FDRE Education and Training Authority
7.77K subscribers
809 photos
13 videos
23 files
145 links
በኢፌድሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን
http://www.eta.et/

9799 "በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል"
Download Telegram
#ማስታወቂያ
#ለሁሉምየግልከፍተኛትምህርትተቋማት
#ባሉበት
ጉዳዩ ፡-በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ብቁ እጩ ተፈታኞች መረጃ ስለመጠየቅ፤
----------------------------------------------------------------
በ2016 ዓ.ም ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳን ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የሶፍት ዌር ቴምፕሌት በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡በመሆኑም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈታኞቻቸውን መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሶፍት ዌር ቴምፕሌት ላይ እስከ 16/09/2016 ዓ.ም እንድታስገቡ እያልን ለበለጠ መረጃ በሚያዝያ 28 ቀን 2016 ዓ.ም በቁጥር 8/756/365/16 ከትምህርት ሚኒስቴር በወጣው ደብዳቤ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግልባጭ የሆነውን እንድትመለከቱ እና ተግባራዊ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
#ማስታወቂያ
#ለሁሉምየግልከፍተኛትምህርትተቋማት
#ባሉበት
ጉዳዩ፦ የተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዘር መረጃ እንድትልኩ ስለማሳሰብ ይሆናል፤
የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለማቋቋም በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም መሰረት በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 17 ንኡስ አንቀፅ 2 መሰረት ተቋማት የተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ ወቅቱን ጠብቃችሁ ለባለስልጣኑ መላክ እንዳለባችሁ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ግን ባለስልጣኑ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ክትትል ያስመረቋቸውን ተማሪዎች ወቅቱን ጠብቀው አለመላካችው እና የተናጠል(የግለሰቦች) መረጃዎች የላኩ መሆኑ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ስለዚህ ተቋማት ያስመረቋቸውን ተማሪዎች መረጃ አጠናቅረው በወቅቱ ባለማቅረባቸው ምክንያት የተመረቁ ተማሪዎች ለእንግልት ተዳርገዋል፡፡
በመሆኑም በተቋማችሁ ፈቃድ በተሰጣችሁ ትምህርት መስኮች፣ትምህርት ደረጃ፣መርሃ ግብር እና ካምፓስ ከዚህ በፊት ያላካችሁትን የተመረቁ ተማሪዎችን መረጃዎች በ2015 ዓ.ም አና 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ያለፉ ብቻ ከዚህ በፊት በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ ለመጨረሻ ጊዜ እናሳስባለን፡፡
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
#ማስታወቂያ
#ማስታወቂያ
#ለሁሉምየግልከፍተኛትምህርትተቋማት
#ባሉበት
ጉዳዩ፦ የተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዘር መረጃ መላኪያ ቅፅ ለውጥ ስለማሳወቅ፤
ከባለስልጣኑ ፈቃድ የተሰጣቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከዚህ በፊት ያላካችሁትን የተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ እና በ2015 ዓ.ም፣ 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ያለፉ ብቻ ከዚህ በፊት በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ ለመጨረሻ ጊዜ ብለን በቀን ሰኔ 10/2016 ዓ.ም በቁጥር 11/77/868/16 በወጣው ደብዳቤ ማሳወቃችን ይታወቃል፡፡
ሆኖም ግን የመላኪያ ቅጹ ይዘት ለትምህርትና ማስረጃ ማረጋገጥ የስራ ክፍል ለሚጠቀምበት ሲስተም አመቺ ይሆን ዘንድ ቅጹ ላይ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ከዚህ ደብዳቤ ጋራ አባሪ አድርገን በላክነው ቅፅ በመጠቀም ዝርዝር መረጃውን እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ ለመጨረሻ ጊዜ እናሳስባለን፡፡
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
#ማስታወቂያ
#ለሁሉምየግልከፍተኛትምህርትተቋማት
#ባሉበት
ጉዳዩ፡- የስብስባ ጥሪን ይመለከታል
ተቋማችን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በደንብ ቁጥር 515/2014 በተሰጠው ሥልጣን እና ተግባር መሠረት የከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ካዘጋጀ በኋላ አጽድቆ በሥራ ላይ እንዲውል አድረጓል፡፡ ይህንን መመሪያ ተከትሎ ዝርዝር አሠራር የሚገልጽ ስታንዳርድ አዘጋጅቶ በባለሥልጣኑ ቦርድ እንዲጸድቅ አድርጓል፡፡ መመሪያውንና ስታንዳርዱን ማዘጋጀት ያስፈለገበት ዋና ምክንያት የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማሻሻል እንዲሁም ለተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያሥችል ግልጽ አሠራር ለመዘርጋት ታስቦ ነው፡፡
ይህንን መመሪያና ስታንዳርድ ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/2016 አንቀጽ 4 (26)መሠረት ሁሉንም በሥራ ላይ ያሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ማካሄድ በማስፈለጉ ይህንኑ ለማስፈጸም የተዘጋጁ የዳግም ምዝገባ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት አሠራሮች ላይ ግልፀኝነት ለመፍጠርና የዳግም ምዝገባ ሂደት ለማስረዳት ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው ስብሰባ ሁሉም ተቋማት ባለቤት ወይም አንድ ተወካይ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት እንዲገኙ እናሳስባል፡፡
#ማስታወቂያ
#ለሁሉምየግልከፍተኛትምህርትተቋማት
#ባሉበት

ጉዳዩ፡- የዳግም ምዝገባ ዝግጅት ይመለከታል
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያግዙ የተለያዩ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያና ማሻሻያ ዘዴዎች መካከል አንዱ የፈቃድ አሰጣጥ ነው፡፡ ይህንን የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ መመሪያ እና ስታንዳርድ ጸድቆ ስራ ላይ ውሏል።
በመሆኑም መመሪያና ስታንዳርድ ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/2016 አንቀጽ 4(26) መሠረት ሁሉንም በስራ ላይ ያሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በፌደራል ደረጃ ፈቃድ የተሰጣቸው ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ለዳግም ምዝገባ መዘጋጀታችንን ሀምሌ 22/2016 ዓ.ም ባደረግነው ስብሰባ መግለጻችን ይታወሳል።
በዚህ መሠረት ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዳግም ምዝገባ መምሪያ መሰረት እስከ ነሃሴ 30/2016 ዓ.ም በተቋም፣ በካምፓስ እና በፕሮግራም ደረጃ በሀርድ ኮፒ እና ሶፍት ኮፒ የተደራጁትን መረጃዎች በአካል በመቅረብ እንዲሁም በየጊዜው በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት መረጃዎችን እንድታደራጁ እና በቂ ዝግጅት በማድረግ እንድታመለክቱ አጥብቀን እናሳስባለን።
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ