FDRE Education and Training Authority
7.3K subscribers
753 photos
13 videos
23 files
132 links
በኢፌድሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን
http://www.eta.et/

9799 "በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል"
Download Telegram
በ2016 በጀት ዓመት የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተገለጸ
============ =========== =========
የትምህርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እና የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ (ሳይንስ ፋክሌቴ) መሰብሰቢያ አዳራሽ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን በጋራ በገመገሙበት ወቅት እንደተገለጸው የትምህረትን ጥራት ለማስጠበቅ፣የትምህርት ተደራሽነት እና የትምህርት አሳታፊነትን ለማሳደግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ላይ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች፤ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች እንዲሁም በቀጣይ ሊከናወኑ የታቀዱ ሥራዎች ቀርበዋል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ያቀረቡት የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ሀምሳሉ የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና የትምህርት ማስረጃዎች ማረጋገጥና የአቻ ግመታ አገልግሎት በበይነ መረብ ጥያቄ ማቅረብ የተቻለበት ፤ለባለስልጣኑ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎች እና ስታንዳርዶች ጸድቀው ስራ ላይ የዋሉበት እና የባለስልጣኑን አሰራር በማዘመንና ከብልሹ አሰራር በማላቀቅ ረገድ በርካታ ተግባራት በበጀት ዓመቱ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር ዘርፍ፣የአጠቃላይ ትምህርት እና የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ እቅድ አፈጻጸም ፤ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም፤ እና የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎትየ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች እንዲሁም የትምህርት ሴክተር ሪፎርም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተው በትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ፤አዲስ አበባ
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
#ማስታወቂያ
#ለሁሉምየግልከፍተኛትምህርትተቋማት
#ባሉበት

ጉዳዩ፡- የዳግም ምዝገባ ዝግጅት ይመለከታል
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያግዙ የተለያዩ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያና ማሻሻያ ዘዴዎች መካከል አንዱ የፈቃድ አሰጣጥ ነው፡፡ ይህንን የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ መመሪያ እና ስታንዳርድ ጸድቆ ስራ ላይ ውሏል።
በመሆኑም መመሪያና ስታንዳርድ ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/2016 አንቀጽ 4(26) መሠረት ሁሉንም በስራ ላይ ያሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በፌደራል ደረጃ ፈቃድ የተሰጣቸው ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ለዳግም ምዝገባ መዘጋጀታችንን ሀምሌ 22/2016 ዓ.ም ባደረግነው ስብሰባ መግለጻችን ይታወሳል።
በዚህ መሠረት ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዳግም ምዝገባ መምሪያ መሰረት እስከ ነሃሴ 30/2016 ዓ.ም በተቋም፣ በካምፓስ እና በፕሮግራም ደረጃ በሀርድ ኮፒ እና ሶፍት ኮፒ የተደራጁትን መረጃዎች በአካል በመቅረብ እንዲሁም በየጊዜው በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት መረጃዎችን እንድታደራጁ እና በቂ ዝግጅት በማድረግ እንድታመለክቱ አጥብቀን እናሳስባለን።
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ