምንም የማትፈልግ ሚስት አዘጋጅቼልሀለው፡፡" አለችና #እንዲህ ስትል ቀጠለች "ከአንተ የማልደብቀው ሁለት ነውር አላት አንደኛው ነውሯ አግብታ ታውቃለች ሁለተኛው በዕድሜ ከአንተ ትበልጣለች " አለች፡፡
#መሀመድም "አንቺ ጥሩዋ ሴት ሆይ ማናት እሷ የትስ ነው ያለችው " አላት
"ያንተ ምርኮኛ ናት እዚሁ ቅርብ አጠገብህ ታያታለህ ስሟም ከድጃ ይባላል" አለችው፡፡
#መሀመድም ሁሉም ነገር በተገለጠለት ጊዜ ምንም መልስ ሳይሰጥ ዝም አለ፡፡
ከድጃም "የእሺታ መልስ ስጠኝና ልቤን አሳርፈው" አለችው፡፡
አሁንም ከወጣቱ መልስ ስታጣ "አላህ ካለ እኔ ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ አንተንም በምንም አልወነጅልህም" አለች፡፡
#መሀመድም (ሰዐወ) "ከድጃ ሆይ አንቺ የተከበርሽና ባለብዙ ሀብት እኔ ደግሞ የአንቺ ተቀጣሪና ከምትሰጪኝ ገንዘብ ሌላ ምንም የለኝም እናም ገንዘብ የሌለው ፈልጎም ቢሆን ቢጤውን ያገባል" አላት፡፡
.
.
.
አላለቀም

#part 6⃣

ይ...ቀ...ጥ...ላ....ል

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
#የከባድም #ከባድ
=============
አብደላህ (ረድየላሁ አንሁ) የአላህ መልክተኛን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
#አላህ #ዘንድ #ታላቁ #ወንጀል #የቱ #ነው? ብዬ ጠየቋቸው፡፡


#እሳቸውም ‹‹አላህ ብቻውን ፈጥሮህ ሲያበቃ፤ በእርሱ ላይ ባላንጣን
(ሸሪካን፤ ቢጤን) ማድረግ››
‹‹ይህ ታላቅ በደል ነው›› አልኩ


#ከዚህ #ቀጥሎስ? ብዬ ጠየቅኩ

#እሳቸውም ‹‹#ልጄ #ምግቤን #ይሻማዋል #ብለህ #ልጅህ #መግደል›› ነው፡፡

#ከዚህ #ቀጥሎስ? ብዬ ጠየቅኩ

#እሳቸውም ‹‹#ከጎረቤትህ #ሚስት #ጋር #ዝሙት #መፈፀም›› ነው አሉ፡፡ ሰሂህ
አል ቡኻሪ 6/4477


↘️↘️ከሃዲሱ የምንወስደው ትምህርት
==========================
#ሁሉም #ወንጀል #እኩል #አይደለም፡፡ ወንጀሉ አንድ አይነት ሆኖ፤ ከቦታ እና
ሁኔታ አኳያ ይለያል፡፡
✏️ለምሳሌ ነፍስ ማጥፋት ከባድ ወንጀል ሆኖ ሳለ፤
የገዛ ልጅህን ምግቤን ይሻማኛል ብሎ መግደል ደግሞ ከባድ ነፍስ
ማጥፋ ነው፡፡

✏️ጎረቤት ሃቁ ሊጠበቅለት፤ እሱ ለስራም ይሁን ለዘመቻ በሄደበት፤ ሚስት
እና ልጆቹን በአማና ጥሎ ሄዶ ከእርሱ ሚስት ጋር ዝሙት መስራት
እንደማንኛውም ዝሙት አይደለም፡፡
የወንጀሎች ሁሉ ታላቅ ወንጀል፤

✏️ በአላህ ላይ ማሻረክ እና ማጋራት፡፡ አላህ
ብቸኛው ፈጣሪ ከሆነ ለምን የአምልኮ ክፍሎች ከእርሱ ውጭ ለፍጡራን
ይደረጋሉ?

🌼🌼ይህ ነው የበደሎች ሁሉ በደል፡፡
#የመካ #ሙሽሪኮች #ሲጠየቁ ሰማይ እና ምድርን ማን ነው የፈጠረው?
አለሙን የሚያስተናብረው ማን ነው? እናንተን የፈጠራችሁ ማን ነው? እና
ሌሎች የአላህን ብቸኛ ፈጣሪነት የሚያረጋግጡ ጥያቄዎች ሲጠየቁ
‹‹#አላህ›› #ብለው #መልስ #ይሰጣሉ፡፡

🔰🔰ነሳራዎች ሰማይ እና ምድርን ማን ነው የፈጠረው ሲባሉ ‹‹አንድዬ››
ብለው አንድ መሆኑን እና ብቸኛ ፈጣሪ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
✏️✏️ታድያ ለምን ይሆን #ከአላህ #ውጭ ያሉ መላኢካም ይሁን (ጂብሪልን፤
ሚካኤልን (አለይሂሙሰላም)) ይመስል፤ ነብያት (ኢሳን፤ ኡዘይርን፤
ሙሃመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም))፤ ሷሊሆችን (አልይ፤ ሁሴን፤ ሀሰን፤
ፋጢማ (ረድየላሁ አንሁማ)) እና የመሳሰሉት ይመስል ከአላህ ውጭ
ፍጡራን ሆነው ሳለ የሚመለኩት????????????


✏️✏️#አላህ #ለእርሱ #ፍፁም #አምልኮዋቸውን #ካደረጉት #ባሪያዎቹ #ያድርገን


⭐️ #ከከባባድ #ወንጀሎችም #ይጠብቀን፡፡

Join👇👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
ለሴቶች ብቻ 👍የኢስላም ልጆች መማርያ ግሩፕ
https://t.me/joinchat/FzVfbg99dS04PKYpII1fdg
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/joinchat/GEQ8ElEcRL9ieYh6HErQcg
#እውነተኛ #ፍቅር
#ክፍል 6⃣
... #ከድጃም እንዲህ አለችው "ገንዘቡን ብናደባልቀው ይበዛል እንጂ አያንስም"፡፡ ወጣቱም በድጋሚ ምንም ሳይመልስላት ዝም አለ፡፡
#ከድጃም "በግልፅም ሆነ በድብቅ የሚሰሩትን የሚያውቅና የሚያይ በሆነው ጌታዬ ይሁንብኝ በኔ በኩል ምንም የሚሸፍነው ነገር የለም፡፡ #ሁሉም #ነገር እውነት ነው በል አሁን ወደ ቤተሰቦችህ ሂድና አጎትህን ለጋብቻ እንዲጠይቁኝ ንገራቸው፡፡ ምናልባት አባቴ ብዙ ገንዘብ ለኒካህ ከጠየቃቸው የጠየቀውን በሙሉ እኔ እሰጥሀለው፡፡ #እኔ ያንተ ነኝ እኔው መረጥኩህ ከአንተ ሌላ ማንንም አልፈልግም፡፡ ልቀርብህ ሳስብ አትራቀኝ " አለችው ልመና በተቀላቀለበት አነጋገር፡፡
#መሀመድ (ሰዐወ) ተነስቶ ከቤቷ ወጣ፡፡ ከድጃ መሀመድ (ሰዐወ) ከመምጣቱ በፊት ለወዳጅ ጓደኛዋ ለነፊሳ አጫውታት ነበር፡፡ ነፊሳም እሱን አሳምና ከምትወደው ሰው ጋር እንደምታጋባት ቃል ገብታላት ነበር፡፡ #ወጣቱ መሀመድና ነፊሳ ሲገናኙ ነፊሳ ስለታላቋ ሴት ስለ ከድጃ መልካም ባህሪና እንዲሁም እሱን ማግባት እንደምትፈልግ ከገንዘቧ እንደምታስበልጠው አንድ በአንድ ነገረችው፡፡ ጥያቄዋን እንዲቀበልም አሳመነችው፡፡
#ታላቁ #ሰው አጎቱ ቤት ተመለሰ፡፡ አቡጣሊብን ከወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር ቤት ቁጭ ብሎ አገኛቸው፡፡ አጎትዬው በፈገግታ ተቀበሉት ከዚያም "ከድጃ ከከባድ ስጦታ ጋር እንደላከችህ እገምታለው" አሉት፡፡ መሀመድም "አጎቴ ሆይ ግምትህ ትክክል ነው፡፡ #ከአንተ ጉዳይ አለኝ " አለ፡፡
#አቡጣሊብም "ከአንተ ጉዳይ ጀርባ ጌታህ አለ፡፡ ለመሆኑ ምንድናት ጉዳይዋ" አሉት፡፡
#መሀመድም "ሂዱና ከድጃን ለትዳር እንደምፈልጋት ቤተሰቧን ጠይቁና አምጡልኝ " አለ፡፡
የመሀመድ አጎቶች ተያዩ ከአቡጣሊብ በስተቀር ማንም ምንም መናገር አልፈለገም፡፡ #አቡጣሊብም "ልጄ ሆይ ከድጃ እጅግ የተከበረችና በሰዎች ዘንድ የተወደደች ብዙ ሀብት ያላት ከአሁን በፊት ሁለት ሰዎች አግብታና በሞት የተለዩዋት ንብረታቸውን ወርሳ የምትኖር አሁን በቅርቡ ታላላቅ ሹማምንቶች ለጋብቻ ጠይቀዋት እንቢ ያለች ናት፡፡ አንተ የወንድሜ ልጅ ደግሞ ምንም ንግድ የለህም የርሷ ተቀጣሪ ነህ፡፡ ስለዚህ ራሷን አሳልፋ አትሰጥህም" አሉት፡፡
#ሙሀመድም (ሰዐወ) "አጎቴ ሆይ አሁን ያልከውን በሙሉ አውቀዋለሁ እረዳሀለው የጋብቻ ጥያቄው ግን ከራሷ ነው የመጣው፡፡ " አላቸው
.
.
.
አላለቀም

#Part 7⃣

ይ...ቀ....ጥ....ላ,.....ል

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY via @like
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወንዶች ሴታሴት ሁነዋል..ትዉልዱ ተበላሽቷል ኢስላምን እንዴት ነዉ የያዝነዉ የእኛ ትዉልድ ኢስላምን መርቶ ለትዉልድ የሚያስረክብ ዘመን ላይ ነዉ ያለነዉ ?? #በሸህ ኻሊድ ረሻድ
@IslamisUniverstiy_public_group 😔😔