FDRE Education and Training Authority
7.77K subscribers
809 photos
13 videos
23 files
145 links
በኢፌድሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን
http://www.eta.et/

9799 "በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል"
Download Telegram
#ማስታወቂያ
#ለሁሉምየግልከፍተኛትምህርትተቋማት
#ባሉበት
ጉዳዩ፡- የስብስባ ጥሪን ይመለከታል
ተቋማችን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በደንብ ቁጥር 515/2014 በተሰጠው ሥልጣን እና ተግባር መሠረት የከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ካዘጋጀ በኋላ አጽድቆ በሥራ ላይ እንዲውል አድረጓል፡፡ ይህንን መመሪያ ተከትሎ ዝርዝር አሠራር የሚገልጽ ስታንዳርድ አዘጋጅቶ በባለሥልጣኑ ቦርድ እንዲጸድቅ አድርጓል፡፡ መመሪያውንና ስታንዳርዱን ማዘጋጀት ያስፈለገበት ዋና ምክንያት የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማሻሻል እንዲሁም ለተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያሥችል ግልጽ አሠራር ለመዘርጋት ታስቦ ነው፡፡
ይህንን መመሪያና ስታንዳርድ ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/2016 አንቀጽ 4 (26)መሠረት ሁሉንም በሥራ ላይ ያሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ማካሄድ በማስፈለጉ ይህንኑ ለማስፈጸም የተዘጋጁ የዳግም ምዝገባ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት አሠራሮች ላይ ግልፀኝነት ለመፍጠርና የዳግም ምዝገባ ሂደት ለማስረዳት ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው ስብሰባ ሁሉም ተቋማት ባለቤት ወይም አንድ ተወካይ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት እንዲገኙ እናሳስባል፡፡
የሀዘን መግለጫ
,,,,, ,,,,,,,

የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ምክንያት በዜጎች ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦችና ለመላው ኢትዮጵያዊያን መፅናናትን ይመኛል፡፡

የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የሀገራችን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የአየር ንብረትን በማመቻቸት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ
============= ============= =========
ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የትምህርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ የሁኑት የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እና የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት በጋራ በመሆን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሎሜ ወረዳ ባደረጉት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የአረንጓዴ አሻራ መረሀ የሀገራችን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የአየር ንብረትን በማመቻቸት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ገልጸዋል ፡፡በመረሀ ግብሩ ላይ ለስሬ ሊበን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተደረገው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸው የአካባቢው ማኅበረሰብ ለተተከሉት ችግኞች እንክብካቢ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራን ማኖር የአየር ንብረት ተጽእኖን ለመቋቋም የሚያስል መሆኑን ገልጸው አረንጓዴ አሻራን ማኖር አገር የሚያሻግር ኢትዮጵያን ወደፊት የሚወስድና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ተግባር ነው ብለዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራ ማኖር ድርቅንና ተጓዳኝ ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስች ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ግርማ ባይሳ የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ላደረጉት የችግኝ ተከላ እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አመስግነው የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ፤አዲስ አበባ
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፈቃድ እና ፈቃድ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያ ፣ ስታንዳርዶች እና የዳግም ምዝገባ መምሪያ ላይ ውይይት ተደረገ
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የዳግም ምዝገባው ዋነኛ ዓላማዎች ተቋማት የትምህርትና እና ስልጠና መስኮቻቸውን በአዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት ለመገምገም እና ለመመዝገብ፤ በፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት አልፈው ያልተመዘገቡ ተቋማትን በመገምገም እንደ ሀገር ወጥነት ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ፤ ባለስልጣኑ የተሟላና የተደራጀ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት መረጃ እንዲኖረው ለማድረግ፤ በመንግስት እና በግል ተቋማት መካከል ያለውን የፈቃድ አሰጣጥ የአሰራር ስርዓት ልዩነት ለማስቀረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው በተቀናጀ የከፍተኛ ትምህርት የመረጃ አስተዳደር ስርዓት(HEMIS ) ያስገቡ ተቋማት ቁጥር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ጋር በተያያዘም 87 በመቶ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውደቃቸውን ፤ዘንድሮ በተሰጠው የመውጫ ፈተና 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን፤የግል የከፍተኛ ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል ያሳለፋት 13 በመቶ ብቻ መሆኑን እና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት በወ/ሮ ሂወት አሰፋ በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፈቃድ እና ፈቃድ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያ ፣ ስታንዳርዶች እና የዳግም ምዝገባ መምሪያ ዙሪያ ገለጻ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ እና በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ፤አዲስ አበባ
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ