TIKVAH-ETHIO
708 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#Ethiopia

ዛሬ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ሁለተኛዋን ሳታላይት አምጥቃለች።

' ET-SMART-RSS ' በስኬት መምጠቋን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በይፋዊ ፌስቡክ ጉፁ ላይ አስታውቋል፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#update

የኢንዶኔዢያ ባለስልጣናት የመንገደኞች አውሮፕላኑ ወድቆበታል ብለው ያመኑትን ቦታ ባሕር ላይ መለየታቸውን አስታውቀዋል።

ዛሬ ከባሕር ውስጥ የአውሮፕላኑ የበረራ መመዝገቢያ ሳጥን ሳይሆን አይቀርም የተባለ ምልክት በፍለጋ ላይ በተሰማሩ ሠራተኞች ተገኝቷል።

አውሮፕላኑ ወድቆበታል ወደተባለው የባሕሩ ክፍል ከ10 በላይ መርከቦች ከባሕር ኃይል ጠላቂ ባለሙያዎች ጋር ተሰማርተዋል።

"በሁለት ቦታዎች ላይ ከአውሮፕላኑ ጥቁር ሳጥን ውስጥ የተላለፉ ሳይሆኑ የማይቀሩ ምልክቶችን ለይተናል" ሲሉ የኢንዶኔዢያ የአደጋ ጊዜ ፍለጋና ነፍስ የማዳን ተቋም ኃላፊ ባጉስ ፑቱሂቶ ተናግረዋል።

መርማሪዎች የአውሮፕላኑ ናቸው በተባሉ ጎማ እና ሌሎች ስብርባሪዎች ላይ ምርመራ እያደረጉ ነው።

የጃካርታ ፖሊስ ቃል አቀባይ ዩስሪ ዩኑስ እንደተናገሩት በፍለጋና ነፍስ የማዳን ሥራ ላይ ከተሰማሩ ሠራተኞች ሁለት ሻንጣዎችን መቀበላቸውን አሳውቀዋል።

"አንደኛው ሻንጣ የተሳፋሪዎችን ንብረት የያዘ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ የሰው አካል ያለበት ነው" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አክለው "አስካሁን የመለየት ሥራ እያከናወንን ነው" ብለዋል።

የፍለጋና ነፍስ የማዳን ሥራው ቅዳሜ ምሽት ላይ እንዲቋረጥ ተደርጎ ዛሬ ዕሁድ ጠዋት ተጀምሯል።

በፍለጋው ላይ እንዲያግዙ አራት (4) አውሮፕላኖች ተሰማርተዋል።

የጠፋው አውሮፕላን #ኢትዮጵያ ውስጥ ተከስክሶ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውና ከበረራ ውጪ እንዲሆን የተደረገው የቦይንግ ማክስ 737 አይነት እንዳልሆነ አየር መንገዱ አሳውቋል። ~ BBC

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

የጋዜጠኛና ሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሀብቴ ያዕቆብ አስክሬን ትላንት ምሽት #ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ገብቷል።

ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሀብቴ ያእቆብ ባጋጠመው ህመም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ይታወቃል።

አስከሬኑ ይኖርበት ከነበረበት ደቡብ አፍርካ ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ደርሷል።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ደግሞ ሀዋሳ ኤርፖርት ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

የጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሀብቴ ያዕቆብ ስርዓተ ቀብር በሀዋሳ ምሺን መቃብር ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

* አስክሬኑ ወደኢትዮጵያ ከመሸኘቱ በፊት በደቡብ አፍሪካ የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዶ ነበር። ፕሮግራሙ ላይ ቤተሰቦቹ ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ወዳጆቹ ፣ በደ/አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ተገኝተው ነበር። (ፎቶው ከላይ ተያይዟል)

Via Getahun D Darimo , UMH
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#UnitedStates

USAID በ5ኛ ዙር የኢትዮጵያ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ከ550 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ያደርጋል።

የUSAID የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሾን ጀንስ የአሜሪካ ህዝብ ለዚህ #ኢትዮጵያ መር ለሆነ ፕሮግራም ያለው ቁርጠኝነት አመታት የዘለቀ መሆኑን ተናግረዋል።

የ5ኛው ዙር የሴፍቲኔት ፕሮግራም 5 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በ9 ክልሎች ከ8 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

በአጠቃላይ በዚህኛው ዙር የሴፍቲኔት ፕሮግራም ከ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የሚደረግ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 65 % በለጋሽ ድርጅቶች ፣ 25 % በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን እና 10% ከባለድርሻ አካላት የሚዋጣ ነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ፎቶ ፦ ፌልትማን ኢትዮጵያ ገብተዋል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጄፍሪ ፌልትማን ዛሬ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ገብተዋል፤ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላም ከሙሳ ፋኪ ማሃመት ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ፌልትማንን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ጄፍሪ ፌልትማንን በቢሯቸው ተቀብለው በ #ኢትዮጵያ እና #ሱዳን ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን አሳውቀዋል።

Credit : Moussa Faki Mahamat (Twitter)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA