TIKVAH-ETHIO
687 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#Update

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ በውጭ ሀገር በሳዑዲ አረቢያ ዓለምአቀፍ ትምህርት ቤት የ2012 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ከ2013 ተፈታኞች ጋር ፈተናውን እንደሚወስዱ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አስታውቋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሪ እንደገለፁት ፥ ፈተናውን በጊዜ መስጠት ያልተቻለው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ነው ብለዋል፤ ከሁለት ወር በኃላ የ2013 ብሄራዊ ፈተና ሲሰጥ አብረው እንዲወስዱ ይደረጋል ሲሉ ተናገርዋል።

ትክክለኛው ጊዜ ባይወሰንም ግንቦት ወይም ሰኔ ላይ ፈተናው ይሰጣል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና በውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ትምህርት ቤቶች በመጨረሻ ሰዓት መሰረዙን ተገልጾ ነበር።

ከቀናት በፊት የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ በትግራይ ክልል በፀጥታ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተና መፈተን ካለባቸው ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱት 2,130 እንደሆኑ ገልፆ የቀሩት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ከ2013 ተፈታኞች ጋር ከሁለት ወር በኃላ ፈተናውን እንዲፈተኑ እንደሚደረግ መግለፁ አይዘነጋም።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

ግብፅ በኪንሳሻ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውይይት ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ከመደረጉ በፊት ስምምነት ላይ ለመድረስ የመጨረሻው እድል ሊሆን ይችላል ብላለች።

ግብፅ ይህን ያለቸው ግብፅ ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተደረገ የሚገኘውን ውይይት አስመልክታ ባወጣችው መግለጫ ነው።

ዛሬ ሰኞ እንደሚጠናቀቅ በሚጠበቀው ውይይቱ 3ቱ ሃገራት በዕድሉ ተጠቅመው ከመጪው ክረምት በፊት ከአንዳች ስምምነት እንዲደርሱ ፍላጎታቸው መሆኑን የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሳእቋል።

ሶስቱን ሃገራት የማደራደር ሃላፊነቱን የተረከቡት የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፍሌክስ ሺሴኬዲ «ሃገራቱ አንድ አልያም በርካታ የተስፋ በሮችን ይከፍቱ ዘንድ አዲስ ጅማሬ እንዲያሳዩ እጋብዛለሁ » ብለዋል።

በእሁዱ ውይይት ስለተነሱ ሀሳቦች ሆነ ስለተደረሰ ስምምነት የተባለ ምንም ነገር የለም።

የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ባለፈው ሳምንት የግብጽ የውሃ ድርሻ ከተነካ «በቀጣናው አለመረጋጋት ሊያስከትል ይችላል።» ብለው ነበር።

ምንም እንኳ ግብጽ እና ሱዳን ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት እንዲራዘም ቢፈልጉም ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የግድቡን ውኃ ሙሌት የፊታችን የክረምት ወራት የመሙላት ዕቅድ እንዳላት ቀደም ብላ አስታውቃለች።

[Reuters, DW]

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

የግል ተፈታኞችን በተመለከተ የመቁረጫ ነጥብ ፦

- በተፈጥሮ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ።

- በማህበራዊ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ።

ከኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (#MinistryoSHE) የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ የተላከልንን ዝርዝር መግለጫ ከላይ ያንብቡ ፤ ለሌሎችም ያጋሩ።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

የሱማሌ ክልል እና አፋር ክልል መንግስታት ችግሮቻቸውን በሰላም ለመፍታት መስማማታቸው ተገልጿል።

የአፋር እና የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት በርዕሳነ መስተዳድሮቻቸው የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን ዛሬ በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ሰብሳቢነት ምክክር አድርጓል።

በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠሩትን ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰላም ሚኒስቴር ማምሻውን አሳውቋል።

የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እና የፌደራል መንግስት የጸጥታ አካላት በተገኙበት የተከሰቱ ግጭቶችን በአፋጣኝ ለማስቆምና በቀጣይ ችግሮችን ለመፍታት ስምምነት አድርገዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሣኔ የምርጫ ምልክት ይፋ ተደርጓል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ ጋር በጋራ የሚከናወነው ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክት ዛሬ በይፋ አሳውቋል።

- የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቤንች ሸኮ ዞን ፣ የካፋ ዞን፣ የዳውሮ ዞን እና የሸካ ዞን ከደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ወጥተው የጋራ አንድ ክልል መመስረታቸውን እንደግፋለሁ - የባለ 6 እጆች ጥምረት ምልክት።

- የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቤንች ሸኮ ዞን ፣ የካፋ ዞን፣ የዳውሮ ዞን እና የሸካ ዞን የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል አካል ሆነው መቀጠላቸው እደግፋለሁ - የጎጆ ቤት ምልክት።

@ETHIO_TIKVHA
#Update

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ ዛሬ ጥዋት ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዮቹ መረጃዎች ሰጥተወል ፦

- አጣየ እና አካባቢው ስጋት ቢኖርም ትላንት እና ዛሬ አንፃራዊ ሰላም/መረጋጋት አለ/የተኩስ ድምፅ የለም።

- ከሸዋሮቢት ወጥተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።

- በአጣየ ከተማ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ነዋሪው ከመመለሱ በፊት ዳግም ጥቃት እንደማይከሰት ዋስትና ስለመኖሩ ከሚመለከታቸው አካላት ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

- በአብዛኛው ከተቃጠለችው እና ከወደመችው አጣየ ከተማ ፣ ከሸዋሮቢት የሸሹ ዜጎች በደብረብርሃን፣ መሀል ሜዳ፣ የተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ተጠልለዋል።

- ከአጣየ ከተማ ጥቃት የሸሹ በርግቢ፣ ይምሎ፣ መሀልሜዳ በሚባሉ አካባቢዎች ብቻ ከ10 ሺህ - 15 ሺህ ዜጎች ይገኛሉ።

- በአጣየ በርካታ የግለሰብ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ የመንግስት ተቋማት ፈርሰዋል፣ ውሃ መብራት የለም። እስረኞች ተለቀዋል።

- የከተማው አመራሮችም ከነዋሪዎች ጋር ከተማውን ጥለው ሸሽተዋል። አመራሮች እንዲመለሱ ፣ የውሃ እና መብራት ችግር እንዲፈታ እየተሰራ ነው ተብሏል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ ለሁለት ዓመታት የተራዘመ የስልጣን ዘመናቸውን በመሰረዝ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

ሰሞኑን ከተራዘመው የፕሬዚዳንቱ የስልጣን ዘመን ጋር ተያይዞ የእርሳቸው ደጋፊና ታቃወሚዎች ጎራ ለይተው ግጭት ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።

ግጭቱን ተከትሎ ነዋሪዎች ቀያቸውን በመልቀቅ እየሸሹ እንደነበር መገለፁ ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ለሃገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር በሀገሪቱ ምርጫ እንዲካሄድ የወሰኑ ሲሆን የስልጣን ዘመኑን መራዘም የተቃወሙትን ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴንን አድንቀዋል፡፡

በርካቶች አልሻባብ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም ችግር ይፈጥራል በሚል ስጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ዙሪያ እየመከረ ነው።

በመድረኩ ላይ ትላንት የተጠናቀቀውን የመራጮች ምዝገባ በተመለከተ ጊዜያዊ መረጃ ተሰጥቷል።

በዚህ መሰረት ፦

- እስከ ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ያ36 ሚሊዮን 245 ሺህ 444 ሰዎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል።

- ምርጫ ካርድ ከወሰዱት ውስጥ 16.6 ሚሊዮኑ ሴት ፤ 19.5 ሚሊዮኑ ወንድ ናቸው፡፡

- 50 ሚሊዬን ዜጎች ካርድ ሊወስዱ እንደሚችሉ ተገምቶ ነበር፡፡ አሁን ያለው ካርድ የወሰዱ ዜጎች ቁጥሩ የግምቱን 78 በመቶ ይሸፍናል።

- ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ሶማሌ እና አፋር ክልሎች ከተገመተው በላይ የመራጮች ካርድ የተወሰደባቸው ናቸው።

- በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአንጻራዊነት ዝቅተኛ የመራጮች ምዝገባ የተከናወነበት ክልል ነው።

በዝርዝር ስንመለከተው ፦

• በአዲስ አበባ ከ1.4 ሚሊዬን፣
• በአፋር ከ1.7 ሚሊዬን፣
• በአማራ ከ5.9 ሚሊዬን፣
• በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ174 ሺ፣
• በጋምቤላ ከ326 ሺ፣
• በኦሮሚያ ከ15.9 ሚሊዬን፣
• በሃረር ከ135 ሺ፣
• በድሬዳዋ ከ177 ሺ፣
• በደቡብ ብ/ብ/ህ ከ4.8 ሚሊዬን፣
• በሲዳማ ከ1.5 ሚሊዬን እና በሶማሌ ከ3.9 ሚሊዬን በላይ መራጮች ካርድ መውሰዳቸውን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል። (አል ዓይን)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያለው የድምጽ መስጫ ወረቀት ማሸጊያው ባለመከፈቱ ምክንያት የምርጫ ሂደቱ እንዲቀጥል የተወሰነባቸው የምርጫ ክልሎች ስለመኖራቸው አሳውቋል።

እነዚህም ፦

• ስንቄ 1 እና 2 የምርጫ ቁሳቁስ ሳጥኑ (ሰማያዊ ሳጥን) ወድቆ በመሰበሩ የተወዳዳሪ ፖርቲዎች ወኪል ባሉበት ቃለጉባኤ ተይዞ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ የታሸገው ባለመከፈቱ ምርጫው እንዲካሄድ ተወስኗል።

ይህ ምርጫ ጣቢያ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚወዳደሩበት ነው።

• መተማ ላይ የምርጫ ቁሳቁስ መያዣ ሳጥኑ (ሰማያዊ ሳጥኑ) ቢነካካም የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹ ማሸጊያ ባለመከፈቱ ምርጫው እንዲቀጥል ቦርዱ ወስኗል።

#SolianShimeles #TikvahEthiopia #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ አንድ ምርጫ ክልል 19 ምርጫ ጣቢያ 16 ላይ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫውን ሂደት እየዞሩ እየገመገሙ ነው።

በሂደቱ የምርጫ ጣቢያ ውስጥ የታዛቢነት ካርድ ሳትይዝ የገባች አንድ ሴት ነበርች ፥ ወ/ሪት ብርቱካን ይህችን ሴት ከጣቢያው እንድትወጣ አድርገዋል።

የምርጫ ጣቢያ ኃላፊው ፖሊስ እንዲጠራ በማስደረግም ያለ ምርጫ ታዛቢነት ካርድ የገባችው ሴት ላይ በፖሊስ ምርመራ እየተደረገ ነው።

ታዛቢ ነኝ ብላ ምርጫ ጣቢያ ውስጥ የተገኘችው ሴት "የብልፅግና ፓርቲ ታዛቢ ነኝ" ያለች ሲሆን አንድ ዳብዳቤ ይዛ ነበር ደብዳቤው ግን ህጋዊ አይደለም መባሉን በቦታው የሚገኙት የቤተሰባችን አባላት አሳውቀውናል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA